እስኪ የአባቶቼን የአንደበት ፍሬ ላካፍላችሁ።
‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› ..............አባ እንጦንስ
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››
.................................ቅዱስ አትናቴዎስ
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››
.......................................ቅዱስ ሚናስ
‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››
..................................ታላቁ አባ መቃርስ
‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
.................................ቅዱስ አርሳንዮስ
‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››
....................................ቅዱስ እንድርያስ
‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››
...................አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
‹‹ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
...................ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
....................ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ·
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር››
............................ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
‹‹ኃጢያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጢያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
......................................ቅዱስ እንጦስ
የአባቶቻችን ፀሎት አይለየን
ደቂቀ እስጠመፋኖስ
https://t.me/mahibereestifanos111

Telegram
ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu

ቅዱስ ዮሀንስ
☞ወር በገባ በ4 የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ወልደ ነጎድጎድ) ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ያዕቆብ እናቱ ማርያም (ሰሎሜ) ይባላሉ፡፡ቁጥሩ ከ12ቱ ሀዋርያት ነው፡፡☞ዮሐንስ ማለት ፍሥሓ ወሐሴት ማለት ነው፡፡
☞በገሊላ ባሕር ከአባቱ ከዘቢዴዎስና ከወንድሙ ከዪዕቆብ ጋር ዓሣ ሲያጠምድ
መስከረም 30ቀን ጌታ ለሐዋርያነት መረጠው፡፡ ከዚያም መረብን ትቶ ጌታውን
ተከተለ፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለመስበክ ዕጣ የደረሰው አስያ ነበር በዚየም ቡዙ
ኢአመንያን ወደአማኝነት በትምህርቱ መልሷቸዋል፡፡
☞ ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላሰተማረው ምስጢር የለም፡፡
☞ወንጌልንም መጻፍ ሲጀምር "መጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር
ዘንድ ነበር በማለት ገለጾል፡፡
☞ቅድስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግር መስቀሉ ድረስ በመከተል ክርስቲያኖችን
ሁሉ ወክሎ እመቤታችን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለእመቤታችን በአደራ የተሰጠ
ሲሆን፡፡
☞እመቤታችንን ከወሰዳት በኃላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡
☞እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡
☞ዮሐንስ ሥዕል ሲስል በተለይ የስቅለቱን ስዕል ሲስል በመጀመሪያ ጌታችን
ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱ ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕል
አፍ አውጥቶ በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ አሁን ደግሞ
አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትስቅለኝን?ብሎ ተናገረው፡፡ዮሐንስም እጅግ
ደንግጦ እንዴት አድርጌ ልሳለህ? ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም
(ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ አለው)፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ
ከሳለው በኃላ ሥዕሉ ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩሉ
ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡
ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችን ስነ ስቅለት
የሚሳዮ ሥዕሎች መገናቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዮ ስሞች ይጠራል፡፡
1:- በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችን ለመምሰል ይጥር ነበረና ጌታችንም እጅግ
ይወደው ሰለ ነበረ( ፍቁረ እግዚእ)ተባለ፡፡
2:- የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ሰለሆነ አባቱም ዘብድዎስ ሰለ ሚባል
(ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ)ተባለ፡፡
3:- ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ
እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ(ወለደ ነጎድጎድ )ተብሏል፡፡
4:- ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶ አምልቶ በማስተማሩ (ነባቤ
መለኮት ወይም ታኦሎጎስ)ተብሏል፡፡
5:- ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዮ ሰለገለጠ(አቡቀለምሲስ)ተባለ፡፡
6:- የጌታችን መከራ መስቀል እያስተወሰ 70ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ሰለኖረ ፊቱ
በኅዘን ሰለ ተቋረጠ (ቁጹረ ገጽ)ተብሏል፡፡
☞ከዚ ሁሉ በኃላ በጥር 4ቀን ሞትን ሳያይ ተሰውሯል፡፡
☞የቅዱስ ዮሐንስ (ወለደነጎድጎድ )ጥበቃው አማላጅነቱ አይለያችሁ፡፡
