መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ኦርቶዶክሶች

💠ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ ይድረስ፡፡

🔘እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦

👉እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል
(ማቴ1:23) ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ
ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ
ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2 ) ንፅህት በስጋሽም ድንግል ነሽ
(ማቴ1:23) (ህዝ44:2) ያሸናፊ የልኡል እግዚአብሔር እናት ሆይ
(ሉቃ1:35)ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ1:28 እና ሉቃ1:32) የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ
ይበልሽ ልኡል እግዚአብሄር ካንች ጋር ነውና(ሉቃ1:28-30) ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመዳህኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን በ(1ቆሮ5:20) በፅድቅ ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልና ሃጢአታችንም ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን።
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
👉ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡

ኦርቶዶክስ መልሥ አላት

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመሥቀሉ ክቡር አሜን

ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ
#ሼር
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ የአባቶች ድንቅ ጥበብ የተሞሉ መልሶች +

ባለ ብዙ ታሪኩ የወሊሶው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያጠምቁና ያስተምሩ በነበረበት ሥፍራ አንድ በትዕቢት መንፈስ የሚሰቃይ ወጣት መጣና መፈክርነት ያዘለ ቃል ተናገረ:: ክብር ይግባትና ንግግሩ የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚቃወም ነበር::

ወደ አባ ዲዮስቆሮስ ቀርቦ እንዲህ አላቸው :-
ወጣቱ :- "ድንግል ማርያም እኮ ብዙ ልጆች አሉአት"
አቡኑ :- "ባታውቀው ነው እንጂ ለአንተም እኮ እናትህ ናት!"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

የቦሩ ሜዳው መምህር አካለ ወልድ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ኢየሩሳሌምን ሲሳለሙ ድንገት የሌላ ሀገር መነኮሳት መጥተው በዱላ አጣደፉአቸው:: ነገሩን ሲጠይቁ ለምን በእግዚአብሔር ሦስትነት እንደማያምን ሰባልዮሳዊ
አንድ ጣታችሁን ብቻ ወደላይ ጠቁማችሁ ታማትባላችሁ? ለምን እንደ እኛ ሦስት ጣቶቻችሁን (እንደሚጎርስ ሰው) በአንድ ገጥማችሁአታማትቡም?" አሉና በቁጣ ጮኹ::

መምህር አካለ ወልድ በፈሊጥ እንጂ በፍልጥ የሚሆን ነገር ስለሌለ ቁጭ ብለን እንነጋገር አሉ::

"እኛ በአንድ ጣት ብናማትብም ሦስትነቱን እናምናለን:: አንድዋ ጣትም እኮ ሦስት አንጉዋዎች አሉአት:: አንድ መሆንዋ አንድነቱን ሦስቱ አንጉዋ ሦስትነቱን ያስረዳል::
የታችኛው አንጉዋ መሠረት ነውና የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መሠረት ይሆነው የአብ ምሳሌ ነው:: የመካከለኛው በሁለቱ ህልው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው : የላይኛው ጥፍር የለበሰው ደግሞ ባዕድ ሥጋን የተዋሐደ የወልድ ምሳሌ ነው:: ሀገራችሁ ሔዳችሁ አስተምሩበት" አሉአቸው

(ይህ ትርጓሜ በወንጌል አንድምታ ላይ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን አወጣለሁ የሚለው በተተረጎመበት ሥፍራ ይገኛል)

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስን ደግሞ አንድ ወጣት መጥቶ
"ለእግዚአብሔር የአምልኮ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት እንደሚሰገድ አውቃለሁ:: ግን በቅዱሳን ሥዕል ፊትና በፈጣሪ ፊት ስሰግድ እንዴት ለይቼ የጸጋ የአምልኮ እያልኩ መስገድ እችላለሁ?" አላቸው
ንቡረ ዕድ መለሱ
"አንተ ዝም ብለህ ስገድ እነርሱ የድርሻቸውን ይወስዳሉ!"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ሺኖዳ ከሾፌራቸው ጋር ሲሔዱ ሾፌሩ መኪናውን ከመጠን በላይ አበረረው
ፓትርያርኩ እንዲህ አሉ
"ልጄ ስለምንቸኩል ቀስ በል”

