መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ምን አለ ያጎደልክብኝ
ሳትነፍገኝ ሁሉን ሰጠኸኝ
ሁነኸኝ እናት እና አባት
አለፈ ብዙ ዘመናት (2)
አዝ...
አኖርከኝ ዛሬም በጤና
ወጥቸ ገባሁ በደና
መንገዴን ሰጥቸሀለው
ስትመራኝ እከተላለው
አዝ...
ወረት አታውቅም ጌታየ
መች ቀረ ፈሶ እንባየ
ህይወቴ በመድሀፍህ ነው
መፍራቴ ከቶ ለምን ነው
አዝ...
አውቀኸኝ ሳሰራኝ ገና
ሞልተኸኝ ቅኔ ምስጋና
ካንተ ነው የተቀበልኩት
በመዝሙር የሰለጠንሁት
አዝ....
መዛሌ በውሀ ጥም
በባእድ ሀገር መድከም
በብዙ ስጋት ተጉዤ
ቁሜአለው ስምህን ይዤ
አዝ....
በትዳር በልጅ ባርከኸኝ
የልቤን ደስታ ሰጠኸኝ
ስለያዝኩ ጌታ ያንተን እጅ
ተባልኩኝ የንጉሱ ልጅ

-
አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል /2x/
የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን /2x/
አዝ............
ጥቂቶች ሆነን ተነስተን ነው
እንዲሁ ምድርን የሞላ ነው
ብንጣል ከውሀ ከእሳት
ፅኑ ነው የያዝነው እምነት

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል /2x/
የተክለ ሐይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን /2x/
አዝ.........
ድሆች ስንባል ባለ ፀጋ
ሁሉን የያዘ ነው ከእኛጋ
ብርቱዉን ጎልያድ የጣለ
በወንጭፋችን ጠጠር አለ

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል /2x/
የክርስቶስ ሰምራ የአርሴማ ልጆች ነን /2x/
አዝ...........
በሕይወት በቃል ያስተማረን
አምላካችን ነው የነገረን
የዚአለም ጨው ተብለናል
አልጫውንም አጣፍጠናል

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል /2x/
የቅዱስ መርቆርዮስ የማርቆስ ልጆች ነን /2x/
አዝ.........
እንደ ደመና የከበቡን
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩን
ስላሉን ብዙ ምስክሮች
ደካሞች ሲሉን ነን ሀይለኞች

ቤተክርስቲያን እማማ ዝናሽ በአለም ይሰማ
ቤተክርስቲያን እማማ ዝናሽ በአለም ይሰማ

እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ
ለሚመጣ ትውልድ ሁሉ
ክብርህን ሃይልህን ፅድቅህን እስክነግር ድረስ
አቤቱ አትተወኝ
አትንኩን
ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
"አንድ ሰውስ እንኳ ድኻ ነኝ ወይም ድኻ አደግ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ፤ ከድኻ ማኅበረሰብ የተገኘሁ ነኝ ብሎ ማንም አይዘን፤ ከአንካሳ ልብና ከሰነፍ ሕሊና በቀር የሚያሳዝን ምንም ምን የለምና። በጎ ምግባርን እንዳንይዝ የሚከለክለን አንዱና ብቸኛው ዕንቅፋት መንፋሳዊ ድካም እና የሕሊና ዓቅመ ቢስነት እንጂ ሌላ ምንም አይደለምና።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ውዳሴ ጳውሎስ መጽሐፍ
ጾመ ነቢያት

ጾመ ነቢያት የተባለበት ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡

ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ ወደ ግብፅ ስለ መሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለመጠመቅ፣ በትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ። ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡

#የነቢያት_ጾም
ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት
ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ ኢሳ 58-1፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡

#ጾመ_ስብከት
የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡ ዘመነ ስብከት ከታኅሣሥ 7 ቀን እስከ ታኅሣሥ 13 ቀን ድረስ ያሉት ዕለታት ናቸው፡፡ ምን ጊዜም ወደ ታኅሣሥ 6 አይወርድም ወደ 14ም አይወጣም፡፡ ስብከት ማለት ዐዋጅ ትምህርት ማለት ነው፡፡ ይህም ከልደተ አብርሃም እስከ ልደተ ዳዊት ያለው ትውልድ የሚታሰብበት ሙሴ በኦሪት፣ ነቢያት በትንቢት፣ ዳዊት በመዝሙሩ በብዙ ምሳሌ ይወርዳል ይወለዳል ሲሉ የተናገሩት የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ መዝ.143-7 ፤ ኢሳ 64-1፡፡ የሚዘመረው መዝሙር «ወልደ መድኅነ ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፤ ከዓለም በፊት የነበረውንና መድኃኒት የሆነውን ወልድን እንሰብካለን» የሚል ነው ቅዱስ ያሬድ፡፡ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት የተናገሩለትንና ሱባዔ የቆጠሩለትን ሐዋርያት ያላቸውን ትተው ተከተሉት ፈቃዱንም ፈጸሙ፡፡ ስለዚህ ምእመናን ክፉ ሐሳባቸውን አርቀው ርኩሰትን አስወግደው ፍጹም ለእግዚአብሔር እንዲገዙ ትምህርት ይሰጣል፣ ስብከት ይሰበካል፡፡ የሚነበበውም ምንባብ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ ዮሐ.1÷44-49 ፤ ዕብ.1÷1-2፡፡

#ብርሃን
ከስብከት ቀጥሎ ያለችው ሰንበት ስትሆን እንደ ኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አስተምህሮ ከልደተ ዳዊት እስከ ፍልሰተ ባቢሎን ያለው 14 ትውልድ ይታሰብበታል፡፡ ክቡር ዳዊት «አቤቱ ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ» /መዝ. 42÷3/ እያለ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ከርሱ ወገን እንዲወለድ ትንቢት ስለተናገረ ይህ የሚታሰብበት ነው፡፡ ነቢዩ ዓለም በጨለማ ስለሆነች ብርሃንህን ላክ፣ ሐሰትና የሐሰት አባት ነግሦባታልና እውነትህን ላክ አለ፡፡ ወልድን ላክልን ማለቱ ነው፡፡ ይህንም ቅዱስ ዮሐንስ «ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ» ብሎ ሲመሰክር ጌታም ራሱ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም» ብሎ ተናግሯቸዋል፡፡ ዮሐ. 8÷12 ፡፡ እንዲሁም ብርሃንን እውነት ማለቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ ላክልን ሲል ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ስደድልን ማለቱ ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን አውጣን፣ ሥጋህንና ደምህን ስጠን ሲልም ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚዘመሩት መዝሙራት «ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ወይዜንዎ ለጽዮን በቃለ ትፍሥሕት፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፣ የምስጋናን ቃል ለጽዮን የሚነግራት ወልድ በክብር፣ በጌትነት እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ነገረ፤ አስታወቀ፡፡» የሚሉ ናቸው፡፡ ንስሐ ከመግባት ቸል እንዳይሉ ይነግራቸዋል፡፡
ነቢያት የጥል ግድግዳን ሰብሮ መለያየትን አጥፍቶ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያወጣቸውን ሽተው ውረድ ተወለድ አድነንም እያሉ ጮኹ፣ እውነተኛ ብርሃን ጌታችን ጊዜው ሲደርስ ወደ ዓለም ወጣ፡፡ በመምጣቱም በጨለማ ያለው በብርሃን እንዲገለጥ ለሰው ልጆች እግዚአብሔርን የሚያውቁባት ዕውቀት ተሰጠች፡፡

