Love - ፍቅር
6.53K subscribers
41 photos
4 files
31 links
ስለተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አብረን እንድንማማር መድረኩን ከፍተናል። በሚመቸን እንሳተፍ።

@kkzinu1
@TgKassa
@Nahooom
@Yona4501
@Fkr_Orthodox

https://t.me/lovefkr
https://t.me/lovefkrlove
youtube.com/lovefkrlove
https://LoveFkrLove.com
www.facebook.com/lovefkrlove
Download Telegram
. ''እርሳስ የሆነ ነፍስ ይስጠን'

👉ይህን ታሪክ ያገኘሁት ድንቅ ከሆነው የባህርማዶው ፀሃፊ፣ ከፓውሎ ኮሄሎ አጫጭር የታሪክ ስብስቦች ላይ ነው….የጎበጠን ህይወት ለማቅናት ከስነፅሁፍ
የላቀ ሃይል ያለው ነገር ምን አለ?
ለእኔ ምንም የለም። ይህችንም አጭር ፅሁፍ ሳነብ፣ ነፍሴ ሲሞረድ ተሰማኝ። እናም ለናንተም እንዲህ ተርጉሜ ላቀርበው
ወደድኩኝ

👉ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን አያቱ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል። እናም እናቱን
እንዲህ ሲል ይጠይቃታል
“አያቴ ይህ የምትፅፊው ደብዳቤ ስለኛ ነው? እኔ እና አንቺ ስላደረግነው ነገር?”

👉አያቱም መልሰው “አዎ ልጄ የምፅፈው ስለ አንተ ነው፣ ነገር ግን ከምፅፈው ፅሁፍ
ይበልጥ የምፅፍበት እርሳስ ትልቅ ትርጉም አለው፤ አንተም ስታድግ እና ትልቅ ሰው ስትሆን እንደዚህ እርሳስ እንድትሆንልኝ እመኛለው “ አሉት የልጅ ልጃቸውን
ቁልቁል እየተመለከቱት።

👉ህፃኑም አያቱ በጨበጡት እርሳስ ላይ ምንም አዲስ ነገር ባለማየቱ ግራ ተጋብቶ
“አያቴ አሁን የያዝሽው እርሳስ ከሌላው እርሳስ በምን ይለያል” አላቸው፤ አያቱም ቀጥለው
“አየህ ልጄ፤ ሁሉም ነገር እንዳመለካከትህ ይለያል፤ ይህ እርሳስ አምስት ድንቅ ባህሪዎች አሉት

👉አንደኛው፤ ይህ እርሳስ ያለ እጅ መፃፍ አይችልም፤ አንተም ምንም ድንቅ ተዓምር መስራት እና መከወን የምትችል ሰው ብትሆንም እጅ የሚሆንህ ፈጣሪ ከሌለ ወጋ የለውም።

👉ሁለተኛው፤ እንደምታየኝ እፅፍ እፅፍና እርሳሱ ሲዶለዱም አረፍ እልና በመቅረጫ እቀርፀዋለው፤ ይበልጥም ሹል ይሆናል። ሰውም ቢሆን በህይወቱ ብዙ ውጣ
ውረዶች ያጋጥሙታል፤ ፈተናውም ሲያልፍ ግን ይበልጥ ሹል ይሆናል ማለት ነው።

👉ሶስተኛው ደግሞ ልጄ….. ይህ እርሳስ በማንኛውም ሰዓት የምሰራውን ስህተት
በላጲስ አጥፍቼ እንዳስተካክል እድል ይሰጠኛል። ይህ ማለት በህይወታችን የምንፈፅማቸውን ስህተቶች ማስተካካል ነውር አይደለም፤ ይልቁንም እራሳችንን
እያረምን እረጅም መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል:

👉አራተኛው ድንቅ ባህሪ ደግሞ፤ የዚህ እርሳስ ታላቅነት ያለው የውጪ አካሉ ላይ ማለትም አንጨቱ ላይ ሳይሆን፤ ውስጡ የተቀበረው ቀጭን ነገር ላይ ነው።
ሰውም ቢሆን እንደዛው፤ ሁሌም ቢሆን ታላቅ ነገር የሚሰራው ውስጣችን ያለው
ነገር ነው። እናም ልጄ ለውስጥህ ሰላም እና ደስታ ትኩረት ስጥ። ውስጥህ መልካም ነገር ከሌለ መልካም ነገር ማድረግ ይሳንሃል።

👉አምስተኛው እና የመጨረሻው ምን መሰለህ ልጄ….. ይህ እርሳስ በተፃፈበት ቁጥር ምልክት ይተዋል። አንተም እንደዛው…. በህይወት ጎዳና ስትጓዝ ምልክትህን መተውህ አይቀርምና በኑሮህ የምትወስናቸውን ነገሮች ሁሉ አስተውል። ምልክት ጥለው ማለፋቸው ስለማይቀር።” አሉት

🙏ድንቅ ታሪክ አይደለም?…የዚህ ገፅ አለማ ምንም ሳይሆን መልካም መልዕክትን
ማስተላለፍ ብቻ ነው። እንደ እኔ አስተሳሰብ፤ ቤተሰብን፤ ማህበረሰብን፤ አገርን
ብሎም አለምን ለመለወጥ ከማሰባችን በፊት፤ እራሳችንን መለወጥ መቻል አለብን። እስቲ አስቡት፤ ቀና አሳቢ ትውልድ ማነፅ ከቻልን፤ ምን አይነት ተዓምር
መስራት እንደምንችል? ቅድሚያ ግን እራሳችንን ለመለወጥ እንትጋ…ይህንን

----------------------------------------------


አይደለም ስተኛ፣
በአልጋዬ ስወድቅ፣ ሌሊት የሚመጣ፣
አይደለም ፍራሽ ስር፣
ጋደም ባልኩ ጊዜ፣
በሰመመን እንቅልፍ፣ ተጭኖ እሚወጣ።
የምን እንቅልፍ ነው???
ይልቅስ ነቃ በል፣
የምን በረከክ በረከክ፣
እያለ ጧት ማታ፣ የሚወዘውዘኝ፣
እሱ ነው የኔ ህልም፣
አተኛትም ዛሬ!!!!!!
በል ተነስ!!!!!! እያለ፣ የሚነዘንዘኝ።

Tnx for ማንንም አልፈልግም😏😏

@lovefkrlove

@lovefkr
/// ለአንቺ ብቻ !!!

🎋 አንቺ ልትይዥው ያልቻልሸውን ነገር ሌሎች እንዲይዙልሸ አታሰገድጃቸው፡፡ ልታደርጊ የምትፈልጊውንም ነገሮች ከመናገርሸ በፊት ደግመሸ አሰቢበት!!! ማድረግ እንደምትችይ እርግጠኛ ከሆንሸ ዝም ብለሸ የማድረግ ልምድ ይኑርሸ:: ብዙዎች ሜዳ ላይ ወድቀው የቀሩት ያደረጉት ሳይሆን የተናገሩት ናቸውና !!! አሰቢበት::


🎋 መውደድ ማፍቀር የተፈጥሮ ህግጋት ናቸው፡፡ አንቺ ግን የሚወራ ሳይሆን በልብ የሚያኖሩት "ፍቅር" ማህተም ነውና ከንግግር በላይ በልብሸ አኑሪው:: በለፈለፉ ይጠፉ ነውና ነገሩ ፍቅርሸን በጉያሸሸ ሸሸጊው እንጂ በአደባባይ አትዝሪው!!! በአደባባይ የተዘራ ፍቅር አደባባይ ላይ እንደተሰጣ ልብሰ ነውና ነጣቂውና ቀማኛው ይበዛበታልና !!! አንቺ ግን? ለታይታ ብለሸ የምታደርጊያቸው ነገሮች ዋጋ ሊያሰከፍሉሸ ይችላሉና ጥንቃቄ አይጉደልሸ !!!

