መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
‹‹ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣሉ፤ በየሀገሩም ረኀብ፣ ቸነፈርም፣ የምድርም መናወጥም ይሆናል›› (ማቴ.፳፬፥፯-፰)

ሕዝብ በሕዝብ ላይ የተባለው በሀገራችን ሕዝቦች መካከል እንደሚነሡት ዓይነት ፍጅቶች ማለት ነው፡፡ በእነዚህ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል እየተደረጉ ያሉ አስከፊ የእርስ በርስ ግጭቶች ከጉዳታቸው አስከፊነት ባሻገር ዘረኝነትን የሚያስፋፉ በመሆናቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በእኛ ላይ እንዲበረታ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ዘረኝነት እርስ በርስ ከመዋደድ ይልቅ በሰዎች መካከል ጥላቻ እንዲፈጠር ያደረጋል፡፡ ይህንም አምላካችን ፈጽሞ የሚጠላው ነገር በመሆኑ ቸርነቱን ይነፍገናል፡፡

መንግሥት በመንግሥት ላይ ማለት ጎረቤት የሆኑ ሀገራት እርስ በርስ እንደሚፋጁ ጌታችን ሲገልጽልን ነው፤ ለምሳሌ ኢትዮጵያና ግብጽ በዓባይ ወንዝ እንደሚጣሉት፣ እስራኤልና ፍልስጥኤም በሃይማኖት እንዲሁም በድንበር ግጭት እንደሚጣሉት ዓይነት ነው፡፡ አንድ የሀገር መንግሥት በሌላው ላይ የሚያደርገውንም ጥቃት ያመለክታል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ በአንድ ሃይማኖት በአንድነት እንድንኖር እንጂ በሰው ሀገር ድንበር መጣላትም ሆነ ከሌሎች ሀገር ጥቅም ፈልጎ የሀገራትን ድንበር መጣስ፣ ሕዝብን መጨረስ እና ሰላም መንፈግ ወንጀል ከመሆኑ ባሻገር እጁግ ከባድ ኃጢአትም ነው፡፡

በየሀገሩም ረኀብ ቸነፈር፣ የምድርም መናወጥም ይሆናል የተባለው በዓለም ሁሉ ላይ ነጋ ጠባ የምንሰማቸው ዜናዎች ስለእነዚህ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቈጠሩ ሕዝቦች ተርበዋል፤ መድኃኒት ባልተገኘላቸው በሽታዎች ሕይታቸውን አጥተዋል፤ በመሬት መንቀጥቀጥና መንሸራተት እንዲሁም በእሳተ ገሞራ ሀገራቸው ተናውጧል፡፡

በዚህ ጊዜ በዓለማች ላይ በከተሠተው ቸነፈር እና ባስከተለው ረኀብም ልክ ምድር ተናውጣለች፡፡ በየሀገራቱም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በየታው ይሞታሉ፤ ወይንም በዚያ ሳቢያ ንብረተቻውን አጥተው ለረኀብ ይጋለጣሉ፡፡ ይህም እየተፈጸመ ያለው ጌታችን ኢየሱስ እንደተናገረው በዋዜማው ላይ በመሆኑ ገና ያላተፈጸሙ ምልክቶች አሉና ያንን ማወቅ እንዲሁም በኃጢአት ምክንያት የመጣብን መሆኑን በመረዳት በንስሓ መመለስ አለብን፡፡

ይቀጥላል .....

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
‹‹ያን ጊዜም ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም›› (ማቴ.፳፬፥፱)

ሰዎች በምድር ላይ በሃይማኖታቸው ታምነው ሲኖሩ ብዙ መከራ ይደርስቸዋል፤ ይራባሉ፤ ይጠማሉ፤ ይታሠራሉ፤ ይሰደዳሉ፤ ይገደላሉ፤ ይህም በዚህ ትውልድ እንደታየውና በርካቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው እና ማዕተባቸውን አልበጥስም በማለታቸው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው እንደተሰደዱት፣ ንብረተቻው በመናፍቃን ተቃጥሎባቸው ለረኀብና ለጥም መጋለጥና በግፍ መገደል ለዘመኑ ፍጻሜ ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ እነዚህም መከራዎች የምጥም መጀመሪያዎች ናቸውና በዚህ እንደማያቆም ጌታችን ኢየሱስ በወንጌል ተናግሯል፡፡

