ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ምን እያደረገ እንደሆነ ለኔም ለሱም አልገባኝም።
ይመስለኛል ውስጡ ያለው ፍርሀት የፈጠረበት ጭንቀት ነው።
እኔ የሁል ጊዜ ህልሜ ያብስራን አጊቼው ልጅ እንዳለው ነግሬው አውቆ የሚለው... የሁልጊዜ ፀሎቴ የነበረ ቢሆንም መጓጓቴና መጠበቄ ልክ አለመሆኑን በድጋሜ መጥቶ አረጋገጠልኝ።
ከዚህ ቡሀላ ልጄ አባት የላትም ከዚህ ቡሀላ መጠንከር ግዴታዬ ነው።
ያለኋት የቆምኩላት የእድሜ ዘላለሟ እናትም አባትም እኔ ነኝ ብዬ አሰብኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ያብስራ ላይ የነበረኝ ተስፋ ሞቷል።
ግን ደሞ ቀን በቀን በሄድኩ ቁጥር ለብሶ አምሮበት የሀብታም ልጅ መስሎ እንደዛ ተንደላቆ ተመችቶት እኔ የሰራሁትን ምግብ እየበላ እግሩን ሰቅሎ ይውላል።
የእነ ሜሪ መመረቂያ እየደረሰ ስለነበር ከነሱ ማገኘውን ጥቅማጥቅም እያጠራቀምኩላት ነበር።
ምን እንደማደርግላት ባላቅም ብቻ ሲሰጡኝ ሁላ እንቢ ማለት ትቼ እየተቀበልኳቸው እሮጬ ወደማጠራቀሚያዬ እየከተትኩ ነበር።
ያብስራና እኔ ወደኖርማል ኑሯችን ገባን አለቀ።
እንኳን የልጄ አባት ከዚህ በፊት የምንተዋወቅ ሰዎች አንመስልም።
ህይወታቸው ግራ የሚያጋባና በእንቆቅልሽ የተሞላ ስለሆነ ጎረቤቴን ስለህይወቱ እንዲነግረኝ መገፋፋቴን ብቀጥልም እሱ ግን ወይ ፍንክች አለ።
በስህተት የሚተነፍሰው ነገር የለም::
ቀናቶች ሄዱ እነ ሜሪ ተመርቀው ለመምጣት 1 ሳምንት
ለመጋባት ደሞ 1 ወር ከ15 ቀን ቀራቸው።
ምንም አይነት የምርቃት ድግስ ሳያደርጉ በአዲሱ አመት ደሞ ሞቅ ያለ ሰርግ ተደግሶ ቀጥታ ወደትዳር መግባት እንደሚፈልጉ ለቤተሰቦቻቸው አሳወቁ።
የሀይሌ ቤተሰቦች ምን አስቸኮለህ ገናኮ ነው እድሜህ ስራ ሳይኖርህ ገንዘብ ሳትይዝ ብለው ትንሽ ቅር ቢሰኙም እሱ ግን በአቋሙ ፀና።
የሜሪ ቤተሰቦች ግን ደስተኛ ነበሩ።
ልጃቸው ተምራ ተመርቃ ስትመለስ ደሞ ሰርግ ደግሰው ከዳሯት ሌላ ለነሱ ወግ ማእረግ የለም።
አንዳንዴ ውስጤ ቅናት ይሁን የበታችነት ስሜት ይሰማኛል።
አንዳንዴ ምግብ እየየሰራሁ የጨመርኩትን ነገር ደግሜ እጨምራለሁ።
አንዳንዴ መንገድ እየተራመድኩ የማቀው መንገድ ይጠፋኝና መሀል መንገድ ላይ እደናበራለሁ።
ከምንም በላይ ደሞ እናቴ ስለሜሪ ስታቅ ያለችኝን አረሳውም።
አየሽ በአባት እጅ ስታድጊ እንደዚህ ተምረሽ ተመርቀሽ በክብር ትዳሪያለሽ እናት አባት ይኮራብሻል ።
አቤት ታድለው ከዚህ በላይ አለም ምን አለ።
ልጄ እንደዛ ሆና አይቻት በነጋታው ብሞትም አይቆጨኝ ብላኝ የበር።
https://t.me/mane121921

❤102👍3
mane.shopping
ይሄ የቲክቶክ አካውንት አሁን 150 ተከታይ አለው 1 ክፍል በፈለጋችሁት የfollower መጠን አባዝቼ እለቅላችኋለሁ::
ለምሳሌ 1 ክፍል በ10 follower
ከዛም በታች ወይ ከዛ በላይ ሊሆን ይችላል።
ያው መደበኛ ከምለቅላችሁ ክፍል ውጭ ነው ይሄኛው
👇👇👇👇
http://mane.shopping

🙉16❤7
ህላዌ (✍️✍️ማኔ
በበኩሉ አቤል እነሱ ሊመረቁ ነው እኔ ሲሄዱ የለበስኩትን ቲሸርት መቀየር አቅቶኝ እየማቀኩ ነው።
