መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
☞ መቅናት ካለብህ በሚያነቡት ቅና!
...
• ማንበብ ጭንቀት፣ ድብርትና የአዕምሮ ውጥረትን ያጠፋል፤
• ማንበብ የማሰብና የፈጠራ ክህሎትን ይጨምራል፤
• ማንበብ አንደበትን ይገራል፤ የሐሳብ እጥረትን ያስወግዳል፤
• ማንበብ ሠላማዊና ጤናማ እንቅልፍ ለማግኘት ይረዳል፤
• ማንበብ አዕምሮን ያንፃል፣ የመገንዘብ አቅምን ያጎለብታል፤
• ማንበብ አማራጭ ሐሳቦችን በማመንጨት መፍትሄን ያፈልቃል፤
• ማንበብ አእምሮን በማረጋጋት መልካም ስብእናን ያጎናፅፋል፤
• ማንበብ መርሳትን አርቆ የማስታወስ ችሎታን ያዳብራል፤
• ማንበብ ግንኙነትን በማሳደግ ማህበራዊ ተሳትፎን ያሻሽላል፤
• ማንበብ በመረጃ የተደገፈ ውብ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያደርጋል፤
• ማንበብ በራስ መተማመንን ይፈጥራል፤
• ማንበብ አሉታዊ ሀሳቦችን በማስወገድ ሙግትና ጭቅጭቅን ያስቀራል፤
• ማንበብ ልክና ስህተት የሆኑ የህይወት ፍልስፍናዎች እንድንለያቸው ይረዳል፤
• ማንበብ ዕውቀትና ክህሎትን በማስገኘት ስኬታማ ሠዎች ያደርገናል፤
• ማንበብ የሠው ልጅ ባህርያት ጠንቀቅን እንድናውቅ ይረዳል፤
• ማንበብ ህይወታችን ቅርፅ እንዲኖረውና በመርህ እንድንመራ ይጠቅማል፤
• ማንበብ የሀሳብ ድርቀትን ያስወግዳል፤
• ማንበብ ሀገርና ትውልድ ያንፃል፤
• ማንበብ ግጭትና መለያየትን ይቀንሳል፤
• ማንበብ የአንድን ማህበረሰብ ስልጣኔ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አኗኗርን ይቀይራል፤
• ማንበብ ጨለምተኝነት በማራቅ ግጭትና ጦርነትን ይቀንሳል፤
• ማንበብ ልዩነትና ክርክርን ቀንሶ መግባባትን ያጎለብታል፤
• ማንበብ ግምታዊነት፣ ተጠራጣሪነትን፣ አስመሳይነት፣ ደመነብሳዊነትን፣ ስሜታዊነትን፣ ሐሰት፣ ሐሜት... አስወግዶ ምክንያታዊና የመረጃ ሠው እንድንሆን ይረዳልና ንባብን እንለማመድ።
....
#Share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#ለመለወጥ_ጥረት_ስለምታደርግ_ነፍስ#ለመለወጥ_ጥረት_ስለምታደርግ_ነፍስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ለአንድ መነኰሴ ያስተማረበት ምሳሌ....

..... “በከተማ መካከል ብዙ ወዳጆች ያሏት አንዲት ቆንጆ ሴተኛ አዳሪ ነበረች፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ወደ እርሷ ቀርቦ፡- "#መልካም_ሴትመልካም_ሴት #እንደምትሆኚ_ቃል_ከገባሽልኝ_አሁኑኑ_አገባሻለሁ#እንደምትሆኚ_ቃል_ከገባሽልኝ_አሁኑኑ_አገባሻለሁ" ይላታል፡፡
እርሷም በሐሳቡ ተስማምታ ቃል ስለገባችለት ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ፡፡ ወዳጆቿ ድጋሚ ሊያገኟት ስለ ፈለጉ እንዲህ እያሉ ይመካከሩ ነበር፡- "የከተማው ከንቲባ ወዳጃችንን ወደ ቤቱ ወስዷታል፡፡ በግልጽ ወደ ቤቱ ከሄድን ስለሚያውቅብንና ስለሚያስፈርድብን በቤቱ ጓሮ ዞረን እናፏጭላት፡፡ የፉጨታችንን ድምጽ ለይታ ስለምታውቃቸው ከቤቷ ወርዳ ትመጣለች፡፡ ለማንኛውም ግን እርሷ ትምጣልን እንጂ እባ አንጣላም" አሉ፡፡
በመጨረሻ እንደተመካከሩት በቤቱ ጓሮ ዞረው ሲያፏጩላት ጀሮዎቿ ቆሙ፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ ልትወርድ ስላልፈለገች #ፈጠን_ብላ_ወደ_እንግዳ_መቀበያው_አዳራሽ_ገባችና_በሮቹን_ዘጋግታ_ከውስጥ_ተቀመጠች፡፡

✥✥✥ ልክ እንደዚሁ ነፍሳችን በዚህች ሴት ስትመሰል ወዳጆቿ ደግሞ ምኞቶቻችን ይመስላሉ፡፡ ከንቲባው የሚመሰለው በምንወደው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያለው የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ በዘላለማዊ ቤታችን ወይም በመንግሥተ ሰማያት ሲመሰል የሚያፋጩላት ሰዎች ደግሞ በርኩሳን መናፍስት ይመሰላሉ፡፡✥✥✥

በመጨረሻም ይህን ምሳሌ ነፍሳችን ሁል ጊዜ እግዚአብሔር ከተጠጋች በእርሱ ኃይል እንደምትኖር ያስረዳናል፡፡”....

