መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ጾም ስጦታ ነው:- የጾምን ጥቅሞች እያወቅን ስንመጣ ጾም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እንረዳለን፡፡ አዎን፤ጾም እንዲሁ ከአሥሩ ትእዛዛት እንደአንድ ትእዛዝ የሚቆጠር ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ ስጦታ፣ጸጋ እና በረከት ነው፡፡ እኛን ሥጋና ነፍስ አድርጎ የፈጠረን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የሚጠቅመው ጾም እንደሚያስፈልገን የሚያውቀው ለመንፈሳዊ ዕድገታችንና ለዘላለማዊነታችን የሚያስብልን እግዚአብሔር ጾምን ተግባራዊ የምናደርግበትን እውቀት አድሎናል፡፡ እሱም እንደ ቸር አባትና እንደ ጠቢብ መምህር ጾምን ለእኛ አዞልናል፡፡ በራሱ ኃይልና እውቀት የሚተማመን ሰው በራሱ ይመካል፤ ድካሙን የተገነዘበ ሰው ግን ችግር ሲገጥመው ልመናውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው በጾም ውስጥ ሆኖ ነው፡፡እግዚአብሔረ ለችግሮቻችን ሁሉ የደርስ ዘንድ ጾም ትክክለኛው ጊዜያችን ነው፡፡ ይህ ጊዜ የተሰበረ ልብ ወደ እግዚአብሔር የሚጣራበት እግዚአብሔር ደግሞ የሚሰማበት ጊዜ ነው፡፡ በእውነተኛ ጾም ውሰጥ ሰው የእግዚአብሔርን ልብ ማራራት ይችላል፡፡ አንድ ቅዱስ መነኩሴ "ፀሐይ ምግብ ስበላ ከተመለከተችኝ እንሆ ሠላሳ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡" በማለት ተናግረዋል፡፡ እስክንድርያዊው ቅድስ መርቆርዮስ ምግብ ይበላ የነበረው በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነበር፡፡ሰው በተራበ ጊዜ የሚያቀርበው ልመና(ጸሎት) ይበልጥ ተሰሚነት አለው፡፡ሆድህ በምግብ ተሞልቶ ከምትጸልየው ሰዓታት ከሚወስድ ፀሎት ይልቅ በረሀብ ውስጥ ሆነህ የምታቀርበው የሁለት ደቂቃ ጸሎት ጥልቀት፣ ተሰሚነትና ተቀባይነት አለው፡፡

አቡ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
1
ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ? ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ? ፍቅር ? ሰላም ? መቻቻል ? ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ? እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?

💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21💛
❤️ @linkortodoxe21❤️
"ነገ ለአንተ የተሻለ ነው"
ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡
ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።
ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
⁵ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
👉@linkortodoxe21
እንካን ለጻድቁ ተክለ ሀይማኖት አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳቹ 🌿🌿🌿🌱🌱🌱🍀🍀🍀🌿🌿🌿🌱🌱🌱🍀🌿🌱🍀🍀🌿🌿🌿🌱🌱🌱🌿🌿
እሱ ማነው???


ሀይማኖቱን ከከሀዲ ዮዲት ጉዲት መሳይ
የሚከላከለው መንጋን ተመለስ ባይ
ማርያን- ጠንቋዩን ለአምላክ ያስገዛ
የወንጌል ገበሬ የኢትዮጵያ መዓዛ
እኮ እርሱ ማነው??
የትሩፋት መምህር የእግዚአርያ በረከት
የክርስቶስ ወታደር የብዙዎች አባት
ኢትዮጵያን ያበራት በወንጌል አዝመራ
ባለ ብዙ ሰብል በመኸር ጎተራ
በሰባኬ ክረምት በተዓምራት ፀደይ
የበረከት አባት በፍሬው የሚለይ
እኮ እርሱ ማነው??
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ለምስጋና ሚቆም ከመንበረ ስሉስ
እንደ መላእክቱ ክንፍ የተሸለመ
እርሱስ ባህታዊው ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡
"" እንኳን ለአባታችን ለፃዲቁ ለአቡነ ተክለሀይማኖት በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡""
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤

✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አምላክ ለምን ሰው ሆነ ????
* ለአዳም የገባለት ቃል ኪዳን ይፈፀም ዘንድ
* የዓለምን ሕዝብ ከኃጢአት ለማንፃት
* የዓለምን ሕዝብ ከጽኑ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት
* ከእኛ በላይ ማንም የለም ይሉ ለነበሩ ሁሉ የሁሉም የበላይ አምላክና ጌታ
መኖሩን ያውቁ ዘንድ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ተገለጠ።
* አምላክ አካል የለውም ይሉ ለነበሩ አካላዊነቱን ይገልጽ ዘንድ ወልድ
በተዋህዶ ሰው በመሆን ተገለጠ።
* ምድር ለመልካም ተፈጥራ ሳለ ስለ ሰው ኃጢአት በመረገሟ ምክንያት
ምድርን ሊቀድሳት፣ሊባርካት እርግማኗን በንጹህ ደሙ ያጠፋላት ዘንድ ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆነ። ኢሳ. 45፥18 ዘፍ. 3፥17
* እውነተኛ ሠላምና እርቅን ለመስጠት
* ከዘላለም ሞት ለማዳን 1ኛ. ዮሐ.5፥20
* የአለም ብርሃን ለመሆን ዮሐ 8፥12
* እውነት የሆነው የሕይወት መንገድ ለጠፋባቸው ሰዎች ኢየሱስ
እውነትም፣መንገድም፣ሕይወትም ሆኖ ተገለጠ።ዮሐ 14፥6
* የሰው ልጅ በትዕዛዝ የተሰጠውን ሕግ ይፈፅም ዘንድ ባለመቻሉ ምክንያት
ሕግን ሠርቶ ፈጽሞ ያሳየው የለምና እግዚአብሔር በተዋህዶ ተገልጦ ህግን
ፈጽሞ ያሳየን ዘንድ ሰው ሆነ። ማቴ. 5፥17

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ በሁለት ሰዎች ላይ ሞት ፈርዶ ሲያበቃ ለመጨረሻ ጊዜ የምትናገሩት ሐሳብ ካለ ይዛችሁት ከምትሞቱ ሐሳባችሁን ግለጹ አላቸው። አንደኛው የሞት ፍርዱ ላይነሳልኝ ምን አደከመኝ ብሎ ያስብና ምንም የምናገረው ነገር የለኝም የለኝም ይላል።

ሌላኛው ግን ዝም ብዬ ከምሞት ብሎ ያስብና አንድ መላ ያመጣል። ንጉሱ አንድ በጣም የሚወዳት ምርጥ ፈረስ እንዳላቸው ስለሚያውቅ "ንጉስ ሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ! እኔ የሚወዱትን ፈረስዎ ለአንድ ዓመት መብረር ላለማምውደ እችላለሁ" ይህ የሚሆነው ግን የአንድ ዓመት ዕድሜ ከተሰጠኝ ብቻ ነው ይላል።

ንጉሡም አባባሉ ቢያስገርመውም "የሚበር ፈረስ ያለው በዓለም ላይ ብቸኛ ንጉሥ" መባሉን ውስጡ ስለወደደው በነገሩ ተስማምቶ የአንድ ዓመት ዕድሜ እንዲሰጠው ፈቀደ ።

ከችሎቱ መልስ ያ ዝም ያለው ባልንጀራው በዚህኛው ላይ ስላቅ ተናገረበት "ወፈፍ ያረግሃል ልበል? አሁን በየት ሀገር ነው ፈረስ የሚበረው? አንድ ዓመት ረዥም መስሎህ ነው ይህን የማይሆን ነገር የምትናገረው? ምናለ ጣርህን ባታበዛው" አለው።

ብልሁ ሰው ግን ተኩራርቶ እኔ እንዳንተ ዝም ብዬ አልሞትም ይህን ሃሳብ ሳቀርብ ነጻ ለመውጣት አራት አማራጮች አሉኝ እነርሱም፡-
፩ኛ. #በዚህ #አንድ #ዓመት #ንጉስ #ሊሞቱ #ይችላሉ

፪ኛ. #እኔ #እራሴ #ልሞት #እችላለሁ

፫ኛ. #ፈረሱ #ሊሞት #ይችላል

፬ኛ. #ማን #ያውቃል #ምንአልባት #ፈረሱን #መብረር #አስተምረው #ይሆናል። አለው ይባላል።
እኛም ዝም ብለን ከነኃጥያታችን ልንሞት አይገባም ንስሐ ገብተን ሥጋ ወደሙን ተቀብለን ነጻ ወጥተን ብንሞት ይሻለናል

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"እገድልሐለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ።"

.በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን
ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሠውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስጸያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውሐ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብህ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሠውየውን "እገድልሐለሁ።" ብሎት ይሄዳል። ሠውየውም ይሄ ዲያቆን እገድልሐለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው? ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል።

. ከእለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሠዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ
ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው
ሠውየ ልጅ መሆኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ
ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሠውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል
ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ? ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን
አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሠውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ "እገድልሐለሁ ያልከኝ
እውነትም ገደልከኝ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? " ሲለው
ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይህን ብቻ
ነው።" ብሎ አለው።

.በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሠውየዉን እገድልሐለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው
ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልሐለሁ ያልኩት ሠውየውን
አይደለም እኔ እገድልሐለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው። እግዚአብሔርም
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን
ገደልኩት።" ብሎ አላቸው። ግሩምና በጣም ጣፋጭ ትምህርት ነው። እኔ እራሴን ታዘብኩት እናንተስ? ከዲያቆኑ ምን ተማራችሁ?

(ይሄን ፁሑፍ የትም ልታነቡት ትችላላችሁ ዋናው አንብባችሁ መማር መቻላችሁ ነው)
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM