ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
የአቤል መውደቅ ያስከተለው ከባድ ዝምታ ቢኖርም ይበልጥ ያሰጨነቀን ግን አባቱ ሲሰማ ምን ይል ይሆን የሚለው ነው።
የአቤል አባት አንባገነን፣ ቃሉ የማይታጠፍና በሰው ስሜት ላይ ጨካኝ የሆነ ኃይለኛ ሰው ነው።
እንደተፈራው የአቤልን መውደቅ እንደሰማ ቁጣውን መቆጣጠር አቃተው።
በቁጣ እየተንቀጠቀጠ ወደ እኛ መጣ።
አቤል ፊት ለፊት ሲጋፈጠው፣ አባቱ ለአንድም እንኳ አባትነቱ ሳይታወሰው፣ የአቤልን የተሰበረ ሞራል ይበልጥ የሚያደቅ አፀያፊ ቃል መናገር ጀመረ።
“አንተ ዲቃላና ሸርሙጣ እየሰበሰብክ ግቢዬን ከማርከስ ውጭ ምንም አትጠቅምም!” እያለ በቁጣ ጮኸ።
አቤል አንገቱን ደፍቶ ቆሟል።
አባቱ ግን አልበቃውም፤ ይበልጥ እየተቃረበው፣ “አንድ ልጅ ብወልድ እሱም የመከነ! አንተን የመሰለ ፈዛዛ እንዴት እወልዳለሁ?” እያለ ንቀቱንና ጥላቻውን በላዩ ላይ አፈሰሰው።
እነዚያ ቃላት ለአቤል ከውጤቱ በላይ የሚከብዱ፣ መላ ማንነቱን የሚያደቁ ነበሩ።
እኔና እቴቴ በድንጋጤና በሐዘን ደርቀን ቀረን።
አቤል የአባቱን ቃላት ሲሰማ ያቺ ሁልጊዜ ፊቱ ላይ የምትታየው ፈገግታ ጨርሶ ጠፋች፤ በምትኳ ግን በንዴትና በሐዘን ከንፈሩ ሲንቀጠቀጥ አየሁት።
የገዛ አባቱ እንዲህ ባለ ከባድ ቀን አጠገቡ መቆም ሲገባው፣ ይበልጥ እንደዚህ ሞራሉን ሲያወርደው ውስጡ የሚሰማውን ህመም መገመትም ከባድ ነው
አባቱ ያንን ሁሉ መርዝና አፀያፊ ቃል ተናግሮት ግቢውን ጥሎ ወጣ።
እኔ ግን ውስጤ በእንባና በቁጭት እየተቃጠለ ነበር።
አባቱ “ዲቃላና ሸርሙጣ እየሰበሰብክ ግቢያችንን አረከስክ” ሲል እኔንና ልጄን ማለቱ ነበር።
ገና ገዛሬው ገና በዚህ እድሜዋ ዲቃላ ሚለው ቃል ለልጄ ተሰጣት።
ወደፊት ደሞ በራሱ እየሰማች ማገናዘብ ስትጀምር ዲቃላ የሚለውን ቃል እየሰማች እየተሸማቀቀች ነው ምትኖረው?
እንባዬን ዋጥ አድርጌ ወደቤቴ ገባሁ።
ወደናቴ ቤት ሄጄ ብኖር ለካ ዲቃላ ይዛ ነው የጠፋችው ሚለው የሰፈር ሰው ወሬ ልጄን ሲያሸማቅቃት ነው ሚኖረው እዚህም ባሳድጋት እሷ ዲቃላ እኔ ደሞ.....እየተባልን መኖራችን ጨነቀኝ ምንድነው ማደርገው ምክንያቱም ይሄን ቃል ደግሜ ከሌላ ሰው ብሰማው ማበዴም ሚቀር አይመስለኝም።
ለልጄ አባት ሚሆናትን ሰው እንኳን ማግኘት ምችልበት አንዳች አጋጣሚ የለኝም ደግሜ ወንድን ልጅ አምኜ አፍቅሬ ምከተለው አይመስለኝም አላስበውምም
https://t.me/mane121921

❤96👍7🔥6💔5😡4🤷♀2🥰2🙊2🤔1
ህላዌ)✍️✍️ማኔ)
ያን ቀን እናቴ እኔጋ ስለምታድር መጣች።
ፊቴ ተቀያይሯል።
የተፈጠረ ነገር ካለ ጠየቀየችኝ ምንም እንደሌለ ነገርኳት።
ሜሪ ለእረፍት መጥታ ስለነበር እሷጋ ደውዬ ቤት እንድትመጣ አደረኩ።
ቤተክርስቲያን ብላ ነጠላዋን ለብሳ መጣች።
ማታ ቤት ቡና ጠጣን አቤልንም ጠርታ አወራችው እናቴም መከረችው ሁሊም ለበጎ ነው የሚለውን የተለመደ ተረት ይዘው አፅናኑት።
ማታ ሜሪ ሊቴድ ስትል ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን።
የተጨነኩበትን ነገርኳት።
የአቤል አባት በተናገረኝ አፀያፊ ቃል ውስጤ የተሰማኝን ህመም ነገርኳት። መፍትሄ ምትለው ነገር ካለ እንኳን ብታማክረኝ ብዬ ነበር።
ሳላስበው አለቀስኩ ገና ካሁኑ በልጄ ጉዳይ ስሜታዊ መሆን ጀምሬ ነበር።
ሜሪ እንደኔ ግራ ገብቷታል ምን እናድርግ ታዲያ አሁንኮ ህይወትሽ ውስጥ ሰው ቢኖር በቃ አግብተሽ እራሱ ወደናትሽ ቤት መመለስ ትችይ ነበር ግን በቃ ያለሽ አማራጭ ለምንም ነገር ግድ ሳይሰጥሽ ችላ ብለሽ ማለፍ ነው ነገ ሚመጣው አይታወቅም እግዚአብሔር ያውቃል አለችኝ።
ምንም እንኳን ቢመሽም እሷን ለመሸኘት ከግቢ ውጭ ወጣሁ ሀይሌ ሊወስዳት እኛ ሰፈር ቆሞ እየጠበቃት ነበር።
ከሲጋም ተገናኝተኝ ሰላም ተባባልንና ትንሽ አወራን።
እሷም በጣም መሽቶባት ስለነበር ሄዱ።
ሲሄዱ ከኋላቸው ቆሜ እያየኋቸው ነበር።
እንዴት በስስት እንደሚተያዩ እንዴት እንደሚያቅፋት እንደዛ መሽቶ ብርድ ላይ ቆሞ አውርተን እስክንጨርስ ጠብቆ በክብር ወደቤቷ ሊያደርሳት ይዟት እየሄደ እንደሆነ ሳይ ልቤ ደስ አለው ጓደኛዬ የውስጧን ንፁህነት አይቶ ፈጣሪ ሊክሳት የሰጣት ሰው እንደሆነ ተሰማኝ።
በሌላ በኩል ደሞ እኔ ድንገት ህይወቴ ውስጥ በገባው ሰው ዛሬንም ነገንም እያለቀስን ለመኖር እኔና ልጄ እንደተፈረደብን ተሰማኝ።
አንዴ ሆደ ባሻ ሆኜ የለ አለቀስኩ።
እንባዬን እየጠረኩ ወደግቢ ስገባ ጎረቤቴ ከነስካሩ ጋን ጋን እየሸተተ ባጠገቤ እልፍ አለኝ።
ምንም አላልኩትም ተከትዬው ገባሁ።
ድንገት ዞር አለና ከፊት ፊቴ ቆመ።
እኔ ምልሽ ማልቀስ አይሰለችሽም ቱሌ እኝኝኝኝኝ አረ ተይ ይሰለቻል አንዳንዴ ዋጥጥ ማድረግን ልመጂ እንጂ አለኝ።
መልስ አጣሁ ድንገት እናቴ ግቢ ውስጥ ቆሜ ከሱጋ ብታየኝ ምን እንደምትሆን አስቤ

