መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
☞ ተሐድሶ
የሌሊት ወፍ ሁለት ግብር አለው
1 እንደወፎች ክንፍ አለው ይበራል ይከንፋል
2 እንደ አይጦች ጥርስ አለው ይነክሳል
የሌሊት ወፍ ግን ክንፍም ጥርስም አለው
በሁለት ግብር ይመላለሳል
በጥርሱ ሲታይ አይጥ መስሎ ይታያል
በክንፉ ሲታይ ወፍ ይመስላል
ለልማዱ ወፎች ክንፍ እንጂ ጥርስ የላቸውም
አይጦች ደግሞ ጥርስ እንጂ ክንፍ የላቸውም
ይህ የሌሊት ወፍ ግን ሁለቱንም የያዘ ነው ጠባዩ አይታወቅም ይቀያየራል ስሙም የሌሊት ወፍ የተባለው ጨለማውን ተገን አድርጎ የአይጥነትንና የወፍነትን ስራ ስለሚሰራ ነው በቀን አይበርም ጨለማ ይፈልጋል
ተሐድሶም ልክ እንደሌሊት ወፍ ነው
1 ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መስሎ ይታያል
2 ለፕሮቴስታንት ደግሞ ተሀድሶ ሁኖ ይታያል
ከኦርቶዶክሶች መሀል ሲፈለግ ይገኛል
ከተሀድሶዎችም መሀል ሲፈልግ ስራ አስፈፃሚ ሁኖ ይገኛል ተሃድሶ ሃይማኖት የለውም ሃይማኖት ቢኖረውማ ከዛም ከዛም አይረግጥም ነበር
ወፉ ጨለማ ለብሶ ስራውን እንሚሰራ ተሀድሶም ጨለማ ለብሶ ቤት ለቤት እየተሰበሰበ የክደት ተግባሩን ያከናውናል
ቀን ሲያዩት ቀሚስ ለብሶ ካባ ደርቦ ሻሽ አምሞ ነጠላ ለብሶ እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ብሎ በተዋህዶ በረት ይገኛል ሌሊት ግን ስራው ሌላ ነው
የሌሊት ወፍ መልኩ ሁለት አይነት እንደሆነ ተሀድሶም ከሁለቱ ቤት ይገኛል ከተዋህዶ አለው ይላል ለፕሮቴስታነት ይሰራል የሌሊት ወፍ በሩቅ ሲያዩት ወፍ ይመስላል ሲቀርቡት ግን ጥርስ አለው ይነክሳል
ተሀድሶም በላይ ሲያዩት የተዋህዶን ልብስ ለብሶ ሃይማኖት ያለው ይመስላል ሲቀርቡት ግን የተሀድሶንት ግብሩን ገልጦ ሲክድ ይገኛል በክደቱም ብዙ ሰዎችን ይጎዳል የሌሊት ወፍ ከሰውነቱ የሚፈሰው ፈሳሹ መርዝ ነው የተሀድሶም ትምህርቱ ነፍስን የሚገድል የክህደት መርዝ ነው
የሌሊት ወፍ በጭስ ታፍኖ ይገደላል
ተሀድሶንም በሃይማኖት ጭስ አፍኖ ድምጥማጡን
ማጥፋት ነው
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

መራራ እና ከፍቅር የራቀ አሳሳቢ ሁኔታ ለይ ነዎት? እንግስያውስ የሚያነቡት ❤️የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች❤️

💜(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ.13)💜

1፤ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

2፤ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

3፤ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

4፤💜 ፍቅር ይታገሣል፥ 💛ቸርነትንም ያደርጋል፤ 💚ፍቅር አይቀናም፤ 💙ፍቅር አይመካም፥ ❤️አይታበይም፤

5፤❤️ የማይገባውን አያደርግም፥💛 የራሱንም አይፈልግም፥ 💙አይበሳጭም፥ 💚በደልን አይቆጥርም፤

6፤ 💚ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤💚

7፤ 💜ሁሉን ይታገሣል፥ 💛ሁሉን ያምናል፥ 💚ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥💙 በሁሉ ይጸናል።

8፤ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን #ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ# ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን #ይሻራል

13፤ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው💛 ፍቅር ነው💛

https://t.me/linkortodoxe21
✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️
ሃጥያትዎ በዝቶ ሰላም ሲነሳዎት(ወደ አምላክዎ ለመመለስ)እነዚህን የመጽሃፍቅዱስ ጥቅሶች ያንብቡ(ይጸልዩም)

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 51)
1፤ አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን #ደምስስ
2፤ ከበደሌ ፈጽሞ# እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም #አንጻኝ
3፤ እኔ መተላለፌን #አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
4፤ አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።
7፤ በሂሶጵ እርጨኝ፥ ♥️እነጻማለሁ፤♥️ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ♥️ ነጭ እሆናለሁ።♥️
8፤ ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።
9፤ ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ #ደምስስልኝ
10፤ አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ 🔶የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።🔶
11፤ ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
12፤ የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።
13፤ ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።
14፤ የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።
15፤ አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።

♥️(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 1)♥️

4፤ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
5፤ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር 🔶ብርሃን🔶 ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
6፤ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም 🔶አናደርግም፤🔶
7፤ ነገር ግን እርሱ ♥️በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ♥️ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ 💙ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።💙
8፤ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን #እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
9፤ በኃጢአታችን $ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም❤️ ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ❤️

https://t.me/linkortodoxe21
የፍርሃት ስሜት ሲደርስቦ የሚያነቧቸው የመጽሃፍ ቅዱስ ቃላት

💜(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 34)💜

4፤ እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ #አዳነኝ
5፤ ወደ እርሱ ቅረቡ #ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም 💛አያፍርም።💛

💙(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 10)💙

28፤ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን #አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን #ፍሩ

29፤ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ $ያለ #አባታችሁ #ፈቃድ #በምድር $ላይ #አትወድቅም
30፤ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ #ተቈጥሮአል
31፤ እንግዲህ ❤️አትፍሩ❤️ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ #ትበልጣላችሁ

" እግዚአብሔር #የኃይልና ❤️የፍቅር❤️ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ #የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።"
💚(2ኛ ወደ ጢሞ 1፥7)💚

💛(ወደ ዕብራውያን ምዕ. 13)💛

5፤ አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ #መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም #ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። ❤️አልለቅህም ከቶም አልተውህም❤️ ብሎአልና፤
6፤ ስለዚህ $በድፍረት። ጌታ #ይረዳኛልና #አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።

https://t.me/linkortodoxe21
ፈተና

" ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13)
ውጣ ውረድ ፈተና

" በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።
"
(የዮሐንስ ወንጌል 16:33)
እኔ አላይም ካንተ ሌላ
ዞር ብዬ ወደ ኋላ
ኪዳን ገባው ከአምላኬ ጋር
ይሻለኛል ቤትህ መኖር



ማራኪ ነህ እውነተኛ
የማትደክም የማትተኛ
በችንካርህ ስበሀኛል
እንዳንተ ያለ ከየት ይገኛል

ድንጋይ ነበር የኔ ደሞዝ
በዚህ አለም ስቅበዘበዝ
ነጻ ወጣው ባንተ ፊት
እልሃለው መድሃኒት

አመጸኛ ወንበዴ ነኝ
የአለም ውበት የማረከኝ
እንዴት ብለህ ወደድከኝ
አሸነፍከኝ ደነከኝ

ወንበር ስበህ አሳረፍከኝ
ቤትህ ገባው ስትፈልገኝ
አልገባኝም ገና ፍቅርህ
በዘመኔ የምማርህ

https://t.me/linkortodoxe21
+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ብዙ መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ‹ምስጋና የሚገባውን› እግዚአብሔርን ሳታቋርጥ የማመስገን አገልግሎትዋ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለዓመታት የዜማ ስልት ተምረው የተመረቁ የስብሐተ እግዚአብሔር ሊቃውንት ያሏት ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝማሬዋ ፣ ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ የሃያ አራት ሰዓታት ጊዜ የማይበቃው ፣ ለሰዓት ሲባል በንባብ እየተባለ ፣ ዜማው እያጠረ የሚተው በመሆኑ ፀሐይ በማይጠልቅበት በዘላለማዊው መንግሥት ለማመስገን ዝግጁ ሆና የምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን ያሰኛታል፡፡ ከዚህ እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው ስብሐተ እግዚአብሔር ጋር የእግዚአብሔር ቅዱሳንንም በሰፊው ታመሰግናቸዋለች፡፡
በዚህች አጭር ጽሑፍ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው እግዚአብሔር ከሆነ ፍጡራን ለሆኑ ለቅዱሳን ሰዎች ፣ ለቅዱሳን መላእክትና ለድንግል ማርያም የሚዘመረው መዝሙርና የሚቀርበው ውዳሴ ምን ያህል ተገቢ ነው? ለቅዱሳን መዘመር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሳስብ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደር ያልተገኘለትን ዘማሪ ለመጠየቅ ወደድኩ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ መቶ አምሳ መዝሙራት የተጻፉለት ፣ ራሱ ሰማኒያ ሰባት መዝሙራትን የዘመረና በሥሩ ያሉ መዘምራን ደግሞ አብረውት ብዙ መዝሙራትን የዘመሩበት የዝማሬ ባለ ጠጋ ንጉሥ ዳዊትን ‹‹እውነት ለፍጡራን ምስጋና ይገባል ወይ?›› ብዬ ልጠይቀው አስቤ ወደ መዝሙረ ዳዊት ገሰገስኩ፡፡
ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡
ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?
ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡
ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡
የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡
በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡
በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ ተነሥተን ነው፡፡
ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤ መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል› ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው
፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ?
ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።
የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡
አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ. ፲፫፥፵፫)
‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3)
‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡ (2ነገሥ. 1፡13)
በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር አያጡም፡፡ ሆኖም ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡
ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-
‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡14)
አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ ‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)
ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ› ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)
የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡
ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣ "ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)
ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-
ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14)
የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን? የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?
እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል አይደለም።
ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎ
ስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡
ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ 26:13)
ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :–
"ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2: 7
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
1. ማቶዎስ = #በሰው ገጽ ተመስሏል፣ የክርስቶስን በስጋ ከአብርሃም ከዳዊት መምጣት ልደቱን በመዘርዘር አስረድቷልና፥፥

2. ማርቆስ = #በአንበሳ ተመስሏል፣ ግብጽ የነበሩትን የአንበሳ ጣኦታት በስብከቱ አፍርሶ አንበሳ የተባለ ክርስቶስን ሰብኳልና፥፥

3. ሉቃስ = #በላም ገጽ ይመሰላል፣ ጌታ ኢየሱስ በከብቶች ማደርያ መወለዱን ከሌሎች ይልቅ አስፍቶ ስለጻፈ፥፥

4. ዮሃንስ = #በንስር ይመሰላል፣ ንስር ከሌሎች አእዋፍ ሁሉ ተለይቶ ወደ ላይ መጥቆ ይበራል። በላይም ሆኖ በመሬት ያሉትን ረቂቃን ነገሮች አጣርቶ መመልከት ያውቅበታል። ወንጌላዊው ዮሃንስም ከሌሎች ወንጌላውያን አጻጻፍ በተለየ በምስጢረ ስላሴ ይጀምርና ስለ ተዋህዶም ሲጽፍ ወደ ላይ መጥቆ በማሰብ ቅድመ ዓለም ስለነበረው ቃል ይተርክና ዝቅ ብሎ "ያም ቃል ስጋ ሆነ" በማለት ይጽፋል።

https://t.me/linkortodoxe21
ወንጌል.pdf
11.9 MB
#የአራቱ_ወንጌላት አንድምታ ትርጓሜ

ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሃንስ

https://t.me/linkortodoxe21
ኦርቶዶክስ (Orthodox)

“ኦርቶዶክስ” የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን የተቀናበረው “ኦርቶ” እና “ዶክስ” ከሚሉት ሁለት ቃላት ነው፡፡ትርጉማቸውም ኦርቶ ማለት ቀጥተኛ: ትክክለኛ ማለት ሲሆን ዶክስ ማለት ደግሞ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ በአንድነት ሲሆኑ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ፡ ትክክለኛ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡

ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባዔ ነው፡፡ በኒቅያ “ወልድ ፍጡር ነው” የሚለውን የአርዮስን የክህደት ትምህርት ለማውገዝና ሃይማኖታቸውን ለማፅናት የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንት ይህን ቃል የተጠቀሙት  ሐዋርያት  ያስተማሯት ሃይማኖት ቀጥተኛና ትክክለኛ ናት ለማለት ነው፡፡ ሌሎች እንደ አርዮስ ክህደት ያሉት በየዘመኑ የሚነሱት ልዩ ልዩ አዳዲስ ትምህርቶች የምንፍቅና መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይህችን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ  ብለዋታል፡፡

በዘመናችን የቋንቋ አጠቃቀምም  ኦርቶዶክሳዊ መንገድ (orthodox) ማለት ቀጥተኛ (የተለመደ የታወቀ) የችግር አፈታት ሲሆን ኢ-ኦርቶዶክሳዊ (unorthodox) ማለት ደግሞ ከተለመደው ከታወቀው ወጣ ያለ የችግር አፈታት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ይህን ቃል አንዳንዶች ግትርነትን ወይም ለለውጥ ያልተዘጋጀ የሚለውን ለመግለፅም ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ይህ ግን በሂደት የመጣ የትርጉም መዛባት ተደርጎ ሊወስድ ይችላል፡፡

ተዋሕዶ (Miaphysite)

ተዋሕዶ የሚለው ቃል ከልሣነ ግእዝ የመነጨ ቃል ነው፡፡ ትርጒሙም  “አንድ ሆኖ” ማለት ነው። በዚህ ትርጉም ውስጥ አንድ የሆኑት መለኮታዊና ሰብዓዊ ባሕርይ (መለኮትና ትስብዕት) ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የተዋሕዶ ትርጓሜ በአጭሩ “ወልድ ዋሕድ” የሚለው ነው፡፡ ክርስቶስ ሰው የሆነው ያለሚጠት (ያለመመለስ)፣ ያለ ውላጤ (ያለ መለወጥ)፣ ያለ ቱሳኤ (ያለ መቀላቀል)፣ ያለትድምርት (ያለ መደመር)፣ ያለ ቡዓዴ (ያለመለያየት)፣ ያለ ኅድረት (ያለ ማደር) ነው፡፡ ክርስቶስ  ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል የሆነው  በተዋህዶ ነው፡፡  ስለዚህ ተዋሕዶ የሚለው ቃል ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ምስጢር የሚገልፅ ታላቅ ቃል ነው፡፡ ክርስቶስ ሰው የሆነው በ ተ ዋ ሕ ዶ ነው!

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Miaphysite)

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል ሆነ (ሥግው ቃል ነው) ብላ የምታምን ቀጥተኛና ትክክለኛ እምነት/ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ ይህም ነቢያት የተናገሩትን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ያስተማረውን፣  ሐዋርያት የሰበኩትን፣ ሊቃውንት ያመሠጠሩትን አስተምህሮ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ከሐዋርያት (ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች) በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈች ከእኛ ትውልድ ስለደረሰች ቀጥተኛ ናት፡፡ ያልተበረዘች ያልተለወጠች ያልተከለሰች ስለሆነችም ትክክለኛዋ እርሷ ናት፡፡

በማቴ 16፡16-18 ላይ “ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡- ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እነርሱም፡- አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት። እርሱም፡- እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፡- አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” ይላል፡፡

ተዋሕዶ (ወልድ ዋሕድ) የሚለው ይህንን የጴጥሮስን እምነት የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን እንዳረጋገጠው ይህች የጴጥሮስ እምነት ዓለት ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችንም በቀጥታ በዚህ እምነት/ዓለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትባለለች፡፡ ይህች ዓለት የምትለወጥ/የምትታደስ አይደለችም፡፡ ቤት ሲታደስ እንኳን መሠረቱ አይታደስም፡፡ ሃይማኖት መሠረት ነው፡፡ ምግባር ደግሞ ግድግዳና ጣሪያ ነው፡፡ ቤት ቢያረጅ ጣሪያና ግድግዳው እንጂ መሠረቱ አይታደስም፡፡ መሠረቱን ለማደስ መሞከር ቤቱን ሙሉ በሙሉ አፍርሶ እንደገና መሥራት ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (1ኛ ቆሮ 3:11)።” ይላል፡፡ በዚህ መሠረትነት ላይ የጸናች ሃይማኖት ሰውን ታድሳለች እንጂ እርሷ አትታደስም፡፡