☞የጽሑፍ ምንጭ☞(መዝገበ ቅዱሳንመጽሐፍ)

የእግዚአብሔርን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ናችሁ⁉️
ወዳጄ አስተውለህ አንብብ
እግዚአብሔር ለምን ዝሙት ሰራህ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ሰከርክ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ሰው ገደልክ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ወዳጅህን አስቀየምከው አይልህም ❕
ለምን ይቅርታ አልጠየከውም ይልሃል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ወዳጅህ ላይ ቂም ያዝክ አይልህም❕
ለምን ይቅርታ አላደረክለትም ይልሃል እንጂ❗️
👉ባጠቃላይ እግዚአብሔር ለምን ሐጢአት ሰራህ አይልህም❗️
ለምን ተጸፅተህ በንሰሃ አልተመለስክም ይልሃል/ሻል እንጂ❗️❗️
ስለዚህ የፈጣሪን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ እንሁን ንሰሃ እንግባ የበደልነውን ሰው ይቅርታ እንጠይቅ ለበደለንም ይቅርታ እናድርግለት
ያንጊዜ ለፈጣሪ ጥያቄ መልስ እንሰጣለን
ደቂቀ እስጢፋኖስ
Share አድርጉ
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
ወዳጄ አስተውለህ አንብብ
እግዚአብሔር ለምን ዝሙት ሰራህ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ሰከርክ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ሰው ገደልክ ብሎ አይጠይቅህም❕
ለምን ንሰሐ አልገባህም ይላል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ወዳጅህን አስቀየምከው አይልህም ❕
ለምን ይቅርታ አልጠየከውም ይልሃል እንጂ❗️
እግዚአብሔር ለምን ወዳጅህ ላይ ቂም ያዝክ አይልህም❕
ለምን ይቅርታ አላደረክለትም ይልሃል እንጂ❗️
👉ባጠቃላይ እግዚአብሔር ለምን ሐጢአት ሰራህ አይልህም❗️
ለምን ተጸፅተህ በንሰሃ አልተመለስክም ይልሃል/ሻል እንጂ❗️❗️
ስለዚህ የፈጣሪን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ እንሁን ንሰሃ እንግባ የበደልነውን ሰው ይቅርታ እንጠይቅ ለበደለንም ይቅርታ እናድርግለት
ያንጊዜ ለፈጣሪ ጥያቄ መልስ እንሰጣለን
ደቂቀ እስጢፋኖስ
Share አድርጉ
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
Telegram
ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
“መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ”
— ዮሐንስ 21፥6
ይሄንን የሕይወት ቃል ጌታችን ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ ሲነግራቸው ቅዱስ ዮሐንስ ጽፎ አስቀምጦልናል
ዮሐንስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው፤
² እንዲህም ተገለጠ፦ ስምዖን ጴጥሮስና ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ከገሊላ ቃና የሆነ ናትናኤልም የዘብዴዎስም ልጆች ከደቀ መዛሙርቱም ሌሎች ሁለት በአንድነት ነበሩ።
³ ስምዖን ጴጥሮስ፦ ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ አላቸው። እነርሱም፦ እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ በዚያችም ሌሊት ምንም አላጠመዱም።
⁴ በነጋም ጊዜ ኢየሱስ በባሕር ዳር ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም።
⁵ ኢየሱስም፦ ልጆች ሆይ፥ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው። የለንም ብለው መለሱለት።
⁶ እርሱም፦ መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።...................
በዘመናችን በቅዱሳን ሐዋርያት የሚመሰሉት አባቶቻችን ጳጳሳት ፡ ካህናት፤መምህራነ ወንጌል ናቸው
መርከብ የተባለችው ምድራዊቷ ገነት ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት
መረብ የተባለው ነፍሳትን ከኃጢአት ባሕር ወደ ህይወት መርከብ የሚመልሰው የህይወት መሪ ቅዱስ ወንጌል ነው
በአሳ የተመሰልነው እኛ የሰው ልጆች ነን
https://t.me/mahibereestifanos111
በእውነት ይሄንን ታሪክ ትኩር ብለን ስናነብ ከዘመናችን ጋር ይገናኛል
የሚገርመው መምህራነ ቤተክርስቲያን ቀን ከሌይት ሳያርፉ ቅዱስ ወንጌልን ያስተምራሉ በቅድስቲቷ መርከብ ተሳፍረው በቅዳሴው በማኅሌቱ በሰዓታቱ ሳይደክሙ ነፍሳትን ከሃጢአት ባሕር ከዝሙትና ከስካር ባህር ከክህደትና ከጣኦት አምልኮ ባህር ወደ ቅድስቲቷ መርከብ ለመመለስ ይለፋሉ
ይሁንና ነፍሳት መመለሳቸው ይቅርና ጭራሽ ከመርከቢቷ እየጠፉ የበግ ለምድ በለበሱ አታላይ ተኩላዎች እየተወሰዱ ቅድስቲቷን መርከብ እየካዱ ወደ ኃጢአት ባህር እየሰጠሙ ይገኛል ይህ ለምን ሆነ? ከመምህራን ችግር ነው? ወይስ ከነፍሳቱ?
በእርግጥ ቅድስት ቤተክርስቲያን መምህራን የሏትም ማለት መዋሸት ይሆናል እንቁና ድንቅ መምህራን ወንጌልን አስተምረው ነፍሳትን ሙሉ በሙሉ ወደ ቅድቲቷ ቤት ለመመለስ የሚችሉ ምሁራን እንዳሉ ይታወቃል
https://t.me/mahibereestifanos111
ይሁንና አሁንም ነፍሳቱ እየወጡ በተኩላዎች እየተዋጡ ነው ለዚህ ደሞ ትልቁ ምክንያት የመረብ አጣጣልና እግዚአብሔርን አለመስማት ነው
ብዙ ጊዜ በየመድረኩ የምናየው ትምህርት የሰዉን ክብር የሚያወድስ ነፍሳትን በመመለስ ፈንታ ነፍሳትን የሚያጠፋ ነው ብዙ ጊዜ ወንጌል በጥሩ ሁኔታ ሲሰበክ የምናየው ቅዳሴው ባማረ ሁኔታ ሲካሄድ የምናየው ማኅሌቷ በምእመናን ደምቆ ሲቆም የምናየው በከተማይቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን ነው በየከተማው ቤተመቅደሱ ሞልቶ ጊቢው ሞልቶ ስናይ ብዙ ምእመን ያለ ሊመስለን ይችላል ነገር ግን በየገጠሩ በዚያ እጥፍ የሚሆኑ ምእመናን እየጠፉ ነው መምህራኑና ጳጳሳቱ በአንድ መድረክ ላይ 20 ና 30 ሁነው በአል ሲያከብሩ በገጠሯ ቤተክርስቲያን ግን መቅደሷን ከፍቶ እጣን እንኳ የሚያጥን ካህን እየጠፋ ነው😔 አሉን ብለን የምንኮራባቸው መምህራኖቻችን በየትላልቅ አድባራቱ እየዞሩ ዝናና ክብርን ማግኘት እንጂ የተረሱትን አድባራት መሪ ያጡትን ምእመናን መመልከት ካቆሙ ዘመናት አልፈዋል(እንዲህ ስል ግን ሁሉንም ማለት አይደለም ግን አሁንም ብዙ ይቀራል)
https://t.me/mahibereestifanos111
ታዲያ ለምን ነፍሳቱ አይጠፉም ታዲያ ለምን መንጋው አይበተንም ቆይ ገጠር ያለውስ ቤተክርስቲያ ገጠር ያለውስ አማኝ መች ነው ወንጌልን የሚሰበከው? መች ነው ኃይማኖቱን አውቆ የሚኖረው? መች ነው ለስጋ ወደሙ የሚበቃው?
