መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
እኔ አላይም ካንተ ሌላ
ዞር ብዬ ወደ ኋላ
ኪዳን ገባው ከአምላኬ ጋር
ይሻለኛል ቤትህ መኖር



ማራኪ ነህ እውነተኛ
የማትደክም የማትተኛ
በችንካርህ ስበሀኛል
እንዳንተ ያለ ከየት ይገኛል

ድንጋይ ነበር የኔ ደሞዝ
በዚህ አለም ስቅበዘበዝ
ነጻ ወጣው ባንተ ፊት
እልሃለው መድሃኒት

አመጸኛ ወንበዴ ነኝ
የአለም ውበት የማረከኝ
እንዴት ብለህ ወደድከኝ
አሸነፍከኝ ደነከኝ

ወንበር ስበህ አሳረፍከኝ
ቤትህ ገባው ስትፈልገኝ
አልገባኝም ገና ፍቅርህ
በዘመኔ የምማርህ

https://t.me/linkortodoxe21
+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ብዙ መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ‹ምስጋና የሚገባውን› እግዚአብሔርን ሳታቋርጥ የማመስገን አገልግሎትዋ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለዓመታት የዜማ ስልት ተምረው የተመረቁ የስብሐተ እግዚአብሔር ሊቃውንት ያሏት ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝማሬዋ ፣ ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ የሃያ አራት ሰዓታት ጊዜ የማይበቃው ፣ ለሰዓት ሲባል በንባብ እየተባለ ፣ ዜማው እያጠረ የሚተው በመሆኑ ፀሐይ በማይጠልቅበት በዘላለማዊው መንግሥት ለማመስገን ዝግጁ ሆና የምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን ያሰኛታል፡፡ ከዚህ እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው ስብሐተ እግዚአብሔር ጋር የእግዚአብሔር ቅዱሳንንም በሰፊው ታመሰግናቸዋለች፡፡
በዚህች አጭር ጽሑፍ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው እግዚአብሔር ከሆነ ፍጡራን ለሆኑ ለቅዱሳን ሰዎች ፣ ለቅዱሳን መላእክትና ለድንግል ማርያም የሚዘመረው መዝሙርና የሚቀርበው ውዳሴ ምን ያህል ተገቢ ነው? ለቅዱሳን መዘመር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሳስብ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደር ያልተገኘለትን ዘማሪ ለመጠየቅ ወደድኩ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ መቶ አምሳ መዝሙራት የተጻፉለት ፣ ራሱ ሰማኒያ ሰባት መዝሙራትን የዘመረና በሥሩ ያሉ መዘምራን ደግሞ አብረውት ብዙ መዝሙራትን የዘመሩበት የዝማሬ ባለ ጠጋ ንጉሥ ዳዊትን ‹‹እውነት ለፍጡራን ምስጋና ይገባል ወይ?›› ብዬ ልጠይቀው አስቤ ወደ መዝሙረ ዳዊት ገሰገስኩ፡፡
ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡
ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?
ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡
ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡
የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡
በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡
በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ ተነሥተን ነው፡፡
ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤ መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል› ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው
፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ?
ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።
የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡
አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ. ፲፫፥፵፫)
‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3)
‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡ (2ነገሥ. 1፡13)
በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር አያጡም፡፡ ሆኖም ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡
ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-
‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡14)
አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ ‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)
ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ› ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)
የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡
ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣ "ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)
ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-
ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14)
የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን? የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?
እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል አይደለም።
ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎ
ስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡
ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ 26:13)
ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :–
"ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2: 7
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
1. ማቶዎስ = #በሰው ገጽ ተመስሏል፣ የክርስቶስን በስጋ ከአብርሃም ከዳዊት መምጣት ልደቱን በመዘርዘር አስረድቷልና፥፥

2. ማርቆስ = #በአንበሳ ተመስሏል፣ ግብጽ የነበሩትን የአንበሳ ጣኦታት በስብከቱ አፍርሶ አንበሳ የተባለ ክርስቶስን ሰብኳልና፥፥