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አንድ ታላቅ የጉባኤ መምህር ተጠየቁ
"ካህናት ዶሮና በግ ወዘተ ማረድ የማይችሉት ለምንድን ነው?"
"የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንደ ኦሪት ካህን የእንስሳ ደም አያፈስስም"
"ካህናቱስ መልካም ሴት ልጅስ ማረድ ለምን ትከለከላለች?"
"ሕይወት የምትሠጥ ሴት ሕይወት አታጠፋም"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አለቃ ለማ ልጃቸውን ለምን በጣም እንደሚገርፉት ተጠየቁ
"ልጄን እኔ ካልቀጣሁት እግዚአብሔር ይቀጣብኛል
የእግዚአብሔር ቅጣት ደግሞ ሞት ነው"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አንዱ መጥቶ አንድን የመጽሐፍ መምህር
"ጥምቀት ጋድ አለው ወይ?" አላቸው
እርሳቸውም መለሱ
"አምና ነበረው የዘንድሮን እንጃ"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ዮሐንስ አንድን ሥራ ፈቶ የአብነት ተማሪዎችን
ሲማሩ ከሩቅ የሚያይ ወጣት አዩና
"አንተ አትማርም ወይ?" አሉት
"አይ አባቴ ምን እየበላሁ ልማር ብለው ነው?" አለ እየተቅለሰለሰ
አቡኑ መለሱ
"አሁን ምን እየበላህ ነው የምትደነቁረው?"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሳሉ አንድ ወጣት ሰርቆ ሲያመልጥ አባርረው ይዘው ሰዎች አመጡላቸው
ዕቃው ከተመለሰ በኁዋላ ሌባውን ለሕግ አሳልፈው ሊሠጡ ሲቸኩሉ አይሆንም አሉአቸው:: ሰዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወደ ፖሊስ እንውሰደው አሉአቸው
እርሳቸውም መለሱ
"ኦርቶዶክሶች ተሰራርቀው ተካስሰው መጡ ከሚል ስም ውጪ ምንም አናተርፍም"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ብፁዕ አቡነ ሰላማን አንዱ ባለ ሥልጣን ጉዳይ ሊያስፈጽሙ በሔዱበት ቢሮው "አንተ" ብሎ በማናገር ሊያቃልላቸው ሞከረ::
እርሳቸው እንዲህ አሉት
"የቤተ ክርስቲያኔን ጉዳይ ፈጽምልኝ እንጂ እንኩዋን አንተ ቀርቶ አንቺም ብለህ ጥራኝ

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

የደርግ መንግሥት እንዳሻው ሊዘውራቸው ተስፋ ያደረገባቸው ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በመሪው አማካኝነት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
"የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ወደ ሙዝየምነት የመቀየር ሃሳብ በመንግሥት በኩል ተይዞአል:: ይህንን ለማድረግም የእርስዎን ድጋፍ የግድ ነው"
ፓትርያርኩ መለሱ
"ምን ችግር አለ በቅርቡ የዓመቱ ሥላሴ ክብረ በዓል ስላለ ሕዝቡ ባለበት እናንተም ተገኝታችሁ አብረን ለምን አናወያየውም"
በዚህ ምላሽ ምክንያት እቅዱ ተሠረዘ