❤51🔥1🤔1
አልፌው ሄድኩ እጄን ያዘኝና ነይ አንዴ ብሎ ወደውጭ ይዞኝ ወጣ።
እየውልሽ ሁልጊዜ አታልቅሽ አንዳንዴ የሚመጡብሽን ችግሮች በሳቅ ለመሸኘት ሞክሪ ካሎነ ደሞ ሁሌ ህይወትሽ መከራ ስቃይ ብቻ ከሆነብሽ ልመጅውና ኑሪ እንጂ ሁሌ ጡጦ እንደተቀማ ህፃን ልጅ አትነፋረቂ አለኝ።
አንዳንዴ ንዴት ከአቅማችሁ በላይ ሆኖ ልክ ብውው ብሎ ሊፈነዳ እንደሚተናነቅ አይነት ስሜት ተሰማኝ።
ቆይ አንተ ስለኔ ምን ታቃለህ ያለፍኩበትን የመጣሁበትን መንገድ ህይወቴን ታውቃለህ ?
እንደፈለኩ ብነፋረቅስ አንተን ምን ነክቼህ ነው አልኩት።
በእርግጥ ምንም አልነካሽኝም ግን ቤታችንን ያለው አንድ ግድግዳ ልዩነት ነው ጮክ ብለሽ ስትተነፍሺ እንኳን ይሰማኛል ስለዚህ ከገባሽ ጊዜ ጀምሮ ለቅሶ ነው ይሰማኛል ስታማሪሪ ስታለቅሺ እና ደስ አይልም አለኝ።
ምጮህበት ምተነፍስበት ነገር እየፈለኩ ነበር አደል ያ ሰው ደሞ ንዴቴን ለመወጣት ትክክለኛው ሰው እንደሆነ ተሰማኝ።
ትሰማኛለህ ባለቅስ ብጮህ መብቴ ነው እንባዬን ጥረግልኝ አላልኩህም።
ምን እንዳሳለፍኩ አታቅም ገባህ እንደጓደኞቼ መማር መጫወት በሚገባኝ እድሜዬ ላይ ድንገት ባፈቀርኩት ባመንኩት ሰው ተከድቼ ጨዋና ዝመተኛዋ ልጅ እርጉዝ ሆኜ ተገኘሁ ብቻዋን ያሳደገችኝ እናቴን ትቼ ተደብቄ እዚህ ጉድጓድ የመሰለ ቤት ውስጥ ልጄን ለመውለድ ተገደድኩ እእ የረሀብን ጥግ አየሁት ምግብ ፈልጎ ማጣት ህመሙ እስከምን እንደሆነ ተረዳሁ ከዛ ደሞ ልጄ ዛሬ በየሰው አፍ ዲቃላ እየተባለች ልትጠራ ነው እኔም ባንድ ቀን በደቂቃዎች ስተት ሸርሙ.. ናት እየተባልኩ ትንሹም ትልቁም ልክ እንደፃዲቅ ሰው አፉን እየከፈተብኝ ልኖር ነው ቆይ እኔ አላለቀስኩ እኔ አልተነፋረኩ ማን ያልቅስልኝ ብችልና ቢሆንልኝ በየቀኑ የቤቴ ጣራ ላይ እየወጣቱ ብጮህ ቅር አይለኝም ገባህ የኔ ለቅሶ ከደበረህ ከሰለቸህ ለቅሶ ወደሌለበት መሄድ ትችላለህ ብዬ እንባዬን ጠርጌ ወደግቢ ስገባ እናቴ ህላዌን አቅፋ ወደኔ እየመጣች አየኋት

❤111😭34😡10🤷♀5😐3
Forwarded from ሚተራሊዮን
ለጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ!
ገጣሚ ዓቢይ አለሙ፣ ማራኪ የሆኑ የግጥም ስራዎችን ያካተተበትን «ከአፈር ምን ይገኛል?» የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥም መድብል መጽሐፉን አሳትሞ ለገበያ ሊያወጣ ተዘጋጅቷል።
ይህ ስራ በይፋ ለንባብ ከመብቃቱ በፊት፣ አስቀድማችሁ በመግዛት (Pre-order) የጥበብ ስራውን እንድታበረታቱና ቀዳሚ አንባቢ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
📘 የመጽሐፉ ርዕስ፦ «ከአፈር ምን ይገኛል?»
💰 ዋጋ፦ 300 ብር ብቻ
የምትፈልጉ አነጋግሩኝ።!

ያው ሁላችሁንም በጣም ይቅርታ ትንሽ የግል ጉዳይ ገጥሞኝ ነው።
ino ባሁኑ ቆይቻለሁ የማንበብ ፍላጎታችሁም ጠፍቶ ይሆናል ታሪኩንም በስትክክል ለማስታወስ መቸገራችሁ አይቀርም ግን ያው ካቅሜ በላይ ስለሆነ አዘጋጅቼ ላቀርብላችሁ አልቻልኩም።
ከዛሬ ጀምሮ ተመልሻለሁ🙏

