ለሰጣችሁኝ አስተያየት አመሰግናለሁ አብዛኞቻችሁ መማር ያለባችሁን ነገር እንደምትወስዱ ተስፋ አደርጋለሁ ዛሬ ይለቀቃል::
👏36❤14🥰7🤔3🙏2😡1
ህላዌ (✍️✍️)
ሰአቱ እየመሸ ሄደ።
ተሸፍኜ ሳለቅስ ነበር ያመሸሁት።
ሲመሽ ሜሪም ሀይሌም ተያይዘው ምግብ ሰርተው ይዘው መጡ።
ሜሪ ስራ አጊታ ሁለተኛ ቀኗ ነበር።
ሀይሌም በዘመድ ተቀጥሮ ሁለቱም ቤታቸውን ለማቋቋም ጠንክረው ወደስራ ገብተዋል መልስ ቅልቅል የሚባሉ ነገሮች በእናቴ ሀዘን ምክንያት ቀርተዋል።
እሷ ስትመጣ ተነሽ አንቺ ተኝተሽ ነው አለችኝ።
እየተሳቀቀኩ የለበስኩትን ገለጥኩት።
ሜሪ ጮኸች ምን ሆነሽ ነው ከማንጋ ነው የተጣላሽው አለችኝ።
ከጎረቤቴ ውጭ ሌላ ሰው ይሆናል ብላ ስላላሰበች ወደሱ አፈጠጠችበት ነይ ተነሽ ማነው እንደዚህ ያደረገሽ ማነው ያስለቀሰሽ ቅድስት አለችኝ እልህና ንዴት በሞላው ድምፅ።
ማንም አደለም ከማንምጋ አልተጣላሀሁም ሜሪ አቱጪሂ አልኳት።
ወደጎረቤቴ ሄዳ እየገፈተረችው አንተ ነሀ ካንተ ሌላ ማን ቤት ውስጥ መጣ እእ ማታ እንደዛ ቁልጭ ያለ ፊት ትቼ ሄጅ እንደዚህ ሆና ማግኘት ምን ይባላል ብላ ጮኸችበት።
እውነታው ግን ለተወሰኑ ሰአታት ከቤት ወጥቶ በተመለሰበት ቅፅበት እንደዛ ሆኜ ስለጠበኩት እሱም ደንግጦ ደርቆ ቆሞ ነበር።
እያለቀስኩ እየማልኩ ሜሪ እሱ አደለም አልኳት።
እሺ ምን ሆነሽ ነው ተናገሪ ብላ አፈጠጠች።
ተስፋ ቆርጬ ደብሮኝ ከፍቶኝ እራሴን ከግድግዳጋ እያጋጨሁ ነበር በቃ እሱ ምንም አላጠፋም ፊቴን ሁላ አሁን ነው ከእናንተ እኩል ያየው አልኳትተ።
በዛ ሰአት ፊቱ ላይ ያነበብኩት የጥፋተኝነትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይሄ ነው የሚባል አልነበረም።
ይጨመር?🤔
👍👍👍
https://t.me/mane121921

👍48❤24
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ምሽቱን ሰብሰብ ብለን ከሁሉም በኩል ምክር እየተለገስኩ ሜሪ ያመጣችውን ምግብ በትሪ በልተን ቀለል ብሎን አመሸን።
አልፎ አልፎም እግረ መንገዳቸውን ብቅ ብለው ሚያልፊ የሰፈር ሰዎችም አልጠፉም።
ሲመሽ እነ ሜሪ ባለትዳር እንደመሆናቸው ተያይዘው ወደቤታቸው አመሩ።
ያብስራም ተመልሶ እኔጋ ሳይመጣ ጎረቤቴም ከቤቴ ሳይወጣ ለኔና ለህላዌ ሚያስፈልገንን ሳንጠይቀው እያደረገልን ሁለት ወራት ተቆጠሩ።
ሁለት ወር ሙሉ ለእቴቴ የኔንም የሱንም የቤት ኪራይ እየከፈለ ነበር የቆየው።
እኔም ብሆን ሳልወድ በግድ ለመጠንከር ስሞክር ነበር።
አንድ ቀን እሁድ እነ ሜሪ ቤት ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ኑ ብላ ጠራችን።
እኔም ህላዌና ጎረቤቴን ይዤ ከሷ ቤተሰቦችጋ ተሰብስበን ወደነሜሪና ሀይሌ ቤት ሄድን።
ለመጀመሪያ ጊዜ ቤቷን ያየሁትም ያኔ ነው።
ልክ ሜሪ ከልጅነቷ ጀምሮ ምትመኘው አይነት የቤት ስታይል ነው።
እቃ ያልበዛበት ያልተጋነነ ሲምፕል የሆነ ግን ማራኪ ቤት ።
ቤት ስንደርስ የሀይሌም ቤተሰቦች መተው ነበር።
አንድ ላይ ተሰብስበን ምግብ በላን ቡና ተፈላ እንደቤተሰብ በሚያስቀና መከባበርና ፍቅር ምሽቱን አሳለፉት።
ሀይሌ ከሰዎች መሀል ሚስቱን እንዴት በስስት እንደሚያያት ለተመለከተ ሰው መቅናቱ ግዴታ ነው።
ሲመሻሽ አካባቢ ሜሪና ሀይሌ እጅ ለእጅ ተያይዘው ቆሙና ያው እንግዲ
ደስታችንንም ሀዘናችንንም ቅድሚያ ለቤተሰቦቻችን ነው አሳልፈን ምንሰጠው እና ለሰርጉ ሰሞን ባጋጠመን ትልቅ ሀዘን የመመራረቂያ ሰፊ ጊዜ አላገኘንም።
