መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
+ ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +

ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::

ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::

የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::

ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::

ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::

ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)

ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::

በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 23 2012 ዓ ም
ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ
ፎቶዎች :- ሊባኖስ ቤሩታዊትዋን ባዳነበት ሥፍራ እና ልዳ በቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ሥፍራ የተነሣሁት:: እናንተንም መቃብሩን ለመሣለም ያብቃችሁ::
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
✞✞✞ የልጅነት ጸጋ ካገኝን በኃላ ስለሚሰራ ኀጢአትና የስርአት መንገድ ✞✞✞

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅድስ እንዲሁም ከራሱ ጋር አስታርቆን ካዳነን በኅላ ስለምንሰራው ኀጢአት <<አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር >>በሚለው የዕለት ዕለት ጸሎት ውስጥ <<በደላችንን ይቅር በለን >>እንድንለው ጸሎት በማስተማርና ከኅጢአታችንም እንድንመለስ <<ንስሀ ግቡ >> በማለት ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን የመጀመሪያ መንገድ ንስሀን ሠርቶልናል። በአንድ ሀጢአተኝ ንስሀ መግባት በሰማይ መላእክት ዘንድ ታላቅ ደስታ የመሆኑ ምክንያት እግዚአብሔር የኀጢአተኝውን ንስሀ ተቀብሎ ኀጢአቱን ይቅር በማለቱ ነው። እግዚአብሔር ይቅር ባይለው ኖሮ በኀጢአተኝው ንስሀ መግባት በመላእክት ዘንድ ደስታ ባልተደረገ ነበር።
ማቴ 26:28 ላይ <<ኀጢአትን ለማስተሰረይ ስለ ብዙዎች የሚፈሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው >>ብሎ ለዓለም ሁሉ የኀጢአት ስርየት የሰጠውን ክቡር ደሙን ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐ 1:7-10 <<የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻል >> በማለት ኀጢአትን ብንሰራ ንስሀ ገብተን በምንበላው ቅድስ ስጋና በምንጠጣው ክቡር ደም ከኃጢአታችን እንደምንነጻ ያስረዳል። <<ኀጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኀጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኝ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም ተብሎ የተጻፈውን ማንበብ ግራ ከመጋባት ያድናል>>።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አስተያየት ጥያቄ ካለ
@Mentesnhot በዚ ይላኩልን

Join or share

@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}
:
መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !
( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
✟✟✟ክርስቶስ በአብ ክብር ሆኖ ስለሚሰራው ሦራ ✟✟✟

<<በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ >>ሮሜ 5:12 <<በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኝ እንደ ሆኑ >> ሮሜ 5:19 ተብሎ እንደተጻፈ ዓለም በልጅ እንዲድን እግዚአብሔር አንድያ ልጅን ወደ ዓለም ላከው >> 1ኛ ዮሐ 3:19 ይላል <<ሐጢአታችንን ያስተሰርይልን ልጅን ላከው >> 1ኛ ዮሐ 4:10 <<እርሱም ኀጢአታችንን ያስወግድ ዘንድ እንደተገለጠ ታውቃላችሁ >> 1ኛ ዮሐ 3:5 ተብሎ ተጽፋል። ከመልክቶቹ እንደምንረዳው በአንድ በአዳም በደል ሰው ሁሉ ኀጢአተኛ ቢሆንም ኃጢአተኝነትን ያስወግድ ዘንድ ጌታችን ወደ ዓለም መምጣቱ ነው። መጥቶም የውርስ ኀጢአትን በሞቱ ካስወገደልንና ከድኀነት በኀላ ለሚሰሩ ኀጢአቶች ንስሐ በመግባት ለኃጢአታችን መደምሰሻ ይሆነን ዘንድ ቅድስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንደሰጠን የሚገልጽ ነው። የመናፍቃኑ ስህተት <<በክብር ሆኖ የሰውነትን ሥራ ይሠራል >> ማለታቸው ደግሞ ከሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ ትምህርት ጋር ቀጥታ የሚጋጭ ነው።
ሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮ 5:19 ላይ <<ክርስቶስን ከእንግዲህ ያወቅነው ብንሆን ስንኳን አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም >>አለ። ይህም ማለት ክርስቶስን በሰውነቱ ሥራ በምድር ብናውቀውም ከዕርገት በኀላ በአብ ቀኝ (ክብር) በክብር ተቀምጦ በአምላክነት ሥራ እንጂ በሰውነት ሥራ በመራብ፤ በመጠማት፤ በመሰቀል ፤በመሞት፤ በመጸለይ፤ በማማለድ ወዘተ..... አናውቀውም ማለት ነው።
ስለዚህ ማንን እንስማ? በመንፈስ ቅድስ ሆኖ የተናገረውን ቅድስ ጳውሎስን ወይስ ያለማስተዋል የተጻፈውን የስህተት ትምህርት! መልሱ በሕይወቱ የመሰለ ቅድስ ጳውሎስን እንደሚሆን የታወቀ ነው። ዛሬም ነገም ለዘላለምም ክርስቶስ በአብ ቀኝ በክብር ተቀምጦ የሰውነትን ሥራ ማለትም አባቱን መለመን ሆነ በደሙ ማማለድ (መጸለይ) የለበትም።