❤29🥰2🌚1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ምንም ላለማስነቃት ፈገግ አልኩኝ።
ሜሪኮ በወሬ ይዛኝ ነው ይቅርታ ቆየሁ አደል ብዬ ወደውስጥ ይዣቸው ገባሁ።
ጎረቤቴ ያን ቀን እንደዛ ካወራን ቡሀላ ከእይታዬም ተሰወረ ሲወጣ ሲገባ አደለም ድምፁ ትንፋሹም ጠፋ።
የልጄ አንድ አመት ደረሰ።
እናቴ ልደት ካልደገስን አለች።
እኔ በፍፁም አልኩኝ።
ባልታሰበ ሁኔታ ሀይሌና ሜሪ ኬክ አስጋግረው ልብስ ገዝተው መጡ።
አከበርንላት።
እነ ሜሪ ተመልሰው ወደግቢ ሄዱ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆነው ነበር።
የኔው ምስኪኑ አቤል እድል ስትሰፈር እሱ እንዴት ቢዘለል ነው ብዬ እስከገረም ድረስ ነገሮች አልሳካ አሉት።
የህላዌ ልደት ቀን ሜሪና ሀይሌ ልብስና ኬክ ይዘው ሲመጡ እሱ ባዶ እጁን በመሆኑና ምንም ባለመግዛቱ ተሸማቆ ከበር ስር ዱካ ላይ ቁጭ ብሎ ላለማልቀስ ከራሱጋ እየታገለ እንደነበር ያስተዋልኩት እኔ ብቻ ነበርኩ።
ኮሌጅ ለመማር አቅም የለው።
በዘመድ ስራ አይገባ ሚጠይቃቸው ዘመድ የላቸው በሰው በሰው ስራ ፈልጎ በገባ ወር ሳይሞላው ወይ ያባሩሩታል ወይ ደሞ የጀመሩት ስራ ይቋረጣል።
በዛ ላይ በገባ በወጣ ቁጥር አንተ ሸክም ነህ አንተ አትጠቅምም አንተ ተዘፍዝፈህ ብላ አንተ የወንድ አልጫ እየተባለ ካባቱ የሚሰነዘሩ ስድብና መንቋሸሾች አሉ።
የሰፈር ሰው ወይ አይማር ወይ አይሰራ በዚህ ድህነት ላይ ተቀምጦ ይውላል ብለው ያፌዙበታል።
ማንም የሱን የውስጡን ጭንቀት አያውቅም።
ማንም አቤል እያሳለፈ ያለውን ህመምና ስቃይ አይረዳም ማንም እሱ ከልቡ እንኳን ስቆ ተደስቶ እንደማያውቅ አያስተውልም ሁሉም ሰው ከላይ አይቶ ይታዘባል ከላይ አይቶ ይፈርዳል።
የሆነ ቀን ቁጭ ብለን እያወራን እኔም ስራ መስራት እንዳለብኝ እያወራሁ ነበር።
እቴቴ በመሀል አይ ልጄ እናትሽን ያቆይልሽ እንጂ ወተሽ ስሪ መስራት አይከፋም ገንዘብን ሰርተሽ አምጥተሽ ስታጠፊው ነው ጣእሙን ምታቂው አለችኝ።
በዛ መሀል ነበር እኔ ምልሽ እቴቴ ግንኮ አንቺም ትሰሪያለሽ የቤት ኪራዩም አነሰም በዛም ትንሽ ብር አለው ታዲያ እንዴት ነው ማይበቃሽ አልኳት አይ ልጄ ታሪኩ ብዙ ነው ብላ አጫወተችኝ።
አባትየው እንደአባት ሀላፊነት ወስዶ ማኖር ሲገባው የቤት ኪራዩን ብር እንኳን እየተቀበለ እንደሚወስድ ያ ግን የቤተሰባቸው ሚስጥር እንደሆነ የቤቱን ሙሉ ነገር ሚያሟሉት እሷ ሰርታ ባመጣችውና ከስንት አንዴ በሚተውላት የቤት ኪራይ ብር እንደሆነ ነገረችኝ።

❤60🥰7👏2🤔1💯1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አሳዘኑኝ።
ሴት ልጅ መርጣ ምትገባበት ህይወት የሷን እጣ ፈንታ ብቻ አደለም የልጇቿንም ይወስናል።
እኔም ስራ መግባት እንዳለብኝ ከሜሪም ከእናቴምጋ አውርተን ወሰንን።
የመጀመሪያ ስራዬን ለመፈለግ ወጥቼ የሴቶች ልብስ ቤት ሴልስ ሆኜ ተቀጠርኩ እናቴ ተያዥ ሆናልኝ ነበር።
ግን ደሞ ጠዋት ሁለት ሰአት ስራ ቦታ ገብቼ ማታ ሁለት ሰአት ነው ምወጣው።
ሶስት ቀን እንደምንም ለመቻል ሞከርኩ ግን አቃተኝ ልጄ እየናፈቀችኝ ከሰዎችጋ አውርቶ መግባባት እስኪያቅተኝ ድረስ ነበር ሚያነጫነጨኝ ።
ጭንቅላቴ ብዙ ነገር ያስባል።
ከእናቴ እጅ ላይ አምልጣ ብትወድቅስ ቢርባትስ ወደ ውጭ ብትወጣስ አስሬ እደውላለሁ እናቴ ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች ብላ ሰድቢ ትዘጋብኛለች።
አራተኛው ቀን ላይ ስራ ለመሄድ ወጥቼ ግን ሰዎቹን አመስግኜ ስራውን ለቅቄ ወደቤት ተመለስኩ።
ለልጄ ደና ህይወት መስጠት እፈልጋለሁ ግን ደሞ ካጠገቤ እንድትርቅ አልፈልግም ።
ታሳሳኛለች ውጭ ከወጣሁ ዝም ብዬ እያሰብኳት እንባዬ ይመጣል።
እየተጫወተች ስትስቅ አይ ምስኪን ምስቅልቅል ውስጥ መሆኗንኮ አታቅም እላለሁ።
ስህተቴን እንዳልወቅሰው ሚያደርገኝ አይኗን ማየት ነው።
አቤልን ሌት ተቀን የማመሰግነው ያኔ የተናገረኝ ንግግር ምን ያህል ውሳኔ ላይ እንደረዳኝ ስለማውቅ ነው።
ማታ ማታ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ እናቴ ከሌለችና ልጄ ከተኛች ሜሪጋ እደውልና ምን መስራት እንዳለብኝ ምን ብሰራ እንደሚሻል አወራታለሁ ግን መፍትሄ አላገኘሁም ነበር።
በዛ ሰሞን ላይ ድምፁ ጠፍቶ የነበረው ጎረቤቴ ተመልሶ ብቅ አለ።
ጠዋት ላይ እስክነሳ ጠብቆ እኔ ስራ ላስቀጥርሽ አለኝ

👍66❤59👏7🥰3🫡3😡3
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
መጀመሪያ ላይ ግራ ተጋብቼ የምን ስራ ብዬ ኩስትር አልኩበት።
ክፍለ ከተማ ውስጥ ፅዳትና ተላላኪ ሆነሽ መስራት ነው።
ከዛ እስከ ግማሽ ቀን እየሰራሽ አሪፍ ጥቅማ ጥቅሞች ታገኛለሽ አለኝ።
ተስማማሁ ስራ ጀመርኩ።
ያገኘኋትን በተቻለ መጠን ለራሴም ለአቤልም ለእቴቴም ብዙም ባይሆን እንደቤተሰብ ለማብቃቃት እሞክራለሁ።
ለኔ የወር ትልቁ ወጪዬ ግን የልጅ ልብስ ነው መንገድ ላይ ያየሁት የህፃን ልብስ ለልጄ ካልገዛሁላት ብዬ ድርቅ እላለሁ።
አቤልም በዛ መሀል ግቢ ካሉ ተከራዮችጋ እየሄደ ቀን ስራ መስራት ብሎኬት እየተሸከመ ማመላለስ ጀመረ።
ህይወትን አንድ እስቴፕ በመራመጃው ሰአት ወደታች ገፋችው ከአባቱ እኩዮችና ከተከራዮቹጋ መግባትና መውጣት ሆነ ስራው።
እንደዛ እንደዛ እያልን ለ7 ወር ያህል ስራውን ከሰራሁ ቡሀላ አቆምኩት።
ልጄን ለማሳደግ አንገቴን ደፍቼ ሰርቼ መግባት በምፈልግበት ሰአት ሴት በመሆኔ ብቻ የሚተናኮሰኝ ሰው በዛ።
ዝቅ ብዬ ፅዳት እየሰራሁ ወንበር ላይ ተዘፍዝፎ የሚውለው ሆዱ ሞልቶ ጭንቅላቱ የተራበ ሰው ይነሳና ይዤሽ ልደር ይላል።
ከአንዱ ስሸሽ አንዱ ካንዱ ስሸሽ አንዱ መረረኝ።
የመጣው ይምጣ ብዬ ስራውን አቆምኩት።
እናቴ ከጎኔ መሆኗ በየትኛውም ሰአት አብራኝ መገኘቷ የቤት ኪራይ ብር በየወሩ ማግኘታችን ቢያንስ ትንሽም ብትሆን ነፃነት ሰቶኝ ነበር።
ልጄ እማ እማ ብላ መጣራት ጀምራ ነበር።
ቤት ስገባ ተንሰፍስፋ ፍንድቅ እያለች ትጠብቀኛለች።
ውጭ ቆይቼ ወደቤት እስክሄድ አያደርሰኝም እቸኩላለሁ እስካያት እስክስማት እስካቅፋት እጓጓለሁ ህይወቴ ላይ በየቀኑ አዲስ ነገር አለ እሱም እሷ ናት።
የልጄ ሁለተኛ አመት ደረሰ።
አከበርንላት እንደነገሩ።
እንደሁል ጊዜው ከኔ ማትለየው የምደገፋት ጓደኛዬ ሜሪ የምትችለውን ሳይሆን ከአቅሟ በላይ የሆነ ነገር ነበር ያደረገችላት።
ሜሪና ሀይሌ የሶስተኛ አመት ተመራቂ ተማሪ ሆነው ወደግቢ ተመለሱ።
ያኔ ነበር ልክ እንደተመረቁ ቀለል ያለ ፕሮግራም አድርገው ቀጥታ ወደትዳር ለመግባት እንደወሰኑ የነገረችኝ።
ለሷ ደስ አለኝ።
ጓደኛዬ ልታገባ ነው።
ትናት እንደቀልድ እኔን ለማጣበስ የገባችበት ህይወት ዛሬ ትዳር ሊሆናል በደስታ ህይወቷን ምትጨርስበት ህይወት ሊሆናት ተቃርቧል።

