መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ታላቁ ሊቅ አባታችን

💕ቅዱሰ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

እንዲ ይመክረናል

👉እውነተኛ ክብርን ማግኘት ትፈልጋለህን?

👉ክብርን ናቅ፤ ያን ጊዜም ትከብራለህ፡፡

👉ለምን እንደ ናቡከደነፆር ታስባለህ?

👉እርሱ ክብርን መጨመር በፈለገ ጊዜ ከዕንጨትና ከድንጋይ የራሱን ምስል ሐውልት አቁሞአልና፤

👉 ሕይወት በሌለው በዚህ ግዑዝ ነገር ሕይወት ላለው ለእርሱ ክብር

👉 የሚጨምርለት መስሎት ነበርና፡፡ [ነገር ግን ክብር ሳይኾን ውርደት አገኘው፡፡]

👉እንግዲህ የስንፍናውን መጠን አለፍነት ታያለህን?

👉እከብርበታለሁ ብሎ ባቆመው ነገር እንዴት የገዛ ራሱን እንደ ዘለፈበት ትመለከታለህን?

👉 በራሱና በገዛ ነፍሱ ንጽህና ሳይኾን ሕይወት በሌለው ነገር ላይ መደገፉ፣

👉 በዚያ ረዳትነትም ክብርን ማግኘት ፈልጎ ሐውልቱን ማቆሙ፥ ከዚህ በላይ ምን ሞኝነት አለ?

👉 ራሱን ለማክበር ብሎ የገዛ ሕይወቱን እንደ ማስተካከል፥ በዕንጨት ላይ ዕንጨት እንደ መጨመር ያለ ምን ሞኝነት አለ?

👉 ይህ ማለት “አንድ ሰው ፈሊጥ ያውቃል የሚባለው ሰው በመኾኑ ሳይኾን የቤቱ ምንጣፍ ያማረ ስለ ኾነ፣ የቤቱ ደረጃም የተወደደ ስለ ኾነ ነው” እንደ ማለት ይቈጠራል፡፡

👉 በእኛ ዘንድ በእኛ ዘመን ናቡከደነፆርን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡

👉እርሱ ሐውልት እንዳቆመ አንዳንዶችም ስለ ለበሱት ልብስ፣ ስለ ገነቡት ቤት፣ ስላላቸው ፈረስ፣ ገንዘብ ስላደረጉት ሠረገላ፣ ወይም ስለ ቤታቸው አሠራር ክብር የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡

👉ከሰውነት አፍአ ወጥተው ይህን በመሰለ መጠን አለፍ ዕብደት ይያዛሉ፡፡

👉የራሳቸውን ሕይወት እንደ ማስተካከል ቁሳዊ ነገርን በመሰብሰብ ክብርን ይፈልጋሉ፡፡ 

💚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💚
በረከት አይለየን

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ለ. የንጽሐ ነፍስ መዓርጋት

፩ኛ መዓርገ አንብዕ

ቅዱሳን ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር) ለሰው ልጅ ያደረገውን ፍቅር፣ እስከ ሞትና መቃብር የተጓዘውን የመከራ ጉዞ እያሰቡ በአንጻሩም ምረረ ገሃነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን እያሰላሰሉ ውሉደ አዳም ይህን ዂሉ መከራ ባለመገንዘብ ወደ ሰፊው የፈቃደ ሥጋ መንገድ ሲጓዝ በማየታቸው ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም መሳቀቅ ሲያለቅሱ እንባቸው እንደ ምንጭ ይፈሳል፤ እንደ ሰን ውኃ ይወርዳል፡፡ ሰዎች ለዚህ ዓለም ድሎት ብለው የሚያለቅሱት ልቅሶ ፊትን ያንጣጣል፤ ዓይንን ያመልጣል፡፡ የቅዱሳን ልቅሶ ግን ፊትን ያበራል፤ ኀጢአትን ያስወግዳል፡፡ እርጥብ እንጨት ከእሳት ጋር በተያያዘ ጊዜ እንጨቱ ከነበልባለ እሳት ሲዋሐድ እንጨቱ እርጥብነቱን ትቶ ውኃውን በአረፋ መልክ እያስወገድ ይነዳል፡፡ ቅዱሳንም በግብር (በሥራ) ከመለኮት ጋር ሲዋሐዱ የዚህ ዓለም ምስቅልቅል ሥራ በሰማያዊ የረጋ ሕይወት ተለውጦ አሠራራቸው፣ አካሔዳቸው ፍጹም፤ ሕይወታቸው መልአካዊ ይኾናል፡፡

ይቀጥላል....

