@Dr.Surafel info ዶ/ር ሱራፌል
223 subscribers
7 photos
3 videos
45 links
my name is Dr surafel in this channel you will be geting information about health care!!https:subscribe ይደረግ //youtu.be/3CFMkvRSDns
Download Telegram
#የሙአመር_ጋዳፊ_ትንቢታዊ_ንግግር
"እኔ ወደየትኛውም ሃገር ተሰድጄ ወይም ጥገኝነት ጠይቄ አልሄድም። የተወለድኩት እዚሁ ነው። የምሞተውም በዚሁ በሃገሬ በሊቢያ ነው። እኔ ወደ ስልጣን ስመጣ ይህ ሃገር ሙሉ በሙሉ በረሃ ነበር። እኔ ግን ሁሉም እፅዋት እንዲበቅልበት አድርጌ ወደ ልምላሜ ቀይሬዋለሁ።

ይህችን ሃገር ከራሷ ዜጎች በላይ ማንም አይወዳትም። አሜሪካውያንና አውሮፓውያን እንወዳችኋለን ቢሏችሁ አትመኗቸው። ተጠንቀቁ! እነሱ የሚፈልጉት ሃብታችሁን ነው። እነሱ የሚወዱት የዚህችን ሃገር ነዳጅ እንጅ ህዝቦቿን አይደለም።ዛሬ እናንተ እኔን ትወጉ ዘንድ እያነሳሷችሁና እያገዟችሁ ነው። ነገር ግን እናንተ ከኔ ጎን ቆማችሁ እነሱን ብትዋጉ ብልህነት ነው። ምክንያቱም ምዕራባውያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው።

ለመላው ሊቢያውያን ማስተላለፍ የምፈልገው አንድ መልእክት አለኝ። ዛሬ ምዕራባውያን እናንተ እኔን ትወጉbዘንድ እያስታጠቋችሁና እየደገፏችሁ ነው። ነገርግን እውነት እላችኋለሁ በኋላ ለዚህ ጥፋት በምትከፍሉት መራራ ዋጋ እጅግ ትጎዳላችሁ። ለእናንተ ለአሜሪካኖችና ለአውሮፓውያንም ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር አለኝ። እናንተ ትገሉኛላችሁ። ነገር ግን እኔ ከሞትኩ በኋላ ለምትጋፈጡት ማቆሚያ የሌለው የሽብር ጦርነት ራሳችሁን አዘጋጁ። እናንተ ከድንቁርናችሁ
ሰመመን ከመንቃታችሁ በፊት አሸባሪዎች ጦርነቱን እደጃችሁ ድረስ ያመጡታል።"

ጋዳፊ በአሜሪካ ፊትአውራሪነትነና በምዕራባውያን ደጋፊነት በተከፈተባቸው ጦርነት ከመገደላቸውና ሊቢያም አሁን ባለችበት ሁኔታ ከመፈራረሷ በፊት ጋዳፊ የተገደሉት በሃገር ቤት ለዜጎቻቸው፣ በዓለም መድረክም ለተቀረውbዓለም አንባገነን ስለነበሩ ነበር ከተባለና የጋዳፊ
መንግስትም ለውድቀት ሃገሪቱም ለመበታተን የበቃችው መንግስታቸው አንባገነን ስለነበረ ብቻ ነው ወደሚለው ከእውነታው ያፈነገጠ መደምደሚያ የምንደርስ ከሆነ "አንባገነን" እና "ዴሞክራሲያዊ" የሚሉት ቃላት ፍች በአተረጓጎም ቦታ ተቀያይረዋል ማለት ነው።

እስኪ ጋዳፊ በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን ሊቢያውያን ያገኙ የነበሩትን የዜግነት ጥቅም አንድ በአንድ እንይና ኮለኔል ጋዳፊ በመጨረሻው ዘመናቸው የተናገሩትን ትንቢታዊ መልዕክት፣ የአሜሪካኖች በሰው ሃገር ጣልቃ የመግባት ውጤት ከሆነችው እና ዛሬ ብትንትኗ ወጥቶ ዜጎቿ ቁራሽ ዳቦ ብርቅ እንዲሆንባቸው ከተደረገችው፣ ለአለም ህዝቦች በተለይም ለመሃከለኛው ምስራቅ ሰላም ስጋት የሆኑ ሽብርተኞች መፈልፈያ ከሆነችው ከዛሬዋ ሊቢያ ጋር እናስተያየውና የራሳችንን ፍርድ እንስጥ…

1 #በጋዳፊ ዘመን በሊቢያ የኤሌትሪክ ሃይል ከክፍያ ነፃ ነበር። የኤሌትሪክ ፍጆታ ቢል ብሎ ነገር አልነበረም።

2 #ማንኛውም ሊቢያዊ የባንክ ብድር ከፈለገ ከወለድ ነፃ በ 0% interest የፈለገውን ገንዘብ መውሰድ ይችል ነበር።

3 #በሊቢያ የመኖርያ ቤት ማግኘት ከሰብዓዊ መብቶች እንደ አንዱ ይቆጠር ነበር።
4 #በሊቢያ ህክምናና ትምህርት በነፃ ይሰጥ ነበር። ከጋዳፊ በፊት 25% የነበረው የተማረ ሰው ሃይል መጠን በእሳቸው ግዜ 83% ደርሶ ነበር።

5 በሊቢያ በግብርና ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልግ የእርሻ መሬት፣የግብርና ግብአት ማቀነባበሪያ ቤት፣መሳርያዎችና የተለያየ ቁሳቁስ ከመንግስት በነፃ እንደ ማበረታቻ ይሰጠው ነበር።

6 በሃገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርትና ህክምና ማግኘት ላልቻሉ ዜጎች እነዚህን ወደውጭ ሃገር ሄደው ያሟሉ ዘንድ መንግስት ድጎማ ያደርግ ነበር።

7 ሊቢያውያን አዲስ መኪና ሲገዙ የወጭውን 50% በመንግስት ይደጎሙ ነበር።

8 በሊቢያ የነዳጅ ዋጋ 0.14 ዶላር በሊትር ነበር።

9 ሊቢያ ምንም አይነት የውጭ ብድር ያልነበረባት ሃገር ከመሆኗም በላይ የመንግስት የመጠባበቂያ ካፒታል መጠኗም 150 ቢሊየን ዶላር ነበር።

10 በሊቢያ አዲስ ተመራቂ የሆነ ዜጋ እንደተመረቀ ስራ ካላገኘ በሙያው ቢቀጠር ያገኝ የነበረውን ደሞዝ 50% ያህል ስራ እስኪቀጠር መንግስት ይከፍለው ነበር።

11 ሊቢያ ከነዳጅ ታገኘው ከነበረው ገቢ ግማሽ ያህሉ ወደ እያንዳንዱ ሊቢያዊ የባንክ ሂሳብ ፈሰስ ይደረግ ነበር።

12 በሊቢያ አዲስ ህፃን የምትወልድ ሴት ከመንግስት 5ሺህ ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣት ነበር።
13 በሊቢያ በቁጥር 40 የሚደርስ ሙልሙል ዳቦ ዋጋው የአንድ ዶላር 15 ሳንቲም አካባቢ ነበር።

14 ከሊቢያ ዜጎች 25% ያህሉ የዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ማግኘት ችለዋል።

15 ጋዳፊ በዘመናቸው በዓለም 1ኛ የሆነውንና ሰው ሰራሽ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ፕሮጀክት በመስራትና በእያንዳንዱ በረሃማ ከተሞች ውሃ በየቤቱ እንዲዳረስ ያስቻለ ስራ ሰርተዋል።

እንግዲህ ጋዳፊን ለሞት፣ ሃገሪቱን ደግሞ ለማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነትና መበታተን የዳረጋት የአንባገነንነት መገለጫ ከላይ የተገለፀው ትሩፋት ከነበረ፣ የሰው ሃገር ሉአላዊነት ምእራባዊያን በፈለጉ ሰዓት እየደፈሩ፣መንግስታትና ህዝቦችን እየከፋፈሉ፣ ህፃናትን ሴቶችንና አረጋውያንን ለማያባራ ሰቆቃ እየዳረጉ ያሉትና ራሳቸውን የዴሞክራሲ
መሲሆች አድርገው የሚቆጥሩት አሜሪካውያን፣አውሮፓውያንና ሌሎች የመሳሰሉት የዓረቡ ዓለም አንባገነን መንግስታት መሪዎች መገለጫቸው ምን ይሆን…⁉️⁉️

እኛስ ለሀገራችን ምን ማድረግ አለብን? እውነት የውጭ ሀገራት እጅ የለበትም ነው የምትሉኝ? ለምንስ አንረጋጋም? ሁላችንም ስለእውነት ቆም ብለን እናስብ!