❤68🔥2👍1👏1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
እኔም ህይወት ግራ እንዳጋባችኝ ቋሚ ነገር ሳልይዝ ጊዜው እየሄደ ነበር።
የሰላም እንቅልፍ መተኛት የተረጋጋ ህይወት መኖር እፈልጋለሁ።
ግን ደም በብዙ ሀሳብ ጭንቅላቴ እየናወዘ እራስ ምታትና ድብርታ የየእለት ተግባሬ ሆነው ነበር።
በዛ መሀል ድራማ የማያልቅበት ውዱ ጎረቤት በድጋሜ ስራ ሊያስገባኝ ነገረኝ።
ድምፁና ድራሹ ጠፍቶ የቆየው ጎረቤቴ ድንገት ብቅ ብሎ የችግር መፍትሄ ፈቺ ካሎንኩ ሚለው ነገር አለ።
ያኔም አንድ ቤት ውስጥ ጠዋት ገብቼ ቤቱን አፅድቼ ምግብ ሰርቼ አሰቀምጬ በጨረስኩ ሰአት የምወጣበት ስራ አገኘልኝ።
የሰአት ገደብ የለውሞ በዚህ ሰአት ግቢ በዚህ ሰአት ውጭ የሚባል ነገር የለም።
በጨረስኩበት ሰአት መውጣት በደረስኩበት ሰአት መግባት እችላለሁ።
ደሞዜን ቅድሚያ ሰቶኝ ስራውን ጀመርኩ።
ፅድት ያለ ቤት ነው።
ሰው አይኖርበት።
አንድ ክፍል ኪችን ለብቻው አለው።
በስራት የተዘጋጀ ጠረጴዛ ሶፋ አለ።
የምግብ እቃዎች በሙሉ ተሰናድተዋል።
የመጀመሪያ ቀን ስጀምር ትንሽ ፍርሀት ተሰምቶኝ ነበርና ለሜሪ ሁሉንም ነገር ነግሪያት ነው የሄድኩት።
አብረን ሄድን ስራሽን ጀምሪ አለኝ።
ምኑን ላፅዳው ምኑን ልጠበው ቤቱ በራሱ ፅድት ፍክት ያለ ነው።
የመጀመሪያ ቀን ገብቼ ምግብ ሰራርቼ እስክወጣ ቁጭ ብሎ ጠበቀኝ።
ምግቡን እየሰራሁ የነበረኝ ፍርሀት እኔ ነበርኩ የማቀው መቼ ከኋላዬ መጥቶ ያዘኝ እያልኩ ስሳቀቅ ነበር።
ስጨርስ ጨርሻለሁ ልሄድ ነው አልኩት።
መሄድ ትችያለሽ በሩ በሱጋ ነው አለኝ።
ጫማዬን አደራርጌ ስወጣ አየር ላይ በራሪ የመሰለች ሙልቅቅቅ ያለች ልጅ በሩን ለመክፈት እየታገለች አይን ለአይን ተገጣጠምን።
ሰላም ነው እናቴ ጨረሽ ልቴጅ ነው ብላ አልፋኝ ገባችና ጉንጩን ስማው አቅፋው ቁጭ አለች
(እንደው ይሄንን ነገር በድምፅም ቢሆን እንጨርሰውና እናንተም እኔም ግልግል እንበል መሰለኝ)

❤181👍16🥰15😡14👏2😱1
ሰላም ለእናንተ ይሁን🤗
ሁላችሁንም በጣም ይቅርታ እየጠየኩ ከሀምሌ 1_30 በስራ ምክንያት እዚህ አልነበርኩም እና የጠፋሁት ለዛ
ለጠየቃችሁኝ inbox ለፃፋችሁልኝ ደህንነቴ ላሳሰባችሁ ሰዎች በሙሉ እግዚአብሔር በብዙ ያክብርልኝ።
በዚህ ዘመን ጠያቂ ሰው ማግኘት መታደል ነው።
ታሪኩን እቀጥልላችኋለሁ የረሳችሁት ሰዎች ተመልሳችሁ ማንበብ ሳይኖርባችሁ አይቀርም😀
inbox ላልመለስኩላችሁ በሙሉ ይቅርታ🙏

❤72😡13🤔12👍2👏2🥰1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
እኔም ህይወት ግራ እንዳጋባችኝ ቋሚ ነገር ሳልይዝ ጊዜው እየሄደ ነበር።
የሰላም እንቅልፍ መተኛት የተረጋጋ ህይወት መኖር እፈልጋለሁ።
ግን ደም በብዙ ሀሳብ ጭንቅላቴ እየናወዘ እራስ ምታትና ድብርታ የየእለት ተግባሬ ሆነው ነበር።
በዛ መሀል ድራማ የማያልቅበት ውዱ ጎረቤት በድጋሜ ስራ ሊያስገባኝ ነገረኝ።
ድምፁና ድራሹ ጠፍቶ የቆየው ጎረቤቴ ድንገት ብቅ ብሎ የችግር መፍትሄ ፈቺ ካሎንኩ ሚለው ነገር አለ።
ያኔም አንድ ቤት ውስጥ ጠዋት ገብቼ ቤቱን አፅድቼ ምግብ ሰርቼ አሰቀምጬ በጨረስኩ ሰአት የምወጣበት ስራ አገኘልኝ።
የሰአት ገደብ የለውሞ በዚህ ሰአት ግቢ በዚህ ሰአት ውጭ የሚባል ነገር የለም።
በጨረስኩበት ሰአት መውጣት በደረስኩበት ሰአት መግባት እችላለሁ።
ደሞዜን ቅድሚያ ሰቶኝ ስራውን ጀመርኩ።
ፅድት ያለ ቤት ነው።
ሰው አይኖርበት።
አንድ ክፍል ኪችን ለብቻው አለው።
በስራት የተዘጋጀ ጠረጴዛ ሶፋ አለ።
የምግብ እቃዎች በሙሉ ተሰናድተዋል።
የመጀመሪያ ቀን ስጀምር ትንሽ ፍርሀት ተሰምቶኝ ነበርና ለሜሪ ሁሉንም ነገር ነግሪያት ነው የሄድኩት።
አብረን ሄድን ስራሽን ጀምሪ አለኝ።
ምኑን ላፅዳው ምኑን ልጠበው ቤቱ በራሱ ፅድት ፍክት ያለ ነው።
የመጀመሪያ ቀን ገብቼ ምግብ ሰራርቼ እስክወጣ ቁጭ ብሎ ጠበቀኝ።
ምግቡን እየሰራሁ የነበረኝ ፍርሀት እኔ ነበርኩ የማቀው መቼ ከኋላዬ መጥቶ ያዘኝ እያልኩ ስሳቀቅ ነበር።
ስጨርስ ጨርሻለሁ ልሄድ ነው አልኩት።
መሄድ ትችያለሽ በሩ በሱጋ ነው አለኝ።
ጫማዬን አደራርጌ ስወጣ አየር ላይ በራሪ የመሰለች ሙልቅቅቅ ያለች ልጅ በሩን ለመክፈት እየታገለች አይን ለአይን ተገጣጠምን።
ሰላም ነው እናቴ ጨረሽ ልቴጅ ነው ብላ አልፋኝ ገባችና ጉንጩን ስማው አቅፋው ቁጭ አለች
(ለረሳችሁት ሰዎች

