መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ክርስቲያን ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖሩት ያስፈልጋል ???

ሁላችሁም እንድትሳተፍ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መምህር ዘበነ ለማ 😍😍


✝️ @linkortodoxe21 ✝️
✝️ @linkortodoxe21 ✝️
✝️ @linkortodoxe21 ✝️
መንፈሳዊ ህይወት
ክርስቲያን ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖሩት ያስፈልጋል ??? ሁላችሁም እንድትሳተፍ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ
 

✝️ ክርስቲያን ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖሩት ያስፈልጋል?✝️

1.መንግሥተ ሰማያትን መውረስ፡- አንድ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣው ለጊዜያዊ ችግሩ ብቻ መፍትሔ ለማግኘት አስቦ ሳይሆን ሰማያዊ ክብርና ዋጋ ለማግኘት ነው፡፡ “ድንኳን የሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘለዓለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንፃ እንዳለን እናውቃለን፡፡ 2ቆሮ.5፥1

 

2.የሚታወቅና ግልጽ ዓላማ፡- ክርስቲያን ያለ ዓላማ በጭፍን አይጓዝም፡፡ ሳይታሰብ በድንገት በአጋጣሚ የሚል ነገር በርሱ ዘንድ እምብዛም ቦታ አይኖረውም፡፡ የሚታወቅ ግልጽ ዓላማ ኖሮት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሳካለት ይጸልያል፡፡ “ሳታቋርጡ ጸልዩ፡፡” 1ተሰ.5፥18 ከዚህ አንጻር አንዱን ዓላማው አድርጎ ይጓዛል ጋብቻ ወይም ምንኩስና መካከል ሆኖ አያወላውልም፡፡

 

3.ራስን መግለጽ፡- ክርስቲያን በሄደበት ሁሉ ማንነቱን መግለጥ አለበት፡፡ በተራራ ላይ ያለች ከተማ መሰወር አትችልም፡፡ ይህም ሲባል እኔ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ እያለ በማወጅ ወይም በማስታወቂያ ሳይሆን አኗኗሩ ማንነቱን ይገልጠዋል፡፡ ይህም ኑሮው በቤተሰብ፣ በት/ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በአካባቢው ኅብረተሰብ ዘንድ ወዘተ…… መገለጥ አለበት፡፡

 

4.ታማኝነት፡- እውነተኛ ክርስቲያን ምሎ የማይከዳ፣ አደራ የማያጠፋ፣ የማያወላውል ለምስክርነት የሚበቃ ነው፡፡ ታማኝ ሰው መልካም የሚለውን ይናገራል፡፡ የሚናገረውን ይሠራል በሓላፊነት ቢቀመጥ ያለ አድልዎ ወገናዊነት ያስተዳድራል፡፡ “በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሀለሁ፡፡” ማቴ.25፥21 ይባልለታል፡፡ ታማኝነት ለራስ ታማኝ መሆን ለእግዚአብሔር ሰዎች በመታመን ይገለጣል፡፡ ይህም በትዳር፣ በሥራ፣ በተሰጠው ሓላፊነት መታመን አለበት፡፡ ምሳሌ ዮሴፍ ዘፍ.39፥9

 
ከተመለሰው ነው 5

5.ፍቅር፡- ክርስቲያናዊ ፍቅር የያዘ ሰው በሰውና በእግዚአብሔር ፍቅር ያለነቀፋ ይኖራል፡፡ ፍቅር የክርስቲያንነታችን መገለጫ ነው፡፡ አምላክን ከዙፋኑ ያወረደው ራሱንም እስከ ሞት አሳልፎ ለሰው ልጅ እንዲሰጥ ያደረገው ፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ አንደ ሰው ፍቅር ከሌለው ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የለውም ማለት ይቻላል፡፡ የምናፈቅረው ማንን ነው?

