ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ወደሱጋ ወጣሁና ይቅርታ ምግቡኮ አልነካም ተበላሽቷል ምን ሆኖባችሁ ነው ምን አጊታችሁበት ነው አልኩት።
ምንም አላገኘንበትም ምን እንደሰራሽ እራሱ ያየው የለም እሱን ድፊና አዲስ ሰርተሽ ሂጂ አለኝ።
ተናደድኩ።
እኔ ምግብ አልደፋም ሰው ይሄንን አጥቶ አደል እንዴ ሚንከራተተው ሲጀመር ካልበላችሁት ለምን ስሪ አላችሁኝ አልኩት።
ዝም አለኝ።
ንቀቱ እስከምን ድረስ እንደሆነም አላቅም ችግሩ ከኔ ይሁን ወይ ተፈጥሮው አላቅም።
ህይወቱ ምን እንደሆነም ለኔ ግልፅ አደለም ሚኖረው እንዴት እንደሆነም አይገባኝም።
ድራማው ይሰለቻል።
እኔ እዛ ቤት ውስጥ ምንም አፌን የመክፈት ስልጣን እንደሌለኝ ስለማውቅ ሶፋ ላይ ያስቀመጥኩትን ስልኬን ብድግ አድርጌ ልወጣ ስል.
በዚህ ድህነትና ሀላፊነት ላይ ይሄ ጥጋብ ተጨምሮበት ህይወትሽን እንዴት ልትገፊው ባክሽ አለኝ።
ዝም ብዬው ቤቱን ትቼ ወጣሁ።
መንገድ ለመንገድ እንደእብድ ብቻዬን እየለፈለፍኩ ቤት ደረስኩ።
መጀመሪያ አቤልጋ ገባሁና እኔ ምልህ አብሮ የረገመን ሰው አለ እንዴ ሰርተን ብር ማግኘት ወደተሻለ ነገር መጠጋት አልቻልንምኮ አልኩት።
ዝም ብሎ አየኝና ይኖር ይሆን እንዴ አለኝ።
ንግግሩ ያስታውቃል ሰልችቶታል አስጠልቶታል ድክምም ብሎታል።
ይልቅ ምግብ ካለ ስጭኝ ማታ አሞኝ ሳልበላ አድሬ አሁን እማ እስክትመጣ እራበኝ አለ።
ውስጤ ስፍስፍ አለ።
ወደቤት ገብቼ እናቴ ለኔ ያዘጋጀችውን ምግብ በሰሀን አስደርጌ ይዤለት ሄድኩና እያጎረስኩት አብረን በላን።
ደስ እንዲለው እነሱጋ ቡና አቀራርበን እቴቴም እስክትመጣ ጠብቀናትና ሰብሰብ ብለን ቡና ጠጣን።
በሰአቱ ፈገግ እንድንል ምታደርገን ህላዌ ነበረች ንግግሮቿ ተግባሮቿ እየተኮላተፈች ምታወጣው ቃሎቶች የሰውን መንፈስ የሚያድሱ ናቸው።
ሁላችንም አይናችን እሷ ላይ ነው።
ፈልገንም ይሁን ሳንፈልግ ፈገግ ታሰኘናለች እንኳንም ወለድኳት እላለሁ ያን ጊዜ
አሁንስ ? ይጨመር ወይ?

👍56❤28
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ማታ መሸ።
እናቴም እኔጋ አላደረችም ነበር።
ህላዌም ተኝታ ስለነበር በሀሳብ ምስጥ ብዬ ጣራ ጣራን እያየሁ በሬ ተንኳኳ።
ማነው አልኩኝ።
እኔ ነኝ አንዴ ላወራሽ ነው አለኝ።
ጎረቤቴ ነበር።
በሩን ከፈትኩለት ይቅርታ ልግባ አለኝ
አፉ ጋን ጋን ይሸታል።
አይ አይቻልም አልኩት።
ሳቅ አለ የንቀት እያየኝ።
ጠዋት ልክ አልሰራሁም ይቅርታ ለተናገርኩሽ ነገር እና ያው ስራሽን ቀጥይ ሰሞኑን እህቴ ከፍቅረኛዋጋ ከከተማ ወጥታ ስለነበር ነው ምግቡ ያልተበላው እንጂ ካሁን ቡሀላ እነሱም ስለተመለሱ በስርአት እንበላዋለን አለኝ።
በተራዬ ዝም አልኩት።
በውስጤ ያቺ ያየኋት እህቱ ናት ብዬ ከራሴጋ እያወራሁ ነበር።
እና ደሞ ትናት ከጓደኛሽጋ ስታወሪ ሰምቼሻለሁ ስለዚህ ለአከራይሽ የሰጠሽውን ብር እንኪ እንቢ እንዳትይኝ ምትክ ነው አለኝ።
እሺ ብዬ ተቀበልኩትና እንደቆመ በሩን ዘግቼበት ገብቼ ቁጭ አልኩ።
ነገረ ስራዬ ለራሴም አሳቀኝና ግራ ተጋባሁ::
ጠዋት ለእናቴ ግማሹን ብረ ቁጭ አድርጌላት ለፈገችው ነገር እንድታጠፋው ነግሪያት እኔ ወደስራዬ ሄድኩ።
መንገዱ ላይ እንደ እብድ እየተብሰለሰልኩ ነበር።
ስደርስ በር ሳንኳኳ ግቢ አለኝ።
ገባሁ።
ሰላም አደርክ ብዬ ስልኬን አስቀምጬ ወደኪችን ገባሁ።
ደና አደርሽ አለኝ።
ስገባ ድስቶቹ ተጣጥበው ፅድት ብለው ተቀምጠዋል በውስጤ ፈገግ አልኩና መሰራራት ጀመርኩ።
በመሀል ስልኬ ጠርቶ ዞር ስል ተመስጦ እያየኝ አይን ለአይን ተጋጨን ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ኮምፒውተሪ ጎንበስ አለ።
እናቴ ነበረች በሰጠኋት ብር ከህላዌጋ ወተው ለሷ ሚያምር ልብስ እየገዛችላት እንደሆነ ነገረችኝ ።
ደስ እንዳላችሁ ስራ ስጨርስ እደውላለሁ ብያት ስልኩን ዘግቼ ወደስራዬ ተመለስኩ።
ጎረቤቴ ያ የትዝታ ዘፈን የመክፈት አባዜው እዛም ቤት መጥቶ የትዝታ ዘፈን ከፍቶ እየሰማ ነበር ስራውን ሚሰራው።
እኔም በዘፈኑ ምስጥ ብዬ እየሰራራሁ።
በሩ ተከፈተ ስገባ ሳልቆልፍ ዝም ብዬ ዘግቼው ነበር የገባሁት።
እህቱ ናት ሸበላዬ መጣሁልህ ብላ እየሳቀች ወደውስጥ ገባች።
ዞር ብዬ አየኋት።
አብሯት ሌላ ሰው አለ።
እ ብሮ እንዴት ነህ ተባብለው ሰላምታ ተቀያየሩ ከጎረቤትጋ።
በዛ መሀል ልጅቷ ወደኔ መጣችና እናቴ እንዴት ነሽ አለችኝ።
ደና ነኝ ብዬ ሰላምታ ለመስጠት ወደሷ ተጠጋሁ ሰላም ብላ አቀፈችኝ በሷ ትከሸ አሻግሬ አብሯት የመጣውን ሰው አየሁት ውስጤ ለሁለት ሲከፈል ታወቀኝ ፊቱ አዲስ አልሆነብኝም እጄ መንቀጥቀጥ ሲጀምር ልጅቷን ለቀቅ አድርጊያት ፊቴን አዞርኩ እእ ያቢሻ ሻወር ትወስዳህ? አለችው
በልቤ አዎ ያብስራ ነው እራሱ ነው አልኩ.....