🎋የሚሄደውን መሸኘት የሚመጣውን ደግሞ መቀበልና ማሰተናገድ ልምዳቸው ያደረጉ ቤተኞች አይጠፋም፡፡ የፈጠጠ እውነት ላይ ቆመው በሃኪት መንገድ ህይወታቸውን የሚኖሩትነ ማየትም አዲሰ ነገር አይደለም:: አጠገባቸው ያለውን መያዝ ያልቻሉ የሩቁን ቢመኙም የሚያሰደንቅ ላይሆን ይችላል? የሚያሳዝነው ደግሞ ትርፉ ራሰን ማድከም ብቻ መሆኑ እንጂ እናም አንቺ የበረታሸ ሁኚ!!! ሩቅ አሰቦ ቅርብ ከማደር ቅርብ አሰቦ ሩቅ ማደሩ የተሻለ ነውና !! በተሰጠሸ ማንነትሸ ተጠቀሚበት ያዋጣኛል ያዛልቀኛል ብለሸ የጀመርሸውን መንገድ (ጉዞ) ቀጥይበት !!! ብዙዎች ረጅሙን የህይወት ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምሩታል ግን አይዘልቁበትም አንቺ ግን??? ለመጀመርም አትቸኩይ ከጀመርሸው ግን ከግብ አድርሺው፡፡



/// ጥሩ ገበያ የምትሸምቱበት ጥሩ የመገበያያ ቀን ይሆንላችሁ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው ሠናይ ቀን👏👏👏



አዘጋጁና አቅራቢ እውነት ይሆናል
🌹🌹እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ክፍል 11

🌿 እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሆነው የውጭ እድሉን ከማግኝቴ በፊት የሆነ ታሪክ ነው ብዙ ውጣ ውረዶችን ፈተናዎች በትዕግሰት አልፈናቸዋል በህይወት ወሰጥ የሚከሰቱ እያንዳንዱ ነገሮች ለቀጣይ ህይወት ድልድይና ምርኩዝ ናቸው ፡፡ ከሚሚ ጋረ የነበረኘ ግንኙነት አሁን ተሰተካክሎዋል እኔም ወደ ውቢቷ ጏንደር ተመልሻለሁ በሰልክ እንገኛኛለን እንደዋወላለን ከቻልኩ በአሰራ አምሰት ቀን በአካል እንገናኛለን ካልተመቸኘ ግን የወሩ መጨረሻ ምንም ቢፈጠር አልቀርም ፡፡

🌿 በዚህ ሁኔታ ውሰጥ እያለሁ ነበር ለትምህርት ወደ ቤልጅየም ያቀናሁት ቤልጅየም እጅግ በጣም የምታምር ሃገር ናት ብዙም የዮኒቨርሰቲ ተቁዋማት ያሉባት ሃገር ናት የበርካታ ዜጎች መገኛም ነች በይበልጥ ዮኒቨርሰቲ ውሰጥ የበርካታ ዜጏች መገኛ ነች እኔም የማሰተርሰ ትምህርቴን ጀምሬያለሁኝ ከሚሚ ጋር ያለን ግንኙነት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ነው የምንገናኘው እሱዋም የዲግሪ ትምህርቱዋን እየተማረቸ ነው እኔም ባለሁበት ቦታ ሁኜ በደሰታ እየተማርኩኘ ነው ፡፡ በቀን ወሰጥ ሳንገናኘ የምንውልበት ቀን የለም ድንገት ባይመቸኘ እንኩዋን መልክት አሰቀምጥላታለሁ አብረውኘ የሚማሩ በሙሉ የሷ ነገር እንደማይሆንልኝ ያውቃሉ እኔም ሰለሚረዱኝ በጣም ደሰ ይሉኛል፡፡

🌿 እኔ ትምህርት በምጨርሰበት ሠዓት እሷም የምትመረቅበት የጊዜ ሂደት አንድ ነው እነዚህን ቀናቶች እኔም በጉጉት የምጠብቀው ቀን ነው ከሚሚ ጋር ያሳለፍኩት ጥሩ የፍቅር ጊዜ እኔን ደሰተኛ አድርጎኛል በትምህርቴም ጥሩ ውጤት እያመጣሁኝ ነው ለዚህ ደግሞ ጥሩ ቆይታ እንዲኖረኝ አድርጎኛል

🌿 የቤልጀም የትምህርት ቆይታዬ እጅግ ጥሩ ነበር በጥሩ ውጤትም ጨርሼ የሁለት አመት ቆይታዬን አጠናቅቄ በ2009 ወደ ትውልድ ሃገሬ ተመለሰኩኝ ይሄ ለቤተሰቤ ትልቅ ነገር ነበር በይበልጥ እህቴ ደሰታዋ እጥፍ ሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ቆይታን አሳለፍኩኘ ሚሚ እጅጉን ናፍቃኛለች ከሷ ጋርም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘናል መሰሪያ ቤቴ ደግሞ የተመደብኩበትን ሃገር ነግሮኘ መጥቼ ፎርም እንድሞላ ነግሮኛል ከዛ በፊት ግን የልቤን ንግሰት ማግኘት እንዳለብኝ ወሰኛለሁ ያ ውጪ ሆነን ሰናሰብ የነበረው አብሮ የመኖር ጉጉት አሁን መፍትሄ የሚያገኝበት ትክክለኛ ሠዓቱ ላይ ነን በዚ ደግሞ እኔ በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል በትንሹም ቢሆን ለእሷ የምትሆን ሰጦታ ይዥ በቀጠሮዋችን መሠረት ከቤቴ ወጣሁኝ.....................
ይቀጥላል



አዘጋጅና አቅራቢ እውነት ይሆናል
🌹
#የግሩፕ_ሜሴጅ_ድምጽ_እንዳይረብሻችሁ

1-Telegram ከሚለው በስተግራ ያሉትን ሶስት ዳሽ መንካት
2- Setting
3- Notification and Sound
4- Group Notification
5- Uncheck

🌹🌹
#የሚላከው_ድምጽና_ምስል_አውቶ_ዳውንሎድ_እንዳይሆንና_ሚሞሪ_እንዳይሞላ

1-Telegram ከሚለው በስተግራ ያሉትን ሶስት ዳሽ መንካት
2- Setting
3- Data and Storage
4- When Using Mobile Data
5- Uncheck Boxes

🌹🌹🌹
#ዳውንሎድ_ያደረግነው_ለብዙ_ግዜ_ስልካችን_ላይ_እንዳይቆይ

1-Telegram ከሚለው በስተግራ ያሉትን ሶስት ዳሽ መንካት
2- Setting
3- Data and Storage
4- Storage Usage
5- Keep Media
6- 3 Days/ Keep Forever ሳይሆን/

🌹🌹🌹🌹
#ቻት_ባክግራውንድ_ለመቀየር

1-Telegram ከሚለው በስተግራ ያሉትን ሶስት ዳሽ መንካት
2- Setting
3- Chat Background
4- Choose Picture/Background
5- Check ✔️

🌹🌹🌹🌹🌹
#ግሩፕ_ፒን_ለማድረግ

1-Open_Telegram
2- Press_and_Hold_Love-ፍቅር
3- Pin_To_Top

ይመቻችሁ! @lovefkrlove
💞⸽⸽ፍ⸽⸽ቅ⸽⸽ር⸽⸽በ⸽⸽ፍ⸽⸽ቅ⸽⸽ር⸽⸽💞
       
    

