መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ክፉ ሰው ክፋትን ለመስራት ደፍሮ ሲሄድ መልካም ሰው በጎ ነገር ለማድረግ ፈሪ ሆነ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚወመራ ነዉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ዓብይ ጾም››

ጾም የቃሉ መሠረታዊ ትርጉም መታቀብ መከልከል ማለት ነው በቤተክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ጾም ማለት የሰው ልጅ ሕይወቱን ለሰጠው የሕይወትን መመሪያ ላዘጋጅለት ፈጣሪ እየታዘዘ ኃጢዓትን ለማስተሰረይ የምኞት ፍትወትን ኃይል አድክሞ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ትገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መጠጥ በመከልከልና የመንፈስ ብርታት ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው::

ጾም ጸሎት ምጽዋት የተያያዙ የሥነ ምግባር ሰንሰለቶች ስለሆኑ በተግባር ተጠብቀው ሲተረጎሙ የእኛንም ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እንደምናነበው አበው ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት ሲያስቡና ሲያቅዱ፣ ሲጀምሩና ሲፈጽሙ በጾም በጸሎት ነው፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ›› እንዲል (ኤፌ 6፡10) የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር የተባሉ መሣሪያዎች ጾም፣ ጸሎት ፣ ምጽዋት አጠንክሮ የሚጠቀምባቸው ክርስቲያን የችግርን ጊዜ የማለፍ ኃይል ይኖረዋል፡፡

ጸሎት እምነት እንዲለመልም እንዲፋፋ እንዲያፈራ ይረዳል፣ ጾም ደግሞ እምነትን ጸሎትን እያጠናከረ ብዙ ድንቅ ሥራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡

ጾም ነፍስን በእግዚአብሔር ፊት ትሑት ያደርጋል የሥጋን ፈቃድ አስገዝቶ ነፍስ እንድትነፃ እንድትቀደስ አቋሟን እንድታስተካክል ይረዳታል ጾም ለነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋ ሕይወትም ለሆድ ዕቃዎች (ለሰውነታችን) የውስጥ የምግብ ማዘጋጃ ክፍሎች ዕረፍትን ይሰጣል ጾም ትሑትና ቅን ያደርጋል በሥጋዊ ፍላጎቶቻችን ፈቃዶቻችን ላይ አዛዦች መሆናችንን ያረጋግጥልናል፡፡

ጾም ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ተቃራኒ በሆኑ ርኩሳን መናፍስትና በአጋንንት ላይ ኃይል እንድናገኝ ከፈተናዎች እንድንድን ይረዳል ክህደትን ጥርጥርን ያጠፋል እምነትንና በእምነት የምንሰራቸውን ሥራዎች ያጠናክራል የጥበብን መንገድ የሕይወትን ጎዳና ይገልፃል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትና ድንጋጌ (የሕግ ምንጭ) በሆነው ፍትሐ ነገሥት ስለጾም በተመለከተው አንቀጽ እንደተገለጸው ጾም

_ ጾመ ሕግ

_  ጾመ ፈቃድ ተብሎ በሁለት ይከፈላል

ጾመ ሕግ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ የኒቂያ ጉባኤ ሊቃውንት አበው በወሰኑት መሠረት ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ የተመለከቱትና ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲጾሟቸው የታዘዙት አፅዋማት ሰባት ሲሆኑ

ዐብይ ጾም

ጾመ ድህንት (ረቡዕና ዓርብ)

ጾመ ነነዌ

የልደትና ጥምቀት (ጋድ/ገሐድ ጾም)

የሐዋርያት (የሰኔ) ጾም

የነቢያት (የገና) ጾም

የፍልሰታ ጾም ናቸው

እነዚህ አጽዋማት የየራሳቸው የሆነ ታሪክና ትንታኔ ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም ያለ ልዩነት በሁሉም ክርስቲያኖች በይፋ በማህበር እንዲጾሙ የተወሰኑ ናቸው፡፡

ጾመ ፈቃድ በግል ውሳኔ በኀጢዓት ስሜት የሻከረ ኅሊናን ለማጥራት ወይም ቅድስናን ጸጋና የበለጠ መንፈሳዊ ክብር ለማግኘት በመምህረ ንስሐ አማካኝነት አለዚያም ብቻ ለብቻ በሥውር አይቶ በግልፅ የሻቱትን ለሚሰጥ አምላክ የሚቀርብ ነው፡፡