#ኖላዊ
ኖላዊ ተብሎ የሚጠራው ከብርሃን ቀጥሎ ያለው ሳምንት ነው፡፡ የቃሉ ፍች እረኛ ማለት ነው፡፡ እረኞች ለበጎቻቸው
የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውኃ ሳያጓድሉ እንዲጠብቁ
እግዚአብሔርም ሕዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነው፡፡ ይኽንን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሲያብራሩ ከፍልሰተ ባቢሎን እስከ ልደተ ክርስቶስ ድረስ ያለው 14 ትውልድ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ዘመን እሥራኤላውያን ከሀገራቸው ተሰደው በባቢሎን 70 ዘመን ከኖሩ በኋላ ዘሩባቤልን አንግሦላቸው ይዟቸው እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ከዚያ በፊት እሥራኤል ጠባቂ እንደሌለው መንጋ ተበታትነው ሲኖሩ ነቢያት ከኪሩቤል ላይ የሚገለጥ እረኛቸው እንዲገለጥ የእሥራኤል ጠባቂያቸው ሆይ፣ አድምጥ እያሉ የጠየቁበት መታሰቢያ ነው፡፡ መዝ.79-1-3፡፡ መዝሙሩም «ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃለ እግዚአብሔር ዘወረደ እምላዕሉ፤ የእግዚአብሔር ልጅና ቃሉ የሆነ ክርስቶስ ከላይ የወረደ ወደ ዓለም የመጣ እረኛ» የሚል ሲሆን የሚነበበው ደግሞ አንቀጸ አባግዕ የተባለው የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ ዮሐ. 10÷1-22፡፡ እረኛ የሌለው በግ ተኩላ ነጣቂ እንዲበረታበት በበደሉ ከትጉኅ እረኛው የተለየው የሰው ልጅም በሲኦል አጋንንት በርትተውበት ሲጠቀጠቅ ኖሯል፡፡ እንዲሁም ከመንጋውና ከእረኛው የተለየ በግ እንዲቅበዘበዝ አምላኩን ዐውቆ አምልኮቱን ከመግለጽ የወጣው ሕዝብ በየተራራው መስገጃዎችን እየሠራ የሚታደገውን አምላክ በመፈለግ ሲንከራተት ኖሯል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ «እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር» እንዳለ፡፡ 1ኛ ጴጥ.2÷25፡፡ ነቢያት በዓለም ተበትነው የሚቅበዘበዙትን ሕዝቡን በቤቱ ሰብስቦ የሚጠብቃቸው እውነተኛ ቸር እረኛ እንዲወለድ ስለተናገሩ ያን ለማስታወስ ሳምንቱ ኖላዊ ተባለ፡፡

ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደጾሙ እንደጸለዩ በልደቱም እንስሳት፣ ሰዎች እንዲሁም መላእክት በአንድነት በደስታ እንደዘመሩ የእኛም ደስታ የተረጋገጠበት ነው፡፡ በመሆኑም በፍቅር፣ በጾም በጸሎት ዛሬም እናስበዋለን፡፡ ነቢያት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን ለዚህም አምላካችን ይርዳን አሜን፡፡

ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!
"ጻዲቁ ዮሴፍ እጅግ ከባድ የሆነ ውጪያዊ ውጊያ ከጲጥፋራ ሚስት ቢገጥመውም አልወደቀም ። እርሱ ኃጢአትን በልቡ ውስጥ ስላልተቀበለው ፈተናውንም አልተቀበለውም ። ስለሆነም ጥቃቱን ሊቋቋም ችሏል ። ዲያብሎስ አሳቦችን ያቀርብልሃል እንጅ ተቀብለህ ተግባራዊ እንድታደርጋቸው አያስገድድህም " ።

[የዲያብሎስ ውጊያዎች ፪ኛ መጽሐፍ] pop shenouda
"ትህትና"

