መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር? ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣ ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡

ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡

ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡

ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
‹ጠላትህን ውደድ›› ማቴ. 5፥45

‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ማቴ. 5፥43-45

የዚህኛው ሕግ ዋና መልእክት ፍቅር ነው፡፡ ይህን ሕግ የሰጠን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶችን በመውደድ እኛም እንዲሁ እንድናደርግ አስተምሮናል፡፡ ሰውን ሁሉ መውደድ የክርስትና ሕግ ነው፡፡ ይህ ሕግ ፍጹም የሚሆነው ደግሞ የሚያውቁትን ወዳጅን በማፍቀር ብቻ ሳይሆን ጠላትን በመውደድ በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ነው፡፡ ክርስቶስ ሁሉንም በመውደድ በፍጹም ፍቅር እንደተገለጠ ክርስቲኖች ሁሉ ደግሞ ሁሉን በመውደድ ፍጹማን እንድንሆን ይህ ሕግ ግድ ይለናል፡፡ ማቴ. 5፥43-46

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
ሕግጋተ እግዚአብሔር ገጽ 211-212

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!

እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ። ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።

እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት። ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

#join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ድነኀል ወይስ አልዳንክም?

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?

መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው። ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።

ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”

በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)። ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።

ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!

አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
Tእግዚአብሔር በሁሉም ቦታ አለ!

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ ስላለ ሰዎች የሚሠሩትን ያያል የሚናገሩትንም ይሰማል። እያንዳንዱ ሰው ከእግዚአብሔር ቁጥጥር በታች ነው። እግዚአብሔር ኃያል አምላክ ስለ ሆነ አንድ ሰው የሠራውን ስራ በእርሱ ፊት ሊክድ አይችልም። ይህን አስመልክቶ ነቢዩ ኤልያስ ሲናገር “በፊቱ የቆምኩት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን!” 1ኛ ነገ 18፥15 ብሏል። የሰው ልጆች በምድር ላይ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚቆሙ መላእክት ደግሞ በሰማይ በፊቱ ይቆማሉ።

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ ከመሆኑ ሌላ ማንኛውም ቦታና ማንኛውም ነገር በእርሱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር አይችልም።

እርሱ በንጹህ ልባቸው በሚያመሰግኑት በቅዱሳኑ መካከልና ክፉ ስራቸውን እየተመለከተ ፈጥነው ይመለሱ ዘንድ በሚገስጻቸው ክፉዎች መካከል ይገኛል። ለሁሉም “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ” ራዕ. 3፥20 ይላቸዋል።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የእግዚአብሔር ጸጋ

የእግዚአብሔር ጸጋ ማንንም ሳያስቀር ሰዎችን ሁሉ ስለሚጎበኝ ኃጢአተኞች እንኳ ከዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ጉብኝት ተቋዳሾች ናቸው። ስለ ጌታችን እንዲህ ተብሎ ትጽፏል “እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስ የተገዙትንም እየፈወሰ ዞረ” ሐዋ. 10፥38። እርሱ የጠፉት ነፍሳት ባለመታመናቸው በልበ ደንዳናነት ከእርሱ ርቀው ቢጠፉም እርሱ ግን መፈለጉን አላቋረጠም። የነበሩበት እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳ መልሶ እስከሚያመጣቸው ድረስ ፍለጋው አልተቋረጠም።

ሰዎች ስለ ድኅነታቸው ተስፋ የሚቆርጡ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን በሰዎች ላይ ተስፋ ማሳደሩን አያቋርጥም። እግዚአብሔር በመንፈሳቸው የደከሙትን ቀርቶ ሞቶ ሥጋው በመሽተት ላይ ያለውን ሰው እንኳ ሳያስቀር ለሁሉም ሁሉ ጊዜ በጎ ነገርን ይሰራል። (ዮሐ. 11፥39) ከዚህ በተጨማሪ እርሱ በሕይወቱ የመጨረሻ ህቅታ ለነበረው ወንበዴ፣ ለቀረጥ ሰብሳቢው ዘኪዎስና አምስት ባሎች ለነበርዋት ሳምራዊት ሴት ይሰራ ነበር። (ሉቃስ. 23፥43፣ ሉቃስ. 19፥9፣ ዮሐ. 4፥18)። እርሱ ያቺ ጠፍታ የነበረችው ሳምራዊት ሴት ወደ ንስሐ ሊመራት ያለችበት ድረስ ሄዶ ፈልጓታል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእግዚእብሔርን ፍቅር በማስመልከት “እግዚአብሔር ለድኅነታችን ምክንያት ይሆን ዘንድ አንዲት ዘለላ እንባ እንኳ ትበቃዋለች። ይህች ዘለላ እንባ የከንቱ ደስታ ባለቤት በሆነው በዲያብሎስ ከመነጠቅዋ በፊት ለእኛ ለድኅነታችን ምክንያት እንድትሆን እግዚአብሔር ይቀበላታል” ብሎ ነበር።