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
" አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።"
(መዝሙረ ዳዊት 47:5)
@linkortodoxe21
፬ኛ ማዕረገ ሑሰት

ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ላይ ሲደርሱ ባሉበት ኾነው ዂሉን ማየትና መረዳት ይችላሉ፡፡ ጠፈር ሳይከለክላቸው ርቀት ሳያግዳቸው ዂሉን በዂሉ ይመለከታሉ

#join or #share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
፫ኛ መዓርገ ፍቅር

ቅዱሳን ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ እንደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ዂሉን አስተካክለው ይወዳሉ፡፡ አማኒ፣ መናፍቅ፣ ኃጥእ፣ ጻድቅ፣ ዘመድ፣ ባዕድ፣ ታላቅ፣ ታናሽ፣ መሐይም፣ መምህር፣ ሳይሉ ዂሉንም አስተካክለው በመውደድ የመፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ልጆች መኾናቸውን ይገልጻሉ፡፡

#join or #share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🔴 በህይወት ውስጥ አብዛኞቻችን የመቶ ሜትር ሯጮች ነን።

👉ቶሎ ሮጠን ቶሎ ቀድመን ማሸነፍ እንፈልጋለን፤

👉 ሲጀምር የ 100 ሜትር ሯጭ ለአመታት የሚያደርገው ልምምድ አስደንጋጭ ነው፤

👉ሲቀጥል ደግሞ በህይወት ረጅም ርቀት መጓዝ የሚፈልግ ሁሉ የማራቶን ሯጭ ነው መሆን ያለበት።

👉የማራቶን ሯጭ ስትሆን ጓደኞችህ አሁን ቀድመውህ ቢሄዱ አይገርምህም!

👉ምክንያቱም ራስህ ላይ ከሰራህ ከኋላ ተነስተህ ማንንም ልትቀድም ትችላለህ።

👉 ኤሊ ጥንቸልን የቀደመቻት ፈጣን ሆና አይደለም፤

👉 ግን በሁለት ምክንያት ነው

1⃣ መቀደሟ ተስፋ አላስቆረጣትም
2⃣ ቀስ ብላም ቢሆን እንደምታሸንፍ ታውቃለች

👉አንተም የጎደለህ
🍒🍒ትዕግስት🍒🍒 ነው እንጂ የምትፈልግበት መድረስህ አይቀርም።

👉ህልምህ ትልቅ ከሆነ አሁኑኑ ለምን አልተሳካም ብለህ አትዘን፤

👉 ለመጪው ስኬትህ ኤሊ በቂ ምስክር ናት!

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
👉ቀንህን የምታበራው ደማቋ የጠዋት ፀሀይ አይደለችም!

👉በውስጥህ ያለው የተስፋ ፀሀይ ነው።

👉ህይወት በአጋጣሚ የተሞላችና አስደሳች እንድትሆንለት የሚፈልግ ሰው እየጣረ እየለፋ ተስፋ ማድረግ አለበት።

👉ቀጭን ገመድ ላይ የሚራመድ ሰው ጉዞውን በስኬት እንደሚጨርስ ተስፋ ያደርግና ያንን ቀጭን ገመድ በእምነት እየረገጠ ይጓዛል።

👉ቀጭኑ ገመድ የዚህ አለም ከባድ ፈተናዎች ናቸው፤

👉ተስፋና እምነትን ጨብጠህ ካልጓዝክ በቅርቡ ወራጅ ነህ።

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

#መንፈሳዊ#ህይወት#(ሰው)
ሐ. የንጽሐ ልቡና ማዕረጋት

፩ኛ ማዕረገ ንጻሬ መላእክት

ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ለአገልግሎት ሲወጡ ሲወርዱ ማየት፤ ተልእኳቸውን ያለ ምንም አስተርጓሚ መረዳት፤ ማነጋገርና ማማከር የመሳሰሉትን ዂሉ መፈጸም ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ መልአኩን ዐሥር ዓመት እንዳቆመው እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ ማለት ነው፡፡

