መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ዕለተ ዐርብ/ዓርብ/

ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/
የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡

በመስቀል ላይ ሳለ 7 ነገሮችን ተናገረ/7ቱ " አጽርሐ መስቀል " በመባል ይታወቃሉ። እነሱም፦
" አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" ማቴ 17፦46
" አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ሉቃ 23፦34
" ዛሬ በገነት ከኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሀለሁ" ሉቃ 23፦4
" አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" ሉቃ 23፦ 46
" እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ" ዮሐ 19፦26
" ተጠማሁ" ዮሐ 19፦28
" ሁሉ ተፈጸመ " ዮሐ 19፦ 30

ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤

በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/

1. ፀሐይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም ሆነች
3. ከዋክብት ረገፉ

በምድር፤/ማቴ 27፦51_53/
1. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ
2. ምድር ተናወጠች
3. መቃብሮች ተከፈቱ
4. ሙታን ተነሱ

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ቀዳሜ ስዑር/ቅዳሜ/

ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዘፍ.1፡3፡፡

ዕለተ ቀዳሚት /ሰንበት ዐባይ/ በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ሁሉ የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ አምላክ በመቃብር አርፎባታል፡፡ ማቴ.27፡61፡፡

በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሜ ስዑር » ትሰኛለች፡፡ ስዑር ቀዳሜ የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡
ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡

በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ «ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፡-በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» የምሥራች እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን ቄጠማ ይታደላል ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡

«ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡
የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#መዝ_
@senbet_tmehert_bet
#አልፋና_ኦሜጋ
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
.....
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡህ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሰህ
ለአዳም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
....
ቅዱሳን እጆጅህ የፊጥኝ ታስረው
እንደበግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመፃደቅ
....
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳለፈው ሰጡህ አጋለጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
....
ግርፋት ህማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
....
5ቱ ችንካሮች ቅንዋተ መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
....
ግፈኞች አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፋብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖችህ ኀጢአት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን

ለመቀላቀል👇
@senbet_tmehert_bet
💒እንካን አደረሳችሁ 💒

ክርስቶስ ተንሥአ ሙታን
በዐቢይ ኅይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ
ኮነ ፍስሀ በሰላም

🙏እንካን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ 🙏
@linkortodoxe21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን #ተነሥቶአል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:20)
🌹🌹🌹 እንካን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ!!! 🌹🌹🌹

🌹በዓሉ 🌼የሰላም
🌼የፍቅር
🌼የጤና
🌼 የመተሳሰብ
🌼የአብሮነት ይሁንልን 🥀🥀🥀

🌷🌷🌷በዓሉን ስናከብር ልክ እንደ ቃሉ 🌸🌸🌸

🌹የታመመን ጠይቀን
🌹የተራበውን አብልተን
🌹የተጠማውን አጠጥተን
🌹የታረዘውን አልብሰን
🌹የታሰረውን ጠይቀን
🥀🥀🥀ፈጣሪ የሚወደውን መልካም ስራዎችን እየሰራን ልናከብር ያስፈልጋል 🌷🌷🌷🌹🌹🌹🌸🌸🌸🥀🥀🥀

