Forwarded from Her Glow Bar
ሊኖርሽ የሚገቡ እቃዎች 🛍
ሚኒ ዋሌት : 550 ብር
የቦርሳ መስታወት : 500
ቀበቶ : 400
ጆሮ ጌጥ እሽግ 1800 በፍሬ 350
የሽቶ መቀነሻ : 300
የእግር ማለስለሻ ካልሲ :650
የቅባት / ሎሽን መቀነሻ : 1000
የፅጉር እስቲም : 1300
📩 ለማዘዝ @SamriiGetu
✨ነፃ ዴሊቨሪ በተወሰኑ አካባቢዎች አለን እንዲሁም ለነጋዴ በብዛት እና በቅናሽ እናስረክባለን!
🚨በቅርብ ጊዜ ውስጥ Giveaway ስለሚኖረን
ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ!

❤1🔥1
የተለያዩ አዲስ የስፌት ማሽኖችን የመገጣጠም እንዲሁም የተበላሹትን የመጠገን ሥራ እንሠራለን።
-ማሽኖ ክር ይበጥሳል? ወይስ በትክክል አይሰፋም?
-ያልተለመደ ድምጽ እየሰጠ ነው?
-የማሽን ክፍል በትክክል አይሰራም?
-ከመጠን በላይ ሙቀት ወይም ሙቀት አስተውለዋል?
የምንገጣጥማቸው እና የምንጠግናቸው የልብስ የማሽን አይነቶች:-
-ሲንግል ኒድል
-ከቨር ስቲች/ኦቨር ሉክ
-ኢምፕሮደሪ/የጥልፍ ማሽን
-ኢንተር ሎክ
-በተን አታች(ቁልፍ የሚተክል)
-በተን ሆል
-ራውንድና ስትሬት ናይፍ
ለበለጠ መረጃ:- +251925447525 ወይም username @amanu97 ላይ ያናግሩን፥ ያሉበት መጥተን መፍትሄ እንሰጣልን።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/machine_maintenance

❤2🔥2
11 ተዘውትረው የሚከሰቱ የልብስ ስፌት ማሽን ብልሽቶችና መፍትሄዎቻቸው
በልብስ ስፌት ማሽኖች ላይ የሚከሰቱ ብልሽቶች በአብዛኛው በትክክል ካልተያዙ፣ ካልተጸዱ፣ በተሳሳተ አጠቃቀም ወይም በመለዋወጫ ክፍሎች መበስበስ/መዛግ ምክንያት ይከሰታሉ። እነዚህ ብልሽቶች የስፌት ጥራትን፣ የምርት ፍጥነትን እና የማሽኑን ዕድሜ ሊያሳጥሩ ይችላሉ።
1. የላይ ክር መበጠስ
የላይ ክር መበጠስ በብዛት የሚከሰተው የክር ቴንሽን (Tension) ከመጠን በላይ ሲጠብቅ፣ መርፌው ሲጎዳ ወይም ክሩ በትክክል ባልገባ ጊዜ ነው። መፍትሄው የክር ቴንሽንን ማስተካከል፣ መርፌውን በአዲስ መቀየር እና ክሩን በማሽኑ መመሪያ መሰረት እንደገና ማስገባት ነው።
2. ስፌት መዝለል (Skipped Stitch)
ማሽኑ አንዳንድ ስፌቶችን ሳይሰፋ ሲያልፍ የሚከሰተው በተታጠፈ ወይም በደከመ መርፌ፣ ተስማሚ ያልሆነ የመርፌ መጠን ወይም የማሽኑ ጊዜ አቀማመጥ (Timing) ሲዛባ ነው። መፍትሄው ተስማሚ እና አዲስ መርፌ መጠቀም እና አስፈላጊ ከሆነ የማሽኑን Timing ማስተካከል ነው።
3. የታችኛው ክር መጠቅለል