ይቀጥላል....
፪ኛ መዓርገ ተሰጥሞ

ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ሲደርሱ በባሕረ ብርሃን መዋኘት፣ ባሉበት ኾነው ወደ ላይም ወደ ታችም መመልከት ይቻላቸዋል፡፡

ይቀጥላል.
መንፈሳዊ ህይወት
፪ኛ መዓርገ ተሰጥሞ ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ሲደርሱ በባሕረ ብርሃን መዋኘት፣ ባሉበት ኾነው ወደ ላይም ወደ ታችም መመልከት ይቻላቸዋል፡፡ ይቀጥላል.
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ቆያቹ? እንደሚታወቀው ለትንሽ ጊዜ ጠፍቻለሁ ለሱ ይቅርታ እየጠየኩ በቅርቡ ሀሪፊ ነገሮችን እንለቃለን እና ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት በሚሎ ርዕስ የጀመርነውን ትምህርት ዛሬ እንጨርሳለን ሁላችሁም ያወቃችሁትን ለሌሎች እንድታሳውቁ በእግዚአብሔር ስም አሳስባለሁ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ያወቁትን ማሳወቅ ፍጽም ደግነት ነው

፫ኛ መዓርገ ከዊነ እሳት (ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ)

መዓርገ ከዊነ እሳት በሌላ አጠራር ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ ይባላል፡፡ ይኸውም ሥላሴን በዓይነ ሥጋ ለማየት የሚቻልበት መዓርግ ነው፡፡ ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ሲደርሱ በተዋሕዶ ከመላእክት ጋር ኾነው፣ ረቀው እግዚአብሔርን ማመስገን ይቻላቸዋል፡፡ የለበሱትን ሥጋ ለብቻቸው ለይተው ማየት፤ በአካለ ነፍስ ሰማየ ሰማያትን መጐብኝት፤ ገነት ውስጥ መግባት ይችላሉ፡፡

በአጠቃላይ ‹‹ኩኑ ቅዱሳነ እስመ ቅዱስ አነ›› (ዘሌ. ፲፱፥፪) ተብሎ እንደ ተጻፈው፣ ቅዱሳን የቅዱስ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሶች ናቸውና ሕይወታቸው የቅድስና ነው፡፡ ዐሥሩ የቅዱሳን መዓርጋት የሚባሉትም ከላይ የዘረዘርናቸው ናቸው (ዮሐ. ፩፥፵፤ ፪ኛ ጴጥ. ፩፥፬-፲)፡፡ እነዚህም የዐሠርቱ ትእዛዛት ምሳሌዎች ናቸው (ዘፀ. ፳፥፫-፲፯፤ ዘሌ. ፲፱፥፲፰)፡፡ አንድም የዐሥሩ ብፁዓን ምሳሌዎች ናቸው (ማቴ. ፭፥፫-፲፪፤ ዮሐ. ፲፫፥፫፯)፡፡ የቅዱሳን በረከት አይለየን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✟✟✟እንካን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል

🌹 በሰላም
🌹በፍቅር
🌹በጤና
አደረሳችሁ አደረሰን 🌹🌹🌹

🌷ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር በዙሪያው ያሉትን አብቅታል ለክብር ስለ ፍጽሙ ምልጃው ለኔግን ይለያል መልአኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኝል 🌷

የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ረድኤት በረከት አይለየን አሜን 🌹🌹🌹

@linkortodoxe21
✟ርደተ መንፈስ ቅድስ✟

ርደተ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በብሉይ ኪዳን በትንቢት የተነገርና  በሐዲስ ኪዳን የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ኢዮኤል ስለ መንፈስ ቅዱስ ወደዚህ ዓለም መውረድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብትነት ዓለም እንደሚታነጽና ሃይማኖት እንደሚጸና እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ካይ አፈሳለሁ፡፡›› (ኢዩ. ፪፥፳፰)