ከሕግ አጽዋማት መካከል በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቢያተ ክርስቲያናት እምነትና ሥርዓት በየአመቱ ከሚመላለሱት አጽዋማት ዋናውና ትልቁ ጾመ ሁዳዴ (አብይ ጾም) ነው፡፡

ይህንን ጾም የምንጾመው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን  አብነትና አርአያ አድርገን ነው:: አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ በመሄድ ከቆመ ሳይቀመጥ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ እህል ውሃ ሳይቀምስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ የዚህ ዓለም ተፈታታኝ የሆነ ዲያብሎስን ከነፈተናው ድል ነስቶታል፡፡ በስስት ፣ በትዕቢት፣ በፍቅረ ንዋይ የመጣውን ፈተና አጥፍቶ የኃጢዓትን እሾህ አቃጥሏል፡፡

–    ስስት ያልተሰጡትን መሻት የሌሎችን ድርሻ በይበልጥ ለመሻማት መሞከር

–    ትዕቢት አምላክ እሆናለሁ ማለት በሌሎች ላይ ታላቅነትን፣ የበላይነትን መመኘት

–    ፍቅረ ንዋይ ያለኝ ይበቃኛል አለማለት በተሰጡት አለማመስገን ነው
እነዚህ ሦስቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ይባላሉ፡፡ እያንዳንዳችን የልቡናችን በር ከፍተን እንደገና ካላስገባናቸው በቀር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ተወግዷል

ሀ/ ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ

እርሱ ሠራዔ ህግ (ህግን የሠራ) ነውና፣ ሕግንና ነቢያትን ያጸና ዘንድ አንድም ሕግን ይሠራ ዘንድ ጾምን የሥራው መጀመሪያ አደረገ

አንድም ለሐዋርያት ለሊቃውንት እንዲሁም ከዚያ በኋላ ለሚነሱት ክርስቲያኖች ሁሉ አርአያና ምሣሌ አብነትም ለመሆን 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ሥራ ጀምሯል፡፡ ከዚያ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ከእርሱ በተማሩት መሠረት የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ጾምን ነው፡፡ (ሐዋ 13፡1)

መብል ለኃጢዓት (ለጥንተ አብሶ) መሠረት በመሆኗ በመብል ምክንያት ኃጢዓት ወደ ዓለም መጥቷልና፣ በመብል ምክንያት ወደ ዓለም የገባው ኃጢዓትና ኃጢዓት ያስከተለው ሞት ከሥራቸው ተነቅለው ተደምስሰው፣ የጠፋው የሰው ሕይወት የታደሰው በጌታችን ጾም ነው:: ሰው በሥጋዊ መብልና መጠጥ ብቻ ሰውነቱ የሚያምር በጾም የሚጠወልግ የሚጎዳ እየመሰላቸው ጾምን የሚፈሩት የሚሸሹት ጥቅም እንደማይሰጥ ሰው ሰራሽ ሥርዓት አድርገው የሚመለከቱትም ብዙ ናቸው፡፡ አስተዋዮች ግን ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃለ እግዚአብሔር ጭምር እንጂ በእህል ውሃ ብቻ ሊኖር እንደማይችል ጠንቅቀው አውቀው እየጾሙ ይጠቀሙበታል አስፈላጊም በሆነ ቦታና ጊዜ ከማይፈለግ ጮማና ወይን ይልቅ ጥራጥሬ ተመግቦ መውዛት ማማር እንደሚኖር ከሶስቱ ወጣቶች (አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል) ታሪክ መማር ይቻላል፡፡ (ዳን 1፡8-16)

ምሳሌው ይደርስ ዘንድ (ለጊዜው)

ቀድሞ አባቶቹ ነቢያት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመዋል ከዚያ ቢያተርፍ አተረፈ ብለው ቢያጎድል አጎደለ ብለው አይሁድ ደገኛይቱን ሕግ ሕገ-ወንጌል ከመቀበል ይከላከሉ ነበር፡፡

‹‹እኔ ሕግና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም›› ብሏልና (ማቴ 5፡17) ሕግና ሥርዓትን እየፈጸመ ከሕግ በታች ሆኖ ተመላለሰ

ሀ/ ሙሴ በአርባ ዘመኑ ለዕብራዊው ወገኑ አግዞ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ ቀብሮታል (ዘጸ 2፡11) ሙሴ የወልድ እግዚአብሔር፣ ዕብራዊው ወገኑ የአዳም ፣ ግብጻዊው የዲያብሎስ፣ አሸዋው የመስቀል ምሳሌ ነው፡፡

ሙሴ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ እንደቀበረ ጌታችንም ጾሞ ጸልዮ ዲያብሎስንና ፈተናዎቹን ድል ነስቷል፡፡

ለ/ ሙሴ 40 ዘመን በምድያም ኖሮ እስራኤልን ከግብፅ የባርነት ቀንበር ነፃ አውጥቷል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም እንጂ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ነፍሳትን ከሲኦል ነጻ ያወጣልና

ሐ/ ሕዝበ እስራኤል የገዳም ምሳሌ በሆነው በቃዴስ በረሃ 40 ዘመን ኖረው ምድረ ርሥት ኢየሩሳሌም ገብተዋል፣ (ዘጸ 14፡19 ፣ 32፡34) እናንተም 40 ቀንና 40 ሌሊት ብትጾሙ ርስት መንግስተ ሰማያትን ትወርሳላችሁ (ዘጸ 16፡4-17)

መ/ ሙሴ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ለሕይወታችን መመሪያ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉ አስርቱ ቃላት ያለባቸው ጽላቶች ተቀብሏል፡፡ ሕገ – ኦሪትን ሠርቷል (ዘጸ 34፡28)

ኢየሱስ ክርስቶስም እንጂ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸሊዮ ሕገ-ኦሪትን አጽንቶ ደገኛይቱን ሕግ ህገ-ወንጌልን (ስድስቱን ቃላተ ወንጌል) ሠርቷል፡፡

#join #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

#መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
መንፈሳዊ ህይወት pinned «ዓብይ ጾም›› ጾም የቃሉ መሠረታዊ ትርጉም መታቀብ መከልከል ማለት ነው በቤተክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ጾም ማለት የሰው ልጅ ሕይወቱን ለሰጠው የሕይወትን መመሪያ ላዘጋጅለት ፈጣሪ እየታዘዘ ኃጢዓትን ለማስተሰረይ የምኞት ፍትወትን ኃይል አድክሞ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ትገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መጠጥ በመከልከልና የመንፈስ ብርታት ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው:: ጾም ጸሎት ምጽዋት የተያያዙ…»
ሠ/ ነቢዩ ኤልያስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ በእሳት ሠረገላ በአውሎ ንፋስ ተነጥቆ ወደ ገነት (ብሔረ ሕያዋን) አርጓል፣ ገብቷል እናንተም 40 ቀንና 40 ሌሊት ብትጾሙ ገነት መንግስተ ሰማያት ትገባላችሁ፡፡ (1ኛ ነገ 19፡8 ፣ 2ኛ ነገ 2፡11)

ረ/ ነቢዩ ሕዝቅኤል በግራ ጎኑ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተኝቶ ስድስት መቶ ሙታን አስነስቷል እናንተም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ብትጾሙ ትንሣኤ ዘለ ክብር ትነሣላችሁ ለማለት ፣

ሰ/ ዕዝራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከምግብ ተከልክሎ የጥበብ ሕይወት መመሪያ መጻሕፍትን ጽፏል (ዕዝ 7፡6) እነዚያ ቀን ሲጽፉ እየዋሉ ማታ ይመገባሉ እርሱ ግን ቀን ሲያጽፈው የሚውለውን ማታ ሲያስበው ያድር ነበር፡፡

እናንተም 40 ቀንና 40 ሌሊት ብትጾሙ ምሥጢር ይገለጥላችኋል ለማለት፡፡

ሰ/ ነቢዩ ዳንኤል ከሀገሩ ከኢየሩሳሌም በምርኮ በተወሰደበት ሀገር በአንድ አምላክ ላይ ከነበረው ጽኑ እምነት ሳያወላውል በጾም በጸሎት ተወስኖ በመገኘቱ ከአንበሶች አፍ እንደ ዳነ ፣ ሕልምን የመተርጎም ዕውቀት ጥበብ እንደተሰጠው ሀገሩ ኢየሩሳሌም ነጻ የምትሆንበትን ወገኖች እስራኤል ከስደት የሚመለሱበት ከዚህም በላይ ረቂቅና ጠለቅ ያለ የክርስቶስ ሰው የመሆን ምስጢር እንደተገለጸለት በሱባዔው ፍጻሜ መላዕክት ተልከው እንዳረጋጉት የምስራች ዜና እንዳሰሙት ፈተናውን ሁሉ ድል እንዳደረገ (ዳን 9፡2-4 ፣ ዳን 10፡2-14)

