መንፈሳዊ ህይወት
4.04K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ሁልግዜም ምንግዜም ቢሆን ይህን አስታውስ🙏
@linkortodoxe21
5🥰1
"የማለዳ ጸሎት"

"የጊዚያት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ የጨለማዉን ግርማ ገፈህ ብርሀንን እንድመለከት ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ በምኝታየ ስለጠበከኝ ከሞት ስለሰወርከኝ እጅ መንሳቴን አቀርባለሁ።
ቸር እረኛየ ትጉህ የማታንቀላፋ ነህና ለሊቱን ከ እኔ ጋር ሁነህ እደጠበከኝ
ይህንንም ማለዳ ባርከህ ቀድሰህ የሰላም ዉሎ እንድዉል ቀኝህ ትርዳኝ።
መንገዴን ሁሉ ከፊት እየሆንክ ምራኝ።
ከደካማ ፍጡርነቴ የተነሳ
በኃላየ ምን ምን እንዳለ
አላዉቅምና አንተ ጠብቀኝ።
በዙሪያየ ሁሉ ጠላት ያስቀመጠብኝን እንቅፋትና መሰናክል አስወግድልኝ።
ከፈተና የተነሳ ብወድቅ እንኳን አንሳኝ እንጅ አትተወኝ።
በዚእች ቡርእክት እለትም
በስራየ፣በንግዴ በመንገዴ፣
በክብሬ፣በአገልግሎቴ ሁሉ
የጥፋት መረቡን ዘርግቴ
ሰላሜንና በረከቴን ሊያሳጣኝ
የተዘጋጀዉንና የሚያሴርብኝን
ጠላቴን(ዲያቢሎስን)እቅድና
ስራዉን አፍርሰህ ሰላሜን
አጎናፅፈኝ።
በዚህ እለት ሀጢያትን አቅጀ
በድፍረት እንዳልፈፅም በመዘናጋትም እንዳልተገብር
አድርገኝ።
ደም ከሚፈስበት ፍርድ ከሚዛባበት ድሀ ከሚበደልበት በማታለልና በማጭበርበር ከሚከበርበት
ጣኦትና ሰይጣን ከሚመለክበት ስራና ቦታ ሁሉ
ፈፅመህ ጠብቀኝ።
ደካማዉ ልጅህ እጆቸን ዘርግቸ መንገዴን እንድትመራኝ በቀረቡህ ጊዜ
ሀጢያቴንና በደሌን አይተህ
ሳትጠየፈኝ ተቀብለህ ምራኝ።
እለቱን ሁሉ ፍቃድህን ማድረግ እንድችል በቃልህ
አስተምረኝ።
መንፈስ ቅዱስ ሂወቴን ይቆጣጠር።
ትናንትን እንደጠበከኝ እንደ መገብከኝ ከክፉም እንደሰወርከኝና እንደ ፈወስከኝ ዛሬም እንደ ፈቃድህ ጠብቀኝ።
አንተ ያልከዉ ይሆን ዘንድ ግድ ነዉና በከንቱ ከመጨነቅና ተስፋ ከመቁረጥ ሰዉረኝ
ለዘልአለሙ አሜን አሜን አሜን

ወስብአተ ለእግዚአብሔር
ወወላዲተ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን አሜን


በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
👍5
"በመንፈሳዊው መንገድ ላይ የምትጓዙ ከሆነ እንዳትወድቁ በራሳችሁ አትደሰቱ። ትዕቢትን የምንፈራው እድገታችንን እንዳያቆመው ብቻ ሳይሆን እንዳይጥለንም ነው። መጽሐፍ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል፦"ትዕቢት ጥፋትን ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።"ምሳ 16፥18..."

#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
👍1
🌻
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።
🌻
ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
👍81
🙏እውነተኛ ክርስቲያን 🙏


እውነተኛ ክርስቲያን "እኔ" ሳይሆን "እኛ" እያሉ የሚኖሩት ሕይወት ነው ክርስትናም ፍቅር ነው እንደ ቅድስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደነ ቅድስ ባስልዮስ የሰው ቁስል ከተሰማህ ረሃባቸው ከራበህ አንተ ክርስቲያን ነህ እስከመስዋትነት ለመድረስ ከችግረኞች ጎን ከቆምክ የሚያስፈልግህ ሁሉ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ካመንክ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ነህ

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@linkortodoxe21
13👍3
🔹እውነት ከውሃ ጉድጓድ ሥር !!"

#አንድ ቀን እውነት እና ውሸት ይገናኛሉ። "ውሸት ለእውነት ማዛሬ አስደናቂ ቀን ነው” ትላታለች። እውነት ወደ ሰማይ ቀና ብላ ትመለከትና እውነትም ቀኑ እጅግ ውብ መሆኑን ታስተውላለች። ከዚያም ቀኑን ሙሉ አብረው ያሳልፉና በመጨረሻ በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ይደርሳሉ ፡፡ ውሸት እውነትን በድጋሚ “ውሃው በጣም ጥሩ ነው፤ አብረን እንታጠብ!” ትላታለች። እውነትም የጉድጓዱን ውሃ ባየች ጊዜ ጥሩ መሆኑን ተገነዘበች፡፡ በዚህም፣ እውነት የአብረን እንታጠብ ግብዣውን ተቀብላ ልብሳቸውን ከጉድጓዱ ዳር አስቀምጠው መታጠብ ይጀምራሉ።