ህይወት ግን ፍትሀዊ አደለችም ታዳላለች አደል ይለኛል።
አንድ ቀን ማታ ላይ ሁሉም ነገር ምርር ብሎኝ ሰልችቶኝ ሳለቅስ አደርኩ።
ጠዋት ስነሳ አይኔ አብጦ ነበር።
ቢሆንም ስራ ግዴታ መሄድ ስላለብኝ ተነስቼ ወደስራ ሄድኩኝ።
ቤት ውስጥ ጎረቤቴ(እዩኤል) ቁጭ ብሎ ነበር።
ሲያየኝ ደነገጠ።
የተፈጠረ ነገር ካለ ጠየቀኝ።
የለም ብዬ ዋሸሁት።
ሶፋ ላይ አስቀመጠኝና።
አንቺ ተስፋ ለመቁረጥጥ በጣም ገና ነሽ መቁረጥም አትችይም ምክንያቱም ልጅ አለሽ::
ልጅሽ ተስፋሽ ናት ህይወትሽ ናት ለመኖር ታጓጓሻለች ለሷ ታገይላት ጥሩ ህይወትን ለመስጠት ሞክሪ ልትወድቂ ልትሰበሪ ልታለቅሺ ስትይ ልጅሽን ጥንካሬሽን አስቢያትና እንዳድስ ቁሚ።
አንቺ ወደፊት በምትጦሪያት እናትሽና በምታሳድጊያት ልጅሽ መሀል ነሽ።
ሁለቱንም እጅሽን ዘርግተሽ የመቀበል ግዴታ አለብሽ ስለዚህ ሌላውን ነገር እርግፍፍፍ አድርገሽ ተይው አጉል አትጨነቂ አጉል አታስቢ ።
ሁልጊዜ እጅሽን ልይዝሽ አለሁልሽ ልልሽ እፈልጋለሁ ታሳዝኚኛለሽ ግን ደሞ የኔ ህይወት እንደምታይው ነው።
ተስፋ ማደርገው ነገር የለኝም ከራሴና ከእውነታው ለመሸሸግ አፈር ቤት ውስጥ አንጥፌ እየተኛሁ ነው እራሴን ሽሽት ከራሴ ለማምለጥ እየሞከርኩ ነው።
እንደወንድ ልጅ መጋፈጥ በሚገቡኝ ጉዳዮች ላይ እኔ እጅ ሰጥቻለሁ ግን አንቺ ሴት ነሽ በእድሜ ገና ነሽ ተስፋ አትቁረጪ በህይወትሽ ምንም ነገር ቢፈጠር ብርቅ አይሁንብሽ ማጣትንም ማግኘትንም ተለማመጃቸው።
ሰዎች ላይ እንዳትደገፊ ምክንያቱም መቼ ልታጭያቸውና ሊከዱሽ እንደሚችሉ ፈፅሞሞ አታውቂም ለሱ ደሞ ከኔ ህይወት በላይ አስተማሪ የለሞ አለኝ።
በናትህ ስላንተ ንገረኝና እስቲ ልጠንቅርበት ልማርበት አልኩት ከየት ያመጣሁት ድፍረት እንደሆነም አላቅም

❤41👍9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አልነግርሽም ምክንያቱም አይመለከትሽም።
እኔ ህይወቴን ለሰዎች አላወራም ማንም ስለማይመለከተው።
እሺ ብዬ ተነስቼ ወደስራዬ ገባሁ።
ጊዜው በድጋሜ መሮጥ ጀመረ።
እነ ሜሪ ተመርቀው መጡ።
ጓደኛዬ ተመርቃ ስትመጣ በክብር መቀበል ቢኖርብኝም እኔ ግን እሱን አላደረኩም።
ምክንያቱም እዛ ቦታ ላይ መገኘት አልችልም።
ወዲያው የመስክ ፎቶ ለመነሳት ዝግጅታቸውን ቀጠሉ።
እንደጓደኛ አብሪያት መሆን የነበረብኝ እኔ ነበርኩ ግን ጓደኛዬ ምን አይነት ቬሎ ለብሳ እንደምትሞሸር እንኳን የማየት እድሉን አላገኘሁም።
በጓደኛዬ ደስታ ልቧ የተሰበረው ብቸኛ ሰው እናቴ ናት።
እሷ ስትመረቅ አይ ልጄ አንቺምኮ ጎበዝ ነበርሽ እንደው የዛኔ ጭክን ብለሽ ልጅሽን ለኔ ሰተሽ ተምረሽ ቢሆን ይሄን ምርቅ ትይልኝ ነበር።
ይሄኔ አንቺም እንደጓደኛሽ ትሞሸሪ ነበር።
ወገቤን አስር አድርጌ ከሰፈር ሰውጋ እየተጠራራሁ ለሰርግሽ እየተዘጋጀሁ ነበር።
ልጄ ስታገባ የሰርጓ ቀን በአበሻ ቀሚስ ጎርደዶ ጎርደድ እያልኩ አስቢው እስቲ ብላ ከትትት ብላ ትስቅና እንባዋ ይፈሳል። ግን ሴት ያሳደገው ከዚህ አይዘልም እያሉኝ ስለኖርኩ ምፈራው ነገር ነው ሰተት ብሎ ቤቴ የገባው ትላለች።
ታሳዝነኛለች።
አቤል ከነ ሀይሌጋ ለሰርጋቸው ዝግጅት ሲያደርጉ አብሯቸው እየዞረ ነበር።