ምንተስኖት
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አስተያየት ጥያቄ ካለ
@Mentesnhot በዚ ይላኩልን

Join or share
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል ጥገና ሱቅ ሔዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ" ብለው ሰጡት።
የሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ
"አባባ ስልክዎ ምንም አልሆነም ይሠራል" አላቸው።
ሽማግሌው ዓይናቸው ዕንባ አቀረረና
"ስልኩ ካልተበላሸ ... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድን ነው?" አሉ በደከመ ድምፅ።
★ ★ ★
ለወላጆቻችን የምናደርገው ትልቁ ሥጦታ ቢኖር ጊዜ መሥጠት ነው። የመኖራቸው ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። ዕድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በሕይወት ካሉ አሁኑኑ እንደውል። ይህንን ለማንበብ ጊዜ ካገኘን መቼም ለነሱ ለመደወል ጊዜ አናጣም።

"በምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር" ዘዳ 5:16
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Reposted 2011 ዓ ም

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
💠💠💠
አስገድደው ከቤተ ጣኦት እንኳ ቢያስገቡህ በዚያ እግዚአብሔር አምላክህን አመስግን። ሰይጣን በሚመለክበት ምድር መሃል ቢወስዱህም በዚያም ለአምላክህ ስገድ። በከሃድያን መሃልም ለአምላክህ ታመን።
የጣኦትና የሰይጣን ምድር የለውምና።

ይልቁንም ምድርና መላዋ የእግዚአብሔር ናት እንጅ!💠💠
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

#የክርስቲያን_መከራ እና ሌሎች #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

👉@linkortodoxe21
👉@linkortodoxe21
👉@linkortodoxe21
ድንጋይ በድንጋይ ላይ

ነቢዩ ዕንባቆም ሊያስተምር ሲሄድ የይሁዳ አባት ከባልንጀሮቹ ጋር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ባልንጀሮቹ ነቢዩን አክብረው ከመቀመጫቸው ተነሥተው ሲያሳልፉት እርሱ ግን ተቀምጦ ክብር ሳይሰጥ አሳለፈው፡፡

አስተምሮ ሲመለስም ከዚያው ድንጋይ ላይ ተቀምጦ እንዳይነሣ ኮርቶ እንዳይቀመጥ ፈርቶ ተሸፋፍኖ ሊያሳልፈው በሞከረ ጊዜ “እብን ላዕለ እብን ነቢሮ”፡፡ 

  ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል ከዚህ ሰው የሚወለደው ልጅ "አባቱን የሚሰልብ፣ እናቱን የሚያገባ፣ ጌታውን የሚሸጥ ነው" በማለት ትንቢት ተናገረበት፡፡

ክብር ለሚገባው ክብር አለመስጠት ምን ያህል እንደሚጎዳ ተመልከቱ፡፡ የነቢዩ ቃል ይፈጸም ዘንድ የይሁዳ እናትና አባት ያደረጓቸው ሥጋዊ ጥበቦች ይሁዳን ከመወለድ ማስቀረት አልቻሉም፡፡

ትንቢት የተነገረበት ልጅ በተወለደ ጊዜም ቢሆን እናትና አባቱ  የወሰዱት እርምጃ ትንቢቱን አላስቀረውም፡፡

ይሁዳን ወላጆቹ ከባሕር ቢጥሉትም የሌላ አገር ሰዎች አግኝተው ከባሕር እውጥተውት በሌላ አገር አደገ፡፡

እናትና አባቱ በባሕር ስለጣሉት ለጊዜው የሞተ ቢመስላቸውም  ይሁዳ ግን የነቢዩን ቃል ሳይፈጽም ሊሞት አይችልም፡፡

የነቢዩ ቃልም ተፈጸመ አባቱን ጦር ሜዳ ላይ ገደለው፣ እናቱንም ከሰፈር ፈልጎ ሚስት አደረጋት በመጨረሻም አምላኩን ኢየሱስ ክርስቶስን በሠላሳ ብር አሳልፎ ለአይሁድ ሸጠው፡፡