🇪🇹 ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ሰላሙን ያምጣላት 🙏🙏
👍1
Dr.surafel

#ስንፈተ_ወሲብ

• ስንፈተ ወሲብ ወይም የብልት መልፈስፈስ ችግር የሚሊየኖች ወንዶች ችግር መሆኑ ይታወቃል። ይህ ቢሆንም ግን ችግሩን በተለያየ መንገድ መቅረፍ ይቻላል።

• አብዛኸኛዎቹ ወንዶች ችግሩን የሚያባብሱት ስለችግራቸው ለማንም ሳያማክሩ በውስጣቸው አምቀው በመያዛቸውና ይህም ለጭንቀትና ውጥረት እንድሁም ፍራቻ ምክናየት በመሆኑ ነው።

• ከዚህ ችግር ለመውጣት የመጀመሪያው ቁልፍ መንገድ በግልፅ ስለችግሩ ከጤና ባለሙያ ጋር መነጋገር ነው።

• ይመኑ ይህ ችግር ካለበዎት የሚፈታ ነው።

• ይህ ችግር የርስዎ ብቻ አይደለም። የሚሊየኖች እንጅ። ደግሞም አብዛኸኛዎቹ ከዚህ ችግር ወጥተዋል። ለመውጣት ያልሞከሩት ሰዎች ደግሞ እዛው ናቸው። እርስዎስ ከዚህ ችግር ለመገላገል ምን ያህል ዝግጁ ነዎት?
#እስኪ የሚከተሉትን አስር ነጥቦች በዝርዝር እንይና በሰፊው እንቀጥላለን።
1. ያጨሳሉ? ካጨሱ ያቁሙት። ማቆም ከባድ መሆኑን ብንረዳም ረጫሽ ከሆኑ ከዚህ ችግር ለመጣዉጣት አይችሉም። በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ብልት እንድወጠር የሚያደርጉትን የደም ቱቦዎች ያጨማድዳቸዋል። ይህም ብልት በደም ተሞልቱ መጠኑ እንዳይጨምርና እንዳይጠነክር ይዳርገዋል።
2. አመጋገበዎት እንደት ነው? አመጋገብ ትልቅ ተፅእኖ ያሳድራል። የኮሌስትሮል መጠንን የሚጨምር፡ ክብደትን የሚጨምሩ ምግቦች ለስንፈተወሲብ አጋላጭ ናቸው። በራሱ ውፍረት ስንፈተ ወሲብን ያመጣል። ስለዚህ ጤናማ ምግቦችን ይመገቡ። ጥራጥሬ፡ ፍራፍሬ፡ ቅጠላቅጠል፡ ማርና ሌሎች
3. አልኮል ያዘወትራሉ? አልኮል ከመጠን ሲያልፍ ድብርት ያመጣል። ፆታዊ ስሜትንም ይገላል። ስለዚህ ይቀንሱ። ይተውት።
4. በየቀኑ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋሉ? በቀን ከ20-30 ደቂቃ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ የራስመተማመንዎን ከመጨመረዎ በላይ ወደብልት የሚሄደው የደም መጠን እንድጨምር ያደርጉታል።
5. በህይዎተዎ ጭንቀት፡ ውጥረትና ፍራቻ አለበዎት? እነዚህ ችግሮች ካሉ በፆታዊ ግንኙነት ውጤታማ ስለማይሆኑ ያስወግዱ። ይቀንሱ።
6. ሌላ የጤና ችግር እንደሌለበዎት አረጋግጠዋል? የጤናዎትን አጠቃላይ ሁኔታ ይወቁ። የችግሩ ምንጭ ሌላ የጤና ችግር ሊሆን ስለሚችል አጠቃላይ የጤና ምርመራ ያድርጉ።
7. ከትዳር አጋር ወይም ጎደኛ ጋር ስለ ችግሩ ተወያይተዋል? ይህን ችግር ደብቀው ሊቀርፉት ስለማይችሉ በግልፅ ተነጋግረው በተቃራኒ ፆታ ፆታዊ አነሳሽነት ችግሩን ለመቅረፍ መሞከር ጥሩ ነው። በኩርፊያና ንትርክ ችግሩ አይቀረፍም።
8. የራስዎን የSex ህይዎት ከሌሎች ጋር ለማወዳደር ይሞክራሉ? ይህ የበታችነት ስሜትን ስለሚፈጥርበዎት አያስቡት። ውጤታማም አያደርገዎትም።
9. የጤና ባለሙያ አማክረዋል? ካላማከሩ ሳይዘገዩ ያማክሩ።
10. የወሲብ ግንኙነት አይሳካልኝም ብለው ያስባሉ? እንድህ ካሰቡ ተሳስተዋል።
#በጥሞና አናንብበው። ያልገባንን እጠይቅ። ስለርሰዎ ጤና የማንፈነቅለው ድንጋይ የማንወጣው ተራራ አይኖርም።

