መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁

መድኃኔዓለም ሰውን እንዴት አዳነው? 🤔

👉 የአዳምን ዕዳ ፍጡራን ሊከፍሉት አልቻሉም። ስለዚኽም እግዚአብሔር ወልድ ሰው ኾኖ ዕዳችንን ከፈለልን 🙏 አዳም ሊቀበለው የሚገባውን ኹሉ ተቀብሎ አዳምን ነጻ አወጣው።

👉አዳም በበደሉ ከገነት ወደ ሲዖል ቢሰደድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ያለ በደሉ የገነት ምሳሌ ከኾነች ከነዓን የሲዖል ምሳሌ ወደ ኾነች ግብጽ ተሰደደ 🙏

👉አዳም ከዓለመ መላእክት ተሰድዶ ከእንስሳት መካከል ቢገኝ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በእንስሳት በረት ተወለደ 🤲

👉አዳም በመብል ድል ተነሥቶ ከገነት ቢወጣ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ጭምር እንጂ"ብሎ ፈቃደ ሥጋን እና ስስትን ድል ነሣለት 🙏

👉 አዳም ሕግ ጥሶ ከጸጋ ቢራቆት፤ ክርስቶስ ራቁቱን በመልዕልተ መስቀል ተሰቀለለት 🙏

👉 የአዳም እጅና እግሮች ወደ ዕጸ በለስ ቢያመሩ፤ የክርስቶስ እጅና እግር በቅንዋት ተቸነከሩ 🙏🙏🙏

አቤቱ ጌታ ኾይ ማረን 🤲🤲🤲
ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያገኘነው ምንድን ነው?
#ዳግም_ልደት
በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል።
#ሰላም
በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና።
#ብርሃን
“በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ሥራ ተወስነን ብርሃን ሆነን ልንኖር ይገባል።
#ነጻነት
“በነጻነት እንኖር ዘንድ ክርስቶስ ነጻ አወጣን። ከእንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገና በባርነት ቀንበር አትያዙ”። ገላ 5፥1። የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በነጻነት እያመሰገነ ይኖር ዘንድ ተፈጥሯልና። ኃጢአት በመሥራት የዲያብሎስ ባርያ ሳንሆን በተሰጠን ነጻነት በመጠቀም የጽድቅ አገልጋዮች ሆነን ልንመላለስ ይገባል።
#ይቅርታ
በአዳም በደል ምክንያት ከአብራኩ የተከፈሉ በሙሉ በደለኛ ሆነው የነበሩበትን ዘመን ለውጦ አዳምንና የልጅ ልጆቹን በደል ደምስሶ ፍቅርን ይመሰርት ዘንድ ጌታ ተወለደ። በምድርና በሰማይ ላሉት ፍቅርን መሠረተ። እርሱ የሰው ልጆችን በደል ሳይቆጥር ሁሉን ይቅር እንዳለ ክርስቲያንም የበደሉትን ሁሉ ይቅር ይል ዘንድ የፈጣሪው ትዕዛዝ ነውና ዘወትር ሊፈጽማት የምትገባ ከእግዚአብሔር ጸጋ የምታስደምር የልደቱን ብርሃን ለማየት እንደበቁ በዚህም ደስ እንደተሰኙ እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእውነተኛ ምስጋና የምታደርስ የጽድቅ መሠረት የበረከት በር ናት። ማቴ 18፥21-23፣ ማቴ 5፥23-25። መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ የሚለው አምላካዊ ቃል ይቅርታ የክርስትና ሕይወት መመሪያ መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልንፈጽማት ይገባል።
#ፍቅር
ፍቅር ሰሃቦ ለወልድ ኃያል እም መንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት /ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።/ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅን በደል ሳይቆጥር በዙፋኑ ሆኖ ምሬሃለሁ ማለት ሲችል ፍቅሩን ይገለጽ ዘንድ በከብቶች በረት ተወለደ። እውነተኛ ፍቅሩ ለክርስትናችን መሠረት ለጽድቃችን ፋና እንደሆነ መጻሕፍት ያረጋግጣሉ።
እንግዲህ በልደቱ ያገኘነውን ሰላም፣ ነጻነት፣ ይቅርታ፣ ብርሃንና ፍቅር ዋጋ የተከፈለበት ጸጋ የወረስንበት በመሆኑ ዘወትር በድንቅ ፍቅሩ የሚታደገን አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን እንድንኖር ክብራችንንና ጸጋችንን አስተውለን ከኃጢአት ርቀን በንሰሐ ታጥበን እራሳችንን ለክርስቶስ የተወደደ መስዋዕት አድርገን እንድናቀርብ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን።
አሜን።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
​​እንኳንለብርሃነ
🕯🕯🕯🕯
🕯🕯🕯🕯
🕯🕯🕯🕯ዋዜማ በሰላም
🌹
🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹
🌹🌹
🌹🌹🌹
"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ

🕯🕯📖📖🕯🕯

📖📖📖
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)
📖📖📖
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)
📖📖📖
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6
🕯🕯🕯🕯🕯
ውድ አባቶቼ እናቶቼ ወንድም እህቶቼ፡ህፃናት የተዋህዶ ልጆች


🌷በሀገርም🌷
💜ውስጥ💜
🌹ከሀገርም🌹
💜ውጭ💜
🌷ያላችሁ🌷
🌹በስደት🌹
🌳በእስራት🌳
🌳በጎዳና🌳
🌳በጭንቅ🌳
🌳በአልጋ🌳
🌳በዱር🌳
🌳በበረሃ🌳
🌳በዋሻ🌳
🌳ያላችሁ🌳
💜ለመላው💜
🌹የክርስትና🌹
💜እምነት💜
🌷ተከታይ🌷

💜በሙሉ💜

🌹እንኳን🌹
💜💜
ለብርሃነ ልደቱ
ለጌታችን ልደት
💙በዓል 💜
🌹በሰላም🌹
💜አደረሳችሁ💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
ባ ለ ው ለ ታ ች ን
🌷🌷🌷🌷🌷
ጌ ታ ች ን
🌹🌷🌹🌷
አ ም ላ ካ ች ን
🌹🌳🌹🌳🌹
መ ዳ ኒ ታ ች ን
🌹🕯🌹🕯🌹
🍸🍸
🍸🍸
🍸🍸
🍸🍸
🕯🕯 ክርስቶስ🕯🕯
🕯🌳🌹የእናታችን 🍸
🕯🌳🌹የቅድስት 🍸
🕯🌳🌹ድንግል🍸
🕯🌳🌹ማሪያም🍸
📖📖
📖📖
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯

🌺🌺በቸርነቱ 🌺🌺
🌺
🌺🌺
🌺🌺🌺
🌺
🌺
🌷💜🌷 🌹🌳🌹
🌹 የሰላም 🌳
🌹የደስታ 🌳
🌹 የፍቅር🌳
🌹የበረከት🌳
🌹የአንድነት 🌳
🌳🌳🌳🌳🌳🌳
🌳በዓል
🌳🌳ይሁንልን
🌳አሜን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳
🌹
🕯
🍸
📖
ባ ለ ው ለ ታ ዬ

🌹🌳🌹🌳🌹🌳

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ :
እምቅድስት ድንግል :
ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ :
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ:
አማን:
መንክር ስብሐተ ልደቱ።


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ህፃን ተወልዶልናል፡ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ስሙም
ድንቅ መካር ኃያል፤የዘላለም አባት የሰላም አለቃ
ተብሎ ይጠራል ኢሣ9:6
እንኳን አደረሳችሁ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያውያን ናቸውን?
በልደት ዋዜማ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
💥 የሦስቱ ነገሥታት የአነሣሣቸውና የተነሡበት ሀገር ምንነት የዓለም ሊቃውንትን አነጋግሯል፤ የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን ትኩረት ስቧል፤ ወንጌላዊው ማቴዎስ አመጣጣቸውንና ስጦታቸውን ተናገረ እንጂ ሀገራቸውንና ስማቸውን አልጻፈም፨

