ልዩ ዜና
3.98K subscribers
452 photos
20 videos
11 files
5 links
ድል ለኢትዮጵያ
ጥቆማ‼️
በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ‼️‼️
Download Telegram
የግብጽ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚ መሆን መብቷ ቢሆንም ሉዓላዊነት ማክበር አለባት አሉ

በግብጽ የስራ ጉብኝት ላይ የሚገኙትን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ማህሙድን ያነጋገሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሳትጥስ ወደብ መጠቀም መብቷ ነው አሉ።

የሶማሊያ እና ግብጽ መሪዎች በጋራ የሰጡትን መግለጫ አዲስ ማለዳ ከ‘ኢጂፕት ቱዴይ‘ እንደተመለከተችው፤ ፕሬዝዳንት አልሲሲ “ኢትዮጵያ የኤርትራ፣ ከሶማሊያ ወይም ከጅቡቲ በኩል ወደብ መጠቀሟን አንቃወምም” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ግብጽ “ኢትዮጵያ በሌሎች አገራት ግዛት ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ እጇን ማስገባቷን” ትቃወማለች ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል። አክለውም ግብጽ በሶማሊያ የሚደርሱ ስጋቶችን አትታገስም ብለዋል።

የግብጹ ፕሬዝዳንት “ግብጽን በመሰል ጉዳዮች አትፈትኑ” ሲሉ መግለጻቸውም ተዘግቧል። አያይዘውም ለሶማሊያ መንግስት ሽብርተኛነትን በመቀነስ፣ እዳ በማሰረዝ እንዲሁም የጦር መሳሪያና ወታደራዊ ማዕቀቦች በመነሳታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሰነድ በተመለከተ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) እንዲሁም ከአረብ ሊግ የተሰጡን መግለጫዎች ማውገዟ ይታወሳል።
ዛሬ የክብር ሽኝት እና ቀብር ይከናወናል

የነፍስኄር ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስንብት እና የቀብር ስነስርዓት ዛሬ  ይከናወናል። አስከሬን ዛሬ ማለዳ  አዲስ አበባ ገብቷል።

የሙያ  አድናቂዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ እና የተለያዩ  የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባብል አድርገውለታል።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በዋሽንግተን ዲሲ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ የካቲት 4/2016 ዓ.ም ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል።

ከጠዋቱ 4:00 እስከ 4፡30 ሰዓት ሚሌኒየም አዳራሽ ይደርሳል።

ከጠዋቱ 5:00 እስከ ቀኑ 6፡30  በሚሌኒየም አዳራሽ  የስንብት መርሐግብር ይካሄዳል።

ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት  ቅ/ሥላሴ  ካቴድራል ፍትሃት እና የቀብር ስነ ስርዓት ይፈጸማል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታማሚዎች አሶሳ ከተማን ከአዲስ አበባ የሚያገናኙ መንገዶች በጸጥታ ችግር በመዘጋታቸው ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሆስፒታሎች ለመጓዝ እንደተቸገሩ ከሆስፒታሉ መስማቱን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል። በዚኹ ሳቢያ አዲስ አበባ ሂደው ከፍተኛ ሕክምና እንዲያገኙ ከሐኪሞች ወረቀት የሚጻፍላቸው ታማሚዎች ሕይወታቸው እያለፈ መኾኑን የሆስፒታሉ አስተዳደር መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ሆስፒታሉ፣ ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት እንዳለበትና ባኹኑ ወቅት ከጤና ሚንስቴር መድሃኒት የሚያገኘው በአየር ትራንስፖርት ብቻ እንደኾነ መግለጡን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። አምቡላንሶች በጸጥታ ችግር በክልሉ ውስጥ መንቀሳቀስ አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰው የገለጠው የሆስፒታሉ አስተዳደር፣ ታጣቂዎች ካኹን ቀደም አንድ ታማሚዎችን የያዘ አምቡላንስ እንዳቃጠሉ ጠቅሷል ብሏል።
በአጼ ሀይለስላሴ ስም የተሰየመው ፈጣን መንገድ በኬንያ ተመረቀ