 

6.እግዚአብሔርን፡- እግዚአብሔርን ማፍቀር ሲባል እግዚአብሔርንና የእርሱ የሆነውን ሁሉ ማፍቀር ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ፍቅረ እግዚአብሔርን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡

 

1.ትእዛዙን ማክበር፡- እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዛቱን በመፈጸም ይገለጣል፡፡ “ትእዛዙ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፡፡” ዮሐ.14፥21

2.የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ መውደድ ይህን በሦስት ከፍለን መመልከት እንችላለን

ይቀጥላል ...
ለሌሎች ሼር እናድርግ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
'''ሆዳችሁ ጠግቦ ከምታቀርቡት አንድ መቶ ጸሎትና ተራራ ከሚያርድ ድምጻችሁ ይልቅ በጾም ውስጥ ሆናችሁ የምታቀርቡት አንድ ጸሎት ተሰሚነት አለው።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

✝️ @linkortodoxe21
✝️ @likonrtodoxe21
✝️ @linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት
  ✝️ ክርስቲያን ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖሩት ያስፈልጋል?✝️ 1.መንግሥተ ሰማያትን መውረስ፡- አንድ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣው ለጊዜያዊ ችግሩ ብቻ መፍትሔ ለማግኘት አስቦ ሳይሆን ሰማያዊ ክብርና ዋጋ ለማግኘት ነው፡፡ “ድንኳን የሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘለዓለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንፃ እንዳለን እናውቃለን፡፡ 2ቆሮ.5፥1   …
ከዚህ የቀጠለ ........

2.1.    ቅዱሳንን መውደድና ማክበር፡- ቅዱሳን እግዚአብሔር የመረጣቸው ያከበራቸውና የወደዳቸው ናቸው፡፡ “የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው የጠራቸው እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው ያጸደቃቸው እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡” ሮሜ.8፥29 ፍቅረ እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑ ቅዱሳንን በማክበር እንገልጻለን፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር የትሕትናና የኦርቶዶክሳዊነት ውጤት ነው፡፡

2.2.   ሀገርን መውደድ፡- ሀገር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር በሰጠው ሀገር ሆኖ እርሱን ሊያመሰግን ሀገሩን ሊወድ ግዴታ አለበት፡፡ ሀገር ከሌለ ሠላም ካልሆነ እግዚአብሔርን በደስታ ማመስገን አይቻልምና፡፡ “ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድ፡፡” መዝ.136፥5

2.3.   ቤተሰብን መውደድ፡- ክርስቲያን እምነትን፣ ምግባርን፣ ሥርዓትን በመጀመሪያ የሚማረው ከቤተሰቡ ነው፡፡ ቤተሰብ የመጀመሪያዎቹ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ነቢዩ ሙሴ የእግዚአብሔርን፣ የወገንን፣ የሀገርን ፍቅር የተማረው ከእናቱ ነውና፡፡ ወልደው፣ አሳድገው፣ አስተምረው ለትልቅ ደረጃ ያበቁትን ቤተሰቡን ክርስቲያን ሊወድ ይገባዋል፡፡ “ስለ ቤተሰቦቹ የማያስብ ማንም ቢኖር ሃይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡” 1ጢሞ.5፥8

3.   የሰው ልጆችን ሁሉ ማፍቀር፡- /ፍቅረ ቢጽ/ የሰውን ልጅ ሁሉ ማፍቀሩ ፍቅረ ቢጽ ይባላል፡፡ ይህም በሥላሴ አርአያ የተፈጠረውን ሰው ሁሉ መውደድና ማፍቀር ነው፡፡ ይህም ኀጥእ ጻድቅ፣ አማኒ መናፍቅ፣ ዘመድ ባዕድ ሳይሉና ሳይለዩ ሁሉን አስተካክሎ መውደድ ነው፡፡ ይህም ትእዛዝ ጠላትን እስከመውደድ በመድረስ ነው፡፡ “በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ፡፡” ማቴ.5፥44

 

