መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
"ወዳጄ ሆይ!

🌷መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡

🌷ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡

🌷እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡

🌷እነዚህ በርግጥ አንተ ገንዘብ አድርገሃቸው እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥምህ ነውና፡፡

🌷 ስለዚህ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡"

#join or #share
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
ተግሳፅ

🌷 አንዳንዴ እድሜያችን ከፍ ሲል ከልባችን ስሜት ይልቅ ለአይምሯችን ምክንያት ማድላት አለብን።

🌷 እኛ በጣም ወደናቸው እነሱ ብዙም ከማይፈልጉን ይልቅ ለኛ ልዩ ስሜት ላላቸው ሰዎች እድል መስጠት አለብን።

🌷አስተውላችሁ ከሆነ ሰዎች እንደሚወዱን ካወቅን ትክክለኛውን ቦታ አንሰጣቸውም፤

🌷 ወርቅ ፀባይ ቢኖራቸው እንደ መዳብ ይቀሉብናል።

🌷 ግን ቀና ብለህ ኮከቦቹ ላይ ስታፈጥ ትልቋን ጨረቃ ሳታያት እንዳይነጋብህ እንደሚባለው ስሜታችንን ብለን የማይጠቅሙንን ሰዎች ስንከተል ምርጥ ፈላጊዎቻችንን እንዳናጣ።

🌷 ለበሰለ ሰው ከስሜት ይልቅ ምክንያት ይቀድማል።
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

ወዳጄ ሆይ!

🌷 ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ?

🌷ነፍስህ በኃጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ?

🌷አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን?

🌷 አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከሆነ ከሰው እጅ
ሳይሆን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡

🌷ሁል ጊዜ “የማደርገው ነገር
እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትሁን
ብዬ እመክርኻለሁ፡፡

ሐዋርያው 💕ቅዱስ ጳውሎስ💕 ሲመክረን፡-

🌷“እንግዲህ የምትበሉ ወይም
የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር
አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ሁሉ እግዚአብሔርን
ለማክበር እንዘጋጅ /፩ኛ ቆሮ.፲፡፴፩/፤


🌷ለመሆኑ ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል መብላት ወይም መጠጣት ማለት ምንድነው? ድኻውን
ወደ ቤታችን ስንጠራው፤ በማዕዳችንም ክርስቶስ አብሮ ሲኖር ለእግዚአብሔር ክብር በላን
ወይም ጠጣን ይባላል፡፡


🌷ሐዋርያው የመከረን ግን በመብላችን ወይም በመጠጣችን ብቻ እግዚአብሔርን
እንድናከብረው አይደለም፡፡

🌷 ጨምሮም “ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ለእግዚአብሔር ክብር
አድርጉት” አለን እንጂ፡፡

🌷ስለዚህ ወደ ሸንጐም ብንሔድ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ብንሔድ
ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡

🌷እነዚህን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ
የምንችለውስ እንዴት አድርገን ነው? ወደ ቤተ ክርስቲያን፣ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴው፣ ወደ
ጉባኤው፣ ወደ ሌላውም አገልግሎት ስንሔድ አካሔዳችን እግዚአብሔር የሚከብርበት መሆን አለበት፡፡

🌷እግዚአብሔር የማይከብርባቸው ብዙ ምልልሶች አሉና በአዲሱ ዓመት ወደ ቤተ
ክርስቲያን መመላለሳችን ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት፡፡

🌷ከቤት ቁጭ ማለትን የምንመርጥ ከሆነም ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡

🌷 “ምን ማለት ነው?” ልትል ትችላለኅ፡፡ ከቤት ወጥተን ክፋት ወደ መላበት ሥፍራ፣ ክርክርና ክስ ወደ
ሰፈነበት ሸንጐ፣

🌷ዘፈን ስካርና ገቢረ ኀጢአት ወደሚደገስበት ነፍስንም ወደሚያውክ ስፍራ
ከመሔድ ተቈጥበን ከቤት ቁጭ ብንል ለእግዚአብሔር ክብር አደረግነው ይባላል፡፡

🌷ስለዚኽ🌷
ከቤት ውስጥ ቁጭ ማለትም ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድም እኩል ለእግዚአብሔር ክብር
ማድረግ ይቻለናል ማለት ነው።
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕 ወዳጄ ሆይ! 🌷 ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? 🌷ነፍስህ በኃጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? 🌷አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? 🌷 አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከሆነ ከሰው እጅ ሳይሆን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ 🌷ሁል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር…»
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