በኬንያ በአፄ ኃይለስላሴ ስም የተሰየመው የፍጥነት መንገድ መውጫ መጠናቀቁ የትራፊክ ፍሰትን ከማቃለሉም በላይ አሽከርካሪዎች በቀላሉ ወደ መሃል ከተማ እንዲገቡ ያስችላል ተብሏል። የፍጥነት መንገድ በ2021 ከተጀመረ ወዲህ ወደ መሃል ከተማ የሚገቡ አሽከርካሪዎች ወደ ሙዚየሙ መውጫ እና ወደ መሃል ከተማ ለመድረስ ዩኒቨርሲቲ ሙንገድ፣ ኡሁሩ መንፈድ ወይም ኪፓንዴ መንገድን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን ይጠቀሙ ነበር።

አዲሱ የመውጫ መንገድ በአምስት ወራት ውስጥ በቻይና እና ኬንያዊያን የመንገድ ተቋራጮች የተገባ ሲሆን ኬንያ የፈጣን መንገዷን መውጫ ኢትዮጵያን ከ40 ዓመት በላይ ለመሩት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በመሰረቱት አጼ ሀይለስላሴ ስም ሰይማለች።ካሳለፍነው ሀምሌ ጀምሮ ግንባታው ሲከናወን ነበር።

ባለ አምስት መስመር መውጫ መንገዱ አሽከርካሪዎች ወደ ማዕከላዊ የንግድ አውራጃ በቀላሉ እንዲገቡ እና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ ያለመ ነው። የቻይና መንገድ እና ድልድይ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ዩዋን ቹንኩን፣ ፈጣን መንገድ ኩባንያ ሊሚትድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስቲቨን ዣኦ፣ የኬንያ የመንገድ እና ትራንስፖርት ዋና ፀሀፊ ጆሴፍ ምቡጓ እና እና የኬንያ ብሔራዊ አውራ ጎዳናዎች ባለስልጣን (KeNHA) ዋና ዳይሬክተር ኩንጉ ንዱንጉ በተገኙበት መንገዱ ተመርቋል።

የዚህ የፍጥነት መንገድ ጥቅም ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን ከማዕከላዊ ቢዝነስ አውራጃ (ሲቢዲ) እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች እምብርት ከሆነው ከሃራምቤ ጎዳና የቅርብ መውጫ ሆኖ ያገለግላል ሲል የኬንየው ዘ ስታንዳርድ ዘግቧል።
በበዓሉ ዋዜማ ካጋጠሙ ሁለት የእሳት አደጋዎች ውጪ የጥምቀት በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም ተከብሯአል።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በዓለ ጥምቀተ በባህሩ ቦታና ታቦታቱ  ከመንበራቸዉ ሲወጡም ሆነ ሲመለሱ  በነበሩ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳላጋጠማቸው ለጣቢያች ገለፁ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣቢችእንደተናገሩት  ከበዓላቱ ቀናት አስቀድሞ  ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከበዓሉ አስተባባሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተለያዩ መድረኮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን  በመስራቱና ህብረተሰቡም ከኮሚሽን መ/ቤቱ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጉ በዓሉ  በሰላም ተከብሯል ብለዋል።

ሆኖም በበዓሉ ዋዜማ በከተራ ዕለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ራስ ደስታ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንደዚሁም  በልደታ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 9 በግተራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ  በአጋጠሙ ሁለት የእሳት አደጋዎች ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደርሷል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሁለቱም ቦታዎች ያጋጠሙት  የእሳት አደጋዎች ተዛምተዉ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ  መቆጣጠር  ችለዋል።

በአደጋዉ በሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስት እና ከገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት ተሰናበቱ

ላለፉት 11 ዓመታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ ደመቀ መኮንን፤ ከመንግስት እና በገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት መሰናበታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። አቶ ደመቀ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት በነበራቸው የኃላፊነት ቦታ ላይ፤ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መተካታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል]
B