መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ኒቆዲሞስ ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ› የሚል ስያሜ ያለው ሲኾን፣ የስያሜው መነሻም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ የተመዘገበው ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ታሪክ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በሦስት መንገድ የአይሁድ አለቃ ነበር፤ በሥልጣን፣ በዕውቀትና በሀብት፡፡ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ሀብትና ዕውቀት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ሀብት ቢኖረውም ዕውቀትና ሥልጣን…»
አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?

አዕማደ ምስጢራት አምስት የሆኑት አራቱ ባህርያተ ሥጋና (አፈር፣ ውኃ፣ እሳትና ነፋስ) አምስተኛው ባህርየ ነፍስ (ልባዊት፣ ነባቢት፣ ሕያዊት የሆነች) ምሳሌ ያደረገ ሲሆን በዮሐ 5፡1 ያለችው አምስት እርከኖች የነበራት መጠመቂያም የእነዚህ ምሳሌ ናት፡፡ ያቺ መጠመቂያ ለድኅነተ ሥጋ ነበረች፤ አዕማደ ምሥጢር ግን ለድኅነተ ነፍስና ለድኅነተ ሥጋ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምስቱን አዕማደ ምስጢራት በረቂቅነታቸው እና በአኳሃን ቅደም ተከተላቸው እንደሚከተለው ታስቀምጣቸዋለች፡፡ እነዚህም ምሥጢረ ሥላሴ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የምንማርበት)፣ ምሥጢረ ሥጋዌ (የአምላክን ሰው መሆን የምንማርበት)፣ ምሥጢረ ጥምቀት (ስለ ዳግም መወለድ የምንማርበት)፣ ምሥጢረ ቁርባን (ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም የምንማርበት) እና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን (ስለ ዳግም ምጽዓት የምንማርበት) ናቸው። አምስቱ አዕማደ ምሥጢር በአፈጻጸማቸው በሦስት ይከፈላሉ ። እነዚህም ምሥጢረ ሥላሴና ምሥጢረ ሥጋዌ አምነን የምንቀበላቸው፤ ምሥጢረ ጥምቀትና ምሥጢረ ቁርባን አምነን የምንተገብራቸው፤ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን አምነን በተስፋ የምንጠብቀው ናቸው። ከዚህ ቀጥሎ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ምስጢራቱን ያብራራሉ፡፡

1.✍️ምስጢረ ሥላሴ፡  “አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፡፡” ማቴ 28፡20

2.✍️ምስጢረ ሥጋዌ፡  “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” ዮሐ 1፡14

3.✍️ምስጢረ ጥምቀት፡ “ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” ማር 16፡16

4.✍️ምስጢረ ቁርባን፡ “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፡፡” ዮሐ 6፡54

5.✍️ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን፡  “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡” ዮሐ 11፡23

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?

አዕማደ ምስጢራት ይዘት ምንጭ የጌታና የሐዋርያት ትምህርት ነው፡፡ ይሁን እንጅ አነሳሱ በጸሎተ ሃይማኖት ወይም አባቶቻችን ምዕመናንን በትክክለኛው ሃይማኖት ለማጽናትና መናፍቃንን ድል ለመንሳት በተካሄዱ በጉባዔ ኒቂያና ጉባዔ ቁስጥንጥንያ ነው፡፡ ‎ከዚህ በኋላ አባቶቻችን ጸሎተ ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ከብሉያት ከሐዲሳትና ከሊቃውንት መጽሃፍት በማውጣጣት አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን አዘጋጅተዋል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሰረት የሆኑት አምስቱ አዕማደ ምስጢራት መሰረታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያድርጉ እንጂ ስያሜ መሰረታቸው 318ቱ ሊቃውንት በኒቂያ አርዮስን ካወገዙ ቦኋላ ካስታወቁት የሃይማኖት ቀኖና (ጸሎተ ሃይማኖት) ነው፡፡

