መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
'"የንጉስ ስልጣን በስጋ ላይ ነው የካህን ስልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው '"
@linkortodoxe21
"የጭንቅ ቀን አማላጅ ወላዲተ አምላክ "

""እንደአንቺ ያለ አማላጅ እንደ ልጅሽ ያለ መሀሪ የለም የተራበ ሰው ምግብ ለመብላት እንደሚቸኩል ክርስቶስም ለመማር ይቸኩላል ""

@linkortodoxe21
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 28)
----------
16፤ ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ። በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው፤ እኔ አላወቅሁም ነበር አለ።

17፤ ፈራ፥ እንዲህም አለ። ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።

" ዳዊትም። ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነው፥አለ "
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 22:1)

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
" ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15)

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🔘ሰባቱ አባቶች የምንላቸው

▪️.ልዑል እግዚአብሔር
▪️.የንስሐ አባት
▪️.ወላጅ አባት
▪️.የክርስትና አባት
▪️.የጡት አባት
▪️.የስልጣን አባት
▪️.የቀለም አባት

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
⚪️ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 7 ጊዜ እኔ ነኝ እኔ እያለ የተናገራቸው

🔶የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ

🔶የዓለም ብርሀን እኔ ነኝ

🔶እኔ የበጎች በር እኔ ነኝ

🔶መልካም እረኛ እኔ ነኝ

🔶ትንሳኤ ህይወት እኔ ነኝ

🔶እኔ መንገዱና እውነት ህይወት እኔ ነኝ

🔶እውነተኛ የህይወት ግንድ እኔ ነኝ

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🔶አምስቱ ፍኖተ ጻድቅ የተባሉት🔶

✏️ፍቅር
✏️ትህትና
✏️ጾም
✏️ፀሎት
✏️ምጽዋት ናቸው

@linkortodoxe21
🔶አምስቱ ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት 🔶
✏️ትዕቢት
✏️ስስት
✏️ምቀኝነት
✏️ስርቆት
✏️ዝሙት ናቸው

@linkortodoxe21
''እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" ሉቃ 1÷19
እንካን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ልቡና ውስጥ የእመቤታችን ፍቅር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በደስታቸውም በኅዘናቸውም የእመቤታችን ስም ሰዓሊ ለነ ቅድስት ሳይሉ አይውሉም ፣አያድሩም።- አንድ የውጭ ሀገር ጸሐፊ ስለ እመቤታችንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለድንግል ማርያም ስላለው ፍቅር ሲናገር” የኢትዮጵያ ምእመናን ደማቸው ቢመረመር ማርያም ማርያም የሚል ጽሑፍ በውስጣቸው ተጽፎ ይገኛል”አለ። -እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእኛ ለሰው ልጆች ሁሉ ትምክህታችን መመኪያችን ፣የመዳናችን ተስፋ ናት። የመንፈስ ቅዱስ ዋሽንት፣የመንፈስ ቅዱስ በገና በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የምሥራቅ ቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በድርሰቱ “አክሊለ ምክሕነ ወመሠረተ ንጽሕነ:የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችን መሠረት ” ይላታል(የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም )
የቊስጥንጥንያ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስም” ልዑል እግዚአብሔር የተካነባት መቅደስ እመቤታችን እንደምን ያለች ድንቅ ናት” አለ (ሃይ•አበው ዘኤራቅሊስ48÷17). ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዘወትር ሥርዓተ አምልኮዋ ጊዜ የምትገለገልባቸው የተለያዩ የጸሎትና የቅዳሴያት መጻሕፍት ሁሉ ነገረ ማርያም አስተምህሮዋን በስፋትና በጥልቀት የሚመሰክሩና የሚያስረዱ ናቸው። ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም በዕለተ ዓርብ የጌታ ወዳጅ በሆነው በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አማካኝነት (አንጻር) ለዓለም ሁሉ እናት ሆና በጸጋ ተሰጥታለች። “በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት”(ዮሐ ፲፱÷25).መዝገበ በረከት የሆነችው እመቤታችን ከሥላሴ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች።ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “የምሕረት ባሕር ” በማለት ይጠሯታል። በቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር የሚጸለየው በጉባኤ ኒቅያና በጉባኤ ቊስጥንጥንያ የተረቀቀው ጸሎተ ሃይማኖት (Niceo Constantinopolitan Creed)
የእመቤታችን የድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት ከነገረ ድኅነት ጋር ያለውን ጥልቅ ምሥጢር አጉልቶ ያሳያል። – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባሏት መጠነ ሰፊ ውዳሴያትና ዝማሬያት ውስጥ ሁሉ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ተገቢውን ምስጋና ታቀርባለች። የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ልቡና ውስጥ የጠለቀና ሥር የሰደደ ነው። በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴያችን ሁሉ ከስመ ሥላሴ ቀጥለን የምንዘምረው የድንግል ማርያምን ምስጋና ነው።ድንግል ማርያምን ስናመሰግናት የንዴት ረመጥ የሚያቃጥላቸው አሉ። እኛ ምን እናድርግ እናትነትን ከ ድንግል ጋር አስተባብራ ስለተገኘች ፣ቅዱስ ገብርኤልም፣ ቅድስት ኤልሳቤጥም አስተማሩ (ሉቃ1÷43-44)- ለድንግል ማርያም የሚሰጠውን ክብር መቃወም በምንም አይነት ዘዴ ልጇን ማክበር ሊሆን አይችልም።ክርስቶስ ለተቀመጠባት አህያ ፣ልብስ ከተነጠፈላት ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅጸንዋ ለተሸከመቺው ፣ለወለደችው ፣ላጠባችው ለድንግል ማርያም ክብር መስጠት የክርስቶስን ክብር የሚሸራርፍ ሒሳብ የለውም፣ሊኖረውም አይችልም። –
በኦርቶዶክሳዊ የነገረ ማርያም አስተምህሮ መሠረት እመቤታችንን ድንግል ማርያም የምትጠራባቸው ፫ ዋና ዋና ስያሜዎች አሏት።እነዚህም ወላዲተ አምላክ (Thotokos -Mother of God):ወትረ ድንግል (ዘለዓለማዊት ድንግል)(Aeiparthenos-Ever Virgin):በአማን ንጽሕት ወቅድስት በኲሉ(panagia-All pure And All holy) ናቸው። – ኢትዮጵያዊ ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ” አልቦ ጸሎት ፣ወአልቦ ትንባሌ እንበለኪ ማርያም ዘያዓርግ ሉዓሌ፣ ድንግል ሆይ! የሰው ልጆች ጸሎትና ልመና ውስተ ኑኅ ሰማይ የሚያርግብሽ ምዕራገ ጸሎት አንቺ ነሽ” እንዳለ በኦቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን አማላጅነት የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትና ምልጃ አክሊል (ጉልላት) ነው ።(ማኅሎተ ጽጌ )
አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ “እመቤታችን ማርያም ሆይ! ርኅራኄሽ ለሰው ልጅ ብቻ አይደለም፣ይልቁንም ለፍጥረት ሁሉ ርኅርኅተ ልቡና ነሽ “ሲል ገልጾ ተናግሯል። ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም በወላዲተ አምላክነት ጸጋዋ በድቀት ኃጢአት የነበረውን መላውን የሰው ዘር ወደ ቀደመው ክብሩ የተመለሰባትና ወደ ጥንተ ርስቱ የገባባት ምክንያተ ድኅነት መሠረተ ሕይወት ናት። ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያድለን
!

#join or #share
▫️ @linkortodoxe21
🔸 @linkortodoxe21
🔹 @linkortodoxe21