ይህ ታሪክ ብዙዎቻችንን ከንፈር የሚያስመጥጥ ነው፡፡ ነገር ግን በሕይወታችን ከዚህ ያልተሻለ ሥራ ላይ ተሰማርተን ልብሱ ላማረ፣ ሰውነቱ ለወፈረ፣ መልኩ ለጠራ፣ ቦርሳ ላዘለ ወዘተ… በማድላት ፈርተን አክብረን ዝቅ ብለን እንቀበላለን፡፡ በጣም ጥሩ ነው፡፡

በአንጻሩ ግን ምንም ለሌለው ድሃ፣ ልብሱ ላደፈ፣ መልኩ ለጠቆረ፣ ድሪቶ ለለበሰ ወዘተ… በማክበር ፈንታ ምራቃችንን እስከመትፋት ድረስ እንጸየፋለን፡፡

ለምን? የሰው ልጅ የሚያየው ፊትን፣አለባበስን፣አረማመድን አነጋገርን ወዘተ… ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር በውስጣችን ስላልሰረጸ የምንሠራው ሥራ ሁሉ በማድላት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

በየቢሮው ስትገቡ የአብዛኞች የዕለት ከዕለት ተግባር አድርገው የያዙት ፍርድን የመንፈግና የማድላት ሥራ ነው፡፡

ምናልባትም ጎንበስ ብላችሁ ሰላምታ ስታቀርቡለት በኩራት ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ መልስ ላይሰጣችሁ ይችላል፡፡

የደረሰባችሁን ችግር  እያነባችሁ አስረድታችሁትም ከምንም ሳይቆጥራችሁ መፍትሔ ሊነፍጋችሁ ይችላል፡፡

የተበደላችሁትን ነገር ምርር ብላችሁ እየነገራችሁት እንደ ሞኝ ቆጥሮም የሚስቅባችሁ ቢሆን በዚያ ሰው አትበሳጩ ያ ሰው በወንበር ላይ የተቀመጠ ግዑዝ ነገር እንጅ ሰው ሊባል ከቶ አይችልም፡፡

ያልተደረገውን ተደረገ፣ የተደረገውን አልተደረገም፤ የሆነውን አልሆነም፣ ያልሆነውን ሆነ እያለ ሊሸነግልና ሊያታልል የሚሞክር ሰው በዋዘኞች ወንበር የተቀመጠ ድንጋይ ነው፡፡

ምክንያቱም ፍርድ የመስጠት አቅሙ በአለባበስ፣ በዘር፣በወገን፣በቋንቋ ወዘተ… ላይ የተመሠረተ ነውና በተጨማሪም ሰው ሊባል የሚችልበትን ሥራ በአግባቡ እየሠራ አይደለምና፡፡

ፈሪሐ እግዚአብሔር በውስጡ የሌለው ሰው መቼም ቢሆን ሰውን ለማክበር የሚችል ትሑት ልቡና ሊኖረው አይችልም፡፡

ሳይማር ያስተማረውን የወገኑን ገንዘብ እየበላ ያረጀ ልብስ የለበሰ ወገኑን ከወገን የማይቆጥር ሰው በግብር የይሁዳን አባት ይመስለዋል፡፡

የእግዚአብሔር ክቡር ፍጡር የሆነን ሰው መቀበል፣ማክበር በረከት የምናገኝበት እንጅ የምንዋረድበት አይደለም፡፡

ስለዚህ የይሁዳ አባት በሄደበት መንገድ ተጉዘን ከመጎዳት ለመዳን ክብር ለሚገባው የሰው ልጅ ሁሉ ክብርን መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ከዚያ ውጭ ግን "ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል" የሚለው የነቢዩ ትንቢት በእኛ እና በልጆቻችን ላይ መድረሱ አይቀርም፡፡

ስለዚህ በትሕትና ራሳችንን ዝቅ አድርገን ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘባችን አድርገን ለመኖር በቤቱ እስከ ፍጻሜያችን ድረስ መኖርን መምረጥ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