love you......❤

😱122❤39🙊1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
እጄም እግሬም እየተቀጠቀጠ ስለነበር ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ።
ስራውን እረስቼው የሚያወሩትን ለመስማት ጆሮዬን ወደነሱ ላኩት የሆነ ነገር የምር ተፈጥሮ ግን ማመን ስለማንፈልግ ነገሩን በጥርጣሬ መያዝ አለ አደል እሱ ስሜት ተሰማኝ።
የኔ ፍቅር በቃ እሺ ወደስራችን እንግባ ወንድሜ ቀጥል አለች።
እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ቅድስቴ አትቃዢ ቆይ ተረጋጊ ስራሽን ጨርሺና ሹልክ ብለሽ ውጭ እሱ አደለም ተመሳስሎብሽ ነው።
አታይም እንዴት እንደወፈረ አታይም ምን እንዳከለ በዚች ጊዜ ውስጥኮ እንደዚህ አይቀየርም ስም ያለው ሞኝ ነው ሆነሽ ነው ተረጋጊ ብዬ እራሴን አረጋጋሁና ስራዬን ጨረስኩ።
የስራው ዋናው ጎረቤቴ ሲሆን ልጁና ልጅቷ ደሞ የስራውን ዝርዝር ተረጂዎች ናቸው።
የሚንቀጠቀጠውን ጉልበቴን እንደምንም አረጋግቼ ለመውጣት ምትታገለኝን ልቤን አፍኜ ይዤ ስራዬን ብጨርስም እዛው ኪችን ውስጥ ቆምኩኝ።
በቃ ምንም አልሰማሁም አላየውሁም በቃ ቅድስት ተረጋጊ ብዬ ያለኝን ድፍረት አሰባሰቤ ወደነሱ ተመለስኩና ስልኬን አንስቼ አንገቴን እንደደፋሁ ልወጣ ስል እእ ልቴጂ ነው አለችኝ እህቱ።
አዎ አልኳት አቀርቅሬ።
እሺ የትራንስፖርት ብር ይዘሻል እንኪ አለችኝ ከቦርሳዋ አውጥታ አይ አመሰግናለሁ አለኝ ብያት ቀና አልኩኝ ወደነሱ ሶስቱም አይናቸው እኔ ላይ የኔ አይን ደሞ ያብስራ ላይ አረፈ።
እራሱ ነው ።
ያብስራ ነው።
አሁንም ዝም ሲል የተኮሳተረ ሚመስለው እራሱ ነው።
ሰዎችን ሲመለከት እኔ ማቀው አስተያየቱ እራሱ እሱ ነው።
ኦያየሁት እሱ የተገኘበትን ቦታና እኔ ያለሁበትን ቦታ አይቼ የዛን ቀን ያለኝን በሱ ምክንያት ያሳለፍኩትን ሁሉም ሀሳቦች ባንዴ እኩል ሰአት ጭንቅላቴ ውስጥ መተው አቃጨሉ
ጭንቅላቴ ጭጭጭጭ በሚል ድምፅ ሲሞላ ትዝ ይለኛል ከዛ ምን እንደተፈጠረ አላቅም እራሴን ስቼ እዛው ፊት ለፊታቸው ወደኩ
https://t.me/mane121921

❤80💔13😡1
tiktok.com/@mane.shopping
ሰዎች አዲስ የስራ አካውንት ከፍቻለሁ እና ገና 0 followers ብቻ ነው ያለው ግዴታ 1000 ሰው ያስፈልገኛል
please support me

👍14❤2
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ስነቃ ምን እንደተፈጠረ አላቅም ግን እዛው ሶፋ ላይ አስተኝተውኝ ጎረቤቴና እህቱ በድንጋጤ ውሰጥ እያዩኝ ነበር።
ብድግ አልኩኝ እህቱ በስርአት ተነፈሰች ምን ሆነሽ ነው አስደነገጥሽኝኮ በሽታ ነገር አለብሽ ወይስ ምንድነው አለችኝ።
ወደ በሩ ዞር ስል ያብስራ እጁን በደረት አድርጎ ጅንን ብሎ ቆሞ ነበር እንደ አክተር እያደረገው ነበር።
አለቀስኩ በትንሹ አደለም ስቅስቅ ብዬ ጉልበቴ ላይ ድፍት ብዬ አለቀስኩ።
ስለክብሬም ስለምኔም አልተጨነኩም ውስጤ ያለው እልህ ይባስ እየተናነቀኝ እያፈነኝ ነበር።
እህቱ በጣም ግራ ተጋብታ አረ ምን ሆነሻል አረ በጌታ እያለች ስፍስፍ ብላ አባባበለችኝ።
ጎረቤቴ ልማዷ ነው ደሞ ጀመራት በሚል አስተያየት ነበር ሲያየኝ የነበረው።
ትንሸ ካለቀስኩ ቡሀላ እንባዬን ጠራርጌ ይቅርታ ጠይቄ ለመውጣት ስነሳ እህቱ ብቻሽን ላውራሽ አለችኝ።
እነሱ ወጡ እኛ ቤት ተቀመጥን።
በናትሽ የሆንሽውን ንገሪኝ እኔ እንደዚህ አይነት ጭንቀት ምናምን አልችልም የሆንሽውን በግልፅ ንገሪኝ ገንዘብም ከሆነ እኔ እሰጥሻለሁ እኔ የገንዘብ ችግር የለብኝም ጠይቂኝ ምንም አታስቸግሪኝም አለች።
አይ አደለም እናቴ መልእክት ልካልኝ ነበር እና ትንሸ አመመኝ ብላኝ ደንግጬ ይቅርታ አልኳት።
አይዞሽ እንደደረሽ ሀኪም ቤት ውሰጃቸው ብላ ቅድም ልትሰጠኝ ከነበረው ብር ላይ ጨምራ ሰጠችኝ።
እኔ በፍፁም አልኩ እሷ ግን ተቆጣችኝና ብሩን በእጄ አስጨብጣኝ ከቤት ወጣን።
በቃ ሰላም ዋሉ አልኳቸው።
ሰላም ዋይ አሉኝ... ያብስራ ግን አረ ደሞ ድጋሜ ብትወድቅስ ቢያንስ taxi ላስይዛት ታሳዝናለች መጣሁ አለ።
ጥርሴን ነክሼ ፊቴን አዞርኩ ተከተለኝ ..