3. ሉቃስ = #በላም ገጽ ይመሰላል፣ ጌታ ኢየሱስ በከብቶች ማደርያ መወለዱን ከሌሎች ይልቅ አስፍቶ ስለጻፈ፥፥

4. ዮሃንስ = #በንስር ይመሰላል፣ ንስር ከሌሎች አእዋፍ ሁሉ ተለይቶ ወደ ላይ መጥቆ ይበራል። በላይም ሆኖ በመሬት ያሉትን ረቂቃን ነገሮች አጣርቶ መመልከት ያውቅበታል። ወንጌላዊው ዮሃንስም ከሌሎች ወንጌላውያን አጻጻፍ በተለየ በምስጢረ ስላሴ ይጀምርና ስለ ተዋህዶም ሲጽፍ ወደ ላይ መጥቆ በማሰብ ቅድመ ዓለም ስለነበረው ቃል ይተርክና ዝቅ ብሎ "ያም ቃል ስጋ ሆነ" በማለት ይጽፋል።

https://t.me/linkortodoxe21
ወንጌል.pdf
11.9 MB
#የአራቱ_ወንጌላት አንድምታ ትርጓሜ

ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሃንስ

https://t.me/linkortodoxe21
ኦርቶዶክስ (Orthodox)

“ኦርቶዶክስ” የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን የተቀናበረው “ኦርቶ” እና “ዶክስ” ከሚሉት ሁለት ቃላት ነው፡፡ትርጉማቸውም ኦርቶ ማለት ቀጥተኛ: ትክክለኛ ማለት ሲሆን ዶክስ ማለት ደግሞ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ በአንድነት ሲሆኑ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ፡ ትክክለኛ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡

ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባዔ ነው፡፡ በኒቅያ “ወልድ ፍጡር ነው” የሚለውን የአርዮስን የክህደት ትምህርት ለማውገዝና ሃይማኖታቸውን ለማፅናት የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንት ይህን ቃል የተጠቀሙት  ሐዋርያት  ያስተማሯት ሃይማኖት ቀጥተኛና ትክክለኛ ናት ለማለት ነው፡፡ ሌሎች እንደ አርዮስ ክህደት ያሉት በየዘመኑ የሚነሱት ልዩ ልዩ አዳዲስ ትምህርቶች የምንፍቅና መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይህችን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ  ብለዋታል፡፡

በዘመናችን የቋንቋ አጠቃቀምም  ኦርቶዶክሳዊ መንገድ (orthodox) ማለት ቀጥተኛ (የተለመደ የታወቀ) የችግር አፈታት ሲሆን ኢ-ኦርቶዶክሳዊ (unorthodox) ማለት ደግሞ ከተለመደው ከታወቀው ወጣ ያለ የችግር አፈታት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ይህን ቃል አንዳንዶች ግትርነትን ወይም ለለውጥ ያልተዘጋጀ የሚለውን ለመግለፅም ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ይህ ግን በሂደት የመጣ የትርጉም መዛባት ተደርጎ ሊወስድ ይችላል፡፡

ተዋሕዶ (Miaphysite)

ተዋሕዶ የሚለው ቃል ከልሣነ ግእዝ የመነጨ ቃል ነው፡፡ ትርጒሙም  “አንድ ሆኖ” ማለት ነው። በዚህ ትርጉም ውስጥ አንድ የሆኑት መለኮታዊና ሰብዓዊ ባሕርይ (መለኮትና ትስብዕት) ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የተዋሕዶ ትርጓሜ በአጭሩ “ወልድ ዋሕድ” የሚለው ነው፡፡ ክርስቶስ ሰው የሆነው ያለሚጠት (ያለመመለስ)፣ ያለ ውላጤ (ያለ መለወጥ)፣ ያለ ቱሳኤ (ያለ መቀላቀል)፣ ያለትድምርት (ያለ መደመር)፣ ያለ ቡዓዴ (ያለመለያየት)፣ ያለ ኅድረት (ያለ ማደር) ነው፡፡ ክርስቶስ  ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል የሆነው  በተዋህዶ ነው፡፡  ስለዚህ ተዋሕዶ የሚለው ቃል ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ምስጢር የሚገልፅ ታላቅ ቃል ነው፡፡ ክርስቶስ ሰው የሆነው በ ተ ዋ ሕ ዶ ነው!

