መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
መንፈሳዊ ህይወት
ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት ቅዱሳን› ማለት ‹የተቀደሱ፣ የከበሩ፣ የተመሰገኑ፣ የተለዩ፣ የተመረጡ፣ ንጹሐን የኾኑ፣ የጠሩ› ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና የጌትነቱ መገለጫ የኾኑ ዂሉ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ቅዱሳን፣ በሃይማኖት ጸንተው፣ በምግባር ጐልምሰው፣ የሥጋ ምኞታቸውን ትተው ሲገኙ የቅድስና ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር እነርሱን (ቅዱሳንን) መሣሪያ አድርጐ ኀይሉንና ሥልጣኑን የገለጸባቸው…
ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት ክፍል ሁለት

<አፍቅርዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ ጻድቃኑ እስመ ጽድቀ የኀሥሥ እግዚአብሔር፤ ቅዱሳን፣ እውነትን ይዛችሁ ትሕትናን ተላብሳችሁ እግዚአብሔርን ውደዱት፡፡ እግዚአብሐር እውነትን፣ ትሕትናን ይወዳልና፤›› (መዝ. ፴፥፳፫) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ የቅዱሳን ፍሬ ትሕትና ነው፡፡ በዓይነ ሕሊናቸው ፈጣሪያቸውን፣ በዓይነ ሥጋቸው የእነርሱን ምንነት እንደዚሁም የዓለምን ከንቱነት ይመለከታሉ፡፡ ፍሬ የያዘ ተክል ዂሉ ቁልቁል የተደፋ መኾኑ ትሕትናን ያስተምራል፡፡ ይህም የጻድቃን ምሳሌ ነው፡፡ በፈሪሃ እግዚአብሔር ልቡ የተሰበረ፣ እሱርነቱን (ማንነቱን፣ ምንነቱን) የመረመረ ሰው በዓይነ ሕሊናው የፈጣሪውን ቸርነት፣ በዓይነ ሥጋው የራሱን ውድቀት ይመለከታል፡፡

ይህ አመለካከት ለጸጋ እግዚአብሔርና ለፍሬ ክብር ያደርሰዋል፡፡ በመቅረዝ ላይ ያለች መብራት መሰወር እንዳይቻላት፣ የመቅረዙ ከፍታ እንደሚገልጻት በተራራ ላይ ያለች ቤትም ለእይታ እንደማትሰወር፣ የተራራው ከፍታ እንደሚገልጻት በጥበበ እግዚአብሔር ከብረው በጸጋ እግዚአብሔር ተውበው የሚኖሩ ቅዱሳን ጻድቃንም ደረጃ በደረጃ መዓርጋትን አልፈው ከመለኮት ባሕርይ ተካፍለው የተአምራት መገለጫ ይኾናሉ፡፡ ‹‹መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ በወዳጆቹ አድሮ የሚሠራው ሥራ ድንቅ ነው፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፷፯፥፴፭፤ ፪ኛ ጴጥ. ፩፥፫)፡፡

ቅዱሳን፣ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ሙታንን ማስነሣት፣ ዕውራንን ማብራት፣ በአጠቃላይ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ማድረግ የዘወትር (የዂልጊዜ) ተግባራቸው ነው፡፡ የጸጋና የክብር ባለቤቶች ኾነዋልና በዓለም ላይ ሳሉ የሚመጣባቸውን ፈተና ዂሉ ተቋቁመው የጸጋ መቅረዞች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ጸጋቸውም የአናብስቱን አፍ ዘጉ (ዳን. ፯፥፩-፰)፡፡ ውኃውን ወደ ኋላው መለሱ (ዘፀ. ፲፬፥፳፪)፡፡ ዝናም እንዳይሰጥ ሰማይን ለጎሙ (፩ኛ ነገ. ፲፯፥፩፤ ያዕ. ፭፥፲፯)፡፡ ነበልባለ እሳትን አበረዱ (ዳን. ፫፥፩-፲፫)፡፡ የቅዱሳን ወዳጅ እግዚአብሔር አምላካችን ሥጋዊ ሀገረ ተድላን ጥለው፣ ኃላፊ ጠፊ ምድራዊ ምቾታቸውን ንቀው ጸጋውን ከሚጠባበቁት ጋር ዂሉ አብሮ ይኖራል፡፡ ትዕግሥትን የጠዋት ቍርስ፣ የቀን ምሳ፣ የማታ እራት አድርገው የሚመገቧትን ዂሉ ማደሪያ ቤተ መቅደሱ ያደርጋቸዋል

ይቀጥላል .....
#join or #share
🌷 @linkortodoxe21
🌷 @linkortodoxe21
🌷 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ክብረ ቅድሳን እና አስሩ ማዕረጋት ቅዱሳን› ማለት ‹የተቀደሱ፣ የከበሩ፣ የተመሰገኑ፣ የተለዩ፣ የተመረጡ፣ ንጹሐን የኾኑ፣ የጠሩ› ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና የጌትነቱ መገለጫ የኾኑ ዂሉ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ቅዱሳን፣ በሃይማኖት ጸንተው፣ በምግባር ጐልምሰው፣ የሥጋ ምኞታቸውን ትተው ሲገኙ የቅድስና ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር እነርሱን (ቅዱሳንን) መሣሪያ አድርጐ ኀይሉንና ሥልጣኑን የገለጸባቸው…»
"ወዳጄ ሆይ!