ለዚህም  የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን፡

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሰውየው ብልህ ነጋዴ ነው፡፡ ቤቱ መንገድ ዳር ስለሆነ እዛው በሩ ላይ መሬት አንጥፎ ጫማ ይነግዳል :: የንግድ ቦታው ለወጪ ወራጁ ሁሉ ቶሎ ዓይን ውስጥ የሚገባ ስለነበር ገብያው ተጧጧፈለት:: ይህን የተመለከቱ መሰል ነጋዴዎች የልብስ ንግዳችውን ትተው ከእርሱ አጠገብ ሆነው ጫማ ደርድረው መሸጥ ጀመሩ:: በዚህም የብልው ነጋዴ ገቢ ከዕለት ወደ ዕለት መቀነስ ጀመረ:: ይህን ያስተዋለው ብልሁ ነጋዴም አንድ ሀሳብ መጣለት ነግዶ ያጠራቀመውን ገንዘብ በሙሉ አውጥቶ ትንሺዬ ሱቅ ከፍቶ ከጫማ የተለየ በአካባቢው የማይሸጡ ነገሮችን መሸጥ ትርፋማ መሆን:: እንደ ሀሳብም አደረገ በአካባቢው ሱቅ ስላልነበረ ገብያው በወረፋ መዥጎድጎድ ጀመረ.... ይህን የተመለከቱ እነዛ ጫማ መሸጥ የጀመሩት ነጋዴዎች ብዙ ሳይቆዮ በግራና በቀኝ ተመሳሳይ ነገሮችን የሚሸጡበት ሱቆችን ከፈቱና ብልሁን ነጋዴ መሀል ከተቱት :: ገብያውንም ዘጉበት ይህን ጊዜ ብልሁ ነጋዴ የእራሱ ሱቅ ላይ አንድ ነገር ጽፎ ለጠፈ.....

"የሁለቱ መስኮቶች በር ይህ ነው".......የሚል ጽሁፍ

👇👇👇👇
ኩረጃ የሰውን የመመኘት ውጤት ነው ::አንዱ ጫማ ሲሸጥ ሊላው ካልሲ መሸጥ ሲችል በተመሳሳይ ጫማ ካልሸጥኩ የሚል ከሆነ የሌላውን ገብያ ከመዝጋቱም በላይ ለራሱም ማትረፍ አይቻለሁም:: የሚተረፈው ብዙዎች የሚሸጡትን በመሸጥ ሳይሆን ጥቂቶች ያልያዙትን ይዞ በመገኘት ነው :: እኛ ኢትዮጲያውያን መተማማትና እንደ ባህላችን ከቆጠርን ዋል ሰንበት በለናል በዚሁ ከቀጠልን ለኩረጃም የማይመጥነውን ኢትዮጲያዊ ዜግነት ሳንሰጠው አንቀርም::

"፤ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።" (ኦሪት ዘጸአት 20: 17


@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ተስፋ ሊቆረጥለት አይገባም

ዲያብሎስ ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ኃጢአት መስራትና እንዲሰሩ ማድረግ ወይም ክፋ ማሰብ እና ክፋቱንም የሰው ልጆች እንዲቀበሉት ማድረግ አያቆምም ፤
ከውድቀቱ ጀምሮ መልካም ነገር ሰርቶ አያቅም
ስለዚህ የሰው ልጆች የትኛውንም ያህል ኃጢአት ብንሰራ ከእርሱ እንደምንሻል ማወቅ አለብን ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ መልካም ስራ ሊያሰራን ይችላል ።

የሰው ልጅን ነፍስ ለክፋት እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሚከራከራት ሰይጣን ነው አትድኝም ፣ አትፀድቂም ፣ አትለወጪም ወዘተ... በማለት ተስፋ ሳይኖረው ተስፋ ለማስቆረጥ ሚጥረው ነገረ ግን
ማስተዋል ያለብን ሰይጣን ነው ምህረት ስላሎደደ ያልዳነው ፣ ያልፀደቀው ፣ ያልተለወጠው ። ስለዚህ በዘመኑ ሁሉ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ተጠግቶ መልካም ነገር ቢሰራ ፤ ለምሳሌ ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ቢፈፅም ፣ ቢፀልይ ወዘተ... መንፈሳዊ ትሩፋቶችን ቢሰራ ይድናል ዲያብሎስንም ያሸንፈዋል ። ምክንያቱም ሰይጣንና ሰራዊቱ ምህረት መጠየቅን እና መልካም ስራ መስራትን አሎደዱምና ። ስለዚህ ተስፋ ሊቆረጥለት አይገባም ምክንያቱም በምንም ቢሰላ በኃጢአት እሱ ይበልጠናል ። እኛ ግን ከእግዚአብሔር ይቅርታንና ምህረትን ለምነን ንስሐ ገብተን ቀኖናችንን ጨረሰን ፍትሐት ተደሮጎልን ስንቆርብ እና መንፈሳዊ ስራዎችን በቻልነው እና ባቅማችን ልክ በእግዚአብሔር እርዳታ ስንሰራ ፈጣሪያችን ይምረናል ይደሰትብናል ። ያኔ ሰይጣንንም እንበልጠዋለን ፤ ግን ከሰይጣን ጋር ለመፎካከር ሳይሆን ዋና ነጥቡ የሰው ልጆች የለበስነው ስጋ ድካም አለበትና ድንገት ባለማወቅ ፈጣሪያችንን ብናሳዝነው ተስፋ ለማስቆረጥ ቀድሞ ሚከሰን ሰይጣን ስለሆነ ተስፋ ሳንቆርጥ ከእግዚአብሔር ምህረት ተይቀን እንደምንድን እንድንነቃበት ነው ። ስለዚህ በሰው ልጅ መልካም ስራ እየቀናና እየተቃጠለ እየሰለቸው እየራቀን ይመጣል ።