በአጠቃላይ ክርስቲያን ከአለባበሱ ጀምሮ ውጫዊ አቋሙም ሆነ አጠቃላይ ሕይወቱ በማናቸውም ጊዜና ቦታ ሁሉ ክርስቲያንነቱን ሊገልጡ ይገባቸዋል፡፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ኖረው ለሰውም ብርሃን ሆኖ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆኑትን አስደሰተ የሚባለው ያን ጊዜ ነው፡፡ እንግዲህ ክርስቲያን በምድር ሲኖር በግል ሕይወቱም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮው ምን መምሰል እንዳለበት ራሱን ከላይ በተገለጸው በሦስቱ ሕግጋት አንጻር እየመረመረ መጓዝ አለበት፡፡ በግል ሕይወቱ ዘወትር ንስሓ እየገባ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እየጾመ፣ እየጸለየ፣ እየመጸወተ ሰማያዊ መንግሥትን ተስፋ በማድረግ ይጓዛል፡፡ በማኅበራዊ ኑሮውም ደግሞ ሰዎችን በሐዘናቸው ጊዜ ማጽናናት፣ በደስታቸው ተካፋይ መሆን፣ ከቸገራቸው ለችግራቸው ደራሽ በመሆን እውነተኛ ፍቅሩን ሊገልጽ ያስፈልጋል፡፡ “የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁል ጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን፡፡” 2ቆሮ.4፥10


ክርስትያናዊ ስነ ምግባር በሚለው ርዕስ የነበረን ክፍል ተጠናቃል ።

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ደብረ ዘይት

አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ደብረ ዘይት› ይባላል፡፡ ስያሜው የተወሰደውም ከማቴዎስ ወንጌል ፳፬፥፫ ካለው ትምህርት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኝ በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ትልቅ ተራራ ነው፡፡ ጌታችን ምሥጢራትን በተለያየ ቦታ ገልጧል፡፡ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴሴማኒ፤ ምሥጢረ መንግሥቱን በደብረ ታቦር፤ ምሥጢረ ቊርባንን በቤተ አልዓዛር፤ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን በቤተ ኢያኢሮስ፤ ምሥጢረ ምጽአቱን ደግሞ በደብረ ዘይት ገልጧል፡፡ ደብረ ዘይት ጌታችን ዳግም ለፍርድ መምጣቱንና ምሥጢረ ምጽአቱን ለደቀ መዛሙርቱ በሚገባ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡ ደብረ ዘይትን ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ለማደሪያነት ተጠቅሞበታል፡፡ ቀን ቀን በምኲራብ ያስተምራል፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በደብረ ዘይት ያድራል፡፡ ይህንም ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይመሰክራል፤ ‹‹ዕለት ዕለት በመቅደስ ያስተምር ነበር፡፡ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር፡፡ ሕዝቡ ዅሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር›› (ሉቃ. ፳፩፥፴፯)፡፡ በዚህ ለማደሪያነት ባገለገለው ተራራ ምሥጢረ ምጽአቱን ስለ ገለጠበት አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ደብረ ዘይት የሚል ስያሜ ተሰጥተታል፡፡ ደብረ ዘይት ጾሙ እኩል የሚኾንበት፤ አምላካችን በግርማ መንግሥቱ ለፍርድ በመጣ ጊዜ መልካም ለሠሩ ክብርን፣ ክፉ ለሠሩ ቅጣቱን የሚያስተላልፍ መኾኑ የሚነገርበት፤ ስለ ዓለም መጨረሻ እና ስለሚመጣው ሕይወት የምንማርበት የክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ ዕለት ነው፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
በመንፈሳዊ ሕይወት ለመኖር ከእኛ የሚጠበቁ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚል ጥያቄ በሕሊናችን መመላለሱ አይቀሬ ነው። ለጥያቄያችሁ መልስ ለማግኘትና በመንፈሳዊ ሕይወት ጸንተን ለመኖር የሚከተሉትን ትዕዛዞች ተግባራዊ እናድርጋቸው፡፡