እሱሞ ቢሆን ወይ እንደሀይሌ ሻል ካለ ሰው አልተወለድኩ ወይ አፍቅራኝ አፍቅሪያት ምታጠነክረኝ ፍቅረኛ አልያዝኩ ወይ ሰርቼ አልተለወጥኩ እያለ ያጉረመርማል።
ዙሪያችን ያለው ሰው እራሱ በልጠነው ስንገኝ ደስ አይልም የራሱን ኑሮ እያሰበ ይቆዝማል እንጂ።
በስተመጨረሻም የሜሪ ሰርግ ደረሰ
ያለውን ነገር እንዳይከፋኝ እንዳይደብረኝ እዛ እንዳለሁ እንዲሰማኝ ብላ ሁሉንም ከስር ከስር ትነግረኝ ነበር።
የሰርጉ ቀን ደረሰ።
እኔ ስራ አልገባሁም ነበር።
እናቴ ከቤት ዝንጥ ብላ ለባብሳ መጣች።
ሳያት ደነገጥኩ አምሮባት ነበር።
በዚህ ልክ አምሮባት አይቻት አላቅም።
ቢያንስ በሷ ሰርግ እንኳን ልዘንጥና እልሄን ልወጣ እንጂ እኔ እንደሆንኩ ቆሜ ልጄን ለመዳር አልታደልኩም አለችኝ።
በዛሬው ቀን እንኳን ነገር ባትፈልጊኝ ምናለበት ብዬ ብስጭት አልኩባት።
በይ በይ ሙሽሪት ከቤቷ ሳትወጣ ልድረስ ብላኝ ፍንድቅድቅ እያለች ከቤት ስትወጣ ህላዌ አትሄጂም ብላ ቤቱን ቀወጠቸው።
እላይዋ ላይ ተለጥፋ አለቅም አለቻት።
እኔም እሷም በግድ አስጥለናት እናቴ ወሰርጉ ሄደች።
እኔና ህላዌ በራችን ዘግተን ቁጭ አልን።
ህላዌ ለቅሶዋን አላቆም አለች ብለምናት ባባብላት አሻፈረኝ አለች።
ውስጤ አፍኜ የያዝኩት እልህና ንዴት ገንፍሎ ወጣ።
መታኋት።
ለመጀመሪያ ጊዜ ልጄ ላይ እጄን አነሳሁ።

❤82💔15😱6🥰4🤯1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ቅጥቅጥ አደረኳት።
አልቅሳ ሲደክማት እንቅልፍ ወሰዳት።
እሷ ስትተኛ እኔ ተተካሁ።
ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ።
አብሮ አደጌ የልብ ጓደኛዬ ስትሞሸር መገኘት እንዳልችል ያደረገኝ ያብስራ ነው።
እናቴ አጋጣሚ እየጠበቀች ምትወቅሰኝ በሱ ምክንያት ብዬ አሰብኩ ውስጤ የሚሰማኝ የጥላቻ ነደደ ይሄ ነው የሚባል አደለም።
አቤል ሰርጉ ላይ ሄዷል።
ከሀይሌ ልብስና ጫማ ተበድሮ በሙሽራው ልብስና ጫማ ሰርጉን ለመታደም ሄዶ ነበር።
ምሽቱን ማልቀስ ማቆም አልቻልኩም።
እራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አቃተኝ እቴቴ መጥታ ከአንዴም ሁለቴ በር ብታንኳኳም እንደተኛ ሰው ዝም አልኳት።
ማታ እየመሸ ሲሄድ ህላዌ ከእንቅልፏ ነቅታ እማማጋ እንሂድ አለችኝ።
እረፊ ብዬ ተቆጣኋት።
አጠገቧ ተቀምጬ እላዬ ላይ ወጥታ እያቀፈችኝ እንባዬን ጥርግ እያደረገች ሳም ሳም ታደርገኝ ጀመር።
መልሼ አቅፌ ሳምኳት።
መልሳ አሳዘነችኝ እሷ ምን በወጣት እሷ ምን ባጠፋች ልገላምጣት ልቆጣት።
ማታ አንድ ሰአት አካባቢ ላይ ለእናቴ ደወልኩ አታነሳም።
ለሜሪ እንዳልደውል ጨነቀኝ።
እቴቴጋ ሄድኩ አቤል ቆየኮ አልኳት።
አዎ ቆየ ግን ሰርግ አደለ እንዴት ቶሎ ይመለሳል አለችኝ።
ትንሽ እሷጋ ቁጭ አልኩና አባትየው ሳይመጣ ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩ።
ቤት መግባት ስላልፈለኩ ህላዌን አቅፌ በሻርፔ ጥቅልል እንዳደረኳት ቁጭ ብዬ ሰማይ ሰማይ እያየን ሁለታችንም መሳሳቅ ጀመርን።
እዛው ቁጭ ብለን ጎረቤቴ መጣ።
ሲያየን ፈገግ ብሎ መቀላቀል ይቻላል አለ?
