ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
2.23K subscribers
410 photos
2 videos
7 files
108 links
🌷ይህ ቻናል የተከፈተው ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ዋና አላማውም ምዕመናን በንስሐ ህይወት ተመላልሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድወርሱ የሚያስችል ትምህርት መስጠት ነው፡፡
🌷💚የቅዱሳን ገድላት
🌷💛ስንክሳር
🌷 ቅዱሳን ስዕላት
መንፈሳዊ ትምህርቶችና ጽሑፎች
🎤 ስብከቶች ............ይቀርቡበታል፡፡🌎
Download Telegram
ሁለተኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹

ሰላም ውድ የማኀበረ ቅዱሳን ቻናል ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ ። በረድኤት ያልተለየን በቸርነቱ የጠበቀን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏🙏
#አድስ-ኮርስ ነው እንድትከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን ።
__________
🌺ሁለተኛ
ኮርስ🌹
🌺🌺🌺💚💛🌺🌺
🌺 #ነገረ__ሃይማኖት 🌺
🌺🌺🌺💚💛🌺🌺

🌹#ምዕራፍ-፩ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት መግቢያ🌹

#ሃይማኖት_ምንድነው?
ሃይማኖት፦ ሐይመነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተሰደ ሲሆን ትርጉሙ ማመን መታመን ማለት ነው።

ማመን፦ ማመን ማለት በአንድ ስጋ/በእዝነ ስጋ / ጀሮ ሰምቶ፣ በልብ አስቦ በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳትም ቢሆን አድምጦ እና ዳሶ ሊመረምሩት የማይቻለውን በእርቀት (እሩቅ በመሆን) እና በርቀት (በረቂቅነት) ያለውን ይሆናል።
ይደረጋል ብሎ መቀበልና እግዚአብሔርን አለ፣ ይኖራል ሁሉን ያዥ፣ ሁሉን ገዥ ነው ብሎ በልብ በረቂቅ መሳልና ማሰብ ሀሳብን በማወቅ ማረጋገጥ፣ መፍቀድ፣ መውደድ፣ መመካት ተስፋ ማድረግ ማለት ነው።

መታመን፦ መታመን ማለት ደግሞ በልብ በረቂቅ ሀሳብ ያመኑትን በአንደበት መመስከር መናገር፣ ወዶና ፈቅዶ በደስታ መቀደስ፣ ማመስገን፣ በግብር መግለፅ መተግበር፣ መስገድ፣ መገዛት፣ መገበር ማለት ነው።
እንዲሁም መታመን ማለት ይሆናል ይደረጋል ብሎ በእምነት የተቀበሉትን እንዲሆን እንዲደረግ፣ እንዲፈፀም ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው።
እነዚህን ሁለቱን ከያዘ ከተገበረ ሀይማኖት አለው ይባላል። (ማር 16፥16 ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል።)

ምላሹ፦ በማመንና በእግዚአብሔር መጠመቅ ነው። ሉቃ 15፥11-32
ልብስ የተባለው ሀይማኖት ነው፣ ቀለበት እሰሩለት የተባለው ቃል ኪዳኑን ነው፣ ለእግሩ ጫማን አጨሙት የተባለው፣ ወንጌልን ስጡት ነው፣ የሰባውን ፍሪዳ እረዱ እና እንብላ ማለቱ ስጋወደሙን ነው። ይህ ልጅ ሙቶ ነበር አሁን ግን ህያው ሁኖል ማለት የሰው ልጅ በህይወት እያለም ይሞታል ማለት ነው። ምክኒያቱ ደግሞ ከሀይማኖት ሲለይ
/ሲወጣ፣ አባት የተባለው እግዚአብሔር አምላክ ነው ከሞትም ወደ ህይወት ተለውጧል ያለው በንስሐ ነው።
~~~~~~~~

