Mane Writer
4.66K subscribers
215 photos
20 videos
5 files
1.05K links
ምርትና አግልግሎቶን ለማስተዋወቅ ያናግሩኝ !!!

ለሀሳብ አስተያየታችሁ

ሀሳብ አስተያየት 👉 @Maneget
Download Telegram
Forwarded from D.NØXE
የተሳሳተው መስመር

የአዲስ አበባ ክረምት በከባድ ዝናብ እና በብርድ ታጅቦ ከተማዋን አውኳታል። ኤልያስ በአሮጌው ካዛንቺስ ሰፈር በሚገኘው አነስተኛ የቤት ኪራዩ ውስጥ ብቻውን ተቀምጧል። በጠረጴዛው ላይ የተረሳው የሻይ ብርጭቆ ቀዝቅዟል። እሱ በአንድ ትልቅ የህትመት ድርጅት ውስጥ ዋና አራሚ (Editor) ሆኖ ቢሰራም፣ የራሱን ህይወት ግን ማረም ያቃተው ይመስላል። ከአንድ ዓመት በፊት ከደረሰበት ከባድ የፍቅር ስብራት በኋላ፣ በሰዎች ላይ ያለው እምነት ተሸርሽሮ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት ዓለም ውስጥ ተዘግቶ ነበር። መጻሕፍት ማንበብ እና ማታ ማታ የዝናቡን ድምፅ ማዳመጥ ብቸኛ የህይወት መደገፊያዎቹ ነበሩ።


ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ join ይበሉ pin ተደርጓል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/ke_kaloche1
https://t.me/ke_kaloche1
https://t.me/ke_kaloche1
🔥43🥰2🤗2
Forwarded from Ķůń fé¥éķůń 🕌🕌🕋
የተለያዩ ምርጥ ምርጥ ጫማዎችን የምታገኙበት ምርጥ ቻናል
የቴሌ ግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉

#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand


💬በ inbox  @Reisbrandi  አዋሩኝ ☎️፣                 0995235877
10
ይለቀቅ?
80👍21🙏6😡4🫡2
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)

ከዛ ምን እንደተፈጠረ ለመስማት  ወደሱ ቀረብ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ።

ከዛስ አልኩት..
ከዛማ ያው እነሜሪም እንዳያችሁት ሙሽሮቹጋ እየሄደች መሀላቸው እየገባች ፎቶ ስትነሳ ።

ዝም ብላ እልልልል ስትል ነበር።
እዛ የነበሩት ሁሉም አብዳለች እንዴ በሚል አስተያየት እያዩአት ነበር።

እና ሊያረጋጋት የሞከረ ሰው ወደሷ ሲጠጋም እላያቸው ላይ መጠጥ እየደፋች አንድ ሰው እንዳይነካኝ እያለች ስታብድ ነበር።

ከዛ ቡሀላ እኔም ከሙሽራውጋ ወጥቼ ሄድኩኝ።
ማታ ላይ ከሙሽራው ቤት ወጥቼ እሷን ይዤ ወደቤት ለመውሰድ ስመጣ የለችም።

ከስንት ፍለጋ ቡሀላ አገኘኋት ሳገኛት ግን ከነሜሪ ቤት ወደታች ያለው አጥር ስር ወድቃ ነበር ስትወደቅ ደሞ በሀይል ተጎድታለች ጭንቅላቷምጋ ደም ነበር አለኝ።

ይባስ አለቀስኩ።
እናቴ መሞቷ ሳያንሳት በመጨረሻም ቀን እንደዛ ተዋርዳ መሞቷ አመመኝ።
ውስጧ ምን ያህል እንደቆሰለ ምን ያህል እንደታመመ ቀድሞ ቢገባኝም ያን ቀን ደሞ የባሰ ነበር።
ሰባቱ እስኪወጣ ድረስ የተወሰነ ሰው ነበር አልፎ አልፎም ቢሆን

ከዛ ቡሀላ ሁሉም ወደየራሱ ስራ ገባ።
እቴቴ ወደሰው ቤት ስራዋ ተመለሰች።
ሜሪም ብቶን አሁን ሚጠብቃት ህይወት ትዳር አለ።
እንደድሮው ልጅነት የለም።

በስተመጨረሻ እኔ ጎረቤቴና ህላዌ ብቻ መሬት ላይ የወረደው ፍራሽ ላይ እራሳችንን አገኘነው።

አንተ አቴድም የሚጠብቅህ ስራ የለህም ሂድ በቃ አልኩት።

አይ ችግር የለም ከጎንሽ መሆን ፈልጌ ነው አለኝ።
በለቅሶው መሀል ከህላዌጋ ሀይለኛ ወዳጅነት መስርተው ነበር።

እሷም ሙሉ ጊዜዋንና ትኩረቷን እየሰጠችው ነበር።
ህላዌ መሀላችን ቁጭ እንዳለች እንቅልፍ ወሰዳት።
እኔም ደገፍ አልኩኝ።

በዛ መሀል ጎረቤቴ ታሳዝኛለሽ ማለቴ በዚህ እድሜሽ ያሳለፍሽው ሁሉ አይገባሽም አይንሽን ሳየው አይንሽ ውስጥ ያለው ስብራትና ህመም ያስፈራኛል።

ካወኩሽ ጀምሮ  እኔ እስከዛሬ ለኖርኩት ህይወት መፀፀት ጀምሪያለሁ።
ለካ ምንም አሎንኩም ለካ ምንም አልተነካሁም ለካ እንደዚህም ሚኖር አለ እንድል ነው ያደረገሽኝ እና የምር ነው ማመሰግነው አለኝ።

