✥ #አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ ✥
✥በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው :- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
✥በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው :-
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
✥ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር:- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
✥ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል::
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
✥"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ"
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
✥የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን✥
@linkortodoxe21

መጋቤ ሀዲስ እሽቱ አለማየሁ
ቁንጅና ለትዳር ዋስትና አይሆንም!
መታመም ማለት ትሞታለህ ማለት አይደለም!
ሃብታም መሆን የጥሩ እድል ትርጉም አይደለም!
ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር የድሎት ምንጭ አይሆንም!
ጥሩ መኪና መንዳት ለምትደርስበት ቦታ ዋስትና
አይሰጥህም !
ለቤተሰብህ ዶክተር ብትቀጥር ቋሚ የጤና ዋስትና አይኖርህም!
ብዙ መማር ጥበበኛ አያደርግህም!
ሃብታም ማግባት ለደስተኛ ለህይወት ማረጋገጫ አይሆንም!
ክርክር ማሸነፍ ትክክል መሆን አይደለም !
***
ገነት የማያሸልም ምንም ነገር ብትሰራ ጊዜያዊ እና
ውሸት ነው ። ያለ አምላክ የሚራመድ ሰው በድን
ነው፣አንተ በራስህ ላይ ስልጣን የለህም
አንተ ሰውነትህን ታያለህ እሱ ደምስርህን ያያል ። ሁሉም
ነገር ለርሱ ይቻላል በሁሉም ነገር ውስጥ አምላክህን ጣልቃ አስገባ።

ከእለታት በአንድ ቀን ድህነት ያንገላታው አንድ ሰው ሚስቱንና ሁለት ልጆቹን ትቶ ወደ ሩቅ ሀገር ለሥራ ይሄዳል እዛም ለ10 ዓመታት ከሠራ በኋላ 2500ብር ብቻ አግኝቶ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ መንገድ ይጀምራል።
ሲጓዝም አንድ መነኩሴ መንገድ ላይ ያገኙትና " ልጄ የያዝከውን ብር ስጠኝና በህይወትህ እጅግ የሚጠቅሙህን 3 ምክሮች ልስጥህ ይሉታል። ምንም ሳያንገራግር ብሩን ሰጣቸው።
መነኩሴውም:-
፩. አቋራጭ ነው ብለህ በአቋራጭ አትሂድ
፪. በማያገባህ አትግባህ
፫. ለውሳኔ አትቸኩል
ብለው ምክር ለግሰውት ይሰናበቱታል።
ይህ ሰው ሲጓዝ ቆይቶ መንገድ የሚጓዙ ነጋዴዎችን ይቀላቀላል እነሱም " በዚህ በኩል የሚወስድ አቋራጭ መንገድ አለ" እንሂድ ወደ ከተማው በፍጥነት ያደርሰናል ይሉታል ...እሱም በአቋራጭ አትሂድ የተባለው ትዝ አለውና "የለም እኔ በዚህ በቀጥታው እሄዳለሁ" ብሎ ከነሱ ተለይቶ ሄደ.....ተጉዞ ከተማው ሲደርስ የከተሜው ሰው ሁሉ "ዛሬ ጠዋት በአቋራጭ ሲሄዱ የነበሩ ነጋዴዎች በሽፍቶች ተገድለው ተገኙ" ብለው ሲያወሩ እጆሮው ገባ። በጣም ተገረመ ቀኑም ስለመሸ በቆመበት አካባቢ የሚያልፍ አንድን ሰው ጠጋ ብሎ" እባክህን ወደ ሃገሬ እየሄድኩ ስለመሸብኝ የማድርበትን ቤት ብትጠቁመኝ ብዬ ነው ይለዋል።