#እስከ አሁን ባለው መረጃ በአለም ላይ 30 ሚሊዮን ወንዶች የስንፈተ ወሲብ ችግር አለባቸው። ስንፈተወሲብ ስንል የወንድ ልጅ ብልት ለግብረስጋ ግንኙነት ብቁ ሆኖ አለመገኘት ማለት ነው። ይህ ችግር ደግሞ መፈታት አለበት። ይፈታልም። ካልተፈታ ስነ-አእምሮአዊ ጠባሳው ከባድ ስለሆነ።
#መቸ ነል የሚከሰተው?
• በቂ የሆነ የደም ፍሰት ወደ ብልት ሳይሄድ ሲቀር
• ብልትን የሚቆጣጠረው ነርቭ ላይ ችግር ካለ
• በግንኙነት ሰአት ጭንቀት፡ ፍራቻና ውጥረት ካለበዎት
• ስሜትዎ የሚዘበራረቅ ከሆነ
• የደም ቱቦ መጥበብ፡ የልብ ችግር፡ ከፍተኛ ደም ግፊት፡ ከፍተኛ ስኳር መጠንና ውፍረት ካለ
#ከላይ የዘረዘርናቸው ለክስተቱ ከሌሉበት ችግሩ ስነ-አእምሮአዊ ነው ማለት ነው። መቸና ለምን ስንፈተወሲብ እንደሚፈጠር ካወቅን በቀላሉ ማካም ይቻላል።
• ፆታዊ ግንኙነት ስሜት ሲፈጠር ነርቭ ኬሚካል ወደ ብልት ይለቃል። በዚህ ወቅት ብልት ውስጥ ያሉ የደም ቱቦዎች ይሰፋሉ። በውስጣቸውም ብዙ ደም ያከማቻሉ። ይህን ጊዜ ብልት ይወጠራል። ይጠነክራል። ችግሩ ካለ ግን ይህ አይሆንም።
• የብልት መልፈስፈስ ወይም ስንፈተወሲብ ከሚከተሉት የጤና ችግሮችም ሊሆን ስለሚችል አጠቃላይ የጤና ምርመራ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው። ከልብ ቾግር፡ ከስኳር በሽታ፡ ከውፍረት፡ ከከፍተኛ ደም ግፊት፡ ከነርቭ ችግር፡ ከደም ቱቦ መጥበብ፡ ከሆርሞንና ሌሎችም ችግሮች አኳያ ሊሆን ይችላል። እንደቀላል ይህን ችግር ዝም ካሉት ለራስዎት የሚሰጡትን ክብር ይቀንሳል፡ በራስ መተማመንን ያወርዳል፡ በትዳርና ፍቅረኛ መሀል ክፍተትን ይፈጥራል።
#ዋና ምክናየቶች
• የእድሜ መጨመር ወይም እርጅና
• የስኳር ታማሚ መሆን
• ከፍተኛ ደም ግፊት
• የልብ ችግር
• የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
• ማጤስ
• አልኮል ጠጭ መሆን
• ወፍራም መሆን
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
• የመድሀኒቶች ሱሰኛ መሆን
• አድሜ መጨመር ስንል ለሁሉም ማለት አይደለም። ብዙ ወንዶች እስከ 100 አመት አካባቢ ውጤታማ ናቸው።
#በተጨማሪ
• በቂ ደም ወደብልት አለመሄድ
• ብልት በቂ ደም መያዝ አለመቻሉ
• የነርብ ጫፍ ብልት ላይ አለመድረሱ
• የብልት ደም ቱቦዎች መጎዳት
• የተለያዩ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ተፅእኖ
#አስቡ ከላይ የዘረዘርናቸው ችግሮች ካልሆኑስ? አይጠራጠሩ የችግሩ ምክናየት ስነ-አእምሮአዊና የስሜት ችግር የፈጠረው ነው። ትክክለኛ የግብረ ስጋ ግንኙነት አእምሮ፡ ስሜትና አካላችን ተናበው በአንክሮ የሚከወን ነው። በሩጫ፡ በፍራቻና በውጥረት በውክቢያ የሚሆን አይደለም።
#ግንኙነት የሚከተሉት ካሉበት ስነአእምሮአዊ ችግሮችን ተላብሶአል ማለት ነው።
• ድብርት
• ጭንቀት
• ውጥረት
• ከትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛ ጋር ፀብ ካለ
• በህይዎት ውስጥ እረፍት ከሌለ
• በማህበራዊ ህይዎት፡ በባህልና እምነት የሚደርስ ተፅእኖ መኖር
• ለግብረ ስጋ ግንኙነት ብቁ አይደለሁም የሚል እምነት ቀድሞ መኖር
#የዚህን ችግር ምንጭ ለማወቅ ከላብራቶሪ ምርመራዎች ጀምሮ የተለያዩ በመሳሪያዎች የታገዘ ምርመራ ይሰራል። ህክምናውም ችግሩን እንዳመጣው ምክናየት ይለያያል።
#ህክምናው
• በአፍ በሚወሰዱ ክኒኖች እንደ viagra, Levitra, Cialis, Stendra, Slindafil አይነት
• በሆርሞን በመታገዝ
• በብልት ላይ በሚወጋ መርፌ
• በሽንት ትቦ በኩል በሚሰጥ መድሀኒት
• ብልትን የሚወጥር መሳሪያ በመጠቀም
• የብልት ጡንቻ ውስጥ በሚቀመጥ ተመሳሳይ ስሪት
• በቀዶ ጥገና በማስተካከልና በሌሎችም መንገድ ህክምናው ይሰጣል።
#በቀጣይ የሴቶችን ፆታዊ ግንኙነት ችግሮች እናቀርባለን። ከዛ በመቀጠል ስለ ዘርፈሳሽ ቀድሞ መልቀቅ እንቀጥላለን።
የዜግነት ክብር?