በጸሎተ ሃይማኖት “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር(በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን)” ሲል በእግዚአብሔር አብ ያለውን እምነት፣ “ወነአምን በአሃዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ (በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን)” ሲል በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት፣ “ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ (በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን)” ሲል በመንፈስ ቅዱስ ያለውን እምነት በመግልጽ ምስጢረ ሥላሴን ያጸናል፡፡ እንዲሁም “ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፣ ተሰብእ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ፤ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል (ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ)” በማለት ምስጢረ ሥጋዌን ያጸናል፡፡ በተጨማሪም “ወነአምን በአሃቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን)” በማለት ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበትን ቤተ-ክርስቲያን በመጥቀስ ምስጢረ ቁርባንን ያጸናል፡፡ “ወነአምን በአሃቲ ጥምቀት (በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን)” በማለት ምስጢረ ጥምቀትን ያጸናል፡፡ “ወንሴፎ ትንሳኤ ሙታን (የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን)” በማለት ምስጢረ ትንሳኤ ሙታንን ያጸናል፡፡

#join or #share
ለሌሎች ሼር በማረግ ያድርሱ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?

በሥጋዊ ዐይን እግዚአብሔርን ማየትና በውስን አዕምሮ ሐልዎተ እግዚአብሔርን መመርመር አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ  ስለራሱም ይሁን ለእርሱ አንክሮና ተዘክሮ ስለተፈጠሩት ፍጥረታት ገና ያልደረሰባቸው ነገሮች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን እርሱ በወደደው መጠን ለአባቶቻችን ለቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት አዕምሮአቸው ሊረዳው በሚችለው መጠን በብዙ ምሳሌና በብዙ ጎዳና ማንነቱን ገልጾላቸዋል (ዕብ 1፡1-2)፡፡ እግዚአብሔርንም የምናውቀው እርሱ ራሱን ለሰው ልጆች በገለጠው መጠንና የሰው ልጅ መረዳት በሚችለው መጠን ብቻ ነው፡፡

አንድ ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር አምስቱን አዕማደ ምስጢራት በሚገባ ከተማረ በሕይወቱ ምንም እንኳን ነፋሳት ቢነፍሱ ጎርፍም ቢጎርፍ ከእምነቱ ምንም ሊያናውጠው አይችልም፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ከደሙና ከአጥንቱ ተዋሕደው የዚህን ዓለም ፈተና እንዲቋቋም ያስችሉታል፡፡ አዕማደ ምስጢራትን ያወቀና ያመነ እና የሥላሴ ልጅነትን በጥምቀት ያገኘ አባት እናት ቢሞቱበት በሥላሴ አባትነት ይጽናናል፡፡ መከራ ቢደርስበት አምላክ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ የደረሰበትን መከራ እያሰበ ከምንም አይቆጥረውም፡፡ ረኀበ ነፍስ ቢደርስበት ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፤ ክቡር ደሙንም ይጠጣል፡፡ በእምነቱ ምክንያት እንገድልሀለን ቢሉት ትንሣኤ ዘጉባዔን (ትንሣኤ ሙታንን) ተስፋ ያደርጋል፡፡ ይህም በመሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከኅሊና እግዚአብሔር እንዳይርቅና ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት እንዲጸና እነዚህን ምሰሶዎች (ምስጢራት) ታስጨብጠዋለች፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች (ምስጢራት) የተደገፈ ጠላቶቹን አጋንንትንና መናፍቃንን ድል ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ አዕማደ ምስጢራትን በሚገባ ማወቅ ሃይማኖትን በሚገባ ለመረዳት፣ ከጥርጥርና ከኑፋቄ ለመጠበቅና በሃይማኖት ጸንቶ ጽድቅን ለመፈጸም ይጠቅማል፡፡