ዝም አልኩት።

በመሀል ስልኬ ጠራ።
ያኔ ነው ስልኬ እሱጋ እንደነበር ያወኩት።
የሚጠራውን ስልክ ብድግ አደረገና ውይ መጡ ቆይ ልቀበላቸው ብሎ ወጣ።

እህቱና ያብስራ ለቅሶ ሊደርሱ መምጣታቸው ነበር

https://t.me/mane121921
76🥰11
ህለዌ (✍️✍️ማኔ)


ሳያቸው ምንም አልተሰማኝም ደንዝዣለሁ ያብስራ ኮፍያ አድርጎ ለመሸፋፈን ሞክሮ ነበር የመጣው።

ወደውስጥ ገቡና ቁጭ አሉ።

እህቱ በስስት እያየችኝ እኔ ሰው ማፅናናት አልችልበትም ግን በቃ አይዞሽ የኔ እናት አለችኝ።

እነሱ ገብተው ብዙም ሳይቆዩ ህላዌ ብንን ብላ ብድግ አለችና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።

ምን እንደሆነች አልገባኝም ጎረቤቴ እቅፍ አድርጎ ሊያባብላት ሞከረ እሷ አሻፈረኝ አለች።
ተነስቼ ተቀበልኩት ግን እሷን የመሸከም አቅም ስላልነበረኝ ወደመኝታ ቤት ይዣት ገባሁና ለማስተኛት ሞከርኩ ትንሽ ትንሽ ተረጋጋችና በዛው ወደማሸለቡ ገባች።
ግን በሰመመን ውስጥ ስቀ ስቅ እያለች ነበር።
ከእቅፌ ለማስተኛት እየሞከርኩ በሩ ተከፈተና ያብስራ ወደውስጥ ገባ።

ይቅርታ ተረጋጋችልሽ የማግዝሽ ነገር ካለ ለመጠየቅ ነበር አለኝ።
ምንም የለም አልኩት።

የምር ልጅሽ ናት እንዴ እኔኮ የእዩ እህት ስትነግረኝ አላመንኩም አለኝ።
አንገቴን ነቀነኩለት።

ስንት አመቷ ነው አለኝ?
አይመለከትህም አልኩት።

ህላዌ ስትተኛልኝ ተነስቼ ወደሳሎን ሄድኩ ተከተለኝ።
ጎረቤቴና እህቱ ሳሎን ስላልነበሩ ወደውጭ ስመለከት ከግቢው ውጭ የነበረው መኪና ውስጥ ገብተው በኮምፒውተር ስራ እየሰሩ ይሁን ምን አላቅም ግን እያስተካከሉ አየኋቸው የውጭውን  በሩን ክፍት አድርገውት ነበር የወጡት።

ሳሎን ቁጭ ከማለቴ ህላዌ በድጋሜ መጮህ ጀመረች።

ብድግ ብዬ ወደሷጋ ገባሁ ከአልጋው ላይ ላነሳት ስሞክር አቅም አንሶኝ መልሼ ወደኩኝ።

ያኔ ያብስራ ብድግ አድርጎ አቀፋትና ጀርባዋን እያሻሸ እሷን ለማስተኛትና ለማረጋጋት እየሞከረ ነበር።

እንደዛ ሆነው ሳያቸው እንባዬ መጣ አባቷ አቅፏት መቆሙን እሷ አታቅም እሱም ልጁን እንዳቀፈ አያቅም ለኔ ግን ያ ነገር ህልሜ ምኞቴ ነበር።

ህላዌ አሁንም ቀስ በቀስ መረጋጋትና ዝም ማለት ጀመረች።
ትከሻው ላይ እጇን ዝርግት አድርጋ ተኝታ ነበር።

እሷን እንዳቀፈ በጥርጣሬ አይን እያየኝ ምታሳሳ ልጅ ነው ያለችሽ በህይወቴ ልጅ ሳቅፍ የመጀመሪያዬ ነው እና ደስ የሚል ስሜት አለው እንዴት ወለድሻት ታድለሽ አለኝ።

ተሰቃይቼ ነው የወለድኳት የሰው ፊት ገርፎኝ ትምህርቴን ትቼ እናቴን ትቼ ነው የወለድኳት እሷን አርግዤ የእናቴን ቤት ትቼ ወጣሁ ይኸው እናቴ ስትሞት ይሄንን ሰፈርና ቤት እረገጥኩት ።

እሷን ለማግኘት እራሴን አጥቼ ነበር አሁን ደሞ እናቴን አጣሁ  አልኩት በእልህ ተሞልቼ።

መቼ ነው ይሄ ሁላ የተፈጠረው ልጅሽ ስንት አመት ሆናት ብሎ ድጋሜ ጠየቀኝ በመርማሪ አይን እያየኝ ነበር።
አይመለከትህም እሱ አንድ አመት የሆናት ባለፈው እንደምታያት ትንሽ ናት አልኩት።

ፊቱን አዙሮ ወደሳሎን ሄደና እንዳቀፋት ሶፋ ላይ በጀርባው ደገፍ ብሎ ቁጭ አለ።

በዛን ሰአት ውስጡ ምን እየተሰማው እንደሆነ አላቅም።
ደስ ይበለው ይክፋው አላቅም።
ምን እንደሚያስብም በፍፁም አላቅም።
ሁለቱ በዛ መልክ ሲሆኑ እኔ ደሞ መሬት ላይ ወዳለው ፍራሽ ሄጄ እግሬን ዘርግቼ ቁጭ አልኩ።

እየሰረኩኝ ሳያቸው ነበረ
አሁንም ቢሆን ልቤ ህላዌ ከአባቷጋ ብታድግ ቤተሰብ ቢኖራት የኔን ህይወት ባትደግመው አባቴ ማለት እየፈለገች አባቴ ሳትል ባትቀርብኝ የሆነ ተአምር ተፈጥሮ አባት በሆነላት ብዬ እየተመኘሁ ነበር።
ፊቴ ተኮሳትሮ ልቤ ግን ሌላ ነበር።

ብዙም ሳይቆይ እዩኤልና እህቱ ወደውሰጥ ገቡ ያብስራን ሲያዩት ሁለቱም በንፁህ ልባቸው ፈገግ አሉ።

ልጅ ያምርብሀል ለምን አባት አትሆንም ቶሎ ውለዱ እንጂ ብሎ ጎረቤቴ በትንሹ ፈገግ አለ።

ሰአቱ ሲሄድ እነሱም ተያይዘው ሄዱ።

ቤት ውስጥ እኔና ህላዌ ብቻችንን ቀረን።
በሩን ዘጋግተን ባዶ ቤት ውስጥ ቁጭ እንዳልን በሩ ተንኳኳ።
ተነስቼ ከፈትኩ ያብስራ ነው ፍቃዴን ሳይጠይቅ በሩን ዝግት አድርጎ ወደውስጥ ገባ ተከተልኩት....

ቅድስት እውነቱን ንገሪኝ አውቄ ነው እነዛን ሁለት ከረፈፍ ከቤት ያስወጣኋቸው ንገሪኝ ይቺ ልጅ የኔ ልጅ ናት አደል?አለኝ

ዝም ብዬ አየሁት ።
ጥሩ ዝምታሽ እራሱ መልስ ነው በይ አሁን ሶስታችንም ተያይዘን እንጠፋለን ማንም ወደማያቀን ማንም ወደማያገኘን ቦታ እሺ አለኝ።
መቼም አላደርገውም እንዳንተ አይነት ሴጣን ተከትዬ የትም አሌድም አልኩት።

ጥፊ ይሁን ቦክስ በትክክል የማላስታውሰው ምት ፊቴ ላይ አሳረፈብኝ.....

https://t.me/mane121921
95😨56🤯1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)


ዝም አልኩ።
አይኔን የሞላውን እንባ ብቻ አፈሰስኩት።

ቅድስት ያምሻል እንዴ በእርግጥ አሁን ላልወድሽ ላላፈቅርሽ እችላለሁ ግን ፍቅር በጊዜ ሂደት ይመጣል።

ቀስ ብለን መዋደድ እንችላለን።
ልጃችን አለች በመሀል እሷ ታስማማናለች።
ለሷ ስንል አብረን መሆን እንችላለን።
አብረን ወደባህርዳር እኔዳለን።

እኔ እዛ ትልቅ ኮስሞቲክስ ቤት ከፍቻለሁ ከተማ ውስጥ አደለም ግን ከከተማው ትንሽ እራቅ ብሎ ቤት አለኝ።
አሪፍ ገንዘብም ሰርቻለሁ እዛ ተጨማሪ ስራ መስራት እንችላለን አለኝ።

የሚያወራው ግራ ገባኝ።
እኔ ያብስራን ሳቀው ሰው ቼክ የማያደርገው መሞትና መኖሩ ማንም ግድ የማይሰጠው ሰው ነበር ዛሬ ደርሶ ቤት አለኝ ሱቅ አለኝ ሲል የተለያየንበት ጊዜ ይሄን ያህል እሩቅ ሆኖ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ።

ቢሆንም በአቋሜ ፀናሁ አሌድም የትም አሌድም አረሳሁልህም ያን ሁላ ለፍልፈህ አብረኸኝ ተኝተህ ለስሜቴ ለክብሬ ሳትጨነቅ በነጋታው ትተኸኝ መጥፋትህን አረሳሁትም ባንተ ምክንያት ያለቀስኩትን ደም እንባ አረሳሁልህም ባንተ ምክንያት እርቦኝ ቁራሽ እንጀራ የናፈቀኝን ቀን አረሳሁትም።
አንተ ልጅነቴን ህይወቴን ህልሜን ሳቄን ነው የቀማኸኝ።

ለመጨረሻ ጊዜ ከልቤ ፈገግ ያልኩት የሳኩት ያኔ የተለያየንበት ቀን ላይ ነው ገባህ።
ብትገለኝ እንኳን ተመልሼ ካንተጋ አልሄድም ብሞት ይሻለኛል አልኩት።

ያኔ ምን እንደተፈጠረም አላቅም እንደዛ ከሆነ ለምን ወለድሻት።
መውለድ ውለጅ ለምን ከኔ እእ ።
ያሳለፍኩትን ህይወት ነግሬሻለሁ።
የእናትና ያባት ፊት እያየሁ ነው ያደኩት።

ለአንድ ቀን በሳቁልኝ ለአንድ ቀን ባቀፉኝ ለአንድ ቀን ከእናትና አባቴ መሀል ቁጭ ባልኩኝ እያልኩ ስመኝ ነው የኖርኩት።

በኔ እድሜ ያሉት የቅንጦት ጫማና ልብስ ሲመኙ እኔ ግን እናትና አባቴ በስሜ እንኳን በክብር ያብስራ ብለው በጠሩኝ ነበር ምኞቴ ገባሽ።

ትምህርቴን  አቋርጬ ሁሉንም ነገር ትቼ ጠፍቼ ሄጄ ይሄን ህይወት ለመገንባት እዚህ ህይወት ውስጥ ለመግባት ስንት ሌሊቶቹን ያለ እንቅልፍ አሳልፊያለሁ።

