ህፃን ተወልዶልናል፡ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ስሙም
ድንቅ መካር ኃያል፤የዘላለም አባት የሰላም አለቃ
ተብሎ ይጠራል ኢሣ9:6
እንኳን አደረሳችሁ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ስሙም
ድንቅ መካር ኃያል፤የዘላለም አባት የሰላም አለቃ
ተብሎ ይጠራል ኢሣ9:6
እንኳን አደረሳችሁ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያውያን ናቸውን?
✍በልደት ዋዜማ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
💥 የሦስቱ ነገሥታት የአነሣሣቸውና የተነሡበት ሀገር ምንነት የዓለም ሊቃውንትን አነጋግሯል፤ የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን ትኩረት ስቧል፤ ወንጌላዊው ማቴዎስ አመጣጣቸውንና ስጦታቸውን ተናገረ እንጂ ሀገራቸውንና ስማቸውን አልጻፈም፨
💥 ለማንኛውም ነቢያት ስለነዚኽ ነገሥታት ሀገር በትንቢት ምን ተናገሩ? የሚለው ለሁሉም መልስ ይሆናል።
ከነቢያት ዳዊትና ኢሳይያስ የሰብአ ሰገል አመጣጥ ተገልጾላቸው ትንቢት ሲናገሩ፤ ይልቁኑ ኢሳይያስ ሀገራቸው የሳባ ምድር ኢትዮጵያ እንደኾነና ኹሉም ከዚኽ እንደሚኼዱ፦
💥"የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ" (ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 6) አለ፨
💥 ዳዊትም በመዝሙሩ ላይ ለአምላክ ልደት ስጦታ እንደሚመጣ ጠላት ሰይጣን ጠላት ሄሮድስ እንደሚያፍሩ ኢትዮጵያውያን በፊቱ እንደሚሰግዱ፦
💥 "በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ ነገሥታትም ሁሉ ይሰግዱለታል" (መዝ 71 (72):9-10) ይላል። ይህም የትንቢት ቃል ሲፈጸም፦
“ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።” (ማቴዎስ 2፥11) ይለናል።
💥 በተጨማሪም ዳዊት "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር" ( ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች (ታደርሳለች)፤ የምድር ነገሥታት እግዘአብሔርን አመስግኑት" በማለት ትንቢት ተናግሮላታል፨
💥 ታላላቅ ሊቃውንት እንደገለጹት የግእዝ ቋንቋችን እንደሚያስረዳን "በጽሐ" የሚለው የግእዝ ቃል ቀጥታ የዐማርኛ ትርጉሙ (ደረሰ) ማለት ሲኾን ታበጽሕ ማለት ደግሞ (ታደርሳለች) ማለት ነው፨ "ሰፍሐ" ማለት ግን (ዘረጋ) ማለት ነውና ትሰፍሕ ቢል ትዘረጋለች ባልን ነበር፤ መዘርጋት ማንም ሊዘረጋ ይችላል፤ ዘርግቶም ሊቀበልም ላይቀበልም ይችላል፤ ይኽቺ ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ግን "ታበጽሕ" (ታደርሳለች) ተብላ ተነግሮላታልና አምላኳ ሲወለድ ሥጦታን በማቅረብ በእውነት አድርሳለች ነገሥታቱም አመስግነዋልና ይኽም ከአምላኳ ለርሷ ብቻ የተሰጠና የተነገረላት ነው (መዝ 67:11)፨
♥ ሥጦታም መስጠት ጥንቱኑ በብሉይ ኪዳን በነ ንግሥት ሳባ የጀመረችው እንጂ ለሀገሪቱ እንግዳ አይደለም "ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር" እንዲል (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 10: 10)፨
