መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትን መገለጫዎችን እናቀርብላችኋለን፡፡ ሁላችንንም በአማላጅነቷ ትጠብቀን፡፡🙏🙏🙏
ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም ያላትን ክብር ለመግለጥ የተለያዩ ምሳሌዎችን ትሰጣለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ ስትመሰገን የምትኖር ናት። እመቤታችን ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት ያላትን ክብር ለመግለጽ በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። በተለይም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በማመስገን በቤተክርስቲያናችን ዘወትር የሚነሱት የሶርያው ቅዱስ ኤፍሬም፤ የብህንሳው አባ ሕርያቆስ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይገኙበታል። የእመቤታችንን ክብር ያለተረዱ ሰዎች ለምን እኛ ኦርቶዶክሳውያን እንደምናመሰግናት ዘወትር በጸሎታችን እንደምናነሳት ጥያቄ የሚያቀርቡ አሉ። ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከሕጻንነቱ ጀምሮ የእመቤታችንን ምስጋና ይማራል ሁልጊዜም ኣባታችን ሆይ ብሎ ጸሎት የጀመረ በመልኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብሎ ድንግል ማርያምን ሳያመሰግን የሚቀር የለም። ቤተክርስቲያናችን ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። እኛም የእመቤታችንን ክብር ስንናገር ስለ እርሷ የተነገረውን በመረዳት መሆን ይገባል። ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትና የክብሯ መገለጫ ከሆኑት መካከል እናቀርብላችኋለን ለጋደኞቻችሁ ሼር በማረግ ወደ ቻናሉ ይጋብዙ 🙏🙏🙏

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትን መገለጫዎችን እናቀርብላችኋለን፡፡ ሁላችንንም በአማላጅነቷ ትጠብቀን፡፡🙏🙏🙏 ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም ያላትን ክብር ለመግለጥ የተለያዩ ምሳሌዎችን ትሰጣለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ ስትመሰገን የምትኖር ናት። እመቤታችን ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት ያላትን ክብር ለመግለጽ…»
ወላዲተ አምላክ መሆኗን
እመቤታችን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት። አንዳንዶች የአምላክ እናት የኢየሱስ እናት በማለት ይጠራሉ በእርግጥ ይህ አጠራር በበጎ ህሊና አነጋገር ችግር ባይኖርበትም የትርጉም ፍቺ ላይ ችግረ እንዳያመጣ ወላዲተ አምላክ ብሎ መጥራት የበለጠ የተዋሕዶን ምሥጢር የሚገልጥ ይሆናልና ሁሉም ሰው ይህንን መጠሪያ ቢለምደውና ቢጠቀምበት ይመረጣል። አንዳንድ የመናፍቃን ድርጅቶች የኢየሱስ እናት ብለው እመቤታችንን የተቀበሉ ለማስመስል በራሪ ጽሑፍ የሚያሰራጩበት ጊዜ ነበር ምክንያቱም ወላዲተ አምላክ መባሏን የሚቃወሙ ነገር ግን የኢየሱስ እናት ብለው የሚጠሩ ከዚህ በፊት ነበሩና ያሳደገም እናት ተብሎ ሊጠራ ይችላልና። በተለይም ንስጥሮስ የተባለው ከሃዲ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባም ብሎ በክህደት በመነሳቱ ዓለማቀፋዊ ጉባኤ እንዲጠራና ውግዘት እንዲተላለፍበት ሆኗል። እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ናት የሚለው አነጋገር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ስለሚገልጽ ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱት ውስጥ ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ ከእመቤታችን መሆኑን አንዱን ለምሳሌ ያህል አንስተን መመልከት እንችላለን። ቅዱስ ጴጥሮስ የተናገረውን ማስተዋል ለዚህ መልስ ይሰጣል
“ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ይላልና። ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፥ እንዳልታወክ በቀኜ ነውና።ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ልሳኔም ሐሤት አደረገ፥ ደግሞም ሥጋዬ በተስፋ ያድራል፤ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም። የሕይወትን መንገድ አስታወቅኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን ትሞላብኛለህ።ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን”  /ሐዋ 2፥25—32/
በዚህ ቃል ላይ እንደተነገረው ቅዱስ ዳዊት ሥጋዬ ብሎ የሚጠራው በእርግጥ የማንን ሥጋ ነው? ብለን ብንጠይቅ ክርስቶስ የተዋሐደውን ሥጋ መሆኑን ምንባቡ ይናገራል ። ዳዊት ሥጋዬ ብሎ የተናገረው በእርግጥም የእርሱ ሥጋ ነው ነገር ግን ሥጋዬ አይበሰብስም ብሎ ሲናገር ደግሞ ምሥጢራዊ ትርጉም እንዳለው ያመለክታል ፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ሲነሳ ብቻ ነውና ። ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ እና ቅዱስ ሉቃስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት አቆጣጠር ብለው ያስቀመጡት ጌታችን ከእመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያም የተዋሐደውን ሥጋ መሠረት አድርገው ነውና፤ ይህ ባይሆን ኖሮ የትውልድ ሐረግ ለመቁጠር ባልተነሱ ነበር ። ስለዚህ እኛ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ወላዲተ አምላክ ብለን እናታችንን እንጠራታለን በዚህም የተዋሕዶን ምሥጢር እንመሰክራለን።