ምንም እንዳልተፈጠረ እጁን ትከሻዬ ላይ አድርጎ ደረቱን ነፋ እያደረገ
ትንሽ ከሳሽና ጠቆርሽ እንጂ ፊትሽ አልተቀየረም ያው ነሽ ግን በዚህ ሁኔታ ማገኝሽ አልመሰለኝ ግቢ ገብተሽ ምናምን ብዬ አስቤ ነበር አለኝ ....
(Sewoch please follow adrgulgn
👇👇👇👇👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping)

❤103😡10🔥9🤔8
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አስታውሰኸኛል ማለት ነው አልኩት?
ደንግጬ ነበር
አዎ ቅድስቴ አስታውሼሻለሁ እረጅም ጊዜ አደለምኮ ከተለያየን ለማንኛውም እንደዚህ ባትሆኚ አሪፍ ነበር ።
ጭራሽ ሰው ቤት ተመላላሽ ምናም ተይ ደስ አይልም ላንቺ አይመጥንም ገና በዚህ እድሜሽማ እንደዚህ ዝቅ ብለሽ አትስሪ ለማን ብለሽ ነው ይሄን ያህል ፈታ በይ እንጂ አለኝ።
ምንድነው ምመልሰው ምንድነው ማወራው ልጩህበት ወይ ያለኝን አቅም ተጠቅሜ ልምታው ወይስ እንዴት ነው ልቤን ያፈነኝ ነገር የሚወጣልኝ።
ጫፍ አስፋልት ደረስን እኔ አልተነፈስኩም ዝምምም
ለማንኛውም አላቅሽም አታቂኝም እሺ።
ለልጁ ወይ ለሷ ለአንዳቸው እኔን ከዚህ በፊት እንደምታቂኝ ትንፍሽ አልሽ ማለት አለቀልሽ አሁን ያ ያብስራ አደለሁም እሺ እነሱ ብር ማትምባቸው ማሽኖቼ ናቸው የገቢ ምንጮቼ ሲነኩብኝ ደሞ አልወድም።
እኔ እነሱ ቤተሰብ ውስጥ የገነባሁት ማንነት አለ ከዚህ በፊት ካንቺጋ ለአንድ ቀን እንኳን አደለም ተኝቼ ታይቼ እንደነበር ከታወቀ ጥሩ አደለም አጋጣሚ አቃጣሪ ነው መልሶ አገናኘን ግን አንቺም እኔን አይተሽኝ አታቂም እኔም አንቺን አይቼሽ አላቅም እሺ የኔ ሚጢጢ አለኝ ።
አስተያየቱ አነጋገሩ ያስፈራ ነበር ልክ እንደ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ በድፍረት እየተመለከተኝ በአስተያየቱ ብቻ ከባድ ማስጠንቀቂያ እየሰጠኝ ነበር።
የኔን መልስ አልጠበቀም ትቶኝ ሄደ።
መንገድ ለመንገድ እንደ እብድ እያደረገኝ እያለቀስኩ እንባዬን በሻርፔ እየጠረኩ እዛው አስፋል ተሻግሮ ከፍ ብሎ ወዳለው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ገባሁ።
ከምን ጀምሬ ፀሎት እንደማደረግ ግራ ገባኝ ብቻ አየኸው አደል አየኸኝ አደል።
እኔ ለነሱ ወጥ ቀቃይ እሱ የኔ አለቃ ሆኖ ተገናኘን ።
ዛሬም እኔ እታች ነኝ።
ትናት በድሎ አስለቅሶ ትቶኝ የሄደው ቦታ ላይ ወርጄ ነው ያገኘኝ።
ሲያየኝ አልደነገጠም በጥፋቱ አላፈርም አየኸዎ አደለ እኔም እሱም እኩል ሰው ነን አደል በቃ ፍረድልኝ ወይ አጠንክረኝ ወይ ከዚህ ድራማ አውጣኝ ምንም አላየሁም ምንም አልሰማሁም በቃ
ተነስቼ ወደቤት ሄድኩ።
ልጄን ሳያት አቃተኝ እንዴት ነው አባትሽ እንደሱ አይነት ሰው ነው ገንዘብ አምላኩ ነው ብዬ የምነግራት እንዴት ነው ማስረዳት አቅፊያት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ እናቴ በሁኔታዬ ግራ ገብቷት ዝም ብላ አየችኝ።
አንዳንዴ ይደክማል ይሰለቻል አደል አልቅሽ ቢያንስ አንቺ ምታለቅሺበት እድሜ ላይ ነሽ ሚታዘብሽ ሚቆጣሸ የለም ውስጥሽ ያለው እሳት በረድ እስኪል አልቅሸ ማልቀሻ ማግኘትም አንድ መታደል ነው አፍነሽ ስትይዥው ነው ውስጥ ውስጡን ሚጨርስሽ አለችኝ።
ምተነፍስባት ሜሪጋ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኳት ደነገጠች።
ተመሳስሎብሽ ነው እንዴት ሊሆን ይችላል አለችኝ።
ያለኝንም ነገርኳት።
ተሳደበች ይሄ ውሻ እሱም ወንዶ ነው ሊያስፈራራሽ ይሞክራል ድጋሜ እዛ ቤት እንዳቴጂ የቀረው ይቅር ድጋሜ እሱን እዛ እያየሽ እንዳትጎጂ በቃ እንደሞተ ቁጠሪው ከህይወትሽ አውጭው ያብስራ ሚባል ሰው የለም አልነበረም አለችኝ።