መራራ እና ከፍቅር የራቀ አሳሳቢ ሁኔታ ለይ ነዎት? እንግስያውስ የሚያነቡት ❤️የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች❤️

💜(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ.13)💜

1፤ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

2፤ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

3፤ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

4፤💜 ፍቅር ይታገሣል፥ 💛ቸርነትንም ያደርጋል፤ 💚ፍቅር አይቀናም፤ 💙ፍቅር አይመካም፥ ❤️አይታበይም፤

5፤❤️ የማይገባውን አያደርግም፥💛 የራሱንም አይፈልግም፥ 💙አይበሳጭም፥ 💚በደልን አይቆጥርም፤

6፤ 💚ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤💚

7፤ 💜ሁሉን ይታገሣል፥ 💛ሁሉን ያምናል፥ 💚ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥💙 በሁሉ ይጸናል።

8፤ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን #ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ# ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን #ይሻራል

13፤ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው💛 ፍቅር ነው💛

https://t.me/linkortodoxe21
ፃድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ ወይበዝህ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ
ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር
መዝሙር 91:12
በመጀመሪያ የዚህን ትምህርት ርዕስ ትርጉም ማወቅ ይበጃልና ትርጉሙም ይኸውና
። ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል።
ይህን መነሻ በማድረግ ስለ ቅዱሳን ሰዎች በብዙ ሳይሆን በጥቂቱ በረጅሙ ሳይሆን ባጭሩ አቅማችን የፈቀደውንና አእምሮአችን የቻለውን ያህል በመጠኑ እንማማራለን ይህን ለማለት የቻልነው እግዚአብሔር በቅዱሳን ላይ አድሮ ያደረገውና የሚያደርገው ተሰፍሮና ተቆጥሮ ስለማያልቅ ነው
እንግዲህ ፃድቅ ወይም ፃድቃን ማለት እውነት እውነቶኞች ማለት ሲሆን ይህም ስያሜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ በማለት ይገልፁታል
። ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
የዮሐንስ ወንጌል 14 : 6
ቅዱስ ጳውሎስም ፃድቅ የክርስቶስ ስም መሆኑን ሲገልፅ
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4 : 8
ታዲያ ይህን የራሱ የሆነውን ስም ለቅዱሳን ሲሰጣቸው እናያለን
። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
የማቴዎስ ወንጌል 10 : 41
በተጨማሪም በዚሁ ወንጌል
። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
የማቴዎስ ወንጌል 13 : 43
ወደ ብሉይ ኪዳንም ስንመለስ በመዝሙር 33 :15
። የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
በቁጥር 17ም
። ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
ለምሳሌ ያህል እና ለትምህርታችን መነሻ እንዲሆነን ታስቦ የተጠቀሱ ጥቅሶች ናቸው እንጅ መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ስለ ቅዱሳን ክብርና ባለሟልነት በሰፊው ይገልፃል
ይህም የእግዚአብሔር የቸርነቱ ብዛት ነው
ፃድቅና ቅዱስ የሚባሉት የቅፅል ስሞች የራሱ ሆነው እያለ በጥቂት ሥራችን ለዚያውም ከእነኃጢአታችን ይህን የክብር ስም እንድናገኝ መደረጉ ከምንናገረው በላይ ነው
። መንክር እግዚአብሔር በላእለ ቅዱሳኒሁ ።የሚባለውም ለዚህ ነው
በሌላ በኩል ደግሞ ።
። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
የዮሐንስ ወንጌል 15 : 5
የሚለውን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርርስቶስን ቃል መዘንጋታችን አይደለም አሁንም ያለዕርሱ ማንም ቢሆን ማድረግ አይችልም ቅዱሳን ከእርሱ ጋር ስለሚኖሩ ነው ከእርሱ ጋር የሚኖር ብዙ ፍሬ ያፈራል ተብሏልና በተጨማሪም እንዲህ ይገለፃል
። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥
የዮሐንስ ወንጌል 14 : 12
በዚህ ሁኔታ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ተብሎ እንደተፃፈው ቅዱሳንም ባህር የመክፈል ተራራ የማፍለስ ፀሐይን የማቆምና ሰማይን የመለጎም እንዲሁም አራዊትና እንስሳትም ሳይቀሩ እንዲገዙላቸው ስልጣን ሰጥቷቸዋል
። የሚሳናችሁ ነገር የለም። እንደተባለ ማቴዎስ 17:20
በቅዱስ ማርቆስ ወንጌልም
። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
የማርቆስ ወንጌል 16 : 17
እንግዲህ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ለቅዱሳን ቃል የገባላቸው ታሪክ ተዝቆ ስለማያልቅ በዚሁ እንግታውና ።እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል በሚለው መለኮታዊ ቃል በመስማማት በመግቢያችን ላይ በእግዚአብሔር ቤት ተተክለው የሚኖሩትን ቅዱሳን በማሰብ የበረከታቸው ተካፋይ እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን ።አሜን።
1
Forwarded from 💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 (Gedion)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

👉 የመስቀል አደባባይ ጉዳይ አሁንም #ትኩረትን ያሻል!