ምኑ ላይ ነው ምትቀላቀለው አልኩት።
አብሪያችሁ ልቀመጥ አለኝ።
ዝም ብዬ አየሁት።
ቁጭ አለ።
ሞቅ ብሎት ነበር።
እናትና ልጅ በቃ ፍቅራችሁ እያስቀናኝኮ ነው አባት አትፈልጉም ብሎ እራሱ ባወራው ቀልድ እራሱ ከት ብሎ ሳቀቀ ግራ ገብቶኝ አየሁት።
በዛ መሀል ነው የእናቴ ስልክ ወደኔ ስልክ ሲጠራ ያየሁት።
ተጣድፌ አነሳሁት የአቤል ድምፅ ከስልኩ ውስጥ ተሰማኝ።
እየተርበተበተ ነበር ሄሎ ቅድስት እናትሽ እናትሽ ሀኪም ቤት ገብታለች አለኝ ከአጠገቡ የለቅሶ ድምፅና ጫጫታ እየተሰማኝ ነበር
ዋናው እስኪለቀቅ ቲክቶክ የሌላችሁ ሰዎች አንብቡት

👍35❤20😱9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
በድንጋጤ እንዴት እንደተነሳሁም አላውቅም።
ህላዌ ተንሸራታ ከእጄ ሾልካ ከመውደቋ በፊት እዩኤል ይዟት ነበር።
እንዳትደነግጥ ጥብቅ አድርጎ ቢያቅፋትም ስለፈራችው እሪ ብላ አለቀሰች።
እኔ እጄ እየተንቀጠቀጠ አቤልን ምን ምን ሆና ነው ምን ሆና ነው ብዬ ከመጠየቅ ውጭ ሌላ ምንም መናገር አልቻልኩም አቤልም ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው።
ወዴት እንደምሄድ አላወኩም በሩ ሁላ ጠፋብኝ።
ብቻ በቆምኩበት እንባዬ እየፈሰሰ ሳላስበው እቴቴ እቴቴ እያልኩ እየተጣራሁ ነበር።
እቴቴ ደንግጣ ወጣችና አቤል ምን ሆነ ልጄ ምን ሆነ ድሮም ሲጨንቀኝ አውቄው ነበር አለችኝ።
እናቴ ሀኪም ቤት ገባች አቤል ደውሎ ነገረኝ አልኳት።
ደነገጠች።
እሷ ህላዌን ያዘቻት አደራ ልጄን እቴቴ ብያት እሷጋ ትቻት ዝም ብዬ በደመነፍስ ወጣሁ።
እናቴ የት እንዳለች አላቅም።
የtaxi አልያዝኩሞ የለበስኩትን ልብስ አላስተዋልኩትም።
ብቻ ዝም ብዬ እየሄድኩ ነበር።
በዛ መሀል ጎረቤቴ እየተከተለኝ ወዴት ነው ምቴጂው የት ነው ያለችው ይለኛል መልሼ ስልክ እደውላለሁ አያነሱም ።
ከስንት ሙከራ ቡሀላ አቤል ስልኩን አንስቶ እናንተ ሰፈር ያለው ኤልቤተል ትልቁ ክሊኒክ ነው ያለነው አለኝ።
ጎረቤቴና እኔ ተያይዘን በላዳ ወደዛ ሄድን።
ላዳ ውስጥ ተቀምጠን ከኔ በላይ ሲጨነቅ እየተሳቀቀ አይን አይኔን ሲያየኝ ነበር።
በድንጋጤ ስካሩ ሁላ ሳይጠፋለት አይቀርምተ
ሰፈር ደረስኩ።
ቅንጣት ታክል የሰው ወሬ አላስጨነቀኝም ትዝም አላሉኝም።
ጎረቤቴ ለላዳው ሹፌር ብሩን እስኪከፍልም አልጠበኩትም እኔ እየሮጥኩ ነበር።
እሱም ተከተለኝ።
ሆስፒታል ደረስን የተወሰኑ የሰፈሩ ሰዎች በሀበሻ ቀሚስ እንዳሸበረቁ ነጠላቸውን አፋቸው ላይ ሸፍነው ቆመዋል።
እኔ ስደርስ ዶክተሩ ከአቤልጋ አውርቶ አቤል መሬት ላይ ብርክክ ብሎ እባክህ ዶክተር የሆነ ነገር አድርግ በናትህ መሞት የለባትም ሲለው ጆሮዬ ውስጥ ጥልቅ አለ እናቴ ሞታ ነበር

💔80❤39😱7
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
በዛ ሰአት ስለሱ ማሰብ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላቅም።
በለቅሶ ውስጥ ልቤ ተሰብሮ ከስብርባሪው የተረፈችው ትንሿ አካሌ ደሞ ልጄጋ ነበረች።
እናቴ በስተመጨረሻ ለመቀበር ተያይዘን ወደቤተክርስቲያን አስክሬን አጅበን ሄድን።
እኔ ከግራና ከቀኝ ሜሪና አቤል ይዘውኝ ተረጋጊ ማለት አቅቷቸው አብረውኝ እያለቀሱ ነበር።
ቤተክርስቲያን እስክንደርስ ድረስ ጎረቤቴ ህላዌን ይዟት ከኛ እራቅ ብለው ሲሄዱ አልፎ አልፎ በአይኔ እያየኋቸው ነበር ግን በሰመመን ውስጥ ስለነበር በስርአት ላያቸው አልቻልኩም።
ደረስን ቆሜ እያለቀስኩ እናቴን አፈር ቆፍረው ሰቀብሯት አየሁ።
የኔም ተስፋ ህልሜ ህይወቴ ሙሉ ማንነቴ አብሯት የተቀበረ መሰለኝ።
እስክሞት ድረስ እየጮኩና እያለቀስኩ እባካችሁ አፈር አታርጉባት እባካችሁ አትቅበሯት ድንገት ብትነቃስ እግዜር ቢራራልኝስ እያልኩ እየለመንኳቸው ነበር ምክንያቱም ብቸኛ በሆንኩበት ምድር ላይ በላሽ ጠጣሽ ተነሳሽ ተኛሽ እረፍት አድርጊ ልብሽ አጊጪ ላንቺ እኔ አለሁልሽ ለልጅሽም እኔ አለሁላት ምትለኝን ሰው ፈጣሪም ጨክኖ አይወስዳትም በሚል ተስፋ ውስጥ ነበርኩ።