❤45🤯9💔1
ህላዌ (✍️✍️ ማኔ)
ለምን በዛ ልክ እንደደነገጥኩ አላቅም ግን ድንጋጤዬ በግልፅ ፊቴ ላይ ይታይ ነበር።
ዞር ብዬ ሳያቸው እኔን ቼክም አላደረጉኝም ዝም ብዬ ወደቤቴ ሄድኩ።
ቤት ስደርስ እናቴ ከት ብላ እየሳቀች ደረስኩ።
ህላዌን አየኋት ጧ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል።
ደነገጥኩና አየኋት።
ከማንጋ ነው ምትስቂው አልኳት ድንግጥ አለችና ቅድምኮ ህላዌ አልተኛ ብላኝ ስንሯሯጥ የነበረው ነገር ትዝ ብሎኝ ነው አለችኝ።
ሁኔታዋ ግራ አጋብቶኝ ምግብ ለመብላት እየተዘገጃጀን ድንገት እቴቴ ወይኔ ልጄ እያለች ስትጮህ ሰማኋትና ደንግጬ እየሮጥኩ ወጣሁ።
ምን እንደተፈጠረ ጠየኳት አቤል ከፎቅ ወደቀ ልጄ ወደቀ በቃ አይተርፍም ልጄ ወደቀ እያለች ወደውጭ ስትሮጥ በደመነፍስ ተከተልኳት ።
አቤል ቀን ስራ ከሚሰራበት ቅርብ ቦታ ወደነበረ ጤና ጣቢያ ወስደውት ነበር።
እዛ ደረስን።
ስንደርስ ከደረጃ ተንሸራቶ ነው የወደቀው ብዙም አልጎዳም ግን ጀርባው አካባቢ ትንሽ ስብራት ነገር ሳያጋጥመው አይቀርም በደንብ መታየትና ቼክ መደረግ አለበት አለን ዶክተሩ።
እኔም ጎረቤቴ ቅድሚያ የሰጠኝን ብር በሙሉ ለእቴቴ ሰጥቻት እንዲታከም አደረግን።
በዛ መሀል ለሶስት ቀን ጎረቤቴጋ ሳልሄድ ቀረሁ።
ማታ እስኪመጣ ጠብቄው ይቅርታ አቤል ታሞ ነው ያልመጣሁት ነገ ወደስራዬ እመለሳለሁ አልኩት።
አንቺ ፈጣሪ አደለሽምኮ የሁሉም ሰው ህይወት ውስጥ ጣልቃ እየገባሽ አክተር ለመሆን ምትሞክሪው ነገር ደስ አይልም አለኝ።
መልስ ሳልሰጠው ወደቤቴ ገባሁ።
አቤል ከቀን ስራው አቅም መስራት አልቻለም።
ምሽቱን በጣም እንዳይከፋው ቤት ሄድኩና ከህላዌጋ እንዲጫወት አደረኩት።
ህላዌ እንቅልፍ ወሰዳት በደረቱ እንደተኛ እኔ ምልሽ ቅድስቴ አንዳንዴ እግዚአብሔር የማያውቀው ሰው አለ እንዴ? አለኝ።
ግራ ገባኝ ማለት አልኩት።
ማለቴ እድል የሚባል ነገር አለ እንበል እድል የሚባለውን ነገር የሚሰጠው እግዜር ነው አደል ታዲያ ለአንዳንዱ ብዙ ሰጥቶ ለኔ ጥቂት እንኳን እንዴት አልሰጠኝም አሁንስ ነገሮች እንዲህ ሲበላሹብኝ እንዲህ ሲያስጨንቁኝ እንዲህ ከስር ከስር የነካሁት የሞከርኩት ሁሉ ሲበላሽ አላሳዝነውም ወይስ አያውቀኝም ቢያወቀኝማ አደለም ለሱ ሴጣንም ቢሆን ሁኔታዬን አይቶ ይራራልኝ ነበር አለኝ የሚፈሰውን እንባውን በለበሰው ብርድ ልብስ እየጠረገ።
አሳዘነኝ ግን እንዴት ማፅናናት እንዳለብኝ ምን ማለት እንደምችልም ስለማላውቅ ዝም አልኩት።
አይኑን ጨፍኖ ዝም አለኝ።
በተጨፈነው አይኑ ውስጥ ሚወርዱትን እንባውን ሳይ አሳዘነኝ ውስጤ ተላወሰ ተነስቼ ወደቤቴ ገባሁና ህላዌን አስተኝቼ ካጠገቧ ቁጭ አልኩና ሜሪጋ ደወልኩ።
አወራኋት ስለ አቤል ነገርኳት ምን ያህል እንዳሳዘነኝ ያለኝን ብር ለህክምና እንደሰጠሁት ሁሉንም አወራኋት እሷ አዳምጣኝ ስትጨርስ አይዟችሁ እግዚአብሔር አለ ብላኝ ስልኩ ተቋረጠ።
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ትንሽ አርፍጄ ነበር።
እናቴም ሳትመጣ ቀረች።
ደወልኩላት።
መጣሁ ለህላዌ ቁርስ እየገዛዛሁ ነው አለችኝ።
እሷ እስክትመጣ እኔ ልብሴን ለባብሼ ጨረስኩ።
ልክ ስትመጣልኝ ተነስቼ ወጣሁና ወደጎረቤቴ ቤት ለመሄድ ወጣሁ።
ደረስኩ።
ስገባ ሶፋ ላይ በጀርባው ተኝቶ ኮምፒውተር ላይ አፍጥጧል።
ይቅርታ አረፈድኩኝ አደል አልኩት።
መልስ አልሰጠኝም ቅንድቡን ሰቅሎ ተመለከተኝ ።
መልስ አልጠበኩም ቀጥታ ወደኪችኑ ገባሁ።
ምግብ ለመስራት እቃውን ክፍትፍት ሳደርገው።
ባለፈው ሰርቼ ያስቀመጥኩት ምግብ ሳይነካ ተበላሽቶ ቁጭ ብሏል።
ደነጥኩ
ይጨመር👍