https://t.me/mahibereestifanos111
ኢየሱስ ክርስቶስ የመበለቲቱን መባ እንደተቀበለ እናንተም መምህራን ዝቅ ብላችሁ ሰው የረሳቸውን አድባራት አስቧቸው አባቶች ጳጳሳት የመስቀል ቡራኬ የናፈቃቸውን ምእመናንን ተመልከቷቸው ብዙ ነፍሳትን ለማዳን በጨለማ ከመዳከር ይልቅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው መረባችሁን በቀኝ ጣሉት።
ደቂቀ እስጢፋኖስ
Share እናድርግ

🌹🌹 ግንቦት ፲፪ [12] ቀን 🌹🌹
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
† እንኳን አደረሳችሁ †
ግንቦት ፲፪ [12]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ፫፻፵፯ [347] ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ [ፍልስፍና] ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ፲፭ [15] ዓመቱ ነበር:: በ፪ [2] ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::
ቅዱሱ ገና በ፲፮ [16] ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::
ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::
ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::
ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ ፲ [10] ዓመት አቁሞታል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ ፪ [2] ጊዜ አጋዘችው::
በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ፬፻፯ [407] ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ፷ [60] ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::
አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ [ግብዣ አዘጋጀ]:: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ ፲፪ [12] ቱ ሊቃነ መላእክት [እነ ቅዱስ ሚካኤል] በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::
ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::
በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::
"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ [ማቴ.፩፥፳፭] (1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::
"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::
አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::
ሊቁ ባረፈ በ፴፭ [35] ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::
ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው :-
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
- አፈ በረከት
- አፈ መዐር [ማር]
- አፈ ሶከር [ስኳር]
- አፈ አፈው [ሽቱ]
- ልሳነ ወርቅ
- የዓለም ሁሉ መምሕር
- ርዕሰ ሊቃውንት
- ዓምደ ብርሃን [የብርሃን ምሰሶ]
- ሐዲስ ዳንኤል
- ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ [እውነተኛው]
- መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
- ጥዑመ ቃል - - -
እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን::
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

❤️❤️ፍቅር❤️❤️
ፍቅር ፍቅር ይላል ሁሉም በአንደበቱ
በልቡ አዝሎ ይዞ ሲሳሳም በአንገቱ
ይህ ፍቅር አይደል ከሆነ እንጂ ከንቱ
ፍቅር ነው ብላችሁ እንዳትሳሳቱ
በብዙ መከራ ቢገኝ እንኳ በጭንቅ
አሳልፎ የሚሰጥ ነፍሱን ስለፃድቅ
እንኳን ለሰው በደል ይቅርና መሞት
ራሱን የሚሰጥ ስለ ሌላው ሕይወት
አሳልፎ አይሰጥም ጀርባን ለግርፋት
አባት እንኳ ለልጁ በፈጸመው ጥፋት
እና ማነው ታዲያ ፍቅር ያስገደደው?
ከሞት ቋጥ አዳምን ማነው ያወረደው?
ፍቅርን ልንገራችሁ ካለችበት ቦታ
ዓይናችን ከፍ ይበል ወደ ጎልጎታ
ፍቅር ማለት ያ ነው የተሰዋው ጌታ
ክንደ ብርቱነቱን ጌትቱን ትቶ
ስለሰው ልጅ ፍቅር በመስቀል ላይ ወቶ
የተሰቀለው ነው እጆቹን ዘርግቶ
ጣፋጭ ያጠጣን ነው መራራ ጠጥቶ
ተከሶ ተገርፎ በአይሁድ ሸንጎ ውሎ
ፍቅርን አስተማረን በመስቀል ተሰቅሎ
በዲ/ን ደመላሽ ጎንፋ
ደቂቀ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ትምህርቶችን ግጥሞችን መዝሙሮችን በአንድ ላይ ለማግኘት ተቀላቀሉን
ቻይናል
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
ግሩፕ
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
ፍቅር ፍቅር ይላል ሁሉም በአንደበቱ
በልቡ አዝሎ ይዞ ሲሳሳም በአንገቱ
ይህ ፍቅር አይደል ከሆነ እንጂ ከንቱ
ፍቅር ነው ብላችሁ እንዳትሳሳቱ
በብዙ መከራ ቢገኝ እንኳ በጭንቅ
አሳልፎ የሚሰጥ ነፍሱን ስለፃድቅ
እንኳን ለሰው በደል ይቅርና መሞት
ራሱን የሚሰጥ ስለ ሌላው ሕይወት
አሳልፎ አይሰጥም ጀርባን ለግርፋት
አባት እንኳ ለልጁ በፈጸመው ጥፋት
እና ማነው ታዲያ ፍቅር ያስገደደው?