#መታጠቢያ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ ውሸት ከውሃው በድንገት ትወጣለች፤ የእውነትንም ልብስ ትለብስና ትሸሻለች፡፡ በሁኔታው በጣም የከፋት እውነት ከጉድጓዱ ትወጣና ውሸትን ለማግኘት እና ልብሷን ለመቀበል በየቦታው ትሯሯጣለች፡፡ በየመንገዱ የምታገኛቸው ሰዎች እውነትን እርቃኗን በማየታቸው በንቀት እና በንዴት ይመለከቷታል፡፡ ውሸትን ሮጣ መያዝ ያልቻለችው ምስኪኗ እውነት ወደ ጉድጓዱ ተመልሳ የውሃው ጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ለዓለም ስትል እርቃኗን ለዘላለም ትሸፍናለች፡፡

#እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት እንደ እውነት ለብሶ በዓለም ዙሪያ በመዘዋወር የኅብረተሰቡን ፍላጎቶች በማርካት ላይ ይገኛል። ዓለምም እውነትን የመፈለግ በጭራሽ ፍላጎት የለውምና የእውነት ለዘለዓለም በጉድጓዱ ውስጥ መቅረት አያስጨንቀውም፡፡ ዓለም፣ እውነት እርቃኗን ስትሆን የሚሸከምበት ሞራልም ስለሌለው በመደበቋ ደስተኛ ነው።

#share and join for more👍
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
👍1610
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
⇛ኦርቶድክሳዊ ፎቶና ስዕላድኖች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍትች...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ ዜናወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ TikTok video ወችን...♡
⇛ኦርቶዶክሳዊ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን..🙏
ማግኘት ከፈለጉ JOIN የሚለውን ይንኩት 🙏❤️‍🩹
Forwarded from Quality button
የአእላፋት ዝማሬ የሚደረግበት ቀን እና ሰአት መቼ እንደሆነ በ ጃን ያሬድ የቴለግራም ቻናል ላይ ተለቋል!
የመመዝገቢያ ፎርም ለመሙላት JOIN በሉ::

@yeaelafat_zmare
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
33k channel መግዛት ለምፈልጉ inbox አውሩኝ @pilupadier
🙏 ከአንዱ ወዳጄ🙏 መልክት 🥹

ሁለት ጊዜ ቀላል (Minor surgery) እንዲሆም ህመሙ በነዚህ ሁለት ቀዶ ጥገና ሊፈታ ባለመቻሉ በቅርቡ ከባድ ቀዶ ጥገና(major surgery)  ተደርጎለት ነበር።እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ሆኗል፣ ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን! 🥹

ነገር ግን ይህ የጤና መታመም ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ፈጥሮበታል።ቤተሰቦቹ ለህክምና ወጪዎች ሲሉ ያለውን ሁሉ አውጥተዋል፣ እሱም ምንም አልያዘም። በአሁኑ ወቅት አካውንቱ ላይ ያለው ገንዘብ የገንዘብ መጠን በጣም ትንሽ ነው። 😢 ቤተሰቡም ለዛ ሕክምና ወጪ ያወጡት ተበደረው ነውና እሱን በትምህርቱ ለሚያስፈልገው ነገር እገዛ ማድረግ እጅጉን ከባድ ሆኖባቸዋል::

አሁን ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል።የመጀመሪያ ሳምንት ለሚያስፈልገው ሰርተፍኬት ፕሪንት ለማድረግ ከነበረችው 200 ብር ላይ አውጥቶ አሁን 100 ብር ብቻ ነው የቀረው።እንደ ማንኛውም ተማሪ ፕሪንት እንኳ ማድረግ አልቻለም።

"ይህ ሁሉ የኃጢአቴ ውጤት ነው፣ እሄ ሲያንሰኝ ነውና ጸልዩልኝ" በማለት የመንፈስ ጭንቀቱንና ትህትናውን አሳይቷል።ስመ ክርስትናውም ኃይለኢየሱስ ይባላል በፀሎት በቆምን ሰዓት ሁሉ በፀሎት እንድናስበው ጠይቆናል 🙏🙏🙏::"ለሰው መድኃኒቱ ሰው ይባል የለ፣ አደራችሁን" በማለት ከእኛ እርዳታን ይፈልጋል።

ቢያንስ ለመማሪያ የትምህርት ግብዓት ሚያሟላበት እና ለፕሪንት ለኮፒ ሚሆን ነገር ብናግዘው መልካም ነው።ወንድማችን "ማርያምን 50 ብር ቢሆን ለእኔ ትልቅ ነገር ነው!" ብሏል።
የቻልነውን ያህል በጸሎትም ሆነ በገንዘብ እንርዳው።እያንዳንዱ ትንሽ እርዳታ ትልቅ ለውጥ ያመጣለታል። 🙏

የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥሩ:
1000670545788
ስለ እናታችን ስለ እማምላክ ስለ ኪዳነምህረት ስንል ሁላችንም ከጉድለታችን ላይ ያቅማችንን እንርዳው እናግዘው በፀሎትም እናስበው::
👍1