ሼር ሼር ሼር ይደረግ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትን መገለጫዎችን እናቀርብላችኋለን፡፡ ሁላችንንም በአማላጅነቷ ትጠብቀን፡፡🙏🙏🙏
ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም ያላትን ክብር ለመግለጥ የተለያዩ ምሳሌዎችን ትሰጣለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ ስትመሰገን የምትኖር ናት። እመቤታችን ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት ያላትን ክብር ለመግለጽ በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። በተለይም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በማመስገን በቤተክርስቲያናችን ዘወትር የሚነሱት የሶርያው ቅዱስ ኤፍሬም፤ የብህንሳው አባ ሕርያቆስ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይገኙበታል። የእመቤታችንን ክብር ያለተረዱ ሰዎች ለምን እኛ ኦርቶዶክሳውያን እንደምናመሰግናት ዘወትር በጸሎታችን እንደምናነሳት ጥያቄ የሚያቀርቡ አሉ። ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከሕጻንነቱ ጀምሮ የእመቤታችንን ምስጋና ይማራል ሁልጊዜም ኣባታችን ሆይ ብሎ ጸሎት የጀመረ በመልኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብሎ ድንግል ማርያምን ሳያመሰግን የሚቀር የለም። ቤተክርስቲያናችን ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። እኛም የእመቤታችንን ክብር ስንናገር ስለ እርሷ የተነገረውን በመረዳት መሆን ይገባል። ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትና የክብሯ መገለጫ ከሆኑት መካከል እናቀርብላችኋለን ለጋደኞቻችሁ ሼር በማረግ ወደ ቻናሉ ይጋብዙ 🙏🙏🙏

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልዩ የሚያደርጋትን መገለጫዎችን እናቀርብላችኋለን፡፡ ሁላችንንም በአማላጅነቷ ትጠብቀን፡፡🙏🙏🙏 ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም ያላትን ክብር ለመግለጥ የተለያዩ ምሳሌዎችን ትሰጣለች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ ስትመሰገን የምትኖር ናት። እመቤታችን ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት ያላትን ክብር ለመግለጽ…»
ወላዲተ አምላክ መሆኗን
እመቤታችን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት። አንዳንዶች የአምላክ እናት የኢየሱስ እናት በማለት ይጠራሉ በእርግጥ ይህ አጠራር በበጎ ህሊና አነጋገር ችግር ባይኖርበትም የትርጉም ፍቺ ላይ ችግረ እንዳያመጣ ወላዲተ አምላክ ብሎ መጥራት የበለጠ የተዋሕዶን ምሥጢር የሚገልጥ ይሆናልና ሁሉም ሰው ይህንን መጠሪያ ቢለምደውና ቢጠቀምበት ይመረጣል። አንዳንድ የመናፍቃን ድርጅቶች የኢየሱስ እናት ብለው እመቤታችንን የተቀበሉ ለማስመስል በራሪ ጽሑፍ የሚያሰራጩበት ጊዜ ነበር ምክንያቱም ወላዲተ አምላክ መባሏን የሚቃወሙ ነገር ግን የኢየሱስ እናት ብለው የሚጠሩ ከዚህ በፊት ነበሩና ያሳደገም እናት ተብሎ ሊጠራ ይችላልና። በተለይም ንስጥሮስ የተባለው ከሃዲ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባም ብሎ በክህደት በመነሳቱ ዓለማቀፋዊ ጉባኤ እንዲጠራና ውግዘት እንዲተላለፍበት ሆኗል። እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ናት የሚለው አነጋገር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ስለሚገልጽ ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱት ውስጥ ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ ከእመቤታችን መሆኑን አንዱን ለምሳሌ ያህል አንስተን መመልከት እንችላለን። ቅዱስ ጴጥሮስ የተናገረውን ማስተዋል ለዚህ መልስ ይሰጣል
“ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ይላልና። ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፥ እንዳልታወክ በቀኜ ነውና።ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ልሳኔም ሐሤት አደረገ፥ ደግሞም ሥጋዬ በተስፋ ያድራል፤ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም። የሕይወትን መንገድ አስታወቅኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን ትሞላብኛለህ።ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን”  /ሐዋ 2፥25—32/
በዚህ ቃል ላይ እንደተነገረው ቅዱስ ዳዊት ሥጋዬ ብሎ የሚጠራው በእርግጥ የማንን ሥጋ ነው? ብለን ብንጠይቅ ክርስቶስ የተዋሐደውን ሥጋ መሆኑን ምንባቡ ይናገራል ። ዳዊት ሥጋዬ ብሎ የተናገረው በእርግጥም የእርሱ ሥጋ ነው ነገር ግን ሥጋዬ አይበሰብስም ብሎ ሲናገር ደግሞ ምሥጢራዊ ትርጉም እንዳለው ያመለክታል ፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ሲነሳ ብቻ ነውና ። ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ እና ቅዱስ ሉቃስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት አቆጣጠር ብለው ያስቀመጡት ጌታችን ከእመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያም የተዋሐደውን ሥጋ መሠረት አድርገው ነውና፤ ይህ ባይሆን ኖሮ የትውልድ ሐረግ ለመቁጠር ባልተነሱ ነበር ። ስለዚህ እኛ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ወላዲተ አምላክ ብለን እናታችንን እንጠራታለን በዚህም የተዋሕዶን ምሥጢር እንመሰክራለን።