ከሞት ቋጥ አዳምን ማነው ያወረደው?
ፍቅርን ልንገራችሁ ካለችበት ቦታ
ዓይናችን ከፍ ይበል ወደ ጎልጎታ
ፍቅር ማለት ያ ነው የተሰዋው ጌታ
ክንደ ብርቱነቱን ጌትቱን ትቶ
ስለሰው ልጅ ፍቅር በመስቀል ላይ ወቶ
የተሰቀለው ነው እጆቹን ዘርግቶ
ጣፋጭ ያጠጣን ነው መራራ ጠጥቶ
ተከሶ ተገርፎ በአይሁድ ሸንጎ ውሎ
ፍቅርን አስተማረን በመስቀል ተሰቅሎ
በዲ/ን ደመላሽ ጎንፋ
ደቂቀ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ትምህርቶችን ግጥሞችን መዝሙሮችን በአንድ ላይ ለማግኘት ተቀላቀሉን
ቻይናል
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
ግሩፕ
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
Telegram
ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
❤️❤️❤️እግዚአብሔር❤️❤️❤️
እግዚአብሔር ሩቅ ነው፣ ጥበቡ አይታይምና።
እግዚአብሔር ቅርብ ነው፣ ቶሎ ይሰማልና።
እግዚአብሔር መኮንን ነው፣ ቶሎ ይፈርዳልና።
እግዚአብሔር ትሑት ነው፣ ሰውን አይንቅምና።
እግዚአብሔር መሐሪ ነው፣ ቶሎ ይቅር ይላልና።
እግዚአብሔር ሐኪም ነው፣ ሁሉን በጥበቡ አድርጓልና።
እግዚአብሔር ምስጉን ነው፣ ጸሐይን ጨረቃን ፈጥሯልና።
እግዚአብሔር ክቡር ነው፣ ሰማይና ምድር የእርሱ ናቸውና።
እግዚአብሔር ባለጸጋ ነው፣ ለሁሉም ይመግባልና።
እግዚአብሔር ረቂቅ ነው፣ አይጨበጥምና።
እግዚአብሔር ግዙፍ ነው፣ በዓለም ሁሉ ሞልቷልና።
እግዚአብሔር ብሩህ ነው፣ ጨለማ የለበትምና።
እግዚአብሔር ሐያል ነው፣ የሚቋቋመው የለምና።
እግዚአብሔር እሳት ነው፣ እጅግ ያስፈራልና።
እግዚአብሔር መካር ነው፣ መጻሕፍትን ሰጥቶናልና።
እግዚአብሔር አባት ነው፣ አሳድጎናልና።
እግዚአብሔር ወንድም ነው፣ ሰው ሆኗልና።
እግዚአብሔር ወዳጅ ነው፣ የሆዱን ነግሮናልና።
እግዚአብሔር አገር ነው፣ እንኖርበታለንና።
እግዚአብሔር ማርና ስኳር ነው፣ ይጣፍጣልና።
እግዚአብሔር ገናና ነው፣ የሚያህለው የለምና።
እግዚአብሔር ትልቅ ነው፣ ሥፍራ አይበቃውምና።
እግዚአብሔር ጥልቅ ነው፣ በዋና አይገኝምና።
እግዚአብሔር ፋሲካ ነው፣ ለሁሉ ታርዷልና።
እግዚአብሔር ዓመት በዓል ነው፣ ለሁሉ ደስታ ነውና።
እግዚአብሔር ጨው ነው፣ ሁሉን ያጣፍጣልና።
እግዚአብሔር ክረምት ነው፣ ሁሉን ያበቅላልና።
እግዚአብሔር አይጠራጠርም፣ ሁሉን ያውቃልና።
እግዚአብሔር አይዘነጋም፣ በሁሉ ድካም የለበትምና።
እግዚአብሔር አይሰጋም፣ የሚያህለው የለምና።
እግዚአብሔር የሰው ሎሌ ነው፣ በክረምት ለማብቀል በበጋ ለማብሰል የተዘጋጀ ነውና።
እግዚአብሔር እንግዳ አይደለም፣ ከጥንት የነበረ ነውና።
ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረው አሁንም ላለ ነገም አለማትን አሳልፎ ለሚኖር አሜን።
+++
ከመጽሐፈ ጨዋታ ወመንፈሳዊ የተወሰደ

ወዳጄ
ምናልባት ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ገጥሞክ ይሆናል
ምናልባት የተሳሳተ ውሳኔ ላይ እንድትደርሺ የሚያደርግ ከባድ ችግር ገጥሞሽ ሊሆን ይችላል
ነገር ግን ከነዚህ ከገጠሙን ችግሮች በላይ እግዚአብሔር ይበልጣል
መድኃኔዓለም ለኢዮብ የሰጠዉን ትእግስት ለሁላችንም ያድለን
ሰናይ ሌሊት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ስላሳያችሁኝ ፍቅር እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ።
( መምህር ብርሃኑ አድማስ )
በፌደራል ፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብዬ መወሰዴን ሰምታችሁ አጋርነታችሁን ላሳያችሁኝ፣ በጸሎት ላስሰባችሁኝ፣ እኔን ባልገጠመኝ ሐዘንንና ጭንቀት ውስጥ ሆናችሁ ለተጨነቃችሁ ሁሉ እግዚአብሔር መከራንና ጭንቀትን ከእናንተ ያርቅላችሁ ዘንድ የእኔ የደካማው ወንድማችሁ ልባዊ ምኞቴ እና ጸሎቴ ነው።
መለቀቄን ከሰማችሁ በኋላም በስልክ፣ በቴክስት፣ በተለያዩ የመልእክት ማድረሻ መንገዶች ሁሉ ስሜትን በሚነኩ ቃላት ላደረሳችሁኝ መልእክት ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
እጅግ ለብዙ ሰዎች ስልኮቻችሁን መመለስ አልቻልኩም። የዚህ ምክንያቱ በግል ስልኬም ሆነ በቢሮ ስልኬ ከዚያም በተለያዩ መተግበሪያዎች በተመሳሳይ ሰዓት እጅግ ብዙ ስልኮች ይመጡ ስለነበር እና በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ማናገር ባለመቻሌ ብቻ መሆኑን እንድታውቁልኝ በታላቅ ትሕትና እጠይቃለሁ። ሌላው ቀርቶ ይህችን የምስጋና መልእክት እስካሁን መጻፍ ያልቻልኩት ፋታ በማጣቴ ምክንያት ነው። ይጨናነቃል ብላችሁ በማሰብ ያልደወላችሁትንም ሁሉ ስለበጎ አሳባችሁ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። በተለያየ መንገድ መልእክት ለጻፋችሁልኝም ምስጋናዬን እያቀረብሁ አንድ ባንድ ለመመለስ ብመኝም የማልችለው መሆኑንም ተገንዝቢያለሁ።
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን። ስለፍቅራችሁ እና ስለ በጎ ሀሳባችሁ ሁሉ እናንተንም እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፣ እግዚአብሔር
ያክብርልኝ

❤#አጭር አስተማሪ ታሪክ ናት አንብቧት📍
📱"አዲስ ተች ስልክ የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . . . ››
