ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
27.2K subscribers
3.01K photos
39 videos
4 files
311 links
The channel of mahibere kidusan
Download Telegram
ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
Photo
አዲስ መረጃ
""""""""""""
መጋቢት ፲፱/ ፳፻፲፭ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን

ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር አስገብተዋል።

ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል። በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ 6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል።
ምንጭ፡ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 24/2015 ዓ.ም "እኔ የተዋሕዶ ድምፅ ነኝ! እናንተስ?" ልዩ ጉባኤ ይካሄዳል።

"እኔ የተዋሕዶ ድምፅ ነኝ! እናንተስ?" በሚል መሪ ቃል ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ የስቱዲዮ እቃ፣ መኪና እና ጄኔሬተር በአስቸኳይ ለመግዛት ገቢ እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱን ለመደገፍ

ጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ
https://www.gofundme.com/f/gtbbd?utm_source=customer...

ወገን ፈንድ
Www.wegenfund.com/mk01

የባንክ አካውንት ቁጥር አማራጮች
****
ንግድ ባንክ 1000010822657 (BETH.TEW.SENBET.TBET MAHIB.KID
+++++++++++++++++++++++++
ወጋገን ባንክ 0039595010103
+++++++++++++++++++++++++
አቢሲንያ ባንክ 4753388
+++++++++++++++++++++++++
ዳሸን ባንክ 0088872166011
+++++++++++++++++++++++++
አዋሽ ባንክ 01304800017700
±++++++++++++++++++++++
አሐዱ ባንክ 0003488710101
+++++++++++++++++++++
አማራ ባንክ 9900017695658
+++++++++++++++++++++
ኦሮምያ ኅብረት ስራ ባንክ 1033100028173
ሕጻናት ሆይ የኔታ ጥዑም ይጠብቋችኋልና ደውሉ! ተሳተፉ!

ወላጆች ልጆቻችሁ በሃይማኖት በምግባር የሚያድጉበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ነውና በመደገፍ ከበረከቱ አሳትፏቸው ጥሪያችን ነው!

''እኔ የተዋሕዶ ድምፅ ነኝ እናንተስ'' 4ኛ ዙር ጉባኤ እና ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 24/2015 ዓ.ም ተዘጋጅቷል::

አገልግሎቱን ለመደገፍ

ጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ
https://www.gofundme.com/f/gtbbd?utm_source=customer...
ወገን ፈንድ
Www.wegenfund.com/mk01
የባንክ አካውንት ቁጥር አማራጮች
****
ንግድ ባንክ 1000010822657 (BETH.TEW.SENBET.TBET MAHIB.KID
+++++++++++++++++++++++++
ወጋገን ባንክ 0039595010103
+++++++++++++++++++++++++
አቢሲንያ ባንክ 4753388
+++++++++++++++++++++++++
ዳሸን ባንክ 0088872166011
+++++++++++++++++++++++++
አዋሽ ባንክ 01304800017700
±++++++++++++++++++++++
አሐዱ ባንክ 0003488710101
+++++++++++++++++++++
አማራ ባንክ 9900017695658
+++++++++++++++++++++
ኦሮምያ ኅብረት ስራ ባንክ 1033100028173
''እኔ የተዋሕዶ ድምፅ ነኝ እናንተስ'' 4ኛ ዙር ጉባኤ እና ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 24/2015 ዓ.ም ተዘጋጅቷል::
እሑድ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንና ዩቱዩብ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።

አገልግሎቱን ለመደገፍ
ጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ
https://www.gofundme.com/f/gtbbd?utm_source=customer...
ወገን ፈንድ
Www.wegenfund.com/mk01
የባንክ አካውንት ቁጥር አማራጮች
****
ንግድ ባንክ 1000010822657 (BETH.TEW.SENBET.TBET MAHIB.KID
+++++++++++++++++++++++++
ወጋገን ባንክ 0039595010103
+++++++++++++++++++++++++
አቢሲንያ ባንክ 4753388
+++++++++++++++++++++++++
ዳሸን ባንክ 0088872166011
+++++++++++++++++++++++++
አዋሽ ባንክ 01304800017700
±++++++++++++++++++++++
አሐዱ ባንክ 0003488710101
+++++++++++++++++++++
አማራ ባንክ 9900017695658
+++++++++++++++++++++
ኦሮምያ ኅብረት ስራ ባንክ 1033100028173
ኒቆዲሞስ
ሰው ሥልጣን ቢኖረው ዕውቀት ሊጎድለው እንዲሁም ሀብት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ማካበት ያዳግተዋል፡፡ ሀብት ቢኖረውም እንኳን ዕውቀት ይጎድለዋል፤ ሥልጣንም አይኖረውም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡
 
ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውን ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ሁሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሄድ ነበር፡፡ ፈሪሳውያን ማመን በተሳናቸው በዚያን ጊዜ ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፣ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡
 
እናውቃለን በማለት የሚመካኙ በርካታ ሰዎች ከመልካም ነገር ሲከለከሉ እርሱ ግን “ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡” ቀርቦም እንዲህ አለው፤ ‹‹መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡›› ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም›› አለው፡፡
 
ነገር ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ ስላልተገለጠለት ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጌታን መልሶ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡››
 
አሁንም ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› በማለትም ጌታን ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም…›› በማለት አስረድቶታል፡፡ (ዮሐ.፫፥፪-፲፭)
 
የዓለም መድኃኒት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች ሰዓት፣ ሐዋርያት በተበተኑባትና አይሁድ በሠለጠኑባት ጊዜ እንኳን ከጌታችን ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ እንዲሁም ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ ሰው ኒቆዲሞስ ነው፤ ስለዚህም ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡
 
ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን ገልጾ ያዳነውና ያከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛም ምሥጢሩን ይገልጽልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
 
መልካም ዜና፤ በዕለተ ሆሳዕና!

እኔ የተዋሕዶ ድምፅ ነኝ የመዝጊያ መርሐ ግብር በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴዴራል እሑድ ከ9 ሰዓት ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣መዘምራን እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል።

ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከየካቲት 30 ጀምሮ የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብር እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ጎ ፈንድ ሚ ማስፈንጠሪያ
https://www.gofundme.com/f/gtbbd?utm_source=customer...

ወገን ፈንድ
Www.wegenfund.com/mk01

የባንክ አካውንት ቁጥር አማራጮች
****
ንግድ ባንክ 1000010822657 (BETH.TEW.SENBET.TBET MAHIB.KID
+++++++++++++++++++++++++
ወጋገን ባንክ 0039595010103
+++++++++++++++++++++++++
አቢሲንያ ባንክ 4753388
+++++++++++++++++++++++++
ዳሸን ባንክ 0088872166011
+++++++++++++++++++++++++
አዋሽ ባንክ 01304800017700
±++++++++++++++++++++++
አሐዱ ባንክ 0003488710101
+++++++++++++++++++++
አማራ ባንክ 9900017695658
+++++++++++++++++++++
ኦሮምያ ኅብረት ስራ ባንክ 1033100028173
ዕለተ አኮቴት (የምሥጋና ቀን) በማኅበረ ቅዱሳን ሁሉም ማእከላት እየተከበረ ይገኛል።

መጋቢት 29/2015  ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን በሁሉም መዋቅሮች ውስጥ የሚገኙ አባላት በጋራ በመሆን በአቅራቢያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በመሰባሰብ ስለ አገልግሎታቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በቀጣይም አብሯቸው እንዲሆን እየጸለዩ ይገኛሉ።

አዲስ አበባ የሚገኙ የማኅበሩ የዋና ማእከል እና የአዲስ አበባ ማእከል አባላት በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ደብር በመገኘት መርሐ ግብሩን እያከናወኑ ይገኛሉ።