#መልካም_የትንሣኤ_በዓል_ይሁንልን
@linkortodoxe21

ከምንተስኖት
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡


#እንኳን ለብርሃነ
#ትንሳኤው በሰላም
#አደረሳችሁ
#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የእግዚአብሔር የአካሉ ማደሪያ መሆኗን
😍የእመቤታችን ክብር ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች ተብሎ እንዲነገር ምክንያት ከሆኑት አንዱ የእግዚአብሔር አካሉ ማደሪያ መሆኗ ነው። እግዚአብሔር በሰዎች ላይና በቅዱሳን መላእክት የሚያድረው በጸጋው ነው በእመቤታችን በቅድሰት ድንግል ማርያም ላይ ግን ጸጋ የተሞላች ብቻ ሳትሆን የእግዚአብሔር ወልድ የአካሉ ማደሪያም ሆናለች ። ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በድንግል ማርያም ማኀፀን መቀመጡ የሚደንቅ ምሥጢር ነው ። አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ እጅግ ተደንቆ የገለጸው ይህንን ምሥጢር ነው። “ከአባቱ አጠገብ ሳይለይ ቃል ወደ አንቺ መጣ ሳይወሰን ፀነስሽው በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨመር በማኀፀንሽ ተወሰነ መመጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በሆድሽ አደረ” በማለት እመቤታችን የወልድ ማደሪያ መሆኗን መስክሯል። ስለዚህ ነው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ የምንላት አምላክ በማኀፀንዋ 9 ወር ከ 5 ቀን ተቀምጦ በድንግልና ወልዳዋለችና ።
#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
ትንሣኤዋ እንደ ልጇ ትንሣኤ መሆኑን
የቤተክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርት እንደሚያስረዳው ሰዎች ሁሉ በመጨረሻው ቀን ለፍርድ እንደሚነሱ እናውቃለን ፤ሰው ሞቶ እንደማይቀር ተስፋ ለመስጠትም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ እና በኩር ሆኖ አረጋግጦልናል። በዚህም መሠረት ሰዎች ሁሉ የሚነሱት በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ ዘጉባኤ መሆኑ የተረጋገጠ ነው። በዚህ የፍርድ ቀን መንግሥተ ሰማያት ትከፈታለች መልካም ያደረጉና በሃይማኖት የጸኑ ሰዎች እርሷን ይወርሳሉ። እስከዚህ ቀን ድረስ ግን ከሰው ወገን መንግሥተ ሰማያት የሚወርስ የለም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በቀር። ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን በጻፈው መልእክቱ እንደገለጸው የሃይማኖት ገድል የፈጸሙ ቅዱሳንን ከገለጸ በኋላ ያለ እኛ ፍጹማን አይሆኑም በማለት የተናገረው መንግሥተ ሰማያት ተከፍታ ቅዱሳን ሁሉ እንዲወርሳት በምድር ያሉት ሁሉ ለፍርድ መቅረባቸው የሚጠበቅ መሆኑን ለመግለጽ ነው። “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና” /ዕብ 11፥39-40/ ይህ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ግን እመቤታችንን የሚመለከት አይደለም ምክንያቱም እመቤታችን ከውርስ ኀጢአት ነጻ የሆነችና ጸጋን የተሞላች በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች ስለሆነች የፍርድ ቀን እርሷን አይመለከትም ለጥያቄ አትቀርብምና። ለዚህ ነው የእመቤታችን ትንሣኤ ከሰው ልጆች ሁሉ ትንሣኤ የተለየ ነው የምንለው ድንግል ማርያም 64 ዓመት ከኖረች በኋላ ሞተ እረፍትን አልፋ እንደ ልጇ ተነስታለች። አሁን ደንግል ማርያም በታላቅ ክብር በመንግሥተ ሰማያት ትገኛለች። ቅዱስ ዳዊት ይህ የድንግል ማርያም ትንሣኤ አስቀድሞ እንደሚፈጸም አውቆ ትንቢት ተናገሯል። “አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ 131፥8/። እዚህ ላይ የመቅደስህ ታቦት ያለው እመቤታችን ድንግል ማርያምን ነው፤ ታቦት ማለት የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ እግዚአብሔር በአካሉ ያደረባት አማናዊ ታቦት እመቤታችን ናትና። ቅዱስ ዳዊት የእመቤታችን የቅድሰት ድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ተገልጦለት እንዳመሰገናት “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” /መዝ 45፥9/ ያለው በእግዚአብሔር መንግሥት ዘላለማዊ ንግሥት ድንግል ማርያም መሆናን ለመግለጽ ነው።

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
😍 ሰውም በቅዱሳን መላእክት የምትመሰገን መሆኗን 😍
እግዚአብሔርን የሚያምኑ ፈቃዱ ምን እንደሆነ የሚያስተውሉ ሁሉ ድንግል ማርያምን ያመሰግኗታል። አንዳንድ ይህንን ያልተረዱ ሰዎች ለምን ድንግል ማርያም ትመሰገናለች ሲሉ ይደመጣሉ። እንኳን ደካማ የሆነው የሰው ልጆች ይቅርና በሰማይ ያሉ ቅዱሳን መላእክትም ያመሰግኗታል። ድንግል ማርያምን የምናመሰግናት የተሰጣትን ክብር በመግለጽ፤ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ምክንያት መሆኗን በመግለጽ እና አሁንም አማላጅ መሆኗን በመመስከር ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነገደ መላእክትን በመወከል ኤልሳቤጥ ደግሞ የሰው ልጆችን በመወከል ጸጋን ተሞላሽ በማለት ለእመቤታችን ምስጋና አቅርበዋል። እመቤታችንም በሰጠችው የሃይማኖት ምስክርነት “ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” /ሉቃ 1፥49/ ብላለች። ይህን የተናገረችው ለእርሷ ምስጋና ማቅረብ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ሰዎች ተረድተው ፡ በዚሁ ፈቃድ መሠረት እንዲመሩ ነው። ድንግል ማርያም እንድትመሰገን እግዚአብሔር ከፈቀደ ሰዎቸ በተቃዉሞ ቢነሱ በመጨረሻው ቀን ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ምክንያቱም “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” /ማቴ 7፥21—23/ ብሎ ጌታችን ተናግሯል። እኛ ግን እንደተማርነው ድንግል ማርያምን ዘወትር እናመሰግናታለን፤ ይህንን በማድረጋችን የበለጠ ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን እንጂ አንርቅም።