ቃለ እግዚአብሔርን መማር

መንፈሳዊ ሕይወት ቀስ በቀስ የሚያድግ ስለሆነ በአንዴ ተነስቶ መንፈሳዊ ሰው መሆን አይቻልም። ያለንን መንፈሳዊ ጸጋም እስከመጨረሻው አጽንተን የምንጓዝ ምግበ ነፍስ የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር  ስንሰማና ስንማር ነው።  ሰው መማሩን፣ መጠየቁን፣ የአባቶችን ምክር ካቆመ ለተለያዩ ፈተናዎች እየተጋለጠ መሄዱን ያሳያል። “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም” /ማቴ 4፥4/  ተብሎ እንደተጻፈ መማር፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብ፣ አባቶችን መጠየቅ በእግዚአብሔር እንድንታመን፤ በቅዱሳን አማላጅነና ተራዳይነት አምነን እንድንጠቀም፤ የቤተክርስቲያናችንን ታሪክ፣ ሕግ፣ ሥርዐት፣ ዶግማና ቅኖና እንድናውቅ ያደርጋል።

ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” /2ጢሞ 3፥16/  እንዳለ ቅዱሳት መጽሕፍት ለመንፈሳዊ ሕይወት እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው። በእርግጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቀላሉ ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ዛሬ የምንኖርባት ዓለም በቴክኖሎጂ ሰውን ከሰው ማገናኘት፣የምንፈልገውንም ነገር በፍጥነት  ለማገናኘት የምታስችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች። ስለዚህ ይህን የቴክኖሎጂ የመረጃ  መረብ ለመንፈሳዊ አገልግሎት በመጠቀም ለነፍሳችን የሚያስፈልጋትን ምግብ መመገብ እንችላለን


መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)


#join or share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የዓብይ ጾም ሳምንታትን pin የሚለውን በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ
የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?›› (ማቴ.፳፬፥፫)


በዓለም ፍጻሜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን ደግሞ በግራው ለይቶ እንደየሥራችን ሊፈርድ ይመጣልና ምልክቶቹን እናውቅ ዘንድ በወንጌል ተጽፎልናል፡፡

ጌታችን ኢየሱስም በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ስለዳግም ምጽአት ጥያቄ አቀረቡለት፤ ‹‹ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?›› ጌታችንም ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ጦርነትን፥ የጦርነትንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠንቀቁ፤ አትደንግጡ፤ ነገር ግን ፍጻሜው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣሉ፤ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድርም መናወጥም ይሆናል፡፡ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ ያን ጊዜም ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ ያንጊዜም ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ይለውጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፡፡ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ከዐመጽም ብዛት የተነሣ ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች፡፡ እስከ መጨረሻው የሚታገሥ ግን እርሱ ይድናል፡፡ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ምስክር ሊሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ያንጊዜም ፍጻሜ ይደርሳል፡፡›› (ማቴ.፳፬፥፫-፲፬)

ጌታችን ኢየሱስ የነገራቸው የዓለም ፍጻሜ ምልክት ለደቀ መዝሙርቱ ቢሆንም ትንቢቱ ግን በእኛ ትውልድ እየተፈጸመ መሆኑን በሚገባ ልናውቅና ተረድተንም የሚጠበቅብንን ጥንቃቄ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ግን ብዙዎች ዓለም በደረሰችበት የሥልጣኔ ደረጃ የተነሣ የሚኖሩት ምድራዊ ሕይወትን እንጂ መንፈሳዊውን አይደለም፤ ለሃይማኖትም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አመለካከት ከተቀየረ ሰንብቷል፡፡ በእነርሱ አስተሳሰብ ሰዎች ዓለማዊ (በእነርሱ አጠራር ዘመናዊ) ሕይወትን እንዲኖሩ የተፈቀደ ነው፡፡ ነገር ግን በማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው የጌታችን ኢየሱስ ቃል እንደነገረን በሰዎች ኃጢአት የተነሣ የምንኖርባት ዓለም የሰይጣን ማደሪያ ወደ መሆን ርሳለች፤ ጌታም ስለምጽአት ቀን የተናገረው ትንቢት እየተፈጸመ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዝሙርቱ የነገራቸውን ምልክት እያንዳንዱን ነጥለን እንመልከት፡-

ይቀጥላል ......

