#ከተራ_ምንድን_ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
መልካም የከተራ በዓል
@linkortodoxe21

ጌታችን ለምን በውሃ ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)
አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡
አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡
አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)

ቃና ዘገሊላ
ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ)
የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው:: ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል
ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ
መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ):
ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው
ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን
ቻይ' እያልን የምንጠራው:: እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1ነገሥትን ተመልከት) እንደ ነበር ይታወቃል
እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12) እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)
ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ 2 ላይ
እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው:: "ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: (ዮሐ. 2:11) ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም
ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው
የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: (ማቴ. 4:1) አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ
ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ
+ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት 23 ነው:: ጥር 11 ተጠምቆ: የካቲት 21 ቀን ከጾም ተመልሷል:: ከዚያም የካቲት 23 ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል
ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር 12 ቀን አድርገውታል
በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ
ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ
ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ
የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና)
ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ
የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው
ሲቀመጡ: ሌሎች
ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ
ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ::
ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ:- በጸጋ: አንድም 'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል:: እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ አልቦሙ-ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው
+ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ ቃሉንና ክቡር ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል:- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!)
ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር
ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ" አላት::
ምክንያቱም ጌታ:-
የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: (አበረከተ ይሉታልና) አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው:: (እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ) አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ:: ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት:: "አባትህንና እናትህን አክብር" (ዘጸ. 20) ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?ልቡና ይስጠን!
ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን "ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ-የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: (ዮሐ. 2:5) ጌታም በ6ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን አደረጋቸው
+እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው) ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ: ተገለጠ

ይህ ✝የህይወት መንገድ✝ የተሰኘ ቴሌግራም ቻናላችን
👉ምክሮችና የአባቶች ተግሳጾች
👉የተለያዩ የህይወት ትምህርቶች
👉የህይወት ችግሮችና መፍትሄዎች
👉መንፈሳዊ ግጥሞች
👉መንፈሳዊ ታሪኮች
👉የቮይስ ትምህርቶች
👉የቪድዮ ትምህርቶች
👉እለታዊ የብሩክ ንጋት ብሩህ ቀን መርሃግብሮች 👉መንፈሳዊ መዝሙሮችና የተለያዩ🔵መንፈሳዊ🔵 አገልግሎቶችን ያቀርባል።የአገልግሎቶቻችን ተካፋይ ለመሆን ይህንን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
@yehywetmenged
@yehywetmenged
@yehywetmenged
የዚህ ቻናል #እህት የሆነውን ✝ህይወት ቲዩብ✝የተሰኘውን ብዙ አገልግሎቶችን የምናቀርብበትን ቻናል ይመልከቱ።ከወደዱትም❤️ሰብስክራይብ❤️ በማድረግ ቤተሰባaችን ይሁኑ።
youtube.com/c/hiwottube