እውነታው ግን ልጄ አለች እሷን በማይበት በእያንዳንዱ ቅፅበት እሱን አስታውሳለሁ።
ግን በቃ ደግሜ እዛ ቦታ አሌድም ደግሜ እዛ ቤት እግሬ አይረግጥም ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ።
ግን ጎረቤቴስ ምን እለዋለሁ ምን ምክንያት አቀርባለሁ አላውቅም።
በዛ ውዝግብ መሸ።
ማታ ላይ አይኔ አብጦ ነበር ሳለቅሽ አምሽቼ ።
ወደ 3 ሰአት አካባቢ ጎረቤቴ መጣ።
በሩን አንኳኳ
ከፈትኩለት ።
ሰላም አመሸሽ አንዴ ላውራሽ አለኝ።
አፉ ጋን ጋን ይሸታል።
እሺ ብዬ በሬን ዘግቼ ወጣሁ።
ምን ሆነሽ ነው ቀን እንደዛ የሆንሽው አለኝ እጁን በኪሱ ከቶ።
ምንም አልሆንኩም።
ግን ካሁን ቡሀላ አልመጣም እዛ አልሰራም አመሰግናለሁ ስለሰጠኸኝ እድል ግን አልተመቸኝም ልጄን መያዝ አለብኝ አልኩት።
ሳቀ ድረማ ምናምን ነገር ትወጃለሽ ልበል ለማንኛውም እንደተመቸሽ ከመጀመሪያ ከሰጠሁሽ ደሞዝ አንስቶ ዛሬ ስትወጪ ሲስተር የሰጠችሽን ገንዘብ ሙሉ ደማምሪና ሁሉንም ነገ ትከፍያለሽ ካሎነ ደሞ እኔ በግድ እቀበልሻለሁ ደና ደሪ ብሎ ገፍትሮኝ ወደቤቱ ገባና ቆርቆሮ በሩን ወረወረብኝ
ደና ደሩ😌
ከተመቻችሁ 👍👍

❤84👍19😭14🙉5😱4🥰1
4600 ተከታይ እያለኝ 1000 ሰው ቲክቶክ ላይ ያሰፈልገኛል ለስራ ብዬ ፖሰት አድርጌ 22 ሰው ብቻ ነው follow ያደረገኝ
የምትችሉ ሰዎች follow አድርጉልኝ
የምር የምር ስለሚያስፈልገኝ ነው
👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping
የምትችሉ ሰዎች follow አድርጉልኝ
የምር የምር ስለሚያስፈልገኝ ነው
👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping
❤15👍1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አንዳንዴ ነገሮች ድርብርብብብ ይሉና ጭንቅላታችንን ማሰብ እንዳይችል ይከለክሉታል።
ዝም ማልቀስ መጮህ በነበረባችሁ ጉዳይ ላይ ዝም እንድትሉ ያደርጋችኋል በቃ ዝምም አታለቅሱም አትጮኹም አትናገሩም እንዲሁ ዝም።
ያኔም እኔ እንደዛ ነው የሆንኩት ዝም ብዬ ወደቤቴ ገብቼ ቁጭ አልኩ።
ዝም ብዬ ግድግዳው ላይ በጀርባዬ ደገፍ አልኩ።
ልጄን አየኋት ስለዚህ ምስቅልቅል ህይወት ምታቀው ነገር የለም ጧ ብላ ተኝታለች።
ልጅነት ደስ ይላል።
እያደጉ በሄዱ ቁጥር ደስታ ከኛ ይርቃል።
ሀላፊነት በበዛ ቁጥር የመጀመሪያ ምናጣው ምቾታችንና ደስታችንን ነው።
እንዲሁ ስገላበጥ የሰጡኝን ብር ስደምር ስቀንስ ትንሽ እንዳሸለበኝ ሌሊቱ ነጋ።
ጠዋት ላይ ጎረቤቴ ከቤቱ ሳይወጣ እየጠበቀኝ ነበር።
እኔ አገር አማን ብዬ ህላዌን አጣጥቤ ልብስ ቀይሬ አቤልጋ ሄጄ እንዴት እንዳደረ ጠይቄው እናቴ እስክትመጣ ውጭ ፀሀይ ለመሞቅ ወጥቼ ቁጭ አልኩኝ።
በጨረፍታ ቤቱን አየሁት ከውጭ አልተዘጋም ገርበብ እንዳለ ነው።
ፊቴን አዙሬ ቁጭ አልኩ ህላዌን አቅፊያት ከሷጋ እየተሳሳኩ ነበር።
ከጀርባዬ ቆሞ ልጅሽ በጣምም ነው ምታምረው በማን ወጥታ ነው አለኝ።
ዞሬም አላየሁትም አመሰግናለሁ አልኩት።
ከፊት ለፊቴ መጥቶ ድንጋዩ ላይ ቁጭ አለ።
ህላዌን ሊያወራት ሊያሳስቃት ሞከረ።
ህላዌ ፈርታው ነበር ወደሱ አልጠጋም አለች።
አጋጣሚውን ተጠቅሜ ልጆችኮ ውስጡ ንፁህ የሆነን ሰው ነው ሚወዱት አልኩት።
ፈገግ ብሎ አየኝ።
አየሁት የተጎሳቆለ በሚመስለው ሰውነቱ ውስጥ በምቾትና በቅንጦት ያደገው ማንነቱ አንፀባርቆ ይታያል ።
እሺ ምን አሰብሽ አለኝ።
ምንም አላሰብኩም እናቴ ትምጣና ከሰው ተበድሬ ያለብኝን ብር እሰጥሀለሁ ለአቤል መታከሚያ ሰጥቼው ስለነበር ሁሉም ጠፍቷል ድጋሜ የሰጠኸኝንም ተጠቅሜዋለሁ የትናቱ ግን ሙሉ አለ እሱን ልስጥህ ያኛውን እስከማገኝ አልኩት።
አሳዘንኩት መሰለኝ።