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Miaphysite)

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል ሆነ (ሥግው ቃል ነው) ብላ የምታምን ቀጥተኛና ትክክለኛ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ ይህም ነቢያት የተናገሩትን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ያስተማረውን፣  ሐዋርያት የሰበኩትን፣ ሊቃውንት ያመሠጠሩትን አስተምህሮ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ከሐዋርያት (ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች) በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈች ከእኛ ትውልድ ስለደረሰች ቀጥተኛ ናት፡፡ ያልተበረዘች ያልተለወጠች ያልተከለሰች ስለሆነችም ትክክለኛዋ እርሷ ናት፡፡

በማቴ 16፡16-18 ላይ “ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡- ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እነርሱም፡- አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት። እርሱም፡- እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፡- አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” ይላል፡፡

ተዋሕዶ (ወልድ ዋሕድ) የሚለው ይህንን የጴጥሮስን እምነት የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን እንዳረጋገጠው ይህች የጴጥሮስ እምነት ዓለት ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችንም በቀጥታ በዚህ እምነት/ዓለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትባለለች፡፡ ይህች ዓለት የምትለወጥ/የምትታደስ አይደለችም፡፡ ቤት ሲታደስ እንኳን መሠረቱ አይታደስም፡፡ ሃይማኖት መሠረት ነው፡፡ ምግባር ደግሞ ግድግዳና ጣሪያ ነው፡፡ ቤት ቢያረጅ ጣሪያና ግድግዳው እንጂ መሠረቱ አይታደስም፡፡ መሠረቱን ለማደስ መሞከር ቤቱን ሙሉ በሙሉ አፍርሶ እንደገና መሥራት ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (1ኛ ቆሮ 3:11)።” ይላል፡፡ በዚህ መሠረትነት ላይ የጸናች ሃይማኖት ሰውን ታድሳለች እንጂ እርሷ አትታደስም፡፡

የተዋሕዶ ምሳሌዎች (Examples of Miaphysite)

የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ፡- ነፍስና ሥጋ ተዋሕደው አንድ ሰው ይባላል እንጂ ሁለት አይባልም፡፡

የብረትና የእሳት ተዋህዶ፡- ብረት በእሳት ሲግል የጋለ ብረት እንጂ ይህ ብረት ነው፣ ይህ ደግሞ እሳት ነው ተብሎ አይለይም፡፡

የሲና ሐመልማል፡- እሳቱ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው፣ ሐመልማሉም እሳቱን ሳያጠፋው በአንድነት (በተዐቅቦ) መታየታቸው የተዋህዶ ምሳሌ ነው (ዘፀ 3፡2)፡፡

ይህንን አስተምህሮ የተቀበሉት (Miaphysite churches)

የተዋሕዶን (Miaphysite) አስተምህሮ የተቀበሉት ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ይባለሉ፡፡ እነዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)፡ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Eritrean Orthodox Tewahedo Church)፡ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Coptic Orthodox church)፡ የአርመንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Armenian Orthodox Church)፡ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና (Syrian Orthodox Church) የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Indian Orthodox church) ናቸው፡፡ እነዚህ  ጉባዔ ኬልቄዶንን የማይቀበሉ የምሥራቅ ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት በዶግማቸው አንድ ናቸው፡፡

አንዳንድ ወገኖች “ኦርቶዶክስ የሚል ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም::” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን በትንቢት “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን። አንሄድባትም አሉ (ኤር 6፡16)።” ይላል፡፡ በሐዲስ ኪዳንም “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው (ዕብ 13፡8)።” ይህ የሚያሳየው አንዲት ቀጥተኛ መንገድ/ሃይማኖት እንዳለች ነው፡፡ እርሷም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት

https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21

❤️መንፈሳዊ ህይወት(ሰው)❤️
ኃያሉ ሚካኤል
ዝማሬ ዘኦርቶዶክስ
✞ ኃይሉ ሚካኤል

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ለሶርያው ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባሉ ውስጥ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከዳር ወገን የሆነ በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው የጌታ መላዕክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት በዘር ፍሬ ባረካት

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዬን የተገለጠው
እስራኤልን ከምድር ረሀብ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

አንተ ጽኑ ሃያል ሰው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ ተልኪያለው ከጌታ
አይዞህ ጌድዮን ያለው ቁርባኑን ያሸተተው
ከኛ ጋር ነው ሚካኤል ሰልፋችንን ይመራል