ከ"ልጅ በእድሉ ያድጋል" ወደ "ሃገር በእድሏ ትኑር" ተፈጥፍጠናል። ጠዋት ሰንድቅዓላማችንን የምንሰቅልበት ማታ የምናወርድበት ብሔራዊ መዝሙራችንን ስንጀምር "የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ" ብለን ነው።

ከዜግነቱ እንጀምር
መንግስት እንደዜጋ የሚያውቃቸው እነማንን ነው? "የኑሮ መወደድ እና የዋጋ ንረትን አብራራ" ሲባል "ስጋ ቤት ነው የምትውሉት፤ ኑሮ ባይወደድባችሁ ነው" የሚል መልስ ምንም ሳይዘገንነው ፓርላማ ላይ የሚመልስ መሪ ነው ያለን። መንግስት እንደ ዜጋ የሚያየው ጮማ ቆራጩን ክፍል ነው ለማለት እንገደዳለን። ሃገሪቱ ላይ ማንም መኖር ይችላል ዜጎች ደግሞ privilege ኖሯቸው ይኖራሉ። ዜጋ ያልሆኑት ሊያገኙ የማይችሉትን እያገኙ። ታዲያ በእውነታው ሃገሪቱ ላይ privileged ሆኖ እየኖረ ያለው ማነው? እንደዜጋ የሚቆጠረውስ? ያልን እንደሆነ ከባለስልጣናቱ በቀር "እኔ" ማለት የሚችል አይኖርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ስጋ ቤቶች መጣበብ በሚያወሩበት ሰዓት በድርቅ ከተጎዱት የቦረና እና የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች በተጨማሪ በቤት ኪራይ ዋጋ፤ በምግብ እና በሌሎችም ወሳኝ ነገሮች ከማበድ ያልተናነሰ ኑሮ እየኖረ የነበረው ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም። መንግስት ቅጥ ባጣ ሁኔታ አትሞ ባሰራጨው ገንዘብ ምክንያት የተከሰተውን የዋጋ ንረት አሁንም በስግብግብ ነጋዴዎች እያሳበበ "ተራብን" ለሚለው ህዝብ "አብሽር አሪፍ ቤተመንግስት ልሰራላችሁ ነው" የሚል የንቀት መልስ እየሰጠ ይገኛል። ሃገር በግለሰባዊ አንባገነንነት ቁምስቅሏን እያየች ነው። በዚህ መጠን "የዜግነት ውርደት" ተከናንበን ነው "የዜግነት ክብር"ን የምንዘምረው።