#join or #share
💚 @linkortodoxe21
💛 @linkortodoxe21
❤️ @linkortodoxe21
እንካን አደረሳችሁ 🌹🌹🌹
በቀደመው ዘመን በዘመነ ብሉይ “የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል” ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እዉነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችው እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል “የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት /መዝ 111፥7/

በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሠላሳ ሦስት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደው በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመው እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸው ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረው መጽሐፈ ዜና መዋዕል “የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል” /1ኛ ዜና 29፥29/
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (Mentesenhot)
የበዓሉ አከባበር 🌹🌹🌹🌹🌹

በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደው በአድባረ ሊባኖስ ሥር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸው “ንፍሮና ጥራጥሬ”ነበር፡፡ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ውጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማውን ማስፈጸም የሚፈልገው ዲያብሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነው፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለውጋር ነው፣ቆሌውን ለመለመን ነው፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ቡና የሚረጩ፣ቂቤ የሚቀቡ፣የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡

ሃይማኖታዊ ሥርዐት እያደገ ጠቃሚ ባህል ወደ መሆን ለመወጡ ደስ ያሰኛል፡፡ ወገኖቻችንም በእመቤታችን የልደት ቀን የተቸገረውን በመርዳት በዓሏን ለማክበር ሚያደርጉት ጥረት መልካም በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ በልደታ ማርያም በዓል ሰበብ የሚደረግ ጣዖት የማምለክ ሥርዐት ካለ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት አይደለምና እናውግዘው፡፡ ስለሆነም ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረው የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡ አሜን!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱድንግል
 ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
!!!
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
😍የሰው ልጆች ሁሉ አማላጅ መሆኗን😍

ድንግል ማርያም የዓለሙ ሁሉ መዳን ምክንያት ስለሆነች ለአማላጅነቷ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። አማላጅነት በእግዚአብሔር ዘንድ ለተከበሩ በፈቃዱ ለሚሄዱ የሚሰጥ የክብራቸው መገለጫ የሆነ የቅድስና ደረጃ ነው። ድንግል ማርያም አማላጃችን እንድትሆን ከሁሉ በላይ የፈቀደ እግዚአብሔር ነው። አዳምና ልጆቹ እንደ ሰዶምና ገሞራ ከመጥፋት ምክንያተ ድህነት የሆነች እመቤታችን ናት /ኢሳ 1፥9/። ቅዱስ ዳዊት ሲናገር ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ያለው እመቤታችንን ሲሆን በቀኝህ ማለቱ በፈቃዱ እንዳለች የሚገልጽ ሲሆን ትቆማለች ማለቱ ደግሞ ለሰው ልጆች ምልጃ እንደምታቀርብና እግዚአብሔርም እንደሚቀበላት የሚገልጽ ነው። እመቤታችን ድንግል ማርያም በቃና ሰርግ ቤት ተገኝታ የወይን ጠጅ የላቸውም ብላ እንዳማለደች /ዮሐ 2፥1-11/ በእኛም ሕይወት የጎደለብንን ነገር እግዚአብሔር እንዲሞላልን ዘወትር ትጠይቃለች። እውነቱ ይህ ከሆነ የእመቤታችንን ክብር መቀበል ያልቻለ ሰው፤ አማላጅነቷን የናቀ ሰው፤ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዴት ሊያገኝ ይችላል? ለቅዱሳን አባቶቻችን ምሥጢሩን ጥበቡን የገለጸ እግዚአብሔር ለእኛም የእመቤታችንን ክብር እንዲገልጽልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!

🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
🌹 @linkortodoxe21
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 6)
----------
20፤ ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤

21፤ ሁልጊዜም በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው።

@linkortodoxe21