መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ተስፋ_መቁረጥ_የኃጢአት_መጨረሻ_እና_ሌሎችም(480p)_9
<unknown>
✟✟✟ ተስፋ መቁረጥ የኀጢአት መጨረሻ ሌሎችም

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ተወዳጆች ሆይ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጥቶ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነውን? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነውና፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡

ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የሰማእታ የቅድስት አርሴማ እረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
#Valantines_day_እውነት_የፍቅር_ቀን ?
ከልደተ ክርስቶስ በኋላ በአለም ላይ የሠለጠኑት ሮማውያንና ግሪካውያን አምልኮተ እግዚአብሔርን ጠልተወ ሐዋርያትንና ተከታዮቻቸውን እያሳደዱና እየገደሉ በምትኩ ፍጡራን የሆኑ ምድራውያን ነገስታትንና የተለያዩ ጣኦታትን ለአምልኮ ይጠቀሙ
ነበር። ከፍ ሲልም ለእነዚህ ጣኦታቶቻቸው ክብር ሲሉ የተመረጡ እለታትንና ወራትን በስማቸው ይስይሙላቸው ነበር።እንደምሳሌ ዛሬ sunday, የፀሀይ ቀን/ monday, የጨረቃ ቀን.......እያልን እለታቱን የምንጠራበት ምክንያት ይሄው ነወ። በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተነሱ
ጣኦት አምላኪያን ደግሞ (february ·15) ቀንን የተኩላ አዳኙ«ሉፐርካልያ (Lupercalia)» ቀን ብለው ሰይመውት ነበር። በአደኑ የሚፈሰውን ደምም በቀይ ቀለም መስለው ለነገራቸው ሁሉ ምልክት በማድረግ እለቷን በየአመቱ በቀይ ነገር እየሰሸበረቁ ያከብሯት ነበር። በ 323 ዓ·ም አካባቢ በቁስጥንጥንያ የነገሠው ክርስቲያኑ ንጉሥ ታላቁ "ቆስጠንጢኖስ"ይህ አይነቱ የባዕድ አምልኮ ሥርዓት እንዲቀር አዘዘ። በዚህ ጊዜ እነርሱ በተለየ መልኩ (february ·15) የሚያከብሯትን የተኩላ አዳኙ« ሉፐርካልያ (Lupercalia)» ቀን በአንድ እለት ወደ ኋላ ስበው (february ·14)ን የፍቅር ቀን በማለት በሽፋን በ valantines ስም ሰይመው ባዕድ አምልኳቸውን
ቀጠሉ። ነገረ valantine ንን ከየት አመጡት ከተባለ በ2ኛው
መ·ከ·ዘ ማብቂያ ላይ "ክላውዴዎስ 2ኛ" በሮም በነገሰበት ወቅት የሰራዊቱን ቁጥር ለማብዛት ሲል ትዳር የሚመሰርቱ ወጣቶች እንዳይኖሩ ከለከለ ምክንያቱ ደግሞ ቤተሰብ ያፈራ ሰው ቤተሰቡን ትቶ ወደ ውትድርናው አለም እንዲገባ ስለማይገደድ ወጣቶቹ ይህን ሳይፈፅሙ በእነሱ ለመጠቀም በማሰቡ ነበር። ታዲያ ይህንን አዋጅ ብዙ ሰው ስላልደገፈው ልጆቹን በድብቅ ያጋባ ነበር። አቶ valantine ም ይህን ሀሳብ ከሚቃወሙት መካከል ስለሆነ ብዙ ወጣቶቹን በድብቅ እየሞሸሩ ያጋቡ ጀመር።ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ይህ ድርጊታቸው በንጉሱ ክላውዴዎስ ዘንድ በመታወቁ አቶ valantine መጀመሪያ የእስር ቀጥሎ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው። ይህኔ በሮም ግዛት ሁሉ ስማቸው ገነነ ሥራቸውም በሁሉ ዘንድ ተሰማ ለወጣቶች ፍቅር ሲሉም እራሳቸውን ለአደጋ እንዳጋለጡ በማሰብ የፍቅር አባት እስከመባል ደረሱ።