+ሜልኮል ግን በልቧ ናቀችው+
ሜልኮል ዳዊትን በልቧ ለምን ናቀችው? ለምንስ ዕርቃኑን ሆኖ በመዝለሉ ተገረመች? ለዚህ መልስ በሜልኮል ልብ የተናቀው ዳዊት መልስ አለው።
እግዚአብሔር የሚገለጥበት ታቦት በከተማው ሲገባ የተመለከተ ዳዊት በእስራኤላውያን ዘንድ ያለው ክብር አላሳሰበውም የንግስናውም ካባ አልያዘውም በደስታና በተመስጦ እየዘመረ ይዘል ነበር። መጎናጸፊያው ከመሬት ወድቆ እርቃኑን እስኪሆን ድረስ ዓለምን ለጥቂት ሰዓታት በተመስጦ ዘንግቶ ነበር።
ዳዊት ምን አይነት ተመስጦ ውስጥ ነበር? ደስታውስ ምን ያህል ቢሆን ነው የምድር ሹማምንተ መተው የማይፈልጉትን ክብር እስኪንቅ ድረስ ያዘለለው? የዳዊት ዝማሬና ዝላይ በፍጹም ከስጋዊ ስሜት የመነጨ ሳይሆን ነፍስ ስትደሰት የሚፈጠረ ተመስጦ ነው። ይደንቃል? ለታቦት ሊሰጥ የሚገባውን ክብር ዳዊት እየወደቀና እየተነሳ አስተማረን። የእግዚአብሔርን ታቦት ስትመለከቱ ዓለማዊ ክብራቹ ሊይዛቹ አይገባም የልባሳቹ ማማር እና መድመቅ ወደኋላ ይመልሳቹ ዘንድ የተገባ አይደለም የሚል ምክር ለገሰን።
በኤልሳቤጥ ማኅፀን የዘለለው ፅንስ ታቦት የተሰኘች የእመቤታችንን ድምፅ በሰማ ጊዜ ነበር። ፅንሱ ሰምቶ በስውር ሲዘል ዳዊት ደግሞ አይቶ በግልጥ ዘለለ። የሁለቱም መዝለል ምክንያት ግን ደስታ ነው። የእግዚአብሔር ታቦት በአደባባይ ሲወጣ ሐዘን የለም ለቅሶና ጸብ አይኖርም የሚኖረው "ደስታ" ብቻ ነው። ደስታችን ፍጹም ሲሆን ከጥግ ቆመው የሚስቁ ሜልኮሎች ትዝ እይሉንም።
ሜልኮል ከመስኮት ላይ ቆማ የታቦቱን መምጣት ሳይሆን ስትከታተል የቆየችው የዳዊትን መዝለልና መዘመር ነበር። ይህን በማድረጉ ከክብሩ የተዋረድ መስሎ ታያት። በዚህም ምክንያት በልቧ ናቀችው። ታቦቱ ተነስቶ ሕዝቡን ባርኮ ወደ ክብር ቦታው እስኪመለስ ድረስ ዳር ቆመው የልብስ ዓይነት ሚያማርጡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚገመግሙ ከሚከብረው ታቦት ይልቅ ሰዎችን ለማመስገንም ይሁን ለመናቅ ልቦናቸውን ያዘጋጁ ሜልኮሎች አይጠፉም።
ምስጢር ሲሰወርብን እንዲ እንሆናለን። ለታቦት ከሚሰጠው ክብር በተጨማሪ በደስታ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይፈለጋል። በፍጹም ደስታ ውስጥ ሆኖ ያከበረንን እግዚአብሔርን ከማመስገን ፈንታ ለጸብ የሚጋብዝ ንቀትና ስላቅ ስናበዛ በተመስጦ ያሉ ዳዊቶችን እንረብሻቸዋለን። ወይ አንደስት ወይ ደግሞ በታቦቱ መመጣት ለሚደሰቱት ሰዎች ምክንያት ላለመሆን አንታቀብም።
ዳዊት በፍጹም ተመስጦ እና ደስታ የተቀበለውን ታቦት ይዞ መሰዋዕትን አቅርቦ ሲመለስ ቀድሞውንም የዳዊት ምስጋና ከልቧ ያልገባው ሜልኮል"የእስራኤል ንጉስ በአገልጋዮቹ ሚስቶች ፊት በመገለጡ ምነኛ የተከበረ ነው" በማለት በነገር የሚወጋ ንግግር ተናገረች። ዳዊት ግን እንደዛ በማድረጉ አንድም ነገር የማፈር ስሜት አልተሰማውም በልበ ሙሉነት ድንቅ ቃላቶችን አወጣ እንዲህ አላት "በእግዚአብሔር ፊት ዘምሬአለሁ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ እዘምራለሁም አሁንም እገለጣለሁ በዕይንሽ ፊትና እንዴት ከብረሕ ባልሽባቸው ሴቶች ልጆች ፊት የተናቅሁ እሆናለው" አላት
አሸማቀው እና ተሳልቀው ደስታህን ለሚቀሙ ሜልኮሎች ተብሎ የሚቀር ዝማሬ የለም። ለታቦት ክብር መስጠት ያልገባቸው በመስኮት ለሚያጮልቁ ሰዎች ሲባል የሚተው ምሰጋና የለም። መቋሚያና ጸናጽል ይዘን ከበሮ አንግበን ማመስገን ቢሳነን እንኳን በተፈጥሮ የተሰጠን የድምጽ መሳርያ ጭብጨባና በእልልታን ተጠቅመን የእግዚአብሔርን ታቦት እናከብራለን።
ዲ/ን ሞገስ አብረሃም
4-5-2013