#የእውነተኛ_ፍቅር_መሰናክሎች
~~~~~~~//~~~~~~~//~~~~~~~
1. ቅናት
2. የሰው ወሬ መስማት
3. በመሃከላቸው መተማመን መጥፋት
4. ለኔ ብቻ ግዜ ስጠኝ/ስጪኝ ማለት ሲመጣ
5. እሱ ከሴቶች / እሷም ከወንዶች ጋር አትገናኝ /አትገናኝ ማለት ሲጀመር
6. መደማመጥ ሲያቅታቸው
7. በጋራ የወሰኑትን ጉዳይ በተናጥል ሲንዱት
8. ሲገናኙ የፍቅር ጨዋታ ቀርቶ ክርክር ሲመጣ
9. የሱን እንከን / የሷን እንከን መተያየት ሲጀምሩ
10. ላለመስማማት ሲስማሙ
11. እኔን ብቻ ስሚኝ/ስማኝ ማለት ሲመጣ
12. ራሳቸውን ለማሳደግ መጣር ሲያቅታቸው
13. በአስተሳሰብ እየተራራቁ ሲመጡ
.... ከላይ ያሉት ነጥቦች በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ መከሰት ሲጀምሩ ያኔ
ለፍቅራችሁ ስትሉ ንቁ ... እመኑኝ ንቁ! አለበለዚያ የት ይደርሳል ያልነውን ዛፍ
ቀበሌ ቆረጠው እንደሚባለው ...
ይህ ፍቅር ያማረ ነው ፣ ፍቅር የሆነ ቤተሰብ ይመሰርታል ፣ መጨረሻው ያምራል
እያልን የተደነቅንበት ፍቅር ታሪክ ወደመሆን ይቀየርና ጊዜው አልፎ "ወይኔ ምነው
እንዲህ ባደረኩኝ" እያልን በፀፀት አለንጋ የምንገረፍበት ጊዜ እንዳይመጣ ካሁኑ
እናስብበት ...
አዎ ፍቅር ህይወት ነው ...
* ጥንዶች ሆይ ራሳችሁን እዩበት ***
ለሌሎችም #ሼር_ያድርጉ


💞ፍቅር_ያሸንፋል💞

@a1mekdi
ከደራሲያን አለም
#ብስለት
~~~
📚ሳይመች ተለማማጭ ሲመች ተሳዳቢ አለመሆን ነው ።

📚ከሰው እጅ በሉም አልበሉ ሰውን አለመብላት ነው ።

📚ሰምቶ መቻል እና ንቆ መተው ነው ።
ድሀን ሊሠርቀኝ ሀብታምን ሊጠቅመኝ ነው ብሎ አለማሰብ ነው ።

📚በደህና ቀን ያከበሩትን ሰው ቀን የከፋ እንደሆነ አለማዋረድ ነው ።

📚አለመግባባትን በሀይልና በቁጣ ሳይሆን በውይይትና ምክክር መፍታት
ነው ።

📚ዋሽቶ ለማስታረቅ መልፋት እንጅ ዋሽቶ ከማጣላት መራቅ ነው ።

📚ሁሌም ስለራስ ትክክለኛነት ስለሌላው ስህተተኛነት አለማውራት ነው ።

📚ከበደሉም ሆነ ከተበደሉ በኋላ ለይቅርታ መሽቀዳደም ነው።

📚በሰዎች ውድቀት አለመደሰት በእድገታቸውም አለመመቅኘት ነው ።

📚ያላወቁትን አላወቅኩም ማለት ዕድሜ ቢገፋ እንኳን ከመማር አለማፈር ነው ።

📚ለመጣላት አለመቼኮል ለመታረቅ ደግሞ አለመቀደም ነው ።

📚ራስን ለመሆን መጣር በራስ መተማመን ነው።

📚በሰው ስህተት አለመሳቅ ሰውንም አለመናቅ ነው ።

📚ራስን ከልክ በላይ አለመውደድ የሰውንም ችግር እንደራስ ችግር
ማየት ነው ።

📚በሌላው አጥፊነት ያለመደሰት በራስ ንፅህና ያለመመካት ነው ።

📚አብረው ችግር ያዩትን ጓደኛ ያለፈልን እንደሆነ ያለመሸሽ ነው ።

📚ድሀም ሆነ ሀብታም ተማረም አልተማረም በአንድ ፊት ሰውን

📚በሰውነቱ ብቻ ማስተናገድ ነው ።
ውለታን ከዋሉ በኋላ መርሳት መልሱንም አለመጠበቅ ነው ።

📚በአደባባይ አለመዋሸት በራስ ላይም ቢሆን እውነትን መናገር ።

📚የሰውን ደስታ መካፈል ሀዘኑንም መጋራት ነው ።

📚ስህተትን ከተረዱ በኋላ መመለስ ተሳስቼ ነበር ለማለትም አለመግደርደር ነው ።

📚በችግር ጊዜ ተስፋ አለመቁረጥ በሀዘንም ጊዜ አለመደንገጥ ነው ።

📚የተጣሉትን ወዳጅ ሚስጥር አለማባከን መልካም ውለታውንም አለመርሳት ነው።

@yordnan @Lovefkrlove
በምንም ነገር እንዳትበሳጭ
.
.
እርግጥ ነው ከተበሳጨህ እዚህ ዓለም ላይ ምን የማያበሳጭ ነገር አለ? ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ቶሎ መንጋቱ ያበሳጭሃል።ቁርስ ልትበላ ትፈልግና ቀርቦ ስታየው👀 ለሳምንታት ለቀናት የበላው ራሱ ቁርስ ነው።እናም ቀኑ ይምታታብሃል ትላንት ላይ ያለህ ይመስልሃል።እሱም ደግሞ ያበሳጫል።ሁሉም ይሁን ብለህ ወደ ስራ ልትሄድ ስትል፣ስራህ ቤትህ ላይ እና ህይወትህ ላይ ለውጥ እዳላመጣ ጉረቤትህ ይነግርሃል።

እሱም ሰላም አይሰጥህም ያበሳጫል ።ቢሆንም አትቀርም ትሄዳለህ።ትራንስፓርት ከማቆራርጥ ብለህ በባቡር ትሄዳለህ። ባቡር ውስጥ አንድም ሁለትም ሆነው የተቦከመ ሙድህን ይቦክሙታል።ይሄም ያበሳጭሃል።ወደ ስራ ስትገባ ደንበኛው፣አለቃህ፣ሰራተኛው፣...ኡኡኡ ሁሉም አንተ ላይ የተነሱ ይመስልሃል።ከተበሳጨህ ደግሞ ወዳጄ ይሄ ሁሉ ያበሳጫል።ሰው ወዶ መሰለህ ሳትገፋው ገፋኸኝ፣ሳታወራ ዝም በል፣እያወራህ ዘጋኸኝ የሚልህ።ስለሚበሳጭ ነው።አንተ ግን ለምን ትበሳጫለህ?ከተበሳጨህ እዚህ አለም ላይ ምን የማያበሳጭ ነገር አለ?

❤️ ዉብ ቀን ❤️


@fkerte
@lovefkr
@lovefkrlove
//ማፍቀሬ ካልገባህ //

በደሜ ልፃፍልህ ካልገባህ በብዕሬ
ዉስጤ ያለውን ፍቅሬን ዘርዝሬ

ልፃፍልህ ደሜን አፍስሼ
ላንተ ከሆነ እንኳንስ ደሜ
ሰጥቼህ የለም ዉይ ልቤን ከነነብሴ

ፍቅርህን ለመግለፅ ቃላትን ገጣጥሜ
ላንተ ያለኝን ፍቅር ልግለጸው በደሜ

ደሜም ይፍሰስ ይክሳሰዉነቴ
ዉበቴ ይርገፍ ይወላልቅ አጥንቴ

በፍቅርህ ይቃጠል መላው አካላቴ
እኔነቴ ይጥፋ ከእነ አካቴ

ፍቅርህን ልንገርህ የልቤን ዘርዝሬ
ቃላትን ባጣነዉ ይህን መደርደሬ
በደሜ ልፃፍልህ አይካድም ማፍቀሬ

አመሌ ስቀያየር ሆኖባቸዉ ተራራ
አበደች ይላል ሰዉ ሁሉ ስያዉራ
አንተን ባፈቅር ስንቱ ተወራ

በደሜ ልፃፍልህ
መዉዴድን ሁሉ ልንገርህ

ያፈቀረህ ልቤ ሁሌም ንፁህ ነው
ጉራ ነው አትበለኝ ይህ ያለ እዉነት ነው
ማስመሰል አይደለም ሕይወቴም ያንተዉ

ለምን መሰለህ ፍቅሬ ?