ብዙ ዘመን የተባለውም ሰዎች በኃጢአት አረንቋ የኖሩበትን እንዲሁም እግዚአብሔር ወልድ ለሰዎች ድኅነት ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ በፊት የነበሩትን ፭፼፭፻ (አምስት ሺህ አምስት መቶ) ዘመናት ነው፡፡ አምላካችንም መንፈሱን በሰዎች እንደሚያፈስ የተናገረበት ምክንያት  በመጽሐፍ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ‹‹መንፈስ ቅዱስ መላባቸው›› ተብሎ እንደተገለጸው የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ በቅዱሳኑ እንደሚያሳድርባቸው ሲያመለክት ነው፡፡ እነርሱም ትንቢትን እንደሚናገሩ፣ እንደሚያስተምሩ፣ አስተዋይና ዐዋቂ እንደሚሆኑ በነቢዩ ኢዩኤል ላይ አድሮ በተናገረው መሠረት ለሰዎች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት ተሰጥቷል፡፡  (ሐዋ. ፪፥፬)

በብሉይ ኪዳን የተነገረው ትንቢትም በሐዲስ ኪዳን ተፈጽሞ በአባቶቻችን ላይ እንዲሁም በሰዎች በሙሉ መንፈስ ቅዱስ እንደተሰጠ እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬፥፲፪-፲፯ ያለውን ኃይለ ቃል ስንመለከት እግዚአብሔር አምላክ ወደ ሰማይ እንደሚያርግ፣ ከዚያም በኋላ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክልን ይገልጻል፤‹‹አብ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ ይልክላችኋል፡፡ እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይችለው የእውነት ነው፡፡›› ጌታችን ኢየሱስም ዓለም እንደማያየው የተናገረው መንፈስ ቅዱስ የሰዎች ልዩ ኃይልና ሀብት መሆኑን ሲገልጽ ነው፡፡  (ዮሐ. ፲፬፥፲፭-፲፯)

ይቀጥላል.....

#join or #share

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት
✟ርደተ መንፈስ ቅድስ✟ ርደተ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በብሉይ ኪዳን በትንቢት የተነገርና  በሐዲስ ኪዳን የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ኢዮኤል ስለ መንፈስ ቅዱስ ወደዚህ ዓለም መውረድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብትነት ዓለም እንደሚታነጽና ሃይማኖት እንደሚጸና እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ካይ አፈሳለሁ፡፡›› (ኢዩ. ፪፥፳፰) ብዙ…
በሉቃስ ወንጌል እንደተጻፈው ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ድኅነተ ዓለምን ፈጽሞ  ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በ፵ኛው ቀን ወደ ሰማየ ሰማያት በሚያርግበት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ቢታንያ ከወጣ በኋላ በተስፋ እንዲጠብቁና ከሰማይ የሚወርደውን መንፈስ ቅዱስ እስከሚጎናጸፉ ድረስ የእግዚአብሔርን ትእዛዛ እንዲመጠበቅ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ ‹‹እነሆ፥ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡›› ከዚህም መመሪያ በመነሣት አባቶቻችን የአምላካቸውን ትእዛዝ አክባሪዎችና ጠባቂዎች በመሆናቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ቆዩ፡፡ (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)

ከዚህም በኋላ ዓለምን ዞረው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሁሉም ቋንቋ ተናገሩ፤ አስተማሩም፡፡ ‹‹ኀምሳው ቀንም በተፈጸመ ጊዜ ሁሉም በአንድነት በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር፡፡ ድንገትም እንደ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅ መጣ፤ የነበሩትንም ቤት ሞላው፡፡ እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም ታዩአቸው፤ በሁሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገር ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር›› እንዲል፤ (ሐዋ. ፪፥፩-፬)