ዛሬ ደሞ ምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ጓደኛዬ እህቴ አብሮ አደጌ በተገኘችበት ምናበስራችሁ ዜና አለ አለች ሜሪ ሀይሌ ቀበል አደረገና አዎ ያው እንግዴ በቶሎ ወደትዳር ለመግባት ስናስብ ሳትቃወሙ ፍቃዳችሁን ስለሰጣችሁን ሀላፊነት እንድንወስድ ስላመናችሁን እናመሰግናለን በመቀጠል ዛሬ ሜሪ የሁለት ወር ከምናምን እርጉዝ ናት ስለዚህ እናንተ ቤተሰቦቻችን ፈጣሪ የባረከው ልጅ እንድናቅፍ እንድትመርቁን ነው ዛሬ እዚህ የጠራናችሁ ብለው ተናገሩ የቤቱ ሰው እንዳለ ጥርስ በጥርስ ሆነ።
እልልታ ተሰማ።
ሁሉም በየተራ መልካም ምኞታቸውን ተናገሩ የሜሪ አባቴ ወንድ ልጅ አያለቅስም የሚለውን መፈክር ወደጎን ትቶ አበባዬ ልጄ ወግ ማእረግ አሳይተሽኝ ዛሬ ደሞ አያትህ እንድሆን እያዘጋጀሽኝ ስለሆነ የነካሽው ያሰብሸው የተመኘሽው ሁሉ ይሁንልሽ ይመርልሽ ብሎ መረቃት ።
እኔ ምንም መናገር አልቻልኩም ገና ላወራ ስል እንባና ሳግ እየተናነቀኝ ምንም ሳልተነፍስ ከሜሪጋ ተቃቅፈን አለቀስን።
ቤተሰቡ በደስታ ሳጥን ሳጥን ቢራ እየገዛ መጣ ዛሬ እዚሁ ነው ምናድረው ከዚህ በላይ ደስታ ከዚህ በላይ አለም የለም ብስራት አሰማችን አሉ።
እኔና ጎረቤቴ አመስግነን ወጣን።
እነሱም አልተጫኑንም ነበር
ይጨመር🤔

❤101👍32
https://vt.tiktok.com/ZS9SBTWY2NxRt-ZG3s4/
1 የቻናላችን ተከታይ ቲክቶክ ኮሜንቱን like አድርጉለትና ለበአል ምንጣፍ አሸልሙት የኔ ቤተሰቦች ኮሜንቱን ብቻ like አድርጎ ማለፍ ነው ከእናንተ ሚጠበቀው

👍18❤7
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ህላዌ እንቅልፍ ወስዷት የጎረቤቴ ትከሻ ላይ ቸኝታ ነበር።
እሱ አቅፏት እየሄድን መንገድ ላይ አይን አይኔን እያየ ውስጥሽ ምን እየተሰማሽ ነው ?አለኝ
ምንም አልኩት ጥርሴን ነክሼ።
እህህ ውስጥሽ እልህ ይሁን ቅናት ማታውቂው ስሜት እየተሰማሽ ነው።
አንቺም እንደሴት ልጅ መከበር ይገባሽ ነበር ግን እሱን ክብር አንቺ አላገኘሽም።
በክብር ማግባት በክብር መውለድ አለቻልሽም ምንም እንኳን ጓደኛሽን ብትወጃትም ዛሬ እሷን እንደዚህ ስታያት ለምን እኔስ የሚል ጥያቄ ውስጥሽ ተፈጥሯል አደል አለኝ።
መልስ በመመለስ ፋንታ አለቀስኩ።
እንደ ህፃን ልጅ ድምፅ እያወጣሁ ነበር ያለቀስኩት ዝም ብሎኝ በዝግታ ባጠገቤ ከመራመድ ውጭ ምንም አላደረገም አላባበለኝም አይዞሽ አላለኝም ዝምምምም አለኝ።
ሲበርድልኝ ለቅሶዬን ዋጥጥ አድርጌ ዝም አልኩ።
ሰፈር ደርሰን እስከቤት ወክ አደረግንና ወደቤት ገባን ህላዌን አስተካክለን አስተኛናትና ሁለታችንም ፍራሹ ላይ ቁጭ አልን ህላዌ ከመሀላችን ነበረች።
በዛ መሀል ሊጠይቀኝ ሚፈልገው ነገር እንዳለ ነገረኝ።
ምንድነው በሚል አስተያየት አየሁት።
ለምን እኔና አንቺ አብረን አንሆንም ለምን እንደባልና ሚስት ሆነን ህላዌን አናሳድግም ለምን የቅርብ የልብ ጓደኛሽ አታደርጊኝም አለኝ።
ግራ ገብቶኝ ማለት አልኩት
ምን ማለት አለው አግቢኝ ወይ ደሞ ፍቅረኛዬ ሁኚ እያልኩሽ ነው አለኝ

❤23👍9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ደክሞኛል በሚል የተሰላቸ አስተያየት አየሁት።
ለምን እንደዚህ ጠየከኝ ወደኸኝ ወይ አፍቅረኸኝ አደለም ለምን አብሬህ እሆናለሁ አልኩት።
ልወድሽ እችላለሁ ወደፊቴ ውስጥ ሚስቴና የልጆቼና እናት ምኖርላት ሴት ልትሆኚ ትችያለሽ አለኝ።
ልሆን እችላለሁ?