🌷መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡

🌷ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡

🌷እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡

🌷እነዚህ በርግጥ አንተ ገንዘብ አድርገሃቸው እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥምህ ነውና፡፡

🌷 ስለዚህ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡"

#join or #share
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
ተግሳፅ

🌷 አንዳንዴ እድሜያችን ከፍ ሲል ከልባችን ስሜት ይልቅ ለአይምሯችን ምክንያት ማድላት አለብን።

🌷 እኛ በጣም ወደናቸው እነሱ ብዙም ከማይፈልጉን ይልቅ ለኛ ልዩ ስሜት ላላቸው ሰዎች እድል መስጠት አለብን።

🌷አስተውላችሁ ከሆነ ሰዎች እንደሚወዱን ካወቅን ትክክለኛውን ቦታ አንሰጣቸውም፤

🌷 ወርቅ ፀባይ ቢኖራቸው እንደ መዳብ ይቀሉብናል።

🌷 ግን ቀና ብለህ ኮከቦቹ ላይ ስታፈጥ ትልቋን ጨረቃ ሳታያት እንዳይነጋብህ እንደሚባለው ስሜታችንን ብለን የማይጠቅሙንን ሰዎች ስንከተል ምርጥ ፈላጊዎቻችንን እንዳናጣ።

🌷 ለበሰለ ሰው ከስሜት ይልቅ ምክንያት ይቀድማል።
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

ወዳጄ ሆይ!

🌷 ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ?

🌷ነፍስህ በኃጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ?

🌷አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን?

🌷 አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከሆነ ከሰው እጅ
ሳይሆን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡

🌷ሁል ጊዜ “የማደርገው ነገር
እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትሁን
ብዬ እመክርኻለሁ፡፡

ሐዋርያው 💕ቅዱስ ጳውሎስ💕 ሲመክረን፡-

🌷“እንግዲህ የምትበሉ ወይም
የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር
አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ሁሉ እግዚአብሔርን
ለማክበር እንዘጋጅ /፩ኛ ቆሮ.፲፡፴፩/፤


🌷ለመሆኑ ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል መብላት ወይም መጠጣት ማለት ምንድነው? ድኻውን
ወደ ቤታችን ስንጠራው፤ በማዕዳችንም ክርስቶስ አብሮ ሲኖር ለእግዚአብሔር ክብር በላን
ወይም ጠጣን ይባላል፡፡


🌷ሐዋርያው የመከረን ግን በመብላችን ወይም በመጠጣችን ብቻ እግዚአብሔርን
እንድናከብረው አይደለም፡፡

🌷 ጨምሮም “ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ለእግዚአብሔር ክብር
አድርጉት” አለን እንጂ፡፡

🌷ስለዚህ ወደ ሸንጐም ብንሔድ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ብንሔድ
ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡

🌷እነዚህን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ
የምንችለውስ እንዴት አድርገን ነው? ወደ ቤተ ክርስቲያን፣ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴው፣ ወደ
ጉባኤው፣ ወደ ሌላውም አገልግሎት ስንሔድ አካሔዳችን እግዚአብሔር የሚከብርበት መሆን አለበት፡፡

🌷እግዚአብሔር የማይከብርባቸው ብዙ ምልልሶች አሉና በአዲሱ ዓመት ወደ ቤተ
ክርስቲያን መመላለሳችን ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት፡፡

🌷ከቤት ቁጭ ማለትን የምንመርጥ ከሆነም ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡

🌷 “ምን ማለት ነው?” ልትል ትችላለኅ፡፡ ከቤት ወጥተን ክፋት ወደ መላበት ሥፍራ፣ ክርክርና ክስ ወደ
ሰፈነበት ሸንጐ፣

🌷ዘፈን ስካርና ገቢረ ኀጢአት ወደሚደገስበት ነፍስንም ወደሚያውክ ስፍራ
ከመሔድ ተቈጥበን ከቤት ቁጭ ብንል ለእግዚአብሔር ክብር አደረግነው ይባላል፡፡

🌷ስለዚኽ🌷
ከቤት ውስጥ ቁጭ ማለትም ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድም እኩል ለእግዚአብሔር ክብር
ማድረግ ይቻለናል ማለት ነው።
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
💠 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕 ወዳጄ ሆይ! 🌷 ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? 🌷ነፍስህ በኃጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? 🌷አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? 🌷 አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከሆነ ከሰው እጅ ሳይሆን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ 🌷ሁል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር…»
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

መራራ እና ከፍቅር የራቀ አሳሳቢ ሁኔታ ለይ ነዎት? እንግስያውስ የሚያነቡት ❤️የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች❤️

💜(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ.13)💜

1፤ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

2፤ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

3፤ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

4፤💜 ፍቅር ይታገሣል፥ 💛ቸርነትንም ያደርጋል፤ 💚ፍቅር አይቀናም፤ 💙ፍቅር አይመካም፥ ❤️አይታበይም፤

5፤❤️ የማይገባውን አያደርግም፥💛 የራሱንም አይፈልግም፥ 💙አይበሳጭም፥ 💚በደልን አይቆጥርም፤

6፤ 💚ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤💚

7፤ 💜ሁሉን ይታገሣል፥ 💛ሁሉን ያምናል፥ 💚ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥💙 በሁሉ ይጸናል።

8፤ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን #ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ# ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን #ይሻራል

13፤ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው💛 ፍቅር ነው💛

https://t.me/linkortodoxe21