ስለዚህ አሁንም ይቺ ልጅ እኔ ያሳለፍኩትን የኖርኩትን እንድትደግመው አልፈልግም ።
የፈለገ ጨካኝ አጭበርባሪ ውሸታም ብሆን እንኳን በዚህ ጉዳይ ሁለተኛ ጊዜ እንኳን አላስብም ።
ምን እንዳሳለፍኩ አቀዋለሁ።
የእናትና አባትን ፊት ፊት እያዩ በሰቀቀን መኖር ደስ አይልም ገባሽ ወደሽ አደለም በግድሽም ቢሆን ትሄጃታለሽ አለኝ።

የማወራውን አላውቅም ንዴት ጭንቅላቴን አውሮኝ ነበር።
እናትና አባትህ የማይወዱህ እንደዚህ አይነት አስቀያሚ ሰው እንደሆንክ ቀድሞ ታውቋቸው ነው።
ልጄ እንዳንተ አይነት ሌባ አጭበርባሪ አባት የላትም።

እንደውም ለእዩኤል ሁሉንም ነገር እነግረዋለሁ አሁን ለመታኸኝ ምት ዋጋ ካላስከፈልኩህ ታያለህ አልኩት።

ከቁጥጥር ውጭ ሆነ ቦክስ ጥፊ እርግጫ ምንም አልቀረልኝም ደም በደም እስክሆን ጠፈጠፈኝ ሀዘን ላይ ናት ብሎ ትንሽ እንኳን ርህራሄ አላሳየኝም..........

https://t.me/mane121921
😱7831💔18😨6😭4👍1
በየትኛውም ሁኔታ ሰዎችን እንዳትደገፉ።
ለሰዎች ሙሉ እምነታችሁን እንዳትሰጡ።

ህይወታችሁ ደስታችሁ በሰዎች ላይ እንዳይመሰረት።

የኔ ያላችሁት ሰው መቼ እንደሚጥላችሁ መች እንደሚሰብራችሁ መቼ እንደሚቀየርባችሁ አታቁም።

ድጋፋችሁ ፈጣሪ ይሁን ከሱ በመቀጠል በራሳችሁ ቀጥ ብላችሁ መቆምን ልመዱ።
ፉክክራችሁ ከራሳችሁጋ ይሁን ደስታችሁን ከልባችሁና ካጠገባችሁ አታርቁት።

ስኬታችሁን ከፍታችሁን ከሰውጋ እንዳታወዳድሩ ውድድራችሁ ከራሳችሁና ከትናታችሁጋ ይሁን።

በህይወታችሁ ውስጥ በፆምም ይሁን በፀሎት ማስወጣት ያለባችሁ ነገር ምቀኝነትና ቅናትን ነው።

ምቀኝነት እራስን ደስታን ሰላምን ያሳጣል።
ከእናንተ ሚጠበቀውን ነገር ከእናንተ ሚጠበቀውን ክብር ካለመሰሰት ለሰው ስጡ።

ሰዎችን አብዝታችሁ ውደዷቸው ግን በፍፁምምም እንዳትደገፏቸው
37👏11
Forwarded from Sirius_black
ምንድነው ፍላጎትህ/ሽ ? ለነገሩ ምንም ቢሆን Don't worry ....

ግጥም ......

ድርሰት ........

አዝናኝ ወግ......

አጫጭር የፍቅር ታሪክ......

ወይስ ገራሚ ጥቅስ....

የፈለጋችሁበትን አማርጣችሁ ምታገኙበት ድንቅ Channel ጀባ ልበላችሁ.....

በደራሲ
@sirius_black1212 የተፃፉ ውብ የ ብዕር አርማዎች እለት በእለት እሚታተምበት ምርጥ Channel

ተቀላቀሉ አትፀፀቱም!

Join us
https://t.me/yebier_arbegna
11
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)


መጮህ አልቻልኩም ከውርደቴ ከሀዘኔ ሳላገግም ሌላ ድራማ መፍጠር አልፈለኩም።
ዝም አልኩ።
እራሴን ለመከላከል በተቻለኝ መጠን ሞከርኩ የህላዌ ለቅሶ ወደቀልቡ መለሰው መሰለኝ አንድ ነገር ትንፍሽ ካልሽ ያንቺም የልጅሽም ህይወት አደጋ ላይ ነው ሚወድቀው ነግሬሻለሁ እስከማታ ወይ እስከነገ አስቢበት ከዛ ሚጠቅምሽን ውሳኔ ወስኚ ብሎኝ በሩን ወርውሮት ወጣ።

ከልጄጋ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ።
እናቴ ስሌለች ገና ከዛሬው ማንም እየመጣ ሊሰደሰበኝ ማንም እየመጣ ሊመታኝ ነው ብዬ አለቀስኩ።

ከሁሉም ነገር ጥፍት ብዬ ከሁሉም ነገር እራቅ ብዬ ልጄን ብቻ ይዤ መኖር በምፈልግበት ህይወት ውስጥ ግን እሱን ማድረግ አልችልም።
አሁንም ድረስ እናቴ ከሰዎች መሀል ተመልሳ እስክትመጣ እየጠበኩ ነው።

አሁንም አንቺ አረፍ በይ ህላዌን እኔ አበላታለሁ እኔ አስተኛታለሁ እንድትለኝ እየጠበኩ ነበር።
ልጄም ብትሆን እንደትልቅ ሰው አውጥታ የውስጧን አትናገር እንጂ እማ እንደናፈቀቻት ግልፅ ነው ድንገት ምርር ብላ የማልቀሷና የመቆጣቷ መንስኤ እሱ እንደሆነ አቃለሁ።

ምን እንደምወስን ምን እንደማረግ ግራ በገባኝ ሰአት ጭንቅላቴ ውስጥ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለ።
በቃ ያብስራን እሺ ብዬው ከሱጋ ብጠፋስ ማንም ወደማያቀኝ ማንም ወደማያገኘኝ ቦታ ብሄድስ እዚህ እናት የለኝ አባት የለኝ።
የልጄ ሞራል ከሚነካ ከምትጎዳብኝ ከሱጋ ብሄድስ ብዬ አስብኩ።