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ›› (ማቴ.፳፬፥፭)

በተለያዩ ዘመናት ‹‹እኔ ክርስቶስ ነኝ›› በሚል ሐሰተኛ ትንቢት ከሕዝብ ዘንድ ተነሥተው ሰዎችን ሲያውኩ እና ሲያስቱ የነበሩ ከሓድያን ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት የተነሡ ሐሳውያን ሰባኪዎች በስሙ ተልከናል በማለት በክርስቶስ ስም የሐሰት ትምህርት ያስተማሩ ነበር፡፡ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ በዚህ ዘመን የሚያስተምሩ ሐሰተኞች አሉ፡፡

በአፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት የእነዚህ ሐሰተኞች የክሕደት ትምህርት ብዙዎችን አስቷል፤ ዛሬም እንደምናየው ብዙዎችን ወደ ጥርጣሬ እና ክሕደት የሚያስገባቸው የሐሳውያን ነቢያት መነሣት ነውና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ በየትኛው ሰዓት ወይንም ቦታ እንደሚያጋጥሙን ስለማናውቅ እውነተኞቹን ጠንቅቀን መለየት አለብን፡፡ ለምሳሌ ያህል በቴሌቭዥን መስኮታችን ቀርበው እኔ ክርስቶስ ነኝ ብለው እንደ ጌታችን ተአምራት ለማድረግ በማስመል በአስማታቸው የተለያዩ ነገሮች ሲያሳዩን ከርመዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ‹ክሪስ ኤንጅል› በሚል ስያሜ ከምዕራባውያን ወገን የመጣ አንድ ታዋቂ ሰው ጌታችን ለሐዋርያትና ለደቀ መዛሙርቱ በውኃ ላይ ተራምዶ የእምነትን ኃይል እንዳስተማራቸው እርሱ ደግሞ በውኃ ላይ እንደተራመደ በማስመሰል፣ ልጅ የነበረቸውን ሕፃን ደቂቃ ባልሞላት ጊዜ ወደ ብላቴና በመቀየር፣ አንድን ሴት ከወገቧ በታች ለሁለት በመክፈል ልዩ ኃይል እንዳለው በሰዎች ዘንድ ተአማኒት ያገኘ ሰው አለ፡፡ ይህም ሰው የሚጠቀመው የሰይጣንን መንፈስ እንጂ በእግዚአብሔር ኃይል አይደለም፡፡ ነገር ግን የእርሱን ፕሮግራም ብዙዎች ይመለከቱታል፡፡ በዚህም ስለ እርሱ ለማወቅ በሚጥሩ ጊዜ የእርሱን አመለካከት ወደ መቀበልና በሰይጣን ወደ ማመን አንዲሁም እስከማምለክ ደርሰዋል፡፡ ስለዚህም ከእንደነዚህ ዓይነቱ ሰዎች ለመጠበቅ በአካል ብቻም ሳይሆን በዓይናችን የምንመለከታቸውን ወይንም በጆራችን የምንሰማቸውን ማናቸውንም ነገር መመርመር እንዲሁም በጸሎት ከፈተና እንዲያወጣን መማጸን ያስፈልጋል፡፡

ይቀጥላል ....

#join or #share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ጦርነትን፥ የጦርነትንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ›› (ማቴ.፳፬፥፮)

በዳግም ምጽአት ጌታችን ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በዓለማችን ፍጻሜ ዋዜማ የሆነው ክንውን አንዱ በምድር ላይ ጦርነት በዓለም ሀገራት መካከል ጦርነት መብዛቱ ነው፡፡ ይህን እውነት በጆራችን እየሰማንና በዓይናችን እያየን በመሆኑ ልንክድ አንችልም፡፡ ወንድም ከወንድሙ ጋር ጦርነት ውስጥ ገብቶ ብዙ ወገኖቻችን በሞት እያለቁ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን የዓለም ፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆናችንን ነው፡፡ ስለዚህም ሁላችንም በኃጢአታችን ሳቢያ የመጣብንን ችግር እና መከራ ተቋቁመን እንድናልፍና በዳግም ምጽአት ቀን በቀኙ እንዲያቆመን በንስሓ ኃጢአታችንን ማንጻት እና ሥጋ ወደሙን መቀበል ያስፈልጋል፡፡

ይቀጥላል ......

#join or #share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21