(ምንጭ፡- የበረሃ አባቶች ምክሮች በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
Share or join

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ የዝምታ ጩኸት +

እስራኤል ጭንቅ ላይ ናቸው:: ከባርነት ተላቅቀው ከግብፅ ከወጡና ጉዞ ከጀመሩ በኁዋላ ፈርኦን የለቀቀው ሕዝብ ጉልበት ቆጭቶት በቁጣ ነድዶ ሠራዊቱን አስከትቶ በፈጣን ሠረገላ እየጋለበ መጣባቸው:: ከፊታቸው ደግሞ የሚያስፈራ ባሕር ተደቅኖአል::

ሕዝቡ የፈረደበት ሙሴ ላይ ጮኹበት:: መጽሐፈ መቃብያን "ያንን ሁሉ ሕዝብ ሲጠብቅ ያልተበሳጨ ሙሴን አስበው" እንደሚል እንደ ሙሴ ትሑትና ታጋሽ መሪ ታይቶ አይታወቅም:: ልክ በዚያች ዛፍ ላይ እሳት ሲነድባት እንዳልተቃጠለች እስራኤላውያንም ሙሴ ላይ ለዓመታት ቢነዱም አላቃጠሉትም::

"በግብፅ መቃብር ጠፍቶ ልታስፈጀን ነው?" "ከሞት ባርነት በስንት ጣዕሙ?"
እስራኤል በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሙሴን በቁጣ እየጮኹ አስጨነቁት::

መሪነት ከባድ ነው:: ያንን ሁሉ ድንቅ ነገር አድርጎ እግዚአብሔር ነፃ ሲያወጣቸው ሙሴ ለእነርሱ ቤዛ ሆኖ ተሹሞ ብዙ ዋጋ ከፍሎአል:: ውለታውን ረስተው አፋጠጡት::

"ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ፡ አላቸው"

ሙሴ ሕዝቡን ከጩኸታቸው ሲያረጋጋ ሳለ የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሙሴ መጣ
"ሙሴ ሆይ ለምን ትጮኽብኛለህ?" አለው::

ልብ አድርጉ የጮኸው ሕዝቡ ነው ሙሴ አረጋጋ እንጂ ቃል አልተናገረም::

ሆኖም ሙሴ አፉ ዝም ቢል ልቡ ይጮኽ ነበር:: ከእስራኤል ጩኸት ይልቅ የሙሴ ዝምታ እግዚአብሔር ጆሮ ደረሰ:: እግዚአብሔር ኤልያስ እንዳላገጠባቸው የአሕዛብ አማልክት በጩኸት ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለም:: በትዕቢትና አመፅ ከሞላበት ጩኸት ይልቅ በተሰበረ ልብ የሚቀርብ ዝምታ እግዚአብሔር ጋር ይጮኻል::

የእስራኤል ጩኸት ፍርሃት ይነዛል:: ልናልቅ ነው የሚል ሽብር ይፈጥራል:: የሙሴ ዝምታ ግን ባሕር ይከፍላል::

ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን::
የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም::
የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም::
በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::

የኤርትራ ባሕር በዝምታ ተከፈለ:: እስከ ራማ የተሰማው ራሔል ስለ ልጆችዋ ያለቀሰችው ዕንባ ባሕር ከፈለ:: እመቤታችን ሆይ ስለ እኛ ስለልጆችሽ እባክሽን አልቅሺ:: የራሔል ዕንባ ራማ ከደረሰ የአንቺ ዕንባ የት ሊደርስ ነው? በየበረሃ እየወደቀ ስላለው ልጅሽ ስለሞተለት ወንድም እባክሽን ለምኚ::

በሙሴ በትር ባሕሩ ተከፈለ:: የኤርትራ ባሕር (ቀይ ባሕር [በግሪኩ erythos ማለት ቀይ ነው]) እጅግ ባለ ታሪክ ባሕር ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደረቅ ሆኖ ፀሐይ ያየውና ግማሽ ሚልየን የሚሆን ሕዝብ በመካከሉ ተራምዶ ያለፈበት ይህ ባሕር እንንደ ግድግዳ የቆመ ብቸኛው የዓለማችን ባሕር ነው::