♥ ከምንኖርባት ፕላኔት መሬት ላይ ካሉ የዓለም ሀገራት በብቸኝነት ጌታችን የተወለደበትን ወር ለክርስቶስ አምላኳ የሰጠች ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ይኸውም ጌታ የተወለደበትን ወር "ታኅሣሥ" ብላለች በቋንቋዋ በግእዝ፤ ይኸውም በግእዝ ቋንቋ "ኀሠሠ" ማለት ፈለገ ማለት ሲኾን ታኅሣሥ ማለት "ወርኀ ተኀሥሦ" (የማሰስ ወር፣ የፍለጋ ወር) ማለት ሲኾን፤ ሊቃውንት ይኽነን ያሉበት ምክንያት ሦስቱ ነገሥታት "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና" እያሉ አስሰው ፈልገውት ስላገኙት ይኽ ሥያሜን ቀደምት አባቶቻችን ሰጥተዋል (ማቴ 2: 1-2)

"የጌታ ልደት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"
ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡
መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡
እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡

"ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ"
(ብፁእ አቡነ ሺኖዳ)
ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ኑ በፀሎት ወደአምላክ ቅረቡ ፤ በፀሎት ማለት እንዴት ነው? ይህስ የልባችሁን ምስጢር ሁሉ ሳትደብቁ እርሱ እግዚአብሄር እንደሚያስፈልጋችሁ መናገር ማለት ነው ፤ እንዲህም በሉ ፦ “ጌታ ሆይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁ ፡ ጌታ ሆይ ካንተ ተለይቼ እኔ ምንም ነኝ ፡ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴን አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ደስታየን ሁሉ አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ትርጉም አልባ ሆነ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ጣእም አልባ ሆነ” በሉ ፤ ዳግምም ከእግዚአብሄር እግር ስር ተደፍታችሁ እንዲህ በሉት፦ “ አምላኬ ሆይ ፦ ወደ አንተ መመለስ እፈልጋለሁ ፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ከእኔ በእጅጉ የሚበልጡ ናቸው ፤ ነፍሴንም አምላክሽ አያድኑሽም የሚሏት ብዙ ናቸው” ፡፡
ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ “ ጌታ ሆይ ታደገኝ ወደ አንተ የምመለስበትን መንገድ ምራኝ” በሉት ፤ ለአምላካችሁ ንገሩት ፦ “ካንተ ከተለየሁ ወዲህ አቅሜ ሁሉ ተዳክሟልና ጌታ ሆይ ልዩ ሃይልህን ላክልኝ ፡ ወዳንተ የምመለስበትን ልዩ ርዳታህን ስጠኝ ፤” በማለት፡፡ ብዙ ሰወች በመደጋገም “ወደ እግዚአብሄር የምመለሰው እንዴት ነው ?” ይላሉ፡፡ ከእግዚአብሄር እግር በታች ራሳችሁን ጣሉ ፡ እንዲህም በሉት ፦ “ ጌታ ሆይ ሳትባርከኝ አልለቅህም ፡ ወዳንተ አቅርበኝ ፡ ከልጆችህ እንደአንዱ አድርገኝ ፡ ሃጢአቴን ብቻ ይቅር እንድትልልኝ አልሻም ፡ ይልቁንም ከሃጢአት ፍቅር ትለየኝ ዘንድ ጭምር እንጂ ፡”በሉት ፦ ዳግምም “ ጌታ ሆይ የሃጢአት ፍቅር ልቤን ተቆጣጥሮታልና ይህን ካላስወገድኩ ወዳንተ መቅረብ አይቻለኝም ፡ ጌታ ሆይ የሃጢአትን ፍቅር ከልቤ ላይ ንቀል ፡” በሉት ዳግምም እንዲህ በሉት ፦ ”ጌታ ሆይ ከሃጢአቴ ነፅቼ ወዳንተ መምጣት እንደምን ይቻለኛል? ይልቁንስ መጀመሪያ አንተ ናልኝ ሃጢአቴንም ደምስስ እንጂ “ እንዲህም በሉት ፦ “ በራሴማ ሃጢአትን ማስወገድ ብችል ወዳንተ መቼ መመለስ ያቅተኝ ነበር? እኔ ግን አንተ ከሃጢአቴ እንድታርቀኝ እወዳለሁ ፡ ጌታ ሆይ ፦ ሃይልህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” በሉት፡፡
