መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
እንካን አደረሳችሁ 🌹🌹🌹
በቀደመው ዘመን በዘመነ ብሉይ “የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል” ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እዉነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችው እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል “የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት /መዝ 111፥7/

በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሠላሳ ሦስት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደው በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመው እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸው ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረው መጽሐፈ ዜና መዋዕል “የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል” /1ኛ ዜና 29፥29/
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (Mentesenhot)
የበዓሉ አከባበር 🌹🌹🌹🌹🌹

በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደው በአድባረ ሊባኖስ ሥር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸው “ንፍሮና ጥራጥሬ”ነበር፡፡ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ውጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማውን ማስፈጸም የሚፈልገው ዲያብሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነው፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለውጋር ነው፣ቆሌውን ለመለመን ነው፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ቡና የሚረጩ፣ቂቤ የሚቀቡ፣የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡

ሃይማኖታዊ ሥርዐት እያደገ ጠቃሚ ባህል ወደ መሆን ለመወጡ ደስ ያሰኛል፡፡ ወገኖቻችንም በእመቤታችን የልደት ቀን የተቸገረውን በመርዳት በዓሏን ለማክበር ሚያደርጉት ጥረት መልካም በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ በልደታ ማርያም በዓል ሰበብ የሚደረግ ጣዖት የማምለክ ሥርዐት ካለ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት አይደለምና እናውግዘው፡፡ ስለሆነም ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረው የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡ አሜን!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱድንግል
 ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
!!!
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
😍የሰው ልጆች ሁሉ አማላጅ መሆኗን😍

ድንግል ማርያም የዓለሙ ሁሉ መዳን ምክንያት ስለሆነች ለአማላጅነቷ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። አማላጅነት በእግዚአብሔር ዘንድ ለተከበሩ በፈቃዱ ለሚሄዱ የሚሰጥ የክብራቸው መገለጫ የሆነ የቅድስና ደረጃ ነው። ድንግል ማርያም አማላጃችን እንድትሆን ከሁሉ በላይ የፈቀደ እግዚአብሔር ነው። አዳምና ልጆቹ እንደ ሰዶምና ገሞራ ከመጥፋት ምክንያተ ድህነት የሆነች እመቤታችን ናት /ኢሳ 1፥9/። ቅዱስ ዳዊት ሲናገር ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ያለው እመቤታችንን ሲሆን በቀኝህ ማለቱ በፈቃዱ እንዳለች የሚገልጽ ሲሆን ትቆማለች ማለቱ ደግሞ ለሰው ልጆች ምልጃ እንደምታቀርብና እግዚአብሔርም እንደሚቀበላት የሚገልጽ ነው። እመቤታችን ድንግል ማርያም በቃና ሰርግ ቤት ተገኝታ የወይን ጠጅ የላቸውም ብላ እንዳማለደች /ዮሐ 2፥1-11/ በእኛም ሕይወት የጎደለብንን ነገር እግዚአብሔር እንዲሞላልን ዘወትር ትጠይቃለች። እውነቱ ይህ ከሆነ የእመቤታችንን ክብር መቀበል ያልቻለ ሰው፤ አማላጅነቷን የናቀ ሰው፤ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዴት ሊያገኝ ይችላል? ለቅዱሳን አባቶቻችን ምሥጢሩን ጥበቡን የገለጸ እግዚአብሔር ለእኛም የእመቤታችንን ክብር እንዲገልጽልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 6)
----------
20፤ ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤

21፤ ሁልጊዜም በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው።

@linkortodoxe21
በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀዱ አምላክ አሜን!!!

ውድ የቻናላችን ተከታዮች ለትንሽ ጊዜ ጠፍተን ነበር ለዛም ይቅርታ እየጠየቅን

በቻናላችን፦
🌷 ብሒለ አበው (የአባቶቻችን ለሕይወታችን መርህ የሚሆኑ ብሒሎች ) እናቀርባለን

@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
"እግዚአብሔር ፀጋ ከሰጠህ እሱን የምትሸከምበት ትህትናን እንዲሰጥህ ለምነው ካልሆነ የሰጠህን ፀጋ ይወስድልህ ዘንድ ተማፀነው"

🌹 ቅድስ ማር ይስሀቅ በረከታቸው ይደርብን

🌸 @linkortodoxe21
"ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል"

🌹ቅድስ አትናቴዎስ በረከታቸው ይደርብን

🌸 @linkortodoxe21
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ቅድሳት ስዕላት በሚል ርዕስ በክፍል በክፍል ትምህርት ልንሰጥ ዝግጅት አርገናል እና ስለ ቅድሳት ስዕላት ምን ያህል ታውቃላቹ በሚል ጥያቄ አዘጋጅተናል ሞክሩ

1.ቅድሳት ስዕላት ለምን አገልግሎት ይውላሉ?


2.ስለ ቅድሳት ስዕላት ከመጽሀፍ ቅድስ ጥቀስ ?


3.ቅድሳት ስዕል መቼ መሳል ተጀመረ ? ማነው የሳለው?

ሞክሩ @Eyasues
@Mentesnhot
መልሱን
<<አንተም÷ የሰው ልጅ ሆይ÷ ጡቡን ወስደህ በፊት አኑራት፤ የኢየሩሳሌምንም ከተማ ሥዕል ሳልባት፤ ክበባት›› (ሕዝ.፬፥፩)

ቅድሳት ሥዕላት ክፍል ፩

ቅዱሳት ሥዕላት አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጸምባቸው ንዋያተ ቅድሳት ናቸው፡፡ እስራኤላውያን ቀደም ሲል ሰዎች ድንጋይን በማዘጋጀት፣ እንጨትን በመጥረብ፣ ቆዳን በመፋቅ፣ ኅብር ባላቸው ቀለማት በመሳል ለትውልድ እንዲተላለፉ ያደርጉ ነበር፡፡ የቅዱሳት ሥዕላት አጀማመር ዘመነ ኦሪትን መነሻ ያደረገ ነው፤ አስቀድሞ ልዑል እግዚአብሔር ለነቢዩ ሙሴ በታቦተ ሕጉ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲሥል አዘዘው፡፡ ‹‹ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን÷ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሰራዋለህ፡፡ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፤ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፤ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ››፡፡ (ዘጸ. ፳፭፥፲፱-፳)

ይቀጥላል ...

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ቅድሳት ሥዕላት ከፍል ፪

ስለ ቅዱሳትሥዕላት አጀማመር በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡፡ ‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤልን ሠራ፡፡ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ÷ የኪሩብም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ አሥር ክንድ ነበረ፡፡ ሁለቱም ኪሩቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበረ፡፡ የአንዱ ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበረ÷ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ፡፡ ኪሩቤልንም በውስጠኛው ቤት አኖራቸው፤ የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ተዘርግተው ነበር፡፡ የአንዱም ኪሩብ ክንፍ አንደኛውን ግንብ ይነካ ነበር÷ የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ ሁለተኛውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለቱም ክንፎች በቤቱ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር፡፡ ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው፡፡ በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ››፡፡(፩ኛ ነገሥት ፮፥፳፫-፳፱) በትንቢተ ሕዝቅኤልም ‹‹አንተም÷ የሰው ልጅ ሆይ÷ ጡቡን ወስደህ በፊት አኑራት፤ የኢየሩሳሌምንም ከተማ ሥዕል ሣልባት፤ ክበባት›› ይላል ሕዝ.፬፥፩)፡፡

ይቀጥላል ......

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21