ከሩቅ ድምፅህን ስሰማ ግራ ምጋባዉ
አይኔ ስያይህ ጥርሴ ሚስቀዉ
ከንፈሬን ሳትስመኝ ዉሀ የሚሆነው
ይህ ሁሉ ያንተዉ ሀያል ፍቅር ነው

ታዲያ ይህን ሁሉ በደሜ ብፅፈዉ
ምን ይገርማል ለሚሰማዉ ሰው

እዉነት እልሀለሁ በማሀተሜ እምላለሁ
ሕይወቴን ካንተ ዉጪ ለማን እሰጣለሁ

አንተም ስትቀርበኝ የልቤ ስገባህ
አሁንም ስምህን በደሜ ልፃፍልህ
------////----///-----///----////

@a1mekdi
ወዳጄ ሆይ እራስህን እወቅ !


ራስን ማወቅ የዕውቀቶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ነው። እራስህን እወቅ የሚለው ምርጥ አባባል በርግጥ የፈላስፍው ሶቅራጠስ ዘመን ተሽጋሪ። የጥበብ ንግግር ነው።


እራስን ከማወቅ ታላቅ ጥቅምን ታገኛለህ ። አንተ ራስህን አመድና ትቢያ እንደሆንክ ስታውቅ ትሁት ትሆናለህ። ሀጥያትህን ስታውቅ ተፀፃች ትሆናለህ። አንተ በውስጥህ ጦርነት ያለብህ ፍጡር እንደሆንክ ስታውቅ ጠላቶችህን ታሽንፍለህ።


ፀጋዎችህን በውል ካወቅህ ፈጣሪህንና በአምሳሉ የፈጠረውን ማነኛውንም ስው ለማክበር ፈጥነህ ትጠቀምበታለህ። እናም ወዳጄ ሆይ !! እራስን በማወቅ ፣ አዕምሮህ ማንነትህንና። አንተነትህን ለማጠናከር በሚርዳህ ፣ ስሜቶችህን በአውንታዊ አካሄድ በሚያሳድጉ ፣ ዓለማዊነትን በልክ በአግባብና በኃላፍነት ገንቢ እውቀቶችን የሚያጎሉ በመያዝ ክፍ በል። ከዛም ለምትኖርበት ማህበርስብ እና ለስው ወገን ሁሉ በሚጠቅም ነገር ላይ ማንነትህንና አንተ ነትህን ለማዋል የሚበጅህ ዋናው ጉዳይ ራስን ማወቅ ነውና እንደዛው ለማድርግ ሞክር ።


ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው።

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ።

ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል።


ስንፍናውን ወደጥበብ፤ አላዋቂነቱንወደእውቀት፤ መጥፎ ጠባዩን ወደ በጎነት የሚመልስ ስው ብርቱ ነው።

🙏 ብሩህ ቀን 🙏


@Lovefk

@a1mekdi
💖💖💖💖💖በቃ እወድሀለሁ

....................

ለምን አትበለኝ ምክንያት የለኝም
ፍቅር ስሜት እንጂ ስበብ አይመስለኝም
ብቻ እወድሀለሁ መውደዴ ጥልቅ ነው
ፍቅርህ ለእኔነቴ የልብ ዙፋን ነው
ህያው የምሆነው አንተን በማፍቀር ነው
*^
ጅልነት አይደለም ሁሌ አንተን ማለቴ
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርህ መክሳቴ
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ

በቃ አንተን መውደድ ነው ደስታ መደሰቴ
ውለታን ፈልጌ ውደደኝ አላልኩም
ፍቅር ስጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም
በቃ እወድሀለሁ ማለቴን አልተውኩም
*
አወ አፈቅርሀለሁ አወ እወድሀለሁ
ፍቅርቅር አድራጌህ ሁሌም እኖራለሁ
አንተን በመውደዴ እፎይታ አገኛለሁ
ውዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ
በፍቅርህ ውቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ
አንተ ካለህልኝ ሙሉ ስው እሆናለሁ።

❤️ለምወድክ 😘😘😘

@a1mekdi
ትዳር ለመመስረት ፍቅር ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ስኬታማ ትዳር ከአንድ ሰው ጋር ደግሞ ደጋግሞ በፍቅር መውደቅን ይጠይቃል:: በልጅነታችን ሁላችንም ፍቅር ካለ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ይሆናል የሚል ህልም ነበረን፤ እውነታው ግን ትዳር ቀላል የማይባል መመቻመች የሚጠይቅ ነገር መሆኑ ላይ ነው፡፡

ፍቅር እና ትዳር ልክ እንደ ፈረሱና ጋሪው ኋላና ፊት ሆነው ነው የሚጓዙት የሚለው እምነት አሁንም ድረስ ሰፊ ቢሆንም ይህንን ሃሳብ የሚሞግቱ ሃሳቦች በአንፃሩ እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡ ይህንን ጥያቄ አብራርቶ ለመመለስ ጥልቅ ፍቅር እንዴት ያለ ነው? የሚለውን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የቅርብ ጊዜ የፍቅር እና ትዳር ትስስር
ትዳር ለመመስረት የጦፈ ፍቅር አስፈላጊ ነው የሚል ድምፅ ጎልቶ መደመጥ የጀመረው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ስቴፋኒ ኮንተዝ(2005) ‹‹ይህ እሳቤ ከሁለት ክፍለ ዘመን ወዲህ የመጣ ነው፡፡ ሰዎች ሁልጊዜ በፍቅር ይወድቁ ነበር፤ እርስ በእርሳቸው ከልብ ይፋቀሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ፍቅር ለመጋባት እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጥ የነበረው ከስንት አንዴ ነው›› ይላል፡፡ ኮንትዝ ቀጠል ያደርግናም እንዲህ ይላል ‹‹ፍቅር የትዳር የጎንዮሽ ተፈላጊ ውጤት እንጂ ወደ ትዳር መግቢያ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ በብዙ ባህሎች አይታሰብም ነበር››
በተመሳሳይ ሁኔታ ፓስካል ብሩክነር(2013) የሚከተለውን ይላል፡፡ ‹‹ትዳር በብዙ ባህሎች ውስጥ የተቀደሰ ትስስር መሆኑ ይታመናል፡፡ ከዚህ ውጭ ፍቅር ኋላ ላይ የሚመጣ ከሆነ እንደ አንድ ተጨማሪ ቦነስ ብቻ ይወስዳል፡፡ አሁን አሁን ግን ትዳር ለመመስረት ፍቅር ቅድመ ሁኔታ ሆኖ በመቀመጡ ከትዳር ይልቅ ፍቅር ቅዱስ ሆኗል፡፡ በምትኩ ትዳር ሁለተኛ ደረጃን እየያዘ ነው›› በዚህ ምክንያት በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተጋቢዎች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ሲሆን የፍቺ እና ያለ አባት ወይም ያለ እናት የሚመሩ ጎጆዎች ቁጥርም በአንፃሩ እያሻቀበ ነው፡፡ ብሩክነር ከዚህ በተጨማሪ ፍቅር ከትዳር ይልቅ ቅድሚያ ቦታ እየተሰጠው ቢሆንም እውስጥ ሆኖ ግን አጥፍቶ እየጠፋ ያለ ይመስላል ይላል፡፡
ትዳር ለመመስረት የጦፈ ፈቅር ቅድመ ሁኔታ ሆኖ በመቀመጡ የትዳር ዋጋ ከፍ ብሏል፡፡ ይህም ትዳር የብዙዎች ቀዳሚ አጀንዳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ይኸው አይነት ፍቅር መልሶ ትዳር መቅኖ ቢስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የጦፈ ፍቅር የለም በሚል ምክንያት ባለትዳሮች እና ጥንዶች መለያትን እንደ ሁነኛ አማራጭ ተያይዘውታል፡፡

ትስስሩን መቃወም
ፍቅርን እንደ ትዳር መሰረት ስናስብ ሁለት አይነት ተቃዋሚ ሃሳቦች ነፍስ ዘርተው ይነሳሉ፡፡

1. ትዳር ከፍቅር በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ነገሮችን ግምት ውስጥ እያስገባን የምንኖርበት ማዕቀፍ ነው፡፡