የተዋሕዶ ምሳሌዎች (Examples of Miaphysite)

የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ፡- ነፍስና ሥጋ ተዋሕደው አንድ ሰው ይባላል እንጂ ሁለት አይባልም፡፡

የብረትና የእሳት ተዋህዶ፡- ብረት በእሳት ሲግል የጋለ ብረት እንጂ ይህ ብረት ነው፣ ይህ ደግሞ እሳት ነው ተብሎ አይለይም፡፡

የሲና ሐመልማል፡- እሳቱ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው፣ ሐመልማሉም እሳቱን ሳያጠፋው በአንድነት (በተዐቅቦ) መታየታቸው የተዋህዶ ምሳሌ ነው (ዘፀ 3፡2)፡፡

ይህንን አስተምህሮ የተቀበሉት (Miaphysite churches)

የተዋሕዶን (Miaphysite) አስተምህሮ የተቀበሉት ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ይባለሉ፡፡ እነዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)፡ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Eritrean Orthodox Tewahedo Church)፡ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Coptic Orthodox church)፡ የአርመንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Armenian Orthodox Church)፡ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና (Syrian Orthodox Church) የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Indian Orthodox church) ናቸው፡፡ እነዚህ  ጉባዔ ኬልቄዶንን የማይቀበሉ የምሥራቅ ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት በዶግማቸው አንድ ናቸው፡፡

አንዳንድ ወገኖች “ኦርቶዶክስ የሚል ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም::” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን በትንቢት “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን። አንሄድባትም አሉ (ኤር 6፡16)።” ይላል፡፡ በሐዲስ ኪዳንም “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው (ዕብ 13፡8)።” ይህ የሚያሳየው አንዲት ቀጥተኛ መንገድ/ሃይማኖት እንዳለች ነው፡፡ እርሷም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት

https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21

❤️መንፈሳዊ ህይወት(ሰው)❤️
ኃያሉ ሚካኤል
ዝማሬ ዘኦርቶዶክስ
✞ ኃይሉ ሚካኤል

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ለሶርያው ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባሉ ውስጥ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከዳር ወገን የሆነ በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው የጌታ መላዕክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት በዘር ፍሬ ባረካት

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዬን የተገለጠው
እስራኤልን ከምድር ረሀብ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

አንተ ጽኑ ሃያል ሰው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ ተልኪያለው ከጌታ
አይዞህ ጌድዮን ያለው ቁርባኑን ያሸተተው
ከኛ ጋር ነው ሚካኤል ሰልፋችንን ይመራል

አዝ


የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርና አውድማ ሰይፍን ይዞ ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

በ3 ቀን ቸነፈር እንዳትጠፋ ምድር
70ሺ ሰዎች ወድቀው መላዕኩ በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን ካአፎቱ ከቷል ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምኦን ጴጥሮስን ከወይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከጠባቂዎች መሃል ኬፋን ከእንቅልፉ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው ጰጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ ዘለለ ስሙን ጠርቶ

ዘማሪ
ገብረ-ዮሀንስ ገብረ-ጻድቅ

════◉❖◉═══◉❖◉═════
●❖
https://t.me/linkortodoxe21
https://t.me/linkortodoxe21
💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱💫🌱

"መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
መልአኮሙ ሥዩሞሙ
የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ

ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው እርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል።"

ቅዱስ ያሬድ

🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
       አሜን
🌸ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
    ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው።

❖ እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው፤ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው፤ የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ።

❖ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ፤ ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው።
❖ ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና።
❖ እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ።
❖ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ።

❖ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው።

❖ ከዚህም በኃላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፤ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው፤ በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ተገኘ።

❖ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ።

❖ በኋላኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፤ እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ፤ እርሱም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው፤ ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ፤ እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቁጠር ብዙ ነው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።