መንፈስ ቅዱስም በብሉይ ኪዳን ለተለያዩ አበው አባቶች ምሥጢራትን እንደገለጠና ትንቢትን እንዳናገረ ሁሉ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሐዋርያት አባቶቻችን በአንድ ዝግ ቤት በነበሩበት ጊዜ በማጽናት ነገሥታትን ሳይፈሩ በአደባባይም እንዲሰብኩ አድርጓቸዋል፡፡ ሰማያዊ ኃይልን ለብሰዋልና ጥበብም ተገለጠላቸው፤ የተለያየ ቋንቋም መናገር የጀመሩት በዚህን ጊዜ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከሳቲ ነውና ምሥጢርን ስለገለጠላቸው በ፸፪ ቋንቋዎችን በአንድ ጊዜ መናገር ችለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር አባቶቻችን በ፸፪ቱ ቋንቋዎች አልተገቱም፡፡ ‹‹በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ተዋሐዳቸው፤ ከዚያም በኋላ በዓለም ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ›› ተብሎ ተነግሯልና፤ ይህም ማለት ዓለም አቀፋዊ ቋንቋዎች ተናገሩ እንጂ በእነዚያ ቋንቋዎች ብቻ አልተገቱም፡፡  (ሐዋ. ፪፥፩-፬)

ሐዋርያት ፸፪ ቋንቋ መቻላቸው ሕዝቡ የ፸፪ቱ ዓይነት ቋንቋ ተናጋሪ ስለነበረ ነው፡፡ ስለዚህም በአደባባይ ወጥተው በሚያናገሩትና በሚገባቸው ቋንቋ ማስተማር ችለዋል፡፡  ቅዱስ ጴጥሮስ ሲያስተምር ፫፼ (ሦስት ሺህ) ሰዎች በአንድ ጊዜ አሳምኖ ያጠምቅ የነበረውም ለዚህ ነው፡፡ ይህም መንፈስ ቅዱስ ከሣቴ በመሆኑ አይገደቤነቱን የሚያስረዳ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ አንድ ስለሆነ አይከፋፈልም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ረቂቅ ሰማያዊ ኃይል ስለሆነ ገናናነቱን ይገልጽ ዘንድ አንድ የሆነው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሁሉ ላይ አደረባቸው፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረው ትንቢት የተፈጸመው ‹‹መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ›› ብሎ በተናገረው መሠረት ነበርና ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን ቃሉን ታስተምራለች፤ ዕለቱን ትዘክራለች፡፡ (ኢዩ. ፪፥፳፰)

ይቀጥላል...

#join or #share

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ወረደው መንፈስ ቅዱስ አምስት መሠረታዊ ትርጓሜ እንዳሉት ያስተምራሉ፡፡ እነርሱም፤🌹🌹🌹

፩ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ ናዛዚ ነው፤ ትርጓሜውም አረጋጊ ወይንም የሚያረጋጋ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያልተረጋጉትን ያረጋጋልና፤ ወንጌል ሲሰበክ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ሰዎችን ወይንም ምእመናን የሚያረጋጋ ኃይል ነው፡፡

፪ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ መጽንዒ ወይም የሚያጸና ነው፤ በተለያዩ ዘመናት የተነሡ ነቢያት፣ ቅዱሳን አባቶችና ሐዋርያት እንዲሁም ጻድቃን ሰማዕታትም ሰይፉና ስለቱን የታገሡት፣ መከራና ሥቃዩን የቻሉትና መስቀሉን የተሸከሙት አጽናኒው መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ስላደረባቸው ነው፡፡

ለምሳሌ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሥቃይ ሲቀበልልን ጴጥሮስ ግን የጌታችን ደቀ መዝሙር እንደሆነ ባጋለጡበት ጊዜ እርሱ እንደማያውቀው በመገዘት ሦስት ጊዜ ክዷል፤ የዚህም ምክንያት እርሱ በዚያን ወቅት የመሰቀልን ነገር ወይንም ቅጣት ሲመለከት በመጀመሪያ ፈርቶ ስለነበር አልጸናም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ከተጎናጸፈ በኋላ የፈራውን መስቀል በሮም ዳግም ሲመለከትና ሊሰቅሉትም ሲይዙት ላለመሰቀል አልፈረም፤ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ እንደተሰቀለው ወደ ላይ ሳይሆን ቊልቊል ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት ነግሯቸው ሰቅለውታል፤ ምክንያቱም ጌታችን ወደ ላይ የተሰቀለው ሰዎችን ለማዳን በመሆኑ ጴጥሮስ ደግሞ እራሱን ማዳን የማይችል ደካማ ፍጡር እንደሆነ ያምን ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ፣ ፭ ቀን)

