መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
💡"የልብ ያልሆነ ትሕትና?"💡

🪔ኦርቶዶክሳዊ ስነ ልቦና🪔

ትሕትና የልብ ነው፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግሥት ፣ መንግሥተ ሥላሴን እየሰበክህ ትሑት ልትሆን ይገባሃል፡፡ ትልቁን ትሕትና ነገረ ሥጋዌን እየተናገርህ ትሑት መሆን ያስፈልግሃል፡፡

ተዋሕዶ ማለት ትሕትና ማለት ነው፡፡ ባለጠጋው መለኮት ከድሃው ሥጋ ጋር የተዋሐደበት ማለት ነው፡፡ የሥጋ ድህነት ለመለኮት፣ የመለኮት ብልጥግና ለሥጋ እንዲነገር የፈቀደው ትልቁ የትሕትና ትምህርት ቤት ምሥጢረ ሥጋዌ ነው፡፡ ምስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን፣ ኃጢአተኞችንና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው በተዋሕዶ አታምንም ማለት ነው፡፡

የተዋሕዶ ምሥጢር ሲገባህ በቀራጮችና በኃጢአተኞች አታፍርም፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ፡፡


J0IN 👉@linkortodoxe21
+ ስለ እመቤታችን +
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ በምድር ያሉ ችግረኞች ሁሉ የሚኖሩበትን ሀብት የሠጣቸውን የነገሥታትን ጌታ የወለደችው የድሆች ሴት ልጅ ፣ ብዙ ሀብት የጫነች ከአብ ቤት በረከትን ይዛ የምድርን ጉስቁልና ልታስወግድ የመጣች መርከብ ፣ የእናትዋን ሔዋንን ዕዳ የከፈለች ።
ከመዋቲያን መካከል ሆና ሕይወትን የወለደች ሁለተኛ ሔዋን ፣ የወደቀችዋን አሮጊት የረዳቻትና በዕባብ ተነድፋ ከወደቀችበት ያነሣቻት አገልጋይዋ፡፡ ዕርቃኑን ሆኖ በዛፍ መካከል የተሸሸገ ሽማግሌ አባትዋን ልብስ ሰፍታ ያለበሰች ሴት ልጅ
ያለ ጋብቻ ሩካቤ እናት የሆነች ድንግል
በድንግልናዋ የኖረች እናት
ንጉሥ ገብቶ የኖረባት ቤተ መንግሥት
በርዋ ያልተከፈተ ማንም ያልገባባት ቤት
የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡ የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ አለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር?
እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ!
ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤ የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡
... ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት!
ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች፡፡

#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘስሩግ

/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ሆድ አምላክ ይሆናልን ?

💡ጉባኤ፦ ተግሳጽ በመጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ💡

የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል ። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር ። ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው ። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን

የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን ፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው ። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው ። እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው ። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና ። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው ስለሆነ ። ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል ። አንደኛ ከስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም ፤ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው

እንግዲህ እናስተውል ! ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል ። መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ ፤ ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ ፤ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም ። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም ። የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችንን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን ?

ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ። ስለ ፍቅር ትጾማለህ ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ ፤ በፍቅር ብሮሃን ደምቀህ ትነሣለህ ። ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር

ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህ ለዘለዓለም ትኖራለህ እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት እንብለው ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው ፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም

እናም ወዳጄ ሆይ " እለ ከርሦሙ ያመልኩ - ሆዳቸው አምላካቸው ነው " እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ ፫ ፥ ፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ ሰለ በእግዚአብሔር ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም !

ጹመን ከጾመኞቹ ነቢያት ፍጻሜ ከቅዱሳን መላእክት ደስታ ከአማኑኤል ልደት እንድንደር የምድራዊ መልአክ የአቡነ አረጋዊ ጸሎት ይርዳን

አባ ገብረ ኪዳን ( ገብራ ወነባሪሃ ለኪዳነ ምሕረት

💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
"እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ኾይ 🙏
በአካል ሦስት ሲኾን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እርሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን ዓይነ ልቡናዬን ያብራልኝ። 🤲🤲🤲

የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ኾይ 🙏 ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የኹሉ እመቤት ነሽ "