ጭንቅላቴና ልቤ መሀል ትልቅ ግጭት ተፈጥሮ ባለበት ሰአት ጎረቤቴ አስቤዛ ምናምን ገዛዝቶ ከውጭ ገባ።

ፊቴን እንዳያየው በጋቢ ሽፍን ብዬ ተኛሁ።
ህላዌ እንዳየችው ወደሱ ተንደረደረችና አቀፈችው።
እኔ እንደተኛ ሰው ለማስመሰል ሞከርኩ።
አጠገቤ መጥቶ ቆመና ህላዌን ባዶ ቤት ውስጥ ትተሻት እንቅልፍ እንደማይወስድሽ አውቃለሁ።

ተነሺና ምግብ እንብላ ህላዌም አልበላችም አለኝ።
ቀስ ብዬ የለበስኩትን ጋቢ ገለጥ አድርጌ እናንተ ብሉ እኔ እቆያለሁ አልኩት።

https://t.me/mane121921
👍7749😡16🥰4🙏3
Forwarded from Sirius_black
ምንድነው ፍላጎትህ/ሽ ? ለነገሩ ምንም ቢሆን Don't worry ....

ግጥም ......

ድርሰት ........

አዝናኝ ወግ......

አጫጭር የፍቅር ታሪክ......

ወይስ ገራሚ ጥቅስ....

የፈለጋችሁበትን አማርጣችሁ ምታገኙበት ድንቅ Channel ጀባ ልበላችሁ.....

በደራሲ
@sirius_black1212 የተፃፉ ውብ የ ብዕር አርማዎች እለት በእለት እሚታተምበት ምርጥ Channel

ተቀላቀሉ አትፀፀቱም!

Join us
https://t.me/yebier_arbegna
8🗿1
ቶሎ ቶሎ ካለመለቀቁ ውጭ
ይሄን ያህል ጊዜ ቅድስትን ስታነቡ በፍቅር ስትከታተሉ የነበራችሁ ሰዎች እስቲ ስለታሪኩ የሆነ ነገር በሉኝ እየተማራችሁበት ነው እየወደዳችሁት ነው?
እስቲ የሆነ ነገር በሉኝ
👇👇
😡4221👏19👍1
ለሰጣችሁኝ አስተያየት አመሰግናለሁ አብዛኞቻችሁ መማር ያለባችሁን ነገር እንደምትወስዱ ተስፋ አደርጋለሁ ዛሬ ይለቀቃል::
👏3614🥰7🤔3🙏2😡1
ህላዌ (✍️✍️)

ሰአቱ እየመሸ ሄደ።
ተሸፍኜ ሳለቅስ ነበር ያመሸሁት።

ሲመሽ ሜሪም ሀይሌም ተያይዘው ምግብ ሰርተው ይዘው መጡ።

ሜሪ ስራ አጊታ ሁለተኛ ቀኗ ነበር።
ሀይሌም በዘመድ ተቀጥሮ ሁለቱም ቤታቸውን ለማቋቋም ጠንክረው ወደስራ ገብተዋል መልስ ቅልቅል የሚባሉ ነገሮች በእናቴ ሀዘን ምክንያት ቀርተዋል።

እሷ ስትመጣ ተነሽ አንቺ ተኝተሽ ነው አለችኝ።
እየተሳቀቀኩ የለበስኩትን ገለጥኩት።
ሜሪ ጮኸች ምን ሆነሽ ነው ከማንጋ ነው የተጣላሽው አለችኝ።

ከጎረቤቴ ውጭ ሌላ ሰው ይሆናል ብላ ስላላሰበች ወደሱ አፈጠጠችበት ነይ ተነሽ ማነው እንደዚህ ያደረገሽ ማነው ያስለቀሰሽ ቅድስት አለችኝ እልህና ንዴት በሞላው ድምፅ።

ማንም አደለም ከማንምጋ አልተጣላሀሁም ሜሪ አቱጪሂ አልኳት።

ወደጎረቤቴ ሄዳ እየገፈተረችው አንተ ነሀ ካንተ ሌላ ማን ቤት ውስጥ መጣ እእ ማታ እንደዛ ቁልጭ ያለ ፊት ትቼ ሄጅ እንደዚህ ሆና ማግኘት ምን ይባላል ብላ ጮኸችበት።
እውነታው ግን ለተወሰኑ ሰአታት ከቤት ወጥቶ በተመለሰበት ቅፅበት እንደዛ ሆኜ ስለጠበኩት እሱም ደንግጦ ደርቆ ቆሞ ነበር።

እያለቀስኩ እየማልኩ  ሜሪ እሱ አደለም አልኳት።

እሺ ምን ሆነሽ ነው ተናገሪ ብላ አፈጠጠች።

ተስፋ ቆርጬ ደብሮኝ ከፍቶኝ እራሴን ከግድግዳጋ እያጋጨሁ ነበር በቃ እሱ ምንም አላጠፋም ፊቴን ሁላ አሁን ነው ከእናንተ እኩል ያየው አልኳትተ።

በዛ ሰአት ፊቱ ላይ ያነበብኩት የጥፋተኝነትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይሄ ነው የሚባል አልነበረም።

ይጨመር?🤔
👍👍👍

https://t.me/mane121921
👍4824
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)