#join or #share💎💎💎
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
📌ግብረ አውናን ምንድነው

📌ግብረ አውናን ተገቢ ነውን

📌ግብረ አውናን በመፅሐፍ ቅዱስ

📌ከግብረ አውናን ለመውጣት ምን ላድርግ

📌ግብረ አውናን እንዳያገኘኝ ምን ላድርግ

ሁሉን ለማግኘት
@senbet_tmehert_bet
 እንካን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን

የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም ‹መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ጉዞ ያደረገበት፤ ትሕትናውን የገለጠበት፤ ይህን ዓለም ከማዕሠረ ኃጢአት መፍታቱን በምሳሌ ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ተጽዕኖ›› ተብሎ ከሚጠራው የዐቢይ ጾም መጨረሻ (ዕለተ ዓርብ) እና ከሰሙነ ሕማማት መግቢያ ጀምሮ ያለው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፡፡ የክርስቶስን ነገረ ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤውን ሆሣዕና ተብሎ ዓለምን ማዳኑን የሚናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት፤ አምላካችን ለሰው ልጅ መዳን መከራ መቀበሉና የማዳን ሥራው በሰፊው የሚታወጅት፤ በሰሙነ ሕማማት ለሚያርፉ ምእመናን ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግበት፤ ወንጌል በአራቱ ማዕዘን የሚሰበክበት ሳምንት ነው – ሆሣዕና፡፡ ከዚያው አያይዞም ሰሙነ ሕማማት ይቀጥላል፤ ወቅቱም የክርስቶስን ነገረ ሕማሙንና ዓለምን ያዳነበት ጥበቡን የምንሰማበት ሳምንት ነው፡፡ በሞቱ ሞታችንን አጥፍቶ መንግሥቱን እንድንወርስ የፈቀደልን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይኹን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!!!