ኢትዮጵያችን
በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች systematicም ገገማም በሆነ መንገድ መንግስት ያልተመቹትን ከፖለቲካውም ከኢኮኖሚውም ከባሰበት ከህይወትም ያገላል። መንግስት የተጎራበጡት ከመሰለው ጋር 'መሃረቤን አይታችኋል?' መጫወት ከጀመረ ሰነባብቷል። የዴሞክራሲያዊ መብት ጠያቂዎች ከቤታቸው እየታፈኑ ነው፤ ነገ ተረኛ የሚሆነው አይታወቅም። እነዚህ መንግስታዊ ውንብድናዎች በጊዜ እንዲቆሙ ካልተደረገ መንግስት ወደማንወጣው ጭልጥ ያለ ጭቆና እና የሃገር መበተን ይዞን መግባቱ የማይቀር እየሆነ መጥቷል። በኢትዮጵያችን ላይ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የሌላ ሃገር ዜጎች የተሻለ የመኖር ነፃነት አላቸው። በጦርነቱ ምክንያት abandon የተደረገ ክልል(ትግራይ እና አፋር)፤ በኦነግ ሸኔ ስም ያለ አንዳች የሚዲያ እውቅና በሁለት ወገን እየረገፈ የሚገኝ የወለጋ ህዝብ፤ በጦርነቱ መጎዳቱ ሳያንስ ለሌላ ዙር ጦርነት የፌደራል መንግስቱ እያሟሟቀበት የሚገኘው የአማራ ክልል ዓይን ባወጣ የጦርነት እና የረሃብ አዙሪት ተዘፍቀዋል። መንግስት በበኩሉ ይሄንን ለመፍታት ወይ አቅም የለውም ወይ ፍላጎት የለውም ይልቁኑም ስለችግሩ በግልፅ የሚናገሩትን በማፈን ተጠምዷል። ኢትዮጵያችን የሚል የባለቤትነት ስሜት ከብሔራዊ መዝሙራችን በቀር ምናችንም ላይ እንዳይቀር እየተሰራ ይገኛል።
👍1
Dr.Surafel info:
የሆድ ድርቀት (constipation) ምንድነው?
የሆድ ድርቀት(constipation ) ከሶስት ጊዜ በላይ በሳምንት የሰገራ አለመውጣት ሲሆን የደረቀ ሰገራ መውጣትና ህመም መገለጫዎቹ ናቸው።
በአለም ላይ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በሆድ ድርቀት ይጠቃሉ። ነገር ግን የሰገራ ድርቀት መገለጫዎቹ እንደሰው ሊለያዪ ቢችሉም ታካሚው ድርቀት በሚሰማው መጠነና ሁኔታ የሆድ ድርቀት አለ ተብሎ ይወሰዳል።
በቀላሉ መታከምና መከላከል የሚቻል ሁኔታ ነው።
የሰገራ ድርቀት በራሱ በሽታ ሳይሆን የበሽታ አመላካች ሊሆን ይችላላል።

2. ምልክቶቹስ?
• የሆድ ህመም
• የአንጀት እንቅስቃሴ መቀነስ
• የደረቀ ሰገራ መውጣት
• ማስማጥ
• ጀርባ ህመም
• ደም የቀላቀለ ደረቅ ሰገራ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ማቅለሽለሽ
• የሆድ ህመም እና መንፋት
👇👇👇👇👇👇👇👇