ያም መንገደኛ በእጁ ወደ አንድ ቤት እየጠቆመ "እዛ ቤት ሂድና ጠይቃቸው ነገር ግን ከገባህ ተመልሰህ አትወጣም ይለዋል" በንግግሩ ግራ ቢጋባም ውጭ ከማደር ብሎ የተጠቆመውን በር አንኳኳ....እጅግ መልከ መልካም የሆነ ሰው ይከፍትለታል ማደርያም እንደሚፈልግ ይነግረውና ያስገባዋል....መልከ መልካሙም ወጣት ወደ ቤቱ ያስገባውና ሚስቱን ያሳየዋል .....እጅግም መልከ ጥፉ ነበረች ....እንግዳውም" እንዴት ይሄ እንዴት ይሆናል.......ብሎ ሊናገር ያስብና #በማያገባህ #አትግባ የተባለው ትዝ አለውና ዝም አለ.....በነጋታውም ያ መልከ መልካም ወጣት እንግዳውን ወደ ጓሮ ወስዶ ብዙ የራስ ቅሎች ያሳየውና........አየህ ወንድሜ እኝህ ሁሉ ስለሚስቴ መልክ በማያገባቸው ገብተው የገደልኳቸው ናቸው.....አንተ ግን ምንም ስላላልክ የሃብቴን እኩሌታ እሰጥሃለሁ ብሎ ሰጥቶ አመስግኖ ይሸኘዋል።
እንግዳውም የተሰጠውን ስጦታ ይዞ ለቤተሰቦቹ ለመንገር እየተቻኮለ በሩን ከፍቶ ሲገባ ባለቤቱ ከሁለት ጎረምሶች መሃል ተኝታ ያገኛታል።
እጅግም በመናደድ ወደ ጓዳ ገብቶ መጥረቢያ አንስቶ ወደ መንታ ክፍል እየተንደረደረ ሲገባ እኛ መነኩሴ #ለውሳኔ #አትቸኩል ያሉት ትዝ አለው።
ራሱንም አረጋግቶ እስኪነሱ ይጠብቃል..
ባለቤቱም ከእንቅልፏ ስትነቃ የናፈቃት ባሏን ስላየች እጅጉን ደስ እያላት ጥምጥም ብላ አቀፈችው......በል ሁለቱ ልጆችህን እቀፍና ሳማቸው አለችው።
(ለካ ጥሏቸው የሄደው ትናንሽ ልጆቹ አድገው ነው)
የአባቶች ምክር ነፍስን ያለመልማል

ታስበላብሃለች
አንድ እምነት የነበረው እረኛ ነበረ ይባላል፡፡ ምሳ ለመብላት ሲፈልግ ያሰማራቸውን በጎች ለቅዱሳን፣ ለመላእክት አደራ ሰጥቶ ይሔዳል፡፡
"ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! እነዚህን በጎቼ ከተኩላ ጠብቅልኝ" ብሎት ይሔዳል፡፡ እንደ እምነቱም በጎቹ ተጠብቀዉለት ያገኛቸዋል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ "ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! አንተ ጠብቅልኝ" ይሏል፡፡ እንዲህ በቅዱሳን እያስጠበቀ ምሳውን በልቶ ይመጣል፡፡
አንድ ቀን፦ "እመበቴ ሆይ! ዛሬ አንቺ ጠብቂልኝ" ብሎ ወደ ቤቱ ይሔዳል፡፡ አባቱ አገኙትና፦ "ዛሬ ለማን አስጠብቀህ መጣህ?" አሉት፡፡ "ለእመቤታችን አስጠብቄ መጣሁ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም፦ "አዬ ልጄ! እርሷ'ማ ታስበላብሃለች" አሉት፡፡ "ለምን? ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ መላእክት የጠበቁትን እርሷ አትጠብቅምን?" ይላቸዋል፡፡ "አይ ልጄ! የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፡ የተራበ አውሬ መጥቶ ቢበላ ትከለክለዋለችን? ታስበላብሃለች" ሲሉት "እውነትም" ብሎ ወደ መንጎቹ ሮጠ ይባላል፡፡
ርህርህተ ሕሊና ሆይ! ዘወትር በምልጃሽ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን፡፡ አሜን!!!
❤❤❤@linkortodoxe21❤

አንድ መነኩሴ ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ቀርቦ በምሬት እንዲህ አለ :-
"አባቴ በዚህ ገዳም ምንም ጸጋ ምንም ትሩፋት የሌለኝ መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ:: አባ እገሌን እዩት እንደ እርሱ የዋህ የለም! አባ እገሌን እዩአቸው እንደርሳቸው ታጋሽ ማን አለ? አባ እገሌን እዩአቸው ለሁሉ ፍቅር አላቸው!