እሺ ምክንያትሽን ንገሪኝ እዛ ማትሰሪበትን እኔኮ ላንቺ የማይጎዳሽ ትክክለኛ ቦታ እንደሆነ ስለማውቅ ነው ደጋግሜ የጠየኩሽ እድል የሰጠሁሽ።
እውነት ለመናገር ቤት የተሰራ ምግብ አይበሉም በየትኛውም አጋጣሚ ውጭ ነው የሚመገቡት እኔ ላንቺ የስራ እድል የፈጠርኩ ስለመሰለኝ ነው እነሱን አሳምኜ ቤት የተዘጋጀውን ምግብ እንዲበሉ ያደረኩት።
እመኝኝ ከደሞዙ በላይ ጥሩ ጥቅማጥቅም ታገኛለሽ በዛ ላይ ልጅሽ እንደኩዮቿ ትምህርት ቤት ምትገባበት ሰአት እንኳን ሲመጣ ማስገባት ትችያለሽ ላንቺም አይጎዳሽም።
በብሩ ምክንያት ሼም እየያዘሽ ከሆነ አታስቢ ነይ አሁን እንሂድ በኔ ይሁንብሽ ሄደሽ በአንድ ሰአት ውስጥ ጨራርሰሽ መውጣት ነው ከዛ ከልጅሽጋ ተኝተሽ ትውያለሽ አለቀኮ ሌላ ምንም የለም አለኝ።
በዛ መሀል እናቴ መጣች እቃዋን ገዛዝታ ለቁርስ ሚያስፈልገንን ይዛ ነበር የመጣችው።
ስታየን ደሟ ፈላ።
ባጠገባችን አለፈች ቤት ገባችና ተመልሳ መጥታ ህላዌን ከላዬ ላይ ብድግ አድርጋ አቅፋ ወደቤት አስገባቻት ነይ እጠብቅሻለሁ ጫፍ አስፋልት ብሎኝ ተነስቶ ወጣ።
እኔም ወደቤት ገባሁ።
እናቴ ንዴቷ ፊቷ ላይ እየታየ እኔ ነግሬሻለሁ ከዚህ ሴጣን ከመሰለ ሰውዬጋ አታውሪ አይ ካልሽ አጋጭሻለሁ ቅድስት ስርአትሽን ያዢ ስትነገሪ ስሜን ጭራሽ ልጄን እሱ ፊት ይዘሽ ቁጭ ትያለሽ ይሄ ቡዳ ቢበላትስ አለችኝ።
ዝም አልኩአት ግድ አልሰጠኝም።
የገዛችውን እቃ እያሳየችኝ ባለችኝ ይቺን ገዛሁ ይሄን ልገዛ ብዬ ብር ጨረስኩ ቆይ ያኛው ተከራይ ሲሰጠኝ ደሞ እንገዛለን አለችኝ።
ደበረኝ እኔም ልጄን እናቴ ላይ ሸክም መሆናችን ነው ።
ምናገባኝ ያብስራ በቃ የት አቀዋለሁ ስራዬን እሰራለሁ ስጨርስ እወጣለሁ ብዬ ልብሴን ቀይሬ እናቴን ቻው ብያት ወጣሁ።
ስወጣ ቆሞ እየጠበቀኝ ነበር።
ሲያየኝ ፈገግ አለ።
መምጣትሽ ላይቀር አይነት አስተያየት አየኝ

❤114
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ምን እያደረገ እንደሆነ ለኔም ለሱም አልገባኝም።
ይመስለኛል ውስጡ ያለው ፍርሀት የፈጠረበት ጭንቀት ነው።
እኔ የሁል ጊዜ ህልሜ ያብስራን አጊቼው ልጅ እንዳለው ነግሬው አውቆ የሚለው... የሁልጊዜ ፀሎቴ የነበረ ቢሆንም መጓጓቴና መጠበቄ ልክ አለመሆኑን በድጋሜ መጥቶ አረጋገጠልኝ።
ከዚህ ቡሀላ ልጄ አባት የላትም ከዚህ ቡሀላ መጠንከር ግዴታዬ ነው።
ያለኋት የቆምኩላት የእድሜ ዘላለሟ እናትም አባትም እኔ ነኝ ብዬ አሰብኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ያብስራ ላይ የነበረኝ ተስፋ ሞቷል።
ግን ደሞ ቀን በቀን በሄድኩ ቁጥር ለብሶ አምሮበት የሀብታም ልጅ መስሎ እንደዛ ተንደላቆ ተመችቶት እኔ የሰራሁትን ምግብ እየበላ እግሩን ሰቅሎ ይውላል።
የእነ ሜሪ መመረቂያ እየደረሰ ስለነበር ከነሱ ማገኘውን ጥቅማጥቅም እያጠራቀምኩላት ነበር።
ምን እንደማደርግላት ባላቅም ብቻ ሲሰጡኝ ሁላ እንቢ ማለት ትቼ እየተቀበልኳቸው እሮጬ ወደማጠራቀሚያዬ እየከተትኩ ነበር።
ያብስራና እኔ ወደኖርማል ኑሯችን ገባን አለቀ።
እንኳን የልጄ አባት ከዚህ በፊት የምንተዋወቅ ሰዎች አንመስልም።
ህይወታቸው ግራ የሚያጋባና በእንቆቅልሽ የተሞላ ስለሆነ ጎረቤቴን ስለህይወቱ እንዲነግረኝ መገፋፋቴን ብቀጥልም እሱ ግን ወይ ፍንክች አለ።
በስህተት የሚተነፍሰው ነገር የለም::
ቀናቶች ሄዱ እነ ሜሪ ተመርቀው ለመምጣት 1 ሳምንት
ለመጋባት ደሞ 1 ወር ከ15 ቀን ቀራቸው።
ምንም አይነት የምርቃት ድግስ ሳያደርጉ በአዲሱ አመት ደሞ ሞቅ ያለ ሰርግ ተደግሶ ቀጥታ ወደትዳር መግባት እንደሚፈልጉ ለቤተሰቦቻቸው አሳወቁ።
የሀይሌ ቤተሰቦች ምን አስቸኮለህ ገናኮ ነው እድሜህ ስራ ሳይኖርህ ገንዘብ ሳትይዝ ብለው ትንሽ ቅር ቢሰኙም እሱ ግን በአቋሙ ፀና።