ይህ ችግር ቦቢን (Bobbin) በትክክል ካልተጫነ፣ የታችኛው ክር ቴንሽን ካልተስተካከለ ወይም ቦቢን ኬዝ ውስጥ ቆሻሻ ከተከማቸ ይከሰታል። ቦቢኑን በትክክል መጫን፣ ቦቢን ኬዙን ማጽዳት እና የክር ቴንሽንን ማስተካከል መፍትሄው ነው።
4. ጨርቅ አለመንቀሳቀስ
ጨርቁ በትክክል ወደፊት የማይሄድ ከሆነ፣ የFeed Dog ጥርሶች ወደ ታች ወርደው ሊሆኑ ወይም Presser Foot ግፊት በቂ ላይሆን ይችላል። Feed Dogን ማንሳት፣ Presser Foot ግፊቱን ማስተካከል እና የጥርሶቹን ቆሻሻ ማጽዳት ይመከራል።
5. መርፌ መሰበር
መርፌ የሚሰበረው የተሳሳተ የመርፌ መጠን ሲጠቀም፣ መርፌው ተታጥፎ ሲሆን ወይም ጨርቁን በኃይል ሲጎትቱት ነው። ተስማሚ መርፌ መጠቀም፣ ጨርቁን አለመጎተት እና መርፌውን በትክክል መግጠም ችግሩን ይቀንሳል።
6. ማሽኑ ድምፅ (ጩኸት) ማሰማት
ያልተለመደ ድምፅ በአብዛኛው ዘይት እጥረት፣ ቆሻሻ መከማቸት ወይም የማሽን ክፍሎች መልበስ ምክንያት ይፈጠራል። ማሽኑን በየጊዜው ማጽዳት፣ በተገቢው ዘይት መቀባት እና የተበላሹ ክፍሎችን መቀየር ያስፈልጋል።
7. ማሽኑ መንቀጥቀጥ
ማሽኑ በጣም የሚንቀጠቀጥ ከሆነ የማሽኑ ብሎኖች ሊላሉ ወይም ማሽኑ ያልተረጋጋ ጠረጴዛ ላይ ሊቀመጥ ይችላል። ብሎኖችን ማጥበቅ እና ማሽኑን በተረጋጋ መሠረት ላይ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው።
8. ያልተመጣጠነ ስፌት
ስፌቱ አንዳንዴ ጠብቆ አንዳንዴ ላልቶ ከታየ፣ የላይና የታች ክር ቴንሽን አለመመጣጠን ዋናው ምክንያት ነው። ቴንሽኑን በትክክል ማስተካከል እና ጥራት ያለው ክር መጠቀም ይመከራል።
9. ሞተሩ አለመስራት
ሞተሩ ካልሰራ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ ፔዳል፣ ፊውዝ ወይም የኤሌክትሪክ ሽቦ ችግር ሊኖር ይችላል። የኃይል ግንኙነትን መፈተሽ፣ ገመዶችን መመርመር እና አስፈላጊ ከሆነ ቴክኒሺያን ማማከር ይገባል።
10. ማሽኑ መቆለፍ (Jamming)
ክር በHook ወይም በቦቢን አካባቢ ሲጠቀለል ወይም ብዙ ቆሻሻ ሲከማች ማሽኑ ሊቆለፍ ይችላል። በዚህ ጊዜ ማሽኑን ማቆም፣ ክሩን ማስወገድ፣ ቦቢን አካባቢን በደንብ ማጽዳት እና እንደገና በትክክል ማስገባት ይገባል።
11. Hook Timing መዛባት
Hook Timing ሲዛባ መርፌው ከHook ጋር በትክክል አይገናኝም፣ ይህም ስፌት መዝለል ወይም መርፌ መሰበር ያስከትላል። ይህ የቴክኒክ ማስተካከያ ስለሆነ በባለሙያ ቴክኒሺያን እንዲስተካከል ይመከራል።
ማጠቃለያ
አብዛኞቹ የስፌት ማሽን ብልሽቶች በመደበኛ ጥገና (Preventive Maintenance)፣ በትክክለኛ የማሽን አጠቃቀም፣ ማሽኑን በየጊዜው በማጽዳትና በመቀባት፣ እንዲሁም ተገቢ መርፌና ክር በመጠቀም ሊከላከሉ ይችላሉ። መደበኛ የመከላከያ ጥገና ማድረግ የማሽኑን ዕድሜ ያራዝማል፣ የስፌት ጥራትን ያሻሽላል፣ እንዲሁም የምርት መቋረጥን እና የጥገና ወጪን ይቀንሳል።
ለበለጠ መረጃ:- +251925447525 ወይም @amanu97 ላይ ያናግሩን፥ ያሉበት መጥተን መፍትሄ እንሰጣልን። የተለያዩ አዳዲስ የስፌት ማሽኖችን የመገጣጠም እንዲሁም የተበላሹትን የመጠገን ሥራ እንሠራለን።

👍1🔥1🙏1👌1
12 የልብስ መስፊያ ማሽን ለመግዛት መመልከት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
የልብስ መስፊያ ማሽን መግዛት የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት በመሆኑ ዋጋውን ብቻ በመመልከት መወሰን አይገባም። ማሽኑ ከሚሰሩት ሥራ ጋር ተስማሚ መሆኑን፣ ጥራቱን፣ የጥገና ቀላልነቱን እና የመለዋወጫ እቃዎቹ ተደራሽነት መመርመር ያስፈልጋል። ከታች ያሉት ነጥቦች በዝርዝር ይረዱዎታል።
1. ለምን እንደሚገዙት ይወስኑ
ማሽን ከመግዛትዎ በፊት የሚሰሩትን ሥራ በግልጽ ይወስኑ። ለቤት አገልግሎት ከሆነ በዋጋ ቀላል ማሽን ወይም ረከስ የሚል ማሽን በቂ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ለልብስ ፋብሪካ፣ ለቡቲክ ወይም ለንግድ ስፌት ሥራ ኢንዱስትሪያል ማሽን ይመረጣል በሌላ አባባል የሚሰሩት ስራ ከፍ እያለ ሲሄድ የማሽኑ ጥራትና ጽናት ይበልጥ ያስፈልጋል።
2. የማሽኑ ጥራት (Build Quality)
ጠንካራ ብረት የተሠራ ማሽን ዕድሜው ረጅም ነው። ቀለሙን፣ የማሽኑን አካል፣ ብሎኖችን እና መገጣጠሚያዎቹን ይመልከቱ። የተበላ ወይም የተሰነጠቀ አካል ያለው ማሽን አይምረጡ። በተለይም የሰራ ማሽን ከሆነ ይኼ በአግባቡ መመልከት ወሳኝ ነው።
3. የሞተር አይነት
የ Servo Motor እና Clutch Motor ንጽጽር
Servo Motor (ዘመናዊ)
✔️ ኃይል ይቆጥባል
✔️ ጸጥ ያለ ድምጽ
✔️ ፍጥነት መቆጣጠር ይቻላል
✔️ ለጀማሪዎች ቀላል
Clutch Motor
✔️ በጣም ኃይለኛ
✔️ ነገር ግን ጫጫታ አለው
✔️ ኤሌክትሪክ ይበላል
በዘመናዊ ማሽኖች ውስጥ Servo Motor የተሻለ ምርጫ ነው። ከ60% በላይ ኤሌክትሪክ ኃይል ይቆጥባል ፣ ድምፁ ዝቅተኛ ነው ፣ ፍጥነቱን በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል ፣ ለጀማሪዎችም ለባለሙያዎችም ተስማሚ ነው።
4. የስፌት ጥራት
ከመግዛትዎ በፊት ማሽኑን በጨርቅ ላይ ይስፉ። ጥሩ ማሽን፦
እኩል ስፌት ይሰራል? ክር አይቆርጥም? ስፌት አይዘልም (Skipped Stitch)? የላይኛውና የታችኛው ክር በሚዛን ይገጣጠማሉ? የሚሉ ጥያቄዎች በአግባቡ ሊመለሱ ይገባል በተለይ የሰሩ(ያገለገሉ) ማሽን የመግዛት እቅድ ያለን ከሆነ ይህን ጥያቄ መመለስ ወሳኝ ነው።
5. የሚሰራበት የጨርቅ አይነት
ሁሉም ማሽኖች ሁሉንም ጨርቅ በአንድ ደረጃ አይሰፉም። ቀጭን ጨርቅ (Silk, Chiffon) ፣ መካከለኛ ጨርቅ (Cotton, Polyester) ፣ ወፍራም ጨርቅ (Denim, Canvas, Leather) ፣ የሚሰሩትን የጨርቅ አይነት በመያዝ ማሽኑን መሞከር ይመከራል።
6. የመለዋወጫ እቃዎች
ብዙ ሰዎች ይህን ይረሳሉ ወይም እንደመሰረታው ነገር አያዩትም ይሁንና ግን የማሽን መለዋወጫዎች በገበያ በቀላሉ የሚገኙ መሆን አለባቸው። እነዚህም፦ መርፌ (Needle) ፣ Bobbin ፣ Hook ፣ Feed Dog ፣ Presser Foot ፣ Belt...... ወዘተ
መለዋወጫ የማይገኝለት ማሽን ሲበላሽ ለረጅም ጊዜ ሥራ ሊያቆም ይችላል ይኼ ቀላል የማይባል ወጪ በጊዜ መባከን ፣ በሰራተኛ ስራ ማቆም እና መለዋወጫውን በፈለግ ምክንያት ይመጣል ።
7. የጥገና ቀላልነት
ማሽኑን የሚጠግን ባለሙያ በአካባቢዎ መኖሩን ማረጋገጥ በተጨማሪም የአጠቃቀም መመሪያ፣ የዘይት ስርዓት እና ዋስትና (Warranty) እንዳለው ያረጋግጡ። ይህ በብዙ ኤሌክሮኒክስ እቃዎች ላይ የሚያጋጥም ሲሆን ለጥገና ቀላል ያልሆኑ ማሽኖችን መግዛት ላልተፈለገ ኪሳራ ይዳርጋል።
8. ፍጥነት
የአንድ ልብስ መስፊያ ማሽን ፍጥነት በSPM (Stitches Per Minute) ይለካል። ይህም ማለት በአንድ ደቂቃ ምን ያህል የመስፋት ፍጥነት አለው የሚለውን የምንወስንበት ነው። በዚህ መሰረት 3500 SPM ፣ 4500 SPM ፣ 5000 SPM ፍጥነት ያላቸውን ማሽኖች እንደምርት ብዛት መጠቀም ይቻላል። ይህን ያስተውሉ ብዙ ምርት(ፕሮዳክሽን) ከሆነ የሚያመርቱት ከፍተኛ ፍጥነት ይጠቅማል።
9. የብራንድ ስም
በዓለም አቀፍ የታመኑ ብራንዶች ከፍተኛ ጥራትና የተሻለ የመለዋወጫ ድጋፍ ይኖራቸዋል። የታወቁ ብራንዶችን መጠቀም ብዙ ድካም የሚያቀልና እርግጠኝነት የሚጨምር ነው። ለምሳሌ፦ JUKI ፣ JACK ፣ BROTHER ፣ TYPICAL ፣ SIRUBA ፣ ZOJE ፣ PEGASUS በጥሩ ስም ያላቸው ማሽኖች ናቸው።
10. አውቶማቲክ ባህሪያት