👉 አሁንም እጃቸውንም አይናቸውንም ከመስቀል አደባባይ ላይ አላነሱም!! ይባስ ብለው በGoogle map ላይ "መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" በማለት ነገሩን የማወሳሰብ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

😇 ከምንግዜውም በላይ አንድነታችን የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ እንገኛለን። ይህንን "ኢድ አደባባይ" ለማለት ዳር ዳር የተባለለትን ሴራ ለማክሸፍ በጋራ እንቁም!

ይህንን ያድርጉ!
1)Google map ይክፈቱ
2)ቦታ በመፈለጊያው ላይ "Meskel square" ብለው ይፈልጉ
3)"Direction" ከሚለው ስር ወደላይ በማድረግ "Suggest an edit" የሚለውን ይጫኑ
4)"መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" የተባለውን በመምረጥ "መስቀል አደባባይ" በማለት ያስተካክሉ
5)"Category" ከሚለው ምርጫ ውስጥ "place of worship" የሚለውን ይምረጡ
6) በመጨረሻም ከላይ ▶️ የNext ምልክቷን ይጫኑ

ከዚህ በኃላ ለGoogle የስም ማስተካከያ እንዲደረግ መልዕክት መላክዎን የሚገልጽ ማረጋገጫ ይመጣልዎታል።

ስለቤተክርስቲያንና ማምለኪያ ቦታዎቿ ዝም አንልም!!!

ስለቤተክርስቲያን ስትሉ ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልዕክቱን ከዚህ በላይ ከተያያዘው ምስል ጋር ያጋሩ!
መንፈሳዊ ህይወት
ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት ክፍል ሁለት <አፍቅርዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ ጻድቃኑ እስመ ጽድቀ የኀሥሥ እግዚአብሔር፤ ቅዱሳን፣ እውነትን ይዛችሁ ትሕትናን ተላብሳችሁ እግዚአብሔርን ውደዱት፡፡ እግዚአብሐር እውነትን፣ ትሕትናን ይወዳልና፤›› (መዝ. ፴፥፳፫) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ የቅዱሳን ፍሬ ትሕትና ነው፡፡ በዓይነ ሕሊናቸው ፈጣሪያቸውን፣ በዓይነ ሥጋቸው የእነርሱን ምንነት እንደዚሁም የዓለምን ከንቱነት…
ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት ክፍል ሶስት

ቅዱሳን በዚህ ዓለም ይጠበቡበታል፤ ወጥተው ወርደው ሰውነታቸውን ከስስት፣ ኃጢአት ጠብቀው ለወዲያኛው ዓለም ደግሞ በትዕግሥት ደጅ ይጠኑበታል፡፡ ‹‹ፈሪሃ እግዚአብሔር ትፍሥሕተ ልብ ውእቱ ወይሁብ ሐሤተ ወያስተፌሥሕ ወያነውኅ መዋዕለ ሕይወት ለፈራሄ እግዚአብሔር ይሤኒ ደኃሪቱ ወይትባረክ ዕለተ ሞቱ፤ እግዚአብሔርን መፍራት የልብ ደስታ ነው፡፡ ፍጹም የሥጋና የነፍስን ደስታ ይሰጣል፤ በሕይወትም ያኖራል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምርለታል፡፡ እንደ ኢዮብ ከደዌው ተፈውሶ ልጅ የልጅ ልጅ አይቶ ይሞታል፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈው ይህ ዂሉ በረከት የቅዱሳን ፍሬ ነው (ኢዮብ ፴፩፥፲፮)፡፡