እመኑኝ የምወዳችሁ ልጆቼ ፦ ትክክለኛዋን ፀሎት ያወቃት እርሱ ትክክለኛዋንም ንስሃን የሚያውቅ እርሱ ነው ፤ ማር ይስሃቅ እንደተናገረው ፦ “ንስሃ ከፀሎት ውጭ እንደሚገኝ የሚያስብ ሰው እርሱ በዲያቢሎስ የተታለለ ነው” ምክንያቱም በፀሎት ወደ እግዚአብሄር የምትመለሱበትን ሃይልን ታገኛላችሁና፡፡ ስለሆነም ከየትኛውም ስራ ይልቅ ራሳችሁን ለፀሎት አስገድዱ ፤ ምክንያቱም በፀሎት አማካኝነት በእናንተና በእግዚአብሄር መካከል ያለውን ግድግዳ አስወግዳችሁ እንደገና ወደእርሱ ትመለሱ ዘንድ ይቻላችኅልና ፤ በጣም ብዙ ሰወች ከፀሎት ይልቅ ለአገልግሎት መትጋታቸው የሚገርም ነው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በንባብ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በተመስጦ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በመንፈሳዊ ስብሰባወች ለመታደም የሚተጉትም እንደዚያው ፤ ለዚህ እኮ ነው ከእግዚአብሄር ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይሳካላቸው ፤ ይፀልያሉ ያነባሉ ደግሞም ስብሰባወችን ይታደማሉ በዚህ ሁሉ ሰአት ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም ፤ ምንም አይነት ግንኙነት ፡፡
ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ወደእግዚአብሄር ተመለሱና ከእርሱ ውሰዱ ፤ አንዳንድ ሰወች በመፀለይ ለእግዚአብሄር የሚሰጡት እንዳለ ያስባሉ ፡ ለእግዚአብሄር ቃላትን ይሰጡታል ፡ ጊዜን ፡ ምናልባትም ስሜታቸውን ፤ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ፀሎት ከእግዚአብሄር የመውሰድ ጉዳይ ነው ፤ እርሱ ሰጭ እንጂ ተቀባይ አይደለምና ፤ በፀሎቱ ስኬታማ ውጤትን የሚያመጣ ሰው እርሱ ከእግዚአብሄር ስለሚወስደው የፀለየና እንደዚያም የሚያምን ነው ፤ እርሱ ነው በፀሎቱ የተሳካለት፡፡ በምትፀልዩበት ጊዜ ከእግዚአብሄር ሃይልን እንደተቀበላችሁ ከተሰማችሁ ፡ ያን ጊዜ ውጤታማ ፀሎት ፀለያችሁ ፤ አንድ ሰው ፀልዮ ከእግዚአብሄር በረከት ከተቀበለ፡ እንግዲህ ይህ ሰው ነው ውጤታማ ፀሎት ያቀረበው ፤ ማንም በፀሎት በፀፀትና በንስሃ ወደእግዚአብሄር ቢቀርብ እርሱ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ለቅድስና ቢታገል ፡ ይህ ሰው ፀሎቱ ውጤታማ ሆነ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ቢያጠናክር ይሄኔ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ፡፡
እግዚአብሄር እንድትመጡ ይናገራችኅል ፡ በፀሎት ኑ ና የሚያስፈልጋችሁን ልስጣችሁ እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ለሁለት ደቂቃ ብቻ ትፅልዩና ወዲያው ትሰለቻላችሁ ፡ ከእግዚአብሄርም አንዳች ሳትቀበሉ ትሄዳላችሁ ፤ እግዚአብሄር ወደእናንተ ያይና እንዲህ ይላል ፦ “ስለምን ከእኔ ሳትቀበሉ ተመለሳችሁ? የሚያስፈልጋችሁን ልሰጣችሁ ወድጄ ነበርና ፤ ስለምን ቶሎ ተመለሳችሁ ያዘጋጀሁላችሁን ሳትወስዱ?” እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ቶሎ ሰለቻችሁና ለመሄድ ወሰናችሁ ፤ እሺ ሂዱ ፡ ከዚያ ግን እግዚአብሄርን መፈለግ ትጀምራላችሁ አታገኙትም ፤ ጥላችሁ ስትሄዱ ያጣችሁት ምንም ሳትይዙ መሄዳችሁን ብቻ እንዳይመስላችሁ በልባችሁ ለእግዚአብሄር ጊዜ እንደሰጣችሁት ማሰባችሁም ጭምር እንጂ ፤ ወዲያውም ከመንፈሳዊ የስኬት ድርጊቶች ውስጥ መፀለያችሁን ትፅፋላችሁ፡፡