፫ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ መንጽሒ ወይም የሚያነፃ ነው፤ የሰዎችን ኃጢአት የሚያስወግድ፣ ከእድፋችን የሚያነጻ፣ ሰውነትን ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሚያዘጋጅ ነው፡፡

፬ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ ከሳቲ ወይም ምሥጢር የሚገልጽ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ሙሴና ዕዝራን ስንመለከት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በየዘመናቱና በየደረጃው ምሥጢራትን እየገለጸላቸው መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡

ሊቃውንትም መናፍቃንን አውግዘው እየለዩ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምሥጢር እየተገለጸላቸው ለሚጠይቋቸው ጥያቄ መልስ እየሰጡ ጠላትን አሳፍረው፣ የሃይማኖትን ሥርዓት ደንግገው ለእኛ ለጆቻቸው አስተላልፈዋል፡፡ ይህም በሥጋዊ ፍላጎት ተነሣስተው ያደረጉት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያደረጉት መሆኑ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ገላጭነት ምሥጢርን ከምሥጢር እያራቀቊ ያላመኑትን እያሳመኑ ሕግና ሥርዓቱን አስቀምጠውልናል፡፡

፭ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ መስተፍስሒ ወይም የሚያስደስት ነው፤ ያዘኑ ሰዎችን ከኀዘን ያወጣል፤ ኀዘናቸውንም ወደ ደስታ ይቀይራል፤ ሐዋርያት በተዘጋ ቤት ተቀምጠው ያዝኑ ነበር፤ ጌታችን ወደ ሰማይ ባረገ ሰዓት ግን አጽናንቷቸዋል፡፡ ‹‹እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ›› እንዲል፤  ምክንያቱም የማይለይ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ሰጥቷቸዋልና ለዘለዓለም ከእነርሱ ጋር ይኖራል፡፡ (ማቴ. ፳፰፥፳)

በአባቶቻችን ሐዋርያት ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ በሁላችን ላይ አድሮ ትልቅ ሥራን ይሠራልና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዛሬም ጸንተን፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እየተገበርን አምላካችንን የሚያስደስት ሥራ ሠርተን የማያልፈው መንግሥቱን እንድንወርስ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!!!


#join or #share

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ወረደው መንፈስ ቅዱስ አምስት መሠረታዊ ትርጓሜ እንዳሉት ያስተምራሉ፡፡ እነርሱም፤🌹🌹🌹 ፩ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ ናዛዚ ነው፤ ትርጓሜውም አረጋጊ ወይንም የሚያረጋጋ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያልተረጋጉትን ያረጋጋልና፤ ወንጌል ሲሰበክ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ሰዎችን ወይንም ምእመናን የሚያረጋጋ ኃይል ነው፡፡ ፪ኛ🌹 መንፈስ ቅዱስ መጽንዒ ወይም የሚያጸና ነው፤ በተለያዩ ዘመናት…»
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን !!!

ተወዳጆች ትንሽ ጠፍቻለሁ ለእሱም ይቅርታ እየጠየኩኝ በቻናላችን ከዚ በኃላ ምርጥ ምርጥ ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚሆኑ እለቃለሁ ከቻናሉ ሳትወጡ በትዕግሥት ስለጠበቃችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
@linkortodoxe21
✝️ መንፈሳዊ ተጋድሎ ✝️ 


  መንፈሳዊ ተጋድሎ ማለት ምን ማለት ነው?

መንፈሳዊ ተጋድሎ ማለት – አንድ ሰው የሚያምንበትን እምነት፣ የሚመራበትን ሕግ፣ የሚያልመውን ተስፋ እና የሚወደውን ነገር ተከትሎ ከግቡ ለመድረስ ማድረግ ያለበትን በማድረግ÷ ማድረግ የሌለበትን በመተው በነፃ ፈቃዱ ወስኖ፥ በሙሉ ልቡናው፥ በሙሉ ኃይሉ የሚያደርገው የውስጥና የውጭ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ፥ ጥረትና ትግል ነው፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21