አዝ


የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርና አውድማ ሰይፍን ይዞ ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

በ3 ቀን ቸነፈር እንዳትጠፋ ምድር
70ሺ ሰዎች ወድቀው መላዕኩ በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን ካአፎቱ ከቷል ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምኦን ጴጥሮስን ከወይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከጠባቂዎች መሃል ኬፋን ከእንቅልፉ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው ጰጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ ዘለለ ስሙን ጠርቶ

ዘማሪ
ገብረ-ዮሀንስ ገብረ-ጻድቅ

════◉❖◉═══◉❖◉═════
●❖
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱

"መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
መልአኮሙ ሥዩሞሙ
የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ

ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው እርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል።"

ቅዱስ ያሬድ

🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
       አሜን
🌸ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
    ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው።

❖ እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው፤ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው፤ የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ።

❖ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ፤ ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው።
❖ ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና።
❖ እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ።
❖ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ።

❖ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው።

❖ ከዚህም በኃላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፤ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው፤ በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ተገኘ።

❖ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ።

❖ በኋላኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፤ እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ፤ እርሱም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው፤ ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ፤ እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቁጠር ብዙ ነው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
የታወረ ትውልድ

ከእናቱ አፈንግጦ እምነት ወዲያ ብሎ በአለም የታለለ
በዚህ በእኔ ዘመን ልበ ስውር ወጣት እጂግ ብዙ አለ
ዶግማና ቀኖና መፈፀም ሲያቅተው በስጋው ሲታለል
ይችን ቅድስት እምነት መፍትሄ ነው ብሎ ትታደስ ይላታል
የመለውጥ ትርጉም ጠንቅቆ ያልገባው ልበ ስውር ጓዴ
በኃጢያት ያደፈ እሱነቱን ይዞ ትታደስ ይለኛል ያላረጀ ነገር ይታደሳል እንዴ?
እነዲዎስቆሮስ ፂም የተነጩላት የፀናች ሀይማኖት
ቆዳቸው እንደ ድንች በአህዛብ ጭካኔ ያኔ የተላጡላት
በሚያስፈራ እሳት ነጎድጓድ በላበት
ለኛ ያቆዩልን ህይወትን ሰውተው
ተዋህዶ እምነቴ ምኗ ነው ያረጀው
በሀጥያት አረንቋ የተቆሳቆለ እርሱ ተቀምጦ
ፍርሀት እንኳን አያውቅ ትታደስ ይለኛል ካፉ ቃል አውጥቶ
መላ በሉት'ማ ምከሩት ይህን ስው
የመታደስ ትርጉም ምን አልባት ቢገባው!!!

https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
​​​​​​††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††

ኅዳር ፲፪

†††"እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ"†††

#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት

➤ ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር።

➤ ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ፺፰ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል።

➤ ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል ክብርና ርኅሩኅ የለም። በምልጃውም፣ በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው።

➤ መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል። "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል። ቂም የሌለው ለምሕረት የሚፋጠን ደግ መልአክ ነውና።

➤ በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ፣ ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል። እስራኤልን ፵ ዘመን በበርሃ መርቷል፤ መግቧልም። ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል።

➣ “ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ።”
— ዘፍጥረት ፵፰፥፲፮

➣ “ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው? አለው።”
— መሳፍንት ፲፫፥፲፯

➣ “ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።”
— ዳንኤል ፲፥፳፩

➣ “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።”
— ዳንኤል ፲፪፥፩

➣ “በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”
— ራዕይ. ፲፪፥፯

➤ ደስ የሚለው ደግሞ ርኅሩኁ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው። ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ። ደስ ብሎት ይታዘዛታል።

➤ ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ።" ይላታል። ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን፣ በረከትን ያወርዳሉ።

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

✞✞✞"የመላኩ ቅዱስ ሚካኤል ጠብቆነት አይለየን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያማልደን።"✞✞✞

✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

📖ወስብሐት ለ እግዚአብሔ📖

📖✞✞✞✞✞📖


✞✞✞

✞✞✞✞✞✞✞

✞✞✞
Channel name was changed to «✝️መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)✝️»
አንድን አባት ሰዎች መጡና "ዘወትር ጸሎት በማድረግህ በሕይወትህ ላይ የጨመረልኽን ነገር ንገረን?" አሉት::

