መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ቅድሳት ሥዕላት ክፍል ፫

በጥንት ዘመን ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ በዋሻ ውስጥ በሥዕል እያስደገፉ ያስተምሩ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ለእምነታቸው ሲሉ ለተጋደሉ እና መሥዕዋትነትን ለከፈሉ ቅዱሳን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ሥዕል በመሣል ታሪካቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ክርስቲያኖች ይህንን እያደረጉ ለዘመናት ከቆዩ በኋላ በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሮማውያን ክርስቲያኖች እና በቢዛንታይን ክርስቲያኖች ዘንድ አለመግባባት ተፈጠረ፡፡ በዚህም ዘመን ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላትን ምክንያት በማድረግ በሁለት ጽንፍ ተከፈሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ኢኮኖላትሪያ ሲባሉ እነዚህም ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላትን ከመጠን በላይ አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሳ እንደ አማልክት የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ ሁለተኛዎቹ ደግሞ ኢኮኖማኺያ ሲባሉ እነዚህም ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላት ከነጭራሹ አያስፈልጉም በማለት ከአምልኮት ሥፍራ መወገድ አለባቸው የሚል አመለካከት የያዙ ነበሩ፡፡ ይህም አለመግባባት ለረጅም ዘመናት ከቀጠለ በኋላ በ፯፻፹፯ እ.ኤ.አ ሁለተኛው የኒቅያ ጉባኤ ተደርጎ ለቅዱሳት ሥዕላት አክብሮት እና ስግደት እንደሚገባ  ተወሰነ፡፡ በዚህም ጉባኤ መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር ክብሩ መገለጫ ሁነው የሚያገለግሉ የቅድስት ሥላሴ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የቅዱሳን መላእክት፤ የነቢያትና ሐዋርያት የጻድቃንና ሰማዕታት ሥዕላት ናቸው፡፡ (ዐምደ ሃይማኖት ምዕራፍ ፲፫)

በቅድስት ቤተክርስቲያን የምንገለገልባቸው ቅዱሳት ሥዕላት የተሣሉት ባለቤቱ እግዚአብሔር በመረጣቸው ሰዎች አማካኝነት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህልም ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለቱን ሥዕል ለንጉሥ ጢባርዮስ የሣለው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ነበር፡፡ ቅዱሳት ሥዕላት ቀኖና ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረገ የአሣሣል እና የአጠቃቀም ሥርዓት አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚሰቀሉ ምእመናን በሥዕሉ ፊት በመቆም የሚጸልዩበትና ልመናቸውን የሚያቀርቡበት ነው፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ቅድሳት ስዕላት የመጨረሻ ክፍል ፬

ቅዱሳት ሥዕላት በሚሣሉበት ወቅት አስቀድሞ የቅድስና ባለቤት ልዑል እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም የዕውቀት እና የጥበብ ባለቤት እርሱ ስለሆነ ሥዕላቱን ለመሣል የሚያስችል ጸጋ እንዲያድለን ነው፡፡ የቅዱሳት ሥዕላት የቀለም አጠቃቀምም በሥርዓተ ቤተክርስቲያን አንድምታ ያለው እንጂ በዘፈቀደ የሚሆን አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያህል ቀይ ቀለም ለቅዱሳን፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት ወኪል የሆነ ሰማዕትነትን እና ተጋድሎን የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም በሰማዕታት ሥዕላት ላይ ቀይ ቀለም በብዛት ሊስተዋል ይችላል፡፡ ነጭ ቀለም ንጽሐ ባሕርይን ስለሚያመለክት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤ እና የዕርገት ሥዕላት ላይ ሊስተዋል ይችላል፡፡ ሰማያዊ ቀለም የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ አምላክነት እና ቀዳማዊነት ስለሚያመለክት በቅድስት ሥላሴ ሥዕለ አድኅኖ ልንመለከተው እንችላለን፡፡ የቅዱሳት ሥዕላት የአሣሣል ልኬት መጠን እንደ አስፈላጊነቱ ሊተልቅ ወይም ሊያንስ ይችላል፡፡ በጸሎት መጻሕፍት ላይ የመጽሐፉን መጠን መሠረት ያደረገ ሲሆን በሕንጻ ቤተክርስቲያን ላይ ደግሞ የሕንጻውን መጠን መሠረት አድርጎ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

ቅዱሳት ሥዕላትን ለጸሎት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች በምንጠቀምበት ጊዜ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ በዋነኛነትም እንዳይበላሹ እና እንዳይደበዝዙ በክብር ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥዕላቱ የሚገልጹት የሥዕሉ ባለቤት የሆነውን አምላክ ወይም ቅዱስ፤  ጻድቅ ወይም  ሰማዕት ስለሆነ ተገቢውን ክብር እና ሥርዓተ አምልኮ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ምእመናን ትክክለኛዎቹን የሥዕሉን ባለቤቶች አውቀው እንዲያከብሩ እና እንዲማጸኑባቸው ሠዓሊዎች የሚሥሉትን ቅዱስ ሥዕል በትክክል መሣልም አለባቸው፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
"እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥረኝ ሰው አንተ ጠብቀኝ "

🌼አባ እንጦንስ🌼

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

“ተወዳጆች ሆይ!


👉ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡

👉እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡

👉ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡

👉ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡

👉ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡

👉እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡

👉ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡

👉በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣

👉 የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣
👉የመዳን ራስ ቁር፣

የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕

ምጽዋት

🍒

👉.... ልጆቼ ! ለምንድን ነው ቤታችንን አሸዋ ላይ የምንሠራው ?

👉ቤታችንን በዐለት ላይ እንሥራ እንጂ፡፡

👉ይህ በዐለት ላይ የተሠራው ቤታችን የቤት ቃጠሎ ፣

👉የጠላት መምጣት ፣ የሽፍታ መነሣት አያፈርሰውም ፤ አያጠፋውም፡፡

👉 ከእነዚህ አደጋዎች ኹሉ የራቀ ነው፡፡

👉ልጆቼ ! በዚህ ዓለም በምንሠራው ቤት ገንዘብ መዘረፍ አለ ፤ ልብስ መገፈፍ አለ፡፡

👉ፀብ ፣ ክርክር ፣ ነገር ሥራ ፣ ሰልፍ አለ፡፡

👉በዚህ ዓለም በምንሠራው ቤት ብዙ ኀዘን ብዙ ሰቀቀን አለበት፡፡

👉በላይኛው ቤታችን [ በመንግሥተ ሰማያት ] ግን ይህ ኹሉ የለም፡፡

👉ቋንጃ መትቶ ገንዘብ ቀምቶ የሚወስድ ጠላት የለም፡፡

👉ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ የለም፡፡ ገንዘብ የሚዘርፍ ልብስ የሚገፍ የለም፡፡

👉በዚያ ያለው የጻድቃን አንድነት ብቻ ነው፡፡ ጻድቃን ፡ ቅዱሳን ባሉበት ደግሞ ተድላ ደስታ ብጽዓን አለ፡፡

👉 መንግሥተ ሰማያት ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች፡፡

👉ሕልፈት ጥፋት የለባቸውም፡፡ ባለቤቷ አይነዋወጥም ፤ አይለዋወጥም፡፡

👉በዚያ ቤት የሚያልፍ የሚጠፋ የለም፡፡

👉 ኹሉም ከሕልፈት ከመለወጥ የራቀ ነው፡፡

#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
ታላቁ ቅዱስ

🌹ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🌹
እንዲህ ያስተምረናል

ወዳጄ ሆይ!

🌹እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠት እንድትለማመድ ነዉ።

🌹ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ
ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነዉ።

🌹ታዲያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰዉ እንደ ምን ያለ ጎስቋላ ሰዉ ነው ?

🌹እንግዲያዉስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰዉ አይደለምና አትግፋዉ።

🌹በረከትህን ከቤትህ አዉጥተህ አትሸኘዉ።

🌹የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🌹 በረከት አማላጅነት አይለየን ።💚💛❤️

#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ታላቁ ቅዱስ 🌹ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🌹 እንዲህ ያስተምረናል ወዳጄ ሆይ! 🌹እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠት እንድትለማመድ ነዉ። 🌹ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነዉ። 🌹ታዲያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰዉ እንደ ምን ያለ ጎስቋላ ሰዉ ነው ? 🌹እንግዲያዉስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው…»
🌹ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🌹

ተወዳጆች ሆይ

እግዚአብሔር አንድያ ልጁን መስጠቱ ለምንድን ነዉ ያላችሁ እንደ ሆነ

ስለፍቅሩ - ስለቸርነቱ ፣ እንዲሁ ሰዉን ስለመዉደዱ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምን ምክንያት የለውም ።

ይህን ፍቅር መቼም ቢኾን መች አንርሳው ዘወትር እናስበው

አስበንም ዝም አንበል እንፈርም እንጂ ።

" ለምን እናፍራለን ?" ያላችሁኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብየ እመልሳቸዋለሁ

እግዚአብሔር እኛን ከማፍቀሩ የተነሳ ተቀዳሚ ተከታይም የሌለው አንድያ ልጁን

ሳይራራ ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሰጥቶን ሳለ

እኛ ግን የገዛ ነፍሳችንን
በእርኩሰት በዝሙት ለማሳደፍ በኃጥያት ለማርከስ ገንዘባችንን ኹሉ እንሰጣለንና ።

እርሱ የገዛ ልጁን ሰጥቶን ሳለ
እኛ ግን ለእርሱ ስንል ሳይኾን ለራሳችን ስንል ጥቂቷን ነገር

ለምሳሌ
ፍቅረ ንዋይን እንኳን አንንቅምና።

ታዲያ ለዚህ ግብራችን ሊደረግልን የሚችል እንደምን ያለ ይቅርታ ነው ?

ሊደረግልን የሚችል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነዉ?

የታላቁ አባታችን 💚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💛 በረከት አማላጅነት❤️ አይለየን !!!
#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
Forwarded from እርቅ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

👉 የመስቀል አደባባይ ጉዳይ አሁንም #ትኩረትን ያሻል!

👉 አሁንም እጃቸውንም አይናቸውንም ከመስቀል አደባባይ ላይ አላነሱም!! ይባስ ብለው በGoogle map ላይ "መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" በማለት ነገሩን የማወሳሰብ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

😇 ከምንግዜውም በላይ አንድነታችን የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ እንገኛለን። ይህንን "ኢድ አደባባይ" ለማለት ዳር ዳር የተባለለትን ሴራ ለማክሸፍ በጋራ እንቁም!

ይህንን ያድርጉ!
1)Google map ይክፈቱ
2)ቦታ በመፈለጊያው ላይ "Meskel square" ብለው ይፈልጉ
3)"Direction" ከሚለው ስር ወደላይ በማድረግ "Suggest an edit" የሚለውን ይጫኑ
4)"መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" የተባለውን በመምረጥ "መስቀል አደባባይ" በማለት ያስተካክሉ
5)"Category" ከሚለው ምርጫ ውስጥ "place of worship" የሚለውን ይምረጡ
6) በመጨረሻም ከላይ ▶️ የNext ምልክቷን ይጫኑ

ከዚህ በኃላ ለGoogle የስም ማስተካከያ እንዲደረግ መልዕክት መላክዎን የሚገልጽ ማረጋገጫ ይመጣልዎታል።

ስለቤተክርስቲያንና ማምለኪያ ቦታዎቿ ዝም አንልም!!!

ስለቤተክርስቲያን ስትሉ ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልዕክቱን ከዚህ በላይ ከተያያዘው ምስል ጋር ያጋሩ!