የሜሪ ቤተሰቦች ግን ደስተኛ ነበሩ።
ልጃቸው ተምራ ተመርቃ ስትመለስ ደሞ ሰርግ ደግሰው ከዳሯት ሌላ ለነሱ ወግ ማእረግ የለም።
አንዳንዴ ውስጤ ቅናት ይሁን የበታችነት ስሜት ይሰማኛል።
አንዳንዴ ምግብ እየየሰራሁ የጨመርኩትን ነገር ደግሜ እጨምራለሁ።
አንዳንዴ መንገድ እየተራመድኩ የማቀው መንገድ ይጠፋኝና መሀል መንገድ ላይ እደናበራለሁ።
ከምንም በላይ ደሞ እናቴ ስለሜሪ ስታቅ ያለችኝን አረሳውም።
አየሽ በአባት እጅ ስታድጊ እንደዚህ ተምረሽ ተመርቀሽ በክብር ትዳሪያለሽ እናት አባት ይኮራብሻል ።
አቤት ታድለው ከዚህ በላይ አለም ምን አለ።
ልጄ እንደዛ ሆና አይቻት በነጋታው ብሞትም አይቆጨኝ ብላኝ የበር።

❤102👍3
mane.shopping
ይሄ የቲክቶክ አካውንት አሁን 150 ተከታይ አለው 1 ክፍል በፈለጋችሁት የfollower መጠን አባዝቼ እለቅላችኋለሁ::
ለምሳሌ 1 ክፍል በ10 follower
ከዛም በታች ወይ ከዛ በላይ ሊሆን ይችላል።
ያው መደበኛ ከምለቅላችሁ ክፍል ውጭ ነው ይሄኛው
👇👇👇👇
http://mane.shopping

🙉16❤7
ህላዌ (✍️✍️ማኔ
በበኩሉ አቤል እነሱ ሊመረቁ ነው እኔ ሲሄዱ የለበስኩትን ቲሸርት መቀየር አቅቶኝ እየማቀኩ ነው።
ህይወት ግን ፍትሀዊ አደለችም ታዳላለች አደል ይለኛል።
አንድ ቀን ማታ ላይ ሁሉም ነገር ምርር ብሎኝ ሰልችቶኝ ሳለቅስ አደርኩ።
ጠዋት ስነሳ አይኔ አብጦ ነበር።
ቢሆንም ስራ ግዴታ መሄድ ስላለብኝ ተነስቼ ወደስራ ሄድኩኝ።
ቤት ውስጥ ጎረቤቴ(እዩኤል) ቁጭ ብሎ ነበር።
ሲያየኝ ደነገጠ።
የተፈጠረ ነገር ካለ ጠየቀኝ።
የለም ብዬ ዋሸሁት።
ሶፋ ላይ አስቀመጠኝና።
አንቺ ተስፋ ለመቁረጥጥ በጣም ገና ነሽ መቁረጥም አትችይም ምክንያቱም ልጅ አለሽ::
ልጅሽ ተስፋሽ ናት ህይወትሽ ናት ለመኖር ታጓጓሻለች ለሷ ታገይላት ጥሩ ህይወትን ለመስጠት ሞክሪ ልትወድቂ ልትሰበሪ ልታለቅሺ ስትይ ልጅሽን ጥንካሬሽን አስቢያትና እንዳድስ ቁሚ።
አንቺ ወደፊት በምትጦሪያት እናትሽና በምታሳድጊያት ልጅሽ መሀል ነሽ።
ሁለቱንም እጅሽን ዘርግተሽ የመቀበል ግዴታ አለብሽ ስለዚህ ሌላውን ነገር እርግፍፍፍ አድርገሽ ተይው አጉል አትጨነቂ አጉል አታስቢ ።
ሁልጊዜ እጅሽን ልይዝሽ አለሁልሽ ልልሽ እፈልጋለሁ ታሳዝኚኛለሽ ግን ደሞ የኔ ህይወት እንደምታይው ነው።
ተስፋ ማደርገው ነገር የለኝም ከራሴና ከእውነታው ለመሸሸግ አፈር ቤት ውስጥ አንጥፌ እየተኛሁ ነው እራሴን ሽሽት ከራሴ ለማምለጥ እየሞከርኩ ነው።
እንደወንድ ልጅ መጋፈጥ በሚገቡኝ ጉዳዮች ላይ እኔ እጅ ሰጥቻለሁ ግን አንቺ ሴት ነሽ በእድሜ ገና ነሽ ተስፋ አትቁረጪ በህይወትሽ ምንም ነገር ቢፈጠር ብርቅ አይሁንብሽ ማጣትንም ማግኘትንም ተለማመጃቸው።
ሰዎች ላይ እንዳትደገፊ ምክንያቱም መቼ ልታጭያቸውና ሊከዱሽ እንደሚችሉ ፈፅሞሞ አታውቂም ለሱ ደሞ ከኔ ህይወት በላይ አስተማሪ የለሞ አለኝ።
በናትህ ስላንተ ንገረኝና እስቲ ልጠንቅርበት ልማርበት አልኩት ከየት ያመጣሁት ድፍረት እንደሆነም አላቅም

❤41👍9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አልነግርሽም ምክንያቱም አይመለከትሽም።
እኔ ህይወቴን ለሰዎች አላወራም ማንም ስለማይመለከተው።
እሺ ብዬ ተነስቼ ወደስራዬ ገባሁ።
ጊዜው በድጋሜ መሮጥ ጀመረ።
እነ ሜሪ ተመርቀው መጡ።
ጓደኛዬ ተመርቃ ስትመጣ በክብር መቀበል ቢኖርብኝም እኔ ግን እሱን አላደረኩም።
ምክንያቱም እዛ ቦታ ላይ መገኘት አልችልም።
ወዲያው የመስክ ፎቶ ለመነሳት ዝግጅታቸውን ቀጠሉ።
እንደጓደኛ አብሪያት መሆን የነበረብኝ እኔ ነበርኩ ግን ጓደኛዬ ምን አይነት ቬሎ ለብሳ እንደምትሞሸር እንኳን የማየት እድሉን አላገኘሁም።
በጓደኛዬ ደስታ ልቧ የተሰበረው ብቸኛ ሰው እናቴ ናት።