#join በማለት ተቀላበሉን
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned « እንካን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም ‹መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ…»
የዓብይ ጾም ሳምንታትን pinned የተደረገውን በመንካት የሁሉንም ሳምንታት ከመጀመሪያው ጀምሮ ማግኝት ትችላላችሁ
ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን
እመቤታችን ድንግል ማርያም ክብሯ ከሚገለጽበት መንገድ አንዱ ዘላለማዊ ድንግልናዋን በመናገር ነው ። ድንግል ማርያም በሀሳብም በሥጋም ድንግል ናት። የሀሳብ ድንግልና ማለት በህሊናዋ ከአንድ ሀሳብ በቀር መንታነት ያለው ሌላ ሀሳብ ፈጽሞ አለመኖሩን ለመግለጽ ነው። ከሰው ወገን የህሊና ድንግልና ያለው የለም ስለዚህ ድንግል ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረው ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ናት የምንለው ይህንኑ የህሊና ድንግልና ለመግለጽ ነው። እመቤታችንን ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ የህሊና/የሀሳብ ድንግልናዋን የሚገልጽ ነው። የሥጋ ድንግልናዋም ቢሆን ከሴቶች ሁሉ የተለየ ነው ይህንንም የድንግልናዋን ክብር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲገልጹ ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደች ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት በማለት በስድስት ጊዜ /ሁኔታ / ከፍለው ይናገራሉ። ይህም ሰዎች የድንግልናዋን ክብር እና ታላቅነት በመረዳት ድንግል ማርያም እንዲያከብሩና በረከትን እንዲያገኙ ነው።
ድንግል ማርያም ጌታችንን የወለደችው ማኀተመ ድንግልናዋ ሳይፈርስ ነው ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህንኑ በሚያረጋግጥ መልኩ ገልጸውታል።የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና ነብያት አስቀድመው የተናገሩ ሲሆን በተለይም ነብዩ ሕዝቅኤል እመቤታችን ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በማኀፀንዋ እንደምትሸከም፤ ለመለኮት ማደሪያ እንደምትሆን እውነተኛ እና ዘላለማዊ ቤተመቅደስ በማለት ተናግሯል። “ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር።እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።” /ት. ሕዝ 44፥1-2/ በዚህ ቦታ እንደተነገረው በተዘጋው መቅደስ የገባው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንደሆነና ሌላም ሰው እንደማይገባበት ገልጿል። የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና የሚጠራጠሩና በእምነት እኛን የማይመስሉ ሰዎችና መናፍቃን ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን የተመረጠበትን ምክንያት ባለመረዳትና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወንድሞቹ ተብሎ የተቀመጠውን ቃል መነሻ በማድረግ /ማቴ 13፥55/ ሌላ ትርጉም ለመስጠት የሚነሱ እምነት የጎደላቸው ሰዎች አሉ። ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን የተመረጠው እንዲጠብቃትና እንዲረዳት ስለነበር የተመረጠበትን ኃላፊነት በሚገባ ፈጽሟል። ይህም የእመቤታችን ረዳትና ጠባቂ መሆን ቅድስና እና የልቦና ንጽህና የሚጠይቅ ኃላፊነት ስለነበር ነው ፤ ምክንያቱም ድንግል ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ግብር በመሆኑ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ያለ አባት ከእመቤታችን መወለዱን ለመቀበል እግዚአብሔርን የሚፈራና በሃይማኖት መኖርን ይጠይቅ ስለነበር ነው ።ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደገለጸው ፤ እመቤታችን መፅነሷን ሲረዳ እንዴት እንደፀነሰች ለማወቅ ከህሊናው በላይ ስለሆነበት የመሰለውን ነገር በጥርጣሬ ከመናገር ይልቅ እግዚአብሔር እንዲገልጽለት በመጸለይ በስውር ሊተዋት አሰበ ። “የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።በነቢይ ከጌታ ዘንድ።እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።” /ማቴ 1፥19—25/ እዚህ ላይ እጮኛ ማለት ጠባቂ ማለት እንጂ ከጋብቻ ጋር የተገናኘ ትርጉም የለውም ።

#join or #share ለመናፍቃን ሼር ሼር አርጉት
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#መዝ_
@senbet_tmehert_bet
#አልፋና_ኦሜጋ
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
.....
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡህ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሰህ
ለአዳም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
....
ቅዱሳን እጆጅህ የፊጥኝ ታስረው
እንደበግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመፃደቅ
....
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳለፈው ሰጡህ አጋለጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
....
ግርፋት ህማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
....
5ቱ ችንካሮች ቅንዋተ መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
....
ግፈኞች አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፋብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖችህ ኀጢአት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን

ለመቀላቀል👇
@senbet_tmehert_bet
ጥንተ አብሶ የሌለባት መሆኑን

እመቤታችን ድንግል ማርያም በአዳምና በዘሩ የነበረው የውርስ ኀጢአት ያልደረሰባት ናት። አዳም በፈጸመው ስህተት የእርሱ ልጆች በሙሉ መከራ በበዛበት በዚህ ዓለም ለመኖር ተገደዋል። የነበረው የውርስ ኀጢአት ሸክም ከባድ ስለነበር የሰው ልጆች ሕይወት በድቅድቅ ጨለማ የመኖር ያህል ነበር። ለዚህም ነው ጌታችን ሲወለድ በድቅድቅ ጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ የተባለው የነበረውን ሕይወት ከባድነት ለመግለጽ ነው /ኢሳ 9፥2/። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን የተወለደው፡ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ይህንን የእዳ ደብዳቤ ሊቀድልንና ዘላለማዊ ክብር የምናገኝበትን ሕይወት ሊሰጠን ነው ። የጌታችን መምጣት አዳምንና ዘሩን ከዚህ የውርስ ኀጢአት ነጻ የሚያደርግ ስለሆነ የዓለም መድኃኒት ተብሏል። መጥምቁ ዮሐንስም ሲመሰክር የዓለሙን ሁሉ ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ያለው ከዚህ በመነሳት ነው /ዮሐ 1፥29/። ይህ የተነገረው የውርስ ኀጢአት ግን በእመቤታችን አልነበረም፤ አልደረሰምም። አንዳንድ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም የሚለውን ቃል በመዘንጋት ድንግል ማርያም የአዳም የውርስ ኀጢአት አለባት ለማለት ሲሞክሩ እንሰማቸዋለን። ይህ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው መጻሕፍትን ያላገናዘበ በጥርጣሬ ማእበል ከተጎዳ ህሊና (ልቦና) የሚወጣ ደካማ አስተሳሰብ ነው። በዚህ ቦታ ብዙ ዝርዝር ትንታኔ ለመስጠት ባንችልም ለምስክርነት ያህል ግን እመቤታችን ጥንተ አብሶ /የውርስ ኀጢአት/ እንደሌለባት ሁለት ቦታዎችን በቀላሉ እንመለከታለን።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበስራት የተናገረው ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ብሎ ነው የተናገራት /ሉቃ 1፥28/ መቼም የውርስ ኀጢአት ነበረባት ከተባለች ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ልትባል አትችልም ምክንያቱም የውርስ ኀጢአት ካለ ከጸጋ በታች ያደርጋልና። አንዳንዶች እንደሚናገሩት ደግሞ ወልድ በማህፀኗ ሲያድር አነጻት ቀደሳት እንዳንል የመልአኩ ምስክርነት ጌታን ከመፅነሷ በፊት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ይህንን ለእመቤታችን የነገራት ሦስት ጊዜ በተለያየ ቦታና ወቅት ነው። እመቤታችን በመልአኩ የቀረበላትን ቃል ተቀብላ እንደቃልህ ይሁንልኝ ከማለቷ በፊት ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ማለቱ ከውርስ ኀጢአት ነጻ እንደነበረች የተነገረ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ምስክርነት ነው። በተጨማሪም ነብዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ የተናገረው ምስክርነት ይህንን እውነታ የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው። “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር” /ኢሳ 1፥9/ እዚህ ላይ ዘርን ባያስቀርልን የተባለችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመሆኗ ከሌሎች የአዳም ዘር ሁሉ የሚለያት ነገር እንዳለ፤ በእነርሱ የደረሰ በዚህች ዘር ላይ ግን ያልደረሰ ነገር መኖሩን የሚያስረዳ ነው። ይህም የአዳምን ዘርን በሙሉ የሚመለከተው ኀጢአት ጌታችን በሞቱ ባያጠፋልን ኖሮ ለዘላለማዊ ቅጣት ያበቃን ነበር። ከዚህ በመነሳት ነው እመቤታችን ከአዳም ዘር የተገኘች ብትሆንም አስቀድማ በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር በማለት ሊቃውንት የሚገልጹት።

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
በሰሞነ ሕማማት አለመሳሳም
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡
🙏🙏🙏
ስለዚህ አይሁድ አያንሾካሾኩ “እንስቀለው… አንግደለው” ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ያነን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡
🙏🙏🙏
ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን “ሰላም ለኪ” ብሎ ነው ያታለላት፣ የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል ይቀጥላልም
፡፡
Share share share
#join or #share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የሰሙነ ሕማማት ትርጓሜ፣ ክንዋኔና ሚስጢር

ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ ጀምሮ ያሳለፈውና ከትንሳኤው በፊት ያለው አንድ ሳምንት " የመጨረሻ ሳምንት " ተብሎ ይጠራል፡፡ በሌላ አጠራር ደግሞ " ሰሙነ ሕማማት " ይባላል፡፡ በጌታ ላይ የሞት ምክር የተመከረበትና በብዙ መከራና ሕማማት የተገደለበት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም ሰሙነ ሕማማት የሚለው ስያሜ ጌታ የተቀበለውን ፀዋትዎ መከራን ለማዘከር የሰጠ ስያሜ ነው፡፡ የጌታ የመስቀሉ ሕማሞች ወይም " ሕማማት መስቀል " ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦🙏🙏🙏