ከቀብር ቡሀላ ወደቤት ተመለስን።
እናቴ ሞታ አፈር አልበሰዋት መተው ግድ ሳይሰጣቸው ሆ ተመለሰች እንዴ እስክትሞት ነበር እንዴ የጠፋችው እያሉ በኔ የሚያሽሟጥጡት አበዛዛቸው ይሄ ነው ሚባል አደለም።
ደግነቱ ሜሪ ከኔጋ ነበረች።
ትናት የተሞሸረችዋ ጓደኛዬ ዛሬ ደሞ የሀዘን ልብሷን ለብሳ ሙሽርነቱ ደስታው ፌሽታው ቀርቶ ከኔውጋ ሆነ።
ትናት ግቢ ሄዳ ተረጋግታ እንዳትማር እንደዛ አስሬ እየተመላለሰች ችግሮቼን ስትፈታ ለራሷ ሳይኖራት ብር እየላከች እያለው እንደሌለው ሆና ተማረች።
ዛሬ ደሞ ደስታዬ ነው ብላ ሰርግ ደግሳ ብትሞሸር እናቴን አይኔን አጥቼ ደስታዋ ወደሀዘን ተቀየረ።
ሜሪ ከሰው ግርግር መሀል ወደመኝታ ቤት ይዛኝ ገብታ ትንሽ ምግብ ጉረሺ ካሎነ አንቺም ለልጅሽ መኖር አትችይም ስትለኝ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ያኔ ነበር ህላዌ ከጎረቤቴጋ መጥፋቷን ያስተዋልኩት

💔68❤28😱16👍6
Forwarded from baby ye tsega lej
ለጥቂት ደቂቃዎች ካሉበት ዓለም መዉጣት ይፈልጋሉ? 📖✨
ፍቅር፣ ምስጢር፣ ናፍቆት እና ድንቅ ምናብ ሁሉም በዚህ ይገኛሉ
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇
t.me/Fiction_123
ፍቅር፣ ምስጢር፣ ናፍቆት እና ድንቅ ምናብ ሁሉም በዚህ ይገኛሉ
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇
t.me/Fiction_123
👍5❤1
Forwarded from Sirius_black
ምንድነው ፍላጎትህ/ሽ ? ለነገሩ ምንም ቢሆን Don't worry ....
ግጥም ......
ድርሰት ........
አዝናኝ ወግ......
አጫጭር የፍቅር ታሪክ......
ወይስ ገራሚ ጥቅስ....
የፈለጋችሁበትን አማርጣችሁ ምታገኙበት ድንቅ Channel ጀባ ልበላችሁ.....
በደራሲ @sirius_black1212 የተፃፉ ውብ የ ብዕር አርማዎች እለት በእለት እሚታተምበት ምርጥ Channel
ተቀላቀሉ አትፀፀቱም!
Join us
https://t.me/yebier_arbegna

Telegram
📜 የብዕር አርበኛ
"ብዕር ከሰይፍ ይበልጣል!" 🖋️
❤2👍1
Forwarded from D.NØXE
የተሳሳተው መስመር
የአዲስ አበባ ክረምት በከባድ ዝናብ እና በብርድ ታጅቦ ከተማዋን አውኳታል። ኤልያስ በአሮጌው ካዛንቺስ ሰፈር በሚገኘው አነስተኛ የቤት ኪራዩ ውስጥ ብቻውን ተቀምጧል። በጠረጴዛው ላይ የተረሳው የሻይ ብርጭቆ ቀዝቅዟል። እሱ በአንድ ትልቅ የህትመት ድርጅት ውስጥ ዋና አራሚ (Editor) ሆኖ ቢሰራም፣ የራሱን ህይወት ግን ማረም ያቃተው ይመስላል። ከአንድ ዓመት በፊት ከደረሰበት ከባድ የፍቅር ስብራት በኋላ፣ በሰዎች ላይ ያለው እምነት ተሸርሽሮ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት ዓለም ውስጥ ተዘግቶ ነበር። መጻሕፍት ማንበብ እና ማታ ማታ የዝናቡን ድምፅ ማዳመጥ ብቸኛ የህይወት መደገፊያዎቹ ነበሩ።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ join ይበሉ pin ተደርጓል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/ke_kaloche1

🔥4❤3🥰2🤗2
Forwarded from Ķůń fé¥éķůń 🕌🕌🕋
የተለያዩ ምርጥ ምርጥ ጫማዎችን የምታገኙበት ምርጥ ቻናል
የቴሌ ግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉
#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand
#https://@Reisbrand
💬በ inbox @Reisbrandi አዋሩኝ ☎️፣ 0995235877

❤10
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ከዛ ምን እንደተፈጠረ ለመስማት ወደሱ ቀረብ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ።
ከዛስ አልኩት..