ይህም ሁሉ ግን ጌታችን እንደተናረው ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነውና ጸንተን ልንኖር ይገባል እንጂ ማማረር የለብንም፡፡ ምክንያቱም በክርስቶስ ክርስቲያን እንድንባል የተቀበለውን መከራ መቀበል እንዲሁም መስቀሉን መሸከም አለብን፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
" የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 60:14)
ያሳዝናል ማርያምን.. በሉ እናፍጥነው። በዳታ የምትጠቀሙ ራሱ ገብታቹ ቪድዮ ባታዩም ሰብስክራይብ አድርጉና ውጡ.. ይሄ በቃ ሃላፊነት እናድርገው። አሁን ይሄንን እያየን አንለፍ.. በእርግጥም አናልፍምም እንደውም ሼር ሼር እያደረግን እስቲ ሁሉም ሰብስክራይብ አድርጎ ምን ያህል እንደምንደርስ እንይ.. ከታች የማስቀምጠውን ሊንክ በመጫን "subscribe" የሚለውን ተጫኑ
👇👇👇
https://www.youtube.com/user/EOTCMK
ገብር ኄር

ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡ አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ፣ ዐሥር አድርጎ፣ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ›› ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ፣ ወርዶ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው ‹‹አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ ‹‹አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት፤ እነሆ መክሊትህ!›› ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት!›› ብሎ አዘዘ፡፡

በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው (ክርስቲያን) ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም፣ በጎ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ (አገልጋይ) ይባላል፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ፣ መክሊታቸውን (ጸጋቸውን) ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መክሊትን (ጸጋን) መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ገብር ኄር ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡ አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡…»
ገብር ኄር የዓብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት እንካን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
ትምህርተ ሃይማኖት ወደ እግዚአብሔር የምታደርሰውን ፍኖተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መንገድ) የምናውቅበትና ዘላለማዊ ሕይወትን የምንጎናጸፍበትን “ርትዕት ሃይማኖት” የምንገነዘብበት ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖትን ዶግማ (መሠረተ እምነት) እና ቀኖና (ሥርዓተ ቤተክርስቲያን) ብለው በሁለት ይከፍሉታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሠረት እንደሆኑ የምታምነውና የምታስተምረው አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ነው፡፡ በዚህች የአስተምህሮ ጦማር የአምስቱ አዕማደ ምስጢራት- መግቢያ የመግቢያ ክፍል የሚቀርብ ሲሆን የአንዳንድ ቃላትን ትርጉም በመግለጽ እንጀምራለን፡፡

✍️እግዚአብሔር: እግዚአብሔር የሚለው ቃል ከግዕዝ የተገኘ ሲሆን “እግዚእ” ማለት ጌታ ማለት ነው፡፡ “ብሔር” ማለት ደግሞ ዓለም ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት የዓለም ጌታ (ፈጣሪ፣ ገዥ) ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ እግዚአብሔር እንዳለ ለማረጋገጥ አይሞክርም፡፡ የእግዚአብሔርን ህልውና መሠረት አድርጎ ይጀምራል እንጂ፡፡ ዘፍ 1፡1 እግዚአብሔር በዕብራይስጥ የሚጠራባቸው ሦስት ስሞች አሉ፡፡ እነዚህም ኤል (ኃያል አምላክ)፣ ያህዌ (ያለና የሚኖር፣ እንደ ፈቃዱ የሚሠራ) እና አዶን (ጌታ) የሚሉት ናቸው፡፡ በጽርዕ አልፋና ኦሜጋ (መጀመሪያውና መጨረሻው) ይባላል፡፡ መለኮት ማለት መላኪ(ገዥ) ማለት ነው፡፡ አምላክ ማለትም ፈጥሮ የሚገዛ ማለት ነው፡፡

✍️ እምነትና ሃይማኖት: እምነት የሚለው ቃል መሠረታዊ ቃሉ ግዕዝ ሲሆን ትርጓሜውም ማመን ወይም መታመን ማለት ነው፡፡ ማመን ማለት ስለእግዚአብሔር የሰሙትንና የተረዱትን እንዲሁም የተቀበሉትን ትምህርት እውነት ነው ብሎ በልብ መቀበል ነው (ሮሜ 10፡17)፡፡ መታመን ደግሞ ያመኑትንና የተቀበሉትን እምነት በሰው ፊት ሳይፈሩና ሳያፍሩ መመስከር ነው፡፡ ማቴ 10፡32 ሮሜ 10፡9 ሐዋርያው ቅዱሰ ጳውሎስ ስለ እምነት ሲናገር “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” ብሏል፡፡ ዕብ 11፡1 ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡   ሃይማኖት ማለት ለዓለም ፈጣሪ አለው ብለው የሚያምኑት እምነት ነው፡፡ ለዓለም ፈጣሪ አለው ብለው የሚመሰክሩት ቃል ነው፡፡ ሃይማኖት ሰው ፈጣሪውን የሚያመልክበት፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሚሆንበት፣ ጽድቅንም የሚሠራበት፣ የዘላለም ሕይወትን የሚያገኝበት መንገድ ነው፡፡ ሃይማኖትም አንዲት ናት፡፡ ኤፌ 4፡5