✞ ትህትና መድኅን ነው ከሰይጣን አሽክላ ያድንሃል። / አባ እንጦንስ/
✞ ትህትና የሰው ዘመድ ነው። / አባ አሞን /
✞ ትህትና የማይናድ ደልዳላ መሬት ነው። /አባ አርሳንዮስ /
✞ ትህትና ክርስቲያናዊ ምልክት ነው። /አባ መቃርስ/
✞ ትህትና የሰው ሁሉ ጋሻ ጦር ነው። /አባ በሐይ/
✞ ትህትና ግድግዳን የምታስጌጥ የአፈር ወይዘሮ ናት። /አባ አጋቶን/
✞ ትህትና የመንግስተ ሰማያት መመላለሻ በር ነው። /አባ ሚልኪ/
✞ ትህትና ሕፀጽን የሚያስታውቅ መስታወት ነው። /አባ ጰርዬ /
✞ ትህትና የነፍሳት ወደብ ነው። /አባ ዮሐንስ/
✞ ትህትና የወንጌል ትእዘዝ መጀመሪያ ነው። /አባ ዮሐንስ ሐፂር/
✞ ትህትና ወደ ንፁሐ ልቡና ሰገነት የሚወጡበት ነው
✞ ትህትና ዕፀ ሕይወት ናት።/አባ መቃርስ /
"ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጦም ነው፡፡የምንጦምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጦም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡"
ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✥ ኪዳነ ምህረት እናቴ
ኪዳነምሕረት ልዩ ነሽ ለእኔ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
💚 💚
💛 💛
❤️ ❤️
የልቤን በልቤ ይዥ ከፊትሽ ቁሜለሁ .. ካለኝ ነገር ሁሉ አንችን መርጫለሁ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው Hdbdu
#የልቤን_በልቤ_ይዤ

የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ

ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2)
#አዝ
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2)
#አዝ
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ(2)
#አዝ
አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2)
​​#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ #ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡

እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡

በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡
ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
💚 💚
💛 💛
❤️ ❤️
በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል.. ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡

አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ ወይንም አምስት መቶ ብር መክፈል...፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ «ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡

ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት...፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፡፡ አልቻለም ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና፡፡ «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ
እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው «አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡

«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር
የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።

🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

"አስቦ የሚራመድ ብዙ ርቀት ይጓዛል" ይላሉ አበው።

" ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ "
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:13)

" ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 21:16)
ሰንበተ ክርስቲያን
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ
ምሬሀለሁ በለኝ
እኔ ምንም የለኝ ባዶ ነኝ ጌታዬ
በል እንዲሁ ማረኝ ቸሩ ፈጣሪዬ
ኤሳው ለበረከት ቢጣደፍ ቢቻኮል
አቢሴሎም ቢመጣ የጣፈጠን መብል ለካስ ያልመረጥከው አይቆምም በፀጋ ምሬሃለሁ በለኝ እኔ አንተን ስጠጋ አልክድህም ብዬ በመማል አይደለም እከተልሃለሁ በማለትም አይደለም በህሊናዬ ላይ እኔ አላዝበትም ምሬሃለሁ ካልከኝ እድናለሁ መቼም አንተ ስትሰጥ ነው ጽድቅና ሹመት ማን ሚዛን ይደፋል ጌታ ባንተ ፊት ብዙ በደከመ በሮጠም አይደለ
ማረኝ የኔ ጌታ እንዳንተ ማን አለ
ማረኝ የኔ ጌታ እንዳንተ ማን አለ

ኢትዮጵያ
ሰላም የሚበዛበት የተበታተነው ልብ ለልብ የሚተሳሰርበት የምህረት ፆም ያድርግልን!!!

Share share share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ:
"ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጦም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጦም ጦምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡”(ማቴ.6፡21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡
ጦምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የፆም ወር እንለምነው፡፡
ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

(ቅዱስ ኤፍሬም)
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

"ጽዮን ማርያም"

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን::

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም::

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው::

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19)

#በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:-

1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19)

2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1)

3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21)

4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1)

5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::

6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል::

7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል::

8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው::

" አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን "

"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና::

ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

#እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ)
¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

#ሼር

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21