ኦርቶዶክሶች
💠ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ ይድረስ፡፡
🔘እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦
👉እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል
(ማቴ1:23) ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ
ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ
ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2 ) ንፅህት በስጋሽም ድንግል ነሽ
(ማቴ1:23) (ህዝ44:2) ያሸናፊ የልኡል እግዚአብሔር እናት ሆይ
(ሉቃ1:35)ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ1:28 እና ሉቃ1:32) የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ
ይበልሽ ልኡል እግዚአብሄር ካንች ጋር ነውና(ሉቃ1:28-30) ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመዳህኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን በ(1ቆሮ5:20) በፅድቅ ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልና ሃጢአታችንም ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን።
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
👉ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡
ኦርቶዶክስ መልሥ አላት
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመሥቀሉ ክቡር አሜን
ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ
#ሼር

+ የአባቶች ድንቅ ጥበብ የተሞሉ መልሶች +
ባለ ብዙ ታሪኩ የወሊሶው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያጠምቁና ያስተምሩ በነበረበት ሥፍራ አንድ በትዕቢት መንፈስ የሚሰቃይ ወጣት መጣና መፈክርነት ያዘለ ቃል ተናገረ:: ክብር ይግባትና ንግግሩ የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚቃወም ነበር::
ወደ አባ ዲዮስቆሮስ ቀርቦ እንዲህ አላቸው :-
ወጣቱ :- "ድንግል ማርያም እኮ ብዙ ልጆች አሉአት"
አቡኑ :- "ባታውቀው ነው እንጂ ለአንተም እኮ እናትህ ናት!"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
የቦሩ ሜዳው መምህር አካለ ወልድ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ኢየሩሳሌምን ሲሳለሙ ድንገት የሌላ ሀገር መነኮሳት መጥተው በዱላ አጣደፉአቸው:: ነገሩን ሲጠይቁ ለምን በእግዚአብሔር ሦስትነት እንደማያምን ሰባልዮሳዊ
አንድ ጣታችሁን ብቻ ወደላይ ጠቁማችሁ ታማትባላችሁ? ለምን እንደ እኛ ሦስት ጣቶቻችሁን (እንደሚጎርስ ሰው) በአንድ ገጥማችሁአታማትቡም?" አሉና በቁጣ ጮኹ::
መምህር አካለ ወልድ በፈሊጥ እንጂ በፍልጥ የሚሆን ነገር ስለሌለ ቁጭ ብለን እንነጋገር አሉ::
"እኛ በአንድ ጣት ብናማትብም ሦስትነቱን እናምናለን:: አንድዋ ጣትም እኮ ሦስት አንጉዋዎች አሉአት:: አንድ መሆንዋ አንድነቱን ሦስቱ አንጉዋ ሦስትነቱን ያስረዳል::
የታችኛው አንጉዋ መሠረት ነውና የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መሠረት ይሆነው የአብ ምሳሌ ነው:: የመካከለኛው በሁለቱ ህልው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው : የላይኛው ጥፍር የለበሰው ደግሞ ባዕድ ሥጋን የተዋሐደ የወልድ ምሳሌ ነው:: ሀገራችሁ ሔዳችሁ አስተምሩበት" አሉአቸው
(ይህ ትርጓሜ በወንጌል አንድምታ ላይ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን አወጣለሁ የሚለው በተተረጎመበት ሥፍራ ይገኛል)