#ወስብሐት# _ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan 💚
@mahiberekidusan 💛
@mahiberekidusan

የመጀመሪያ ኮርስ -ነገረ ክርስትና

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹

__________
#ሃይማኖት
1️⃣ የሚቀበሉት ነው~
> (ዮሐ 1፥9 ለተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው።) የሚቀበሉት ስንል በእምነት የሚቀበሉት ማለታችን ነው እንጅ ባለን ውስን ስጋዊ እውቀት መርምረን አረጋግጠን የምንቀበለው ማለታችን አይደለም። እምነት ከስሜት በላይ ነው።
አውቀው የሚያምኑት ወይም የሚቀበሉት ሳይሆን አምነው የሚቀበሉት ነው።

2️⃣ በተስፋ የሚረዱት ነው~> ዕብ 11፥1-5 እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የምናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎችም የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና።

3️⃣ በፍቅር የሚገለፅ ነው~> ሀይማኖት በፍቅር የሚገለጥ ነው። ፍቅር ከፍቅረ እግዚአብሔርና ከፍቅረ ቢፅ/ሰብ (ማቴ 5፥43 ጠላታችሁን ውደዱ / 22፥37-39 ... ጌታ አምላክህን በፍፁም ልብህ በፍፁም ነብስህ በፍፁም አሳብህ ውደድ) (1ኛ ዮሐ 3፥15 ወንድሙን የሚጠላ እራሱ ነብሰ ገዳይ ነው ነብሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ህይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።)

4️⃣ በስራ የሚተረጎም ነው~> በቃል የተነገረውን በስራ የተገበረ ነው በሀይማኖት ውስጥ አለ የሚባለው። በንባብ ሳይሆን በቃል መኖር ያስፈልጋል። ያዕ 2፥26 ከነብስ የተለየ ስጋየ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከስራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

5️⃣ እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ነው~> እብ 11፥6 ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም።

6️⃣ መንገድ/ፍኖት ነው~> ሀይማኖት ከጥንት ጀምሮ ከመጀመሪያው የሰውና የሉዕለ ባህሪይ የህያው እግዚአብሔር ግንኙነት ነው።
አምነህ የምትሄድበት መንገድ ወይም ሂደህም በእርግጥ የምትገባባት (ቢባት) አገር ወይም ህያው መኖሪያ ማለት ነው። (ኤፌ 4፥5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት)

7️⃣ የተሰጠነው ነው~> ሃይማኖት ማንም ሰው ተመራምሮ፣ ተፈላስፎ ያገኘውና የሰራው ለአለምም ያስተዋወቀው አይደለም። ምክንያቱም ሃይማኖት መገለጥ ስለሆነ (ይሁ ... ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።)

8️⃣ የማይታየውን የሚያሳይ እረቂቅ መሳሪያ ነው~> ኢሳ 40፥12 ውሀዋችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማንን በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛኖች የመዘነ ማነው?
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ሃይማኖት እንዴት ተገኘ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹

__________
#ሃይማኖት_እንዴት_ተገኘ
አንዳንዶች
ሃይማኖትን የሰራው ሰው ነው ይላሉ፣ አንዳንዶቹ ከጅንጀሮ፣ አንዳንዶቹ ከድንጋጤ ነው የመጣው ይላሉ፣ አንዳንዶቹ ከዕውቀት ማነስ የተነሳ / እውቀት ከለላቸው ነው ይላሉ። ነገር ግን እንደዚህ ወይም እነሱ እንጀሚሉት አይደለም። ሃይማኖት አፋዊ ነገር ሳይሆን የሰው ልጅ በመንፈሱ አማካኝነት በውስጡ ጠንካራ የሃይማኖት ዝንባሌ አለው።

የሃይማኖት መገኛ እራሱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ሃይማኖትን መቼ ተገለጠ እንጅ መቼ ተጀመረ አንልም።

የተገለጠውም በአለመ መላኢክት ቅዱስ ገብርኤል መልአክ (ንቁሞ በበለባዊነ) በያለነበት እንፅና ብሎ መላኢክትን ከአፀና በኋላ የተገለጠው የብርሀን ጎርፍ ነው።

ሃይማኖት ጥንት የለለው ነገር ነው። ስለዚህ ተገለጠ እንላለን። ጥንት ያለው ነገር ከሆነ ተጀመረ ማለት እንችል ነበር። ሃይማኖት የተቀበልነው እንጅ የጀመርነው አይደለም። ስለዚህ አማኞች ያልነበሩበት ጊዜ አለ እንጅ ሃይማኖት ያልነበረበት ጊዜ የለም። ይሁ 1፥3 / ጢሞ 2፥13 / ሉቃ 18፥8

ከፍጥረት ውስጥ ሃይማኖት ያላቸው ሰውና መላኢክት እንዲሁም አጋንንት ብቻ ናቸው።
አጋንንትም ያምናሉ ያዕ 2፥19 ለዘለአለም ሰውና መላኢክት እያመሰገኑ እንደሚኖሩ (ኢሳ 6፥15 በእግዚአብሔር እንኳን የማያምን የለም።)

#ሃይማኖተ_ክርስቶስ
ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖተ ክርስቶስ ብላ የምትጠራው የክርስትናን ሃይማኖት ነው።
የክርስትና ሃይማኖትን በ3 ከፍፍለን እናያዋለን። እነዚህ፦ ዘመነ አበው/ህገ ልቦና፣ ዘመነ ኦሪት/ኦሪት፣ ዘመነ ወንጌል/ሐዲስ ኪዳን ናቸው።

ሀ,
ህገ ልቦና፦ ከጌታችን ልደት በፊት 5,500 የነበረውን ዘመን (ከአዳም እስከ ሙሴ ያለው ዘመን) ሲሆን ዘመነ አበውም እንለዋለን።
ህገ ልቦና ስንል እግዚአብሔር በልቦናቸው ያስቀመጠላቸውን በመጠቀም ነው። ለምሳሌ አቤል እግዚአብሔርን ንፁሀ በሀሪ ስለሆነ ብሎ ንፁህ መሰዋኢትን አቀረበ። ይህን ስንል በህልም በራዕይም ይገለጥላቸው ነበር።

ለ, ዘመነ ኦሪት፦ (ከሙሴ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ) ዘመነ ኦሪት ስንል ደግሞ የረቀቀን ህግ ሰጣቸው ገለጠላቸው በዚያም ተማሩ ማለት ነው። እግዚአብሔር አብሮአቸው እንደሆን ማሳያው፦ 1,የመገናኛ ድንኳል 2, ታቦት 3, ስርአተ ካሀናት እና ስራአተ መስዋኢት
እንዚአብሔር እነዚህን

ሐ, ዘመነ ወንጌል/ሐዲስ ኪዳን፦ (ከኢየሱስ ክርስቶስ እስከ አሁን) ዘመነ ወንጌል የተባለው በክርስቶስ መገለጥ ወይም መወለድ ነው። በሙላት ተገለጠ ዘመኑም ዘመነ አስተሪዎ /ኢጲፋኒይ ይባላል። መዝሙሩም አስተኋያ ገሀደ አብ 1፥4-4 ፤ መዝ 87፥ 3
~>በክርስቶስ እየሱስ ሁኖ በፍቅር የሚሰራ እምነት ነው።
~>በሰው ፍልስፍና ያልሆነ/በስጋና ደም ያልሆነ በአምላክ የመገለጥ ነው።
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹

_________
#ሃይማኖት_በምን_በምን_ይመሰላሉ
ሀ,መ
ንገድናት፦ ትኤ 6፥16 እግዚአብሔር እዲህ ይላል በመንገዱ ላይ ቁሙ ተመልከቱ የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ መዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነብሳችሁ እርፈትን ታገኛላችሁ እነርሱ ግን አንሄድም አሉ። ለምን ቢሉ መንገድ የሃይማኖት ምሳሌ ናት መንገድ መሄድ የፈለገ እንደሚሄድ ሀይማኖትም መሄድ ሚፈልግ ብቻ ነው ሚሄድባት።