💁አባት ፡ “”ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው ? “” ብሎ ጠየቃት፡፡
🤗ልጅ ፡ “”በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር
ለጠፍኩበት . . . “”
አባት ፡ “” እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ ሰው እለ ?””
ልጅ ፡ “” የለም ! ! ! “”
አባት ፡ “”ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . . .””
ልጅ ፡ “”ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው ! ””
አባት ፡ “” የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው ??? “”
ልጅ ፡ “”” በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . . እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ
እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው ! “”
አባት ፡ “”” ስትሸፍኝው . . . ውበቱን አልቀነሰውም “”
ልጅ ፡ “”” እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ
ይከላከልልኛል “”
አባት ፡ በአባትነት ዓይን እያያት “”” አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ. . .
ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው . . . እሺ ትይኛለሽ ወይ ??? ``
ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር ይጠይቀናል በሰው ላይ አድሮ . . . . ብቻ በብዙ
ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !
☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤
፨ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን
ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)
፠ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ
6፥12-14)
፠ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ
ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)
፠ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ
ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
፠ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ
39፥28)
፠ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)
እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን
አሜን (ለምታውቁት ሰው እና መንፈሳዊ ግሩፕ ትልኩ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም አበክሬ እለምናችሃለሁ።
ደቂቀ እስጢፋኖስ
ቤተሰብ ሁኑ
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
📱"አዲስ ተች ስልክ የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . . . ››
💁አባት ፡ “”ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው ? “” ብሎ ጠየቃት፡፡
🤗ልጅ ፡ “”በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር
ለጠፍኩበት . . . “”
አባት ፡ “” እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ ሰው እለ ?””
ልጅ ፡ “” የለም ! ! ! “”
አባት ፡ “”ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . . .””
ልጅ ፡ “”ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው ! ””
አባት ፡ “” የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው ??? “”
ልጅ ፡ “”” በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . . እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ
እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው ! “”
አባት ፡ “”” ስትሸፍኝው . . . ውበቱን አልቀነሰውም “”
ልጅ ፡ “”” እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ
ይከላከልልኛል “”
አባት ፡ በአባትነት ዓይን እያያት “”” አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ. . .
ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው . . . እሺ ትይኛለሽ ወይ ??? ``
ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር ይጠይቀናል በሰው ላይ አድሮ . . . . ብቻ በብዙ
ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !
☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤
፨ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን
ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)
፠ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ
6፥12-14)
፠ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ
ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)
፠ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ
ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
፠ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ
39፥28)
፠ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)
እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን
አሜን (ለምታውቁት ሰው እና መንፈሳዊ ግሩፕ ትልኩ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም አበክሬ እለምናችሃለሁ።
ደቂቀ እስጢፋኖስ
ቤተሰብ ሁኑ
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
Telegram
ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu
❄️❄️❄️እንኳን አደረሳችሁ❄️❄️❄️
❤️❤️❤️ዕርገት ❤️❤️❤️
ከጌታችና ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ “ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡፡ ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል፡፡ በዓለ ዕርገትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በአብ ቀኝ መቀመጡ የሚከበርበት በዓል ነው፡፡ ለዚህም መሰረት እንዲሆን አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አበው “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ…/ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ…” ብለው ዕርገቱን በቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢነት አስረግጠው ደንግገዋል፡፡
ዕርገቱ የትሕትና ሥራው የመፈጸሙ ምልክት ነው
አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነዉ። ስለዚህ ጌታችን በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም:: ‘ወረደ፣ ተወለደ’ ሲባል ፍጹም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም:: በምድር ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ:: እንዲሁም ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋዉ የተደረገዉን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋዉ በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ ስልጣኑን ያሳያል።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ እንዲሁም “ዓረገ ውስተ አርያም ጼዊወከ ጼዋ፣ ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው – ምርኮን ማርከህ ወደ አርያም ወጣህ፣ ለሰው ልጆችም ጸጋህን ሰጠሃቸው”(መዝ.፷፯፣፲፰) እንዳለው ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ መንፈስ ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት /ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ “ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታችንን በአየር እንቀበለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን” (፩ተሰ. ፬፡፲፯) ብሏል፡፡
ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ/” ብሏል፡፡ ‘ዐረገ’ መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በእመቤታችን ጀርባ መታዘሉን ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናትና። ከማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል” (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው። ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል”(መዝ.፷፯፥፴፫) ብሎ የዘመረው ይህንኑ ያጠይቃል፡፡ ምሥራቅ የተባለች የድንግል ሥጋ ተዋሕዶ ዓርጓልና
ይቀጥላል
Share share

ካለፈው የቀጠለ
እስከ ቢታንያም አወጣቸው
በዓለ ዕርገት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ክብርፐ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን (ከበዓለ ትንሣኤ አርባኛው ቀን) አይለቅም። የጌታችን ዕርገት ከትንሣኤ በኋላ በአርባኛው ቀን (በስድስተኛው ሐሙስ) የሚከበረው ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው” (ሐዋ. ፩፡፫) በማለት የጻፈውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም ይህንን ትምህርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡
ዕርገቱም የተፈጸመው ስለ ምጽአቱ ባስተማረበትና ዳግም ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት በደብረ ዘይት ተራራ ነበር፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ይህንን “እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ” (ሉቃ ፳፬፡፶) ብሎ በወንጌሉ እንዲሁም “በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው” ብሎ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩፡፩፪ አስፍሮታል፡፡
በልደቱና በትንሣኤው የተገኙትና ለሰው ልጆች መልካሙን ዜና ያበሰሩት ቅዱሳን መላእክት በዕርገቱም ተገኝተው ለአሥራ አንዱ ሐዋርያት የዳግም ምጽአቱን ነገር አሳስበዋቸዋል፡፡ ቅዱስ ሉቃሰ ይህንን ሲገልጽ “እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው ” (ሐዋ ፩፡፲-፲፩) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም እንደተናገረው እርሱ ዳግም ሲመጣ ሐዋርያቱ ብቻ ያይደለ የወጉት ጭምር ያዩታል (ራዕ ፩፡፯)፡፡
ሐዋርያቱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ
የጌታችን ዕርገት በመርቀቅ /በርቀት/ ሳይሆን ቀስ በቀስ ሐዋርያት እያዩት በመራቅ /በርኅቀት/ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ይህንን ሲያስረዳ “ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው ” (ሐዋ ፩፡፱) በማለት ገልፆታል፡፡ ይህም የሚያመለክተው የሚታይ የሚዳሰስ ሥጋን ይዞት እንዳረገ ነው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በቅዳሴው “በአካል ወደ ሰማይ ባረግህበት ዕርገትህ ላይ” እንዳለው በአካል ነው ወደ ሰማይ ያረገው። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በቅዳሴው “በዚያች ሥጋ በመለኮት ኃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀድሞ አኗኗሩ ዐረገ” ያለው ይህንን ለማመልከት ነው፡፡ ይህንን ሲያብራራ “ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሔደ፣ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፡፡ ሥጋው አልተለወጠምና” በማለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞቱና ከትንሣኤው አስቀድሞ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ በለበሰው ሥጋ ወደ ሰማይ ማረግም እንደሚቻለው አስረድቷል /ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ክፍል ፲፫ ምዕ.፥፹፯፡፲፪-፲፫/፡፡ ቅዱስ ሉቃስም “እያዩት ከፍ ከፍ አለ” ማለቱ በእርግጥ ዕርገቱ በአካል እንደነበር ያስረግጥልናል፤ ምክንያቱም ሰው መለኮትን መመልከት አይችልምና ።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ስለ ጌታችን ዕርገት “በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲመገብ እጁን በደቀ መዛሙርቱ ላይ አኖረ፤ እያንዳንዳቸውንም ባረካቸው ከዚያም የእሳት ደመና ተቀበለው፤ ከእነርሱም ሰወረው፤ በጨርቅ የጠቀለሉት ይህ ሥጋ በኪሩቤል ክንፎች ተጋረደ፤ በጒልበት ያቀፉት ይህ ሥጋ በእሳት ሠረገላ ተቀመጠ፤ በዚህ ዓለም የተራበና የተጠማ ይህ ሥጋ እህል መብላት፤ ወይን መጠጥን ውሃም መጠጣት ወደ ማይሻበት ወደ አርያም ከፍታ ወጣ፤ በሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችና በጲላጦስ አደባባይ ራቁቱን የቆመ ይህ ሥጋ በምስጋና መብረቅ ተሸፈነ፤ በእሳት ደመናም ተጋረደ፤ ጉንጮቹን በጥፊ የተመታ ይህ ሥጋ ከፍ ከፍ አለ” ብሏል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ የጌታችንን ዕርገት በገለጸበት አንቀጽ “ጌታችን ኢየሱስም ከተነጋገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፥ በአባቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡” (ማር. ፲፮፡፲፱) ብሏል፡፡ “ወደ ሰማይ” የሚለው ቃል ወደ ሰማየ ሰማያት ማለት ነው ። ይህም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሚሠራበት ወቅት በጸለየው ጸሎት ውስጥ እግዚአብሔርን “በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!” (፩ኛ ነገ. ፰፡፪፯) ብሎ በጸለየው ይታወቃል። “ዐረገ” የሚለውም ( መላእክት አሳረጉት አላለም) በራሱ ኃይል ሥልጣንና ማረጉን ያሳያል፡፡ ከጌታችን በቀር በራሱ ኃይል ያረገ የለም። ሌሎች ቅዱሳን፡ ለምሳሌ ኤልያስ እና ሄኖክም ቢሆኑ እግዚአብሔር ዐሳረጋቸው እንጂ በራሳቸው ስልጣን ዐላረጉም ።
ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይህንን “የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለ መሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን (ጉም) ዐረገ፤ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና፤ ነገደ መናብርት ሊያሳርጉት አልመጡም ርሱ ራሱ በመለኮቱ ኀይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው” ሲል ገልጾታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም ስለ ዕርገት በተናገረበት አንቀጽ “በራሱ ሥልጣን ተነሣ፤ ርሱን ያስነሣው ማንም አይደለም፤ በሚያርግም ጊዜ ማንም ርሱን ያሳረገ አይደለም፤ ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካይነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚኽም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት (፪ኛ ነገ ፪፥፲፩)፤ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈው ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኰራኲር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኰራኲር አያስፈልገውም” በማለት የእርሱ ዕርገት በራሱ ስልጣን መሆኑን አብራርቶታል፡፡
የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል

የመጨረሻው ክፍል❤️
👉በአብ ቀኝ ተቀመጠ
ጌታችን በዕርገቱ “በአብ ቀኝ ተቀመጠ” መባሉ ለእግዚኣብሔር ግራና ቀኝ ፥ታችና ላይ ኖሮት ሳይሆን ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን በስልጣን እኩል መሆናቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ፪፡፯ “ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰዉም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። እንደ ሰዉም ሆኖ ራሱን አዋረደ” የሚለዉ ቃል ጌታችን በሥጋዌው ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አደረገ እንጅ በክብር ከአብ ከመንፈስቅዱስ እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት በሥልጣን አንድ መሆንን ያሳያል፡፡ ስለዚህም ነቢዩ ዳንኤል በትንቢቱ “በሌሊትም ራእይ አየሁ፤ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ፤ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘለዓለም ግዛት ነው፣ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፡፡” (ዳን. ፯፡፲፫-፲፬) ሲል ተናግሯል፡፡
ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል በክብር በልዕልና ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው። ይህም ከተዋሕዶ በፊት ደካማ፣ በደለኛ እና ውርደት ይስማማው የነበረው የእኛ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ጸጋን የሚያድል፣ እውነተኛ ፍርድን የሚያደርግ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን ያለው እውነተኛ ፈራጅ አምላክ እንደሆነ ለመግለጽ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብ ሥልጣን ዝቅ ያለበት የዐይን ጥቅሻ ያህል ጊዜ እንኳ የለም። “ቀኝ” የሚለው ቃል ኃይልን ቅድስናን ወይም ክብርን የሚያመለክት ነው ። ኃይልን ከመግለፅ አኳያ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት “የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” (መዝ. ፩፲፯፡፲፭) ሲል ተናግሯል፡፡ ክብርም ከመግለጽ አኳያ “ጻድቃንን በቀኙ ያቆማቸዋል” (ማቴ. ፳፭፡፴፫) እንላለን፡፡ ስለዚህም “የእግዚአብሔር ቀኝ “ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ፣ ጽድቅ ፣ ክብር ማለት ነው፡፡ ይህም በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህልም ያህልም የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡
ጌታ ጌታዬን፡- ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። (መዝ. ፻፱፡፻)
ከእንግዲህ ወዲህ የሰውን ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው። (ማቴ ፳፮፡፷፬)
እነሆ፥ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ። (ሐዋ ፯፡፶፮)
ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፣ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፡፡ (ዕብ ፩፡፫)
በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ (ዕብ ፰፡፩)
እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና፡፡ (ዕብ ፲፪፡፪)
☁️የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤው በተስፋ ለምንጠብቀው ትንሣኤያችን አርአያ እንደሆነው ዕርገቱም ለዕርገተ ነፍሳችን፣ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረሳችን አርአያ ምሣሌ ነው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ፡፡ ከእኛ የተዋሐደዉን ሥጋ በዕርገቱ ከአባቱ ቀኝ በእግዚአብሔርነቱ አስቀመጠው፡፡ እንግዲህ በዕርገቱ የእኛን ሥጋ ከመላዕክት ሁሉ በላይ አክብሮ በሰማያት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስተካክሎ ካስቀመጠውማ እንደምን እኛን መንግሥተ ሰማያትን አያወርሰንም ሊባል ይችላል? (፩ተሰ. ፬፡፲፯) ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን እንደምንቀመጥ የጌታችን ዕርገት ያረጋግጥልናል። የጌታችን ዕርገት ዓይነ ልቡናችንን እሱ ወደ አለባት መንግስተ ሰማያት ይመራል።
ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲያስረዳ እንዲህ ሲል ይላል፡፡ “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ በአለበት በላይ ያለውን ሹ፡፡ የላይኛውን አስቡ ፤ በምድር ያለውንም አይደለም። እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋራ በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰወረች ናትና። ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ ያንጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር ትገለጣላችሁ።” (ቆላ. ፫፡፩-፬)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ የተስፋ ቃል ኪዳን ሰጥቶ ነበር። ለምሳሌ “እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡” (ዮሐ. ፲፮፡፯) ብሏል፡፡ እርሱ በአካል ስለሚለያቸው የሐዘን ሰሜት እንዳይሰማቸው የሚያጽናና መንፈስ እንደሚልክላቸው ከሞቱ አስቀድሞ “አብ በስሜየሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል”(ዮሐ ፲፬፥፮) ብሎ ነግሯቸዋል።
ከምድራዊ አስተሳሰብና ከስጋ መንፈስ እንዲላቀቁ “እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ እናንተ ግን ኃይልን ከላይ እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ሉቃ ፳፬፥፵፱ ብሏቸዋል። ይህንን ተስፋ በማመን ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለዉ ይመለከቱ የነበሩት ደቀ መዛሙርት በሃምሳኛዉ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል። እኛም ዕርገቱን እያሰብን ዓይናችንን ወደ ሰማይ እናነሳለን። የራሳችንንም ዕርገት ተስፋ እያደረግን ልባችንን ወደ ሰማያዊዉ ህይወት ከፍ ከፍ እናደርጋለን። በክብር ያረገ አምላክ ከትንሣኤ ሙታን በኋላ ያለውን ዕርገታችንን የክብር ያድርግልን።
ለብርሃነ እርገቱ ያደረሰን አምላክ ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም ያድርሰን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- astemehero.com
ደቂቀ እስጢፋኖስ
ሼር ማድረግ አትርሱ

ገብርኤል መላከ ራማ
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
ገብርኤል
ገብርኤል (፪)
ገብርኤል መልአከ ራማ (፪)
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ
ድምጽህን እናስማ
ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪)
አዝ
ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪)
አዝ
የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪)
አዝ
አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለአለም (፪)
መዝሙር በዘማሪ
አቤል መስፍን
ገብርኤል (፪)
ገብርኤል መልአከ ራማ (፪)
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ
ድምጽህን እናስማ
ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪)
አዝ
ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪)
አዝ
የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪)
አዝ
አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለአለም (፪)
መዝሙር በዘማሪ
አቤል መስፍን
ይህን ቃል የሌላ ቤት እምነት ነው የሚሉ ስላሉ Share አድርጉ ⁉
🌹ሃሌሉያ🌹
"ብዙዎቻችን ሃሌሉያ ብለን ለማመስገን እንቸገራለን ምክንያቱም የሌሎች እምነት ተከታዮች በሆነው ባልሆነው ሃሌ ሉያ ስለሚሉ የእነሱ መገለጫ አድርገን እንድናስብ ስላደረጉን በዚህ ምስጋና ለማመስገን እንቸገራለን። ነገር ግን ይህ ምስጋና ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን በቅዳሴ፣ በማህሌትና በሰአታት የሚያመሰግኑበት ታላቅ ምስጋና ነው።
ሃሌሉያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ከተተረጎመው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጽሐፈ ሰዓታት ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ፦
"ሃሌ ሉያ ማለት፦ ሃሌ ሉያ (Hallelujah) ሃሌ ሉያህ የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን በዕብራይስጥ "ሃሌል" ማለት የሚመሰገን፣ ለምስጋና የተገባ፣ ምስጉን ማለት ሲሆን "jah" (ያህ) የሚለው ቀል "ያህዌ"ማለት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ጌታ መጠሪያ ነው። እኒህ ሁለቱ ቃላት አንድ ላይ "ሃሌሉያ" ሲባሉ "ምስጉን ጌታን እናመሰግነዋለን" ማለት ሲሆን ሁለቱን ቃሎችን ለያይተን ስናነባቸው ደግሞ "ምስጋና ለጌታ ይሁን" ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይም ከ32 ጊዜያት በላይ ተገልጿል። በተለይ ቅዱስ ዳዊት በተደጋጋሚ ምስጉን የሆነውን ጌታውን በዚህ ምስጋና አመስግኖበታል።
"በዚህ ምስጋና የጻድቃን በኅብረት እንደሚያመሰግኑት ቅዲስ ዳዊት በመዝሙ " ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፤ ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።"(መዝ 149፥1) በማለት ጠቅሶታል። በአፀደ ሥጋ በአፀደ ነፍስ በገነት ያሉት የቅዱሳን ጉባኤ እንደሚያመሰግኑት ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም በዚሁ ቃል ፈጣሪያቸውን እንደሚያመሰግኑ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ላይ" ደግመውም ሃሌ ሉያ አሉ፤ ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።
"ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር። አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት።ድምፅም ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ ሲል ከዙፋኑ ወጣ። እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውኃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሃሌ ሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።" በማለት የመላእክትን ምስጋና ገልጿል። ራእ.19፥3-6
መዝ 104, 105,106,148,150....
እንዲሁም አባቶቻችን በማኅሌቱ ባማረ ዜማ እያደመቁ አምላክን የሚያመሰግኑበት ድንቅ ቃል ነው
"ስለዚህ እኛም እንደ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን አምላካችንን ሃሌ ሉያ ብለን ልናመስገን ይገባል እንጂ የመናፍቃኑ መገለጫ አድርገን ልናስብ አይገባም።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
ሼር SHARE

በታላቅ ሥነ ሥርዐት እየተከበረ ነው።
ደብረ ምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ሕንጻ ቤተ መቅደሱ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በመቶሽ የሚቆጠር ምእመናን በተገኙበት በዓሉ በአማረና በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
እንኳን አደረሳቹሁ የእምዬ ተዋሕዶ ልጆች