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
“ላገቡት” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ባልና ሚስት አንድ መኾናቸውን ብዙ ጊዜ ስለ ተማራችሁት እርሱን አልደግምላችሁም፡፡ ከዚህ ተነሥቼ ግን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦ ከሰውነታችሁ ውስጥ አንዱ ሕዋስ ቢታመም ቆርጣችሁ ትጥሉታላችሁን? ከሕመሙ ይፈወስ ዘንድ የምትጥሩ አይደላችሁምን? ለትዳር አጋራችሁም እንደዚህ መኾን አለባችሁ፡፡ እንደዉም'ኮ፥ ከሰውነታችሁ ሕዋስ ውስጥ ያለው በሽታ አንዳንዴ ላይድን ይችላል፡፡ የትዳር አጋራችሁ ግን፥ ምንም ክፉ ቢኾንም ሊለወጥ ይችላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚኖረው አንዳንዱ ችግር ለምሳሌ ልምሾ እጅ ወይም እግር ሥራ መሥራትን ሊከለክለን፣ በሌላዉ የሰውነታችን ክፍል ላይ ጫና ሊያሳድርብን ይችላል፤ ነገር ግን ይበልጥ እንክብካቤ እናደርግለታለን እንጂ ቆርጠን አንጥለዉም፡፡ ታዲያ መዳን ለማይችለው ሰውነታችን ይህን ያህል እንብካቤ እያደረግንለት ሳለ፥ የመዳን (የመለወጥ) ዕድል ያለው አካላችንን (ባለ ትዳራችንን) መቁረጥ (መፍታት) እንደ አማራጭ ማስቀመጣችን እንዴት ብናብድ ነው?

@linkortodoxe21
አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤ ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው። በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ወርሀዊ በአል በሰላም አደረሳቹ
ጸሎት መተው ለጠላት ምቹ መሆን ነው!

ወዳጄ አይደለም ሁሌ አንድ ቀን ጸሎት መተው ለአንድ ቀን ለሰይጣን እጅ መስጠት ነው፡፡ አንድ ቀን ጸሎት ማስታጎል ለአንድ ቀን በሰይጣን እንደ መማረክ ነው፡፡

ጸሎት ስንተው ለሥጋዊም ለመንፈሳዊም ጠላታችን በነገሮች ሁሉ ምቹ ነው የምትሆነው፡፡ ያ ማለት በየትኛውም የሕይወት አቅጣጫ፣ የጠላት ጡጫ እኛ ላይ ሊያርፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ ለሥጋችን ምግብ መብላት እንደማንተው ሁሉ የነፍስ ምግብ እና የጸጋ ወደብ የሆነውን ጸሎት አንተው፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።

ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡

ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።

ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡

ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።

ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም)
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”
(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡

የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”
(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨

ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።

የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"
(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።
ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል።

ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"
(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።

ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

“ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨

ይቀጥላል...
መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ


@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
+ ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +

ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::

ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::

የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::

ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::

ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::

ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)

ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::

በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 23 2012 ዓ ም
ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ
ፎቶዎች :- ሊባኖስ ቤሩታዊትዋን ባዳነበት ሥፍራ እና ልዳ በቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ሥፍራ የተነሣሁት:: እናንተንም መቃብሩን ለመሣለም ያብቃችሁ::
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
✞✞✞ የልጅነት ጸጋ ካገኝን በኃላ ስለሚሰራ ኀጢአትና የስርአት መንገድ ✞✞✞

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅድስ እንዲሁም ከራሱ ጋር አስታርቆን ካዳነን በኅላ ስለምንሰራው ኀጢአት <<አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር >>በሚለው የዕለት ዕለት ጸሎት ውስጥ <<በደላችንን ይቅር በለን >>እንድንለው ጸሎት በማስተማርና ከኅጢአታችንም እንድንመለስ <<ንስሀ ግቡ >> በማለት ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን የመጀመሪያ መንገድ ንስሀን ሠርቶልናል። በአንድ ሀጢአተኝ ንስሀ መግባት በሰማይ መላእክት ዘንድ ታላቅ ደስታ የመሆኑ ምክንያት እግዚአብሔር የኀጢአተኝውን ንስሀ ተቀብሎ ኀጢአቱን ይቅር በማለቱ ነው። እግዚአብሔር ይቅር ባይለው ኖሮ በኀጢአተኝው ንስሀ መግባት በመላእክት ዘንድ ደስታ ባልተደረገ ነበር።
ማቴ 26:28 ላይ <<ኀጢአትን ለማስተሰረይ ስለ ብዙዎች የሚፈሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው >>ብሎ ለዓለም ሁሉ የኀጢአት ስርየት የሰጠውን ክቡር ደሙን ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐ 1:7-10 <<የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻል >> በማለት ኀጢአትን ብንሰራ ንስሀ ገብተን በምንበላው ቅድስ ስጋና በምንጠጣው ክቡር ደም ከኃጢአታችን እንደምንነጻ ያስረዳል። <<ኀጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኀጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኝ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም ተብሎ የተጻፈውን ማንበብ ግራ ከመጋባት ያድናል>>።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አስተያየት ጥያቄ ካለ
@Mentesnhot በዚ ይላኩልን