#join or #share💎💎💎
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
📌ግብረ አውናን ምንድነው

📌ግብረ አውናን ተገቢ ነውን

📌ግብረ አውናን በመፅሐፍ ቅዱስ

📌ከግብረ አውናን ለመውጣት ምን ላድርግ

📌ግብረ አውናን እንዳያገኘኝ ምን ላድርግ

ሁሉን ለማግኘት
@senbet_tmehert_bet
 እንካን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን

የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም ‹መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ጉዞ ያደረገበት፤ ትሕትናውን የገለጠበት፤ ይህን ዓለም ከማዕሠረ ኃጢአት መፍታቱን በምሳሌ ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ተጽዕኖ›› ተብሎ ከሚጠራው የዐቢይ ጾም መጨረሻ (ዕለተ ዓርብ) እና ከሰሙነ ሕማማት መግቢያ ጀምሮ ያለው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፡፡ የክርስቶስን ነገረ ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤውን ሆሣዕና ተብሎ ዓለምን ማዳኑን የሚናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት፤ አምላካችን ለሰው ልጅ መዳን መከራ መቀበሉና የማዳን ሥራው በሰፊው የሚታወጅት፤ በሰሙነ ሕማማት ለሚያርፉ ምእመናን ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግበት፤ ወንጌል በአራቱ ማዕዘን የሚሰበክበት ሳምንት ነው – ሆሣዕና፡፡ ከዚያው አያይዞም ሰሙነ ሕማማት ይቀጥላል፤ ወቅቱም የክርስቶስን ነገረ ሕማሙንና ዓለምን ያዳነበት ጥበቡን የምንሰማበት ሳምንት ነው፡፡ በሞቱ ሞታችንን አጥፍቶ መንግሥቱን እንድንወርስ የፈቀደልን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይኹን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!!!