#join or #share
@linkortodoxe21
✍️ዶግማና ቀኖና: ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለት ይከፈላል፡፡ ይኸውም ዶግማና ቀኖና በሚል ነው።

✍️ዶግማ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም የእምነት መሠረት ማለት ነው፡፡ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡ በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱ አንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህን የመሰለው መሰረታዊ ትምህርት ዶግማ ወይም መሰረተ እምነት ይባላል፡፡

ቀኖና የሚለው ቃልም የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ቀኖና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖት አባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበት፤ የሚቀነስለት ነው፡፡ ለምሳሌ በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝ ከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ 1ኛ ቆሮ. 14፥40፡፡ 2ኛተሰ. 3፥6-7 ቀኖና (ሥርዐት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነና ወንጌልን የሚያስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ማስተማርና መሰጠት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡ “በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን /የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ ዕለት ዕለትም ቁጥራቸው ይበዛ ነበር፡፡” ሐዋ. 16፥4-5፡፡

#join or #share መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)

https://t.me/joinchat/WPlEyEeAttNFBvZK
ቤተክርስቲያን፡ እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥሮ ቤተ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ግዕዛን ካላቸው ፍጥረታት ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ ይህም ሦስት አይነት ትርጉም አለው፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ኅብረት፡ የክርስቲያኖች አንድነት ነው (1ኛ ቆሮ 11፡28)፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች መኖሪያ፡ የእግዚአብሔር ቤት ነው፡፡ “ቤት” ማለት መኖሪያ ማለት እንደሆነ ሁሉ “ቤተክርስቲያን” ማለት የክርስቲያኖች ቤት/መኖሪያ የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው (ዮሐ 2፡ 16)፡፡  እዚህ ላይ ህንፃ ቤተክርስቲያን ስንል አገልግሎቱንም ጭምር የሚያመለክት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ በተጨማሪም ቤተክርስቲያን ሲል ምዕመናንን ነው፡፡ የእያንዳንዱን ክርስቲያን ሰውነት የሚያመላክት ነው (1ኛ ቆሮ 3፡16)፡፡ ይህም ማለት ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡

የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእምነትና የሃይማኖት መሠረት የሆኑት አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ናቸው፡፡ ሃይማኖት የሚባለውም እነዚህን ምስጢራት ተቀብሎ ሁሉን ማድረግ ከሚችል ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ነው፡፡ አምስት መሆናቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።” (1ኛቆሮ 14፡19) ያለውን መነሻ ያደረገ ሲሆን የስያሜያቸው ትንታኔ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

ይቀጥላል .....

#join or #share

https://t.me/joinchat/WPlEyEeAttNFBvZK
አዕማድ ማለት ምን ማለት ነው?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መፍቻ ቁልፍ የግእዝ ቋንቋ እንደ መሆኑ መጠን በተለይም በቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላት ምንጫቸው ግእዝ ነው፡፡ “አዕማድ” የሚለውም ቃል መገኛው “አምድ” የሚለው የግዕዝ ቃል ነው፡፡ “አምድ” የሚለው ቃል የነጠላ ቁጥርን የሚገልፅ ሲሆን “አዕማድ” ሲሆን ደግሞ ብዙ ቁጥርን ይገልፃል፡፡ ትርጉሙም በቃላዊ ፍቺው ለቤት ሲሆን ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ምሰሶ ቤትን ደግፎ እና አቅንቶ እንደሚይዝ ሁሉ አምስቱ አዕማደ ሚስጥራትም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን አቅንተውና ደግፈው ስለሚይዙ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ዐምድ ለጽሕፈትም ይውላል፡፡ የገጽ ስፋትንም በመክፈል ለንባብ መመጠኛነት ያገለግላል፡፡ በዚህ ፍቺም ባህርየ ሥላሴን ከልክ አልፈን እንዳንመረምር የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