** እርሱ ግን "ጸሎት በማድረጌ ከጨመርኩት ይልቅ የቀነስኹት ይበዛልና እርሱን ልንገራችኹ፡፡
ጸሎት በማድረጌ ከሕይወቴ ውስጥ ጭንቀት፣ ፍርኃት፣ ተስፋ መቁረጥና ቁጡነትን ቀንሻለኹ" አላቸው፡፡
ጾመ ነቢያት

በመ/ር ቀሲስ ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት አሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ደግሞ ጾመ ነቢያት የነቢያት ጾም ነው፡፡ ይህም ነቢያት አምላክ ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት እየተናገሩ ሱባኤ እየቆጠሩ ያንን የተስፋ ቃል በመጠባበቅ የጾሙትን በማሰብ የምንጾመው ጾም ነው፡፡
በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጸች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ጾም ስታውጅ ነቢያትን ትንቢት ያናገርክ፣ የተስፋውን ቃል የሰጠህ አምላካችን ሆይ ለአባቶቻችን የሰጠሃቸውን ተስፋ ፈጽመህ አዳንከን፣ ሞታችንን ሞተህ ሕይወትን ሰጠኸን፣የጨለማውን ዘመን አስወግደህ የብርሃን ዘመን ዓመተ ምህረትን በቸርነትህ ሰጠኸን ብለን የእግዚአብሔርን ማዳን እየመሰከርን መጾም እንደሚገባ በማስተማር ነው፡፡
ያንን የጨለማ ዘመን፣ይልቅሶ ዘመን፣የመከራ ዘመን ብሉይ ኪዳንን በመወለድኅ በሐዲስ ኪዳን የተካህልን አስቀድመህ ቅዱሳን አበው፣ሱባኤ እንዲቆጥሩ ነቢያት ትንቢት እንዲናገሩና ሕዝብህን እንዲያጽናኑ አስቀድመህ የላክ አምላካችን ለአባቶቻችን በገባኃው ቃል መሠረት ጊዜውን እና ሰዓቱን ጠብቀህ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ተወለድክልን ሰው ሆነህም በአዲስ ተፈጥሮ አሮጌአችንን አስወግደህ አዲስ ሰው አደረከን በማለት እንጾማለን፡፡
ጸምንም ስንጾም የጾምን ትርጉምና ዓላማ አስቀድመን መማርና ማወቅ ያስፈልጋልና እነሆ…
ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ በአንድ ምዕራፍ ውስጥ አንቀጸ ምጽዋትን፣አንቀጸ ጸሎትን፣አንቀጸ ጾምን አያይዞ በሰፊው አስተምሯል፡፡በዚህም የምንማረው ምጽዋት፣ ጸሎት፣ጾም የማይለያዩ መሆናቸውን ነው፡፡ይህም ማለት እየጾምን መመጽወት እየጾምን መጸለይ ይገባል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱሳን አበው ጾምን የጸሎት እናት፣ የጽድቅ መሠረት፣የበጎነት ምንጭ እያሉ የገለጹአት፡፡ ጌታችንም ጾምን ስንጾም መጸለይና መመጽወት እንደሚገባ ካሳየን በኋላ እንዴት መጾምና ስንጾም እንዴት መሆን እንዳለብን ያስተማረውን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ግብዞች ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋእውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል እናንተ ግን ስትጦሙ .…ይልና ምን ማድረግ እንደሚገባ ይዘረዝራል፡፡

እሱም፡- 1ኛራሳችሁን ቅቡ(ተቀቡ) ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ ይደርባችሁ ፍቅርን ያዙ፡፡ማለት ሲሆን ፍቅረ እግዚአብሔር እና ፍቅረ ቢጽ ይኑራችሁ ማለት ነው፡፡

2ኛ ፊታችሁን ታጠቡ፡-ማለት ኃጢአታችሁን አስወግዱ፣ንስሓ ግቡ ማለት ነው፡፡

3ኛ በስውር ለሚያይ ለአባታችሁ እንጂ ለሰዎች እንደ ጾማችሁ እንዳትታዩ በስውር የሚያያችሁ አባታችሁም ዋጋችሁን በግልጥ ይሰጣችኋል፡፡ በማለት እውነተኛ ጾም እንዲኖረን አስተምሮናል፡፡

ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ጾም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያለውን ጥቅም ሲገልጽ “ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ፤ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች” ይላል (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)፡፡ የጾምንም ትርጉም ስንመለከት የሚያሳዩን ጥቅሙ ሰውን ለድኅነት ማብቃት እንደሆነ እንረዳለን ይህም ጾም ማለት:- ጾመ ፤ተወ፣ ታረመ፣ ተከለከለ ከሚል የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ጾም ከመባልዕት መከልከል ማለትም ለተወሰነ ሰዓት ከምግብ ተከልክሎ መቆየት እና ከጥሉላት ምግቦች ለአንድ ቀንም ሆነ ለሦስት ቀን፣ለሳምንት፣ ለሁለት ሳምንት ለወርና ለሁለት ወር ወዘተ በመታቀብ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ከላመ ከጣመ ምግብ መከልከል ማለት ነው፡፡ በዚህም ሁሉ ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ማስገዛት ነው፡፡ ጾም ሥጋን አድልበው ለፈቃደ ሥጋ ከሚገፋፋ ስሜት ተላቆ ፍትወተ ሥጋን አጥፍቶ ለፈቃደ ነፍስ ማደር እንዲቻል የመንፈስን ጥንካሬ ገንዘብ ማድረጊያ የጽድቅ መሣሪያ ነው፡፡

የጾም መሠረታዊው ዓላማም ሕዋሳትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያሬድ፡-“ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ኅሡም ዐይን ይጹም አንደበትም ይጹም ጆሮም ክፉ ከመስማት ይጹም ” በማለት የገለጸው(ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ) ፡፡

ስለዚህ ዓይን ክፉ ከማየት ተቆጥቦ የክርስቶስን መስቀል በመመልከት የእግዚአብሔርን ማዳን በመጠባበቅ ደጅ መጥናት መቻል፣ጆሮም ክፉ ከመስማት ርቆ መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ሲችል፣ እጅ ክፉ ከማድረግ ተቆጥቦ ለምጽዋት ሲዘረጋ፣የደከመውን ሲደግፍ የወደቀውን ማንሣት ሲችል
፣እግር ወደ አልባሌ ስፍራ ከመሄድ ይልቅ በቅድስና ስፍራው ተገኝቶ በእግዚአብሔር ፊት መንበርከክ
ሲችል፣ልብም ክፉ ከማሰብ ይልቅ በጎ በጎውን በማሰብ ለእግዚአብሔር የተከፈተ በር ለኃጢአት ግን
የተዘጋ በር ሆኖ ለእግዚአብሔር የሚመች መሆን ማለት ነው፡፡ እነዚህን ሕዋሳት ስም ጠቅሰን ዘረዘርናቸው እንጂ ሰው እንዚህን ከላይ የዘረዘርናቸውን ሁሉ መጠበቅ ሕዋሳቱን መግዛት ስሜቱን መቆጣጠር ሃይማኖታዊም ተፈጽሮአዊም ግዴታው ወይም ኃላፊነቱ ነው ፡፡

ጾም ከእግዚአብሔር ጋር ታስታርቃለች፡፡ “ወታጸምም ኩሉ ፍትወታተ ዘሥጋ፤ የሥጋ ፍልጎትን ሁሉ ታጠፋለች” የሥጋ ፍላጎት ደግሞ ኃጢአት ነው፡፡ እንዲሁም “ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና በወጣትነት ዕድሜ ያሉትን እግዚአብሔርን መፍራት ታስተምራቸዋለች” እንዲል ቅዱስ ያረድ፡፡

ጾም በበደል ምክንያት ከእግዚአብሔር የራቀን ሰው ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለች፡፡ ምክንያቱም ጾም እንዲሁ በልማድ ከእህልና ከውኃ ለተወሰነ ጊዜ ተከልክሎ መቆየት ብቻ ሳሆን ልማድነቱ ቀርቶ ፍጹም መጸጸት ያለበት ኃጢአትን በደልን እያሰቡ በጸሎት የእግዚአብሔርን ምህረት በመጠባበቅ በፍቅሩ ተማርኮ የሚጾሙት መሆን ሲቻል በእውነትም ከእግዚአብሔር ጋር መታረቂያ መንገድ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚያስችል የንስሓ ጉዞ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበጎ ምግባር መጀመሪያ ጾም እንደሆነ በመግለጽ በአብዛኛው በዓላቶቿን ከማክበሯ አስቀድማ ጾምን ታውጃለች እነዚህንም ለአብነት ያህል ጠቅሰን እንመለከታለን፡-

