''እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" ሉቃ 1÷19
እንካን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
እንካን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ልቡና ውስጥ የእመቤታችን ፍቅር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በደስታቸውም በኅዘናቸውም የእመቤታችን ስም ሰዓሊ ለነ ቅድስት ሳይሉ አይውሉም ፣አያድሩም።- አንድ የውጭ ሀገር ጸሐፊ ስለ እመቤታችንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለድንግል ማርያም ስላለው ፍቅር ሲናገር” የኢትዮጵያ ምእመናን ደማቸው ቢመረመር ማርያም ማርያም የሚል ጽሑፍ በውስጣቸው ተጽፎ ይገኛል”አለ። -እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእኛ ለሰው ልጆች ሁሉ ትምክህታችን መመኪያችን ፣የመዳናችን ተስፋ ናት። የመንፈስ ቅዱስ ዋሽንት፣የመንፈስ ቅዱስ በገና በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የምሥራቅ ቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በድርሰቱ “አክሊለ ምክሕነ ወመሠረተ ንጽሕነ:የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችን መሠረት ” ይላታል(የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም )
የቊስጥንጥንያ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስም” ልዑል እግዚአብሔር የተካነባት መቅደስ እመቤታችን እንደምን ያለች ድንቅ ናት” አለ (ሃይ•አበው ዘኤራቅሊስ48÷17). ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዘወትር ሥርዓተ አምልኮዋ ጊዜ የምትገለገልባቸው የተለያዩ የጸሎትና የቅዳሴያት መጻሕፍት ሁሉ ነገረ ማርያም አስተምህሮዋን በስፋትና በጥልቀት የሚመሰክሩና የሚያስረዱ ናቸው። ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም በዕለተ ዓርብ የጌታ ወዳጅ በሆነው በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አማካኝነት (አንጻር) ለዓለም ሁሉ እናት ሆና በጸጋ ተሰጥታለች። “በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት”(ዮሐ ፲፱÷25).መዝገበ በረከት የሆነችው እመቤታችን ከሥላሴ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች።ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “የምሕረት ባሕር ” በማለት ይጠሯታል። በቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር የሚጸለየው በጉባኤ ኒቅያና በጉባኤ ቊስጥንጥንያ የተረቀቀው ጸሎተ ሃይማኖት (Niceo Constantinopolitan Creed)
የእመቤታችን የድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት ከነገረ ድኅነት ጋር ያለውን ጥልቅ ምሥጢር አጉልቶ ያሳያል። – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባሏት መጠነ ሰፊ ውዳሴያትና ዝማሬያት ውስጥ ሁሉ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ተገቢውን ምስጋና ታቀርባለች። የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ልቡና ውስጥ የጠለቀና ሥር የሰደደ ነው። በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴያችን ሁሉ ከስመ ሥላሴ ቀጥለን የምንዘምረው የድንግል ማርያምን ምስጋና ነው።ድንግል ማርያምን ስናመሰግናት የንዴት ረመጥ የሚያቃጥላቸው አሉ። እኛ ምን እናድርግ እናትነትን ከ ድንግል ጋር አስተባብራ ስለተገኘች ፣ቅዱስ ገብርኤልም፣ ቅድስት ኤልሳቤጥም አስተማሩ (ሉቃ1÷43-44)- ለድንግል ማርያም የሚሰጠውን ክብር መቃወም በምንም አይነት ዘዴ ልጇን ማክበር ሊሆን አይችልም።ክርስቶስ ለተቀመጠባት አህያ ፣ልብስ ከተነጠፈላት ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅጸንዋ ለተሸከመቺው ፣ለወለደችው ፣ላጠባችው ለድንግል ማርያም ክብር መስጠት የክርስቶስን ክብር የሚሸራርፍ ሒሳብ የለውም፣ሊኖረውም አይችልም። –
በኦርቶዶክሳዊ የነገረ ማርያም አስተምህሮ መሠረት እመቤታችንን ድንግል ማርያም የምትጠራባቸው ፫ ዋና ዋና ስያሜዎች አሏት።እነዚህም ወላዲተ አምላክ (Thotokos -Mother of God):ወትረ ድንግል (ዘለዓለማዊት ድንግል)(Aeiparthenos-Ever Virgin):በአማን ንጽሕት ወቅድስት በኲሉ(panagia-All pure And All holy) ናቸው። – ኢትዮጵያዊ ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ” አልቦ ጸሎት ፣ወአልቦ ትንባሌ እንበለኪ ማርያም ዘያዓርግ ሉዓሌ፣ ድንግል ሆይ! የሰው ልጆች ጸሎትና ልመና ውስተ ኑኅ ሰማይ የሚያርግብሽ ምዕራገ ጸሎት አንቺ ነሽ” እንዳለ በኦቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን አማላጅነት የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትና ምልጃ አክሊል (ጉልላት) ነው ።(ማኅሎተ ጽጌ )
አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ “እመቤታችን ማርያም ሆይ! ርኅራኄሽ ለሰው ልጅ ብቻ አይደለም፣ይልቁንም ለፍጥረት ሁሉ ርኅርኅተ ልቡና ነሽ “ሲል ገልጾ ተናግሯል። ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም በወላዲተ አምላክነት ጸጋዋ በድቀት ኃጢአት የነበረውን መላውን የሰው ዘር ወደ ቀደመው ክብሩ የተመለሰባትና ወደ ጥንተ ርስቱ የገባባት ምክንያተ ድኅነት መሠረተ ሕይወት ናት። ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያድለን !#join or #share
▫️ @linkortodoxe21
🔸 @linkortodoxe21
🔹 @linkortodoxe21
ሥርዓተ ጸሎት
ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡-ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
#join or #share
@linkortodoxe21

🔴1.በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል
በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/
🔴2.በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል
በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡ ልባችንን የቂም በቀልና የክፋት ምሽግ አድርገን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ “ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመዘርዕ ዘወድቀ ማእከለ አሥዋክ” /የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካል እንደ ወደቀ ዘርዕ ነው/ /መጽሐፈ መነኮሳት/፡፡
🔴3.ሀሳባችንን ሰብስበን አንድ ልብ በመሆን መጸለይ ይገባል
ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የጰራቅሊጦስ ዕለት አንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ /የሐ. ሥራ 2፡1-4/
🔴4.በመፍራት ማለት ንስሐ በመግባት ከልብ በመጸጸት መጸለይ ይገባል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
ነቢዩ ሕዝቅያስ በመፍራትና ከልብ በመጸጸት ሆኖ ስለጸለየ በዕድሜው ላይ አሥራ አምስት ዓመት ተጨምሮለታል፡፡ /2ኛ ነገሥት 20፡1-6/ /ኢሳ. 38፡1-5/
🔴5.በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ተሠርቷል
“በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ ወአስተርኢ ለከ”
/በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እታይሀለሁም/ /መዝ. 5፡3/
🔴6.ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ይገለጽ ዘንድ የተነገረለት ነውና ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
🔴7.በጸሎት ጊዜ መስገድ ይገባል
ይኸውም ጸሎቱን ስንጀምርና ስንጨርስ እንዲሁም በጸሎት ጊዜ ስግደትን ከሚያነሳ አንቀጽ ስንደርስ መስገድ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
🔴8.ጸሎት ስንጀምር በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ይገባል
ስናማትብም ከላይ ወደታች ከግራ ወደ ቀኝ ነው፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፡፡ ከላይ ወደታች የምናማትብበት ምክንያት የሰላም አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት የመውረዱ ምሳሌ ነው፡፡ ከግራ ወደቀኝ የምናማትብበት ምክንያት ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ስለእኛ ሞቶ ከሞት ወደ ሕይወት ከኀሣር ወደ ክብር፣ ከሲኦል ወደገነት የመመለሱ ምሳሌ ነው፡፡ በቀኝ ገነት፣ በግራ ሲኦል ይመሰላልና፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
በመስቀል አምሳል የምናማትብባቸው ጊዜያቶችም ጸሎት ሲጀመርና መስቀሉን ከሚያነሳ አንቀጽ ሲደረስ ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
🔴9.ዐይኖችን ወደላይ አቅንቶ መጸለይ ይገባል
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ባስነሳው ጊዜ ዐይኖቹን ወደላይ አቅንቶ እንደጸለየ ሁሉ የሚጸልይ ሰው ዓይኖቹን ወደ ላይ ማንሳት እንዲገባ ነው፡፡ /ዮሐ. 11፡41/
🔴10.ለሌሎችም መጸለይ ይገባል
ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን፤ ለሌሎችም መጸለይ ይገባል፡፡ ኤርምያስ ለሀገር ሰላም መጸለይ እንደሚገባ ‹‹በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ስለእርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ›› /ት.ኤር. 29፡7/፡፡ ታመው በየሆስፒታሉ፣ በየቤቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን፣ በየማረሚያ ቤቱ ላሉ በአጠቃላይ በተለያየ ችግር ለሚንገላቱ ሁሉ መጸለይ ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአገር መጸለይ ይገባል፡፡ “ትድኑም ዘንድ እያንዳንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ” /ያዕ. 5፡16/
Share share share አድርጉት
#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)

✝መንፈሳዊ ህይወት✝ pinned «🔴1.በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/ 🔴2.በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን…»