አምድ በቁሙ ምሰሶ ብለን የምንጠራው እና ቤቱ እንዳይዘም ወይም ወደ አንድ ጎን እንዳያዘነብል፤ ሚዛኑን እና ልኩን ጠብቆ እንዲቆም የሚያደርግ ነው። በአምድ የተሠራ ቤት አይዛባም ያለዓምድ የተሠራ ቤት ግን ይፈርሳል አይጸናም፡፡ ቤት በአምድ (በኮለም) እንደሚጸና ሃይማኖትም በእነዚህ አዕማደ ምሥጢራት ተጠቃሎ ይገለጻል፤ ምዕመናንም እነዚህን ምሥጢራት በመማር ጸንተው ይኖራሉ። እንደዚህም ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አዕማድ የተባሉ ምሥጢራት ይዞ የተገኘ ሰው ልቡናው በፍቅረ እግዚአብሔር በተስፋ መንግስተ ሰማያት ይጸናል፡፡ እነዚህን አምስቱን እምነታት ሳይዝ የተገኘ ልቡናው በፍቅረ እግዚአብሔር በተስፋ መንግስተ ሰማያት አይጸናም፡፡

“ሁሉም ነገር ድጋፍ ያስፈልገዋል” የሚለው ሃሳብ ለቤቶች ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባለፈ ለብዙ ነገሮች ያገለግላል፡፡ ብዙ የፍልስፍና ሊቃውንት ሰዎች ሁሉ ህይወታቸው በተገቢው መንገድ ለመምራት ሲሉ የሚቀበሏቸው መሰረታዊ እምነቶች (fundamental beliefs) እንዳሉ ይናገራሉ፡፡ በዓለም ላይ ከፍተኛ ህዝብ ይከተላቸዋል የሚባሉት ሃይማኖቶችም ሳይቀሩ መሰረታዊ እምነት የሚሏቸው አሏቸው፡፡ ለአብነትያህል፡- በእስልምናው ሃይማኖት አምስቱ የእስልምና መሰረቶች (The Five Pillars of Islam) ሲኖሩ በቡድሂዝም እምነት ደግሞ አራቱ እውነታዎች (The Four Noble Truths) ይገኛሉ፡፡

በቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ምሰሶዎች አንድን ቤት ደግፈው እንደሚይዙት ሁሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትንም ቀጥ አድርገው የሚይዙ ምሰሶዎች አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት ከሆነ አንድ ሰው አምስቱን አዕማደ ምስጢራት በጥንቃቄ ካወቀ የኑፋቄ ማዕበል አይጥለውም፡፡ ከእምነቱም አይናወጽም፡፡ በህይወቱ የተለያዩ መከራዎች ቢመጡበትም በእነዚህ ትምህርቶች በኩል ራሱን ያፀናል፡፡ እነዚህን አዕማድ ያላወቅ በሙሉ ልቡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ነኝ ማለት አይችልም፡፡ በዚህም ምክንያት እነዚህን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

#share #share #share በማረግ ለሌሎች አድርሱ
#link

https://t.me/joinchat/WPlEyEeAttNFBvZK
ለምን ምስጢራት ተባሉ?

ቅድስት ቤተክርስቲያን አምስቱን አዕማድ “የምስጢር ትምህርቶች” ትላቸዋለች፡፡ “ምሥጢር” የሚለው ቃል “አመሠጠረ” ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ነው፡፡ ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም የፈጣሪ ምሥጢር (ሊገለጥ የማይችል፤ ከ እስከ የሌለው ምሥጢር) እና የፍጡራን ምሥጢር (በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/፤ የሰውና የመላእክት ምሥጢር) ናቸው፡፡ ሊቃውንቱም አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ስለምን ምሥጢር እንደተባሉ ሲያብራሩ በዓይኔ ካላሣያችሁኝ በእጄ ካላሲዛችሁኝ ብሎ አላምንም አልማርም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሯቸው ስለሆኑ ምሥጢር ተባሉ በማለት ገልጸዋል፡፡(ሃይ. አበው ዘአትናትዮስ 14÷ 39 ሃይ. አበው ዘኤራቅሊስ 11÷24 1ኛ ቆሮ 14፥19 1ኛ ሳሙ 17፥40)፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ በመኾኑ፣ በመንፈሳዊው አእምሮና ዓይን፣ ጆሮና እጅ ካልሆነ በቀር በነፍሳዊውና በስጋዊው አእምሮና ዓይን፣ ጆሮና እጅ ብቻ ሊታሰብና ሊታይ፣ ሊሰማና ሊዳሰስ ስለማይቻል ትምህርቱና እውቀቱ “ምስጢር” ተባለ። አምስቱ አዕማደ ምስጢራት “ምስጢር” የተባሉበት ምክንያት በሚከተሉት ሦስት ቁም ነገሮች በበለጠ ይብራራል።