#join በማለት ተቀላበሉን
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned « እንካን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም ‹መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ…»
የዓብይ ጾም ሳምንታትን pinned የተደረገውን በመንካት የሁሉንም ሳምንታት ከመጀመሪያው ጀምሮ ማግኝት ትችላላችሁ
ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን
እመቤታችን ድንግል ማርያም ክብሯ ከሚገለጽበት መንገድ አንዱ ዘላለማዊ ድንግልናዋን በመናገር ነው ። ድንግል ማርያም በሀሳብም በሥጋም ድንግል ናት። የሀሳብ ድንግልና ማለት በህሊናዋ ከአንድ ሀሳብ በቀር መንታነት ያለው ሌላ ሀሳብ ፈጽሞ አለመኖሩን ለመግለጽ ነው። ከሰው ወገን የህሊና ድንግልና ያለው የለም ስለዚህ ድንግል ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረው ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ናት የምንለው ይህንኑ የህሊና ድንግልና ለመግለጽ ነው። እመቤታችንን ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ የህሊና/የሀሳብ ድንግልናዋን የሚገልጽ ነው። የሥጋ ድንግልናዋም ቢሆን ከሴቶች ሁሉ የተለየ ነው ይህንንም የድንግልናዋን ክብር ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲገልጹ ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደች ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት በማለት በስድስት ጊዜ /ሁኔታ / ከፍለው ይናገራሉ። ይህም ሰዎች የድንግልናዋን ክብር እና ታላቅነት በመረዳት ድንግል ማርያም እንዲያከብሩና በረከትን እንዲያገኙ ነው።
ድንግል ማርያም ጌታችንን የወለደችው ማኀተመ ድንግልናዋ ሳይፈርስ ነው ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህንኑ በሚያረጋግጥ መልኩ ገልጸውታል።የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና ነብያት አስቀድመው የተናገሩ ሲሆን በተለይም ነብዩ ሕዝቅኤል እመቤታችን ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በማኀፀንዋ እንደምትሸከም፤ ለመለኮት ማደሪያ እንደምትሆን እውነተኛ እና ዘላለማዊ ቤተመቅደስ በማለት ተናግሯል። “ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር።እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።” /ት. ሕዝ 44፥1-2/ በዚህ ቦታ እንደተነገረው በተዘጋው መቅደስ የገባው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንደሆነና ሌላም ሰው እንደማይገባበት ገልጿል። የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና የሚጠራጠሩና በእምነት እኛን የማይመስሉ ሰዎችና መናፍቃን ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን የተመረጠበትን ምክንያት ባለመረዳትና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወንድሞቹ ተብሎ የተቀመጠውን ቃል መነሻ በማድረግ /ማቴ 13፥55/ ሌላ ትርጉም ለመስጠት የሚነሱ እምነት የጎደላቸው ሰዎች አሉ። ቅዱስ ዮሴፍ ለእመቤታችን የተመረጠው እንዲጠብቃትና እንዲረዳት ስለነበር የተመረጠበትን ኃላፊነት በሚገባ ፈጽሟል። ይህም የእመቤታችን ረዳትና ጠባቂ መሆን ቅድስና እና የልቦና ንጽህና የሚጠይቅ ኃላፊነት ስለነበር ነው ፤ ምክንያቱም ድንግል ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ግብር በመሆኑ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ያለ አባት ከእመቤታችን መወለዱን ለመቀበል እግዚአብሔርን የሚፈራና በሃይማኖት መኖርን ይጠይቅ ስለነበር ነው ።ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደገለጸው ፤ እመቤታችን መፅነሷን ሲረዳ እንዴት እንደፀነሰች ለማወቅ ከህሊናው በላይ ስለሆነበት የመሰለውን ነገር በጥርጣሬ ከመናገር ይልቅ እግዚአብሔር እንዲገልጽለት በመጸለይ በስውር ሊተዋት አሰበ ። “የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።በነቢይ ከጌታ ዘንድ።እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።” /ማቴ 1፥19—25/ እዚህ ላይ እጮኛ ማለት ጠባቂ ማለት እንጂ ከጋብቻ ጋር የተገናኘ ትርጉም የለውም ።

#join or #share ለመናፍቃን ሼር ሼር አርጉት
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#መዝ_
@senbet_tmehert_bet
#አልፋና_ኦሜጋ
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
.....
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡህ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሰህ
ለአዳም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
....
ቅዱሳን እጆጅህ የፊጥኝ ታስረው
እንደበግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመፃደቅ
....
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳለፈው ሰጡህ አጋለጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
....
ግርፋት ህማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
....
5ቱ ችንካሮች ቅንዋተ መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
....
ግፈኞች አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፋብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖችህ ኀጢአት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን

ለመቀላቀል👇
@senbet_tmehert_bet
ጥንተ አብሶ የሌለባት መሆኑን

እመቤታችን ድንግል ማርያም በአዳምና በዘሩ የነበረው የውርስ ኀጢአት ያልደረሰባት ናት። አዳም በፈጸመው ስህተት የእርሱ ልጆች በሙሉ መከራ በበዛበት በዚህ ዓለም ለመኖር ተገደዋል። የነበረው የውርስ ኀጢአት ሸክም ከባድ ስለነበር የሰው ልጆች ሕይወት በድቅድቅ ጨለማ የመኖር ያህል ነበር። ለዚህም ነው ጌታችን ሲወለድ በድቅድቅ ጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ የተባለው የነበረውን ሕይወት ከባድነት ለመግለጽ ነው /ኢሳ 9፥2/። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን የተወለደው፡ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ይህንን የእዳ ደብዳቤ ሊቀድልንና ዘላለማዊ ክብር የምናገኝበትን ሕይወት ሊሰጠን ነው ። የጌታችን መምጣት አዳምንና ዘሩን ከዚህ የውርስ ኀጢአት ነጻ የሚያደርግ ስለሆነ የዓለም መድኃኒት ተብሏል። መጥምቁ ዮሐንስም ሲመሰክር የዓለሙን ሁሉ ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ያለው ከዚህ በመነሳት ነው /ዮሐ 1፥29/። ይህ የተነገረው የውርስ ኀጢአት ግን በእመቤታችን አልነበረም፤ አልደረሰምም። አንዳንድ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም የሚለውን ቃል በመዘንጋት ድንግል ማርያም የአዳም የውርስ ኀጢአት አለባት ለማለት ሲሞክሩ እንሰማቸዋለን። ይህ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው መጻሕፍትን ያላገናዘበ በጥርጣሬ ማእበል ከተጎዳ ህሊና (ልቦና) የሚወጣ ደካማ አስተሳሰብ ነው። በዚህ ቦታ ብዙ ዝርዝር ትንታኔ ለመስጠት ባንችልም ለምስክርነት ያህል ግን እመቤታችን ጥንተ አብሶ /የውርስ ኀጢአት/ እንደሌለባት ሁለት ቦታዎችን በቀላሉ እንመለከታለን።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበስራት የተናገረው ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ብሎ ነው የተናገራት /ሉቃ 1፥28/ መቼም የውርስ ኀጢአት ነበረባት ከተባለች ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ልትባል አትችልም ምክንያቱም የውርስ ኀጢአት ካለ ከጸጋ በታች ያደርጋልና። አንዳንዶች እንደሚናገሩት ደግሞ ወልድ በማህፀኗ ሲያድር አነጻት ቀደሳት እንዳንል የመልአኩ ምስክርነት ጌታን ከመፅነሷ በፊት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ይህንን ለእመቤታችን የነገራት ሦስት ጊዜ በተለያየ ቦታና ወቅት ነው። እመቤታችን በመልአኩ የቀረበላትን ቃል ተቀብላ እንደቃልህ ይሁንልኝ ከማለቷ በፊት ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ማለቱ ከውርስ ኀጢአት ነጻ እንደነበረች የተነገረ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ምስክርነት ነው። በተጨማሪም ነብዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ የተናገረው ምስክርነት ይህንን እውነታ የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው። “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር” /ኢሳ 1፥9/ እዚህ ላይ ዘርን ባያስቀርልን የተባለችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመሆኗ ከሌሎች የአዳም ዘር ሁሉ የሚለያት ነገር እንዳለ፤ በእነርሱ የደረሰ በዚህች ዘር ላይ ግን ያልደረሰ ነገር መኖሩን የሚያስረዳ ነው። ይህም የአዳምን ዘርን በሙሉ የሚመለከተው ኀጢአት ጌታችን በሞቱ ባያጠፋልን ኖሮ ለዘላለማዊ ቅጣት ያበቃን ነበር። ከዚህ በመነሳት ነው እመቤታችን ከአዳም ዘር የተገኘች ብትሆንም አስቀድማ በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር በማለት ሊቃውንት የሚገልጹት።

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21