አዎ ልትሆኚ ትችያለሽ ወይስ ደሞ ወድጄሻለሁ አፍቅሬሻለሁ ብዬ ውሸት እንድነግርሽ ነው የፈለገሽው ማለቴ አላቅም አሁን ላይ በጣም ነው ምታሳዝኝኝ በጣም ነው ምታሳሽኝ እና በየትኛውም አጋጣሚ አብሬሸ መሆን ነው ምፈልገው ካወኩሽ ቀን ጀምሮ ስትስቂ ለማየት እንዴት ልቤ እንደሚጓጓ ብታውቂ ትገረሚ ነበር አለኝ።
ታዲያ ሰው ሳይፋቀር እንዴት ይጋባል እንዴት አብሮ ይሆናል ነገ ህይወትህ ውስጥ አሰልቺ ሰው ብሆን እስከመጨረሻው ልትወደኝ ባትችል ሀላፊነቱን ምወስደው እራሴ ነኝ እና ደሞ እኔም ምንም አይነት ፍቅር ላንተ የለኝም እንዴት አብሬህ እሆናለሁ።
እውነት ለመናገር እንደወንድም እንደጓደኛ ዝም ብለን አብረን ልንሆን እንችላለኝ አምኜል አንድ ፍራሽ ላይ እየተኛሁ ነው አምኜህ ቤቴን ክፍት አድርጌልሀለሁ አምኜህ ልጄን ሰጥቼሀለሁ በዚህ ሰአት ማንም የለኝም ካሳዘንኩህ ካሰብክልኝ አብረኸኝ መቆየት ትችላለህ።
እንደሰው ከሰለቸህ ደሞ የመሄድ ሙሉ መብቱን ሰጥቼሀለሁ ለእስከዛሬው አመሰግናለሁ።
ከብዙ ሰው አፍ አውጥተኸኛል እናቴን በክብር ቆሜ እንድቀብራት አድርገኸኛል ቤቱ ባዶ ሲሆን የነበርከው አንተ ነህ የተኛዎ ሰው ክፉ ቀኔ ላይ እንደሚቆምልኝ መገመት እንደማልችል ነው ያሳየኸኝ አልኩት።
አይ የትም አሌድም የሚያጓጓ ወይ የምመርጠው ህይወት የለኝም እዚሁ እቆያለሁ አንቺ በቃኝ እስካልሽ ድረስ አብሬሽ አለሁ እስካልሰለቸሽ አይሰለቸኝም አለኝ።
በሰአቱ ደስ አለኝ ። የምወዳቸውን ሰዎች በማጣት ውስጥ ነው ህይወቴን ያሳለፍኩት።
ለሱ ምንም አይነት ስሜት ባይኖረኝም ባላፈቅረውም እንኳን እንደሴት ልጅ እናቷን እናዳጣች ሴት ልጇን ብቻዋን እንደምታሳድግ አንዲት ለጋ ወጣት የሆነ የምደገፈው ነገር ያስፈልገኝ ነበር በሰአቱ ደሞ ምሰሶ ሆኖ የቆመልኝ እሱ ስለሆነ ተደገፍኩት አመንኩት አቀረብኩት።
ከምንም በላይ ህላዌ እንደ አንዲት ልጅ በትናንሽ ነገሮች መሳብና መሸወድ ያለ ነው።
እናቴ ስትሞት በተራው እሱ ተትክቶ ምን ልግዛልሽ ምን አማራሾ ብሎ ስላቀበጣት ነፃነት ምታገኝበት ቦታዋ አድርጋዋለች።
እንደአባት እሽኮኮ ይዟት ሱቅ ደርሰው ሲመጡ ሳያቸው ደስ ይለኛል ስትስቅ ትንሽ መረጋጋት ይሰማኛል።
በነጋታው ከሰአት አካባቢ እህቱና ያብስራ ቤት መጡ ።
https://t.me/mane121921
4677 ደርሰናል chanalun share eyaderegachihu 4700 engiba

👍74❤59🥰9🙏5
እንኳን አደረሳቸው የኔ ውድ ቤተሰቦች ።
መልካም በአል ይሁንላችሁ
2019 ስኬታችሁን ምታሳኩበት የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ
መልካም በአል
መልካም በአል ይሁንላችሁ
2019 ስኬታችሁን ምታሳኩበት የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ
መልካም በአል
❤77🙏34
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ሳየው እንዴት ደሜ እንደፈላና ተነስቼ ለማነቅ እራሴን እንዴት ሳዘጋጅ እንደነበር ውስጤ ያቀዋል ግን ደግሞ ነገሮችን ላለማበላሸት ንዴትንና እልሄን ተቆጣጥሬ ዝም ብዬ ተቀበልኳቸው።
ወደቤት ገብተው ማውራት ጀመሩ።
ያብስራ ለደቂቃም ቢሆን ከህላዌ ላይ አይኑን መንቀል አልቻለም።
እነሱ ቁጭ ብለው ስለስራ እያወሩ እኔ ደሞ ተነስቼ ምግብ እየሰራራሁ ህላዌ ለብቻዋ እየተጫወተች ሳታስበው መሬት ላይ ድፍት ብላ ትወድቃለች።