በእርግጥ ከእኛ ልቦናዎች ይበልጥ እጅግ ርኅሩኅ ከሆነው ከአምላካችን ልብ የሚበልጥ የለም። ይህንን በማስመልከትም አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል “ቀኑን ሁሉ ወደማይታዘዝና ወደ ሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ” (ሮሜ. 10፥21፣ ኢሳ. 65፥2)።

አምላካችን እግዚአብሔር ኃጢአት እንጂ ኃጥእ አይጸየፍምና ያለ አድልዎ ለሁሉም በእኩል ዓይን ይጎበኘዋል።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ኑሮየን ንገረኝ
ታላቁ ቅዱስ አርሳንዮስ ቤተ መንግሥትን ለቆ ወደ በረሃ ለምናኔ ሲገባ ጌታን የለመነበት ትልቅ ጸሎት ነበር። ጌታሆይ አለው። ጌታም አርሳኒ ምን ትሻለህ አለው። ቅዱስ አርሳንዮስም ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ ሲል ጠየቀ። ዳግመኛም ጌታ ሆይ ሲል ጮኸ። ጌታም አርሳኒ ምን ትሻለህ አለው። እርሱም ጌታይ ሆይ ኑሮዬን ንገረኝ አለው። ሦስተኛም አለ ጌታ ሆይ? አርሳኒ ምን ትሻለህ? ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ? ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፦
ጌታም መለሰ።
፩. ቦታ ምረጥ
፪.ከሰው ተለይ
፫.ዝም በል
ይህን ነግሮ ሲፈጽም ቃሉ ዝም አለ። አርሳኒም ገዳም ገብቶ ለፍጹምነት በቃ።
ሰው መንገድ ሲሄድ በሁለት መንገድ ሊወድቅ ይችላል።አንደኛ በጠማማ መንገድ በመሄድ። ሁለተኛ በቅን መንገድ ሳያስተውሉ በመሄድ ነው። በጠማማ መንገድ በመሄድ መውደቅ ማለት በጠማማ ሃይማኖት መኖር ነው ። በቅን መንገድ ሳያስተውሉ መጓዝ ማለት ደግሞ በቀናች ሃይማኖት እየኖሩ አካሄድን አለማወቅ ነው። መንገዱ የቀና ቢሆንም አረማመዱ ባለማየት ከሆነ እግሮቹ ተጣልፈውም ቢሆን ይወድቃል። አካሄዱ ካላማረ በክርስቶስ ማመንም ያስኮንናል።የምናውቀው ክርስትና በማናውቀው መንገድ ከኖርነው ያጠፋል።

