M TECH
28.5K subscribers
332 photos
15 videos
365 files
131 links
𝕄 𝕥𝕖𝕔𝕙 CHANNEL 👇

💢App preview
💢App recommendation
💢Tech News
💢Premium apps
💢Useful bot, website, telegram channel
recommendations

CREATOR @mubas20
Download Telegram
የቴሌቪዥን ስርጭት መቋረጥ…..

የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ እስራኤል አካባቢ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ተፈጥሯል፡፡

አብዛኛዎቹ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጧል፡፡

አገልግሎቱን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ተመልሷል

ተቋርጦ የነበረው የቴሌቪዥን ስርጭት አሁን ላይ ተመልሷል።

የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡

በዚሁ ምክንያት የአብዛኛዎቹ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ (ምሽት 4:30)ችግሩ ተፈቶ ወደ ስርጭት ተመልሰዋል።
የተከበራችሁ የባንካችን ደንበኞች
****
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ነገ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በኤቲኤም ማሽኖች እንዲሁም በፖስ ማሽኖች እና በኮር ባንኪንግ የሚሰጡ አገልግሎቶች (Core Banking Services) በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳወቅን፣ ለሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

Source:- combankethofficial
አዲሱ የ GOOGLE SOFTWARE በ ANDROID DEVICE እና በ IPHONE መካከል FILE SHARE መደራረግ ይቻላል ይላል የዛሬ ድንቅ ዜና!!


🔴 ይሄን አገልግሎት የሚያገኙት LATEST በሆኑ ANDROID DEVICE ነውም ይላል!!


ANDROID VERSION 15 እና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ስልኮች ነው የሚሰራው!!



ከዚ በዋላ IPHONE USER 🤝 ANDROID USER
1
6ጂ ኔትወርክን ቀድሞ ለማስተዋወቅ የሚደረገው ፉክክር
***

በዓለማችን ላይ በአሁኑ ሰዓት ከአምስተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5ጂ) ወደ ስድስተኛው ትውልድ (6ጂ) ለመሸጋገር በርካታ ምርምሮች በመደረግ ላይ ናቸው።

በፈረንጆቹ 2030 ምርምሮች ወደ መሬት ወርደው የ6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ ጊዜ ቀድሞ የፈጠራው ባለቤት ለመሆን ሀገራት ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።

ከአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ በ100 እጥፍ ፍጥነት እንደሚበልጥ የተነገረለት የ6ኛው ትውልድ ኔትወርክ አንድ ቴራ ባይት ፋይል ለማውረድ በቀደመው ጊዜ 13 ደቂቃ ይፈጅ የነበረውን ጊዜ ወደ 8 ሰከንድ የሚያሳጥር ነው፡፡

ቻይና አሁን ባለው የምርምር ሁኔታ በ6ጂ ኔትወርክ ፈጠራ ላይ የሚታይ እድገት በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡

እንደቻይና ሳይንስ ዘገባ ሀገሪቱ በሲስተም ዲዛይን እና የኔትወርክ አርክቴክቸርን ጨምሮ ከ300 በላይ ቁልፍ የ6ጂ ኔትወርክ ምርምር እንዳላት አስታውቃለች።

በዚህ ብቻ ያላቆመው የቻይና የሙከራ ሂደት የ6ጂ የሙከራ ሳታላይት ማበልጸግ መጀመሯ አንድ እርምጃ መቅደሟን አመላካች ነው ተብሏል።

አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ሀገራትም በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መድበው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ማን ቀድሞ የቴክኖሎጂው ባለቤት ይሆናል የሚለው የሚጠበቅ ነው።

በቦታዎች ተወስኖ አገልግሎት የሚሰጠውን የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ አዲሱ የስድስተኛ ትውልድ ኔትወርክ ያለገደብ እንዲሰራም የሚያደርግ ነው፡፡

በሀብተሚካኤል ክፍሉ
የቴስላ ባለአክሲዮኖች ለኤሎን ማስክ የ1 ትሪሊዮን ዶላር የክፍያ ስምምነት ፈቅደዋል!!