ከመቅፅበት ዞር ስል ያብስራ ከተቀመጠበት ተነስቶ መቼ እንዳነሳትና እንዳቀፋት አላውቅም አቅፏት እያባበላት ድንጋጤው ሳይለቀው ወደውጭ ወጣ።
ህላዌ እናቴ ከሞተች ቡሀላ ናፍቆቱ ሆድ እያስባሳት መሰለኝ መቼ እንደከፋት በምን እንዳለቀሰች አናቅም አንዴ ደሞ ማልቀስ ስትጀምር አታቆምም ምክንያት ስታገኝ እንደትልቅ ሰው ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች።
ያኔ ያብስራ ይዟት ወደውጭ ስለወጣ እነሱ አርፈው ተቀመጡ እኔም እሱን ተከትዬ ወደ ውጭ ወጣሁ።
ነይ ዝም እንድትል የሆነ ነገር እንግዛላት አለኝ።
አይ አትፈልግም አልኩት።
በናትሽ ቅድስት እረፊ በቃ ነይ እንግዛላት ብሎኝ ወደውጭ ወጣን።
ህላዌ ስታለቅስ ፊቱ ላይ የሚታየው ጭንቀት የምር ያብስራ ነው የአንድ ህፃን ልጅ ለቅሶ በዚህ ልክ እረብሾት ነው ያስብል ነበር።
ሱቅ ሄደን ከተሰቀሉት ኳሶች ውስጥ ምትፈልገውን እንድትመርጥ ሲነግራት ለቅሶዋን እረሳችው የወደደችውን ኳስ አቅፋ ዝም አለቸ።
ወደቤት አብረን እየተመለስን ይቅርታ ቅድስት የዛኔ እንደዛ ማድረግ ፈልጌ አደለም አስተዳደጌ በራሱ የፈጠረብኝ ተፅኖ አለ።
አንዳንዴ እራሴን መቆጣጠር ያቅተኛል ከተወሰኑ ደቂቃዎች ቡሀላ ነወሰ ድንግጥ ብዬ ወደራሴ ምመለሰው በእውነት ግን ፈልጌው አደለም አሁንም ሀሳቤን አልቀየርኩም ምርጥ እናት መሆን እንደምትችይ አቃለሁ ምርጥ አባት ስለመሆኔ ምንም አላቅም ግን ቤተሰቦቼ እኔ ላይ የሰሩትን ስተት እንደማልደግመው ግን እርግጠኛ ነኝ።
እባክሽ ቅድስት በቃ አብረን እንሂድ በእውነት ለህላዌ ስል እንዴት ጥሩ ሰው እንደምሆንልሽ ታያለሽ በናትሽ በቃ እዚህ ምን ቀረሽ አብረን ሆነን ልጃችንን እናሳድግ ካላመንሽኝ ደሞ ከመሄዳችን በፊት የፈለግሽበት ቦታ ሄደን ልምልልሽ እችላለሁ አለኝ።
ዝም አልኩት።
ወደቤት ገባን።
እህቱ ሱቅ ወታችሁ ነው ? ና የኔ ፍቅር ይቺን እንጨርስና ከዛ በቃ ከፈለግን አብረን መውጣት እንችላለን አለች።
ህላዌን ተቀብያቸው ምግቤን ለመጨረስ ወደውስጥ ገባሁ።
አውርተው ሲጨርሱ ምግብ እንዲበሉ ብነግራቸውም ይቅርብን ሁላችንም በጋራ እንውጣና አብረን እራት እንብላ አሉ።
እኔ በፍፁም አልፈልግም አልኩ።
ግን በስንት ልመና አሳምነውኝ የተያያዘውን ፀጉሬን ፈትቼ አበጥሬ የልጄን ፀጉር አጥቤ አሲዤላት ከእናቴ ሞት ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያምር ልብስና ጫማ አልብሻት አሳመርኳት።
እኔ ጥቁር ሙሉ ቀሚስ ለብሼ ከላይ ቡኒ ጃኬት ደርቤበት ለመውጣት ተዘጋጀሁ።
ያብስራ ህላዌን በጣም እንደወደዳት ተናግሮ እሱ አቅፏት ወደመኪናው ሄደ።
እኛ ከኋላ ተከተልነው።
ይጨመር ካላችሁ👍

👍93❤34
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
መኪናውጋ ስንደርስ እዩኤል አንተ ንዳ እኔ እሷኑ እንዳቀፍኩ መጓዝ ነው ምፈልገው ብሎ ቁልፉን ሰቶት ከኋላ ገባ።
እኔን ጋቢና እንድገባ ስለነገረኝ ወደጋቢና ገባሁ።
ያብስራ እህቱ ከኋላ ገቡ።
እዩኤል መኪናውን መንዳት ጀመረ።
ከኋላ ጨዋታውን አደሩት።
እንደዚህ ልጅ እንደምትወድ ባውቅኮ ድሮ ገና እወልድልህ ነበር አለችው።
ህላውን ካየኋት ቡሀላ ነው ልጅ እንደምወድ ያወኩት ከዛ በፊት ታውቂ የለ ልጅ ሳይ እራሱ እናደዳለሁ አልወድም ነበርኮ አላት።
እኮ ፍቅር እሱንኮ ነው ምልህ እኔ ሳውቅህ ልጅ ስታይ እራሱ ፊትህ ነበር ሚቀየረው ገርሞኝኮ ነው አለችው።