2. የጦፈ ፍቅር አጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በረጅም የጊዜ ሂደት የሚመጡ የፍቅር ሌሎች ገፅታዎች ይበልጥ ግንዛቤ ውስጥ ሊገቡ ይገባል፡፡
የመጀመሪያው ሙግት ትዳር በአንድ አይነት ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ስርዓት ውስጥ የሚኖር ቁርኝት እንደመሆኑ መጠን የጥንዶቹ አጠቃላይ የደህንነት ይህንን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ማዕቀፍ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን መቻል አለበት የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የመከራከሪያ ሀሳብ በሌላ በኩል የጦፈ የሚባለው ፍቅር አይነት ያልተረጋጋ፣ እና ለውስን ጊዜ ብቻ ደስታ የሚሰጥ መሆኑ ላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የተረጋጋ ህይወት ምንጭ ሊሆን ከሚችለው ትዳር ጋር ይጋጫል፡፡ እነዚህ ሁለት መከራከሪያ ሃሳቦች ሲጨመቁ ትዳር በሚመሰረትበት ወቅት ለፍቅር ብቻ ቅድሚያ የሚሰጥ ከሆነ መጨረሻው ሲያልቅ አያምር ይሆናል የሚል ነው፡፡
ትዳር ከፍቅር ውጪ የሚያስገኛቸው ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ትዳር ሲመሰረትም ሆኖ የመፍረስ አደጋ ሲያንዣብብበት እነዚህን ከጦፈ ፍቅር ውጪ የሚገኙ ተጨማሪ ሁኔታዎችንም ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ፣ ትዳር ሲመሰረት ጥንዶቹ በጋራም ሆነ በተናጠል ቤት ውስጥ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት እና ጥሩ ወላጅ መሆን መቻላቸው በቀዳሚነት ሊነሳ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ እውነትም በታሪክም ቢሆን ትዳር የጥንዶችን ጤናና ሀብት የሚያሻሽል ቢያንስ ቢያንስ እንኳን የማይጎዳ አብሮነት እንደሆነ ነው የሚታመነው፡፡ ለፍቅር ብቻ ሲሉ ትዳር መመስረት ግን ጥንዶቹ እነዚህን ተጨማሪ ገፅታዎች እንዳይመለከቱ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ እንደውም እንዲህ የሚነበብ አባባል አለ፡፡ ,,ለጦፈ ፍቅር ብቻ ሲሉ የሚጋቡ ጥሩ ምሽቶችን እና መጥፎ ቀኖችን ያሳልፋሉ**

ትስስር መፍጠር
በፍቅር እና ትዳር መካከል ትስስር ለመፍጠር በጊዜያዊ የጦፈ ፍቅር ስሜት እና ዘለቄታ ባለው ጥልቅ ፍቅር መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ ያሻል፡፡

ጥልቅ ፍቅር እንደ ጊዜያዊ የጦፈ የፍቅር ስሜት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ብቻ የሚጎበኘንን ጠንካራ የመፈለግ ስሜት ብቻ ሳይሆን አመለካከታችንን እና ጠባያችንን ዘለቄታ ባለው መንገድ ይቃኛል፡፡ ጠንካራ የሆነ ስሜታዊ ወሲባዊ ፍላጎት ብልጭታ ለተወሰነ ጊዜ ውስጣችን ይቆይ ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ጥልቅ ፍቅር ግን ያለማቋረጥ እያበራ ስሜታችንን ያሞቃል፣ ጠባያችንን ያንጻል እንዲሁም ከጊዜ እና ቦታ ጋር የሚኖረንን ቁርኝት መልክ መልክ ያስይዛል፡፡ የጦፈ የፍቅር ስሜት የሚያሳየው አጭር ጊጊ የሚቆይ የስሜት ኃያልነትን ብቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጥልቅ ፍቅር ግን በረጅም የጊዜ ሂደት ውስጥ የሚፈጠርን፣ በሁሉም መልኩ የሚያበራን፣ የሁለቱንም ጥንዶች ህይወት እንዲያብብ እና እንዲያፈራ የሚያደርግ ፍቅር ነው፡፡ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ህይወት ጥብቅ ከሆነ ጊዜያዊ ስሜት የተለየ ነው፡፡ የአፍታ ወሲባዊ ፍላጎት ከዘመናት የፍቅር ህይወት በላይ ጥብቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ጥልቀቱ እዘህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

ለጦፈ ፍቅር ብቻ ሲባል ትዳር መመስረት በ3 ምክንያት ብልህ ውሳኔ አይደለም፡፡

1. ፍቅር የሚለዋወጥ ስሜት ነው፡፡
2. ፍቅር ብቻውን ጠንካራ መሰረት ሊሆን አይችልም፡፡
3. ከፍቅር በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ነገሮች ያስፈልጉናል፡፡
የአንድን ሰው እንበልና አዕምሮአዊ ብቃቱን ወይም ደግነቱን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ትዳር መመስረት ለጊዜው አፍቃሪ ውሳኔ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በረጅም ጊዜ አብሮነት ውስጥ ዋጋ ባላቸው ማገናዘቢያዎች ሲፈተሽ ግን አስፈሪ ውሳኔ መሆኑ ግልፅ ይሆናል፡፡
ትዳር ለመመስረት በምንነሳበት ወቅት ፍቅር ቦታ ሊኖው ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ የዛሬም ሆነ የወደፊት ህይወት ደስታ እና ትርጉም ጊዜዊ የጦፈ የፍቅር ስሜት ላይ ብቻ ሊመሰረት አይገባም፡፡ ይልቁንም መተሳሰብን፣ መመሳሰልን፣ መጋራትን፣ እና በመጠኑም ቢሆን ስሜታዊ መፈላለግን መሰረት ያደረገ ጥልቀት ያለው ፈቅር ላይ ሊደገፍ ይገባል፡፡ ስኬታማ ትዳር ከአንድ ሰው ጋር ደግሞ ደጋግሞ በፍቅር መውደቅን ይጠይቃል፡፡

ቸር እንሰንብት፡፡

@lovefkr
@lovefkrlove
ቅናት. . . . መቅናትን ማስቀረት እንችላለን!!! – ???


ቅናት መጠኑ ይለያይ እንጅ በአብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ ባህርይ ነው፡፡ እኛ ሰዎች በሁለቱም ማለትም ባለንም በሌለንም ቁሳዊም ሆነ ስነ-ልቡናዊ ጥቅሞች ባላቸው ነገሮች ላይ እንቀናለ።

በሌለን ነገር ላይ የምንቀናው ቅናት (Envy) ሰዎች የሚፈልግቱንና እኛ የሌለንን ሲያገኙ ፣ ሲያሳኩ ወይም የሚያሳኩበትን የተስተካከለ መስመር ሲይዙ የሚሰማን ምቾት የማጣት ስሜት ሲሆን፤ ባለን ነገር ላይ ቅናት (Jealousy) ማለት ደግሞ ሌሎች እኛ ያለንን ቁሳዊ አካል ወይም የስሜት ግኙነት የመሰረትንበትን ሰው ሊያሳጧችሁ የሚመስል መጥፎ ስሜት በውስጣችን ሲፈጠር ነው።


በምሳሌ ለማስቀመጥም የፍቅር አጋርህን ሌላ ወንድ ሲያናግራት ብታይ እና ሰላም የማጣት ስሜት ሲሰማህ ቅናት (Jealousy) ሸነቆጠህ ማለት ነው፡፡ አልያም ህፃናት አዲስ በተወለደው ወንድም ወይም እህት ምክንያት የሚሰማቸው እናቴን ወይም አባቴን ተነጠኩኝ ዓይነት ስሜት እና ባህርይ እንደ አብነት ማየት ይቻላል፡፡ ቅናት ገደቡን ካለፈ በእኛም ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ስነ ልቡናዊ እና አካዊ ጉዳቶችን ይፈጥራሉ።


ሆኖም ግን ቅናትን በበጎ መልኩ የምንጠቀምበት ከሆነ መልካም የሆነ ግንኙነትና እኛ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ወደተሸለ ደረጃ ወይም የምንቀናባቸው ሰዎች ወዳሉበት የስኬት ማማ ላይ ለመድረስ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡


ከላይ እንደተገለጸው ቅናት የተለያዩ ስነ-ልቡናዊ እና አካላዊ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ ቅናት ቤተሰብን ይበትናል፣ ፍቅረኞችን ያለያያል፣ የስራ ባልደረቦችን ያጋጫል፣ ሰላማዊውን የሰው ልጆች መስተጋብር ያፋልሳል …ባስም ሲል ቅናት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን ያስጠፋል (የዴዝዴሞና ታሪክ ትዝ አላችሁ?) ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ?? መቅናትን እንዴት ማቆም እንችላለን??? እስኪ እነዚህን የመፍትሔ አቅጣጫዎች አብረን እንመልከተው...!