ቅዱሳን በሚሠሩት ሥራ በያዙት ቅን መንገድ፣ ኢዮባዊ ትዕግሥት፣ አብርሃማዊ ኂሩት፣ ይስሐቃዊ ፈቃደኝነት፣ ያዕቆባዊ ቅን አገልግሎት፣ ዮሴፋዊ ኀዳጌ በቀልነት ሙሴአዊ ለወገን ተቆርቋሪነት እየጨመሩ በመኖራቸው የፈጣሪአቸው ኃይልና ጌትነት እንደዚሁም የድንቅ ሥራው መገለጫዎች ይኾናሉ፡፡ በጸጋ ላይ ጸጋ እየተጨመረላቸው ወደ ዐሥሩ መዓርጋት ይወጣሉ፡፡ ማዕረጋቸውንም ከዚህ ላይ ይናገሩታል፡፡ ዐሥሩ መዓርጋት የሚባሉት በሦስት ይከፈላሉ፡፡ ሦስቱ የንጽሐ ሥጋ መዓርጋት፣ አራቱ የንጽሐ ነፍስ መዓርጋት፣ እና ሦስቱ የንጽሐ ልቡና መዓርጋት ናቸው፡፡

💠ሦስቱ የንጽሐ ሥጋ መዓርጋት የሚባሉት፡- ጽማዌ፣ ልባዌ እና ጣዕመ ዝማሬ ናቸው፡፡

💠አራቱ የንጽሐ ነፍስ መዓርጋት፡- አንብዕ፣ ኵነኔ፣ ፍቅር እና ሑሰት ናቸው፡፡

💠ሦስቱ የንጽሐ ልቡና መዓርጋት ደግሞ፡- ንጻሬ መላእክት፣ ተሰጥሞ እና ከዊነ እሳት (ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ) ናቸው፡፡ በጠቅላላው ዐሥር ይኾናሉ፡፡


ይቀጥላል....
#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
💕ቅዱስ አቡነ ሺኖዳ💕

💠​​ማንነትህን ማወቅ💠

👉ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን?

👉 ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው?

👉 አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም።

👉 ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።

👉ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው።

👉 ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን?

👉ከሆነ ለምን ትታበያለህ?

👉 ለምንስ ትኩራራለህ?

👉 የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ?

👉ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር።

👉እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና።

👉በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል።

👉"እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።

👉 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
.ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት

የንጽሐ ሥጋ መዓርጋት

፩ኛ መዓርገ ጽማዌ

ይህ የመጀመሪያው መዓርግ ነው፡፡ በዚህ መዓርግ ማስተዋል፣ ውስጣዊ ትዕግሥት፣ ውስጣዊ ትሕትና፣ ውስጣዊ የራስ ሚዛንን ይዞ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡ ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ሲደርሱ እግዚአብሔርን ብቻ መዘከር ይችሉ ዘንድ የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላሉ፡፡ በዚህ መዓርግ ላይ ሳሉ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየሉ፡፡ ነገር ግን ለምን እንደሚወጡና እንደሚወርዱ አያውቁም፡፡ ዮሐንስ ሐፂር የሰፋውን ስፌት ገበያ ላይ ለመሸጥ ተቀምጦ እያለ በተመስጦ ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን እንደዚሁም ሌሎች መላእክትን በየመዓርጋቸው እያየ ያደንቅ ነበር፡፡ ስፌቱን የሚገዛ ሰው ቁሞ ‹‹እንቅቡ ዋጋው ስንት ነው?›› ብሎ ሲጠይቀው እርሱ የሚያየውን የሚያይ መስሎት ‹‹ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል ሚካኤል፤ ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?›› ብሎ በአንክሮ ጠየቀው፡፡ ሰውየውም ‹‹ይኼስ እብድ ነው›› ብሎ ትቶት ሔዷል፡፡

ይቀጥላል...


#join or #share

💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
፪ኛ መዓርገ ልባዌ

መዓርገ ልባዌ፣ ማስተዋል፤ ልብ ማድረግ፤ አሰሙኝ እንጂ ስሙኝ አለማለት፤ ልማር እንጂ ላስተምር አለማለት፤ የተነገረው ትንቢትና ተግሣፅ ምዕዳን ዂሉ የራሱ እንደ ኾኑ መገመት፤ መመርመር፤ ዓይነ ሥጋን ከመጽሐፍ፣ ከሥነ ፍጥረት፣ ዓይነ ነፍስን ከምሥጢር ማዋል ነው፡፡ እንደዚሁም የእግዚአብሔርን ቸርነት ማድነቅ፣ ለሰው ልጅ ያደረገዉን ውለታ ማሰላሰል፣ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከሰው መወለዱን፣ በገዳም መጾሙን፣ መገረፉን፣ ሥጋውን መቍረሱን፣ ደሙን ማፍሰሱን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን፣ እያሰቡ ልብን በፍቅረ እግዚአብሔር፤ አንደበትን በመንፈሳዊ ሕይወት መስበር፤ ዓላማን በገጸ መስቀል (ትዕግሥት) መትከል የመሳሰሉት ናቸው፡፡


#join or #share

💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
፫ኛ መዓርገ ጣዕመ ዝማሬ

ከዚህ ደረጃ ሲደረስ አንደበትን ከንባብ፣ ልቡናን ከምሥጢር ማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱሳን ከዚህ መዓርግ ሲደርሱ አንደበታቸው ዝም ቢልም በልባቸው ግን ዝም አይሉም፡፡ ከአፍ እስትንፋስ፣ ከአፋፍ ላይ ነፋስ እንደማይለይ ዂሉ ቅዱሳንም ከአንደበታቸው ትዕግሥት፣ ከእጃቸው ምጽዋት፣ ከልቡናቸው ትሕትና፣ ከሰውነታቸው ንጽሕና አይለይም፡፡ የሚጸልዩትና የሚያነቡት ቃል ዂሉ ምሥጢሩ እየገባቸው ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ ከዚህ መዓርግ የደረሰ አንድ ባሕታዊ ለብዙ ዘመናት ‹‹አቡነ ዘበሰማያት›› እያለ ብቻ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ‹‹‹ይትቀደስ ስምከ› በል እንጂ›› ቢለው ‹‹ኧረ ጌታዬ፥ እኔስ ‹አቡነ ዘበሰማያት› የሚለው ኃይለ ቃል ምሥጢሩና ጣዕሙ በአፌ እንደ ጨው እየሟሟ አልጠገበኝ ብሏል፤ እንዴት አድርጌ ወደ ፊት ልሒድ?›› ብሎታል፡፡

#join or #share
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
ታላቁ ሊቅ አባታችን

💕ቅዱሰ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

እንዲ ይመክረናል

👉እውነተኛ ክብርን ማግኘት ትፈልጋለህን?

👉ክብርን ናቅ፤ ያን ጊዜም ትከብራለህ፡፡

👉ለምን እንደ ናቡከደነፆር ታስባለህ?

👉እርሱ ክብርን መጨመር በፈለገ ጊዜ ከዕንጨትና ከድንጋይ የራሱን ምስል ሐውልት አቁሞአልና፤

👉 ሕይወት በሌለው በዚህ ግዑዝ ነገር ሕይወት ላለው ለእርሱ ክብር

👉 የሚጨምርለት መስሎት ነበርና፡፡ [ነገር ግን ክብር ሳይኾን ውርደት አገኘው፡፡]

👉እንግዲህ የስንፍናውን መጠን አለፍነት ታያለህን?

👉እከብርበታለሁ ብሎ ባቆመው ነገር እንዴት የገዛ ራሱን እንደ ዘለፈበት ትመለከታለህን?

👉 በራሱና በገዛ ነፍሱ ንጽህና ሳይኾን ሕይወት በሌለው ነገር ላይ መደገፉ፣

👉 በዚያ ረዳትነትም ክብርን ማግኘት ፈልጎ ሐውልቱን ማቆሙ፥ ከዚህ በላይ ምን ሞኝነት አለ?

👉 ራሱን ለማክበር ብሎ የገዛ ሕይወቱን እንደ ማስተካከል፥ በዕንጨት ላይ ዕንጨት እንደ መጨመር ያለ ምን ሞኝነት አለ?

👉 ይህ ማለት “አንድ ሰው ፈሊጥ ያውቃል የሚባለው ሰው በመኾኑ ሳይኾን የቤቱ ምንጣፍ ያማረ ስለ ኾነ፣ የቤቱ ደረጃም የተወደደ ስለ ኾነ ነው” እንደ ማለት ይቈጠራል፡፡

👉 በእኛ ዘንድ በእኛ ዘመን ናቡከደነፆርን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡

👉እርሱ ሐውልት እንዳቆመ አንዳንዶችም ስለ ለበሱት ልብስ፣ ስለ ገነቡት ቤት፣ ስላላቸው ፈረስ፣ ገንዘብ ስላደረጉት ሠረገላ፣ ወይም ስለ ቤታቸው አሠራር ክብር የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡

👉ከሰውነት አፍአ ወጥተው ይህን በመሰለ መጠን አለፍ ዕብደት ይያዛሉ፡፡

👉የራሳቸውን ሕይወት እንደ ማስተካከል ቁሳዊ ነገርን በመሰብሰብ ክብርን ይፈልጋሉ፡፡ 

💚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💚
በረከት አይለየን

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21