የትንሣኤን በዓል(ፋሲካን) ከማክበራችን አስቀድመን ዓቢይ ጾምን፣ ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስን በማሰብ በዓለ ዕረፍታቸውን ከማክበራችን አስቀድሞ ቅዱሳን ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ ሱባዔ እንደገቡና እንደ ጾሙ እኛም ጾመ ሐዋርያትን፣ የእመቤታችንን በዓለ ፍልሰት ከማክበራችን አስቀድሞ ቅዱሳን ሐዋርያት ዕረፍቷን ዓይተን ትንሣኤዋን ሳናይ ብለው ሱባኤ እንደ ገቡና እንደ ጾሙ እኛም በዓሏን ከማክበራችን አስቀድመን እንጾማለን፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ከማክበራችን አስቀድመን ቅዱሳን ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት እየተናገሩ ቅዱሳን አበው ሱባዔ እየቆጠሩ ሲጠብቁት እንደ ነበረ የተስፋው ፍጻሜ ሲደርስ በገባው ቃል መሠረት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የነቢያትም ትንቢት እንደፈጸመ እያሰብን ከበዓለ ልደት አስቀድመን እንጾማለን፡፡ በመሆኑም ጾምን የምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው ለዚህ ነው፡፡
ጾም የሕግ መጀመሪያም ነው፡፡ ይህንንም ሊቀ ነቢያት ሙሴ የሥነ ፍጥረትን ነገር በአስተማረበት መጽሐፉ እንደ ጠቀሰው እግዚአብሔር አምላክ በኤዶም በስተ ምሥራቅ ገነትን እንደ ተከለ እና የፈጠረውን ሰው በዚያ እንዳኖረው ገልጾ አድርግ እና አታድርግ ወይም ብላ እና አትብላ የምትል የጾም ሕግን እንደሰጠው ይናገራል፡፡

“እግዚአብሔር አምላክም አዳምን እንዲህ ብሎ አዘዘው በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና”(ዘፍ. ) በዚህም ቃል መሠረት ጾም ትእዛዘ እግዚአብሔር ፣ሕገ እግዚአብሔር፣እንደሆነና በጾም ሕግ ሕይወትና ሞት እንዳለ ተረዳን፡፡ ማለትም ጾምን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብለን ደስ ብሎን ብንጾም ሕይወትን እንደምናገኝ ሁሉ ጾምን እንደ ግዳጅ ወይም ግዳጅን እንደመወጣት መጾም ስላለብን ብቻ እና ስለ ታዘዝን ብለን ትእዛዝ ለመፈጸማችን ማረጋገጫ አድርገን ለይስሙላ የምንጾም ከሆነ ዋጋ የምናጣበት ነው፡፡ በሌላም መንገድ ጭራሹኑ የጾምን ሕግ በመጣስ ለጾም ያለን አመለካከት ዝቅተኛ ሆኖ ብንገኝ ሞትን እንደምንሞት ከእግዚአብሔር እንደምንለይ ከላይ የተመለከትነው በሙሴ መጽሐፍ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ያስረዳናል፡፡

በመጀመሪያ የጾምን አዋጅ ያወጀው የሁሉ ባለቤት የሆነው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህም “መልካሙንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ” ያለው ነው፡፡ ከዚህ ተነሥተው አበው ቅዱሳን፣ነቢያት ካህናት፣ሐዋርያት ሁሉ ጾምን ሰበኩ፡፡ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር የተለየውን ሰው በጾም ወደ እግዚአብሔር አቀረቡት፡፡ እግዚአብሔርም በጾም፣በጸሎት፣በምጽዋት፣በስግደት፣በፍጹም ፍቅር እና ትሕትና ሆነው ለተመለሱት ቁጣውን በትዕግሥት መዓቱን በምህረት ይመልሳልና አባታችን አዳም በጾም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመመለሱ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ገብቶለት ጊዜው ሲደርስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ አዳነው(ነገር ግን ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ የኦሪትንም ሕግ ፈጸመ”(ገላ.፬፥፬)እንዲል፡፡