በዚህ ባሕር እስራኤል ሲሻገሩ ፈርኦን ከነሠራዊቱ ሰጠመ:: በእግር የሔዱት የተሻገሩትን ባሕር በሠረገላ የሔዱት አቃታቸው:: የኤርትራ ባሕር ለእስራኤል ትንሣኤ ሲሆን ለፈርኦን ግን መቃብር ሆነ:: ፈርኦን ደንግጦ መመለስ የነበረበት ባሕሩ ሲከፈል ሲያይ ነበር:: ፈርኦንን ያደቆነ ሰይጣን ግን ባሕር መካከል ሳያቀስስ አልለቀቀውም::
እግዚአብሔር ማን ነው? ብሎ ነበር በዚያ ባሕር ተዋወቀው:: እሱ ሲሰጥም እስራኤል በኩራት "እግዚአብሔር ማን ነው? " ለሚለው የፈርኦን ጥያቄ ከባሕር ማዶ ሆነው መልስ ሠጡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" አሉ:: እስራኤል በኤርትራ ባሕር መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ "በባሕርና ደመና ተጠመቁ" ተብሎላቸዋል:: ፈርኦን ግን እስራኤል በተጠመቁበት ጠበል ውስጥ ሰጠመ::

የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ ከሙሴ ሌላ እስራኤልን ሲመራ የነበረ ጠባቂ ነበረ:: እርሱም የእስራኤል ጠባቂ (advocate of Israel) በመባል የሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነበር::

"በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ" ዘጸ 14:19 እንዲል ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን ዐምድ እየተመሰለ በመንገድ መራቸው::

ኢትዮጵያውያን ያለነው ከባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው:: ሁሉም መሻገር ይፈልጋል:: ከእኛ መካከል እንደ ፈርኦን ሰጥሞ የሚቀር ይኖራል:: እንደ እስራኤል የሚሻገር ይኖራል: : ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለእኛም ድረስልን:: ይህንን ክፉ ዘመን በክንፎችህ አሻግረን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 12 2013 ዓ ም
ድሬደዋ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

የክርስቲያንመከራ እና ሌሎች ቅዱስዮሐንስአፈወርቅ እንዳስተማረው በገብረእግዚአብሔርኪደ

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡

ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)

በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
  1.  እግዚያብሔርን ማወቅ

መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡

እግዚአብሄርን ማወቅ፡-

ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል

በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡

ታሪክን ይቀይራል

ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
2.በዕምነት ማደግ

ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
3.በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር

እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13)

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
4.እግዚአብሔርን መምሰል

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ  እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”(1ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የስጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል”(2ጢሞ 4፡8)

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
5.ፍቅር ሊኖረን ይገባል

በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” (1ዮሐ 4፡8) በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅ/ጳውሎስ እንደተናገረው ከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”(1ቆሮ 13፡1)

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
6.ከመስቀሉ መካፈል

የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ (ፊሊ 2፡8) ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን መውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ስጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ (ዮሐ 19፡27፤ ዮሐ 6፤56) ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡

ስብሃት ለእግዚያብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን

✍️ምንተስኖት

join or share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሰውየው ከሰው በር ላይ የሆነ ነገር ይሰርቃል ትንሽ ቆይቶ ግን ይጸጸታል ተጸጸቶም አልቀረ መምህረ ንሰሐ (የንስሐ አባቱ) ዘንድ ሄዶ አባ ገመድ ከሰው ደጅ ሰርቄያለው ይቅር ይበሉኝ ብሎ ይናዘዛል አባም የንስሐ ኑዛዜውን ተቀብለው ቀኖና ሰተው እግዚአብሔር ይፍታ ብለው ሸኑት ....
በሌላ ጊዜ ሰውየው ተመልሶ መጣ አባም ምነው መልሰህ በደልክ እንዴ ሲሉ ጠየቁት አ
ሰውዬውም እየተንተባተበ አይ አባ የባለፈው ስርቆቴ ነው አላቸው አባም ላለፈውማ ቀኖና ሰጥቼ ንስሐ ገብተሃል እግዚአብሔርም ምሮሃል ሂድ ብለው መለሱት ሰውየውም ቅር እየተሰኘ ሄደ ነገር ግን ሄዶ አልቀረም ተመልሦ ለሦስተኛ ጊዜ መጣ አባም ግራ ተጋብተው አሁንስ ለምን ተመልሰ መጣህ ሲሉ ጠየቁት ሰውየውም በፍርሃት ድምጽ የ.... የ.. የየባለፈው ገመድ አላቸው ያኔ አባ አንድ ነገር አስተዋሉ ቀና ብለው በፈገግታ ከተመለከቱት በኃላ ልጄ የገመዱ ጫፍ ላይ ምን ታስሮ ነበር? ብለው ጠየቁት ሰውየውም አንገቱን አቀርቅሮ በቀስታ በ......በ......በሬ🐂 አላቸው::

ስንቶቻችን በሬ የሚያክል ኃጢያት ሰርተን የገመድ ንሰሐ ገብተን ይሆን????????? መልሱን ልቦና ይመልሰው
" የንሰሐ ግማሽ ጽድቅን ሁሉ ደርማሽ"

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር? ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣ ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡

ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡

ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡

ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21