እኛም ጥበብ እውቀት እንዲገለጽልን በሀገርና በወገን ላይ የመጣው መዓትና መከራ እንዲወገድ ነውራችን እንዲከባለል ለኃጢዓታችን ስርየት እንድናገኝ፣ ከነፍሳችን ቁስል እንድንፈወስ ጾምን እንጹም፡፡

 

ጌታችንና አምለካችን ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመበት ፍጻሜው ግን፡-

ሀ/ አዳም ልጅነት የተሰጠው በ40 ቀኑ ነበር በተፈጠረበት ምድር ኤልዳ በምትባል ቦታ ቆይቶ ገነት ገብቷል፡፡

በ40 ቀን ተሰጥቶት የነበረውን ልጅነት በመብል ምክንያት አጥቶት ስለነበረ

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ ልጅነቱን (ለአዳም) ሊመልስ ፍጹም ካሣ እንደ ካሰ ለማጠየቅ (ኩፋ 4፡9)

ለ/ አንድም ፅንስ ሁሉ በእናቱ ማህፀን በ40ኛው ቀን ተሰዕሎተ መልክዕ ይይዛል (ይፈጸምለታል)

በመሆኑም በ40ኛው ቀን ተስዕሎተ መልክዕ ለተፈጸመለት ክቡር የሰው ዘር ሁሉ ፍጹም ካሳን ሊክስ እንደመጣ ለማጠየቅ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ፡፡

ሐ/ በሌላው ሰው የተሰራው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአምስተኛ ባሕርያተ ነፍስ በመሆኑ ለአራቱ አስር አስሩን ለመካስ ወይም አራቱ ባሕርያተ ሥጋና አምስተኛ ባሕርያተ ነፍስን አድርጎ ለአምስቱ ስምንት ስምንት ለመካስ እንደመጣ ለማጠየቅ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ

4×10 = 40 ወይም 5×8= 40
ለምን 55 ቀን እንጾማለን ???

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 ቀንና 40 ሌሊት ብቻ ነው፤ በቤተክርስቲያናችን ግን አበው ቀኖና ሰርተው እንድንጾም የወሰኑት 55 ቀን ነው፡፡ ይህ እንደምን ነው ቢሉ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡

1.  አንድም ክርስቶስ 40 ቀናት የጾመው ከቆመ ሳይቀመጥ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ ፣ እህል ውሃ ሳይቀምስ በመሆኑ እኛም እህል ውሃ የሚበላባቸውን በ55ቱ ቀን ያሉትን ቅዳሜና እሁድን ብንቀንሳቸው 40 ቀናት ከእህል ከውሃ፣ ከጥሉላት የሚጾምባቸው ፍጹም ሱባዔ ይሆናልና ነው፡፡

2.  በሌላው ከ40ኛው ቀናት ፊትና ኋላ ያሉትን ሁለቱን ሳምንታት ከፍ ሲል አበው ሐዋርያት ዝቅ ሲል ሃይማኖታቸው የቀና፣ ርቱዓነ ሃይማኖት 318ቱ ሊቃውንት ከዚያም በኋላ የተነሱ አበው ሊቃውንት ከ40ው ጾም ጋር አብሮ እንዲጾም ሕግ ስለሰሩ ነው፡፡

ሀ/ የመጀመሪያው ሳምንት (ከ40ው ቀን በፊት) ያለው እንዲጾም የተወሰነበት ወይም የሚጾምበት ምክንያት ‹‹ፎቃ የተባለ ንጉሥ አገዛዝ አጽንቶባቸው በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ምዕመናን ህርቃል እንዲረዳቸው በጠየቁት ጊዜ ለመርዳት ፈቃደኛ ቢሆንም ሐዋርያት ሰው የገደለ ሰው ዕድሜውን ሙሉ እንዲጾም ስለወሰኑ በጉዳዩ የሚቸገርበት መሆኑን ገለጸላቸው ሕዝቡም የአንድ ሰው ዕድሜ ሰባ፣ ሰማንያ ነው እኛ እንጾምልሀለን ዘምተህ ጠላቶቻችንን አስወግድልን ስላሉት ቃላቸውን ተቀብሎ ችግራቸውን አስወግዶላቸዋል እነርሱም አምስት አምስቱን ቀን ተካፍለው ጾመውለታል›› ያላወቁት ምዕመናኑ ወይም ሕዝበ ክርስቲያኑ አንድ ጊዜ፣ ያወቁት የተረዱት ከምስጢር ባለጸጋ የሆኑት አበው ሐዋርያት ጹሙ ብለው ሥርዓት አድርገው በየዓመቱ የሚጾሙት ሆነዋል፡፡ አበው ሐዋርያት ከትምህርተ ወንጌል ሥምሪት አስቀድሞ አምስት አምስት ቀን የመጾም ልማድ እንደነበራቸውም ታውቋል፡፡