Join or share

@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}
:
መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !
( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
✟✟✟ክርስቶስ በአብ ክብር ሆኖ ስለሚሰራው ሦራ ✟✟✟

<<በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ >>ሮሜ 5:12 <<በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኝ እንደ ሆኑ >> ሮሜ 5:19 ተብሎ እንደተጻፈ ዓለም በልጅ እንዲድን እግዚአብሔር አንድያ ልጅን ወደ ዓለም ላከው >> 1ኛ ዮሐ 3:19 ይላል <<ሐጢአታችንን ያስተሰርይልን ልጅን ላከው >> 1ኛ ዮሐ 4:10 <<እርሱም ኀጢአታችንን ያስወግድ ዘንድ እንደተገለጠ ታውቃላችሁ >> 1ኛ ዮሐ 3:5 ተብሎ ተጽፋል። ከመልክቶቹ እንደምንረዳው በአንድ በአዳም በደል ሰው ሁሉ ኀጢአተኛ ቢሆንም ኃጢአተኝነትን ያስወግድ ዘንድ ጌታችን ወደ ዓለም መምጣቱ ነው። መጥቶም የውርስ ኀጢአትን በሞቱ ካስወገደልንና ከድኀነት በኀላ ለሚሰሩ ኀጢአቶች ንስሐ በመግባት ለኃጢአታችን መደምሰሻ ይሆነን ዘንድ ቅድስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንደሰጠን የሚገልጽ ነው። የመናፍቃኑ ስህተት <<በክብር ሆኖ የሰውነትን ሥራ ይሠራል >> ማለታቸው ደግሞ ከሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ ትምህርት ጋር ቀጥታ የሚጋጭ ነው።
ሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮ 5:19 ላይ <<ክርስቶስን ከእንግዲህ ያወቅነው ብንሆን ስንኳን አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም >>አለ። ይህም ማለት ክርስቶስን በሰውነቱ ሥራ በምድር ብናውቀውም ከዕርገት በኀላ በአብ ቀኝ (ክብር) በክብር ተቀምጦ በአምላክነት ሥራ እንጂ በሰውነት ሥራ በመራብ፤ በመጠማት፤ በመሰቀል ፤በመሞት፤ በመጸለይ፤ በማማለድ ወዘተ..... አናውቀውም ማለት ነው።
ስለዚህ ማንን እንስማ? በመንፈስ ቅድስ ሆኖ የተናገረውን ቅድስ ጳውሎስን ወይስ ያለማስተዋል የተጻፈውን የስህተት ትምህርት! መልሱ በሕይወቱ የመሰለ ቅድስ ጳውሎስን እንደሚሆን የታወቀ ነው። ዛሬም ነገም ለዘላለምም ክርስቶስ በአብ ቀኝ በክብር ተቀምጦ የሰውነትን ሥራ ማለትም አባቱን መለመን ሆነ በደሙ ማማለድ (መጸለይ) የለበትም።

ምንተስኖት
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አስተያየት ጥያቄ ካለ
@Mentesnhot በዚ ይላኩልን