የነነዌ ሕዝቦችም እንዲሁ በነቢዩ ዮናስ ስብከት በጾም በጸሎት በንስሓ ወደ እግዚአብሔር በመመለሳቸው ከተቃጣባቸው መዓት ዳኑ(ዮና.፫፥፩ )፡፡ ሌሎችም በዚህ ክፍል ያልጠቀስናቸው ብዙዎች በጾም በጸሎት የእግዚአብሔር ምህረት ተደርጎላቸዋልና ጾም ሰውና እግዚአብሔር የሚታረቁባት ደገኛ ሕግ ናት፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ ኢዩኤል “በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ ምህላንም ዐውጁ”(ኢዩ. በማለት ለጾም ልዩ ፍቅር እንዲኖረን እና ስንጾም በደስታ ሆነን የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ሞልቶ ምስጋናውን እያቀረብን መሆን እንዳለበት ያስረዳናል፡፡

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም “ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ” (መዝ.109፡24)ይላል፡፡ ዳንኤልም “ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስት ሳምንትም እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም”(ዳን.10፡3) ይላልና ጾምን ጾመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ እንድናገኝ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡አሜን
❤️አንዳንድ ሰዎች የተለየ የህይወት ጫወታ ይጫወታሉ፤ ሁሌም በህብረተሰቡ ዉስጥ የሚነገረን ሰዉ ስኬታማ ለመሆን ተምሮ ፡ዲግሪ ይዞ ፡አግብቶ ጥሩ ስራ ይዞ መኖር እንዳለበት ነዉ፡፡ ግን ህይወትን በሌላ ትምህርት፡ በሌላ ዲግሪ፡ በሌላ ስራ ይተዋወቋታል

♦️ የሆነ ነገር ለማግኘት በፈለክ ቁጥር የበለጠ እየራቀህ ይሄዳል፡፡ በህይወቴ ከተረዳሁት ነገር ዉስጥ የፈለኩት ነገር ጥሎኝ ሲሄድ አይቻለሁ፡፡

💙 ሰዎች ህይወታቸዉን ሊያደላደሉ ሲጥሩ አያለሁ፡፡ ቦታ ካስያዙት በኋላ ሁሉም ነገር ወደነሱ እንደሚመጣ ያስባሉ ነገር ግን ይህ በገሃዱ አለም የማይሆን ነገር ነዉ፡፡

🔶 ሰዎች የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን አስተዉል፡፡ ሰዎች አቁስለዉኛል ምክንያቱም ተግባራቸዉን አተኩሬ ጊዜ ስላልሰጠሁት ዉስጤን አደሙት!

🔷 ከሚሰጡት በላይ የሚቀበሉ ሰዎችን አትታገሳቸዉ፡፡ ከሚጠቅሙበት ነገር በበለጠ የሚጎዱበት ማንነታቸዉ የጎላ ሰዎችን ከህይወትህ ካላወጣሃቸዉ ውስጥህን እንደ'ብል'ይበሉታል

🔶 ብዙ መሰናክሎች እራስህ የምትፈጥራቸዉ ናቸዉ፡፡ ማህበረሰቡ፣ ጓደኞቼ ወይም ቤተሰቦቼ መሰናክል እንደሆኑብኝ አምን ነበር ግን በመስታወት የማየዉ ማንነቴ እርስ በእርሱ ተሰነካክሏል፡፡

🔶 ህይወት አጭር ናት፡፡ ሞት ደግሞ የማይቀር ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህን ማሰብ ላትፈልግ ትችላለህ ግን አንድ ቀን ትሞታለህ፡፡ አንተ ብቻ ሳትሆን የምታየዉ ሰዉ ሁሉ ቀኑን ጠብቆ ይሞታል፡፡ ስለዚህ ሕይወትህን እስከ እንጥፍጣፊዋ ድረስ ኑርባት!
┉┉✽̶»̶̥ĵøïņ✿śĥăŕę»̶̥✽̶┉┉
@ መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)