ይህ ከሆነ ከብዙ ዓመታት በኋላ የተነሳው ቆስጠንጢኖስ ደግሞ የተኩላ አዳኙን ቀን እንዳይከበር ሲከለክል ሕዝቡ እለቷን ሳያስቡ እንዳያልፉ የቆየውንና በህዝቡም ዘንድ በፊት ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ የነበረውን የvalantine ን ታሪክ ስቦ በማምጣት ለባዕድ አምልኳቸው ሰበብ እንዲሆናቸው የፍቅር ቀን ብለው ተጠቀሙበት።እንግዲህ valantines day ከዚህ ጊዜ አንስቶ በፍቅር ቀን ስም መከበር የተጀመረ ሲሆን ከዘመናት በኋላ ደግሞ የካቶሊክ ቤ/ክ ለሰውየው ቅድስና ስለሰጠቻቸው እለቱ በአለም ዙሪያ የቅዱስ ቫላንታይን ቀን ተብሎ እንዲታሰብ ምክንያት ሆነች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሰው በዘር ፣ በቀለምና በሃይማኖት ሳይለያይ መያዝ የማይገባውን ስያሜ ሰጥቶ ሲያከብረው እያየን እንገኛለን።በሀገራችንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው።እኛን በቅጡ ለማይወክለን ባህል ሆቴሎችና መዝናኛ ቦታወቻችን በዚህ ቀን ጥንድ ካልሆናችሁና ቀይ ካለበሳችሁ አናስተናግድም እያሉ ነው።ሰውን የፍቅር "ቀን"ብለው ጠርተውት "ሌሊቱን" እያሳበዱ ያሳድሩታል።የመገናኛ ብዙኃኖቻችን ፍቅር በሀገራችን አልፎ እንደማያውቅ ፣ስለ ፍቅር የተከፈለ መስዋዕትነት በታሪካችን እንደሌለ፣ አብሮነት መዋደድ በማህበረሰባችን እንደማይታወቅና ሃይማኖታችንም ስለፍቅር እንዳልሰበከች ያህል አድርገው የፍቅር ማስተማሪያ ምሳሌዎቻቸውን ሁሉ የሚያመጡልን የኛ ካልሆኑ የምዕራባውያን ታሪኮች ነው። ነጮች ለዚህ ሁሉ ነገር መነሻ የሆነውን ቫላንታይንን ከሰብዓዊነት
የተነሳ ለወጣት ፍቅረኛሞች ህልማቸውን አሳክቶ
ጥሩ ነገር ስላደረገላቸው የፍቅር አባት ብለውት ይሆናል።ነገር ግን ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ ለእኛ ትክክለኛ የፍቅር አባት እርሱ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እኛ ከሰማያዊ መንበሩ በፍቅር ተስቦ የወረደ እዛው ባለበት ሆኖ የወደደውን ማድረግ ሲቻለው ፍፁም ፍቅሩን እንድንረዳ ለአይሁዳውያን ተላልፎ በመሰጠት በሞቱ ሕይወትን ያደለን ክርስቶስ ስላለን valantine ለእኛ የፍቅር አባት መታሰቢያ ቀኑም የፍቅር ቀን ሊሆን አይችልም።እንደው የአምላካችንን ነገር ማንሳት ከከበደንና valantine ን ከእርሱ ጋር አናወዳድረው ካልንም ወደ ሀገራችን ታሪክ ተመልሰን ከቫላላንታይን በላይ ለፍቅር ብዙ የሆኑት ሰዎች አስበን አላከበርናቸውም።በእኛው ታሪክ በ15ኛው መ·ከ·ዘ ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ካህናት አባቶቻችን መጠጊያ መጠለያቸው የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእሳት ስትፈተን ሥርዓተ ጋብቻን በየምዕመኑ ቤት በድብቅ ነበር የሚፈጽሙት ግን እኛ የፍቅር አባት አላልናቸውም። እነ አፄ በካፋ የወደዷትን ለማግባት በንግስናቸው እንደፈለጉ አዘው ማግኘት የሚችሉበት አጋጣሚ እያለ እንደ ተራ ሰው መናኛ ልብስ ለብሰው የሰው ቤት ደጅ መጥናታቸውን አይተን የፍቅር ምሳሌ አላደረግናቸውም። ከማህበረሰቡ የቆየ የመረዳዳትና የመተዛዘን ባህል ለፍቅር ኑሮ ማስተማሪያ ታሪክ አልመዘዝንም። እናም እኛ ኢትዮጵያውያን ይህ ሁሉ እያለን ምንም አለማድረጋችን የባዶነታችንን ክፍተት የአላዋቂነታችንን ጥግ ያሳያልና ቆም ብለን እናስብ የእምነት መግለጫ ማህተባችንን ማሰር ከብዶን ለጣኦት የተገበረን ደም ማሳያ የሆነን ቀይ ልብስ ለብሰን እንዞራለን ፣የቤተ ክርስቲያናችንን ቅዱሳኖች አመታዊ በዓል በዳቦ
ዘክሮ ለማሰብ እጅ የሚያጥረን የካቶሊክን ቅዱስ
ለማክበር ድንጋይ እንፈነቅላለን።በዚህ ወር የተፈፀሙትን የነ አብርሃም ደቦጭ ገድል የታላቁን የአድዋን ድል ታሪክ ለማስታወስ ደንታ የሌለን የ valanine ንን ቀን እንዳንረሳ ማስታሻ እንይዛለን።ማን ያውቃል በዚሁ ከቀጠልን ደግሞ ወደፊት ዋና ዋና በዓላቶቻችንን ትተን የነሱን X-MASS ብቻ እናክብር እንላለን።ነገር ግን ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት እንዲህ እንደ valanine አይነት ያሉ የምዕራባውያን ባህሎችን በመቃወም ለነገ ዛሬን የማስተካከያ እድል አለን። ይህን ካላደረግን ግን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ደም የለንም ማለት ነው። ምክንያቱም እነ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉት ኢትዮጵያ በዚህ አይነቱ የእጅ አዙር ቅኝ ተገዥነት እንዳትያዝ ህዝቦቿም መልካም አላማ የያዙ መስለው ሃይማኖታዊ ሕፀፅንና ሥርዓት የለሽነትን በሚያራምዱ በሽፋን ከሚንቀሳቀሱ የባህል ቅሰጣወችና ማንነት ከሚያጠፉ ነገሮች እንድንጠበቅ ነውና የቆምንበትን እናስተውል።በተለይ ደግሞ ሕዝቧ የሚያከብረው ሃይማኖት የራሱ የሆነ ማንነት አለው በሚባልላት ኢትዮጵያ እንዲህ ሲሆን ማየት ያሳምማልና ከሌላ ወገን የምናመጣቸውን በአላት ከሃይማኖታችን እንደማይጋጭ ከባህል ማንነታችን ጋር እንደማይጣረስ የመጨረሻ አላማና ግባቸው ምን እንደሆነ እንመርምር።
💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
☞ መቅናት ካለብህ በሚያነቡት ቅና!
...
• ማንበብ ጭንቀት፣ ድብርትና የአዕምሮ ውጥረትን ያጠፋል፤
• ማንበብ የማሰብና የፈጠራ ክህሎትን ይጨምራል፤
• ማንበብ አንደበትን ይገራል፤ የሐሳብ እጥረትን ያስወግዳል፤
• ማንበብ ሠላማዊና ጤናማ እንቅልፍ ለማግኘት ይረዳል፤
• ማንበብ አዕምሮን ያንፃል፣ የመገንዘብ አቅምን ያጎለብታል፤
• ማንበብ አማራጭ ሐሳቦችን በማመንጨት መፍትሄን ያፈልቃል፤
• ማንበብ አእምሮን በማረጋጋት መልካም ስብእናን ያጎናፅፋል፤
• ማንበብ መርሳትን አርቆ የማስታወስ ችሎታን ያዳብራል፤
• ማንበብ ግንኙነትን በማሳደግ ማህበራዊ ተሳትፎን ያሻሽላል፤
• ማንበብ በመረጃ የተደገፈ ውብ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያደርጋል፤
• ማንበብ በራስ መተማመንን ይፈጥራል፤
• ማንበብ አሉታዊ ሀሳቦችን በማስወገድ ሙግትና ጭቅጭቅን ያስቀራል፤
• ማንበብ ልክና ስህተት የሆኑ የህይወት ፍልስፍናዎች እንድንለያቸው ይረዳል፤
• ማንበብ ዕውቀትና ክህሎትን በማስገኘት ስኬታማ ሠዎች ያደርገናል፤
• ማንበብ የሠው ልጅ ባህርያት ጠንቀቅን እንድናውቅ ይረዳል፤
• ማንበብ ህይወታችን ቅርፅ እንዲኖረውና በመርህ እንድንመራ ይጠቅማል፤
• ማንበብ የሀሳብ ድርቀትን ያስወግዳል፤
• ማንበብ ሀገርና ትውልድ ያንፃል፤
• ማንበብ ግጭትና መለያየትን ይቀንሳል፤
• ማንበብ የአንድን ማህበረሰብ ስልጣኔ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አኗኗርን ይቀይራል፤
• ማንበብ ጨለምተኝነት በማራቅ ግጭትና ጦርነትን ይቀንሳል፤
• ማንበብ ልዩነትና ክርክርን ቀንሶ መግባባትን ያጎለብታል፤
• ማንበብ ግምታዊነት፣ ተጠራጣሪነትን፣ አስመሳይነት፣ ደመነብሳዊነትን፣ ስሜታዊነትን፣ ሐሰት፣ ሐሜት... አስወግዶ ምክንያታዊና የመረጃ ሠው እንድንሆን ይረዳልና ንባብን እንለማመድ።
....
#Share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#ለመለወጥ_ጥረት_ስለምታደርግ_ነፍስ#ለመለወጥ_ጥረት_ስለምታደርግ_ነፍስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ለአንድ መነኰሴ ያስተማረበት ምሳሌ....

