Happy feast of the nativity of ChristOur Lord and Savior Jesus Christ is born
“For your fore birth is known by your latter birth” (Arganon, Tuesday no 48)
#Happy_Holiday

ኦ ዝ መንክር
ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ
እማርያም እም ቅድስት ድንግል
መጸአ እንዘ ኢይወፅእ እም አቡሁ
ወረደ እንዘ ኢይትፈለጥ እምህላዌሁ
ወረደ እንዘ ኢየሐፅፅ በላዕሉ ወኢይትዌሰክ በታሕቱ
ኃደረ ውስተ ሥጋ ወለት እንዘ ኢየዐርቅ እመንበሩ
ወኮነ ሕፃነ ዘይሥዕሎሙ ለሕፃናት በውስተ ማሕፀን
ወጠብለልዎ በአፅርቅት ለዘይትዐፀፍ ብርሃነ
ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ
ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከአባቱ ሳይወጣ መጣ
ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ
ከላይ ሳይጎድል ከታችም ሳይጨመር ወረደ
ከመንበሩ ሳይለይ በድንግል ማሕፀን አደረ
ሕፃናትን በማሕፀን ውስጥ የሚፈጥር አምላክ ሕፃን ሆነ
ብርሃንን የሚጎናፅፈውን አምላክ በጨርቅ ጠቀለሉት
ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ
እማርያም እም ቅድስት ድንግል
መጸአ እንዘ ኢይወፅእ እም አቡሁ
ወረደ እንዘ ኢይትፈለጥ እምህላዌሁ
ወረደ እንዘ ኢየሐፅፅ በላዕሉ ወኢይትዌሰክ በታሕቱ
ኃደረ ውስተ ሥጋ ወለት እንዘ ኢየዐርቅ እመንበሩ
ወኮነ ሕፃነ ዘይሥዕሎሙ ለሕፃናት በውስተ ማሕፀን
ወጠብለልዎ በአፅርቅት ለዘይትዐፀፍ ብርሃነ
ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ
ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከአባቱ ሳይወጣ መጣ
ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ
ከላይ ሳይጎድል ከታችም ሳይጨመር ወረደ
ከመንበሩ ሳይለይ በድንግል ማሕፀን አደረ
ሕፃናትን በማሕፀን ውስጥ የሚፈጥር አምላክ ሕፃን ሆነ
ብርሃንን የሚጎናፅፈውን አምላክ በጨርቅ ጠቀለሉት
ንዑ ርእዩ
"ንዑ ርእዩ ዘንተ መንክረ ወዘምሮ ዘምሩ በእንተ ምሥጢር ዘተከስተ ለነ /2/
እስመ ዘኢይሰባእ ተሰብአ ቃል ተደመረ ወዘአልቦ ጥንት ኮነ ቅድመ ወለዘአልቦ መዋዕል ኮነ ሎቱ መዋዕል" /2/
"ኑ ይህን ድንቅ ነገር እዩ ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋናን አቅርቡ /2/
ሰው የማይሆነው አምላክ ሰው ሆኖአልና ቃል ተዋህዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት"/2/

በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።
በደብረሊባኖስ ገዳም በጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል ውስጥ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉም ታውቋል።
በትላንትናው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በገዳሙ የጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል በተነሳው የእሳት አደጋ ከ20 በላይ ክፍሎች የወደሙ ሲሆን እሳቱ ሌሎች አደጋዎችን እንዳያደርስ በገዳሙ መነኮሳት፣ በአካባቢው ምእመናን እና በጸጥታ ኃይል አባላት ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

የ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም የጌታችን፣የአምላካችን፣የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተከናወነ።
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመ/ፓ/ጠ/ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር )የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲያቸው ውስጥ የጽዳት ዘመቻ አከናወኑ።
በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ሥር ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ የግቢ ጉባኤ አባላት ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 2፡00 ሰዓት ጀምረው የሚማሩበትን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ እና መመገቢያ አዳራሽ በማጽዳት ትልቅ አርአያነት ያለው ተግባር አከናውነዋል።
ከ400 በላይ የሚሆኑት እኒህ ኦርቶዶክሳውያን የግቢ ጉባኤ አባላት የጽዳት ዘመቻውን ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋናው ምክንያት ዩኒቨርስቲው ለተማሪዎቹ ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ባከናወኑት ተግባርም ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በጽዳት ዘመቻው ወቅት ዩኒቨርስቲውን በመወከል የተገኙት የግቢ ውበት አስተባባሪ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ አባይነህ እንዳሉት በግቢ ጉባኤ ተማሪዎቹ የተከናወነው የጽዳት ዘመቻ እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ይህ አገልግሎታቸው የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳይሆን አደራ ብለዋል። አክለውም ዩኒቨርስቲው በቀጣይ በሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ ከጎናቸው እንደሚሆንም አሳውቀዋል።
በተጨማሪም የወቅቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሪዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ እና የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ሌምቤቦ ሰሎሞን የአባላቱን ተግባር አበረታተው እናንተን ይዘን የማንፈታው ችግር አይኖርም ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
የግቢ ጉባኤው ሰብሳቢ ተማሪ በላይ ደምሌ የግቢ ጉባኤ አባላቱ በዘመቻው ወቅት ላሳዩት ንቁ ተሳትፎ ምስጋናውን አቅርቧል።
ይህ የዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተግባር ተማሪዎች ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው በተጨማሪ ለሀገር አለኝታነታቸውን ያሳዩበት እንቅስቃሴ በመሆኑ እጅግ ሊበረታታ የሚገባው ተሞክሮ ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
የስም ትርጓሜ፡-
ዮሐንስ የሚለው ስም ዮሐናን ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “ከያሕዌ ወይንም ከእግዚአብሔር የተሰጠ” ማለት ነው ሲሉ ብዙ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡በተጨማሪም ዮሐንስ ማለት “የእግዚአብሔር ጸጋ ፤ደስታ ማለት ነው፡፡ በትርጓሜ ወንጌል “ዮሐንስ ማለት ፍስሐ ወሐሴት ማለት ነው ይላል። ከአባቱ ከዘብዴዎስና ከእናቱ ከማርያም ባውፍልያ መስከረም አራት ቀን እንደተወለደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ ያዕቆብ የሚባል ወንድም ነበረው /ማቴ ፬፥፳፩፤ማር ፩፥፳፤ማቴ ፳፥፳/፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ቅጽል ስሞች አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
“ቦአኔርጌስ-ወልደ ነጐድጓድ”፡- የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በመግለጡና ለጌታችን ባለው ቅንዓት ባሳየውም የኃይል ሥራ የተሰጠ ስም ነው፤ /ማር.፫፡፲፯፡፡
ታኦጎሎስ፡- የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት እንዲሁም ምሥጢረ ሥጋዌን አምልቶና አስፍቶ በመጻፉ፣ ይህ ሥያሜ ተሰጥቷል፡፡
ነባቤ መለኮትም፡- የመለኮትን ነገር በምሥጢር የሚናገር ማለት ነው፡፡
አቡቀለምሲስ፡- ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት ይህ ስም ተሰጥቶታል ትጉሙም የራእይ አባት ማለት ነው፤ እንዲሁም ኃላፍያትንና መጻእያትን ስለሚናገር “አቡቀለምሲስ-ረአየ ኅቡአት- ተብሏል፤ ባለ ራዕይ” ማለት ነው፡፡
ቁጹረ ገጽ- የጌታን ጸዋትወ መከራ አይቶ ፊቱ በኃዘን ተቋጥሮ ይኖር ስለ ነበር “ቁጹረ ገጽ- ፊቱ በሐዘን የተቋጠረ” ተብሏል፡፡
ፍቁረ እግዚእ፡- ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም “ጌታ ይወደው የነበረ ደቀ መዝሙር” ተብሎ ስለ ተጠቀሰ “የጌታ ወዳጅ- ፍቁረ እግዚእ” ተብሏል /ዮ.፲፫ሐ፡፳፫/፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንሰን ባሕረ ጥበባት፣ አበ ልሳናት፣ ንስር ሠራሪ ልዑለ ስብከት፡፡ ዮሐንስ ወንጌላዊ ረአዩ ኀቡአት እያለችም ታወድሰዋለች፡፡ ዮሐንስ ዘንሥርም ይባላል
ለወንጌላዊነት በጌታ ስለመጠራቱ፡-
ቅዱስ ዮሐንስ በመጀመርያ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙር ነበር፤ /ዮሐ.፩፡፴፭-፵/፡፡ በኋላ ግን ከታላቅ ወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ዓሣ በመረብ ሲያጠምድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅፍርናሆም ከተማ በገሊላ አጠገብ ሳለ ጠራው /ማቴ.፬፡፳፩/፡፡ እርሱም ወዲያው ከወንድሙ ጋር ታንኳይቱንና አባቱን ትቶ ተከተለው፡፡ እርሱም በወጣትነቱ ጌታን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከተከተለ በኋላ በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያሳለፈው ጊዜ፡-
ጌታችን ግርማ-መንግሥቱን ሲገልጥ /ማቴ.፲፯፡፩/፣ የኢያኢሮስን ልጅ ሲያነሣ /ማር.፭፡፴፯/፣ በጌቴ ሴማኒ የአታክልት ቦታ ሲጸልይ /ማቴ.፳፮፡፴፯/፣ ስለ ኢየሩሳሌም መጥፋት ትንቢት ሲናገር /ማር.፲፫፡፫/ ዮሐንስ አብሮ ስለ ነበር “የምሥጢር ሐዋርያም ”ይባላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ አዕማደ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ከሚጠራቸው ሐዋርያት አንዱ ዮሐንስ ነው /ገላ.፪፡፱/፡፡ ከሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በተለየ አኳኋንም ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት፣ ምሥጢረ መንግሥትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ ነብር፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ስለመቀበሉ፡-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ከእመቤታችን ጋር ከእግረ መስቀሉ ባየው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ፣ ያጽናናሽ”፤ ብሏታል፡፡ ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስንም “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎታል፡፡ ዩሐ. ፲፱፥፳፮፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ “እነሆ ልጅሽ ያጽናናሽ” ማለቱ ለክርስቲያኖች በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን፣ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ዮሐንስ “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ማለቱ እኛን እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስራ አምስት ዓመት በቤቱ ቆይታለች፤ መላእክት ሲያሳርጓትም አብሮ ሂዶ ያረፈችብት ዕፀ ሕይወት ስር መሆኑን ለቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡
አግልግሎቱ ፡-
የፍቅረ እግዚአብሔርን እና የፍቅረ ቢጽን ጠቃሚነት በስፋት የጻፈ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ መምህረ ወንጌል የሃይማኖት መጋቢ ነው፡፡ ሕዝብንና አሕዛብን፣ ፍጡርንና ፈጣሪን በብቃት ያገለገለ ታላቅ ሐዋርያ ነው። ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው:: በኤፌሶን- የጥንቷ ታናሽ እስያ የአሁኗ ቱርክ በምተባለው ቦታ አስተምሯል::
ከሮምና ጋር ያሰላፈው ጌዜ፡
ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ:: ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው:: በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች:: ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ:: ግን ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ:: ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ፵ ቀናት ሳይመገብ ቆየ:: በ፵ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው:: ፪ቱ ቅዱሳን በተገናኙ ጊዜ እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ::
ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች:: ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩም ስለአለተቀበሉት ወደ ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ:: ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት ፪ቱን ቅዱሳን የውሽባ ቤት እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው:: ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ:: ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ሆኖ ሳለ ደንግጦ እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው:: ሮምና እና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ፤ ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው:: ሐዋርያው ይህንን ታግሶ በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ፣ በመስቀልም ባረከውና በጌታችን ስም አስነሳው:: በዚህ ጊዜም ሮምና “ወዮልኝ አንተ ጌታ ክርስቶስ የምተባለው ነህ?” አለችው፤ “አይለሁም፤የእርሱ ደቀመዝሙር ነኝ” አላት፡፡ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ:: እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምህርተ ሃይማኖትንና ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው :: በስመ ሥላሴ አጥምቆ ካህናትን ሹሞ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል::

በኋላም ለሮምና እና ለደሴቷ ሰዎች መልእክትን ጽፎላቸዋል:: ይህች መልእክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልእክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጓዘው ወደ ኤፌሶን ነው:: በዚህች ከተማ በተአምራት አርጤምስን አጠፋ፡፡ በዚያው ቦታ ጉድጓድ ከአስቆፈረ በኋላ ‘’የቀረ የለም ወደ ፊት እኔንም አታዩኝም’’ አላቸው፡፡ እነርሱም ባዘዘቸው መሠረት ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሳለ አልቀሰው ሳሙት፤ ከዚያ በኋላ ከጉድጓዱ በመጡ ጊዜ ተሰወራቸው፡፡ በመጨረሻም ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው ፺ ዓመት በሆነው ጊዜ በጥር አራት ዕለት ተሰውሯል::
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለእግዚአብሔር
በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!
እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው።
በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው።
በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችኋል።
እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል።
በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