ከዛማ ያው እነሜሪም እንዳያችሁት ሙሽሮቹጋ እየሄደች መሀላቸው እየገባች ፎቶ ስትነሳ ።
ዝም ብላ እልልልል ስትል ነበር።
እዛ የነበሩት ሁሉም አብዳለች እንዴ በሚል አስተያየት እያዩአት ነበር።
እና ሊያረጋጋት የሞከረ ሰው ወደሷ ሲጠጋም እላያቸው ላይ መጠጥ እየደፋች አንድ ሰው እንዳይነካኝ እያለች ስታብድ ነበር።
ከዛ ቡሀላ እኔም ከሙሽራውጋ ወጥቼ ሄድኩኝ።
ማታ ላይ ከሙሽራው ቤት ወጥቼ እሷን ይዤ ወደቤት ለመውሰድ ስመጣ የለችም።
ከስንት ፍለጋ ቡሀላ አገኘኋት ሳገኛት ግን ከነሜሪ ቤት ወደታች ያለው አጥር ስር ወድቃ ነበር ስትወደቅ ደሞ በሀይል ተጎድታለች ጭንቅላቷምጋ ደም ነበር አለኝ።
ይባስ አለቀስኩ።
እናቴ መሞቷ ሳያንሳት በመጨረሻም ቀን እንደዛ ተዋርዳ መሞቷ አመመኝ።
ውስጧ ምን ያህል እንደቆሰለ ምን ያህል እንደታመመ ቀድሞ ቢገባኝም ያን ቀን ደሞ የባሰ ነበር።
ሰባቱ እስኪወጣ ድረስ የተወሰነ ሰው ነበር አልፎ አልፎም ቢሆን
ከዛ ቡሀላ ሁሉም ወደየራሱ ስራ ገባ።
እቴቴ ወደሰው ቤት ስራዋ ተመለሰች።
ሜሪም ብቶን አሁን ሚጠብቃት ህይወት ትዳር አለ።
እንደድሮው ልጅነት የለም።
በስተመጨረሻ እኔ ጎረቤቴና ህላዌ ብቻ መሬት ላይ የወረደው ፍራሽ ላይ እራሳችንን አገኘነው።
አንተ አቴድም የሚጠብቅህ ስራ የለህም ሂድ በቃ አልኩት።
አይ ችግር የለም ከጎንሽ መሆን ፈልጌ ነው አለኝ።
በለቅሶው መሀል ከህላዌጋ ሀይለኛ ወዳጅነት መስርተው ነበር።
እሷም ሙሉ ጊዜዋንና ትኩረቷን እየሰጠችው ነበር።
ህላዌ መሀላችን ቁጭ እንዳለች እንቅልፍ ወሰዳት።
እኔም ደገፍ አልኩኝ።
በዛ መሀል ጎረቤቴ ታሳዝኛለሽ ማለቴ በዚህ እድሜሽ ያሳለፍሽው ሁሉ አይገባሽም አይንሽን ሳየው አይንሽ ውስጥ ያለው ስብራትና ህመም ያስፈራኛል።
ካወኩሽ ጀምሮ እኔ እስከዛሬ ለኖርኩት ህይወት መፀፀት ጀምሪያለሁ።
ለካ ምንም አሎንኩም ለካ ምንም አልተነካሁም ለካ እንደዚህም ሚኖር አለ እንድል ነው ያደረገሽኝ እና የምር ነው ማመሰግነው አለኝ።
ዝም አልኩት።
በመሀል ስልኬ ጠራ።
ያኔ ነው ስልኬ እሱጋ እንደነበር ያወኩት።
የሚጠራውን ስልክ ብድግ አደረገና ውይ መጡ ቆይ ልቀበላቸው ብሎ ወጣ።
እህቱና ያብስራ ለቅሶ ሊደርሱ መምጣታቸው ነበር

❤76🥰11
ህለዌ (✍️✍️ማኔ)
ሳያቸው ምንም አልተሰማኝም ደንዝዣለሁ ያብስራ ኮፍያ አድርጎ ለመሸፋፈን ሞክሮ ነበር የመጣው።
ወደውስጥ ገቡና ቁጭ አሉ።
እህቱ በስስት እያየችኝ እኔ ሰው ማፅናናት አልችልበትም ግን በቃ አይዞሽ የኔ እናት አለችኝ።
እነሱ ገብተው ብዙም ሳይቆዩ ህላዌ ብንን ብላ ብድግ አለችና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።
ምን እንደሆነች አልገባኝም ጎረቤቴ እቅፍ አድርጎ ሊያባብላት ሞከረ እሷ አሻፈረኝ አለች።
ተነስቼ ተቀበልኩት ግን እሷን የመሸከም አቅም ስላልነበረኝ ወደመኝታ ቤት ይዣት ገባሁና ለማስተኛት ሞከርኩ ትንሽ ትንሽ ተረጋጋችና በዛው ወደማሸለቡ ገባች።
ግን በሰመመን ውስጥ ስቀ ስቅ እያለች ነበር።
ከእቅፌ ለማስተኛት እየሞከርኩ በሩ ተከፈተና ያብስራ ወደውስጥ ገባ።
ይቅርታ ተረጋጋችልሽ የማግዝሽ ነገር ካለ ለመጠየቅ ነበር አለኝ።
ምንም የለም አልኩት።
የምር ልጅሽ ናት እንዴ እኔኮ የእዩ እህት ስትነግረኝ አላመንኩም አለኝ።
አንገቴን ነቀነኩለት።
ስንት አመቷ ነው አለኝ?