የእዩ እህት የመጨረሳ የዋህ ምስኪን ምንም የማታውቅ ነጭ ወረቀት ናት።
ስትናገር ታሳሳለች።
ካፏ ክፉ አይወጣም ሰዎችን በኔጌትቭ መልኩ አትረዳም።
ያብስራን ደሞ አይታ አታምነውም።
አጠገቧ ቁጭ ብሎ እጁን ያዝ ጭምቅ ሳም ታደርገዋለች።
ሲያወራ አይኑ ውስጥ ለመግባት እየታገለች ይመስል አስተያየቷ ያስተዛዝባል።
ያቢሻ የኔ ፍቅር ስትለው ለመጥራት እራሱ ምታሳሳለት ነው ሚመስለኝ።
በስተመጨረሻ የምንሄድበት ቤት ደረስንና እነሱ ወረዱ እኛ ፓርክ አድርገን እንምጣ ብሎኝ ወደቤዝመንቱ ገባን።
እዛ መኪናውን አስተካክሎ ካቆመ ቡሀላ በየትኛውም ሰአት ከደበረሽ ካስጠላሽ እንሂድ በይኝ እሺ አለኝ።
ተስማምተን ወደውስጥ ገባንና ወደተቀመጡበት ጠረጴዛ ገብተን ቁጭ አልን።
ህላዌን ለሰቀበልህ ብለው ያብስራ በፍፁም አለ።
ህላዌ ምግቡ ታዞ እስኪመጣ እንዳቀፋት እንቅልፍ ወሰዳት።
እሷ ተኝታ እያወሩት ያብስራ የሚሉትን አይሰማም ነበር።
እሷን እያየ በሀሳብ ሂድት ብሎ እእእ ምን ይላል ።
ሁኔታው ግራ ገብቷቸው ነበር።
ምግቡ ሲመጣ እሷ ትተኛ እኛ እንብላ ለሷ ለብቻ ይታዘዛል ቢባል አረ እንደዛ አይሆንም ብሎ ቀሰቀሳት።
ያብስራ ለህላዌ የእዩ እህት ደሞ ለያብስራ እዩ ደሞ ለእህቱ እየተጎራሩ እኔ ብቻ ለራሴ እየበላሁ ምግቡ አለቀ።
የሚጠጣ ታዘዘ።
መጀመሪያ ላይ መጠጣት ባልፈልግም ከነሱጋ ለመመሳሰል ትንሽ ትንሽ ቀመስ አደረኩ።
የተቀዳውን ብርጭቆ ግማሽ ሳላደርሰው እነሱ የትየሌሌ ጠጥተው ነበር።
እኔም በነሱ ግፊት አንዱን ጨርሼ ወደሁለተኛው ስገባ ትንሽ ብዥ የማለት ነገር እራሴ ላይ ስመለከት መጠጣቱን አቁሜ የሚያወሩትን ብቻ መስማት ጀመርኩ።
ሰአቱ ሳይታሰብ ሄደ።
ወደ ሁለት ሰአት ተኩል በቃ ወደቤት እንሂድ ህፃን ልጅ ይዘን ማምሸት የለብንም ተብሎ ተያይዘን ወጣን።
እነሱ እስከቤት አድርሰውን ተመልሰው ሄዱ።
ወደቤት ገብተን እኔና ህላዌ ልብስ ስንቀያይር ጎረቤት በለበሰው ልብስ ቁጭ አለ።
የሆነ ነገሩ አሳዘነኝ።
ህላዌን እንደምንም አባብለን ካስተኛን ቡሀላ እና እኔጋ ለመኖር ወሰንክ አልኩት?
One more?..

❤97👍35
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አዎ ወስኛለሁ አንቺ ፈቀድሽልኝ አለ።
አዎ ፈቅጄልሀለሁ እኔ በዚህ ሰአት ምፈራው ብቸኝነትን ነው አብረኸኝ ከሆንክ ደስ ይለኛል አልኩት።
እሺ እኔም ምፈልገው እሱን ነው ከመስመር ወጥቻለሁ ወደመስመር መልሽኝ አለኝ።
ትንሽ ሞቅታ ውስጥ ነበር።
እሺ እንደዛ ከሆነ ነገ እነ አቤልጋ እኔድና ያሉንን እቃዎች ይዘን እንመጣለን።
ቤቱን ሌላ ሰው ተከራይቶት ቢኖርበት ይሻላል።
እቴቴን በምናግዘው እናግዛታለን ምስኪን ሰው ናት አልኩት።
እኔጃ እኔ አስታውያት አላቅም ምስኪን ትሁን ክፉ አላውቅም አለኝ።
እሺ በቃ ነገ እኔዳለን አልኩት።
እሺ ግን ያ አቤል ፍቅረኛሽ ነበርኮ ሚመስለኝ ስር ስርሽ ሲል አንቺም ስር ስሩ ስትይ አለኝ።
ማለት ?
ማለቴ ይመስለኝ ነበር ነው ያልኩት ምን ያኮሳትርሻል አለኝ።
አይ ምንም የለንም አብረን ነው የተማርነው ህላዌን ባረገዝኩበት ሰአት ያገዘኝ እሱ ነው በምክርም በምንም እረድቶኛል።
የዛኔ የክፉ ቀኔ ላይ የቆመልኝ ሰው ነው ተሳክቶለት ተቀይሮ ለእናቱ ደርሶላት ባየው ደስ ይለኛል ግን ህይወት በብዙ መንገድ ነው የጨለመችበት ያሳዝናል እድል ፊቷን አዙራበታለች ተስፋ ቆርጦ እንዳይወድቅ እፈራለታለሁ አልኩት።
ግን ታድለሽ አለኝ።
እንዴት?
በቃ ጎበዝ ነሽ ጠንካራ ነሽ መቋቋም ትችያለሽ እድሜሽ አልሰበረሽም ጀግና ነሽ አለኝ።
መስሎህ ጊዜና ያለህበት ሁኔታ ነው ጀግናም ሰነፍም ሚያደርግህ ግን ብቻ ተመስገን ስላጠነከረኝ ስላቆመኝ ዛሬን ስላሳየኝ ተመስገን በቃ ማማረር አልችልም አልኩት።
እስቲ እቀፊኝ ያንቺ ኢነርጂ እንዲጋባብኝ አግዥኝ አለኝ።
አቀፍኩት ።
ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።
ለካ መታቀፍም ይናፍቃል በሆነ ሰው ትከሻ ላይ መደገፍም ይናፍቃል ለካ ።
አቅፌው በቃ እንደጋገፍ አግዘኝ ላግዝህ አልኩት።
በሰአቱ ከሱ ውጭ ምርጫ እንደሌለኝ ተሰምቶኝ መሰለኝ እሱን ላለማራቅእሱን ላለማሸሽ ነበር ጥረቴ ሁላ።
ከረጅም መተቃቀፍ ቡሀላ በቃ እንተኛ ብሎ አንገቴ ስር ስሞኝ እዛው ፍራሹ ላይ ሸርተት ብሎ ተኛ።
ተነስቼ ህላዌን ከመሀል አድርጌ ተኛሁ።
ብርድ ልብስ ውስጥ ገብቼ ፈገግ አልኩ ከልቤ ነበር
ከተመቻችሁ👍

❤166👍56🥰6👏4
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
በነጋታው እንደተነሳን ቁርስ በላንና ህላዌን አለባብሰን ይዘናት ወደነቴቴጋ ሄድን ።
እዛ ስንደርስ አቤል ቤት ውስጥ ተኝቶ ነበር።
እኔም ሰላም ብዬው ከህላዌጋ ወደውስጥ ገባሁ።
እዩኤል እዛው በር ላይ ቆሞ ነበር።
ሲያየን ብድግ አለ።
ሰላም ሊለን ወደኛ ሲመጣ ጠረኑ በጣም ያስጠላ ነበር።
አይኑ ደፈራርሷል ሳየው ውስጤ ስፍስፍ አለ።
አንተ በስማም ምን አይነት ሰው ነህ እንዴት እንደዚህ ጥለኸን ትጠፋለህ በዚህ ልክ ነበር አደል ጓደኝነታችን አልኩት።
ፀጉርን እያሻሸ ዝም አለኝ።
መልስ አልሰጠኝም።
ና እስቲ በናትህ ቤት እንግባ በስንት ጊዜው ሊከፈት ነው አልኩት።
አብረን ወደቤት ገባን።
ቤት ገብተን ቆመን እያየን እኔ ውስጤ ናፍቋት የነበረውን ቤቴን እያየሁ ወደውጭ ዞር ስል እናቴ ቆጣጥራ ከውጭ ምትመጣው ነገር በአይኔ ውልብ ውልብ አለብኝ እንባዬን ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩ።
አቤል የተነጠፈውን ፍራሽ ለማንሳት ጎንበስ ሲል እአአአአ ብሎ ብድግ አለ ምነው ምን ሆንክ አልኩት።
ማታ ካባቱጋ ተጣልቶ ወገቡን በዱላ እንደመታውና ትንሽ እንዳመመው ነገረኝ።
አይዞህ የማለት አቅምም አጣሁ።
ህላዌ ካጠገባችን እሮጣ ውጭ ላይ ቆሞ ወደነበረው እዩኤል ሄደችና እቀፈኝ ብላው ተጠመጠመችበት።
አቤል ቆሞ እያያት ነበር ።
ፈገግ አለ።
ከህላዌጋም ተግባብተዋል ደስ ይላል አለኝ።
አዎ አንተ ግን እንደዚህ ጥለኸን ትጠፋለህ አልኩት።
ሌላ ሰው የኔን ቦታ ተክቶ ጓደኛና ወዳጅ ስለሆነ እኔ አላስፈልግም ብዬ አስቤ ነው አለኝ።
ምን ማለት ነው እናቴ ሞታ አንድ ያለችኝን ሰው ቀብሬ ብቻዬን በቀረሁበት ሰአት እንደማንኛውም ሰው እስከሰባቱ ቆይተህ ጥለኸኝ አደል እንዴ የጠፋኸው ከጎኔ መሆን በሚገባህ ሰአት የጠፋኸው አንተ ሆነህ ሳለ ጭራሽ እኔኑ መልሰህ ልትወቅሰኝ ነው ብዬ ተኮሳተርኩበት።
እሺ ይሁን ጠፋሁብሽ ከዛ ግን ትዝ ብዬሽ አቃለሁ ጭንቅላትሽ ውስጥ አቤል በዚህ በሀዘኔ ሰአት የት ጠፌ ብለሽ ጠይቀሻል።
እኔ ታስሬ ነበር።
ምስኪኗ እናቴ ብቻዋን ስታለቅስና ስትንከራተት ነበር።
ያኔ መተሽ ጠየቅሽኝ።
ምነው እቴቴና አቤል ጠፉ ብለሽ ጠየቅሽ?