አውቀን ለምናደርጋቸው እንኳ ቢሆን እንዴት ላድርገው እያልን መጠየቅ በየዕለቱ እናደርገው ዘንድ ይገባል። በየጊዜውና በየሰዓቱ ወደ ክርስቶስ የምንጓዝ ነንና ጥያቄያችን የዘወትር ነው። ጸሎት አይቋረጥም መባሉ ስለዚህ ነው።ቅዱስ አርሳንዮስ ኑሮው ምንኩስና እንዲሆን ወስኖ ነበር። ግን መነኩሴ መሆን እንዳለበት እያወቀ ኑሮየን ንገረኝ ይል ነበር። ለምን ቢሉ ኑሮውን ብናውቀውም አኗኗሩን ግን ካልጠየቅን የሚጠቅመውን በማይጠቅም መንገድ ልንኖረው እንችላለን።፡
ለምሳሌ ከቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስን እንይ። ቅዲስ ጳውሎስ ምሑረ ኦሪት ነበር። ፵፮ቱን የኦሪት መጻሕፍት ተምሯል። መጻሕፍቱ ግን የሚተረጎሙት በክርስቶስ መገለጥ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ግን ጌታን ያሳድድ ነበር። የሚያሳደደውም ለሕግ የተቆረቆርሁ መስሎት ነበር። ጌታም ቅንነቱን አይቷልና ጌታን እያገለገለ መስሎት ጌታን ያሳድድ የነበረውን አልተወውም። መንገዱን ያቀናለት ዘንድ መንገገድ ላይ በመብረቅ ተገለጠለት። ሊያሳድድበት የሄደውን መንገድ ወደ ክርስቶስ እንዲደርስበት መራው። እውቀትን ቅንነት ይመራዋል፤ ቅንነትን እውቀት ያበራዋል። ስለዚህ ስለምናደርገው ነገር በቂ እውቀት ቢኖረንም ያንን ግን እንደመርከብ የሚመራው ረድኤተ እግዚአብሔር ነውና አዘውትረን ኑሮየን ንገረኝ እንበል!

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
ሆዳችሁ ጠግቦ ከምታቀርቡት አንድ መቶ ጸሎትና ተራራ ከሚያርድ ድምጻችሁ ይልቅ በጾም ውስጥ ሆናችሁ የምታቀርቡት አንድ ጸሎት ተሰሚነት አለው።

ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

join or share
@linkortodoxe21
ጻዲቁ ዮሴፍ እጅግ ከባድ የሆነ ውጪያዊ ውጊያ ከጲጥፋራ ሚስት ቢገጥመውም አልወደቀም። እርሱ ኃጢአትን በልቡ ውስጥ ስላልተቀበለው ፈተናውንም አልተቀበለውም። ስለሆነም ጥቃቱን ሊቋቋም ችሏል። ዲያብሎስ አሳቦችን ያቀርብልሃል እንጅ ተቀብለህ ተግባራዊ እንድታደርጋቸው አያስገድድህም።

ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

join or share
@linkortodoxe21
👳ይፍቱኝ👳

አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ካህን የከተማ አውቶብስ ውስጥ ናቸው አውቶብሱ ሞልቷል እንኳንስ መቀመጫ የእግር መቆሚያ ቦታ የለውም መቼስ መሳፈሩ ግድ ነውና ሰው በሰው ላይ ተዛዝሎ በሩም በግድ ተዘግቶ ጉዞው ቀጥሏል ካህኑ መቀመጫ በማጣታቸው የአውቶብሱን ብረት ይዘው ከወዲያ ወዲህ እየተወዛወዙ ሳለ አንድ የኪስ ቀበኛ በኪሳቸው እጁን ጥልቅ ሲያረግ ካህኑም የሌባውን እጅ ከኪሳቸው ጋር ጨምድደው ይይዙታል ይሄኔ ሌባው ኮስተር ብሎ ከካህን መስቀል እንደሚሳለም ምእመን ራሱን ወደ ምድር ዝቅ አድርጎ "ይፍቱኝ" ይላል የሌባው ድፍረትና ዓይን አውጣነት የገረማቸው ካህንም "ወቸው ጉድ እንኳን ተፈተህ ታስረህስ መች ተቻልክ" አሉት ይባላል "

💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

የንስሐ መጀመርያው እየሠሩ ካለው ኃጥያት መለየት ነው ማቴ ፳፮ ፣ ፸፭
ሰው ከእግዚአብሔር ምህረት መጠየቅ ያለበት የበደለውን ክሶ የቀማውን መልሶ ሊሆን ይገባል

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
=> #የምኒልክ_አዋጅ
________________

" እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፣ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም።

ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም ። አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፍል መሬት ይቆፍር ጀመር ።

አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም ጉልበት ያለህ
በጉልበትህ እርዳኝ ጉልበትም የሌለህ ለልጅህ ለምሽትህ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘንህ እርዳኝ ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም #ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ "

ይህን አዋጅ ሰምቶ ህዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ንጉሡን ተከትሎ ህይወቱን ሰጥቶ ሀገሩን እና ክብሩን ታደገ።

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21