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስን ደግሞ አንድ ወጣት መጥቶ
"ለእግዚአብሔር የአምልኮ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት እንደሚሰገድ አውቃለሁ:: ግን በቅዱሳን ሥዕል ፊትና በፈጣሪ ፊት ስሰግድ እንዴት ለይቼ የጸጋ የአምልኮ እያልኩ መስገድ እችላለሁ?" አላቸው
ንቡረ ዕድ መለሱ
"አንተ ዝም ብለህ ስገድ እነርሱ የድርሻቸውን ይወስዳሉ!"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አቡነ ሺኖዳ ከሾፌራቸው ጋር ሲሔዱ ሾፌሩ መኪናውን ከመጠን በላይ አበረረው
ፓትርያርኩ እንዲህ አሉ
"ልጄ ስለምንቸኩል ቀስ በል”
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አንድ ታላቅ የጉባኤ መምህር ተጠየቁ
"ካህናት ዶሮና በግ ወዘተ ማረድ የማይችሉት ለምንድን ነው?"
"የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንደ ኦሪት ካህን የእንስሳ ደም አያፈስስም"
"ካህናቱስ መልካም ሴት ልጅስ ማረድ ለምን ትከለከላለች?"
"ሕይወት የምትሠጥ ሴት ሕይወት አታጠፋም"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አለቃ ለማ ልጃቸውን ለምን በጣም እንደሚገርፉት ተጠየቁ
"ልጄን እኔ ካልቀጣሁት እግዚአብሔር ይቀጣብኛል
የእግዚአብሔር ቅጣት ደግሞ ሞት ነው"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አንዱ መጥቶ አንድን የመጽሐፍ መምህር
"ጥምቀት ጋድ አለው ወይ?" አላቸው
እርሳቸውም መለሱ
"አምና ነበረው የዘንድሮን እንጃ"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አቡነ ዮሐንስ አንድን ሥራ ፈቶ የአብነት ተማሪዎችን
ሲማሩ ከሩቅ የሚያይ ወጣት አዩና
"አንተ አትማርም ወይ?" አሉት
"አይ አባቴ ምን እየበላሁ ልማር ብለው ነው?" አለ እየተቅለሰለሰ
አቡኑ መለሱ
"አሁን ምን እየበላህ ነው የምትደነቁረው?"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሳሉ አንድ ወጣት ሰርቆ ሲያመልጥ አባርረው ይዘው ሰዎች አመጡላቸው
ዕቃው ከተመለሰ በኁዋላ ሌባውን ለሕግ አሳልፈው ሊሠጡ ሲቸኩሉ አይሆንም አሉአቸው:: ሰዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወደ ፖሊስ እንውሰደው አሉአቸው
እርሳቸውም መለሱ
"ኦርቶዶክሶች ተሰራርቀው ተካስሰው መጡ ከሚል ስም ውጪ ምንም አናተርፍም"
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ብፁዕ አቡነ ሰላማን አንዱ ባለ ሥልጣን ጉዳይ ሊያስፈጽሙ በሔዱበት ቢሮው "አንተ" ብሎ በማናገር ሊያቃልላቸው ሞከረ::
እርሳቸው እንዲህ አሉት
"የቤተ ክርስቲያኔን ጉዳይ ፈጽምልኝ እንጂ እንኩዋን አንተ ቀርቶ አንቺም ብለህ ጥራኝ
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
የደርግ መንግሥት እንዳሻው ሊዘውራቸው ተስፋ ያደረገባቸው ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በመሪው አማካኝነት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
"የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ወደ ሙዝየምነት የመቀየር ሃሳብ በመንግሥት በኩል ተይዞአል:: ይህንን ለማድረግም የእርስዎን ድጋፍ የግድ ነው"
ፓትርያርኩ መለሱ
"ምን ችግር አለ በቅርቡ የዓመቱ ሥላሴ ክብረ በዓል ስላለ ሕዝቡ ባለበት እናንተም ተገኝታችሁ አብረን ለምን አናወያየውም"
በዚህ ምላሽ ምክንያት እቅዱ ተሠረዘ
✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!
የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡
ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡
ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

“ላገቡት” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር
ባልና ሚስት አንድ መኾናቸውን ብዙ ጊዜ ስለ ተማራችሁት እርሱን አልደግምላችሁም፡፡ ከዚህ ተነሥቼ ግን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦ ከሰውነታችሁ ውስጥ አንዱ ሕዋስ ቢታመም ቆርጣችሁ ትጥሉታላችሁን? ከሕመሙ ይፈወስ ዘንድ የምትጥሩ አይደላችሁምን? ለትዳር አጋራችሁም እንደዚህ መኾን አለባችሁ፡፡ እንደዉም'ኮ፥ ከሰውነታችሁ ሕዋስ ውስጥ ያለው በሽታ አንዳንዴ ላይድን ይችላል፡፡ የትዳር አጋራችሁ ግን፥ ምንም ክፉ ቢኾንም ሊለወጥ ይችላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚኖረው አንዳንዱ ችግር ለምሳሌ ልምሾ እጅ ወይም እግር ሥራ መሥራትን ሊከለክለን፣ በሌላዉ የሰውነታችን ክፍል ላይ ጫና ሊያሳድርብን ይችላል፤ ነገር ግን ይበልጥ እንክብካቤ እናደርግለታለን እንጂ ቆርጠን አንጥለዉም፡፡ ታዲያ መዳን ለማይችለው ሰውነታችን ይህን ያህል እንብካቤ እያደረግንለት ሳለ፥ የመዳን (የመለወጥ) ዕድል ያለው አካላችንን (ባለ ትዳራችንን) መቁረጥ (መፍታት) እንደ አማራጭ ማስቀመጣችን እንዴት ብናብድ ነው?

አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤ ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው። በል ሒድና ተአምር ሥራ!"
#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

ጸሎት መተው ለጠላት ምቹ መሆን ነው!
ወዳጄ አይደለም ሁሌ አንድ ቀን ጸሎት መተው ለአንድ ቀን ለሰይጣን እጅ መስጠት ነው፡፡ አንድ ቀን ጸሎት ማስታጎል ለአንድ ቀን በሰይጣን እንደ መማረክ ነው፡፡
ጸሎት ስንተው ለሥጋዊም ለመንፈሳዊም ጠላታችን በነገሮች ሁሉ ምቹ ነው የምትሆነው፡፡ ያ ማለት በየትኛውም የሕይወት አቅጣጫ፣ የጠላት ጡጫ እኛ ላይ ሊያርፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ ለሥጋችን ምግብ መብላት እንደማንተው ሁሉ የነፍስ ምግብ እና የጸጋ ወደብ የሆነውን ጸሎት አንተው፡፡

ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።
♥ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡
♥ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።
♥ ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡
♥ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡
♥ ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።
♥❖♥ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም)
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”
(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡
♥❖♥ የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”
(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨
♥♥♥ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።
♥❖♥ የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"
(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።
♥ ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል።
❤ ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"
(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።
♥❖♥ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-
♥ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨
ይቀጥላል...
✍መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ

+ ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +
ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::
ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::
የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::
ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::
ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::
ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)
ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::
በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 23 2012 ዓ ም
ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ
ፎቶዎች :- ሊባኖስ ቤሩታዊትዋን ባዳነበት ሥፍራ እና ልዳ በቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ሥፍራ የተነሣሁት:: እናንተንም መቃብሩን ለመሣለም ያብቃችሁ::
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
Join or share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21