በጾታዊ ፍቅር ምክንያት ከሆነ ቅናት የሚይዘን በግልጽ መነጋገር፡፡ ይሄ ደርጊትሽ(ህ) ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየፈጠረብኝ ስለሆነ መስተካከል ይኖርበታል ማለት አለብን።



ማስተዋል ያለብን ቀንቻለው ማለት የተሸናፊነት ምልክት ሳይሆን ግንኙነቱን ዘላቂና ሰላማዊ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እደሆነ ነው፡፡( መተማመን) በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ዋናው የግንኙነት
መሰረቱ መተማመን ነው፡፡


የማይተማመን ባልንጀራ ካብ ለካብ ይማማላል እንዲሉ አበው፤ መተማመን የሌለው  ጾታዊ ፍቅርም ለቅናት የተጋለጠ ነው፡፡ ሌላው መቼም የምንቀናበት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ እሱ የሌለው እኛ ግን ያለን
ሌሎች ነገሮችም እንዳሉ መገንዘብ።


ሁልጊዜ ራስህን በጥረት ውስጥ ማሳለፍ ይኖርብሃል፡፡ ምክንያቱም የቻልከውን ያህል ስለታተርክ በቅናት ፋንታ እርካታን ታገኝበታለህ።


ከምንቀናባቸው ሰዎች ልምድ መቅሰም አለብን፡፡  ይህም ማለት የቀናህበትን ነጥብ ነቅሰህ አውጣ በዚህም አንተ ማግኘት ያቃተህ ሌሎች ግን ያሳኩት ከሆነ እንዴት እንዳሳኩት በማወቅ ራስህን እንድታሻሽል ይርዳናል።


በመጨረሻም ሌሎች ሰዎች ላይ እና ያላቸው ነገሮች ላይ ያለህን ፅንፍ የያዘ ትኩረትህን ቀንስ፡፡ ምክንያቱም የአዕምሮህን የትኩረት አቅጣጫ በማስቀየር አቅምህን ያሟጥብሀል፡፡

ስለሌለህ ሳይሆን ስላለህ ነገር በማሰብ ለእራስህ እውቅና ስጥ በዚህም በጊዜ ሂደት በራስ መተማመንን አዳብረህ ቅናትን ታስወግዳለህ፡፡

🤓🤓ውብ ምሽት ይሁንላችሁ

@Lovefkr

@a1mekdi
*ልብ በል አንተ ሰው *


ይቺ ዓለም የአንተ ናት አንተም የዚች ዓለም ፣
አንተ ክፉ ሆነህ ለአንተ መልካም የለም ።
ብትችል በማካፈል
ካልሆነ ሳትቀንስ ፣
ሲሆን በማስደሰት ሳይሆን ሳቴስለቅስ ።
ራስህን አዉቀህ ሌሎችን ተረድተህ ፣
ወዶ ለሚጠጋህ ንፁህ ፍቅር ሰጥተህ ።
አሻራ ጣል ለዓለም መንገድህን አጥራ ፣
ከመቃብር በላይ ስምህ እንዲጠራ ፣
ያፈራሀዉ ትዉልድ በአንተ እንዲኮራ ።
ህያው ሆኖ ስምህ ትዉልድ ያወድስህ ፣
መልካም ህይወት ኖረህ ፣
መልካም ሞትን ሞተህ ፣
ሰላም ታግኝ ነብስህ ።
ዓለም በአንተ ምክንያት ይዘቷ እንዳይጠፋ ፣
አንተም በዓለም ምክንያት እንዳትቆርጥ ተስፋ ።
በህይወት ጎዳና በህሊና መስመር ፣
የቃል ኪዳን ግዛት ዘብ ቆሞ ከድንበር ።
የሰላሟ ርግብ የፍቅር
አበባ ፣
የነፃነት አክሊል ሰብዓዊነት ካባ ።
በታሪክ መዝገብ ላይ በክብር የሚያስጠራ ፣
የቅን ሰው ቀሪ ሀብት ስም ነዉና ስራ ።
አንተ በህይወትህ ህይወትህ በዓለም ላይ ፣
በፍቅር ዳኝነት ሰዎችን ሳትለያይ ፣
እስካልሆንክ ድረስ ለእዉነት የቆምክ ታጋይ ።
ልብ በል አንተ ሰው ፣
አትርሳም አስታዉሰዉ ።
ይቺ ዓለም የአንተ ናት አንተም የዚች ዓለም ፣
አንተ ክፉ ሆነህ ለአንተ መልካም የለም ።

Tnx to ማንንም አልፈልግም😏😏😏

@lovefkrlove

@lovefkr
ሠዉ አይናቅም!!!

አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደመኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል።

ይህኔ ይበሳጭ እና አካባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል:: ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ እብድ ነገሩን ተከታትሎ ኖሯል ምን ሆነህ ነው ይለዋል ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገ
የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ
አካባቢው ለይ የለም
ይለዋል በብስጭት ስሜት
ይሄኔ " እብዱ ነው እንዴ ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም " አለው::ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተው አንዳለውም አደረገ

እብዱ ዘዴውን ነገሮት ሊሄድ ሲል ሰውየው
" ቆይ አንተ "እብድ "አይደለህ እንዴ አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቻለ ይለዋል እብዱም ቀበል አድርጎ "ታዲያ እኔ " እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል ፡፡

ብዙዎቻችን ከኛ ዝቅ ያሉ ሰዎች ሲያጋጥሙን ንቀታችን ገደብ የለውም፣ በሁሉ ነገር የምንበልጣቸው ያህል ይሰማናል።

ሰናይ ቀን


@lovefkr
@lovefkrlove
🙏🌹🙏ሰላም የፍቅር ቤተሰቦች 🙏🌹🙏

#ሰው_ሆይ_ይቅር_ባይ_ሁን

አለም በአውንታዊ ና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ነች። ካንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ። በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል። ከዚህም የተነሳ በሌሎች ስዎች መገፋታችን ወይንም እኛም ስዎችን መግፋታችን አይቀርም። ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቅው ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከስቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ህይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው። እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል። ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው። ለሌሎች ሰጭም ነው።

መሳሳት የስው ልጅ ባህሪው ነው ።ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጅ የድክመት ምልክት አይደለም።ስህተት የንቅስቃሴ ና የህይወት ምልክት ነው ። ስለዚህም መሳሳት በየትኛውም የህይወት ገፅ ላይ ሊከስት የሚችለው።በአንድ አይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳት ወይንም ማጥፍት አስቀያሚ ድክመት ነው ። ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ። ይህ የአዕምሮ ብስለትን ና የመንፈስ ጥንካሬን ማሳያ ነው።

🙏 ይቅር ማለት ጥሩ ነው፤ ጨርሶ መርሳት ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ነው።

🙏 ይቅርታ ማድርግ ለተሳሳተ ስው እንጅ ሆነ ብሎ ላጠፋ ብዙም ትርጉም ላይሰጠው ይችላል።

አንዳንድ ስዎች በቀልን ትተው ይቅርታ ማድርግን የማይመርጡበት ምክንያት ዋጋው ስለሚወደድባቸውና የነርሱ ትንሽነትም ስለማይመጥነው ነው።

የበደሉንን ይቅር ማለት መሽነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው።

👌መልካም እለተ ስንበት
👌የምህረት ቀን ይሁንልን
👌አስተዋይና ይቅር ባይ ልቦና ይኑረን!!