መንገድ ከጫፍ እስከጫፍ እንደሚያገናኝ ሁሉ ሀይማኖትም በምድር ያሉትን እና በሰማይ ያሉትን ታገናኛለች።
ሀይማኖት ፈጣሪና ፍጡር የሚገናኙባት ድልድይ ናት።

ለ, ስናፍጭ፦ ስናፍጭ የተባለችበት ምክንያት ስናፍጭ ፍፁም ናት ሃይማኖትም ፍፁም ናት።
ለቅዱሳን የተሰጠች ሃይማኖት ማለት ነው። ይሁ 1፥3
ስናፍጭ ሳትዘራ ትበቅላለች ታፈራለችች ሰውም በሃይማኖት ሲኖር የሃይማኖት ፍሬ ያፈራል።
ስናፍጭ የስጋን ቁስል ትፈውሳለች ሃይማኖት ደግሞ የስጋንም የነፍስንም ቁስል ትፈውሳለች።

ሐ, ወርቅ፦ ወርቅ ከማዕድኑ ሁሉ ንፁህ ነው ሃይማኖትም ንፁህ ነው
ወርቅ ወርቅነቱ የሚታወቀው በእሳት ተፈትኖ ነው ሃይማኖት ጥንካሬው ያሚታወቀው በፈተና ነው።ጴጥ 1፥7
ወርቅ የከበረ ማዕድን እንደሆነ ሀይማኖትም የከበረች ናት።

-->ሃይማኖት መሰረት ነች መግባር እና ቱርፋት ግድግዳ ናቸው።
-->እምነት ያለ ምግባር የሞተ ነው። የዕ 1፥12
-->ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም። እብ 11፥6
-->ሃይማኖት የማትለወጥ፣ የማትሻሻል፣ የማትታደስ ናት

#የሃይማኖት_ጥቅም
~>ፍፁም ሰላምን ታስገኛለች ዮሐ 14፥27
~>በረከትን ታስገኛለች
~>ፅናትን ፀጋን ታስገኛለች 18፥43
~>ከመከራ ስጋ ትጠብቃለች ትዳ 6፥16
~>ለድህነተ ነብስ ትጠቅማለቼ 1፥3
~>ለክብረ ነብስ ታበቃለች ይሁ 1፥3
~>ለሀገር ሀይማኖት መሰረት ናት
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ሃይማኖት እና ሳይንስ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹

__________
#ሃይማኖትእናሳይንስ
ሃይማኖት ማለት በፈጣሪ እና በፍጡር ያለ ግንኙነት ነው።
ሳይንስ ማለት ሲንትየ/ሲያንሰ ከሚለው የላቲን ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በልምድ ወይንም በእውቀት የተገኘ ማለት ነው።

#ሃይማኖት
-የሃይማኖት ምንጭ እግዚአብሔር ነው።
-የሃይማኖት ግቡ የሰውን ልጅ ወደ እግዚአብሔር ማድረስ ነው
-የሃይማኖት ትኩረት አድራጊው ወይንም አስገኝው ላይ ነው(ፈጣሪ)
-
ሃይማኖት የሚጠቅሰው የእግዚአብሔርን ቃል ነው።
#ሳይንስ
-የሳይንስ ምንጭ ከሰው ልጅ አዕምሮ ነው
-የሳይ
ንስ ግቡ የሰውን ልጅ ኑሮውን ማሻሻል ነው።
-ትኩረቱ የተገኘው ላይ ወይንም ከተፈጣሪው ላይ ነው።
ሳይንስ ደግሞ የሚጠቅሰው የቀደሙትን ምርምር ነው።

ሳይንስ በጥንቃቄ ካልተያዘ የሚከተሉትን ጉዳቶች
ያመጣል፦
×ከሚገባው በላይ በሳይንስ መተማመን
×የሃይማኖት ስርዓታችንን ያዳክማል
×ቁሳዊ ረስተሳሰብ ብቻ ያጠናክራል
×የስነ-ፍጥረት ህግን ያዛባል

~>ሃይማኖት ግን ለሳይንስ ግብአት መሆን ይችላል።
ለምሳሌ፦ስለሚበሉና ስለማይበሉ ነገሮች
-ስለግዝረት አዝ 17፥18-22

#ሶስቱ_ጉባኤያት
1️⃣ ጉባኤ ኒቂያ
2️⃣ጉባኤ ቆስጠንጥንያ
3️⃣
ባኤ ዘ ኤፌሶን

እነዚህ ሦስቱ በተለያዬ ጊዜ የተካሄዱ ታላላቅ ጉባኤያት አለማቀፍና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቼው ናት።
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ጉባኤ ኒቅያ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
❷❶