እኔ ግን ምንም የለኝም አልረባም አባቴ እባክዎ ይጸልዩልኝ የእኔ ጸጋ የእኔ ፍሬ ምንድር ነው?" አለ እያለቀሰ::
አበምኔቱም አይዞህ ጸልይ ብለው አሰናበቱት::
እሱ ከወጣ በኁዋላ ግን አብረዋቸው ላሉት መነኮሳት እንዲህ አሉ :-
"ይህ መነኩሴ በዚህ ገዳም ካሉ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ ተሠጥቶታል:: የወንድሞቹ ኃጢአት አይታየውም
ጽድቃቸውን ግን በትሕትና ሲቆጥር ይውላል:: ከዚህ በላይ ምን ጸጋ አለ? ዝም ያልኩት ይህንን ብነግረው ክብሩን አሳንስበታለሁ ብዬ ነው" አሉ::
"ነፍሳችሁን ተመልከቱ የወንድማችሁንም ኃጢአት አትመልከቱ እግዚአብሔር ያያል" ቅዳሴ እግዚእ
ከዲያቆን ሄኖክ ኃይለ ትምህርቶች የተውሰደ
@linkortodoxe21👈

Forwarded from LikeBot
በዓታ ለማርያም (ታህሳስ 3)
በዚህች ቀን ቅድስት እናታችን ራሱዋን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ የብሉዩዋ ቤተመቅደስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ልትተካ መቃረቡዋን ለማብሠር ወደ ቤተ መቅደስ ያመራችበት ቀን ነው፡፡ ጌታችንም ከእርሱዋ የነሳውን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ የራሱ ቤተመቅደስ በማድረግና እኛንም በጥምቀት የአካሉ ሕዋሳት እንድንሆን በማብቃት ሥጋችንን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ቤተመቅደስ መግባት ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር ቃል ከእርሱዋ በሥጋ በመወለዱ ያገኘነውን ድኅነትና ብዙ ጸጋዎችን እናስባለን፡፡ አሁን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከእርሱዋ የተወለደውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለብሰነዋል፤ (ገላ.3፥27) ከእርሱዋ በነሣው ተፈጥሮ በኩል ሞትን በመስቀሉ ገድሎ ሲያስወግደው፣ እኛም በጥምቀት ከእርሱ ሞት ጋር በመተባበራችን ሞትን ድል የምንነሣበትን ኃይልን ታጥቀናል፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋ ሠርተንበትና አብዝተነው ብንገኝ ከትንሣኤው ተካፋዮች መሆንን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመልን እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ ምክንያት ነው፡፡
ቅድስት ድንግል ማርያም ብሉይን ከአዲስ ያገኛኘች መንፈሳዊት ድልድይ ናት፡፡ በብሉይ ያሉት ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን ካለነው ጋር አንድ ማኅበር የፈጠሩትና ከቅዱሳን መላእክትም ጋር እርቅ የወረደው ከእርሱዋ በነሳው ሰውነት በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም” (ኤፌ.2፥19) ብሎ አስተማረ፡፡ ራሷን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ እኛንም በልጁዋ በኩል የመንፈሱ ቤተ መቅደስ እንድንሆን ምክንያት ሆናልናለችና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት ለእኛ ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም አለው፤ ስለዚህም ይህቺን እለት በታላቅ ድምቀት እናከብራታለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን!
Share share

"ከራሳቸው ውጪ ደስታን የሚፈልጉ እንደምን ምስኪኖች ናቸው? ደስታን በባእድ ምድር በጉዞ የሚፈልጉ አሉ። በሀብትና በዝና መካከል የሚፈልጉ ወገኖች አሉ፤ በታላቅ ይዞታና በንብረት መካከል የሚፈልጉ አሉ፤ መራራ ፍፃሜ ባላቸው በውበትና በተቃራኒ ፆታ መካከል የሚፈልጉ አሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ ደስታን ከራሳችን ውጪ ለመገንባት መሞከር በተደጋጋሚ በመሬት ርእደት በሚናወጥ ሥፍራ ላይ እንደ መገንባት ነው።
ደስታ የሚገኘው በእኛው ውስጥ እንጂ ከእኛ ውጪ አይደለም። ምስጉን ማለት ይህን ሁኔታ የተገነዘበ ሰው ነው። ደስታ ማለት የልብ ንፅህና ነው፤ እንዲህ አይነቱን ልብ እግዚአብሔር ማደሪያ ያደርገዋልና። ስለዚህ ንፁህ ልብ ያላቸው ወገኖች ክርስቶስ እንዲህ ይላቸዋል፦ በእነሱ እኖራለሁ፣ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸው እሆናለሁ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 2ኛ ቆሮ. 6፥16 እንዲህ አይነት ወገኖች ምን ይጎድልባቸዋል? ምንም። "
(አባ ሳራባሙን - የበረሃ ፈርጦች መጽሐፍ ገጽ 14 በመምህር ምትኩ አበራ)

#መጽሐፍ_ቅዱስ_ሥዕላትን_ይፈቅዳልን ?
🖋 በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
★ ጽሑፉን ካነበቡ በኋላ #Forward & #Pin በማድረግ ለሌሎችም እናሳውቅ!!!
💠 በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን ፣ የድንግል ማርያም ፣ የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ ፣ መብራት ሲያበሩ ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ደግሞ ‹ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!› ‹‹በላይ በሰማይ ካለው ፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም›› ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ ፳፥ ፬)
💠 በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም ፣ በምድርም ፣ ከምድርም በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን ፣ በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ ለመሳል እንዴት ደፈረች? እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት? የሚለው ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡
💠 በቀጥታ ወደ ምላሹ ከመግባታችን በፊት ከዚያው ከኦሪት ዘጸአት ሳንወጣ ጥቂት ምዕራፎችን እንሻገርና እናንብብ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ … አንደኛውን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ ሥራ … ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘርጉ ፤ የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ ፤ ፊታቸውም እርስ በእርሱ ይተያያል … እኔም በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አነጋግርሃለሁ›› (ዘጸ ፳፭፥ ፲፰-፳፪)
💠 ልብ አድርጉ ፤ ከአምስት ምዕራፎች በፊት ‹ከሰማይ ፣ ከምድርና ከባሕር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› ብሎ ለሙሴ ያዘዘው እግዚአብሔር አሁን ደግሞ በሰማይ ካሉ መላእክት መካከል የሆኑትን የኪሩቤልን ሁለት ምስል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ፣ ክንፎቻቸውን እንዲዘረጉና እንደሚናተፍ ዶሮ እንዲተያዩ አድርጋቸው ፣ እኔም በእነርሱ መካከል አነጋግርሃለሁ አለው፡፡
💠 ከዘጸአት ሳንወጣ እግዚአብሔር አሁንም ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ አድርግ ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ›› በማለት ከወርቅ ከተቀረጹት ሁለት ኪሩቤል በተጨማሪ በመጋረጃ ላይ በጥልፍ መልክ ኪሩቤል እንዲሣሉ አዘዘው፡፡ (ዘጸ ፳፮፥ ፴- ፴፩) እግዚአብሔር በሰማይ ካሉት የማንንም ምሳሌ አታድርግ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ራሱ የሚጥስ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን? ኪሩቤል ‹በሰማይ ካለው ማናቸውም ነገር› ውስጥ አይደሉምን? የተቀጠቀጠ ወርቅስ የተቀረጸ ምስል አይደለምን? ይህን ጥያቄ እንደ ዋዛ መተው እንዴት ይቻላል?