💥 ለማንኛውም ነቢያት ስለነዚኽ ነገሥታት ሀገር በትንቢት ምን ተናገሩ? የሚለው ለሁሉም መልስ ይሆናል።
ከነቢያት ዳዊትና ኢሳይያስ የሰብአ ሰገል አመጣጥ ተገልጾላቸው ትንቢት ሲናገሩ፤ ይልቁኑ ኢሳይያስ ሀገራቸው የሳባ ምድር ኢትዮጵያ እንደኾነና ኹሉም ከዚኽ እንደሚኼዱ፦
💥"የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ" (ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 6) አለ፨

💥 ዳዊትም በመዝሙሩ ላይ ለአምላክ ልደት ስጦታ እንደሚመጣ ጠላት ሰይጣን ጠላት ሄሮድስ እንደሚያፍሩ ኢትዮጵያውያን በፊቱ እንደሚሰግዱ፦
💥 "በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ ነገሥታትም ሁሉ ይሰግዱለታል" (መዝ 71 (72):9-10) ይላል። ይህም የትንቢት ቃል ሲፈጸም፦
“ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።” (ማቴዎስ 2፥11) ይለናል።

💥 በተጨማሪም ዳዊት "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር" ( ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች (ታደርሳለች)፤ የምድር ነገሥታት እግዘአብሔርን አመስግኑት" በማለት ትንቢት ተናግሮላታል፨

💥 ታላላቅ ሊቃውንት እንደገለጹት የግእዝ ቋንቋችን እንደሚያስረዳን "በጽሐ" የሚለው የግእዝ ቃል ቀጥታ የዐማርኛ ትርጉሙ (ደረሰ) ማለት ሲኾን ታበጽሕ ማለት ደግሞ (ታደርሳለች) ማለት ነው፨ "ሰፍሐ" ማለት ግን (ዘረጋ) ማለት ነውና ትሰፍሕ ቢል ትዘረጋለች ባልን ነበር፤ መዘርጋት ማንም ሊዘረጋ ይችላል፤ ዘርግቶም ሊቀበልም ላይቀበልም ይችላል፤ ይኽቺ ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ግን "ታበጽሕ" (ታደርሳለች) ተብላ ተነግሮላታልና አምላኳ ሲወለድ ሥጦታን በማቅረብ በእውነት አድርሳለች ነገሥታቱም አመስግነዋልና ይኽም ከአምላኳ ለርሷ ብቻ የተሰጠና የተነገረላት ነው (መዝ 67:11)፨

ሥጦታም መስጠት ጥንቱኑ በብሉይ ኪዳን በነ ንግሥት ሳባ የጀመረችው እንጂ ለሀገሪቱ እንግዳ አይደለም "ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር" እንዲል (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 10: 10)፨

ከምንኖርባት ፕላኔት መሬት ላይ ካሉ የዓለም ሀገራት በብቸኝነት ጌታችን የተወለደበትን ወር ለክርስቶስ አምላኳ የሰጠች ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ይኸውም ጌታ የተወለደበትን ወር "ታኅሣሥ" ብላለች በቋንቋዋ በግእዝ፤ ይኸውም በግእዝ ቋንቋ "ኀሠሠ" ማለት ፈለገ ማለት ሲኾን ታኅሣሥ ማለት "ወርኀ ተኀሥሦ" (የማሰስ ወር፣ የፍለጋ ወር) ማለት ሲኾን፤ ሊቃውንት ይኽነን ያሉበት ምክንያት ሦስቱ ነገሥታት "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና" እያሉ አስሰው ፈልገውት ስላገኙት ይኽ ሥያሜን ቀደምት አባቶቻችን ሰጥተዋል (ማቴ 2: 1-2)
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"የጌታ ልደት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"

ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡

መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡

እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ"
(ብፁእ አቡነ ሺኖዳ)

ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ኑ በፀሎት ወደአምላክ ቅረቡ ፤ በፀሎት ማለት እንዴት ነው? ይህስ የልባችሁን ምስጢር ሁሉ ሳትደብቁ እርሱ እግዚአብሄር እንደሚያስፈልጋችሁ መናገር ማለት ነው ፤ እንዲህም በሉ ፦ “ጌታ ሆይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁ ፡ ጌታ ሆይ ካንተ ተለይቼ እኔ ምንም ነኝ ፡ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴን አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ደስታየን ሁሉ አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ትርጉም አልባ ሆነ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ጣእም አልባ ሆነ” በሉ ፤ ዳግምም ከእግዚአብሄር እግር ስር ተደፍታችሁ እንዲህ በሉት፦ “ አምላኬ ሆይ ፦ ወደ አንተ መመለስ እፈልጋለሁ ፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ከእኔ በእጅጉ የሚበልጡ ናቸው ፤ ነፍሴንም አምላክሽ አያድኑሽም የሚሏት ብዙ ናቸው” ፡፡

ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ “ ጌታ ሆይ ታደገኝ ወደ አንተ የምመለስበትን መንገድ ምራኝ” በሉት ፤ ለአምላካችሁ ንገሩት ፦ “ካንተ ከተለየሁ ወዲህ አቅሜ ሁሉ ተዳክሟልና ጌታ ሆይ ልዩ ሃይልህን ላክልኝ ፡ ወዳንተ የምመለስበትን ልዩ ርዳታህን ስጠኝ ፤” በማለት፡፡ ብዙ ሰወች በመደጋገም “ወደ እግዚአብሄር የምመለሰው እንዴት ነው ?” ይላሉ፡፡ ከእግዚአብሄር እግር በታች ራሳችሁን ጣሉ ፡ እንዲህም በሉት ፦ “ ጌታ ሆይ ሳትባርከኝ አልለቅህም ፡ ወዳንተ አቅርበኝ ፡ ከልጆችህ እንደአንዱ አድርገኝ ፡ ሃጢአቴን ብቻ ይቅር እንድትልልኝ አልሻም ፡ ይልቁንም ከሃጢአት ፍቅር ትለየኝ ዘንድ ጭምር እንጂ ፡”በሉት ፦ ዳግምም “ ጌታ ሆይ የሃጢአት ፍቅር ልቤን ተቆጣጥሮታልና ይህን ካላስወገድኩ ወዳንተ መቅረብ አይቻለኝም ፡ ጌታ ሆይ የሃጢአትን ፍቅር ከልቤ ላይ ንቀል ፡” በሉት ዳግምም እንዲህ በሉት ፦ ”ጌታ ሆይ ከሃጢአቴ ነፅቼ ወዳንተ መምጣት እንደምን ይቻለኛል? ይልቁንስ መጀመሪያ አንተ ናልኝ ሃጢአቴንም ደምስስ እንጂ “ እንዲህም በሉት ፦ “ በራሴማ ሃጢአትን ማስወገድ ብችል ወዳንተ መቼ መመለስ ያቅተኝ ነበር? እኔ ግን አንተ ከሃጢአቴ እንድታርቀኝ እወዳለሁ ፡ ጌታ ሆይ ፦ ሃይልህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” በሉት፡፡

እመኑኝ የምወዳችሁ ልጆቼ ፦ ትክክለኛዋን ፀሎት ያወቃት እርሱ ትክክለኛዋንም ንስሃን የሚያውቅ እርሱ ነው ፤ ማር ይስሃቅ እንደተናገረው ፦ “ንስሃ ከፀሎት ውጭ እንደሚገኝ የሚያስብ ሰው እርሱ በዲያቢሎስ የተታለለ ነው” ምክንያቱም በፀሎት ወደ እግዚአብሄር የምትመለሱበትን ሃይልን ታገኛላችሁና፡፡ ስለሆነም ከየትኛውም ስራ ይልቅ ራሳችሁን ለፀሎት አስገድዱ ፤ ምክንያቱም በፀሎት አማካኝነት በእናንተና በእግዚአብሄር መካከል ያለውን ግድግዳ አስወግዳችሁ እንደገና ወደእርሱ ትመለሱ ዘንድ ይቻላችኅልና ፤ በጣም ብዙ ሰወች ከፀሎት ይልቅ ለአገልግሎት መትጋታቸው የሚገርም ነው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በንባብ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በተመስጦ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በመንፈሳዊ ስብሰባወች ለመታደም የሚተጉትም እንደዚያው ፤ ለዚህ እኮ ነው ከእግዚአብሄር ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይሳካላቸው ፤ ይፀልያሉ ያነባሉ ደግሞም ስብሰባወችን ይታደማሉ በዚህ ሁሉ ሰአት ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም ፤ ምንም አይነት ግንኙነት ፡፡

ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ወደእግዚአብሄር ተመለሱና ከእርሱ ውሰዱ ፤ አንዳንድ ሰወች በመፀለይ ለእግዚአብሄር የሚሰጡት እንዳለ ያስባሉ ፡ ለእግዚአብሄር ቃላትን ይሰጡታል ፡ ጊዜን ፡ ምናልባትም ስሜታቸውን ፤ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ፀሎት ከእግዚአብሄር የመውሰድ ጉዳይ ነው ፤ እርሱ ሰጭ እንጂ ተቀባይ አይደለምና ፤ በፀሎቱ ስኬታማ ውጤትን የሚያመጣ ሰው እርሱ ከእግዚአብሄር ስለሚወስደው የፀለየና እንደዚያም የሚያምን ነው ፤ እርሱ ነው በፀሎቱ የተሳካለት፡፡ በምትፀልዩበት ጊዜ ከእግዚአብሄር ሃይልን እንደተቀበላችሁ ከተሰማችሁ ፡ ያን ጊዜ ውጤታማ ፀሎት ፀለያችሁ ፤ አንድ ሰው ፀልዮ ከእግዚአብሄር በረከት ከተቀበለ፡ እንግዲህ ይህ ሰው ነው ውጤታማ ፀሎት ያቀረበው ፤ ማንም በፀሎት በፀፀትና በንስሃ ወደእግዚአብሄር ቢቀርብ እርሱ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ለቅድስና ቢታገል ፡ ይህ ሰው ፀሎቱ ውጤታማ ሆነ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ቢያጠናክር ይሄኔ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ፡፡

እግዚአብሄር እንድትመጡ ይናገራችኅል ፡ በፀሎት ኑ ና የሚያስፈልጋችሁን ልስጣችሁ እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ለሁለት ደቂቃ ብቻ ትፅልዩና ወዲያው ትሰለቻላችሁ ፡ ከእግዚአብሄርም አንዳች ሳትቀበሉ ትሄዳላችሁ ፤ እግዚአብሄር ወደእናንተ ያይና እንዲህ ይላል ፦ “ስለምን ከእኔ ሳትቀበሉ ተመለሳችሁ? የሚያስፈልጋችሁን ልሰጣችሁ ወድጄ ነበርና ፤ ስለምን ቶሎ ተመለሳችሁ ያዘጋጀሁላችሁን ሳትወስዱ?” እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ቶሎ ሰለቻችሁና ለመሄድ ወሰናችሁ ፤ እሺ ሂዱ ፡ ከዚያ ግን እግዚአብሄርን መፈለግ ትጀምራላችሁ አታገኙትም ፤ ጥላችሁ ስትሄዱ ያጣችሁት ምንም ሳትይዙ መሄዳችሁን ብቻ እንዳይመስላችሁ በልባችሁ ለእግዚአብሄር ጊዜ እንደሰጣችሁት ማሰባችሁም ጭምር እንጂ ፤ ወዲያውም ከመንፈሳዊ የስኬት ድርጊቶች ውስጥ መፀለያችሁን ትፅፋላችሁ፡፡

ይህ ግን ፀሎት አይደለም!!! ከእግዚአብሄር ከቶ ምን አገኛችሁ? እግዚአብሄርን አጥብቃችሁ ልትይዙት ይገባል አጥብቃችሁ መቼም ቢሆን ካንተ አልለይም መለየትም አልፈልግም ማለት አለባችሁ፡፡ ስለዚህ እኮ ነው ለፀሎት ትእግስት የሚያስፈልገው፤ ያለትእግስት ከእግዚአብሄር አንዳች እንኳን ልትቀበሉ አትችሉም፤ በፀሎታችሁ ትእግስተኞች ልትሆኑ ይገባችኅል፤ እግዚአብሄርን ንገሩት፦ ከእግርህ በታች እንደሆንኩ እቆያለሁ በረከትህንም ሳትሰጠኝ አልነቃነቅም ከእግዚአብሄር በረከትን ካልተቀበልኩ እርሱን መያዜን አልለቅም ካልባረከኝ አልለቅህም እይዘዋለሁ ወዴትም ይሄድ ዘንድ አልተወውም፤ እንግዲህ ይህ ነው በፀሎት ውስጥ ያለው ትግል፤ ሰወች ፀሎት እንዴት እንደሚፀለይ አልተማሩም እነርሱ የሚያስቡት ፀሎት ማለት ጥቂት ቃላትን መናገር ይመስላቸዋል አይደለም፡፡

ፀሎትን አዘውትሩ፡- ከእግዚአብሄርም አንዳች እስክትቀበሉ ድረስ ታገሉ ፤ አንዳች እንኳን ካልወሰዳችሁ ሳትቀበሉ የትም እንደማትሄዱ ንገሩት ፀሎቴን አልገታም በሉት እንደተፃፈ አንተ ሩህሩህ መሃሪ አምላክ ነህ የለመነውን ሁሉ የምትሰጥ ነህና እንግዲህ እኔም ለምኜሃለሁ እስከምትሰጠኝ ድረስ ወዴትም አልሄድም በሉት፤ በፀሎታችሁ ከእግዚአብሄር ጋር ታገሉ ያን ጊዜ ታርፋላችሁ በፍቅር ትሞላላችሁ በፀሎታችሁም ብርቱ ትሆናላችሁ ከንቱ ነገርንም መደጋገም ትተዋላችሁ እንዲያውም ልባችሁን በእግዚአብሄር ፊት ትዘረጋላችሁ፤ የሳሙኤል እናት ሃና በፀሎቷ ጊዜ ታለቅስ ነበር በልቧም ልጅ እንደምታገኝ ቃል ሳይገባላት ከቤተመቅደሱ ላለመውጣት ወስና ነበር ፤ ንጉስ ዳዊት ከእግዚአብሄር በረከትን እስኪቀበል ድረስ ፀሎቱን አላቋረጠም በመጀመሪያ “ጌታ ሆይ ፦ አስጨናቂወቼ ምንኛ በዙ” በማለት ፀለየ፤ ቀጥሎም እንዲህ አለ ፦ “ እናንተ ክፉ አድራጊወች ከእኔ ራቁ እግዚአብሄር ፀሎቴን ሰምቶልኛልና ፡ ጌታየ የልመናየን ድምፅ አድምጧልና ጌታየ ፀሎቴን ሰምቷልና“፡፡ ኑ ወደእግዚአብሄር ተመለሱ፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🕯``ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ``🕯

💡ጉባኤ፦ የድንግል ሕይወት💡


[ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ
ቅዱስ ቄርሎስ]
“Come, O all ye women who desire
virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን
እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ
መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ
ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም
ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ
በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም
በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ
አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ
የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ
አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤
ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን
ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር
ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም

ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን
[መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

Join 👉 @linkortodoxe21💡