የ2026 የIQ ደረጃ ይፋ ሆነ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ ውስጥ ተካታለች
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገራትን የማስተዋልና የማሰብ ችሎታ በመመዘን ውጤት ይፋ የሚያደርገው “International IQ Test” የ2026 የፈተና ውጤቱን ይፋ አድርጓል።
ይህ በኦንላይን በሚቀርብ መጠይቅ አማካኝነት የሚሰላው ውጤት፣ የአገራትን የዕውቀት ደረጃና የአስተሳሰብ ምጥቀት በደረጃ ያስቀምጣል።
የዓለም ቀዳሚ አገራት
በዘንድሮው ውጤት መሠረት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የዓለምን መሪነት የጨበጠችው ደቡብ ኮሪያ ስትሆን፣ ቀሪዎቹ አምስት አገራት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦
1. ደቡብ ኮሪያ (ባለፈው ዓመት ከነበረችበት 2ኛ ደረጃ ወደ 1ኛ ከፍ ብላለች)
2. ቻይና
3. ጃፓን
4. ኢራን
5. አውስትሪያ
6. ሩሲያ
በዘንድሮው ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጥቂት ቀዳሚዎቹ ውስጥ በመመደብ ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግባለች።
• በአፍሪካ ደረጃ፦ ኢትዮጵያ 5ኛ ደረጃን ይዛለች።
• በዓለም ደረጃ፦ ኢትዮጵያ ከዓለም አገራት በ 79ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

DIRECTIVE-NO.-FXD042026-2.pdf
1.1 MB
ሰበር!
ዶላር አካውንት ኢትዮጵያ ላይ ኖርማል ሊሆን ነው
የብሔራዊ ባንክ አዲስ የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎች መገወለጫ አውጥቷል
በቅርቡ ተሻሽሎ የወጣው የባንኩ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁጥር (FXD/04/2026) ምን ይላል ?
1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡
2. ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ሕጋዊ ሰነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክ በማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋሩና ለልጆቹ የትምህርት፤ የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል...
መሉ መረጃው ከላይ ( 19 አንቀፆች) ፋይሉ ላይ ተያይዟል

ታላቁ የረመዷን ጾም ጨረቃ ነገ ማክሰኞ ከታየች ረቡዕ ጨረቃ ካልታየች ደግሞ ሐሙስ የካቲት 12 ይጀምራል።
ታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት አንዱ በመሆኑ ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም እንዲፆም በአላህ የታዘዘ ወር ነው ብለዋል።
ረመዳን የአንድነትና የመተሳሰብ ወር መሆኑን ገልጸው÷ የይቅርታ፣ የእዝነት እና የማህበራዊ ትስስር ጊዜ በመሆኑ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች ከበጎ ስራዎች ጋር እንዲገናኙ አስገንዝበዋል።
አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣ ማዕድን በማካፈል፣ በመተሳሰብና አላህን በመለመን ወሩን ማሳለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ረመዳን የሰላም ወር በመሆኑ ሁሉም ከግጭት እና ከፀብ በመራቅ እንዲያሳልፍ ገልጸው÷ መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።።
የረመዳን ጾም ጨረቃ በሒጅራ አቆጣጠር ሻዕባን 29 ማክሰኞ ቀን ከታየች ረቡዕ ካልታየች ደግሞ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡

❤1
ጎግል የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮውዘራቸውን በአፋጣኝ እንዲያዘምኑ አሳሰበ
ጎግል በክሮም ብሮውዘር ላይ የተገኘን እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት ለመጠገን አስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያ ማውጣቱን አስታወቀ።
ይህ የጥቃት ተጋላጭነት CVE-2026-2441 ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፣ በጎርጎሮሳውያኑ 2026 ዓ.ም ክፍተት መሙያ የተደረገለት የመጀመሪያው ከፍተኛ የጥቃት ተጋላጭነት ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት "Use-after-free" በሚባል የስህተት ዓይነት የተፈጠረ ነው።
የመረጃ መንታፊዎች (Hackers) ይህንን ክፍተት በመጠቀም የብሮውዘሩን ሲስተም ማሰናከል፣ መረጃዎችን መስረቅ ወይም ሌሎች ያልተፈለጉ ትዕዛዞችን በኮምፒውተራችሁ ላይ ማከናወን እንደሚችሉ ጎግል ገልጿል።
ከዚህ ባለፈም፣ ጎግል እንዳረጋገጠው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ጥቃት የሚያደርሱ አካላት በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብሏል።
በመሆኑም ተጠቃሚዎች ጥቃቱን ለመከላከል ጎግል የለቀቃቸውን የሚከተሉትን የክሮም ብሮውዘር ስሪቶች Versions እንዲጠቀሙ ይመከራል፦
👉ለዊንዶውስ Windows) እና ለማክ macOS ተጠቃሚዎች፦ 145.0.7632.75/76
👉ለሊኑክስ Linux ተጠቃሚዎች፦ 144.0.7559.75
ዝማኔውን Update እንዴት መተግበር ይቻላል?
1. በክሮም ብሮውዘርዎ ላይ በቀኝ በኩል ያሉትን ሦስት ነጥቦች ይጫኑ።
2. Help የሚለውን መርጠው About_Google_Chrome የሚለውን ይጫኑ።
3. ብሮውዘሩ አዲስ ዝማኔ ካለ በራሱ ይፈልጋል፤ ፍለጋውን እንደጨረሰም Relaunch የሚለውን በመጫን ብሮውዘሩን እንደገና ያስጀምሩት።

ረመዷን ነገ ይጀምራል።
በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ረቡዕ ይጀምራል።
#TikvahEthiopiaFamily

ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፍለጋ አገልግሎቱ ውስጥ አካተተ
ጎግል (Google) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence - AI) የተደገፈ የፍለጋ አገልግሎቱን ለማሻሻል 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን እንዲደግፍ ማስፋፋቱን አስታወቀ። ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሃውሳ፣ ኪንያርዋንዳ፣ ኪስዋሂሊ እና ሌሎች ቋንቋዎች ተካትተዋል። ይህ እርምጃ በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ብዙ ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ መረጃ ለመፈለግ እና ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በቀላሉ ለመገናኘት እድል ይፈጥራል።
የጎግል አዲሱ ባህሪ የሆነው ኤ አይ ምልከታ (AI Overviews) ተጠቃሚዎች ሲፈልጉ በአጭር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠረ ማጠቃለያ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞድ (AI Mode) ደግሞ በጽሁፍ፣ በድምፅ ወይም በምስል ተጠቅመው ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዲመርመሩ ያግዛል።
ይህ ዕድገት የአፍሪካ ቋንቋዎች በዲጂታል መድረኮች ውስጥ ያላቸውን ተወካይነት ለማሳደግ እና ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ እንደሆነ ተገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ መጀመሩ ተገለጸ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምዝገባቸውን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ያሳሰበው አገልግሎቱ፣ ለምዝገባው ሂደት አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችንም ይፋ አድርጓል።
በመመሪያው መሠረት መደበኛ ተፈታኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አማካኝነት ምዝገባቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ተፈትነው ውጤት ለማሻሻል ወይም በግላቸው ድጋሚ ለመፈተን የሚፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ በራስ-አገዝ (Self-service) የኦንላይን ዘዴ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
የግል ተፈታኞች ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን https://register.eaes.et የተሰኘ ድረ-ገጽ በመጠቀም ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም ተፈታኝ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልተመዘገበ በስተቀር ለፈተና መቀመጥ የማይችል መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጥብቅ አሳስቧል::

ኮሄር የተሰኘው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያ "ትራንስክራይብ" የተሰኘ ንግግርን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር አዲስ የድምፅ ሞዴል አስተዋወቀ።
ይህ ሞዴል ማንኛውም ሰው በነፃ ሊጠቀምበት የሚችል ሲሆን ዋና ተግባሩም የድምፅ መዝገቦችን ወደ ጽሁፍ መቀየር እና ንግግሮችን መተንተን ነው።
ሞዴሉ መጠኑ አነስተኛ በመሆኑ መደበኛ ኮምፒውተሮች ላይ ለመጠቀም አመቺ ነው። በአሁኑ ወቅት እንደ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ እና ፈረንሳይኛ ያሉ 14 ዋና ዋና ቋንቋዎችን ከንግግር ወደ ጽሁፍ መቀየር ይችላል።
ኮሄር እንደሚለው ትራንስክራይብ ሌሎች ኩባንያዎች ከሰሯቸው ተመሳሳይ መተግበሪያዎች በተሻለ ትክክለኛ መረጃ የመመዝገብ ብቃት አለው። በሙከራ ወቅትም የቃላት ስህተት የመሥራት ዕድሉ ከሌሎቹ በጣም ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ሰዎች የትርጉሙን ጥራትና አጠቃቀም በገመገሙበት ወቅት፤ ሞዴሉ ከሌሎች መሰል መተግበሪያዎች በ61 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
እንደ ቴክ ክራንች ዘገባ የዚህ ሞዴል አንዱ አስገራሚ ጎን ፍጥነቱ ሲሆን፤ የ525 ደቂቃ (ከ8 ሰዓት) የድምፅ ፋይልን በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብቻ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይችላል።

ቻይና አዳዲስ የኢንተርኔት ሳተላይቶችን ወደ ዝቅተኛዉ የምድር ምህዋር አመጠቀች
ቻይና ዛሬ ሃሙስ ማለዳ ላይ አዲስ ቡድን ነዉ የተባለ ዝቅተኛ የምድር ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶችን በተሳካ ሁኔታ አምጥቃለች ፣ይህም ማስፋፊያ የህዋ ፕሮግራሟ ላይ ሌላ እርምጃ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ሳተላይቶቹ በሰሜን ሻንዚ ግዛት ከሚገኘው ታይዩዋን የሳተላይት ማስጀመሪያ ማዕከል በጠዋት ወደ ህዋ የተላኩ መሆናቸውን ዢንዋ ዘግቧል።
ባለሥልጣናቱ እንዳረጋገጡት የሳተላይት ቡድኑ 21ኛው ባች ሲሆን ዝቅተኛ ምህዋር ሲሆን የኢንተርኔት ሳተላይቶቹ ወደተዘጋጀለት ምህዋር በተሳካ ሁኔታ መግባቱን አረጋግጠዋል።
ተልእኮው 637ኛው የሎንግ መጋቢት ሮኬት ተከታታዮች በረራ በመሆን ለቻይና የጠፈር ጥረቶች ምእራፍ አዲስ ምልክት ተደርጓል።

#Telegram_update
ቴሌግራም ሰሞኑን ባስተዋወቀው update አንዳንድ features ያካተተ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦
AI Text Editor
ይህ feature telegram ላይ ረዘም ያለ መልእክት በምንፅፍበት ጊዜ Translate ማድረግ፣ በተለያዩ Style መፃፍ እና Grammer fix ማድረግ ያስችላል የተባለም ሲሆን የፃፍነውንም text እንደ formal, Short,Tribal,Corp በመሳሰሉ ስታይሎች style ማድረግ እንደሚያስችልም ተገልጿል።
ይህንንም feature ለመጠቀም የቴሌግራም መተግበሪያን Update ካደረግን በኋላ 3 እና ከዚያ በላይ መስመር message bar ላይ ስንፅፍ የሚመጣውን የAi ምልክት መንካት።
New Features for Polls
Pools ላይ እንደ ፎቶ እና ቪድዮ ያሉ medias ወይም location Attach ማድረግ/ማያያዝ፣ Active በሆኑ polls ላይ ምርጫዎችን ሰዎች suggest እንዲያደርጉ ማስቻል፣ምርጫዎቹ ለየሰው random እደምተከተል እንዲኖራቸው ማድረግ የመሳሰሉ features ተካተዋል።
Document Scanner on iOS
የiOS ቴሌግራም ላይ document scan ማድረግ የሚያስችል feature ሲሆንይህንንም ለማድረግ attachment menu በመክፈት File የሚለውን መንካት ከዚያም Scan Document የሚለውን መንካት።

18 የሙዚቃ ክር የያዘው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አዲሱ አልበም ሐሙስ እለት ይለቀቃል ተባለ
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለዘጠኝ አመታት የለፋበት "ኢትዮሪካ" የተሰኘ አልበሙ የፊታችን ሐሙስ ስምንት ሰዓት በራሱ የዩትዮብ ገፅ ላይ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ከተለያዩ ነጠላ ዜማዎች በተጨማሪ በ1993 ዓ.ም ለህዝብ በቀረበው ‹‹አቡጊዳ›› በተሰኘ አልበሙ የሙዚቃ አድማጭን ቀልብ ለመግዛት በቅቷል፡፡
ከአቦጊዳ አልበም ቀደም ብሎ የተሰራው "ቴዲ" ወይም "ሌቦ" አልበም በመቀጠል ‹‹ያስተሰርያል›› ፣ ‹‹ጥቁር ሰው›› እና ለመጨረሻ ጊዜ ‹‹ኢትዮጵያ›› አልበም የተሰኘ ወጥ የአልበም ስራዎችን እስካሁን አበርክቷል፡፡

❤2
“በኢትዮጵያ የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ኤ.አይ ራሱ የቦርድ አባል ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ቢ.ሲ) ጋር ባደረጉት ቆይታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አንዱ የትኩረት ማዕከላቸው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ዓለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ከአሥሩ የቦርድ አባላት መካከል አንዱ "ድምፅ አልባው" ኤ.አይ ነው። ይህንኑ ተሞክሮ በማስፋት፤ በኢትዮጵያ እየተገነባ በሚገኘው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም ኤ.አይ ራሱ የቦርድ አባል እንደሆነ ጠቁመዋል።
ኤ.አይ በቦርድ ስብሰባዎች ወቅት ድምፅ ባይሰጥም፤ ክርክር በሚደረግባቸው አጀንዳዎች ላይ ግን ዝርዝር መረጃዎችንና ሐሳቦችን ያቀርባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቦርድ አባላቱም ከቴክኖሎጂው የሚያገኙትን ግብዓት መነሻ በማድረግ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኤ.አይ ስለ ማንኛውም ጉዳይ ቢጠየቅ መልሱ ከሰው በተሻለ የመረዳት ጥልቀት ያለውና ፈጣን ነው፡፡ ምላሹ ሙሉ በሙሉ የሚወሰድ ባይሆን እንኳን በሰው ልጅ አ ዕምሮ ለሚደረግ ክርክር ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብለዋል።
ኤ.አይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ምርታማነትን በመጨመር፣ ተመራጭ የኤክስፖርት ምርቶችን በመጠቆም፣ የሥራ ፍጥነትን በማሳለጥና ገበያን በማስተሳሰር ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ
ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም ያላት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ዕቃ ጫኝ መርከብ፣ የመጀመርያ የንግድ ጉዞዋን መጀመሯን ታዉቋል።
ይህን ተከትሎ ቻይና የኮንቴይነር ማጓጓዣ መርከቦቿን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል አማራጭ በመቀየር አዲስ የአረንጓዴ ምዕራፍ እንቅስቃሴ መጀመሯ ተዘግቧል።
በሻንጋይ የንግድ መርከቦች ዲዛይን እና ጥናት ተቋም ሙሉ አቅም የተሠራችው ይህች መርከብ፣ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሪክ የምትሠራና ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነች የረቀቀ የቴክኖሎጂ ሥርዓት የተገጠመላት መሆኗ ተገልጿል።
መርከቧ 127.8 ሜትር ርዝመትና 21.6 ሜትር ስፋት ያላት ሲሆን፤ በጥቅሉ 20 ሺህ ኪሎ ዋት ሃውር (kWh) አቅም ያላቸው 10 ትላልቅ ባትሪዎች ተገጥመውላታል።
ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት ምንም ዓይነት የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት የሌለው ከመሆኑም በላይ፣ መርከቧ በእንቅስቃሴ ወቅት ምንም ዓይነት ድምፅ እንደማታወጣ ተነግሯል።

Apple.Inc
ቲም ኩክን ተክቶ የአፕል ቀጣዩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ( CEO ) ተደርጎ ተሹሟል። ይህም ከሴፕቴምበር 1 ቀን 2026 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ።
በዳይሬክተሮች ቦርድ ሙሉ ድምፅ የፀደቀው ይሄ ሽግግር የረጅም ጊዜ እቅድ እንደነበር አስታውቀዋል።
ኩክ ከቴሩስ ጋር ለተቀላጠፈ ሽግግር ሂደት በቅርበት እየሰራ በቀረው የዋና ስራ አስፈፃሚነት ጊዜው የሚቆይ ይሆናል።
ቲም ኩክ የአፕል ቀጣዩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራ አስፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል ይህን ተከትሎ የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ቲም ኩክን ተክቶ የአፕል ቀጣዩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ( CEO ) ተደርጎ ተሹሟል። ይህም ከሴፕቴምበር 1 ቀን 2026 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ።