መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ከፈተና እንዲያድንህ እግዚአብሔርን መጥራት

"ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም፡፡ ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች» (መዝ. ፲፮ ፥፰-፱)

«እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ፡፡ በአንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ፡፡ በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው:: እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው:: ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።" (መዝ.፻፪ ፥፳፫-፳፰)

‹‹እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጕስቍላሉ፡፡›› (ኤር. ፳፥፲፩)

‹‹አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቁጣው? በልቡ፡፡ አይመራመረኝም ይላልና፡፡ አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቊጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት ድሀ ራሱን ለአንተ ይተዋል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ፡፡" (መዝ. ፲፥ ፲፪-፲፬)

‹‹ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት። ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቈሉም ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይበሉ፡፡ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች። አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል። አቤቱ፥ እንደ ኣንተ ማን ነው? ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።" (መዝ. ፴፭፥፪-፬ ፣ መዝ. ፴፭ ፱-፲)

"አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ:: አቤቱ፥ ድምፄን ስማ ጆሮህ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን፡፡" (መዝ. ፻፳፱ ፥ ፩-፪) "ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም፡፡ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል፡፡" (መዝ. ፻፳ ፥ ፩-፰)

(ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስና ሥራዎቹ - በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ያለነው እንጸናለን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
✞ ያለነው እንጸናለን

ያለነው እንጸናለን /የሔዱት ይመጣሉ/2/2
ከበረቱ ውጪ /ብዙ በጎች አሉ/2/


ቸርነቱን ቀምሰን ምህረቱን አይተናል
ባርነት ሽሮ ልጆቼ ብሎናል
ከዚህ ፍቅር ጌታ ወዴት እንሄዳለን
ግራ ቀኝ አንልም በቤቱ እንፀናለን

አዝ________________

ጠላት እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ቢዘምት
እንሻገራለን ፈተናውን በእምነት
ኃይሉን ያለበሰን ኃይለኛውን አስሮ
ባውሎና በወጀብ ከኛጋር ነው አብሮ

አዝ________________

መንጋውን ሊያበዛ መራራ የጠጣው
ለጠፉት በጎች ነው ኢየሱስ የመጣው
በረቱ እንዲሞላ በፍቅር ይጣራል
ጆሮ ያለው ይሽማ ወዴት ናችሁ ይላል

አዝ________________

ኮብልሎ የሄደው ታናሽህ ሲመለስ
መላእክትን ምሰል ታላቅ ይበልህ ደስ
ይታረድ ፍሪዳው አታጥቁር ፊትህን
ባክኖ እንኮን ቢመጣ ሳመው ወንድምህን

NEW ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?


የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ
ያሳልመናል ይላሉ። ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ
እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ
ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው።
በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን
ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ
ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ
ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት
እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት
በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን።
ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው...
አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦
ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ
ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ
የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ
ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ
ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦
በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል
ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ
መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ
ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያሰቡ ብዙ ግዜ
የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት
እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር
በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን
እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ
በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ
ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል
ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና
ነው
ወንጌል፦
የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ
አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል;
ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው
ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል ፤ ይህም
ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም
አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ
4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን
ናቸው። ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን
የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው
ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል
፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች
ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አያናውጧትም
ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም!
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ
ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንማልዳለን
መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው
ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክቡር አሜን -ይቆየን።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ልጄ ሆይ በራስህ ተሰፋ ልትቆርጥ ትቸላለህ፤
በእግዚአብሔር ግን ፈፅመህ ተሰፋ አትቁረጥ።
መልካም ሥራህ ለንሰሐ ባያበቃህ እንኳን እግዚአብሔር በድንቅ ሥራው ለንሰሐ ሊያበቃህ እንደሚችል ፈፅመህ እመን።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

@linkortodoxe21
✞ ኦ ቅዱስ ሚካኤል

ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል
ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል
ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን
ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)

እረቂቁመላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል
ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል
የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ
እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2)

አዝ__________________

እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት
ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት
ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው
ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)

አዝ__________________

እርህሩነው እና የነፍሳችን ወዳጅ
ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ
ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ
ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2)

አዝ__________________

የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ
በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ
በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ
ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2)


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@linkortodoxe21
-
💡"የልብ ያልሆነ ትሕትና?"💡

🪔ኦርቶዶክሳዊ ስነ ልቦና🪔

ትሕትና የልብ ነው፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግሥት ፣ መንግሥተ ሥላሴን እየሰበክህ ትሑት ልትሆን ይገባሃል፡፡ ትልቁን ትሕትና ነገረ ሥጋዌን እየተናገርህ ትሑት መሆን ያስፈልግሃል፡፡

ተዋሕዶ ማለት ትሕትና ማለት ነው፡፡ ባለጠጋው መለኮት ከድሃው ሥጋ ጋር የተዋሐደበት ማለት ነው፡፡ የሥጋ ድህነት ለመለኮት፣ የመለኮት ብልጥግና ለሥጋ እንዲነገር የፈቀደው ትልቁ የትሕትና ትምህርት ቤት ምሥጢረ ሥጋዌ ነው፡፡ ምስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን፣ ኃጢአተኞችንና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው በተዋሕዶ አታምንም ማለት ነው፡፡

የተዋሕዶ ምሥጢር ሲገባህ በቀራጮችና በኃጢአተኞች አታፍርም፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ፡፡


J0IN 👉@linkortodoxe21
+ ስለ እመቤታችን +
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ በምድር ያሉ ችግረኞች ሁሉ የሚኖሩበትን ሀብት የሠጣቸውን የነገሥታትን ጌታ የወለደችው የድሆች ሴት ልጅ ፣ ብዙ ሀብት የጫነች ከአብ ቤት በረከትን ይዛ የምድርን ጉስቁልና ልታስወግድ የመጣች መርከብ ፣ የእናትዋን ሔዋንን ዕዳ የከፈለች ።
ከመዋቲያን መካከል ሆና ሕይወትን የወለደች ሁለተኛ ሔዋን ፣ የወደቀችዋን አሮጊት የረዳቻትና በዕባብ ተነድፋ ከወደቀችበት ያነሣቻት አገልጋይዋ፡፡ ዕርቃኑን ሆኖ በዛፍ መካከል የተሸሸገ ሽማግሌ አባትዋን ልብስ ሰፍታ ያለበሰች ሴት ልጅ
ያለ ጋብቻ ሩካቤ እናት የሆነች ድንግል
በድንግልናዋ የኖረች እናት
ንጉሥ ገብቶ የኖረባት ቤተ መንግሥት
በርዋ ያልተከፈተ ማንም ያልገባባት ቤት
የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡ የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ አለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር?
እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ!
ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤ የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡
... ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት!
ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች፡፡

#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘስሩግ

/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው/

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ሆድ አምላክ ይሆናልን ?

💡ጉባኤ፦ ተግሳጽ በመጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ💡

የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል ። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር ። ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው ። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን

የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን ፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው ። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው ። እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው ። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና ። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው ስለሆነ ። ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል ። አንደኛ ከስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም ፤ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው

እንግዲህ እናስተውል ! ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል ። መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ ፤ ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ ፤ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም ። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም ። የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችንን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን ?

ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ። ስለ ፍቅር ትጾማለህ ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ ፤ በፍቅር ብሮሃን ደምቀህ ትነሣለህ ። ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር

ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህ ለዘለዓለም ትኖራለህ እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት እንብለው ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው ፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም

እናም ወዳጄ ሆይ " እለ ከርሦሙ ያመልኩ - ሆዳቸው አምላካቸው ነው " እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ ፫ ፥ ፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ ሰለ በእግዚአብሔር ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም !

ጹመን ከጾመኞቹ ነቢያት ፍጻሜ ከቅዱሳን መላእክት ደስታ ከአማኑኤል ልደት እንድንደር የምድራዊ መልአክ የአቡነ አረጋዊ ጸሎት ይርዳን

አባ ገብረ ኪዳን ( ገብራ ወነባሪሃ ለኪዳነ ምሕረት

💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
"እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ኾይ 🙏
በአካል ሦስት ሲኾን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እርሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን ዓይነ ልቡናዬን ያብራልኝ። 🤲🤲🤲

የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ኾይ 🙏 ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የኹሉ እመቤት ነሽ "

✥መልክአ ኪዳነ ምሕረት✥

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21