👍41❤33🤔2
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ወደሱጋ ወጣሁና ይቅርታ ምግቡኮ አልነካም ተበላሽቷል ምን ሆኖባችሁ ነው ምን አጊታችሁበት ነው አልኩት።
ምንም አላገኘንበትም ምን እንደሰራሽ እራሱ ያየው የለም እሱን ድፊና አዲስ ሰርተሽ ሂጂ አለኝ።
ተናደድኩ።
እኔ ምግብ አልደፋም ሰው ይሄንን አጥቶ አደል እንዴ ሚንከራተተው ሲጀመር ካልበላችሁት ለምን ስሪ አላችሁኝ አልኩት።
ዝም አለኝ።
ንቀቱ እስከምን ድረስ እንደሆነም አላቅም ችግሩ ከኔ ይሁን ወይ ተፈጥሮው አላቅም።
ህይወቱ ምን እንደሆነም ለኔ ግልፅ አደለም ሚኖረው እንዴት እንደሆነም አይገባኝም።
ድራማው ይሰለቻል።
እኔ እዛ ቤት ውስጥ ምንም አፌን የመክፈት ስልጣን እንደሌለኝ ስለማውቅ ሶፋ ላይ ያስቀመጥኩትን ስልኬን ብድግ አድርጌ ልወጣ ስል.
በዚህ ድህነትና ሀላፊነት ላይ ይሄ ጥጋብ ተጨምሮበት ህይወትሽን እንዴት ልትገፊው ባክሽ አለኝ።
ዝም ብዬው ቤቱን ትቼ ወጣሁ።
መንገድ ለመንገድ እንደእብድ ብቻዬን እየለፈለፍኩ ቤት ደረስኩ።
መጀመሪያ አቤልጋ ገባሁና እኔ ምልህ አብሮ የረገመን ሰው አለ እንዴ ሰርተን ብር ማግኘት ወደተሻለ ነገር መጠጋት አልቻልንምኮ አልኩት።
ዝም ብሎ አየኝና ይኖር ይሆን እንዴ አለኝ።
ንግግሩ ያስታውቃል ሰልችቶታል አስጠልቶታል ድክምም ብሎታል።
ይልቅ ምግብ ካለ ስጭኝ ማታ አሞኝ ሳልበላ አድሬ አሁን እማ እስክትመጣ እራበኝ አለ።
ውስጤ ስፍስፍ አለ።
ወደቤት ገብቼ እናቴ ለኔ ያዘጋጀችውን ምግብ በሰሀን አስደርጌ ይዤለት ሄድኩና እያጎረስኩት አብረን በላን።
ደስ እንዲለው እነሱጋ ቡና አቀራርበን እቴቴም እስክትመጣ ጠብቀናትና ሰብሰብ ብለን ቡና ጠጣን።
በሰአቱ ፈገግ እንድንል ምታደርገን ህላዌ ነበረች ንግግሮቿ ተግባሮቿ እየተኮላተፈች ምታወጣው ቃሎቶች የሰውን መንፈስ የሚያድሱ ናቸው።
ሁላችንም አይናችን እሷ ላይ ነው።
ፈልገንም ይሁን ሳንፈልግ ፈገግ ታሰኘናለች እንኳንም ወለድኳት እላለሁ ያን ጊዜ
አሁንስ ? ይጨመር ወይ?

👍56❤28
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ማታ መሸ።
እናቴም እኔጋ አላደረችም ነበር።
ህላዌም ተኝታ ስለነበር በሀሳብ ምስጥ ብዬ ጣራ ጣራን እያየሁ በሬ ተንኳኳ።
ማነው አልኩኝ።
እኔ ነኝ አንዴ ላወራሽ ነው አለኝ።
ጎረቤቴ ነበር።
በሩን ከፈትኩለት ይቅርታ ልግባ አለኝ
አፉ ጋን ጋን ይሸታል።
አይ አይቻልም አልኩት።
ሳቅ አለ የንቀት እያየኝ።
ጠዋት ልክ አልሰራሁም ይቅርታ ለተናገርኩሽ ነገር እና ያው ስራሽን ቀጥይ ሰሞኑን እህቴ ከፍቅረኛዋጋ ከከተማ ወጥታ ስለነበር ነው ምግቡ ያልተበላው እንጂ ካሁን ቡሀላ እነሱም ስለተመለሱ በስርአት እንበላዋለን አለኝ።
በተራዬ ዝም አልኩት።
በውስጤ ያቺ ያየኋት እህቱ ናት ብዬ ከራሴጋ እያወራሁ ነበር።
እና ደሞ ትናት ከጓደኛሽጋ ስታወሪ ሰምቼሻለሁ ስለዚህ ለአከራይሽ የሰጠሽውን ብር እንኪ እንቢ እንዳትይኝ ምትክ ነው አለኝ።
እሺ ብዬ ተቀበልኩትና እንደቆመ በሩን ዘግቼበት ገብቼ ቁጭ አልኩ።
ነገረ ስራዬ ለራሴም አሳቀኝና ግራ ተጋባሁ::
ጠዋት ለእናቴ ግማሹን ብረ ቁጭ አድርጌላት ለፈገችው ነገር እንድታጠፋው ነግሪያት እኔ ወደስራዬ ሄድኩ።
መንገዱ ላይ እንደ እብድ እየተብሰለሰልኩ ነበር።
ስደርስ በር ሳንኳኳ ግቢ አለኝ።
ገባሁ።
ሰላም አደርክ ብዬ ስልኬን አስቀምጬ ወደኪችን ገባሁ።
ደና አደርሽ አለኝ።
ስገባ ድስቶቹ ተጣጥበው ፅድት ብለው ተቀምጠዋል በውስጤ ፈገግ አልኩና መሰራራት ጀመርኩ።
በመሀል ስልኬ ጠርቶ ዞር ስል ተመስጦ እያየኝ አይን ለአይን ተጋጨን ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ኮምፒውተሪ ጎንበስ አለ።
እናቴ ነበረች በሰጠኋት ብር ከህላዌጋ ወተው ለሷ ሚያምር ልብስ እየገዛችላት እንደሆነ ነገረችኝ ።
ደስ እንዳላችሁ ስራ ስጨርስ እደውላለሁ ብያት ስልኩን ዘግቼ ወደስራዬ ተመለስኩ።
ጎረቤቴ ያ የትዝታ ዘፈን የመክፈት አባዜው እዛም ቤት መጥቶ የትዝታ ዘፈን ከፍቶ እየሰማ ነበር ስራውን ሚሰራው።
እኔም በዘፈኑ ምስጥ ብዬ እየሰራራሁ።
በሩ ተከፈተ ስገባ ሳልቆልፍ ዝም ብዬ ዘግቼው ነበር የገባሁት።
እህቱ ናት ሸበላዬ መጣሁልህ ብላ እየሳቀች ወደውስጥ ገባች።
ዞር ብዬ አየኋት።
አብሯት ሌላ ሰው አለ።
እ ብሮ እንዴት ነህ ተባብለው ሰላምታ ተቀያየሩ ከጎረቤትጋ።
በዛ መሀል ልጅቷ ወደኔ መጣችና እናቴ እንዴት ነሽ አለችኝ።
ደና ነኝ ብዬ ሰላምታ ለመስጠት ወደሷ ተጠጋሁ ሰላም ብላ አቀፈችኝ በሷ ትከሸ አሻግሬ አብሯት የመጣውን ሰው አየሁት ውስጤ ለሁለት ሲከፈል ታወቀኝ ፊቱ አዲስ አልሆነብኝም እጄ መንቀጥቀጥ ሲጀምር ልጅቷን ለቀቅ አድርጊያት ፊቴን አዞርኩ እእ ያቢሻ ሻወር ትወስዳህ? አለችው
በልቤ አዎ ያብስራ ነው እራሱ ነው አልኩ.....
love you......❤

😱122❤39🙊1
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
እጄም እግሬም እየተቀጠቀጠ ስለነበር ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ።
ስራውን እረስቼው የሚያወሩትን ለመስማት ጆሮዬን ወደነሱ ላኩት የሆነ ነገር የምር ተፈጥሮ ግን ማመን ስለማንፈልግ ነገሩን በጥርጣሬ መያዝ አለ አደል እሱ ስሜት ተሰማኝ።
የኔ ፍቅር በቃ እሺ ወደስራችን እንግባ ወንድሜ ቀጥል አለች።
እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ቅድስቴ አትቃዢ ቆይ ተረጋጊ ስራሽን ጨርሺና ሹልክ ብለሽ ውጭ እሱ አደለም ተመሳስሎብሽ ነው።
አታይም እንዴት እንደወፈረ አታይም ምን እንዳከለ በዚች ጊዜ ውስጥኮ እንደዚህ አይቀየርም ስም ያለው ሞኝ ነው ሆነሽ ነው ተረጋጊ ብዬ እራሴን አረጋጋሁና ስራዬን ጨረስኩ።
የስራው ዋናው ጎረቤቴ ሲሆን ልጁና ልጅቷ ደሞ የስራውን ዝርዝር ተረጂዎች ናቸው።
የሚንቀጠቀጠውን ጉልበቴን እንደምንም አረጋግቼ ለመውጣት ምትታገለኝን ልቤን አፍኜ ይዤ ስራዬን ብጨርስም እዛው ኪችን ውስጥ ቆምኩኝ።
በቃ ምንም አልሰማሁም አላየውሁም በቃ ቅድስት ተረጋጊ ብዬ ያለኝን ድፍረት አሰባሰቤ ወደነሱ ተመለስኩና ስልኬን አንስቼ አንገቴን እንደደፋሁ ልወጣ ስል እእ ልቴጂ ነው አለችኝ እህቱ።
አዎ አልኳት አቀርቅሬ።
እሺ የትራንስፖርት ብር ይዘሻል እንኪ አለችኝ ከቦርሳዋ አውጥታ አይ አመሰግናለሁ አለኝ ብያት ቀና አልኩኝ ወደነሱ ሶስቱም አይናቸው እኔ ላይ የኔ አይን ደሞ ያብስራ ላይ አረፈ።
እራሱ ነው ።
ያብስራ ነው።
አሁንም ዝም ሲል የተኮሳተረ ሚመስለው እራሱ ነው።
ሰዎችን ሲመለከት እኔ ማቀው አስተያየቱ እራሱ እሱ ነው።
ኦያየሁት እሱ የተገኘበትን ቦታና እኔ ያለሁበትን ቦታ አይቼ የዛን ቀን ያለኝን በሱ ምክንያት ያሳለፍኩትን ሁሉም ሀሳቦች ባንዴ እኩል ሰአት ጭንቅላቴ ውስጥ መተው አቃጨሉ
ጭንቅላቴ ጭጭጭጭ በሚል ድምፅ ሲሞላ ትዝ ይለኛል ከዛ ምን እንደተፈጠረ አላቅም እራሴን ስቼ እዛው ፊት ለፊታቸው ወደኩ

❤80💔13😡1
tiktok.com/@mane.shopping
ሰዎች አዲስ የስራ አካውንት ከፍቻለሁ እና ገና 0 followers ብቻ ነው ያለው ግዴታ 1000 ሰው ያስፈልገኛል
please support me

👍14❤2
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
ስነቃ ምን እንደተፈጠረ አላቅም ግን እዛው ሶፋ ላይ አስተኝተውኝ ጎረቤቴና እህቱ በድንጋጤ ውሰጥ እያዩኝ ነበር።
ብድግ አልኩኝ እህቱ በስርአት ተነፈሰች ምን ሆነሽ ነው አስደነገጥሽኝኮ በሽታ ነገር አለብሽ ወይስ ምንድነው አለችኝ።
ወደ በሩ ዞር ስል ያብስራ እጁን በደረት አድርጎ ጅንን ብሎ ቆሞ ነበር እንደ አክተር እያደረገው ነበር።
አለቀስኩ በትንሹ አደለም ስቅስቅ ብዬ ጉልበቴ ላይ ድፍት ብዬ አለቀስኩ።
ስለክብሬም ስለምኔም አልተጨነኩም ውስጤ ያለው እልህ ይባስ እየተናነቀኝ እያፈነኝ ነበር።
እህቱ በጣም ግራ ተጋብታ አረ ምን ሆነሻል አረ በጌታ እያለች ስፍስፍ ብላ አባባበለችኝ።
ጎረቤቴ ልማዷ ነው ደሞ ጀመራት በሚል አስተያየት ነበር ሲያየኝ የነበረው።
ትንሸ ካለቀስኩ ቡሀላ እንባዬን ጠራርጌ ይቅርታ ጠይቄ ለመውጣት ስነሳ እህቱ ብቻሽን ላውራሽ አለችኝ።
እነሱ ወጡ እኛ ቤት ተቀመጥን።
በናትሽ የሆንሽውን ንገሪኝ እኔ እንደዚህ አይነት ጭንቀት ምናምን አልችልም የሆንሽውን በግልፅ ንገሪኝ ገንዘብም ከሆነ እኔ እሰጥሻለሁ እኔ የገንዘብ ችግር የለብኝም ጠይቂኝ ምንም አታስቸግሪኝም አለች።
አይ አደለም እናቴ መልእክት ልካልኝ ነበር እና ትንሸ አመመኝ ብላኝ ደንግጬ ይቅርታ አልኳት።
አይዞሽ እንደደረሽ ሀኪም ቤት ውሰጃቸው ብላ ቅድም ልትሰጠኝ ከነበረው ብር ላይ ጨምራ ሰጠችኝ።
እኔ በፍፁም አልኩ እሷ ግን ተቆጣችኝና ብሩን በእጄ አስጨብጣኝ ከቤት ወጣን።
በቃ ሰላም ዋሉ አልኳቸው።
ሰላም ዋይ አሉኝ... ያብስራ ግን አረ ደሞ ድጋሜ ብትወድቅስ ቢያንስ taxi ላስይዛት ታሳዝናለች መጣሁ አለ።
ጥርሴን ነክሼ ፊቴን አዞርኩ ተከተለኝ ..
ምንም እንዳልተፈጠረ እጁን ትከሻዬ ላይ አድርጎ ደረቱን ነፋ እያደረገ
ትንሽ ከሳሽና ጠቆርሽ እንጂ ፊትሽ አልተቀየረም ያው ነሽ ግን በዚህ ሁኔታ ማገኝሽ አልመሰለኝ ግቢ ገብተሽ ምናምን ብዬ አስቤ ነበር አለኝ ....
(Sewoch please follow adrgulgn
👇👇👇👇👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping)