ለ/ ሌላው ከ40ው ቀን በኋላ ከሆሣእና እስከ ትንሣኤ ያለው ሳምንት ሰሞነ ሕማማት ነው፡፡ በሕማማት ሰሞን የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ደኅንነት ሕማም መከራ የተቀበለበት በመስቀልም የሞትን ጽዋ ተቀብሎ ለሞት ኃጢዓት ከመገዛት ነጻ ያደረገን ስለሆነ ህማሙን፣ ምክረ ሞቱን ለኛ ሲል የተቀበለውን ፀዋትወ መከራ በጾም በፀሎት በሰጊድ በኀዘን ለማሰብ በቤተክርስቲያን አበው የተወሰነ በመሆኑ ማንኛውም ክርስቲያን ‹‹ጾም በእናንተ ዘንድ የከበረ ይሁን›› ብለው የዓለም ብርሃናት ብፁዓን ሐዋርያት በዲድስቅልያቸው (አንቀጽ 29) በወሰኑት መሠረት ከጥሉላት መባልዕት ሥጋ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ ዓሣ ተከልክሎ ከ40ው ቀን ጋር አንድ ላይ ይህን ጾምም ሆነ ሌሎች አጽዋማትን እንዲከታተል ግዴታ አለበት።

#join #share
💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
ጾም ምንድነው???

ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ 

ጌታችን መጾም ሳያስፈልገዉ የጾመዉ በጾም መሳሪያነት ዲያብሎስን ድል ታደርጋላችሁ ሲለን ነዉ፡፡እርሱ ድል አድርጎለታልና ካልጾሙ ካልጸለዩ ሰይጣንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ጌታ አስተምሮናል፡፡

ጾም ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት እንደሆነ በሰብአ ነነዌ ታዉቋል እነዚህ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የተመለሱት በጾም ነዉና፡፡ኃጢአታቸዉ እጅጉን ገዝፎ ቅድመ እግዚአብሔር ስለደረሰ የጌትነቱ ጨንገር ከመምጣቱ አስቀድሞ ንስሓ እንዲገቡ መሐሪ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ላከላቸዉ፡፡ሕዝቡም የነቢዩ ስብከትን ሰምተዉ በክፉ ስራቸዉ ተጸጽተዉ ከሊሒቅ እስከ ደቂቅ ማቅ ለበሱ አመድንም በራሳቸዉ ነሰነሱ፡፡ንጉሱም ከዙፋኑ ወርዶ መጎናጸፊዉን አዉልቆ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ተቀመጠ፡፡አዕምሮ ጠባይዕ ያላደፈባቸዉ ሕጻናትና እንስሳትንም የንስሓቸዉ ተካፋዮች እንዲሆኑ አደረጉ፡፡በዚህ ጊዜ የፍጥረቱን መዳን እንጂ ጥፋቱን የማይወድ እግዚአብሔር ቁጣዉን በትዕግስት መዓቱን በምህረት መልሶ በይቅርታ ጎበኛቸዉ ከጠቀጣዉ መቅሠፍት አዳናቸዉ፡፡ዮና 3-5-10

ወደ እግዚአብሔር በጾም በጸሎት የተመለሱ ድኅነትን እንዳገኙ ሁሉ ያልተመለሱት ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ለምሳሌ ሰብአ ሰዶም ገሞራ እንደ ነነዌ ሰዎች በጾም ወደ እግዚአብሔር ባለመመለሳቸዉ እሳት ከሰማይ ወርዶ አቃጥሎ አጥፍቷቸዋል፡፡ዘፍ 19-23


አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ

መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ

ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ጾምም በመሆኑ ነው

#Join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
ዘወረደ

ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡ ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤›› የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው፡፡ ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡

ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡ የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል፡፡ ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም ሳምንትን (ዘወረደን) ስያሜ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሐዋርያት ተቀብላ ታስተምራለች፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21