✥መልክአ ኪዳነ ምሕረት✥

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ወዳጄ ሆይ"
በጸሎት የተከፈተ ቀን ብሩህ ነው። በእምነት የሆነ ኑሮ አሳራፊ ነዉ።በፍቅር የሆነ አገልግሎት ድል ነሽ ነው ።በይቅርታ የሆነ ጓደኝነት ዘላቂ ነው ። በመተማመን የሆነ ግንኙነት አርኪ ነዉ። በተስፋ የሆነ ጉዞ የማይደክም ነው ።አንተ ወዳጄ ለበጎ ነገር ጊዜና ጉልበት እንዲሰጥህ ፈጣሪን ለምን

ስትቆም የምትወድቅ ካልመሰለህ ትዕቢት አድሮብሃልና ተጠንቀቅ። ስትወድቅ የምትነሳ ካልመሰለህ ራሱ ሰይጣን አድሮብሃልና ተገሰጽ።

ከተቃራኒ ፆታ ጋር ረጅም ሰአት በገለልተኛ ስፍራ አትቀመጥ ። አእምሮህ ንፁህ ቢሆን እንኳ ለሌላው ፈተና እንዳትሆን፣ ደግሞም ለሰዎች የሐሜት ምክንያት እንዳትሆን ፣ ግንኙነትህን በአደባባይ አድርገዉ። የሚያዳልጡ ስፍራዎች ጎበዞችን ሳይቀር እንደሚጥሉ አትርሳ ።

መልካም ቀን!!!!!!!

join join join
👇👇👇👇👇👇
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🍒💙ድንግል ሆይ 💙🍒

በመሃይምናን ሁሉ አንደበት የስምሽ አጠራር እንደምን ይጥማል ድንግል ሆይ የገናንነትሽ ምስጋና እንዴት ያምራል፡፡ ንጽሕት ርግብ ሆይ ከፀሐይ ከጨረቃ ከከዋክብት ብርሃን ይልቅ የሚያምር የመልክሽ ደም ግባት እንዴት ያማረ የተወደደ ነው፡፡


👉. የምስጋናሽስ ዘፈን ማኅሌት ምን ያህል ይወደድ ለሚሰማው እጅግ ያማረ የተስማማ ነው፡፡ መሰንቆ ለጆሮ እንዲያምር እንዲስማማ የሙሽራ ጌጽ ላይን ማር ላፍ ሽቱ ላፍንጫ የወይን ወለላ ለጉረሮ ጸጅ ለልብ ያማረ የተስማማ እንደ ሆነ፡፡ ውዳሴሽም እንዲሁ ያማረ የተስማማ ነው፡፡


👉. ድንግል ሆይ ክብርሽንና ገናንነትሽን መናገር እጅግ ያማረ እጅግም የተወደደ ነው፡፡ ያበባዋም መልክ የማይጠወልግ የማትደርቅ ንጽሕት ተክል ሆይ የማትጠወልግ የሕይወት እንጨት የእሸቷ ፍሬ የማይረግፍ፡፡


👉. የማትሰበር የክህነት በትር የቅዱስ ምሥጢር አገልጋዮች ካህናቱ የሚመረኮዟት የሚጸጉባት ለምዕመናን ሕንፃ ዘወትር ዝግጁ የሆነች የማትነዋወጽ የሃይማኖት መሠረት፡፡


👉. ብል ነቀዝ የማያበላሻት ሌባ የማይቀርባት ድልብ ማዕበል ሞገድ የማይገፉት መርከብ የውስጧም ዋናተኛ ቀዛፊውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱም በቅዱስ ወንጌሉ ቀዛፊዎች በሐዋርያት ዓለምን ሁሉ ከኃጢአት ማዕበል ሞገድ የሚያሻግር ነው፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏🙏🙏


ወዳጄ ኾይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ። አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልኽ ጠላት አለኽና ነገር ግን ወድቀኽ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ኼዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትኽ ዲያብሎስ ቢያቆስልኽ ማንም አይወቅስኽም መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡

የምትወቀሰው ለቁስልኽ መድኃኒት ማድረግኽን ችላ ያልክ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይኽ ከላይ የነገርኩኽ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይኼዳል ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡

አንተም ከወደቅኽበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትኽ ዲያብሎስን ድል አድርገኽ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡

ስለዚኽ በርታና ተነሥ ዘግይቻለኹ ብለኽ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አኹንም መጀመር ትችላለኽና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

መልካም ዕለተ ሰንበት🙏

💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
1
እንካን ለደስታ አብሳሪው ገናናው መልአክ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ 🙏🙏🙏