ይህ ግን ፀሎት አይደለም!!! ከእግዚአብሄር ከቶ ምን አገኛችሁ? እግዚአብሄርን አጥብቃችሁ ልትይዙት ይገባል አጥብቃችሁ መቼም ቢሆን ካንተ አልለይም መለየትም አልፈልግም ማለት አለባችሁ፡፡ ስለዚህ እኮ ነው ለፀሎት ትእግስት የሚያስፈልገው፤ ያለትእግስት ከእግዚአብሄር አንዳች እንኳን ልትቀበሉ አትችሉም፤ በፀሎታችሁ ትእግስተኞች ልትሆኑ ይገባችኅል፤ እግዚአብሄርን ንገሩት፦ ከእግርህ በታች እንደሆንኩ እቆያለሁ በረከትህንም ሳትሰጠኝ አልነቃነቅም ከእግዚአብሄር በረከትን ካልተቀበልኩ እርሱን መያዜን አልለቅም ካልባረከኝ አልለቅህም እይዘዋለሁ ወዴትም ይሄድ ዘንድ አልተወውም፤ እንግዲህ ይህ ነው በፀሎት ውስጥ ያለው ትግል፤ ሰወች ፀሎት እንዴት እንደሚፀለይ አልተማሩም እነርሱ የሚያስቡት ፀሎት ማለት ጥቂት ቃላትን መናገር ይመስላቸዋል አይደለም፡፡
ፀሎትን አዘውትሩ፡- ከእግዚአብሄርም አንዳች እስክትቀበሉ ድረስ ታገሉ ፤ አንዳች እንኳን ካልወሰዳችሁ ሳትቀበሉ የትም እንደማትሄዱ ንገሩት ፀሎቴን አልገታም በሉት እንደተፃፈ አንተ ሩህሩህ መሃሪ አምላክ ነህ የለመነውን ሁሉ የምትሰጥ ነህና እንግዲህ እኔም ለምኜሃለሁ እስከምትሰጠኝ ድረስ ወዴትም አልሄድም በሉት፤ በፀሎታችሁ ከእግዚአብሄር ጋር ታገሉ ያን ጊዜ ታርፋላችሁ በፍቅር ትሞላላችሁ በፀሎታችሁም ብርቱ ትሆናላችሁ ከንቱ ነገርንም መደጋገም ትተዋላችሁ እንዲያውም ልባችሁን በእግዚአብሄር ፊት ትዘረጋላችሁ፤ የሳሙኤል እናት ሃና በፀሎቷ ጊዜ ታለቅስ ነበር በልቧም ልጅ እንደምታገኝ ቃል ሳይገባላት ከቤተመቅደሱ ላለመውጣት ወስና ነበር ፤ ንጉስ ዳዊት ከእግዚአብሄር በረከትን እስኪቀበል ድረስ ፀሎቱን አላቋረጠም በመጀመሪያ “ጌታ ሆይ ፦ አስጨናቂወቼ ምንኛ በዙ” በማለት ፀለየ፤ ቀጥሎም እንዲህ አለ ፦ “ እናንተ ክፉ አድራጊወች ከእኔ ራቁ እግዚአብሄር ፀሎቴን ሰምቶልኛልና ፡ ጌታየ የልመናየን ድምፅ አድምጧልና ጌታየ ፀሎቴን ሰምቷልና“፡፡ ኑ ወደእግዚአብሄር ተመለሱ፡፡

🕯``ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ``🕯
💡ጉባኤ፦ የድንግል ሕይወት💡
[ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ
ቅዱስ ቄርሎስ]
“Come, O all ye women who desire
virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን
እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ
መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ
ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም
ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ
በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም
በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ
አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ
የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ
አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤
ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን
ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር
ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም
ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን
[መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
Join 👉 @linkortodoxe21💡

#ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
💎@linkortodoxe21

ኑ እንግዲህ ይህችን ንጽሕት በግ እናክብራት እናግናት የድኅነታችን መሥዋዕት የሚሆነውን በግ ወልዳልናለችና፡፡ ንጹሑን የዝናም ውሃ የተሸከመችልን የብርሃን ደመና እርሷን እናግናት እናትነት ከድንግልና አስተሳብራ የያዘች እርሷን ኑ እናመስግናት፡፡ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ለአብርሃም ልጆች መመከያ የሆነች እርሷን ኑ ክብሯን ገናንነቷን እንናገር፡፡
ቅድስተ ቅዱሳን የተባለችውን ሁለተኛ ክፍል እርሷን ኑ እናመስግናት በዚች ሕግ በዚህችም ኪዳን አለባት፡፡ ሙሴም በኦሪት የተጻፈውን ለሕዝቡ ከነገረ ወዲያ ድንኳኑንም የሥራቸውንም ዕቃ ሁሉ ንዋየ ቅድሳቱን ይረጫል፡፡ (ዘፀአ ፳፬፥፰) እንዲሁም ልጅሽ ለደቀ መዛሙርቱም የወንጌልን ሕግ ካስተማራቸው በኋላ በዕንጨት መስቀል ላይ ራሱን ሠዋ፡፡ ባምላካዊ ደሙ ፈሳሽነትም መሃይማኑን የተቀቡ አደረጋቸው፡፡
መለኮት የተዋሐደው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እውነት ነው፡፡ ይህ ደም ስላፈሰሰው ወንድሙን እንደሚከስ እንደ አቤል ደም አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ቃየልን እንደተናገረው እንዲህ ሲል የወንድምህ የደሙ ቃል ወደኔ ደረሰ፡፡ (ዘፍጥ ፬ ፥፲ ) የሕዝብና የአሕዛቡን ኃጢአት የሚያርቅ ነው እንጂ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ እንደነገራቸው እንዲህ ሲል ኃጢአት በሚሠረይ ገንዘብ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ይህ ነው ንሡ ጠጡ፡፡ (ማቴ ፳፮፣ ፳፯፣ ፳፰ )
ይህ ደም ስለ ወይኑ ቦታ እንደሞተ እንደ ኢይዝራኤላዊው እንደ ናቡቴ ደም አይደለም፡፡ (፩ ነገ ፳፩፥፲፫ ) ለበጎቹ ቤዛ የተሰቀለ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላካዊ ደም ነው እንጂ፡፡ (ዮሐ ፲፥ ፲፩ ) ይህ ኃጢአትን ለማራቅ የማይችሉ የአሮን ልጆች እንዲሠዉት ላም ደም አይደለም፡፡ የዓለሙን ኃጢአት የሚሸከም የእግዚአብሔር በግ ንጹሕ ደም ነው እንጂ፡፡ (ዕብራውያን ፲፥ ፬-፭ )
ይህ ደም በቀራንዮ የፈሰሰው ነው፡፡ በአሥራ አንደ ሰዓት ጊዜ የአይሁድ ፋሲካ አለፈ ይህም ደም ዘወትር የሚቀዳው ፈሳሽነቱም እስከ ዘለዓለሙ የማይደርቅ ነው፡፡ ይህ ደም የኔ ዋጋ የዕዳዬም ከፋይ ነው፡፡ እኔ በዚህ ደም ተማጥኜአለሁ ዕድል ፈንታዬ ጽዋ ተርታዬ ፍሬ ከሌላቸው ጋራ እንዳይሆን፡፡ ይህም ካንቺ ሰው የሆነው አምላክ ደም የሚረባኝ የሚጠቅመኝ ይሁነኝ፡፡
ቅድስት ድንግል ሆይ በክርስቶስ እንድድን በክርስቶስም እንድኖር በክርስቶስም ነፍሳትን ከሚውጡ እባቦች እንድቤዥ አድርጊኝ፡፡
(አርጋኖን - አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ )

+ ዝም ብለን የምንጠላው ሰው +
ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?
"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"
"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"
"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"
ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::
እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)
ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::
እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::
"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን"
ኤፌ 2:4
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

+ ለምን ትቀናለህ? +
በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡
አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡
ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::
ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡
ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡
ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡
ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡
የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡
ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡
የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡
ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡
ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡
ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡
በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡
‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ
ጥር 5 2013 ዓ.ም.
መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
ሌሎች እንዲያነቡትም share share share አርጉት

"ድንግል ኾይ! 🙏✨🙏
በእውነቱ አንቺ ከታላላቆች ይልቅ ታላቅ ነሽ 🤲
ማኅደረ ቃለ አብ ኾይ! ከፍጡራን ወገን አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው?
ድንግል ኾይ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለኹ? አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ! 💐💐💐
እውነተኛውን መና የተሸከምሽ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መና የተባለውም ሥግው ቃል ነው፡፡" ✨✨✨
ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እንኳን ለበዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ፣ ለቅዱስ ኤልያስ ነቢይ፣ ለቅዱስ ኖኅ ጻድቅ፣ ለታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፣ ለአባ ሙሴ ገዳማዊ እንዲኹም ለአባ ወርክያኖስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ዳግመኛም ዛሬ ጥር 6 ቀን ቅድስት ደብረ ቁስቋም፣ አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን፣ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ፣ ቅድስት ሰሎሜ፣ አባ አርከ ሥሉስ፣ አባ ጽጌ ድንግል እንዲኹም ቅድስት አርሴማ ድንግል ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼

+++እፈርድ ዘንድ እኔ ማነኝ?+++
በአንድ ወቅት አባ ፖርፎርዮስ እና ሦስት መንፈሳዊ ልጆቻቸው ወደ ገዳም ሲመለሱ መንገዱ በጣም ስላደከማቸው ታክሲ መያዝ ፈለጉ። በአጋጣሚ በርቀት ታክሲ ተመለከቱ። ሦስቱ የአባ አገልጋዮችም ታክሲውን ለማስቆም ገና ሲያስቡ ፤ አባ ፖርፎርዮስ "ተዉ አትጨነቁ ታክሲው በራሱ ይቆማል ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ ከገባን በኋላ ከእኔ በስተቀር ከታክሲ አሽከርካሪው ጋር ማንም እንዳይነጋገር" አሉ። አባ ፖርፎርዮስ እንደተናገሩት ለታክሲው ማንም ምልክት ሳይሰጠው ፤ ያሉበት ቦታ መጥቶ ቆመ። ኹሉም ወደ ታክሲው ገቡ ፤ አባ ፖርፎርዮስም የት መሔድ እንደሚፈልጉ ለሾፌሩ ተናገሩ።
አሽከርካሪው መኪናውን መንዳት እንደጀመረ ወዲያው ስለ ካህናት በደል እና ኃጢአት ማውራት ጀመረ። ስለ ካህናቱ በሚያቀርበው በእያንዳንዱ ክስና ዘለፋ ፤ ወደ ኋላ እየዞረ ሦስቱን ወጣት አገልጋዮች "እሺ ስለዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ ወጣቶች?" ይላቸዋል። ሦስቱ ወጣቶች ግን የአባን ቃል በማክበር አንዳች ምላሽ አይሠጡም ነበር። የታክሲ አሽከርካሪው ወጣቶቹ ምንም መልስ እንደማይሰጡት በተረዳ ጊዜ ወደ አባ ፖርፎርዮስ ዞር ብሎ "አባዬ!(በፌዝ መልክ) የተናገርኹት ኹሉ እውነታውን ነው ፤ አይደል እንዴ?" ሲል ጠየቃቸው። አባ ፖርፎርዮስም መልሰው "ልጄ አንድ አጭር ታሪክ እነግርሃለሁ ፤ የምነግርህ አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ኹለት ጊዜ ትሰማው ዘንድም አያሻም" አሉትና ቀጠሉ።
"በአንድ ወቅት አንድ ቦታ ላይ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ጎረቤት በእድሜ ሸምገል ያለና በጣም ትልቅና ሰፊ መሬት ያለው ነበረ። ሆኖም በአንድ ምሽት ይኼ ሰው ባለሀብት የነበረ ጎረቤቱን ገድሎ መሬት ቆፍሮ ቀበረው። ይኼ ሳያንስ በሐሰተኛ መረጃዎች ንብረቱን ወደ ራሱ አዙሮ ፤ ያንን ትልቅ መሬት ሸጠው። ከዚያ መሬቱን በሸጠበት ገንዘብ ምን እንደገዛ ታውቃለህ? <ታክሲ ገዛበት>" አሉት። በዚህ ሰዓት ከሰማው ታሪክ የተነሣ ደንግጦ መንቀጥቀጥ ጀመረ። መኪናውን እንደምንም ወደ ዳር አስይዞ ካቆመ በኋላ እየጮኽ "አባ ዝም ይበሉ! ይህን ጉዳይ እርስዎ እና እኔ ብቻ ነን የምናውቀው ፤ እባክዎ ዝም ይበሉ!" አላቸው። አባም ቀጥለው "ይህን ሥራህን እግዚአብሔርም ያውቀዋል ፤ ይህን እንዳሳውቅህ የነገረኝ እግዚአብሔር ነው ፤ አሁንም ንስሓ ገብተህ ሕይወትህን አስተካክል" አሉት።
+++
+ ተወዳጆች ሆይ! "የምዋቹን ሞት አልፈቅድም" (ሕዝ. 18: 32) ያለው አምላክ እቅፍ ሥር መሆን እንዴት ያለ መታደል ነው? መድኃኔ ዓለም ስንተወው የማይተወን ፣ ስንገፋው የማይገፋን ፣ ስንርቀው በአባታዊ ፍቅር በምክንያት የሚጠራን ፣ ክፋታችንን በፍቅር ፣ መታበያችንን በትዕግሥት የሚያቸንፍ በእውነት ተናግረው የማይፈጽሙለት የነገሥታት ንጉሥ ፣ የኃያላን ኃያል በእውነት እርሱ ነው።
+ እግዚአብሔር ያከበራቸው ካህናትን ከሥጋ ድካም የተነሣ የማይባቸውን ጉድለት አይቼ ልፈርድ ቀርቶ አጠገቤ ስላለው ወንድሜ በደል እና ኃጢአት እገልጥ ዘንድ እኔ ማነኝ? አምላኬ ሆይ! ዛሬ የወደዱኝ ከፍ ከፍም ያደረጉኝ ፣ ቢያውቁት ኖሮ እንዲጠሉኝና እንዲሸሹኝ የሚያደርገውን በደሌን ተሸክመህ በቸርነትህ ሸፍነኽው ባይሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር? ወዴትስ እሸሸግ ነበር?
+ በተስፋ መቁረጥ እንዳልጠፋ የታገሥኽኝን መታገሥ ፣ የምትጠራኝን የንስሓ ጥሪ ሳልረዳ አሁንም በበደል ለምኖር ልጅህ ማስተዋልን አድለኝ! ዛሬም ከእቅፍህ ሳትለየኝ ልጄ ብለህ ቀጥተህ ፤ ዘወትር በማትነጥፍ ቸርነትህ በምሕረትህ ጎብኘኝ!
Source : The Orthodox Life ተሻሽሎ የቀረበ!
ስብሐት ለእግዚአብሔር
✍ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ጥቅምት 11 2013 ዓ.ም