❤103😡10🔥9🤔8
ህላዌ (✍️✍️ማኔ)
አስታውሰኸኛል ማለት ነው አልኩት?
ደንግጬ ነበር
አዎ ቅድስቴ አስታውሼሻለሁ እረጅም ጊዜ አደለምኮ ከተለያየን ለማንኛውም እንደዚህ ባትሆኚ አሪፍ ነበር ።
ጭራሽ ሰው ቤት ተመላላሽ ምናም ተይ ደስ አይልም ላንቺ አይመጥንም ገና በዚህ እድሜሽማ እንደዚህ ዝቅ ብለሽ አትስሪ ለማን ብለሽ ነው ይሄን ያህል ፈታ በይ እንጂ አለኝ።
ምንድነው ምመልሰው ምንድነው ማወራው ልጩህበት ወይ ያለኝን አቅም ተጠቅሜ ልምታው ወይስ እንዴት ነው ልቤን ያፈነኝ ነገር የሚወጣልኝ።
ጫፍ አስፋልት ደረስን እኔ አልተነፈስኩም ዝምምም
ለማንኛውም አላቅሽም አታቂኝም እሺ።
ለልጁ ወይ ለሷ ለአንዳቸው እኔን ከዚህ በፊት እንደምታቂኝ ትንፍሽ አልሽ ማለት አለቀልሽ አሁን ያ ያብስራ አደለሁም እሺ እነሱ ብር ማትምባቸው ማሽኖቼ ናቸው የገቢ ምንጮቼ ሲነኩብኝ ደሞ አልወድም።
እኔ እነሱ ቤተሰብ ውስጥ የገነባሁት ማንነት አለ ከዚህ በፊት ካንቺጋ ለአንድ ቀን እንኳን አደለም ተኝቼ ታይቼ እንደነበር ከታወቀ ጥሩ አደለም አጋጣሚ አቃጣሪ ነው መልሶ አገናኘን ግን አንቺም እኔን አይተሽኝ አታቂም እኔም አንቺን አይቼሽ አላቅም እሺ የኔ ሚጢጢ አለኝ ።
አስተያየቱ አነጋገሩ ያስፈራ ነበር ልክ እንደ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ በድፍረት እየተመለከተኝ በአስተያየቱ ብቻ ከባድ ማስጠንቀቂያ እየሰጠኝ ነበር።
የኔን መልስ አልጠበቀም ትቶኝ ሄደ።
መንገድ ለመንገድ እንደ እብድ እያደረገኝ እያለቀስኩ እንባዬን በሻርፔ እየጠረኩ እዛው አስፋል ተሻግሮ ከፍ ብሎ ወዳለው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ገባሁ።
ከምን ጀምሬ ፀሎት እንደማደረግ ግራ ገባኝ ብቻ አየኸው አደል አየኸኝ አደል።
እኔ ለነሱ ወጥ ቀቃይ እሱ የኔ አለቃ ሆኖ ተገናኘን ።
ዛሬም እኔ እታች ነኝ።
ትናት በድሎ አስለቅሶ ትቶኝ የሄደው ቦታ ላይ ወርጄ ነው ያገኘኝ።
ሲያየኝ አልደነገጠም በጥፋቱ አላፈርም አየኸዎ አደለ እኔም እሱም እኩል ሰው ነን አደል በቃ ፍረድልኝ ወይ አጠንክረኝ ወይ ከዚህ ድራማ አውጣኝ ምንም አላየሁም ምንም አልሰማሁም በቃ
ተነስቼ ወደቤት ሄድኩ።
ልጄን ሳያት አቃተኝ እንዴት ነው አባትሽ እንደሱ አይነት ሰው ነው ገንዘብ አምላኩ ነው ብዬ የምነግራት እንዴት ነው ማስረዳት አቅፊያት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ እናቴ በሁኔታዬ ግራ ገብቷት ዝም ብላ አየችኝ።
አንዳንዴ ይደክማል ይሰለቻል አደል አልቅሽ ቢያንስ አንቺ ምታለቅሺበት እድሜ ላይ ነሽ ሚታዘብሽ ሚቆጣሸ የለም ውስጥሽ ያለው እሳት በረድ እስኪል አልቅሸ ማልቀሻ ማግኘትም አንድ መታደል ነው አፍነሽ ስትይዥው ነው ውስጥ ውስጡን ሚጨርስሽ አለችኝ።
ምተነፍስባት ሜሪጋ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኳት ደነገጠች።
ተመሳስሎብሽ ነው እንዴት ሊሆን ይችላል አለችኝ።
ያለኝንም ነገርኳት።
ተሳደበች ይሄ ውሻ እሱም ወንዶ ነው ሊያስፈራራሽ ይሞክራል ድጋሜ እዛ ቤት እንዳቴጂ የቀረው ይቅር ድጋሜ እሱን እዛ እያየሽ እንዳትጎጂ በቃ እንደሞተ ቁጠሪው ከህይወትሽ አውጭው ያብስራ ሚባል ሰው የለም አልነበረም አለችኝ።
እውነታው ግን ልጄ አለች እሷን በማይበት በእያንዳንዱ ቅፅበት እሱን አስታውሳለሁ።
ግን በቃ ደግሜ እዛ ቦታ አሌድም ደግሜ እዛ ቤት እግሬ አይረግጥም ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ።
ግን ጎረቤቴስ ምን እለዋለሁ ምን ምክንያት አቀርባለሁ አላውቅም።
በዛ ውዝግብ መሸ።
ማታ ላይ አይኔ አብጦ ነበር ሳለቅሽ አምሽቼ ።
ወደ 3 ሰአት አካባቢ ጎረቤቴ መጣ።
በሩን አንኳኳ
ከፈትኩለት ።
ሰላም አመሸሽ አንዴ ላውራሽ አለኝ።
አፉ ጋን ጋን ይሸታል።
እሺ ብዬ በሬን ዘግቼ ወጣሁ።
ምን ሆነሽ ነው ቀን እንደዛ የሆንሽው አለኝ እጁን በኪሱ ከቶ።
ምንም አልሆንኩም።
ግን ካሁን ቡሀላ አልመጣም እዛ አልሰራም አመሰግናለሁ ስለሰጠኸኝ እድል ግን አልተመቸኝም ልጄን መያዝ አለብኝ አልኩት።
ሳቀ ድረማ ምናምን ነገር ትወጃለሽ ልበል ለማንኛውም እንደተመቸሽ ከመጀመሪያ ከሰጠሁሽ ደሞዝ አንስቶ ዛሬ ስትወጪ ሲስተር የሰጠችሽን ገንዘብ ሙሉ ደማምሪና ሁሉንም ነገ ትከፍያለሽ ካሎነ ደሞ እኔ በግድ እቀበልሻለሁ ደና ደሪ ብሎ ገፍትሮኝ ወደቤቱ ገባና ቆርቆሮ በሩን ወረወረብኝ
ደና ደሩ😌
ከተመቻችሁ 👍👍

❤84👍19😭14🙉5😱4🥰1
4600 ተከታይ እያለኝ 1000 ሰው ቲክቶክ ላይ ያሰፈልገኛል ለስራ ብዬ ፖሰት አድርጌ 22 ሰው ብቻ ነው follow ያደረገኝ
የምትችሉ ሰዎች follow አድርጉልኝ
የምር የምር ስለሚያስፈልገኝ ነው
👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping
የምትችሉ ሰዎች follow አድርጉልኝ
የምር የምር ስለሚያስፈልገኝ ነው
👇👇👇
tiktok.com/@mane.shopping
❤15👍1