ምሽቱን ሰብሰብ ብለን ከሁሉም በኩል ምክር እየተለገስኩ ሜሪ ያመጣችውን ምግብ በትሪ በልተን ቀለል ብሎን አመሸን።

አልፎ አልፎም እግረ መንገዳቸውን ብቅ ብለው ሚያልፊ የሰፈር ሰዎችም አልጠፉም።

ሲመሽ እነ ሜሪ ባለትዳር እንደመሆናቸው ተያይዘው ወደቤታቸው አመሩ።
ያብስራም ተመልሶ እኔጋ ሳይመጣ ጎረቤቴም ከቤቴ ሳይወጣ ለኔና ለህላዌ ሚያስፈልገንን ሳንጠይቀው እያደረገልን ሁለት ወራት ተቆጠሩ።
ሁለት ወር ሙሉ ለእቴቴ የኔንም የሱንም የቤት ኪራይ እየከፈለ ነበር የቆየው።
እኔም ብሆን ሳልወድ በግድ ለመጠንከር ስሞክር ነበር።


አንድ ቀን እሁድ እነ ሜሪ ቤት ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ኑ ብላ ጠራችን።

እኔም ህላዌና ጎረቤቴን ይዤ ከሷ ቤተሰቦችጋ ተሰብስበን ወደነሜሪና ሀይሌ ቤት ሄድን።

ለመጀመሪያ ጊዜ ቤቷን ያየሁትም ያኔ ነው።
ልክ ሜሪ ከልጅነቷ ጀምሮ ምትመኘው አይነት የቤት ስታይል ነው።
እቃ ያልበዛበት ያልተጋነነ ሲምፕል የሆነ ግን ማራኪ ቤት ።

ቤት ስንደርስ የሀይሌም ቤተሰቦች መተው ነበር።
አንድ ላይ ተሰብስበን ምግብ በላን ቡና ተፈላ እንደቤተሰብ በሚያስቀና መከባበርና ፍቅር ምሽቱን አሳለፉት።

ሀይሌ ከሰዎች መሀል ሚስቱን እንዴት በስስት እንደሚያያት ለተመለከተ ሰው መቅናቱ ግዴታ ነው።

ሲመሻሽ አካባቢ ሜሪና ሀይሌ እጅ ለእጅ ተያይዘው ቆሙና ያው እንግዲ
ደስታችንንም ሀዘናችንንም ቅድሚያ ለቤተሰቦቻችን ነው አሳልፈን ምንሰጠው እና ለሰርጉ ሰሞን ባጋጠመን ትልቅ ሀዘን የመመራረቂያ ሰፊ ጊዜ አላገኘንም።
ዛሬ ደሞ ምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ጓደኛዬ እህቴ አብሮ አደጌ በተገኘችበት ምናበስራችሁ ዜና አለ አለች ሜሪ ሀይሌ ቀበል አደረገና አዎ ያው እንግዴ በቶሎ ወደትዳር ለመግባት ስናስብ ሳትቃወሙ ፍቃዳችሁን ስለሰጣችሁን ሀላፊነት እንድንወስድ ስላመናችሁን እናመሰግናለን በመቀጠል ዛሬ ሜሪ የሁለት ወር ከምናምን እርጉዝ ናት ስለዚህ እናንተ ቤተሰቦቻችን ፈጣሪ የባረከው ልጅ እንድናቅፍ እንድትመርቁን ነው ዛሬ እዚህ የጠራናችሁ ብለው ተናገሩ የቤቱ ሰው እንዳለ ጥርስ በጥርስ ሆነ።
እልልታ ተሰማ።
ሁሉም በየተራ መልካም ምኞታቸውን ተናገሩ የሜሪ አባቴ ወንድ ልጅ አያለቅስም የሚለውን መፈክር ወደጎን ትቶ አበባዬ ልጄ ወግ ማእረግ አሳይተሽኝ ዛሬ ደሞ አያትህ እንድሆን እያዘጋጀሽኝ ስለሆነ የነካሽው ያሰብሸው የተመኘሽው ሁሉ ይሁንልሽ ይመርልሽ ብሎ መረቃት ።

እኔ ምንም መናገር አልቻልኩም ገና ላወራ ስል እንባና ሳግ እየተናነቀኝ ምንም ሳልተነፍስ ከሜሪጋ ተቃቅፈን አለቀስን።

ቤተሰቡ በደስታ ሳጥን ሳጥን ቢራ እየገዛ መጣ ዛሬ እዚሁ ነው ምናድረው ከዚህ በላይ ደስታ ከዚህ በላይ አለም የለም ብስራት አሰማችን አሉ።

እኔና ጎረቤቴ አመስግነን ወጣን።
እነሱም አልተጫኑንም ነበር

ይጨመር🤔

https://t.me/mane121921
101👍32
🤗143
https://vt.tiktok.com/ZS9SBTWY2NxRt-ZG3s4/

1 የቻናላችን ተከታይ ቲክቶክ ኮሜንቱን like አድርጉለትና ለበአል ምንጣፍ አሸልሙት የኔ ቤተሰቦች ኮሜንቱን ብቻ like አድርጎ ማለፍ ነው ከእናንተ ሚጠበቀው
👍187
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)

ህላዌ እንቅልፍ ወስዷት የጎረቤቴ ትከሻ ላይ ቸኝታ ነበር።
እሱ አቅፏት እየሄድን መንገድ ላይ አይን አይኔን እያየ ውስጥሽ ምን እየተሰማሽ ነው ?አለኝ

ምንም አልኩት ጥርሴን ነክሼ።

እህህ ውስጥሽ እልህ ይሁን ቅናት ማታውቂው ስሜት እየተሰማሽ ነው።
አንቺም እንደሴት ልጅ መከበር ይገባሽ ነበር ግን እሱን ክብር አንቺ አላገኘሽም።
በክብር ማግባት በክብር መውለድ አለቻልሽም ምንም እንኳን ጓደኛሽን ብትወጃትም ዛሬ እሷን እንደዚህ ስታያት ለምን እኔስ የሚል ጥያቄ ውስጥሽ ተፈጥሯል አደል አለኝ።