Join or share
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል ጥገና ሱቅ ሔዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ" ብለው ሰጡት።
የሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ
"አባባ ስልክዎ ምንም አልሆነም ይሠራል" አላቸው።
ሽማግሌው ዓይናቸው ዕንባ አቀረረና
"ስልኩ ካልተበላሸ ... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድን ነው?" አሉ በደከመ ድምፅ።
★ ★ ★
ለወላጆቻችን የምናደርገው ትልቁ ሥጦታ ቢኖር ጊዜ መሥጠት ነው። የመኖራቸው ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። ዕድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በሕይወት ካሉ አሁኑኑ እንደውል። ይህንን ለማንበብ ጊዜ ካገኘን መቼም ለነሱ ለመደወል ጊዜ አናጣም።

"በምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር" ዘዳ 5:16
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Reposted 2011 ዓ ም

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
💠💠💠
አስገድደው ከቤተ ጣኦት እንኳ ቢያስገቡህ በዚያ እግዚአብሔር አምላክህን አመስግን። ሰይጣን በሚመለክበት ምድር መሃል ቢወስዱህም በዚያም ለአምላክህ ስገድ። በከሃድያን መሃልም ለአምላክህ ታመን።
የጣኦትና የሰይጣን ምድር የለውምና።

ይልቁንም ምድርና መላዋ የእግዚአብሔር ናት እንጅ!💠💠
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

#የክርስቲያን_መከራ እና ሌሎች #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

👉@linkortodoxe21
👉@linkortodoxe21
👉@linkortodoxe21
ድንጋይ በድንጋይ ላይ

ነቢዩ ዕንባቆም ሊያስተምር ሲሄድ የይሁዳ አባት ከባልንጀሮቹ ጋር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ባልንጀሮቹ ነቢዩን አክብረው ከመቀመጫቸው ተነሥተው ሲያሳልፉት እርሱ ግን ተቀምጦ ክብር ሳይሰጥ አሳለፈው፡፡

አስተምሮ ሲመለስም ከዚያው ድንጋይ ላይ ተቀምጦ እንዳይነሣ ኮርቶ እንዳይቀመጥ ፈርቶ ተሸፋፍኖ ሊያሳልፈው በሞከረ ጊዜ “እብን ላዕለ እብን ነቢሮ”፡፡ 

  ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል ከዚህ ሰው የሚወለደው ልጅ "አባቱን የሚሰልብ፣ እናቱን የሚያገባ፣ ጌታውን የሚሸጥ ነው" በማለት ትንቢት ተናገረበት፡፡

ክብር ለሚገባው ክብር አለመስጠት ምን ያህል እንደሚጎዳ ተመልከቱ፡፡ የነቢዩ ቃል ይፈጸም ዘንድ የይሁዳ እናትና አባት ያደረጓቸው ሥጋዊ ጥበቦች ይሁዳን ከመወለድ ማስቀረት አልቻሉም፡፡

ትንቢት የተነገረበት ልጅ በተወለደ ጊዜም ቢሆን እናትና አባቱ  የወሰዱት እርምጃ ትንቢቱን አላስቀረውም፡፡

ይሁዳን ወላጆቹ ከባሕር ቢጥሉትም የሌላ አገር ሰዎች አግኝተው ከባሕር እውጥተውት በሌላ አገር አደገ፡፡

እናትና አባቱ በባሕር ስለጣሉት ለጊዜው የሞተ ቢመስላቸውም  ይሁዳ ግን የነቢዩን ቃል ሳይፈጽም ሊሞት አይችልም፡፡

የነቢዩ ቃልም ተፈጸመ አባቱን ጦር ሜዳ ላይ ገደለው፣ እናቱንም ከሰፈር ፈልጎ ሚስት አደረጋት በመጨረሻም አምላኩን ኢየሱስ ክርስቶስን በሠላሳ ብር አሳልፎ ለአይሁድ ሸጠው፡፡