እሷ ስትመረቅ አይ ልጄ አንቺምኮ ጎበዝ ነበርሽ እንደው የዛኔ ጭክን ብለሽ ልጅሽን ለኔ ሰተሽ ተምረሽ ቢሆን ይሄን ምርቅ ትይልኝ ነበር።
ይሄኔ አንቺም እንደጓደኛሽ ትሞሸሪ ነበር።
ወገቤን አስር አድርጌ ከሰፈር ሰውጋ እየተጠራራሁ ለሰርግሽ እየተዘጋጀሁ ነበር።
ልጄ ስታገባ የሰርጓ ቀን በአበሻ ቀሚስ ጎርደዶ ጎርደድ እያልኩ አስቢው እስቲ ብላ ከትትት ብላ ትስቅና እንባዋ ይፈሳል። ግን ሴት ያሳደገው ከዚህ አይዘልም እያሉኝ ስለኖርኩ ምፈራው ነገር ነው ሰተት ብሎ ቤቴ የገባው ትላለች።
ታሳዝነኛለች።
አቤል ከነ ሀይሌጋ ለሰርጋቸው ዝግጅት ሲያደርጉ አብሯቸው እየዞረ ነበር።
እሱሞ ቢሆን ወይ እንደሀይሌ ሻል ካለ ሰው አልተወለድኩ ወይ አፍቅራኝ አፍቅሪያት ምታጠነክረኝ ፍቅረኛ አልያዝኩ ወይ ሰርቼ አልተለወጥኩ እያለ ያጉረመርማል።
ዙሪያችን ያለው ሰው እራሱ በልጠነው ስንገኝ ደስ አይልም የራሱን ኑሮ እያሰበ ይቆዝማል እንጂ።
በስተመጨረሻም የሜሪ ሰርግ ደረሰ
ያለውን ነገር እንዳይከፋኝ እንዳይደብረኝ እዛ እንዳለሁ እንዲሰማኝ ብላ ሁሉንም ከስር ከስር ትነግረኝ ነበር።
የሰርጉ ቀን ደረሰ።
እኔ ስራ አልገባሁም ነበር።
እናቴ ከቤት ዝንጥ ብላ ለባብሳ መጣች።
ሳያት ደነገጥኩ አምሮባት ነበር።
በዚህ ልክ አምሮባት አይቻት አላቅም።
ቢያንስ በሷ ሰርግ እንኳን ልዘንጥና እልሄን ልወጣ እንጂ እኔ እንደሆንኩ ቆሜ ልጄን ለመዳር አልታደልኩም አለችኝ።
በዛሬው ቀን እንኳን ነገር ባትፈልጊኝ ምናለበት ብዬ ብስጭት አልኩባት።
በይ በይ ሙሽሪት ከቤቷ ሳትወጣ ልድረስ ብላኝ ፍንድቅድቅ እያለች ከቤት ስትወጣ ህላዌ አትሄጂም ብላ ቤቱን ቀወጠቸው።
እላይዋ ላይ ተለጥፋ አለቅም አለቻት።
እኔም እሷም በግድ አስጥለናት እናቴ ወሰርጉ ሄደች።
እኔና ህላዌ በራችን ዘግተን ቁጭ አልን።
ህላዌ ለቅሶዋን አላቆም አለች ብለምናት ባባብላት አሻፈረኝ አለች።
ውስጤ አፍኜ የያዝኩት እልህና ንዴት ገንፍሎ ወጣ።
መታኋት።
ለመጀመሪያ ጊዜ ልጄ ላይ እጄን አነሳሁ።

❤82💔15😱6🥰4🤯1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ቅጥቅጥ አደረኳት።
አልቅሳ ሲደክማት እንቅልፍ ወሰዳት።
እሷ ስትተኛ እኔ ተተካሁ።
ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ።
አብሮ አደጌ የልብ ጓደኛዬ ስትሞሸር መገኘት እንዳልችል ያደረገኝ ያብስራ ነው።
እናቴ አጋጣሚ እየጠበቀች ምትወቅሰኝ በሱ ምክንያት ብዬ አሰብኩ ውስጤ የሚሰማኝ የጥላቻ ነደደ ይሄ ነው የሚባል አደለም።
አቤል ሰርጉ ላይ ሄዷል።
ከሀይሌ ልብስና ጫማ ተበድሮ በሙሽራው ልብስና ጫማ ሰርጉን ለመታደም ሄዶ ነበር።
ምሽቱን ማልቀስ ማቆም አልቻልኩም።
እራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አቃተኝ እቴቴ መጥታ ከአንዴም ሁለቴ በር ብታንኳኳም እንደተኛ ሰው ዝም አልኳት።
ማታ እየመሸ ሲሄድ ህላዌ ከእንቅልፏ ነቅታ እማማጋ እንሂድ አለችኝ።
እረፊ ብዬ ተቆጣኋት።
አጠገቧ ተቀምጬ እላዬ ላይ ወጥታ እያቀፈችኝ እንባዬን ጥርግ እያደረገች ሳም ሳም ታደርገኝ ጀመር።
መልሼ አቅፌ ሳምኳት።
መልሳ አሳዘነችኝ እሷ ምን በወጣት እሷ ምን ባጠፋች ልገላምጣት ልቆጣት።
ማታ አንድ ሰአት አካባቢ ላይ ለእናቴ ደወልኩ አታነሳም።
ለሜሪ እንዳልደውል ጨነቀኝ።
እቴቴጋ ሄድኩ አቤል ቆየኮ አልኳት።
አዎ ቆየ ግን ሰርግ አደለ እንዴት ቶሎ ይመለሳል አለችኝ።
ትንሽ እሷጋ ቁጭ አልኩና አባትየው ሳይመጣ ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩ።
ቤት መግባት ስላልፈለኩ ህላዌን አቅፌ በሻርፔ ጥቅልል እንዳደረኳት ቁጭ ብዬ ሰማይ ሰማይ እያየን ሁለታችንም መሳሳቅ ጀመርን።
እዛው ቁጭ ብለን ጎረቤቴ መጣ።
ሲያየን ፈገግ ብሎ መቀላቀል ይቻላል አለ?
ምኑ ላይ ነው ምትቀላቀለው አልኩት።
አብሪያችሁ ልቀመጥ አለኝ።
ዝም ብዬ አየሁት።
ቁጭ አለ።
ሞቅ ብሎት ነበር።
እናትና ልጅ በቃ ፍቅራችሁ እያስቀናኝኮ ነው አባት አትፈልጉም ብሎ እራሱ ባወራው ቀልድ እራሱ ከት ብሎ ሳቀቀ ግራ ገብቶኝ አየሁት።
በዛ መሀል ነው የእናቴ ስልክ ወደኔ ስልክ ሲጠራ ያየሁት።
ተጣድፌ አነሳሁት የአቤል ድምፅ ከስልኩ ውስጥ ተሰማኝ።
እየተርበተበተ ነበር ሄሎ ቅድስት እናትሽ እናትሽ ሀኪም ቤት ገብታለች አለኝ ከአጠገቡ የለቅሶ ድምፅና ጫጫታ እየተሰማኝ ነበር
ዋናው እስኪለቀቅ ቲክቶክ የሌላችሁ ሰዎች አንብቡት

👍35❤20😱9
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
በድንጋጤ እንዴት እንደተነሳሁም አላውቅም።
ህላዌ ተንሸራታ ከእጄ ሾልካ ከመውደቋ በፊት እዩኤል ይዟት ነበር።
እንዳትደነግጥ ጥብቅ አድርጎ ቢያቅፋትም ስለፈራችው እሪ ብላ አለቀሰች።
እኔ እጄ እየተንቀጠቀጠ አቤልን ምን ምን ሆና ነው ምን ሆና ነው ብዬ ከመጠየቅ ውጭ ሌላ ምንም መናገር አልቻልኩም አቤልም ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው።
ወዴት እንደምሄድ አላወኩም በሩ ሁላ ጠፋብኝ።
ብቻ በቆምኩበት እንባዬ እየፈሰሰ ሳላስበው እቴቴ እቴቴ እያልኩ እየተጣራሁ ነበር።
እቴቴ ደንግጣ ወጣችና አቤል ምን ሆነ ልጄ ምን ሆነ ድሮም ሲጨንቀኝ አውቄው ነበር አለችኝ።
እናቴ ሀኪም ቤት ገባች አቤል ደውሎ ነገረኝ አልኳት።
ደነገጠች።
እሷ ህላዌን ያዘቻት አደራ ልጄን እቴቴ ብያት እሷጋ ትቻት ዝም ብዬ በደመነፍስ ወጣሁ።
እናቴ የት እንዳለች አላቅም።
የtaxi አልያዝኩሞ የለበስኩትን ልብስ አላስተዋልኩትም።
ብቻ ዝም ብዬ እየሄድኩ ነበር።
በዛ መሀል ጎረቤቴ እየተከተለኝ ወዴት ነው ምቴጂው የት ነው ያለችው ይለኛል መልሼ ስልክ እደውላለሁ አያነሱም ።
ከስንት ሙከራ ቡሀላ አቤል ስልኩን አንስቶ እናንተ ሰፈር ያለው ኤልቤተል ትልቁ ክሊኒክ ነው ያለነው አለኝ።
ጎረቤቴና እኔ ተያይዘን በላዳ ወደዛ ሄድን።
ላዳ ውስጥ ተቀምጠን ከኔ በላይ ሲጨነቅ እየተሳቀቀ አይን አይኔን ሲያየኝ ነበር።
በድንጋጤ ስካሩ ሁላ ሳይጠፋለት አይቀርምተ
ሰፈር ደረስኩ።
ቅንጣት ታክል የሰው ወሬ አላስጨነቀኝም ትዝም አላሉኝም።
ጎረቤቴ ለላዳው ሹፌር ብሩን እስኪከፍልም አልጠበኩትም እኔ እየሮጥኩ ነበር።
እሱም ተከተለኝ።
ሆስፒታል ደረስን የተወሰኑ የሰፈሩ ሰዎች በሀበሻ ቀሚስ እንዳሸበረቁ ነጠላቸውን አፋቸው ላይ ሸፍነው ቆመዋል።
እኔ ስደርስ ዶክተሩ ከአቤልጋ አውርቶ አቤል መሬት ላይ ብርክክ ብሎ እባክህ ዶክተር የሆነ ነገር አድርግ በናትህ መሞት የለባትም ሲለው ጆሮዬ ውስጥ ጥልቅ አለ እናቴ ሞታ ነበር

💔80❤39😱7
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
በዛ ሰአት ስለሱ ማሰብ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላቅም።
በለቅሶ ውስጥ ልቤ ተሰብሮ ከስብርባሪው የተረፈችው ትንሿ አካሌ ደሞ ልጄጋ ነበረች።
እናቴ በስተመጨረሻ ለመቀበር ተያይዘን ወደቤተክርስቲያን አስክሬን አጅበን ሄድን።
እኔ ከግራና ከቀኝ ሜሪና አቤል ይዘውኝ ተረጋጊ ማለት አቅቷቸው አብረውኝ እያለቀሱ ነበር።
ቤተክርስቲያን እስክንደርስ ድረስ ጎረቤቴ ህላዌን ይዟት ከኛ እራቅ ብለው ሲሄዱ አልፎ አልፎ በአይኔ እያየኋቸው ነበር ግን በሰመመን ውስጥ ስለነበር በስርአት ላያቸው አልቻልኩም።
ደረስን ቆሜ እያለቀስኩ እናቴን አፈር ቆፍረው ሰቀብሯት አየሁ።
የኔም ተስፋ ህልሜ ህይወቴ ሙሉ ማንነቴ አብሯት የተቀበረ መሰለኝ።
እስክሞት ድረስ እየጮኩና እያለቀስኩ እባካችሁ አፈር አታርጉባት እባካችሁ አትቅበሯት ድንገት ብትነቃስ እግዜር ቢራራልኝስ እያልኩ እየለመንኳቸው ነበር ምክንያቱም ብቸኛ በሆንኩበት ምድር ላይ በላሽ ጠጣሽ ተነሳሽ ተኛሽ እረፍት አድርጊ ልብሽ አጊጪ ላንቺ እኔ አለሁልሽ ለልጅሽም እኔ አለሁላት ምትለኝን ሰው ፈጣሪም ጨክኖ አይወስዳትም በሚል ተስፋ ውስጥ ነበርኩ።
ከቀብር ቡሀላ ወደቤት ተመለስን።
እናቴ ሞታ አፈር አልበሰዋት መተው ግድ ሳይሰጣቸው ሆ ተመለሰች እንዴ እስክትሞት ነበር እንዴ የጠፋችው እያሉ በኔ የሚያሽሟጥጡት አበዛዛቸው ይሄ ነው ሚባል አደለም።
ደግነቱ ሜሪ ከኔጋ ነበረች።
ትናት የተሞሸረችዋ ጓደኛዬ ዛሬ ደሞ የሀዘን ልብሷን ለብሳ ሙሽርነቱ ደስታው ፌሽታው ቀርቶ ከኔውጋ ሆነ።
ትናት ግቢ ሄዳ ተረጋግታ እንዳትማር እንደዛ አስሬ እየተመላለሰች ችግሮቼን ስትፈታ ለራሷ ሳይኖራት ብር እየላከች እያለው እንደሌለው ሆና ተማረች።
ዛሬ ደሞ ደስታዬ ነው ብላ ሰርግ ደግሳ ብትሞሸር እናቴን አይኔን አጥቼ ደስታዋ ወደሀዘን ተቀየረ።
ሜሪ ከሰው ግርግር መሀል ወደመኝታ ቤት ይዛኝ ገብታ ትንሽ ምግብ ጉረሺ ካሎነ አንቺም ለልጅሽ መኖር አትችይም ስትለኝ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ያኔ ነበር ህላዌ ከጎረቤቴጋ መጥፋቷን ያስተዋልኩት

💔68❤28😱16👍6