መንፈሳዊ ህይወት
4.04K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ኪዳነምሕረት ልዩ ነሽ ለእኔ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
👍1
ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና።

ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና።

አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን። (መዝሙር 33፥20-22)

@linkortodoxe21
1
🌹❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው🌹

✥##ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ

✥ገብርኤል ነው✥
የአሸናፊና የኃይል መልአክ

✥ገብርኤል ነው✥
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ

ገብርኤል ነው
አማላጅ ነው ፈጥኖ ደራሽ

"የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን"
❖አሜን❖🙏🙏🙏

👉 @linkortodoxe21
5👍2
አዲሱ አመት ባርክልን

አሮጊ አመት አልፎ አዲሱ ዘመን መጣ
ምድረ በዳው ሁሉ አበባን እንዲያወጣ
ጭጋጉ ዝናብ ዘመኑን ጨርሶ
ርዕሰ አውዳመት መጣ ተመልሶ/2/


በአድይ አበባ ምድሩ ተንቆጥቁጦ
ጨለማው በብርሃን ደምቆ ተለውጦ በወርሃ መስከረም ቅዱስ ዮሐንስ
እንደ ምን ደስ ይላል ጌታ ሲወደስ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርክልን/4/ አዲሱ አመት ባርክልን
አውዳመቱን ባርክልን /2/


/አዝ====


የጠራውን ሰማይ እንድናይፈቀደ አዲስ
ቀን ሊሰጠን እግዚአብሔር ወለደ
በዳዩን ሰውነት ጥለን እንድንመጣ
ለአዲስ ማንነት አዲስ አመት መጣ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል/4/ .............

/አዝ =====


በችቦ ብርሃን ስንሰንቅ ተስፋ ችግርና
ስደት ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ እንዲሰማን
አምላክ ምህረት እንዲመጣ ከወቀልና
ግፍ ከቁጣም እንድንወጣ

አበባ አየሽ ሆይ /4/ ................

/አዝ =====

በዙፋኑ ያለ በዘመን የሚኖር አመትን ሊሰጠን ስለ ድንግል ብሎ ልክ እንደ ዘመኑ ልባችን ይለወጥ በቀኙ እንድንቆም ለፍርድ ሲቀመጥ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን /2/

/አዝ =====

በተሰጠሽ ኪዳን ባንቺ አማላጅነት
ለአስራት ሃገርሽ ይምጣላት ምህረት
የፍቅርን ሸማ ኢትዮጵያ ትልበስ
እርጋታን ያድላት የእግዚአብሔርመንፈስ

ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን


አርቲስት ዘማሪ ይገረም ደጀኔ /አስቴር /
ዘማሪ ዲ/ን ሄኖክ ሞገስ


╔​✞═══●◉❖◉●═════7
@linkortodoxe21
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

ዜማ ቅዱስ ያሬድ
1
#አምላክ_ሆይ_ባርክልን_በዓሉን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

ባርክልን ኧኸ በዓሉን
ለዛሬ ዓመት ኧኸ አድርሰን
ሠላም ፍቅር ኧኸ አድለን
በዕምነታችን ኧኸ አበርታን
በአንድነት ኧኸ አቁመን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

ጽኑ ሠላም ኧኸ ለሐገሪቱ
እንዲጦሩ ኧኸ አዛውንቱ
ወጣቱ እና ኧኸ ሕጻናቱ
ያለ ጊዜ ኧኸ እንዳይሞቱ
አንድም ሳይጎድል ኧኸ በመሃላችን
ለዓመት ያብቃን ኧኸ አምላካችን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

አገልጋዩን ኧኸ ከመቅደሱ
እንዲኖሩ ኧኸ ሲያወድሱ
ታቦቱንም ኧኸ ከመንበሩ
አታናውጠው ኧኸ ከደብሩ
ወታደሩን ኧኸ በድንበሩ
ጠብቅልን ኧኸ በበረከት
ቸሩ ጌታ ኧኸ የፍቅር አባት