ይህ ታሪክ ብዙዎቻችንን ከንፈር የሚያስመጥጥ ነው፡፡ ነገር ግን በሕይወታችን ከዚህ ያልተሻለ ሥራ ላይ ተሰማርተን ልብሱ ላማረ፣ ሰውነቱ ለወፈረ፣ መልኩ ለጠራ፣ ቦርሳ ላዘለ ወዘተ… በማድላት ፈርተን አክብረን ዝቅ ብለን እንቀበላለን፡፡ በጣም ጥሩ ነው፡፡

በአንጻሩ ግን ምንም ለሌለው ድሃ፣ ልብሱ ላደፈ፣ መልኩ ለጠቆረ፣ ድሪቶ ለለበሰ ወዘተ… በማክበር ፈንታ ምራቃችንን እስከመትፋት ድረስ እንጸየፋለን፡፡

ለምን? የሰው ልጅ የሚያየው ፊትን፣አለባበስን፣አረማመድን አነጋገርን ወዘተ… ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር በውስጣችን ስላልሰረጸ የምንሠራው ሥራ ሁሉ በማድላት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

በየቢሮው ስትገቡ የአብዛኞች የዕለት ከዕለት ተግባር አድርገው የያዙት ፍርድን የመንፈግና የማድላት ሥራ ነው፡፡

ምናልባትም ጎንበስ ብላችሁ ሰላምታ ስታቀርቡለት በኩራት ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ መልስ ላይሰጣችሁ ይችላል፡፡

የደረሰባችሁን ችግር  እያነባችሁ አስረድታችሁትም ከምንም ሳይቆጥራችሁ መፍትሔ ሊነፍጋችሁ ይችላል፡፡

የተበደላችሁትን ነገር ምርር ብላችሁ እየነገራችሁት እንደ ሞኝ ቆጥሮም የሚስቅባችሁ ቢሆን በዚያ ሰው አትበሳጩ ያ ሰው በወንበር ላይ የተቀመጠ ግዑዝ ነገር እንጅ ሰው ሊባል ከቶ አይችልም፡፡

ያልተደረገውን ተደረገ፣ የተደረገውን አልተደረገም፤ የሆነውን አልሆነም፣ ያልሆነውን ሆነ እያለ ሊሸነግልና ሊያታልል የሚሞክር ሰው በዋዘኞች ወንበር የተቀመጠ ድንጋይ ነው፡፡

ምክንያቱም ፍርድ የመስጠት አቅሙ በአለባበስ፣ በዘር፣በወገን፣በቋንቋ ወዘተ… ላይ የተመሠረተ ነውና በተጨማሪም ሰው ሊባል የሚችልበትን ሥራ በአግባቡ እየሠራ አይደለምና፡፡

ፈሪሐ እግዚአብሔር በውስጡ የሌለው ሰው መቼም ቢሆን ሰውን ለማክበር የሚችል ትሑት ልቡና ሊኖረው አይችልም፡፡

ሳይማር ያስተማረውን የወገኑን ገንዘብ እየበላ ያረጀ ልብስ የለበሰ ወገኑን ከወገን የማይቆጥር ሰው በግብር የይሁዳን አባት ይመስለዋል፡፡

የእግዚአብሔር ክቡር ፍጡር የሆነን ሰው መቀበል፣ማክበር በረከት የምናገኝበት እንጅ የምንዋረድበት አይደለም፡፡

ስለዚህ የይሁዳ አባት በሄደበት መንገድ ተጉዘን ከመጎዳት ለመዳን ክብር ለሚገባው የሰው ልጅ ሁሉ ክብርን መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ከዚያ ውጭ ግን "ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል" የሚለው የነቢዩ ትንቢት በእኛ እና በልጆቻችን ላይ መድረሱ አይቀርም፡፡

ስለዚህ በትሕትና ራሳችንን ዝቅ አድርገን ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘባችን አድርገን ለመኖር በቤቱ እስከ ፍጻሜያችን ድረስ መኖርን መምረጥ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

ለዚህም  የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን፡

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21