ከፍተኛ ሞዴሎች በራሳቸው ተጨማሪ እቃ የሚያስፈልጋቸውን ስራዎች በአንድ ጊዜ በማከናወን የጊዜና የእቃ ብክነትን ይቀንሳሉ። ለምሳሌ፦ Auto Thread Trimmer ፣ Auto Back Tack ፣ Auto Foot Lift ፣ Needle Position ፣ Touch Panel
እነዚህ ምርታማነትን ያሳድጋሉ።
11. የዋጋ እና የጥራት ሚዛን
እጅግ ርካሽ ማሽን መግዛት በኋላ ብዙ የጥገና ወጪ ሊያስከትል ይችላል። ትንሽ ከፍ ያለ ዋጋ ከፍለው የተሻለ ጥራት ያለውን መግዛት በረጅም ጊዜ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።
12. ከመግዛት በፊት የሚደረጉ ሙከራዎች
👌በማሽኑን ከ5–10 ደቂቃ ይስሩ።
👌በተለያዩ ጨርቆች ላይ ይሞክሩ።
👌ያልተለመደ ድምጽ ወይም ከፍተኛ ንዝረት እንደሌለ ያረጋግጡ።
👌ዘይት የሚያፈስ መሆኑን ወይም ክር የሚበጥስ መሆኑን ይመልከቱ።
👌የእግር ፔዳል፣ የፍጥነት መቆጣጠሪያ፣ መብራት እና ሌሎች ተጨማሪ ባህሪያት በትክክል እየሠሩ መሆናቸውን ይፈትሹ።
ተጨባጭ ምሳሌ፦
🥇 JUKI – ከፍተኛ ጥራት፣ ረጅም ዕድሜ፣ ለሙያዊ እና ለከፍተኛ ምርት ተስማሚ።
🥈 JACK – የዋጋና የጥራት ሚዛን ጥሩ ነው፤ ለአብዛኛው አነስተኛና መካከለኛ የልብስ ስፌት ንግድ ተመራጭ ምርጫ ነው።
🥉 Sewkey – በጀት የተገደበ ከሆነ እና የስራ መጠኑ ዝቅተኛ ከሆነ ሊታሰብ ይችላል፣ ነገር ግን ከፍተኛ ምርታማነት ከፈለጉ ከላይ ያሉት ሁለት ብራንዶች የተሻሉ ምርጫዎች ናቸው።
የባለሙያ ምክር
የልብስ መስፊያ ማሽን ለመግዛት ሲያስቡ ዋጋ ብቻ አይመልከቱ ርካሽ ማሽን ፣ ብዙ ጥገና ፣ ብዙ መለዋወጫ ፣ ብዙ መቆም እና ኪሳራ ሊያስከትል ይችላል። ከፍ ያለ ጥራት ያለው ማሽን በረጅም ጊዜ ወጪን ይቀንሳል። የመለዋወጫ ተገኝነት ማሽን ሲገዙ ከውጫዊ ቅርጽ ይልቅ የውስጥ ሜካኒካል ጥራት ይመልከቱ። በተለይ የHook Assembly ጥራት፣ የFeed Mechanism እና የNeedle Bar አሰላለፍ (alignment) ትክክለኛ መሆናቸውን ያረጋግጡ። እነዚህ ክፍሎች ብልሽት ከሌለባቸው ማሽኑ ለብዙ ዓመታት ያለ ብዙ ብልሽት ሊያገለግል ይችላል።
_______
የአዳዲስ ማሽን ገጠማና የተበላሹ ማሽኖችን የመጠገን ስራ እንሰራለን +251925447525 ወይም @amanu97 ላይ ያናግሩን፥ ያሉበት መጥተን መፍትሄ እንሰጣልን።
📍አድራሻ፦ አዲስ አበባ

👍2🔥1👌1
የልብስ መስፊያ ማሽን ለመግዛት ይፈልጋሉ? ምን አይነት ሞዴል እንደሚገዙ መወሰን ከብዶታል? በዚህ ገጽ የተለጠፈውን 12 ወሳኝ ነጥቦቹን ያንብቡ! 12 የልብስ መስፊያ ማሽን ለመግዛት መመልከት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
___

❤1👍1🔥1