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/

ለባርኮ ኧኸ አውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ኧኸ በምሕረት
ያዘነው ኧኸ እንዲጽናና
የተከዘው ኧኸ እንዲል ቀና
በሐገር ውስጥ ኧኸ ውጭም ላለው
በበረከት ኧኸ አትለይው

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/

የናቁሽም ኧኸ ጽዮን ብለው
ይሠግዳሉ ኧኸ ፊትሽ ወድቀው
ካኅናቱ ኧኸ በማሕሌቱ
በቅዳሴው ኧኸ በሠዓታቱ
ከልጅሽ ጋር ኧኸ ከዓለም ጌታ
ዘመሩልሽ ኧኸ በዕልልታ

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/
ባርኪልን ኧኸ /4/


ዘማሪት ፅጌሬዳ ጥላሁን ና
ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
@linkortodoxe21

╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝
ሌሎች የእንቁጣጣሽ መዝሙሮችን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forwarde በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን

​​🌺🌼አበባዮሽ🌺🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(፪)🌼
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን🌻
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ዘመን መጣ ብለን
🌼🌼
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ባልንጀሮቼ - - - ለምለም
ግቡ በተራ - - - ለምለም🌼
በእግዚአብሔር መቅደስ - - - ለምለም
በዚያች ተራራ - - - ለምለም
እንድታደንቁ - - - ለምለም
የአምላክን ሥራ - - - ለምለም
ህይወት ያገኛል - - - ለምለም
እርሱን የጠራ - - - ለምለም

🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼

አበባዮሽ - - - ለምለም (፪)
ክረምት አለፈ - - -ለምለም
ጨለማው ጠፋ- - - ለምለም
የመስቀሉ ቃል - - -ለምለም
ሆነልን ደስታ - - -ለምለም
እናገልግለው - - - ለምለም
ቤቱ ገብተን - - - ለምለም
ትንሽ ትልቁ - - - ለምለም
ተሰልፈን - - - ለምለም🌾

🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼

አበባዮሽ - - -ለምለም(፪)
ያንን ኩነኔ - - - ለምለም
ዘመነ ፍዳ - - - ለምለም
የሞቱ በራፍ - - - ለምለም
ያ ምድረበዳ - - - ለምለም
ልክ አንደ ክረምት - - - ለምለም
ሄደ ተገፎ - - - ለምለም
ፀሐይ ወጣልን - - - ለምለም
ጨለማው አልፎ - - - ለምለም🌼

🌸አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌺

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው መስከረም - - - ለምለም
ይኸው ፀሐይ - - - ለምለም
ንጉሡ ወርዶ - - - ለምለም
ከላይ ሰማይ - - -ለምለም🌼
አውደ ዓመት ሆነ - - - ለምለም
ደስታ ሰላም - - - ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ - - - ለምለም
በአርያም🌿 - - - ለምለም

💐አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌻

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው አበባ - - - ለምለም
ለምለም ቄጤማ🌾 - - - ለምለም
አዲሱ ዘመን - - - ለምለም
አምጥቷልና - - - ለምለም
በሩን ክፈቱ - - - ለምለም
መኳንንቶቹ - - - ለምለም
የክብር ንጉሥ - - - ለምለም
ይግባ ቤታችሁ - - - ለምለም

🌹አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪) 🌼

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ቤታችሁ ይሙላ - - - ለምለም
ሰላም ደስታ - - - ለምለም🌼
ሰጥቷችሁ እርሱ - - - ለምለም
የሁሉ ጌታ - - - ለምለም
ከዘመን ዘመን - - - ለምለም
ያሸጋግራችሁ - - - ለምለም🌺
የሽበትን ዘር - - - ለምለም
ይሸልማችሁ - - - ለምለም

🌼አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ🌼

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ🌼

አብዬ ኧኸ አባብዬ
ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ🌺
ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት
አደረሰዎት ብዬ💐
🌼
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው🌼
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው🌸