አይመለከትህም አልኩት።
ህላዌ ስትተኛልኝ ተነስቼ ወደሳሎን ሄድኩ ተከተለኝ።
ጎረቤቴና እህቱ ሳሎን ስላልነበሩ ወደውጭ ስመለከት ከግቢው ውጭ የነበረው መኪና ውስጥ ገብተው በኮምፒውተር ስራ እየሰሩ ይሁን ምን አላቅም ግን እያስተካከሉ አየኋቸው የውጭውን በሩን ክፍት አድርገውት ነበር የወጡት።
ሳሎን ቁጭ ከማለቴ ህላዌ በድጋሜ መጮህ ጀመረች።
ብድግ ብዬ ወደሷጋ ገባሁ ከአልጋው ላይ ላነሳት ስሞክር አቅም አንሶኝ መልሼ ወደኩኝ።
ያኔ ያብስራ ብድግ አድርጎ አቀፋትና ጀርባዋን እያሻሸ እሷን ለማስተኛትና ለማረጋጋት እየሞከረ ነበር።
እንደዛ ሆነው ሳያቸው እንባዬ መጣ አባቷ አቅፏት መቆሙን እሷ አታቅም እሱም ልጁን እንዳቀፈ አያቅም ለኔ ግን ያ ነገር ህልሜ ምኞቴ ነበር።
ህላዌ አሁንም ቀስ በቀስ መረጋጋትና ዝም ማለት ጀመረች።
ትከሻው ላይ እጇን ዝርግት አድርጋ ተኝታ ነበር።
እሷን እንዳቀፈ በጥርጣሬ አይን እያየኝ ምታሳሳ ልጅ ነው ያለችሽ በህይወቴ ልጅ ሳቅፍ የመጀመሪያዬ ነው እና ደስ የሚል ስሜት አለው እንዴት ወለድሻት ታድለሽ አለኝ።
ተሰቃይቼ ነው የወለድኳት የሰው ፊት ገርፎኝ ትምህርቴን ትቼ እናቴን ትቼ ነው የወለድኳት እሷን አርግዤ የእናቴን ቤት ትቼ ወጣሁ ይኸው እናቴ ስትሞት ይሄንን ሰፈርና ቤት እረገጥኩት ።
እሷን ለማግኘት እራሴን አጥቼ ነበር አሁን ደሞ እናቴን አጣሁ አልኩት በእልህ ተሞልቼ።
መቼ ነው ይሄ ሁላ የተፈጠረው ልጅሽ ስንት አመት ሆናት ብሎ ድጋሜ ጠየቀኝ በመርማሪ አይን እያየኝ ነበር።
አይመለከትህም እሱ አንድ አመት የሆናት ባለፈው እንደምታያት ትንሽ ናት አልኩት።
ፊቱን አዙሮ ወደሳሎን ሄደና እንዳቀፋት ሶፋ ላይ በጀርባው ደገፍ ብሎ ቁጭ አለ።
በዛን ሰአት ውስጡ ምን እየተሰማው እንደሆነ አላቅም።
ደስ ይበለው ይክፋው አላቅም።
ምን እንደሚያስብም በፍፁም አላቅም።
ሁለቱ በዛ መልክ ሲሆኑ እኔ ደሞ መሬት ላይ ወዳለው ፍራሽ ሄጄ እግሬን ዘርግቼ ቁጭ አልኩ።
እየሰረኩኝ ሳያቸው ነበረ
አሁንም ቢሆን ልቤ ህላዌ ከአባቷጋ ብታድግ ቤተሰብ ቢኖራት የኔን ህይወት ባትደግመው አባቴ ማለት እየፈለገች አባቴ ሳትል ባትቀርብኝ የሆነ ተአምር ተፈጥሮ አባት በሆነላት ብዬ እየተመኘሁ ነበር።
ፊቴ ተኮሳትሮ ልቤ ግን ሌላ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ እዩኤልና እህቱ ወደውሰጥ ገቡ ያብስራን ሲያዩት ሁለቱም በንፁህ ልባቸው ፈገግ አሉ።
ልጅ ያምርብሀል ለምን አባት አትሆንም ቶሎ ውለዱ እንጂ ብሎ ጎረቤቴ በትንሹ ፈገግ አለ።
ሰአቱ ሲሄድ እነሱም ተያይዘው ሄዱ።
ቤት ውስጥ እኔና ህላዌ ብቻችንን ቀረን።
በሩን ዘጋግተን ባዶ ቤት ውስጥ ቁጭ እንዳልን በሩ ተንኳኳ።
ተነስቼ ከፈትኩ ያብስራ ነው ፍቃዴን ሳይጠይቅ በሩን ዝግት አድርጎ ወደውስጥ ገባ ተከተልኩት....
ቅድስት እውነቱን ንገሪኝ አውቄ ነው እነዛን ሁለት ከረፈፍ ከቤት ያስወጣኋቸው ንገሪኝ ይቺ ልጅ የኔ ልጅ ናት አደል?አለኝ
ዝም ብዬ አየሁት ።
ጥሩ ዝምታሽ እራሱ መልስ ነው በይ አሁን ሶስታችንም ተያይዘን እንጠፋለን ማንም ወደማያቀን ማንም ወደማያገኘን ቦታ እሺ አለኝ።
መቼም አላደርገውም እንዳንተ አይነት ሴጣን ተከትዬ የትም አሌድም አልኩት።
ጥፊ ይሁን ቦክስ በትክክል የማላስታውሰው ምት ፊቴ ላይ አሳረፈብኝ.....