💞💞💞በፍቅር እንዋል💞💞💞

@Lovefkrlove

@a1mekdi
ከሰኬታማ ሠዎች በሰተጀርባ

መንፈሰ ጠንካራ ሠዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራትና ሰሜታቸውን በመቶጣጠር ይታወቃሉ፡፡ በአዕምሮዎቸው ብሰለትና በአሰተሳሰብና ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሠዎች እነዚህን ነገሮች አያደርጉም፡፡

1ኛ የመጀመሪያው ጥፋተኛ አያደርጉም መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ለራሳቸው የጥፋተኘነት ሰሜትን ለማሰተናገድ አሉታዊ ነገሮች ላይ ረጅም ጊዜ አያባክኑም ከዚያ ይልቅ በአወንታዊ አሰተሳሰብና ተግባራት ላይ ያተኩራሉ መለጭው ጊዜ መልካምነትንም አበክረው ያቅዳሉ ፡፡


2ኛ ራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም አይሸነፋም ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካሮች አካላቸው ቢደክምም በአሰተሳሰባቸውና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይይዛሉ ለሰኬትም ይበቃሉ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡

3ኛ ከአቅማቸው በላይ በሆነ ነገር ጊዜያቸውን አያባክኑም በአዕምሮዋቸው ብሰለታቸው ከፍ ያሉ ሠዎች ሁሉም ነገር እነርሱ ባቀዱት ልክ እንደማይሆኑና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ሰለሚያሰቡ አይጨነቁም ከአቅማቸው በላይ ሆኖ ለጭንቀት የሚዳርጉ ነገሮች በአግባቡ በማሰተናገድም ካልተገባ ውጥረት ራሳቸውን ያድናሉ በዚህም ሰኬታማነታቸውን ያሳኩታል፡፡

እውነት -ይሆናል

@Lovefkrlove
@Lovefkr
🌹 እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ክፍል ---12

🌿 ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን ከልቤ ሰለምወዳት የጏደኞቿን ጥያቄ ለጊዜው ከውሰጤ አውጥቼ ደሰታዬን እያጣጣምኩት ነው፡፡ ከሚሚ ጋር ሰለወደፊት የአብሮነት ህይወትና ምናልባትም ከተሳካልን ለቤተሰብ አሳውቀን ቃል ኪዳን ለማድረግና እኔም የውጪ ጉዞዬን ጨርሼ ሰመጣ ደግሞ ለመጋባት እያሰብን ነበር፡፡

🌿 ይህንንም የሆነ ቦታ ተገናኘተን መነጋገር እንዳለብን ወሰንና በቀጠሮው ተለያየን በወቅቱ በቀጠሮዬ መሠረት ቀድሜ ነበር የደረሰኩት የቀጠሮዬ ሰዓት ሳየው አልፎዋል ፡፡ምናልባት ምን ሆና ይሆናል ሰልም አሰብኩኝ በተደጋጋሚ ሰልክ ብደውልላትም የሰልኳ ጥሪ አይመልሰም፡፡ ምናልባት ተሰርቆባት አልያም ጥላው ይሆናል ብዬ አሰብኩኘ ብቻ ምን አለፋችሁ የባጥ የቆጡን ሳወጣና ሳወርድ ሠዓቱ እየነጎደ ሄዷል እርሷን በመጠበቁ ሳይሆን ምን ሆና ነው ምን በፈጥሮ ነው በሚል መልሰ በሌለው ጥያቄ ወንበሬን እያሞኩት ነው፡፡

🌿በሰተመጨረሻም የሰልክ መልክት አሰቀመጥቁላት አሁንም መልሰ የለም፡፡ ዝም ጭጭ ሆነብኝ ቢያንሰ አሰራ አምሰት የሰልክ ጥሪና አሰር የሚያህሉ መልክት አድርሻለሁ ፡፡ ሠዓቱን ሳየው መሸቶዋል ቀደም ብዬ አክሰቴ ጋር እንደምመጣ ነገርኩዋት እሷን በማሰቡ ቢያንሰ አንድ አራት የሚሆኑ ካፊዎቹን በሻይ ቡናው ጏብኝቼቸዋለሁ አሰተናገጁ ብዙ ቆየህ በሠላም ነው አለኝ?

🌿በእርግጥ ባይጠይቀኝ ነበር የሚገርመኘ ሰምንት ሠዓት የቀጠርኩዋት ሚሚ እሰከ አሰራ ሁለት ድረሰ አልመጣችም ምነው በሠላም ትሉኝ ይሆናል፡፡ እኔም ለራሴ እንዲህ ብያለሁ ሰምንት ሠዓት ነበር የቀጠርኩዋት እሰከ ዘጠኘ እጠብቃትና አሰር ሰዓት ላይ የማትመጣ ከሆነ አሰራ አንድ ሠዓት አይቼያት አሰራ ሁለት ሠዓት ላይ እሄዳለሁ የሚለውን ህግ ተጠቀምክ ፍቅር አይደል ማን ይከለክለኛል፡፡


🌿ከዚህ በላይ መጠበቁ ድካም መሰሎ ሰለተሰማኝ ምንም አማራጭም ሰለሌለኘ ጉዞዬን ወደ አክሰቴ ቤት አደረኩኝ አክሰቴ ቤት ለመድረሰ ቢያንሰ አንድ ሰዓት ፈጅቶብኛል በአጭሩ ቤት ሰደርሰከምሸቱ አንድ ሰዓት ሆኖል ፡፡ ሠውነቴ በጣም ዝሏል ልብሴን ቀያየርኩና ሻወር ገባሁኝ ታጥቤ እንደጨረሰኩ ሰልኬን ቻርጅ ላደርገው ሰል መልክት ደረሰኘ ሰከፍተው እንዲህ ይላል" ሰልኩን አላየሁትም ነበር ጏደኛዬ ታማ እርሷን ሃኪም ቤት ይዘን ሄደን ነው " መልዕክቱ ይህ ነው ታድያ ምን ችግር አለው አንድ የሰልክ ጥሪ አድርጎ መናገረ ማንን ገደለ? አልያም ደግሞ መልክት ብትሠድልኘ ጥሩም ነበር ብቻ ምን አለፋችሁ እኔ ያሰብኩትና የሆነው ነገር ለየቅል ሆነብኝ? መልሰም አልሰጠኃትም እኔም በተራዬ ዝም አልኩኝ በተደጋጋሚ ደወለችልኝ መልሰ አልሰጠኃትም ይህንን የተረዳችው ሚሚ በሰተመጨረሻም መልክት ላከችልኘ እንዲህ የሚል............


🌿 የተቀጣጠርንበተ ቦታ ብርድ ላይ ቆሜያለሁ የሚል ይህንን ሰትለኘ ሠዓቱ ሁለት ሠዓት ላይ ነው መልሴ ግን ዝምታ ሆነ አሁን መሸቶዋል ምን ልላት እንደምችል አላውቅም አክሰቴ እራት በማዘጋጀት ላይ ነች እኔ ግን እንዲህ አደረኩኝ ሰልኬን ዘጋሁትና አክሰቴ ወዳዘጋጀችው ማዕድ ሄድኩኝ አክሰቴ ቀለል አለልህ ልጄ አለችኝ? በሆዴ የተሸከምኩትን ጉድ ባየሸልኝ አልኩዋት መለሰ ብዬ አዋን አክሰቴ አልኳት ብዙም ሳልበላ ትንሸ ቀማመሰኩን በቃኝ አክሰቴ ልተኛ ሰላት ልጄ ውጪ በልተህ ነው እንዴ የመጣህው ሰትለኝ ሆዴን በትኩሰ ነገሮች ሞልቼው እንደሆነ ነገርኩዋት እሷ በልታ እሰክትነሳ ድረሰ ትንሸ ተጨዋወትን በል ልጄ ሂድ ረፍት አድርግ አለችኝ እኔም ለእራቱ አመሰግኛት ወደ መኝታ ክፍሌ አመራሁ ወደ መኝታዬ ከሄድኩ በኃላ ግን ፍራሸ ማሞቅ እንጂ አቶ እንቅልፍ ሊወሰደኝ አልቻለም? ከመኘታዬ ተነሰቼ ቀን የተፈጠረውን ትእይንት በቅጽበት ወደ ኃላ መለሰ ብዬ ማሰብ ማሰታወሰ ጀመርኩኝ ምንም ሰሜት ሊሰጠኝ አልቻለም ጏደኛዬ ታማ ነበር ? በጆሮዬ ላይ ያቃጭልብኛል ለምን እንዳግዛት አልፈለገችም ለምንሰ ሃኪም ቤት አብረን እንድንሄድ አልጠየቀችኘም ቀድማሰ ለምን አልነገረችኘም የኔ ጏደኝነት ትርጉሙ ምንድነው? እሷ በተቸገረችበት በተጨነቀችበት ጊዜ አላሰፈልጋትም ማለት ነው? እያልኩኘ ሳወጣና ሳወርድ ድካሙ ነው መሠል የነጋበትን ሳላው ቀው የሰልኬ አላርም ከሌሌቱ አሰራ አንድ ሠዓት ላይ ቀሰቀሰኘ .....................ይቀጥላል



አዘጋጅና አቅራቢ እውነት ይሆናል


@Lovefkrlove
@Lovefkr
#ቀለበት ምንድነው??