..... “በከተማ መካከል ብዙ ወዳጆች ያሏት አንዲት ቆንጆ ሴተኛ አዳሪ ነበረች፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ወደ እርሷ ቀርቦ፡- "#መልካም_ሴትመልካም_ሴት #እንደምትሆኚ_ቃል_ከገባሽልኝ_አሁኑኑ_አገባሻለሁ#እንደምትሆኚ_ቃል_ከገባሽልኝ_አሁኑኑ_አገባሻለሁ" ይላታል፡፡
እርሷም በሐሳቡ ተስማምታ ቃል ስለገባችለት ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ፡፡ ወዳጆቿ ድጋሚ ሊያገኟት ስለ ፈለጉ እንዲህ እያሉ ይመካከሩ ነበር፡- "የከተማው ከንቲባ ወዳጃችንን ወደ ቤቱ ወስዷታል፡፡ በግልጽ ወደ ቤቱ ከሄድን ስለሚያውቅብንና ስለሚያስፈርድብን በቤቱ ጓሮ ዞረን እናፏጭላት፡፡ የፉጨታችንን ድምጽ ለይታ ስለምታውቃቸው ከቤቷ ወርዳ ትመጣለች፡፡ ለማንኛውም ግን እርሷ ትምጣልን እንጂ እባ አንጣላም" አሉ፡፡
በመጨረሻ እንደተመካከሩት በቤቱ ጓሮ ዞረው ሲያፏጩላት ጀሮዎቿ ቆሙ፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ ልትወርድ ስላልፈለገች #ፈጠን_ብላ_ወደ_እንግዳ_መቀበያው_አዳራሽ_ገባችና_በሮቹን_ዘጋግታ_ከውስጥ_ተቀመጠች፡፡

✥✥✥ ልክ እንደዚሁ ነፍሳችን በዚህች ሴት ስትመሰል ወዳጆቿ ደግሞ ምኞቶቻችን ይመስላሉ፡፡ ከንቲባው የሚመሰለው በምንወደው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያለው የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ በዘላለማዊ ቤታችን ወይም በመንግሥተ ሰማያት ሲመሰል የሚያፋጩላት ሰዎች ደግሞ በርኩሳን መናፍስት ይመሰላሉ፡፡✥✥✥

በመጨረሻም ይህን ምሳሌ ነፍሳችን ሁል ጊዜ እግዚአብሔር ከተጠጋች በእርሱ ኃይል እንደምትኖር ያስረዳናል፡፡”....

(ምንጭ፡- የበረሃ አባቶች ምክሮች በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
Share or join

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ የዝምታ ጩኸት +

እስራኤል ጭንቅ ላይ ናቸው:: ከባርነት ተላቅቀው ከግብፅ ከወጡና ጉዞ ከጀመሩ በኁዋላ ፈርኦን የለቀቀው ሕዝብ ጉልበት ቆጭቶት በቁጣ ነድዶ ሠራዊቱን አስከትቶ በፈጣን ሠረገላ እየጋለበ መጣባቸው:: ከፊታቸው ደግሞ የሚያስፈራ ባሕር ተደቅኖአል::

ሕዝቡ የፈረደበት ሙሴ ላይ ጮኹበት:: መጽሐፈ መቃብያን "ያንን ሁሉ ሕዝብ ሲጠብቅ ያልተበሳጨ ሙሴን አስበው" እንደሚል እንደ ሙሴ ትሑትና ታጋሽ መሪ ታይቶ አይታወቅም:: ልክ በዚያች ዛፍ ላይ እሳት ሲነድባት እንዳልተቃጠለች እስራኤላውያንም ሙሴ ላይ ለዓመታት ቢነዱም አላቃጠሉትም::

"በግብፅ መቃብር ጠፍቶ ልታስፈጀን ነው?" "ከሞት ባርነት በስንት ጣዕሙ?"
እስራኤል በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሙሴን በቁጣ እየጮኹ አስጨነቁት::

መሪነት ከባድ ነው:: ያንን ሁሉ ድንቅ ነገር አድርጎ እግዚአብሔር ነፃ ሲያወጣቸው ሙሴ ለእነርሱ ቤዛ ሆኖ ተሹሞ ብዙ ዋጋ ከፍሎአል:: ውለታውን ረስተው አፋጠጡት::

"ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ፡ አላቸው"

ሙሴ ሕዝቡን ከጩኸታቸው ሲያረጋጋ ሳለ የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሙሴ መጣ
"ሙሴ ሆይ ለምን ትጮኽብኛለህ?" አለው::

ልብ አድርጉ የጮኸው ሕዝቡ ነው ሙሴ አረጋጋ እንጂ ቃል አልተናገረም::

ሆኖም ሙሴ አፉ ዝም ቢል ልቡ ይጮኽ ነበር:: ከእስራኤል ጩኸት ይልቅ የሙሴ ዝምታ እግዚአብሔር ጆሮ ደረሰ:: እግዚአብሔር ኤልያስ እንዳላገጠባቸው የአሕዛብ አማልክት በጩኸት ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለም:: በትዕቢትና አመፅ ከሞላበት ጩኸት ይልቅ በተሰበረ ልብ የሚቀርብ ዝምታ እግዚአብሔር ጋር ይጮኻል::

የእስራኤል ጩኸት ፍርሃት ይነዛል:: ልናልቅ ነው የሚል ሽብር ይፈጥራል:: የሙሴ ዝምታ ግን ባሕር ይከፍላል::

ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን::
የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም::
የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም::
በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::

የኤርትራ ባሕር በዝምታ ተከፈለ:: እስከ ራማ የተሰማው ራሔል ስለ ልጆችዋ ያለቀሰችው ዕንባ ባሕር ከፈለ:: እመቤታችን ሆይ ስለ እኛ ስለልጆችሽ እባክሽን አልቅሺ:: የራሔል ዕንባ ራማ ከደረሰ የአንቺ ዕንባ የት ሊደርስ ነው? በየበረሃ እየወደቀ ስላለው ልጅሽ ስለሞተለት ወንድም እባክሽን ለምኚ::

በሙሴ በትር ባሕሩ ተከፈለ:: የኤርትራ ባሕር (ቀይ ባሕር [በግሪኩ erythos ማለት ቀይ ነው]) እጅግ ባለ ታሪክ ባሕር ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደረቅ ሆኖ ፀሐይ ያየውና ግማሽ ሚልየን የሚሆን ሕዝብ በመካከሉ ተራምዶ ያለፈበት ይህ ባሕር እንንደ ግድግዳ የቆመ ብቸኛው የዓለማችን ባሕር ነው::

በዚህ ባሕር እስራኤል ሲሻገሩ ፈርኦን ከነሠራዊቱ ሰጠመ:: በእግር የሔዱት የተሻገሩትን ባሕር በሠረገላ የሔዱት አቃታቸው:: የኤርትራ ባሕር ለእስራኤል ትንሣኤ ሲሆን ለፈርኦን ግን መቃብር ሆነ:: ፈርኦን ደንግጦ መመለስ የነበረበት ባሕሩ ሲከፈል ሲያይ ነበር:: ፈርኦንን ያደቆነ ሰይጣን ግን ባሕር መካከል ሳያቀስስ አልለቀቀውም::
እግዚአብሔር ማን ነው? ብሎ ነበር በዚያ ባሕር ተዋወቀው:: እሱ ሲሰጥም እስራኤል በኩራት "እግዚአብሔር ማን ነው? " ለሚለው የፈርኦን ጥያቄ ከባሕር ማዶ ሆነው መልስ ሠጡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" አሉ:: እስራኤል በኤርትራ ባሕር መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ "በባሕርና ደመና ተጠመቁ" ተብሎላቸዋል:: ፈርኦን ግን እስራኤል በተጠመቁበት ጠበል ውስጥ ሰጠመ::

የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ ከሙሴ ሌላ እስራኤልን ሲመራ የነበረ ጠባቂ ነበረ:: እርሱም የእስራኤል ጠባቂ (advocate of Israel) በመባል የሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነበር::

"በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ" ዘጸ 14:19 እንዲል ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን ዐምድ እየተመሰለ በመንገድ መራቸው::

ኢትዮጵያውያን ያለነው ከባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው:: ሁሉም መሻገር ይፈልጋል:: ከእኛ መካከል እንደ ፈርኦን ሰጥሞ የሚቀር ይኖራል:: እንደ እስራኤል የሚሻገር ይኖራል: : ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለእኛም ድረስልን:: ይህንን ክፉ ዘመን በክንፎችህ አሻግረን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 12 2013 ዓ ም
ድሬደዋ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

የክርስቲያንመከራ እና ሌሎች ቅዱስዮሐንስአፈወርቅ እንዳስተማረው በገብረእግዚአብሔርኪደ

Join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡

ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)

በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
  1.  እግዚያብሔርን ማወቅ

መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡

እግዚአብሄርን ማወቅ፡-

ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል

በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡

ታሪክን ይቀይራል

ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
2.በዕምነት ማደግ

ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
3.በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር

እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13)

join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)