መዝሙር
🌺በዘማሪያን🌼
ወርቅነሽ ተፈራና ፅጌሬዳ ጥላሁን

<< በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል >>
መዝ ፷፭፥፲፩🌼

@linkortodoxe21
👍32
​​🌼የእንቁጣጣሽ መዝሙር🌼
🌼🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)ጌቶች አሉ ብለን
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ 🌼 ለምለም አበባዮሽ 🌼 ለምለም
እንቆቅልሽ - - ንግሥት ልትፈትል ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - - ንግሥት እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን - ንግሥት አጫወታቸው - - ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ🌼 ንግሥት እያሳየችው - - ንግሥት
መአዛው የሚሸት - - ከሁለቱ የቱ ነው አለቸው - - ለንጉሥ

ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ(፪)
🌼የአገር አምባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ

እንቆቅልሹ - - የሳባ ከበድም ቢለው - -🌼 የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - - ሰለሞን ቢለው ለሎሌው - -ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ - - ሊቀስሙ🌼 ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ - - መለሠ ለተጠየቀው - - በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - - አለ አልተሠወረው 🌼 በእውነት

🌼አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
🌼 ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (፪)
🌼
ለፈጣሪዋ - - ንግሥት ምስጋና አቅርባ - - ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት ንግስተ ሣባ 🌼 ንግሥት
ጥበቡን አይታ - - ንግሥት አደነቀችው - - ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - - ንግሥት ዕንቁ ሰጠችው - - ንግሥት

ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)🌼🌼
የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (፪)🌼🌼

የኢትዮጵያ ሠዎች - -ለንግሥት ቆሙ በተራ - -ለንግሥት
እደጅ ሆነው 🌼 ለንግሥት ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - - ለንግሥት ሀገር ስትገባ - - ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - - ለንግሥት የፈካ አበባ 🌼ለንግሥት

🌼አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)🌼🌼
🌼ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)🌼🌼

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት ደርሠሽ መጣሽ - - ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - - ንግሥት ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

🌼ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)🌼🌼
🌼ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)🌼🌼

🌼የአባቶች ተስፋ - - ለፃድቃን የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - - ለፀሎት የአሮን በትር - - ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት ይዘሸ የመጣሽ - - ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ ለሀገር መሠረት - በእውነት🌼🌼

🌼 አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)🌼🌼
🌼ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)🌼🌼

በህገ ልቦና - - ህጉን ፈጣሪን አውቀሽ - - ህጉን
ህገ ነቢያትን - - ከዓለም ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን 🌼ለጌታ መስዋዕት አቅርበሽ - - ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን- -በፊት ይዘሽ ተገኘሽ 🌼 በፊት

🌼ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)🌼🌼
🌼ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)🌼🌼


ካለፈው ሰህተት - - ሁላችን እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት - - ለሁሉም መጣ ማቴዎስ- -ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - - በጊዜው ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ - - በጊዜው 🌼 ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት - - በጊዜው ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ - - መጥምቁ ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው🌼🌼

🌼አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)🌼🌼
🌼 ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)🌼🌼

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ 🌼 አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ 🌼እያለች እማማ አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)🌼

🌼አበባ ለምለም 🌼 ቀጤማ ለምለም
🌼ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)🌼

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ🌼
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)
🌼
ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

ከበረው ይቆዩ ከብረው 🌼
አመት አወደ አመት ደርሰው
ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
የፍቅር ሸማን ለብሰው🌼
ንስሐ ገብተው ቆርበው
🌼ከብረው ይቆዩ ከብረው

💚@linkortodoxe21💚
💛@linkortodoxe21💛
@linkortodoxe21
2👍1
✟ዘመንን በዘመን✟

ዘመንን በዘመን እየቀያየረ
ዘልዓለም ይኖራል እንደተከበረ


አበባን በሜዳ በተራራው ላይ
ታፈካቸዋለህ ደምቆ እንዲታይ
ጋራው ሸንተረሩ ውሃን ይጠግባሉ
አረንጓዴ ሆነው ፈክተው ይታያሉ

አዝ_______________

ውኆችን በጸሃይ አትንነህ ከምድር
ዝናብ ትልካለህ ሁሉም ጠግቦ እንዲያድር
ህዝብ እና አሕዛብ ማንንም ሳትለይ
ትመግበናለህ አምላክ ነህ ሁሉን ቻይ