መልስ በመመለስ ፋንታ አለቀስኩ።
እንደ ህፃን ልጅ ድምፅ እያወጣሁ ነበር ያለቀስኩት ዝም ብሎኝ በዝግታ ባጠገቤ ከመራመድ ውጭ ምንም አላደረገም አላባበለኝም አይዞሽ አላለኝም ዝምምምም አለኝ።

ሲበርድልኝ ለቅሶዬን ዋጥጥ አድርጌ ዝም አልኩ።

ሰፈር ደርሰን እስከቤት ወክ አደረግንና ወደቤት ገባን ህላዌን አስተካክለን አስተኛናትና ሁለታችንም ፍራሹ ላይ ቁጭ አልን ህላዌ ከመሀላችን ነበረች።

በዛ መሀል ሊጠይቀኝ ሚፈልገው ነገር እንዳለ ነገረኝ።
ምንድነው በሚል አስተያየት አየሁት።

ለምን እኔና አንቺ አብረን አንሆንም ለምን እንደባልና ሚስት ሆነን ህላዌን አናሳድግም ለምን የቅርብ የልብ ጓደኛሽ አታደርጊኝም አለኝ።
ግራ ገብቶኝ ማለት አልኩት

ምን ማለት አለው አግቢኝ ወይ ደሞ ፍቅረኛዬ ሁኚ እያልኩሽ ነው አለኝ
23👍9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)


ደክሞኛል በሚል የተሰላቸ አስተያየት አየሁት።

ለምን እንደዚህ ጠየከኝ ወደኸኝ ወይ አፍቅረኸኝ አደለም ለምን አብሬህ እሆናለሁ አልኩት።

ልወድሽ እችላለሁ ወደፊቴ ውስጥ ሚስቴና የልጆቼና እናት ምኖርላት ሴት ልትሆኚ ትችያለሽ አለኝ።

ልሆን እችላለሁ?

አዎ ልትሆኚ ትችያለሽ ወይስ ደሞ ወድጄሻለሁ አፍቅሬሻለሁ ብዬ ውሸት እንድነግርሽ ነው የፈለገሽው ማለቴ አላቅም አሁን ላይ በጣም ነው ምታሳዝኝኝ በጣም ነው ምታሳሽኝ እና በየትኛውም አጋጣሚ አብሬሸ መሆን ነው ምፈልገው ካወኩሽ ቀን ጀምሮ ስትስቂ ለማየት እንዴት ልቤ እንደሚጓጓ ብታውቂ ትገረሚ ነበር አለኝ።

ታዲያ ሰው ሳይፋቀር እንዴት ይጋባል እንዴት አብሮ ይሆናል ነገ ህይወትህ ውስጥ አሰልቺ ሰው ብሆን እስከመጨረሻው ልትወደኝ ባትችል ሀላፊነቱን ምወስደው እራሴ ነኝ እና ደሞ እኔም ምንም አይነት ፍቅር ላንተ የለኝም እንዴት አብሬህ እሆናለሁ።

እውነት ለመናገር እንደወንድም እንደጓደኛ ዝም ብለን አብረን ልንሆን እንችላለኝ አምኜል አንድ ፍራሽ ላይ እየተኛሁ ነው አምኜህ ቤቴን ክፍት አድርጌልሀለሁ አምኜህ ልጄን ሰጥቼሀለሁ በዚህ ሰአት ማንም የለኝም ካሳዘንኩህ ካሰብክልኝ አብረኸኝ መቆየት ትችላለህ።

እንደሰው ከሰለቸህ ደሞ የመሄድ ሙሉ መብቱን ሰጥቼሀለሁ ለእስከዛሬው አመሰግናለሁ።
ከብዙ ሰው አፍ አውጥተኸኛል እናቴን በክብር ቆሜ እንድቀብራት አድርገኸኛል ቤቱ ባዶ ሲሆን የነበርከው አንተ ነህ የተኛዎ ሰው ክፉ ቀኔ ላይ እንደሚቆምልኝ መገመት እንደማልችል ነው ያሳየኸኝ አልኩት።

አይ የትም አሌድም የሚያጓጓ ወይ የምመርጠው ህይወት የለኝም እዚሁ እቆያለሁ አንቺ በቃኝ እስካልሽ ድረስ አብሬሽ አለሁ እስካልሰለቸሽ አይሰለቸኝም አለኝ።

በሰአቱ ደስ አለኝ ። የምወዳቸውን ሰዎች በማጣት ውስጥ ነው ህይወቴን ያሳለፍኩት።
ለሱ ምንም አይነት ስሜት ባይኖረኝም ባላፈቅረውም እንኳን እንደሴት ልጅ እናቷን እናዳጣች ሴት ልጇን ብቻዋን እንደምታሳድግ አንዲት ለጋ ወጣት የሆነ የምደገፈው ነገር ያስፈልገኝ ነበር በሰአቱ ደሞ ምሰሶ ሆኖ የቆመልኝ እሱ ስለሆነ ተደገፍኩት አመንኩት አቀረብኩት።

ከምንም በላይ ህላዌ እንደ አንዲት ልጅ በትናንሽ ነገሮች መሳብና መሸወድ ያለ ነው።
እናቴ ስትሞት በተራው እሱ ተትክቶ ምን ልግዛልሽ ምን አማራሾ ብሎ ስላቀበጣት ነፃነት ምታገኝበት ቦታዋ አድርጋዋለች።
እንደአባት እሽኮኮ ይዟት ሱቅ ደርሰው ሲመጡ ሳያቸው ደስ ይለኛል ስትስቅ ትንሽ መረጋጋት ይሰማኛል።