Join or share

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ተወዳጆች ሆይ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጥቶ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነውን? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነውና፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡

ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው።

✟ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ✟

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አፍህ ሳይሆን ስራህ ይመስክርብዙ ሰዎች ከመፅሃፍ ያነበቧቸዉን ምክሮች ለራሳቸዉ ሳይተገብሩ ላንተ እንድትተገብረዉ ይነግሩሃል፡ ስለዚህ የተግባር ሰዉ ያልሆነ ሰዉ የቱንም ያህል እዉቀት ቢኖረዉ ከቃላት ዉርጅብኝ ጠብ የማይል ህይወት የለዉም፡፡ አንተ ግን የተግባር ሰዉ ለመሆን እራስህን አስለምድ፡ ተግባር ከቃል በላይ ድምጹ የጎላ ነዉ!

• ከስህተትህ ተማር

ማንም ፍፁም ሰዉ የለም፡፡ በመዉደቅህ የበታችነት ስሜት ሊሰማህ አይገባም ምክንያቱም ሁሉም ወደተሻለ ደረጃ የሚደርሰዉ ወድቆ ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አይነት ስህተት ብዙ ጊዜ እየተሳሳትክ የተሻለ ዉጤት አትጠብቅ

• ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ዉስጥ መልካም ተፅእኖ የሚያደርጉብህን ሰዎች ብቻ ለይተህ ጓደኛ አድርግ

• መናገር በሚገባህ ነገር ላይ ብቻ ተናገር

በሁሉም ስብሰባና ዉይይት ዉስጥ ግዴታ መናገር የለብህም፡፡ ትክክል መሆንህን ለሰዎች ሁሌ ለማሳየት መሞከር እራስህን ያደክምሃል፡፡ ብቻ ትክክል መሆንህን ለራስህ አረጋግጥ፡፡ ሌላዉ እዉነታን ላለመቀበል አትሞክር፤ ከእዉነታዉ ጋር አብረህ ሂድ።
አንዳንዴ እየራበህ የማትበላበት፤ አንዳንዴ ደሞ ጠግበህ የምትመገብበት ጊዜ አለ፡፡

አንዳንዴ ሳትኖር የምትሞትበት፤ አንዳንዴ ደሞ ሞተህም የምትኖርበት ጊዜ አለ፡፡

አንዳንዴ አስደስቶህ የምታለቅስበት፤ አንዳንዴ ደሞ አስለቅሶህ የምትስቅበት ጊዜ አለ፡፡

አንዳንዴ ፈልገህ የማታገኘው፤ አንዳንዴ ደሞ ሳትፈልግ የምታገኘው ብዙ ነገር አለ፡፡

አንዳንዴ ተናግረህ የማትጨርሰው፤ አንዳንዴ ደሞ ጨርሰህ የማታወራው ወሬ አለ፡፡

አንዳንዴ እየወደድክ የምትርቀው፤ አንዳንዴ ደሞ እየጠላህ የምትቀርበው ሰው አለ፡፡

አንዳንዴ ፍቅሩን ሳይገልፅልህ የሚወድህ፤ አንዳንዴ ደሞ እወድሀለው እያለ የሚጠላህም ሰው አለ፡፡

ብቻ ህይወት በብዙ የተጠበቁና ያልተጠበቁ አስደሳች ፣ አሳዛኝ ፣ ተስፋ አስቆራጭ ፣ ተሰፋን ሰጪ ሁነቶች የተሞላች ናት፡፡ በየትኛውም አዳጋች ሁኔታ ውስጥ እንሁን "ነገ የተሻለ ይሆናል" ብለን ለእራሳችን እንንገረው፡፡ ለዚህ እኮ ነው "ነገን ብለን እንጂ ዛሬማ አይነፋም" ያለው አራዳው ጓደኛዬ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM