መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
+ ስለ እመቤታችን +
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ በምድር ያሉ ችግረኞች ሁሉ የሚኖሩበትን ሀብት የሠጣቸውን የነገሥታትን ጌታ የወለደችው የድሆች ሴት ልጅ ፣ ብዙ ሀብት የጫነች ከአብ ቤት በረከትን ይዛ የምድርን ጉስቁልና ልታስወግድ የመጣች መርከብ ፣ የእናትዋን ሔዋንን ዕዳ የከፈለች ።
ከመዋቲያን መካከል ሆና ሕይወትን የወለደች ሁለተኛ ሔዋን ፣ የወደቀችዋን አሮጊት የረዳቻትና በዕባብ ተነድፋ ከወደቀችበት ያነሣቻት አገልጋይዋ፡፡ ዕርቃኑን ሆኖ በዛፍ መካከል የተሸሸገ ሽማግሌ አባትዋን ልብስ ሰፍታ ያለበሰች ሴት ልጅ
ያለ ጋብቻ ሩካቤ እናት የሆነች ድንግል
በድንግልናዋ የኖረች እናት
ንጉሥ ገብቶ የኖረባት ቤተ መንግሥት
በርዋ ያልተከፈተ ማንም ያልገባባት ቤት
የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡ የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ አለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር?
እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ!
ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤ የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡
... ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት!
ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች፡፡

#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘስሩግ

/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ሆድ አምላክ ይሆናልን ?

💡ጉባኤ፦ ተግሳጽ በመጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ💡

የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል ። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር ። ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው ። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን

የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን ፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው ። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው ። እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው ። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና ። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው ስለሆነ ። ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል ። አንደኛ ከስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም ፤ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው

እንግዲህ እናስተውል ! ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል ። መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ ፤ ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ ፤ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም ። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም ። የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችንን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን ?

ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ። ስለ ፍቅር ትጾማለህ ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ ፤ በፍቅር ብሮሃን ደምቀህ ትነሣለህ ። ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር

ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህ ለዘለዓለም ትኖራለህ እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት እንብለው ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው ፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም

እናም ወዳጄ ሆይ " እለ ከርሦሙ ያመልኩ - ሆዳቸው አምላካቸው ነው " እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ ፫ ፥ ፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ ሰለ በእግዚአብሔር ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም !

ጹመን ከጾመኞቹ ነቢያት ፍጻሜ ከቅዱሳን መላእክት ደስታ ከአማኑኤል ልደት እንድንደር የምድራዊ መልአክ የአቡነ አረጋዊ ጸሎት ይርዳን

አባ ገብረ ኪዳን ( ገብራ ወነባሪሃ ለኪዳነ ምሕረት

💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
"እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ኾይ 🙏
በአካል ሦስት ሲኾን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እርሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን ዓይነ ልቡናዬን ያብራልኝ። 🤲🤲🤲

የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ኾይ 🙏 ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የኹሉ እመቤት ነሽ "

✥መልክአ ኪዳነ ምሕረት✥

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ወዳጄ ሆይ"
በጸሎት የተከፈተ ቀን ብሩህ ነው። በእምነት የሆነ ኑሮ አሳራፊ ነዉ።በፍቅር የሆነ አገልግሎት ድል ነሽ ነው ።በይቅርታ የሆነ ጓደኝነት ዘላቂ ነው ። በመተማመን የሆነ ግንኙነት አርኪ ነዉ። በተስፋ የሆነ ጉዞ የማይደክም ነው ።አንተ ወዳጄ ለበጎ ነገር ጊዜና ጉልበት እንዲሰጥህ ፈጣሪን ለምን

ስትቆም የምትወድቅ ካልመሰለህ ትዕቢት አድሮብሃልና ተጠንቀቅ። ስትወድቅ የምትነሳ ካልመሰለህ ራሱ ሰይጣን አድሮብሃልና ተገሰጽ።

ከተቃራኒ ፆታ ጋር ረጅም ሰአት በገለልተኛ ስፍራ አትቀመጥ ። አእምሮህ ንፁህ ቢሆን እንኳ ለሌላው ፈተና እንዳትሆን፣ ደግሞም ለሰዎች የሐሜት ምክንያት እንዳትሆን ፣ ግንኙነትህን በአደባባይ አድርገዉ። የሚያዳልጡ ስፍራዎች ጎበዞችን ሳይቀር እንደሚጥሉ አትርሳ ።

መልካም ቀን!!!!!!!

join join join
👇👇👇👇👇👇
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🍒💙ድንግል ሆይ 💙🍒

በመሃይምናን ሁሉ አንደበት የስምሽ አጠራር እንደምን ይጥማል ድንግል ሆይ የገናንነትሽ ምስጋና እንዴት ያምራል፡፡ ንጽሕት ርግብ ሆይ ከፀሐይ ከጨረቃ ከከዋክብት ብርሃን ይልቅ የሚያምር የመልክሽ ደም ግባት እንዴት ያማረ የተወደደ ነው፡፡


👉. የምስጋናሽስ ዘፈን ማኅሌት ምን ያህል ይወደድ ለሚሰማው እጅግ ያማረ የተስማማ ነው፡፡ መሰንቆ ለጆሮ እንዲያምር እንዲስማማ የሙሽራ ጌጽ ላይን ማር ላፍ ሽቱ ላፍንጫ የወይን ወለላ ለጉረሮ ጸጅ ለልብ ያማረ የተስማማ እንደ ሆነ፡፡ ውዳሴሽም እንዲሁ ያማረ የተስማማ ነው፡፡


👉. ድንግል ሆይ ክብርሽንና ገናንነትሽን መናገር እጅግ ያማረ እጅግም የተወደደ ነው፡፡ ያበባዋም መልክ የማይጠወልግ የማትደርቅ ንጽሕት ተክል ሆይ የማትጠወልግ የሕይወት እንጨት የእሸቷ ፍሬ የማይረግፍ፡፡


👉. የማትሰበር የክህነት በትር የቅዱስ ምሥጢር አገልጋዮች ካህናቱ የሚመረኮዟት የሚጸጉባት ለምዕመናን ሕንፃ ዘወትር ዝግጁ የሆነች የማትነዋወጽ የሃይማኖት መሠረት፡፡


👉. ብል ነቀዝ የማያበላሻት ሌባ የማይቀርባት ድልብ ማዕበል ሞገድ የማይገፉት መርከብ የውስጧም ዋናተኛ ቀዛፊውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱም በቅዱስ ወንጌሉ ቀዛፊዎች በሐዋርያት ዓለምን ሁሉ ከኃጢአት ማዕበል ሞገድ የሚያሻግር ነው፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏🙏🙏


ወዳጄ ኾይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ። አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልኽ ጠላት አለኽና ነገር ግን ወድቀኽ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ኼዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትኽ ዲያብሎስ ቢያቆስልኽ ማንም አይወቅስኽም መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡

የምትወቀሰው ለቁስልኽ መድኃኒት ማድረግኽን ችላ ያልክ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይኽ ከላይ የነገርኩኽ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይኼዳል ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡

አንተም ከወደቅኽበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትኽ ዲያብሎስን ድል አድርገኽ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡

ስለዚኽ በርታና ተነሥ ዘግይቻለኹ ብለኽ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አኹንም መጀመር ትችላለኽና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

መልካም ዕለተ ሰንበት🙏

💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
1
እንካን ለደስታ አብሳሪው ገናናው መልአክ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ 🙏🙏🙏
ቅዱስ ገብርኤል

ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት ። በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው ። በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድየት በረከቱ አይለየን ።
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ጾም ስጦታ ነው:- የጾምን ጥቅሞች እያወቅን ስንመጣ ጾም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እንረዳለን፡፡ አዎን፤ጾም እንዲሁ ከአሥሩ ትእዛዛት እንደአንድ ትእዛዝ የሚቆጠር ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ ስጦታ፣ጸጋ እና በረከት ነው፡፡ እኛን ሥጋና ነፍስ አድርጎ የፈጠረን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የሚጠቅመው ጾም እንደሚያስፈልገን የሚያውቀው ለመንፈሳዊ ዕድገታችንና ለዘላለማዊነታችን የሚያስብልን እግዚአብሔር ጾምን ተግባራዊ የምናደርግበትን እውቀት አድሎናል፡፡ እሱም እንደ ቸር አባትና እንደ ጠቢብ መምህር ጾምን ለእኛ አዞልናል፡፡ በራሱ ኃይልና እውቀት የሚተማመን ሰው በራሱ ይመካል፤ ድካሙን የተገነዘበ ሰው ግን ችግር ሲገጥመው ልመናውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው በጾም ውስጥ ሆኖ ነው፡፡እግዚአብሔረ ለችግሮቻችን ሁሉ የደርስ ዘንድ ጾም ትክክለኛው ጊዜያችን ነው፡፡ ይህ ጊዜ የተሰበረ ልብ ወደ እግዚአብሔር የሚጣራበት እግዚአብሔር ደግሞ የሚሰማበት ጊዜ ነው፡፡ በእውነተኛ ጾም ውሰጥ ሰው የእግዚአብሔርን ልብ ማራራት ይችላል፡፡ አንድ ቅዱስ መነኩሴ "ፀሐይ ምግብ ስበላ ከተመለከተችኝ እንሆ ሠላሳ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡" በማለት ተናግረዋል፡፡ እስክንድርያዊው ቅድስ መርቆርዮስ ምግብ ይበላ የነበረው በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነበር፡፡ሰው በተራበ ጊዜ የሚያቀርበው ልመና(ጸሎት) ይበልጥ ተሰሚነት አለው፡፡ሆድህ በምግብ ተሞልቶ ከምትጸልየው ሰዓታት ከሚወስድ ፀሎት ይልቅ በረሀብ ውስጥ ሆነህ የምታቀርበው የሁለት ደቂቃ ጸሎት ጥልቀት፣ ተሰሚነትና ተቀባይነት አለው፡፡

አቡ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
1
ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ? ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ? ፍቅር ? ሰላም ? መቻቻል ? ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ? እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?

💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21💛
❤️ @linkortodoxe21❤️
"ነገ ለአንተ የተሻለ ነው"
ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡
ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።
ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
⁵ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
👉@linkortodoxe21