75%+ ባለአክሲዮኖች የእሺታ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ይህንንም ለማሳካት በ 10 ዓመት ውስጥ ኢሎን ማስክ ማሳካት ያለበት:

• $TSLA ወደ $8.5T የገበያ ዋጋ ማሳደግ መቻል (ከዛሬው $1.4T የገበያ ዋጋ የ466% ጭማሪ )
• በጥቅል 20 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች ሰርቶ ለገበያ ማቅረብ
• 1 ሚልዮን Optimus humanoid ሮቦቶች መሸጥ
• 1 ሚሊዮን ሮቦ-ታክሲ ( Robotaxis ) በስራ ላይ ማዋል
• 10 ሚሊዮን Full Self-Driving subscriptions ማሳካት

ይህን ማድረግ ከተሳካለት ኢሎን ማስክ በአለማችን የመጀመሪያው Trillionaire እና የ ቴስላ 25% አክሲዮን ባለቤት ይሆናል::
2
ChatGPT ከተለቀቀ 3 አመት ሞላው።
(November 30, 2022)

የChatGPT መለቀቅ ቴክኖሎጂን በከፍተኛ ሁኔታ የቀየረ ሲሆን AIን በዕለት ከዕለት ህይወታችን እንድንጠቀም እስችሎናል።

ከchatGPT በኋላ ትምህርታችሁ፣ ስራችሁ አጠቃላይ ህይወታችሁ ላይ ምን ለውጥ አመጣችሁ?
ምን አቀለለላችሁ?
🐐200 ፍየሎችን የቀጠረው ጎግል

በ2009 ዓ.ም የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል (Google) በካሊፎርኒያ በሚገኘው ማውንቴን ቪው ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኘውን ሣር ለመንከባከብ እጅግ በጣም ኢኮ-ተስማሚ የሆነ መንገድ አስተዋውቋል።

ኩባንያው በጋዝ የሚሠሩ የሣር መቁረጫዎችን ከመጠቀም ይልቅ 200 ፍየሎችን በመቅጠር ግቢውን እንዲያሰማሩ አድርጓል። ፍየሎቹ የቀረቡት “ካሊፎርኒያ ግሬዚንግ” (California Grazing) በተባለ ኩባንያ ሲሆን፣ ፍየሎቹ ለአንድ ሳምንት ያህል እፅዋትን እየተመገቡ፣ አካባቢውን በተፈጥሮ ማዳበሪያነትም አገልግለዋል።

ጎግል እንዳስታወቀው፣ ይህ ዕርምጃ የድርጅቱን የዘላቂነት ግቦች የሚደግፍ ሲሆን፣ የፍየሎቹ አጠቃቀም ድምፅን፣ የአየር ብክለትን እና የእሳት አደጋን ለመቀነስ ረድቷል።

ከዚህም ባሻገር፣ የጎግል ሠራተኞች ፍየሎቹ ወደ ግቢው ያመጡትን ሰላማዊ እና ለየት ያለ ሁኔታ እንደወደዱት ተገልጿል። ይህ ተሞክሮ እጅግ ስኬታማ በመሆኑ፣ ኩባንያው በቀጣዮቹ ዓመታትም የዕፅዋት አስተዳደር ሥራውን ለማከናወን ፍየሎችን መጠቀሙን እንደቀጠለበት ተረጋግጧል።
" የታሰሩት በቂ ስለሆነ ይፈቱ ! "

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።
👏1
አውስትራሊያ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ ክልከላ ልትጀምር ነው

አውስትራሊያ የህጻናትን የኦንላይን ደህንነት ለመጠበቅ በማሰብ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን እና ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀምን የሚከለክለውን ህግ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር ታወቀ።

ይህ አዲስ ህግ እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ፣ ስናፕቻት፣ ዩቲዩብ እና ኤክስ (ትዊተር) ያሉ ታላላቅ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በቀጥታ የሚመለከት ነው።

በእነዚህ መተግበሪያዎች ላይ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት አዲስ አካውንት እንዳይከፍቱ እና ነባር አካውንቶችም እንዲዘጉ የማድረግ ግዴታ በኩባንያዎቹ ላይ ተጥሏል።

የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎቹ ይህንን ህግ ተላልፈው ከተገኙ ወይም በቂ የመቆጣጠሪያ እርምጃ ካልወሰዱ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ማንኛውም ተጠቃሚ ዕድሜውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል የተባለ ሲሆን፤ ህጉ ግን እንደ ዋትስአፕ፣ ዩቲዩብ ኪድስ፣ ጉግል ክላስሩም እና ሮብሎክስ ያሉ ለትምህርት እና ለመልእክት ልውውጥ የሚያገለግሉ መተግበሪያዎችን እንደማይመለከት ተገልጿል።

ምንም እንኳን ህጉ የህግ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም፤ የአውስትራሊያ መንግስት ግን ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ከመሆን እንደማይታገድ አስታውቋል።
5
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የማስተሳሰር ስራ በይፋ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ዲጂታል ለማድረግ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣጣም ስራ በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።

ሆኖም ሁሉም የባንክ ደንበኞች ያላቸውን የባንክ ሂሳብ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያቸው ጋር ማስተሳሰር ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ደንበኞች ይህንን ሂደት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ማጠናቀቅ እንዳለባቸውም ተገልጿል።

አፈፃፀሙ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመሄድ ወይም ባንኮች በሚያዘጋጁት ዲጂታል አማራጭ (App/USSD) በመጠቀም የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን (16ቱ አሃዝ) ማቅረብ ይችላሉ ነው የተባለው።

የፋይዳ መታወቂያ ለሌላቸው ደንበኞች ቅድሚያ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ መመዝገብ ግዴታ መሆኑም ተጠቅሷል።

ይህ አሰራር የማንነት ስርቆትን ለመከላከል፣ የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና በአንድ መታወቂያ ብዙ ሂሳቦችን በቀላሉ ለማስተዳደር ይረዳል ተብሏል ።

በተያያዘም ሁሉም ባንኮች ይህንን አገልግሎት ለመስጠት "VeriFayda 2" ወደ ተሰኘው ዘመናዊ የኢ-ኬዋይሲ (eKYC) ሲስተም ሙሉ ለሙሉ እንዲሸጋገሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
2
CapCut v15.8.0 MOD.apk
284.1 MB
‼️CapCut v15.8.0 MOD‼️
💡 A cool video editor and tool for creating videos with music, universal and easy to use.
⚙️ Features:
✓Advanced video editor
✓Special features
✓Text and stickers
✓Popular effects and filters
✓Music and sound effects
1
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከተመዘገቡ 29 ሚሊየን ዜጎች ውስጥ መታወቂያውን የወሰዱት 7 ሚሊየን ብቻ ናቸው ተባለ

የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን ለማውጣት ከተመዘገቡ 29 ሚሊየን ዜጎች ውስጥ መታወቂያውን የወሰዱት ከ7 ሚሊየን እንደማይበልጡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ይሄን ያስታወቀውከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በጋራ በዲጂታል መታወቂያ ላይ አለ ያሉትን የማንነት መረጃ ስርቆት መጠበቅ የሚያስችል የዲጂታል ምስክር ወረቀት አገልግሎት የተመለከተ መግለጫ በጋራ በሰጡበት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በዲጂታል መታወቂያ ላይ ያለውን የማንነት መረጃ መጠበቅ የሚያስችል አገልግሎትን በይፋ አስጀምሯል፡፡

አገልግሎቱ በይፋ ስራ መጀመሩን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፤የፋይዳ መታወቂያ ሰርተፍኬት አገልግሎት፣ጤና፣ ትምህርት እንዲሁም ባንክን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ ሁነኛ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሪክተሯ፤ በተጨማሪም ከዚህ በኋላ ለፋይዳ መታወቂያ የሚመዘገቡ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ የምስክር ወረቀት አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ በበኩላቸው፤ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ 29 ሚሊየን ዜጎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን ለማውጣት መመዝገባቸውን የጠቀሱ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ የፋይዳ መታወቂያ የወሰዱት ግማሽ እንኳን እንደማይሞሉ አስታውቀዋል፡፡
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ አደጋ ላይ የጣለ አዲስ የክሮም Chrome ክፍተት መገኘቱ ተገለጸ

ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያዉ Browser በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው ለሶስት አደገኛ ክፍተቶች መድፈኛ አዲስ ማሻሻያ Patch መልቀቁን አስታውቋል።

ከእነዚህ ክፍተቶች መካከል አንዱ በተለይ እጅግ አደገኛ ሲሆን፣ የግል መረጃዎችን ለመጥለፍ በመረጃ ጠላፊዎች በንቃት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ Zero_day ጥቃት መሆኑ ታዉቋል።

የደህንነት ባለሙያዎች እንዳስጠነቀቁት ከሆነም ይህ አደገኛ ክፍተት የመረጃ ጠላፊዎች ኮምፒውተራችንን ወይም ስልካችንን ዘልቀው በመግባት የይለፍ-ቃሎችንና ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንዲሰርቁ የሚያስችል መሆኑ ታዉቋል።

እስካሁን መለያ ቁጥር (CVE) ያልተሰጠውና በጎግል የውስጥ መለያ 466192044 ብቻ የሚታወቀው ይኸው ክፍተት፣ በክሮም ተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተገልጿል።

ይህ ጥቃት በፈረንጆቹ 2025 ዓ.ም. የመረጃ ጠላፊዎች በስፋት ሲጠቀሙበት የተገኘ ስምንተኛው የክሮም "ዜሮ-ዴይ" ጥቃት መሆኑም ተረጋግጧል። ይህ የሚያሳየው የክሮም ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማ መሆናቸዉን ነው።

ታኅሣሥ 1, 2018 ዓ.ም. የተለቀቀው ይህ ማሻሻያ ከላይ ከተጠቀሰው ከፍተኛ አደጋ በተጨማሪ፣ ሁለት መካከለኛ ደረጃ የተሰጣቸውን የደህንነት ክፍተቶችም ይደፍናል ተብሎለታል።

ሁሉም የክሮም ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸዉ ሳይጠለፍ እና የባንክ አካውንታቸዉ አደጋ ላይ ሳይወድቅ ለመከላከል፣ እንዲችሉ ሁሉንም የክሮም የመረጃ ማፈላለጊያቸዉን በአስቸኳይ እንዲያዘምኑ Update በጥብቅ ይመከራል።(INSA)
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇧🇷🗽 በብራዚል ግዙፉ የነጻነት ሐውልት አምሳያ ዐውሎ ንፋስ ጣለው

የሐውልቱ ቁመት 35 ሜትር ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሙያዊ ክብርን የሚያዋርዱ፣ ከህብረተሰቡ ባህል፣ እምነትና ሞራል ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን የሚያስተላልፋ" የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎችን" (Social Media Influencers and Content Creators) መያዝ እንደጀመረ አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃ Tikvah_ethiopia

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ መጠቀም የሚጠቅመው ሁላችንን ነው።
BREAKING ....



🔴 አሜሪካ በየዓመቱ የምታካሂደውን የዲቪ ሎተሪ አቆመች።

የቆመበት ምክንያት በ 2017 DV ደርሶት አሜሪካ በገባ ግለሰብ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በትራምፕ ትዛዝ ነው


🗣 ለአሜሪካን ዜጎች ደህንነት ስንል የአሜሪካ ግሪን ካርድ የሚያስገኘውን ፕሮግራም አቁመናል ብለዋል
ኢትዮጵያ ውስጥ ተቋርጦ የነበረዉ የTelegram Wallet verification አሁን ተመልሷል።

በፖስፖርት ወይም በNational ID verify ማድረግ ትችላላችሁ። ሞክሩት።

©️bighabesha_softwares
አስገራሚ ልዩ መረጃ...

ቤቲንግ ቢከለከልም ብሔራዊ ሎተሪ ግን የቤቲንግ ቁማር እያጫወተ መሆኑ ተረጋገጠ

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሀገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ (Betting) ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ተከትሎ፣ ተቋሙ በራሱ ድረ-ገጽ አማካኝነት የተለያዩ የ"ቨርችዋል" (Virtual) ጨዋታዎችን ማጫወት መጀመሩ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።