እንዴት አስቻላቸው እንዴት ዝም አሉ ብለሽ አስበሻል አላሰብሽም አለኝ

❤121😨30👍17💔14😭5🥰2🙉1
ህላዌ እስኪለቀቅ ታናሽ እህቴ ፊደል ወደ2300 ተከታይ ያለው ቻናሏ ስልኳ ሲሰርቅ አብሮ ጠፍቶባት ድጋሜ መክፈት አልቻለችም እስከዛሬ ምትወዱላትና በጉጉት ምትጠብቁትን ታሪክ ለማግኘት አዲስ የከፈተችውን ቻናል ተቀላቀሉና ከዚህ በፊት ተጀምሮ ያላለቀውን ታሪክ መጨረስ ትችላላችሁ
👇👇👇👇
https://t.me/fidelawit1221
👇👇👇👇
https://t.me/fidelawit1221
❤31💔16
ህላዌ(✍️✍️ማኔ)
ለምን ታሰርክ ? አልኩት በቀጥታ።
ምንም አሁን አልፏል በቃ አለኝ።
ንገረኝ ምንድነው አልኩት።
ምንም አደለም የሆነ ሚሰራ ቤት አለ እዛ ቀን ስራ አለ ና ብለውኝ ሄጄ ቤቱ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖረው እንዴት ትሰራላችሁ ብለው ሰብስበው ይዘውን ሄዱ ዋናው ሰውዬ መጥቶ ሌሎቹን ሲያስፈታ እኔን ግን አይመለከተኝም እዛ ለምን እንደመጣ አላቅም ብሎ ትቶኝ ሄደ።
ፖሊሶቹ ሰራተኛ መስለህ ምን ለመስረቅ ነው ብለው መከራዬን አበሉኝ።
የሚገርምሽ ያንን ሰው ከዛ በፊት አይቼው አላቅም ጠላቴ አደለም አልተጣላንም አልተነጋርንም ግን ከሰው መሀል መርጦ እኔን እንደዛ አደረገኝ አለኝ።
አሳዘነኝ።
ምን እንደምለውም ግራ ገባኝ።
አይዞህ በቃ አቤል እኔም ታቃለህ እናትን የሚያህል ነገር አጥቼ እንዴት ልሆን እንደምችል አስበው በዛ ሁላ ሀዘን ውስጥ ምነው ጠፋህ ብዬ መደወል አልቻልኩም ግን አንተም እቴቴም ስትጠፉ በውስጤ አስቢያችሁ ነበር ሰሞኑን አልኩትና በትንሹም ለማፅናናት ሞከርኩ።
ከዛ በመቀጠል የህላዌንና የኔ ልብሶች ብቻ አውጥቼ ሌላው ቤት ውስጥ የነበረውን ሙሉ እቃ ትቼለት እኔ ለእቴቴ በየወሩ ብሩን ለእቴቴ እልክላታለሁ አንተ ደሞ እዚህ ውስጥ ኑርበት በቃ አባትህ በገባ በወጣ ቁጥር ቤት ውስጥ አያግኝህ እሱ ሲወጣላችሁ ከእቴቴጋ ቡናችሁን እየጠጣችሁ ተጫወቱ አልኩት።
በጣም ደስ አለው።
ሄጄ ሄጄ የገደሉ ጫፍ ላይ ቆሜ ልወድቅ ስል እንደዚህ ተስፋ ሚሰጡ ንግግሮችን እሰማና ቆም ብዬ ደሞ ለመኖር እጓጓለሁ አመሰግናለሁ ቅድስቴ ብሎ አቀፈኝ።
ፈገግ ሲል ሳየው እንባዬ መጣ በዚህ ልክ እራሱን እንዳይጥልና ተስፋ ለመቁረጥ ገና እንደሆነ የጎረቤቴን ቤት ደሞ እንዲያከራየው ነግሬው ለእቴቴም እንዲነግራትና ሰላምታ እንዲያደርስልኝ አስጠንቅቄው እዩኤል ህላዌን አቅፎ ይዟት ወደቤታችን ሄድን።
ማታ ላይ እራት ለማዘጋጀትና ቤቱ ውስጥ ቡና ለማፍላት ወሰንን በተቻለ መጠን እኔና እሱ አሁን ካለንበት በላይ መሀላችን መግባባት እንዲፈጠርና ለመተዋወቅ እንዲረዳን ለማድረግ እየሞከርን ነበር።
ቡና አፈላን የተወሰነ አወራን ያው እሱም ብዙ ቃላትን ሚያባክን ሰው አደለም እኔም ወሬ ላይ ጎበዝ አደለሁም የሆነ ነገር አውርተን አው ነው በቃ ዝምምምም ከዛ ደሞ አንድ እርእስ ይነሳ ነው እ እሱ አዎ አቀዋለሁ እንደዛ ነው አደል? አዎ ነው ከዛ ዝምምም...
በቃ ንግግራችን እንደጠበቅነው ሳይሆን አሰልቺና አስቀያሚ ሲሆብኝ ተውኩትና ቡናችንን ጨጨርሰን እንደልማዳችን ህላዌን መሀል አድርገን ተኛን።
ሁለታችንም ጣራ ጣራ እያየን አስሬ ሰአት እያየሁ በስተመጨረሻ እንቅልፍ ሸለብ አድርጎኝ የውጭ በር በሀይል ተንኳኳ ።
ሰአት ሳይ 4:15 ሆኖ ነበር።
ተከራዮቹ ከ3 ሰአት በላይ አያመሹም የቀረም የለም ማነው ብለን ተነስተን ወጣንና በሩን ከፈተን አቤል በር ላይ ቆሟል።
የለበሰው ልብስ ላይ የተንጠባጠበ ደም አየሁ
ደንግጬ ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት።
እዩኤል ግን በተረጋጋ መንፈስ አቤል ደና አመሸክ ና ግባና ቤት የተፈጠረውን ትነግረናለህ ና ግባ ብሎ ይዞት ገባ።
በሩን ዘግቼ ተከተልኳቸው።
በድንጋጤ እጄ ሁላ ሲንቀጠቀጥ ይታወቀኛል።
እቤት ከገባን ቡሀላ ምን እንደተፈጠረ ጠየቅነው።
ካባቴጋ ተጣላን።
ለምን?
ቤቱን ኑርበት ስትይኝ ደስ ብሎኝ ነበር።
ለእቴቴም ስነግራት በጣም ደስ ብሏት ፈጣሪን ስታመሰግን ነበር።
ማታ አባቴ ቤት አምሽቶ ሲመጣ እኔ ሶፋ ላይ አልነበርኩም የት እንደሄድኩ ሲጠይቃት እቴቴ ያለውን ነገር ነገረችው።
መጥቶ አባረቀብኝ።
እኔ እከፍላለሁ ብትልህ እንኳን ከሷም ብሩን እየተቀበልክ እዚህም ቤቱን አከራይተን በሁለት መንገድ ገቢ እናገኛለን እንጂ አንተ የማናባህ ዲታ ነህ አንድክፍል ቤት ውስጥ ብቻህን ምትኖረው ብሎ ሲጮህብኝ አልወጣም ከዚህ ቤት አልኩት ከዛ ስለጠጣም ጭምር ቀጥቅጦ ከቤት አባረረኝ።
ድጋሜ እዚህ ግቢ ካየሁህ በቢላ ነው አንገትህን ምቀነጥሰው ብሎ አስፈራርቶኛል አለኝ።

❤88💔47🙊2
ተመስገን
ተኝተን ስለነቃን።
ተመስገን
ዛሬን ስላሳየን።
ተመስገን
ተነስተን እንደልባችን ስለተንቀሳቀስን።
ተመስገን ስለሆነውም ስላልሆነውም ስላጣነውም ስላገኘነውም ነገር ።

🙏145❤17❤🔥3👏2
ህላዌ(✍️✍️)
ትንሽ የሀፍረት ስሜት እየተሰማኝ ውይ አቤል ተነሳህ እንዴ አልኩት።
እእእ ይቅርታ ለመተኛት እየሞከርኩ እቴቴ እንዳትጨነቅብኝ ደውለሽ ንገሪያት ልልሽ ነበር የመጣሁት ይቅርታ እሺ አለኝ።
ለምኑ ነው ይቅርታ ነግሪያታለሁ ለእቴቴም አትጨነቅ አልኩትና ወደውስጥ ገባን።
እሱ በቀጥታ ወደመኝታ ቤት ገብቶ ተመልሶ ተኛ።
እኔና እዩኤል ቁጭ እዛው ሳሎን ፍራሽ ላይ ቁጭ አልን።
ለመጠየቅ እየፈራሁ ግን ለምንድነው የሳምከኝ ?አልኩት
እኔ አላቅም ሳላስበው ነው ምነው የቀሰቀስኩብሽ ትዝታ አለ እንዴ አለኝ።
የለም ።
እስቲ ንገሪኝ ስለልጅሽ አባት ብሎ ጠየቀኝ።
የማውራት ሞራሌ ከየት እንደመጣ ባላቅም ማውራት ጀመርኩ።
የተዋወቅነው ድንገት ነው ማለቴ እንደቀልድ ትምህርት ቤት ተዋወቅን ያኔ ገና በጣምም ልጅ ነበርኩ ።
ጓደኞቼ በሱ ሙድ እየያዙ ሲያበሸቁኝ ሳላስበው ስለሱ ማሰብ ጀምሬ አፈቀርኩት።
እኔ ብቻ ነበርኩ ያፈቀርኩት እሱ ቼክም አያደርገኝም።
እሱን የኔ ለማድረግ ብዙ ሞክሪያለሁ
ከኔ ጓደኞች አንዷ የሱን ጓደኛ ጠብሳ እኔና እሱን አንድ ላይ ለማድረግ ሁላ ሞክራ ሁላ አልተሳካላትም።
ብቻ ብዙ ብዙ የኔ ፍቅር እየበረታ ሄዶ ክላስ እስከመውደቅ ደርሼ ነበር።
ዞሮ ዞሮ በዛም ተለመነ በዚህም ተለመነ አብሬ አልሆንም አለ።
ከዛ ግን ሀይስኩል ከገባን ቡሀላ የሆነ የኔና የሱ የጋራ ጓደኞች ተሰብስበን ባለበት ድንገት ተነስቶ እስከዛሬ አፍቅሮኝ ሲሰቃይ እንደቆየ ሰው ስብር ቅንጥስ አለ።
እኔ ሆዬ ከዛ በፊት ፍቅር አላውቅ።
መፈቀር እንዴት እንደሆነ አይገባኝ ሲያቅፈኝ ሲቅለሰለስ ፍስስ አልኩ።
አብረን ካልተኛን የኔ መሆንሽን በምን አረጋግጣለሁ አለኝ።
አረ አንተን ከማጣ ያልከው ይሁንልህ ብዬ አብሬው ተኛሁ።
ያቺ ቀን ከንፈሬን የተሳምኩበት በስርአት የታቀፍኩበት ስሜት የሌለው ግንኙነት የፈፀምኩባት የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ቀን ናት።
የሚገርምህ ያን ቀን እስከቤት ድረስ በፍቅር ነበር የሸኘኝ።
ስለመዳኒት ምንም አላውቅመሰ እሱም አልነገረኝም እንደውም ለጓደኞቼ ስለዚህ ነገር እንዳላወራ አስተጠንቅቆኝ ተለያየን።
ሌሊቱን ስስቅ ስፈነድቅ የስንት አመት ፍቅሬን በእጄ ስላስገባሁ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ ነጋ።
ግን ያን ቀን ለካ እየተለያየን ነበር ጥሎኝ ጠፋ።
አልኩት።
ያለምንም ምክንያት ትቶሽ ሄደ እርግጠኛ ነሽ አለኝ።
አዎ አልኩት።
እና አሁን ልጁ የት እንዳለ አታቂም ሲለኝ በድንጋጤ አፈጠጥኩበት

❤110👍1🔥1