በነጋታው ከሰአት አካባቢ እህቱና ያብስራ ቤት መጡ ።

https://t.me/mane121921

4677 ደርሰናል chanalun share eyaderegachihu 4700 engiba
👍7459🥰9🙏5
እንኳን አደረሳቸው የኔ ውድ ቤተሰቦች ።
መልካም በአል ይሁንላችሁ
2019 ስኬታችሁን ምታሳኩበት የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ
መልካም በአል
77🙏34
ዛሬ ህላዌ ይለቀቃል በተለመደው ሰአት::
53🙏9👍2😡2
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)


ሳየው እንዴት ደሜ እንደፈላና ተነስቼ ለማነቅ እራሴን እንዴት ሳዘጋጅ እንደነበር ውስጤ ያቀዋል ግን ደግሞ ነገሮችን ላለማበላሸት ንዴትንና እልሄን ተቆጣጥሬ ዝም ብዬ ተቀበልኳቸው።

ወደቤት ገብተው ማውራት ጀመሩ።
ያብስራ ለደቂቃም ቢሆን ከህላዌ ላይ አይኑን መንቀል አልቻለም።
እነሱ ቁጭ ብለው ስለስራ እያወሩ እኔ ደሞ ተነስቼ ምግብ እየሰራራሁ ህላዌ ለብቻዋ እየተጫወተች ሳታስበው መሬት ላይ ድፍት ብላ ትወድቃለች።

ከመቅፅበት ዞር ስል ያብስራ ከተቀመጠበት ተነስቶ መቼ እንዳነሳትና እንዳቀፋት አላውቅም አቅፏት እያባበላት ድንጋጤው ሳይለቀው ወደውጭ ወጣ።

ህላዌ እናቴ ከሞተች ቡሀላ ናፍቆቱ ሆድ እያስባሳት መሰለኝ መቼ እንደከፋት በምን እንዳለቀሰች አናቅም አንዴ ደሞ ማልቀስ ስትጀምር አታቆምም ምክንያት ስታገኝ እንደትልቅ ሰው ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች።


ያኔ ያብስራ ይዟት ወደውጭ ስለወጣ እነሱ አርፈው ተቀመጡ እኔም እሱን ተከትዬ ወደ ውጭ ወጣሁ።

ነይ ዝም እንድትል የሆነ ነገር እንግዛላት አለኝ።
አይ አትፈልግም አልኩት።
በናትሽ ቅድስት እረፊ በቃ ነይ እንግዛላት ብሎኝ ወደውጭ ወጣን።

ህላዌ ስታለቅስ ፊቱ ላይ የሚታየው ጭንቀት የምር ያብስራ ነው የአንድ ህፃን ልጅ ለቅሶ በዚህ ልክ እረብሾት ነው ያስብል ነበር።

ሱቅ ሄደን ከተሰቀሉት ኳሶች ውስጥ ምትፈልገውን እንድትመርጥ ሲነግራት ለቅሶዋን እረሳችው የወደደችውን ኳስ አቅፋ ዝም አለቸ።

ወደቤት አብረን እየተመለስን ይቅርታ ቅድስት የዛኔ እንደዛ ማድረግ ፈልጌ አደለም አስተዳደጌ በራሱ የፈጠረብኝ ተፅኖ አለ።
አንዳንዴ እራሴን መቆጣጠር ያቅተኛል ከተወሰኑ ደቂቃዎች ቡሀላ ነወሰ ድንግጥ ብዬ ወደራሴ ምመለሰው በእውነት ግን ፈልጌው አደለም አሁንም ሀሳቤን አልቀየርኩም ምርጥ እናት መሆን እንደምትችይ አቃለሁ ምርጥ አባት ስለመሆኔ ምንም አላቅም ግን ቤተሰቦቼ እኔ ላይ የሰሩትን ስተት እንደማልደግመው ግን እርግጠኛ ነኝ።
እባክሽ ቅድስት በቃ አብረን እንሂድ በእውነት ለህላዌ ስል እንዴት ጥሩ ሰው እንደምሆንልሽ ታያለሽ  በናትሽ በቃ እዚህ ምን ቀረሽ አብረን ሆነን ልጃችንን እናሳድግ ካላመንሽኝ ደሞ ከመሄዳችን በፊት የፈለግሽበት ቦታ ሄደን ልምልልሽ እችላለሁ አለኝ።

ዝም አልኩት።

ወደቤት ገባን።

እህቱ ሱቅ ወታችሁ  ነው ? ና የኔ ፍቅር ይቺን እንጨርስና ከዛ በቃ ከፈለግን አብረን መውጣት እንችላለን አለች።

ህላዌን ተቀብያቸው ምግቤን ለመጨረስ ወደውስጥ ገባሁ።

አውርተው ሲጨርሱ ምግብ እንዲበሉ ብነግራቸውም ይቅርብን ሁላችንም በጋራ እንውጣና አብረን እራት እንብላ አሉ።
እኔ በፍፁም አልፈልግም አልኩ።

ግን በስንት ልመና አሳምነውኝ የተያያዘውን ፀጉሬን ፈትቼ አበጥሬ የልጄን ፀጉር አጥቤ አሲዤላት ከእናቴ ሞት ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያምር  ልብስና ጫማ አልብሻት አሳመርኳት።
እኔ ጥቁር ሙሉ ቀሚስ ለብሼ ከላይ ቡኒ ጃኬት ደርቤበት ለመውጣት ተዘጋጀሁ።

ያብስራ ህላዌን በጣም እንደወደዳት ተናግሮ እሱ አቅፏት ወደመኪናው ሄደ።
እኛ ከኋላ ተከተልነው።

ይጨመር ካላችሁ👍

https://t.me/mane121921
👍9334