❤95😨56🤯1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ዝም አልኩ።
አይኔን የሞላውን እንባ ብቻ አፈሰስኩት።
ቅድስት ያምሻል እንዴ በእርግጥ አሁን ላልወድሽ ላላፈቅርሽ እችላለሁ ግን ፍቅር በጊዜ ሂደት ይመጣል።
ቀስ ብለን መዋደድ እንችላለን።
ልጃችን አለች በመሀል እሷ ታስማማናለች።
ለሷ ስንል አብረን መሆን እንችላለን።
አብረን ወደባህርዳር እኔዳለን።
እኔ እዛ ትልቅ ኮስሞቲክስ ቤት ከፍቻለሁ ከተማ ውስጥ አደለም ግን ከከተማው ትንሽ እራቅ ብሎ ቤት አለኝ።
አሪፍ ገንዘብም ሰርቻለሁ እዛ ተጨማሪ ስራ መስራት እንችላለን አለኝ።
የሚያወራው ግራ ገባኝ።
እኔ ያብስራን ሳቀው ሰው ቼክ የማያደርገው መሞትና መኖሩ ማንም ግድ የማይሰጠው ሰው ነበር ዛሬ ደርሶ ቤት አለኝ ሱቅ አለኝ ሲል የተለያየንበት ጊዜ ይሄን ያህል እሩቅ ሆኖ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ።
ቢሆንም በአቋሜ ፀናሁ አሌድም የትም አሌድም አረሳሁልህም ያን ሁላ ለፍልፈህ አብረኸኝ ተኝተህ ለስሜቴ ለክብሬ ሳትጨነቅ በነጋታው ትተኸኝ መጥፋትህን አረሳሁትም ባንተ ምክንያት ያለቀስኩትን ደም እንባ አረሳሁልህም ባንተ ምክንያት እርቦኝ ቁራሽ እንጀራ የናፈቀኝን ቀን አረሳሁትም።
አንተ ልጅነቴን ህይወቴን ህልሜን ሳቄን ነው የቀማኸኝ።
ለመጨረሻ ጊዜ ከልቤ ፈገግ ያልኩት የሳኩት ያኔ የተለያየንበት ቀን ላይ ነው ገባህ።
ብትገለኝ እንኳን ተመልሼ ካንተጋ አልሄድም ብሞት ይሻለኛል አልኩት።
ያኔ ምን እንደተፈጠረም አላቅም እንደዛ ከሆነ ለምን ወለድሻት።
መውለድ ውለጅ ለምን ከኔ እእ ።
ያሳለፍኩትን ህይወት ነግሬሻለሁ።
የእናትና ያባት ፊት እያየሁ ነው ያደኩት።
ለአንድ ቀን በሳቁልኝ ለአንድ ቀን ባቀፉኝ ለአንድ ቀን ከእናትና አባቴ መሀል ቁጭ ባልኩኝ እያልኩ ስመኝ ነው የኖርኩት።
በኔ እድሜ ያሉት የቅንጦት ጫማና ልብስ ሲመኙ እኔ ግን እናትና አባቴ በስሜ እንኳን በክብር ያብስራ ብለው በጠሩኝ ነበር ምኞቴ ገባሽ።
ትምህርቴን አቋርጬ ሁሉንም ነገር ትቼ ጠፍቼ ሄጄ ይሄን ህይወት ለመገንባት እዚህ ህይወት ውስጥ ለመግባት ስንት ሌሊቶቹን ያለ እንቅልፍ አሳልፊያለሁ።
ስለዚህ አሁንም ይቺ ልጅ እኔ ያሳለፍኩትን የኖርኩትን እንድትደግመው አልፈልግም ።
የፈለገ ጨካኝ አጭበርባሪ ውሸታም ብሆን እንኳን በዚህ ጉዳይ ሁለተኛ ጊዜ እንኳን አላስብም ።
ምን እንዳሳለፍኩ አቀዋለሁ።
የእናትና አባትን ፊት ፊት እያዩ በሰቀቀን መኖር ደስ አይልም ገባሽ ወደሽ አደለም በግድሽም ቢሆን ትሄጃታለሽ አለኝ።
የማወራውን አላውቅም ንዴት ጭንቅላቴን አውሮኝ ነበር።
እናትና አባትህ የማይወዱህ እንደዚህ አይነት አስቀያሚ ሰው እንደሆንክ ቀድሞ ታውቋቸው ነው።
ልጄ እንዳንተ አይነት ሌባ አጭበርባሪ አባት የላትም።
እንደውም ለእዩኤል ሁሉንም ነገር እነግረዋለሁ አሁን ለመታኸኝ ምት ዋጋ ካላስከፈልኩህ ታያለህ አልኩት።
ከቁጥጥር ውጭ ሆነ ቦክስ ጥፊ እርግጫ ምንም አልቀረልኝም ደም በደም እስክሆን ጠፈጠፈኝ ሀዘን ላይ ናት ብሎ ትንሽ እንኳን ርህራሄ አላሳየኝም..........

😱78❤31💔18😨6😭4👍1