ምን ያደርግልሻል ቀለበት ማሠሩ፣
ልብሽ ላይ ከሌለ መውደድና ፍቅሩ፣
የመውደድ ማህተም ልብ ላይ ከሌለ፣
የፍቅር ሰው ሆኖ ፍቅር ካላደለ፣
ፍቅርን ተቀብሎ ፍቅሩን ካላጋራ፣
ከልብ ውስጥ ገብቶ ፍቅር ቤት ካልሰራ፣
ጣትሽን ስላሰርሽ ቀለበት አጥልቀሽ፣
ፍቅሬን አገኜሁት ብለሽ ታወሪያለሽ፣
የፍቅር ቀለበት ልብ ላይ ነው ቦታው፣
ለነገር ለወሬ ቦታ የማይሰጠው፣
ምቀኛ ሸረኛ መቼም የማይረታው፣
የልብ ቀለበት ፍቅር በእውነተኛ፣
ተቀብሎ እሚሰጥ ይህ ነው እድለኛ፣
የጣት ላይ ቀለበት ቢያወልቁት ለሚወልቅ፣
ላይኖር ለዘላለም ከእጅሽ ላይጣበቅ፣
ከልብሽ ግን ያለው እውነታው ቀለበት፣
መቼም የማይጠፋ የፍቅር ተምሳሌት፣
ምን ያደርግልሻል ቀለበት በጣትሽ፣
እውነተኛ ፍቅር ከልብሽ ከሌለሽ፣
ፍቅርን ተቀብለሽ ፍቅርሽን ካልሰጠሽ፣
እምነት መተሳሰብ በአንች ላይ ካልታየ፣
በጣትሽ ቀለበት እያልሽው ውድዬ፣
አንተ ትብስ አንች መባባል ከጠፋ፣
ቀለበት ምንድነው ወድቆ ለሚጠፋ፣
የፍቅር ቦታው ልብና ተግባር ነው፣
የጣትስ ቀለበት ቢያወልቁት ጠፊ ነው፣
ፍቅር ቤቱን ሰርቶ ከልብ ካልኖረ፣
የመውደድ ቀለበት በልብ ካልታሰረ፣
ያወለቁት ለታ እንደወጣ ቀረ፣
ግን ....
የመውደድ ሚስጥሩ
የፍቅር ምስጥሩ ፣
የፍቅር ጣዕሙ የፍቅር ምግባሩ፣
የፍቅር ሰው ይዞ ለፍቅር ማደሩ

ማሳሰቢያነቱ ቀለበትን ማሰር ፍቅርን እንደመግለፅ አድርገው ለሚያስቡ ይሁን!#እግዚአብሔር ልብና ልብን ይሰር 💞💞

@a1mekdi
Forwarded from Love - ፍቅር (Belay)
የምሽት ውይይታችንን ለመቀላቀል
JOIN 👉 @lovefkrlove
. `ባዓሉ ግርማ´´´

📚 የበዓሉ ግርማን የፍቅርና የትዳር
ሕይወት በጨረፍታ ሲዳሰስ ደግሞ የሚከተለዉን መስሎ አግኝቼዋለዉ። ፍቅርን የሚዘምሩ ፡ ዉበትን የሚያዘምሩ ሴት ገፀባህርያትን መፍጠር የሚሆንለት በዓሉ ፣ እሱ እራሱ ተንበርካኪ ነዉ - ለፍቅር።

📚 እሱ እራሱ እንደ ወንድ ገፀባህርያቱ ቆንጆ ሴት ካጋጠመችዉ አድናቆቱን ፊት ለፊት ለመግለፅ ቃላት የማይሰስት ነፃ ሰዉ ነዉ። በምን ይሉኝ ጠፍር ልቡንም ፡ ምላሱንም ፡ ገላዉንም ፡ ብዕሩንም ያሰረ አይደለም። ወዳጅ ነዉ ፡ ተወዳጅም ጭምር!

📚 ``በተማሪነት ዘመኑ ፡ አልፎ አልፎ ፡ ከግቢ እየወጣ ይዝናና ነበር። ለማፍቀርም ፡ ለመፈቀርም ጊዜ ነበረዉ´´ ሲባል ሰምቻለዉ። ስለ ወጣትነት የፍቅር ሕይወቱ ያዉቅ እንደሆነ ብዬ ኢየሱስወርቅ ዛፉ{አሁን ላይ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ይሳተፋሉ እንዲሁም ህብረት ባንክ ቦርድ ዉስጥ ይሰራሉ} ጠየቅሁት :-

📚 …ሚስት ከማግባቱ በፊት ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ገርል ፍሬንዱ ነበረች ፡ በጣምም ይወዳት ነበር። እሷም እንዱሁ። ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ ጋብዞኛል እሷጋ። እና ፡ ራስ መኮንን ድልድይ ፡ ከድልድዩ ወደ አራት ኪሎ ስትሄድ ፡ በስተቀኝ በኩል ፡ ቤንዚን ማድያዉጋ ስትደርስ አንድ ግቢ ነበር- እንደ ፔንሲዮንም ፣ እንደ ሆቴልም የሚያገለግል። ብዙነሽ ብዙዉን ጊዜ እዚያ ትዉል ፡ ታመሽ ነበር - ትዝ ይለኛል ፡ በደንብ ዶሮ ሰርታ ፡ ምን ብላ ምን ብላ ጋብዛናለች።

📚 በዓሉ ከብዙነሽ ጋር ስለነበረዉ ቀረቤታ ቀደም ሲል ሰምቼ ነበር። አንድ አንጋፋ ደራሲና ተርጓሚም ''ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ፡ እንደ ጣልያኖቹ…… በየመንገዱ ሲላፉ ፡ ሲሳሳቁ ፡ በሚያስቅና ስሜት ሆነዉ በርጋታ ወክ ያደርጉ እንደነበር ሁልጊዜ ትዝ ይለኛል - የእሷን ዘፈን በሰማሁ - የሱን መፅሐፎች ባነበብኩ ቁጥር'' ብሎኛል።


📚 በዓሉ በኢትዮጵያ ሬድዮ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዜና አንባቢነት ተቀጥሮ ይሰራ በነበረበት በ1950ዎቹ አጋማሽ ፡ የሬድዮ ቴክኒሽያን በመሆን አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ፡ ኪሮስ ወ/ሚካኤል የተባለ የስራ ባልደረባዉም ፡ ``እዉነት ነዉ´´ ብሎኛል።



መ ል ካ ም ን ባ ብ……

የቀረዉን ለእናንተ ትቻለዉኝ…🙏


የመፅሀፉ ርእስ - በዓሉ ግርማ ሕይወቱና
. ስራዎቹ

የመፅሀፉ ደራሲ - እንዳለጌታ ከበደ

የገፅ ብዛት - 440 ገፆች

ዋጋ - 120 ብር

የተወሰደዉ ከገፅ 120 እስከ ገፅ 121

@lovefkr

@lovefkrlove

@Yona4501
ዛሬ የማታ ዉይይት ይኖረናል ፡
በተሳትፎ ይከታተሉን 🙏

@lovefkrlove

@lovefkr