አንድ፡ ረቂቅ እና ስውር ስለሆነው አምላክ የሚናገሩ አስተምህሮቶች ስለሆኑ ነው። የእግዚአብሔርን የአንድነትና የሦስትነት ነገር፣ ቀጥሎ ከሦስቱ አካላት አንዱ ሰው የመሆኑ ነገር፣ እንዲሁም ሰው ከእግዚአብሔር በመንፈስ የመወለዱን ነገር፣ ደግሞም ሰው የሆነውን አምላክ ሥጋውን በመብላትና ደሙን በመጠጣት በእግዚአብሔር መንግስት ለዘለአለም ሕያው ሆኖ የመኖርን ነገርና በመጨረሻም ሰው ለዘላለማዊው ህይወት ወይም ሞት በማይበሰብስ አዲስ አካል እንደገና የመነሳቱን ነገር የሚያስረዳ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት የሚያስረዱ በመሆኑ ነው።

ሁለት፡ ትምህርቶቹን በሥጋዊ ጥበብ ለመረዳት የማይቻል በመሆኑ ነው። ትምህርቱና እውቀቱ እንደሥጋዊ ትምህርትና እውቀት ተፅፎ የሚቀርብና ተነቦ የሚጠና፣ በሥጋዊው ቁሳቁስ ግዙፍ ማስረጃነት እየተደገፈ የሚሰጥ ሳይሆን በአንድ ወገን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ልቦና በእውነተኛ አምልኮ ፈልቆ የሚናገሩትና የሚያስተምሩት፣ በሌላው ወገን ደግሞ በእውነተኛ ፍላጎት በተመሰረት ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ልቦና ሆነው የሚሰሙትና የሚማሩት ረቂቅ የእግዚአብሔር ነገር ስልሆነ ነው።

ሦስት፡ ቤተክርስቲያን ለአማንያን ብቻ የምትነግረው እና የምታስተምረው በመሆኑ ነው። ለማያምኑ የማይገለጥ፣ ለሚያምኑ ግን በእውነተኛው መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ የእውቀት ቁልፍ ከፍተው በዚያው በፍፁም ብርሃን ካዩት በኋላ አክብረው የሚጠብቁት “የማይጠፋ እንቁ” በመሆኑ ነው። (ማቴ. 7፡6፣ ማቴ. 13፡11)

#join or #share

https://t.me/joinchat/WPlEyEeAttNFBvZK
ኒቆዲሞስ

ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ› የሚል ስያሜ ያለው ሲኾን፣ የስያሜው መነሻም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ የተመዘገበው ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ታሪክ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በሦስት መንገድ የአይሁድ አለቃ ነበር፤ በሥልጣን፣ በዕውቀትና በሀብት፡፡ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ሀብትና ዕውቀት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ሀብት ቢኖረውም ዕውቀትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ዅሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሔድ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ፈሪሳውያን ማመን ባልቻሉበት በዚያን ዘመን ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፤ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን ማለት ከመልካም ነገር ሲከለክላቸው ኒቆዲሞስ ግን ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡ ጌታችን ዓለምን ለማዳን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች አስጨናቂ ሰዓት፤ ሐዋርያት በተበተኑባት አይሁድ በሠለጠኑባት በዕለተ ዓርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ፣ እሱን ያገኘ ያገኘኛል ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ ሰው ነው – ኒቆዲሞስ፡፡ ስለዚህም ሰባተኛው ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡

#join or #share
https://t.me/joinchat/WPlEyEeAttNFBvZK
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ኒቆዲሞስ ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ› የሚል ስያሜ ያለው ሲኾን፣ የስያሜው መነሻም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ የተመዘገበው ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ታሪክ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በሦስት መንገድ የአይሁድ አለቃ ነበር፤ በሥልጣን፣ በዕውቀትና በሀብት፡፡ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ሀብትና ዕውቀት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ሀብት ቢኖረውም ዕውቀትና ሥልጣን…»