አዝ_______________

ለአፍላጋት ውሃ ለምድር ልምላሜ
ለአረጋውያን ጤና ለህጻናት እድሜ
ሁሉን እያረካህ በቸርነትህ
ምህረትህ ብዛት ታኖረናለህ

አዝ_______________

የሚመስልህ የለም የሚገዳደርህ
ሁሉ ሲያልፍ የማታልፍ ዘልዓለማዊ ነህ
ከማህጸን ጀምሮ እስከ በት ድረስ
ታደርሳለሀ አንተ ዘመንን እያደስክ




እ______ን_______ዘ______ም___ር
@linkortodoxe21
👍1
✟የአዋጅ ነጋሪው ቃል✟


የአዋጅ ነጋሪው ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሄርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሃንስ ካስረዳ
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/


ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሄርን መንግስት እንመስክር ሁላችን
ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሀብታችን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/


ዘማ___________________


ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/


ዘማ-___________________


ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችን አንጻን አደራህን
በክፋ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገደማ
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/

ዘማ-___________________

ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/



እ______ን_______ዘ______ም___ር
@linkortodoxe21
5
​​የእንቁጣጣሽ


እሰይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)ጌቶች አሉ ብለን
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ ለምለም አበባዮሽ ለምለም
እንቆቅልሽ - - ንግሥት ልትፈትል ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - - ንግሥት እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን - ንግሥት አጫወታቸው - - ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ ንግሥት እያሳየችው - - ንግሥት
መአዛው የሚሸት - - ከሁለቱ የቱ ነው አለቸው - - ለንጉሥ

ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ(፪)
የአገር አምባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ

እንቆቅልሹ - - የሳባ ከበድም ቢለው - - የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - - ሰለሞን ቢለው ለሎሌው - -ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ - - ሊቀስሙ ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ - - መለሠ ለተጠየቀው - - በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - - አለ አልተሠወረው በእውነት

አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (፪)

ለፈጣሪዋ - - ንግሥት ምስጋና አቅርባ - - ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት ንግስተ ሣባ ንግሥት
ጥበቡን አይታ - - ንግሥት አደነቀችው - - ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - - ንግሥት ዕንቁ ሰጠችው - - ንግሥት

ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)
የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (፪)

የኢትዮጵያ ሠዎች - -ለንግሥት ቆሙ በተራ - -ለንግሥት
እደጅ ሆነው ለንግሥት ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - - ለንግሥት ሀገር ስትገባ - - ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - - ለንግሥት የፈካ አበባ ለንግሥት

አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)
ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት ደርሠሽ መጣሽ - - ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - - ንግሥት ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)
ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)

የአባቶች ተስፋ - - ለፃድቃን የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - - ለፀሎት የአሮን በትር - - ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት ይዘሸ የመጣሽ - - ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ ለሀገር መሠረት - በእውነት

አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)
ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)
በህገ ልቦና - - ህጉን ፈጣሪን አውቀሽ - - ህጉን
ህገ ነቢያትን - - ከዓለም ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን ለጌታ መስዋዕት አቅርበሽ - - ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን- -በፊት ይዘሽ ተገኘሽ በፊት

ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)
ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)


ካለፈው ሰህተት - - ሁላችን እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት - - ለሁሉም መጣ ማቴዎስ- -ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - - በጊዜው ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ - - በጊዜው ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት - - በጊዜው ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ - - መጥምቁ ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው

አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)
ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ እያለች እማማ አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)

አበባ ለምለም ቀጤማ ለምለም
ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)

ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

ከበረው ይቆዩ ከብረው
አመት አወደ አመት ደርሰው
ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
የፍቅር ሸማን ለብሰው
ንስሐ ገብተው ቆርበው
ከብረው ይቆዩ ከብረው


በማህበረ ፊልጶስ

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
✥ ✢ ╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
👍62
✞ አበባ አየሽ ወይ

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን

ቸርነቱን አይተን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ምህረቱን አይተን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
አበቦችን ይዘን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ቄጤ ማውን ይዘን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን
ቤቶች አሉ ብለን ሆ መጣን ሆ ብለን
እሜቴ አሉ ብለን ሆ መጣን ሆ ብለን
አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

ስላዘጋጀ ለምለም ሰማይ ምድርን ለምለም
ስለቀመረ ለምለም ብርሃናትን ለምለም
እሱ ነውና ለምለም የጊዜ ጌታ ለምለም
እንዘምርለት ለምለም ሆነን በእልልታ ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

ደመናው አልፏል ለምለም ፀሐይ ወታለች ለምለም
መሬት ልምላሜን ለምለም ተጎናጽፋለች ለምለም
አዲሱ ዘመን ለምለም አዲሱ አመት ለምለም
ሰጠን እግዚአብሔር ለምለም በቸርነት ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

የጥፋት ውኃ ለምለም የጎደለ ቀን ለምለም
ለምለሙን አየ ለምለም እርግቧን ልከህ ለምለም
እኛም መተናል ለምለም ቄጤማ ይዘን ለምለም
ሰላም ለናንተ ለምለም ይሁን እያልን ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

የሰውን በደል ለምለም ይቅር እያለ ለምለም
እድሜን ለሰው ልጅ ለምለም እየቀጠለ ለምለም
ዘመንን ሽሮ ለምለም ዘመን የተካ ለምለም
እስከ ንስሀ ለምለም ይታገሠናል ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

ኢትዮጵያ ትብራ ለምለም ትለምልምልን ለምለም
እጇን ዘርግታ ለምለም ወደአምላካችን ለምለም
የ እግዚአብሔር እርሻ ለምለም ይሁን ኤፍራታ ለምለም
እኛም እንጥገብ ለምለም ከበረከቷ ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

ከዘፈን ዓለም ለምለም ከእርኩት ስፍራ ለምለም
ውጡ ከሴኬም ለምለም ከሞት ተራራ ለምለም
ለ እግዚአብሔር ይሁን ለምለም ትንሽ ትልቁ ለምለም
የጌታን ጥሪ ለምለም እንዳትንቁ ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

አመትን ባመት ለምለም ሲተካ ጌታ ለምለም
ታስሮ የኖረው ለምለም ሁሉም ይፈታ ለምለም
ጰራቅሊጦስም ለምለም ይቀድሰን ለምለም
በአዲሱ መንፈስ ለምለም ያመላልሰን ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

አበባ አየሽ ወይ ለምለም/2/

ወደ ንስሐ ለምለ የሚጠራን ለምለም
በራችን ቆሟል ለምለም አዳኛችን ለምለም
እንቀበለው ለምለም በእምነት ሆነን ለምለም
እንዳይመለስ ለምለም እንዳያልፈን ለምለም

አበባ አሮጌው አልፈፏ አዲስ ተክቷል/2/
አበባ ይክበር ይመስገን ይህን አድርጓል /2/

ይሸታል የእጣን ጢስ /2/ ከቤተ-መቅደስ/2/

ከብረው ይቆዩን ከብረው/2/
ልቦና መንፈስ ገዝተው
ቃሉን በትጋት ሰምተው
ሥጋና ደሙን በልተው
የፍቅርን ሸማ ለብሰው
ከብረው ይቆዩን ከብረው


ዘማሪት ፅጌሬዳ ጥላሁን

╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
@linkortodoxe21

╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝
👍54
ዓውደ ዓመት
ዜማ ቅዱስ ያሬድ በቴሌግራም
ዓውደ ዓመት
ዓውደ ዓመት ለባርኮ/2/ዓውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሳሕል

@linkortodoxe21
የአውደ ዓመት ዝማሬዎች 👆👆👆
እንካን አደረሳችሁ😍
@linkortodoxe21
ገና ከገድሉ ቃላት ስንኞች ሲበተኑ የቤልሆር ሰራዊት እንደ እንፋሎት ተነኑ
🥰52