“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟
✞✞✞ የልጅነት ጸጋ ካገኝን በኃላ ስለሚሰራ ኀጢአትና የስርአት መንገድ ✞✞✞
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅድስ እንዲሁም ከራሱ ጋር አስታርቆን ካዳነን በኅላ ስለምንሰራው ኀጢአት <<አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር >>በሚለው የዕለት ዕለት ጸሎት ውስጥ <<በደላችንን ይቅር በለን >>እንድንለው ጸሎት በማስተማርና ከኅጢአታችንም እንድንመለስ <<ንስሀ ግቡ >> በማለት ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን የመጀመሪያ መንገድ ንስሀን ሠርቶልናል። በአንድ ሀጢአተኝ ንስሀ መግባት በሰማይ መላእክት ዘንድ ታላቅ ደስታ የመሆኑ ምክንያት እግዚአብሔር የኀጢአተኝውን ንስሀ ተቀብሎ ኀጢአቱን ይቅር በማለቱ ነው። እግዚአብሔር ይቅር ባይለው ኖሮ በኀጢአተኝው ንስሀ መግባት በመላእክት ዘንድ ደስታ ባልተደረገ ነበር።
ማቴ 26:28 ላይ <<ኀጢአትን ለማስተሰረይ ስለ ብዙዎች የሚፈሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው >>ብሎ ለዓለም ሁሉ የኀጢአት ስርየት የሰጠውን ክቡር ደሙን ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐ 1:7-10 <<የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻል >> በማለት ኀጢአትን ብንሰራ ንስሀ ገብተን በምንበላው ቅድስ ስጋና በምንጠጣው ክቡር ደም ከኃጢአታችን እንደምንነጻ ያስረዳል። <<ኀጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኀጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኝ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም ተብሎ የተጻፈውን ማንበብ ግራ ከመጋባት ያድናል>>።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አስተያየት ጥያቄ ካለ
@Mentesnhot በዚ ይላኩልን
Join or share
@Ortodoxe19

"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}
{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )
[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}
:
መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !
( መልክአ - መድኃኔአለም )27❤

✟✟✟ክርስቶስ በአብ ክብር ሆኖ ስለሚሰራው ሦራ ✟✟✟
<<በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ >>ሮሜ 5:12 <<በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኝ እንደ ሆኑ >> ሮሜ 5:19 ተብሎ እንደተጻፈ ዓለም በልጅ እንዲድን እግዚአብሔር አንድያ ልጅን ወደ ዓለም ላከው >> 1ኛ ዮሐ 3:19 ይላል <<ሐጢአታችንን ያስተሰርይልን ልጅን ላከው >> 1ኛ ዮሐ 4:10 <<እርሱም ኀጢአታችንን ያስወግድ ዘንድ እንደተገለጠ ታውቃላችሁ >> 1ኛ ዮሐ 3:5 ተብሎ ተጽፋል። ከመልክቶቹ እንደምንረዳው በአንድ በአዳም በደል ሰው ሁሉ ኀጢአተኛ ቢሆንም ኃጢአተኝነትን ያስወግድ ዘንድ ጌታችን ወደ ዓለም መምጣቱ ነው። መጥቶም የውርስ ኀጢአትን በሞቱ ካስወገደልንና ከድኀነት በኀላ ለሚሰሩ ኀጢአቶች ንስሐ በመግባት ለኃጢአታችን መደምሰሻ ይሆነን ዘንድ ቅድስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንደሰጠን የሚገልጽ ነው። የመናፍቃኑ ስህተት <<በክብር ሆኖ የሰውነትን ሥራ ይሠራል >> ማለታቸው ደግሞ ከሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ ትምህርት ጋር ቀጥታ የሚጋጭ ነው።
ሐዋርያው ቅድስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮ 5:19 ላይ <<ክርስቶስን ከእንግዲህ ያወቅነው ብንሆን ስንኳን አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም >>አለ። ይህም ማለት ክርስቶስን በሰውነቱ ሥራ በምድር ብናውቀውም ከዕርገት በኀላ በአብ ቀኝ (ክብር) በክብር ተቀምጦ በአምላክነት ሥራ እንጂ በሰውነት ሥራ በመራብ፤ በመጠማት፤ በመሰቀል ፤በመሞት፤ በመጸለይ፤ በማማለድ ወዘተ..... አናውቀውም ማለት ነው።
ስለዚህ ማንን እንስማ? በመንፈስ ቅድስ ሆኖ የተናገረውን ቅድስ ጳውሎስን ወይስ ያለማስተዋል የተጻፈውን የስህተት ትምህርት! መልሱ በሕይወቱ የመሰለ ቅድስ ጳውሎስን እንደሚሆን የታወቀ ነው። ዛሬም ነገም ለዘላለምም ክርስቶስ በአብ ቀኝ በክብር ተቀምጦ የሰውነትን ሥራ ማለትም አባቱን መለመን ሆነ በደሙ ማማለድ (መጸለይ) የለበትም።
ምንተስኖት