3. መንስኤዎቹ?
• መንስ አልባ(idiopathic constipation)
በአብዛኛው ምንም አመክንዮ የማይገኝለት ሊሆን ይችላል።
• ቋሚ ህመሞች
ማለትም የነርቭ ችግር(hirschisprung disease)፣ የስኳር ህመም(diabetic neuropathy) ፣ የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism)፣ የትልቁ አንጀት እጢ፣ የነርቭና የህብለሰረሰር ጉዳት እንዲሁም የክሮንስ ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።
• አመጋገብ
የምንመገበው ምግብ የፋይበር ዝቅተኛ መሆንና በፋብሪካ ያለቀላቸው ምግቦ ፥ በቂ ውሃ አለመጠጣት የሆድ ድርቀት መንስኤ ይሆናል። ጣፋጭ እናፕሮቲንነታቸው ከፍተኛ የሆኑ እና የታሸጉ ምግቦች ሎላው መንስኤዎች ናቸው
• የአኗኗር ዘዬ
በስራ መወጠር እና ጭንቀት ፣ በጊዜ መፀዳጃ አለመግባት ፣ ያለመንቀሳቀስ ለሰገራ ድርቀት ያጋልጣጣል።
• መድሃኒት መውሰድ
በሃኪም ያልታዘዙ የህመም ማስታገሻዎች (codeine ) አልክሆል ፣ አና ካፌይን፣ ጫት ለሰገራ ድርቀት መንስኤዎች ናቸው።
• እርግዝና
ትልቁ አንጀት ላይ ጫና ስለሚፈጠር የአንጀት እንቅስቃሴ በመቀነስ ለድርቀት ያጋልጣል።
• የጡንቻ ላይ ችግሮች የማህፀን አቃፊ ጡንቻዎች መላላት እንዲሁም የማህፀን መውጣት ለዚህ ችግር ተጠቂ ያደርጋል።

4. ውስብስብ ችግሮቹስ?
ለረጅም ጊዜ የቆየ የሰገራ ድርቀት የራሱ የሆነ ውስብስብ ችግሮችን ያስከትላል
• ኪንታሮት(hemorrhoids )፦የፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች አለአግባብ መስፋትና መቆልመም ሲሆን መድማት እና ህመም የሚያስከትል ችግር ነው።
• መሰንጠቅ( anal fissures ) የፊንጢጣ ላይ መሰንጠቅ ከፍተኛ የሆነ ህመም እና ስቃይ የሚያመጣ ሲሆን ለሆድ ድርቀት አንደመንስኤም እንደ ውጤትም ሊሆን ይችላል።
• ደም መፍሰስ
• ካንሰር

5. መፍትሄውስ?
በመጀመሪያ የሆድ ድርቀት ሊያመጡ የሚችሉ አመክንዮዎችን ማስተካከል ሲሆን ሲቀጥል የሚከተሉት መርሆዎችን መከተል ያስፈልጋል።

1. የአኗኗር ዘዬን መቀየር ማለትም
• በቂ ውሃ መጠጣት ፦ በቀን ቢያንስ 2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት
• በቀን ቢያነስ አንዴ ለመፀዳዳት መሞከር ፦ ማስተላለፍ(postphone) የሰገራ ውሃ በትልቁ አንጀት ውስጥ ሲቆይ ውሃው ተመጦ ስለሚያልቅ ለሰገራ ድርቀት ያጋልጣል።
• ጭንቀት ማስወገድ
• በቂ እንቅልፍ መተኛት
• አመጋገብ ማስተካከል ማለትም የፋይበር መጠናቸው ከፍ ያለ ምግቦች ለምሳሌ በቆሎ ፣ በቄላ ፣ገብስ፣ ጎመን፣ ቆስጣ እና ሰላጣ መመገብ
• ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ
2. የሆድ ማለስለሻ መድሃኒቶች መውሰድ(laxatives) ፦ በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች በታዘዙበት መጠንና ወቅት መውሰድ።
3. የደረቀው ሰገራ ማውጣት (disimpaction፦ ይህም የደረቀ ሠገራ የሰገራ መውጫ ውስጥ ተወትፎ ከሆነና ህመም ከፈጠረ ሃኪሞች ጣት በማስገባት የተወተፈውን ሰገራ በማውጣት ከድንገተኛ ችግር ሊያቃልሉ ይችላሉ።
4. የሆድ እጥበት ( cleancing enema፦ የሳሙና አረፋ ወይም ግላይሴሪን በፊንጢጣ ከገባ በኋላ የደረቀውን ሰገራ አጥቦ እንዲወጣ የሚያደርግ ስርዓት ነው።
👍1