1.🙏😭 በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ

2.🙏😭 ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ

3.🙏 😭65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው

4. 🙏😭120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ

5. 🙏😭365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ

6.🙏 😭80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ

7. 🙏😭6666 ጊዜ መገረፉ

8.🙏 😭አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ

9.🙏 😭136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ

10. 🙏😭ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል በችንካር መቸንከሩ

11.🙏😭 መራራ ሐሞትን መጠጣቱ

12. 🙏😭መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ

13. 🙏 😭በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

በዚህ ሳምንት ውስጥ ካህናትና ምዕመናን በአፀደ ቤተ ክርስትያን ተሰብስበው ከሀጥያት ርቀው ከምግብና ከመጠጥ ተቆጥቦ በጾምና በጸሎት የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ ሲያዜሙ ግብረ ሕማም የሚባለውን መጽሐፍ እያነበቡ ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ከአባታችን አዳም በደል ወይንም ስሕተት በኋላ በሕማማት፣ በደዌያት፣ በመቅሰፍታት፣ ወዘተ በብዙ መከራ የሰው ልጅ ሊኖርባቸው ግድ የሆነባቸው ዘመናት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ ጥሮ ግሮ ወጥቶ ወርዶ ለፍቶ ማስኖ የዕለት ጉርስ የቀን ልብስ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነበር፡፡ ሁልጊዜ የሰው ልጅ ቢያጠፋ ቢበድል ከሕገ እግዚአብሔር ቢወጣ እንኳ የዋህ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ አዛኝ የሆነ አምላክ የጠፋውን ሊፈለግ የተራበውን ሊያጠግብ የታረዘውን ሊያለብስ፣ ፍቅር ያጣውን ፍጹም ፍቅር ሊለግስ፣ ሰላም ለሌለው ፍጹም ሰላም ሊሰጥ፣ ተስፋ የሌለውን ተስፋ ሊያጐናጽፍ ከሰማይ ወረደ፤ ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና ሌሊት ጾመ፡፡ በጾሙም የኃጡአት ሥሮች ወይም ራሶች የተባሉትን ስስትን፣ ትዕቢትንና ፍቅረ ንዋይን ድል አደረገልን፡፡ እኛ እርሱ የጾመውን ጾም እንድናከብር እንድንጾም ምሳሌ ሆነን፡፡ ዲያብሎስን ድል አድርጐ ድል እንድንነሣው ኃይልና ምሳሌ ሆነን፡፡

ይቀጥላል

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «የሰሙነ ሕማማት ትርጓሜ፣ ክንዋኔና ሚስጢር ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ ጀምሮ ያሳለፈውና ከትንሳኤው በፊት ያለው አንድ ሳምንት " የመጨረሻ ሳምንት " ተብሎ ይጠራል፡፡ በሌላ አጠራር ደግሞ " ሰሙነ ሕማማት " ይባላል፡፡ በጌታ ላይ የሞት ምክር የተመከረበትና በብዙ መከራና ሕማማት የተገደለበት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም ሰሙነ ሕማማት የሚለው ስያሜ ጌታ የተቀበለውን ፀዋትዎ…»
ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው?
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ሰመነ ስምንት /ሳምንት/ አደረገ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሰርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ሐመ ማለት ታመመ ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት፤ ኃጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልእት አይበሉም፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን፣ ሕማሙን፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም እግዚአብሔር ይፍታህ አይሉም የሳምንቱ ሥርዓተ ፍትሐት አይደረግም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመሆኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምጽ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መሆናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡🙏🙏🙏

ይቀጥላል .
#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
በሰሙነ ሕማማት የሚገኙ ዕለታትና ስያሜያት

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/

ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ ...»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡

🙏🙏🙏

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (Mentesenhot)
 ፪. ዕለተ ሠሉስ

ሀ. የጥያቄ ቀን፡- ዕለተ ሠሉስ የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፤ ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ዕለት ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ  በዚች ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል፡፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያቀረቡለት ጥያቄም ‹‹ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለ ትምህርት በማስተማር ተአምራት ማድረግ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?›› የሚል ነበር፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፣ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?››ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል ከሰው ነው ብንልም ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያከብሩታል እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን›› ተባባሉና ‹‹ከወዴት እንደሆነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፤ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እንደዚሁ እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው፡፡ ልቡናቸው በክፋት ሥራና በጥርጥር  ስለተሞላ ነው እንጂይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ ሳያውቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡ (ማቴ.፳፩፥፳፫-፳፮፣ማር.፲፩፥፳፯-፴፫፣ሉቃ. ፳፥፩-፰)

ለ. የትምህርት ቀን፡- ይህቺ ዕለት ዕለተ ትምህርት ወይም የትምህርት ቀን በመባልም ትጠራለች፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት በማስተማር የተሰጠው ስያሜ ሲሆን ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ (ማቴ.፳፩፥፳፰፣፳፭፥፵፮፣ማር.፲፪፥፪፣፲፫፥፴፯፣ ሉቃ.፳፥፱፣፳፩፥፴፰)                

#join በማለት ይቀላቀሉን
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19