💠 መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘጸአት ብቻ ቢሆን ሁለት ማስረጃ ጠቅሰን እንተወው ነበር፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር ‹‹እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሠጠው›› ተብሎ የተነገረለት ጠቢቡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ሲፈጽም ይህንን አደረገ፦ ‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሌላኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ… ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው›› ይላል፡፡ (፩ኛ ነገ ፮፥ ፳፫- ፳፰)
💠 ጠቢቡ በዚህ አልበቃውም ፤ የቤተ መቅደሱን ግንብ ዙሪያውን ባዶ እንዲሆን አልተወውም ‹‹በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ›› ይላል፡፡ (፩ኛ ነገ ፮፥ ፳፱) በአጭሩ ጠቢቡ ሰሎሞን እንደ ሙሴ በመጠን ያነሡ ሳይሆኑ ዐሥር ክንድ የሚረዝሙ ኪሩቤልን ከወይራ ሠርቶ በወርቅ ሲለብጥ ከምድርም አበባና ዘንባባን በቤተ መቅደሱ ምስል አድርጎ ቀረጸ፡፡
★ ‹የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡ ሕጉ የሚጠናቀቅበት ‹አትስገድላቸው አታምልካቸውም› የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የከለከላቸው የተቀረጹ ምስሎች አምላኬ ነህ ተብለው ለፈጣሪ የሚገባ የአምልኮ ስግደት የሚሰገድላቸው ጣዖታትን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ለማንኛውም በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከሰማይ ከምድር ከባሕር ያሉ ፍጥረታትን በምስል ቀርጾ አምላኬ አንተ ነህ ብሎ እንዳይሰግድ የተከለከለው ክልከላ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላእክት መቅረጽ አይገባም ለማለት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የተሳሳተ መሆኑን ራሱ ባለቤቱ ሕጉን ከሠራ በኋላ በዚያው ዘመን የመላእክቱን ሥዕልና ቅርጽ በማሠራት አሳይቶናል፡፡
💠 እዚህ ላይ አንድ ነገር እናስተውል ፤ ከላይ ባየናቸው የቤተ መቅደሱ ውስጥ ሥዕላት በተደጋጋሚ የተሣሉት መላእክት ብቻ ከመላእክትም ኪሩቤል ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደምናየው ከሙሴ በፊት የነበሩ እንደ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላቸው በቤተ መቅደሱ ለምን አልተሣለም? ምናልባት ለቅዱሳን ሰዎች ሥዕል አይገባ ይሆን? ያሰኛል፡፡
💠 አይደለም፤ እንደሚታወቀው ቤተ መቅደሱ የሰማያት ምሳሌ ሲሆን በሰማያት በልዕልና የሚኖር አምላክ ከሕዝቡ መካከል በረድኤት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ያሉት ነገሮች ሁሉም በሰማያት በእግዚአብሔር መንግሥትና ከእግዚአብሔር ጋር ያሉትን ነገሮች የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ ወደ ሲኦል በወረዱበት በዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእግዚአብሔር ረድኤት ርቀው በሞት ጥላ መካከል ናቸውና የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ በሆነው መቅደስ ውስጥ አልተሣሉም፡፡ በዚያ ቤተ መቅደስ የተሣሉት መላእክት ከመላእክትም ለታቦቱ ዙፋንነት ምሥጢር የሚቀርቡት በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋኑን የሚሸከሙት ኪሩቤል ናቸው፡፡

✝መንፈሳዊ ህይወት✝ via @like
🕯``ማንኛውም ሰው በዚህ ምድር ሲኖር ከሁለት አንዱን መምረጥ ይኖርበታል ክርስቶስን የሚወድ ወይም ክርስቶስን የሚዋን መሆን ከዚህ ውጪ ምርጫ እድል ፈንታም የለም፡፡"!🕯
💡የነግህ[የጠዋት] ዳቤ💡
💡የነግህ[የጠዋት] ዳቤ💡
#አደራ_አለብኝ
#ብርሃን_ይሆናል ስል
ቢውጠኝ ጨለማ
ለምለም መስክ ስፈልግ
#ቢገጥመኝ_ባድማ
ፍቅር አንድነት ስሻ
መለያየት ሆኖ
ሰላሜን ብቀማ
ለሌላም አይደለም
#ቅድስት_ተዋህዶ !
ላንቺ ነው ለእማማ
ጴጥሮስ የቁልቁሊት
ለእምነቱ ተሰቅሎ
ደግሞም እስጢፋኖስ
በድንጋይ ተወግሮ
ሳትነዋወጪ እንዳለሽ ጠብቀው
አንቺን ያስረከቡኝ
#እኔስ_አልተውሽም
አደራ አለብኝ 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
#ብርሃን_ይሆናል ስል
ቢውጠኝ ጨለማ
ለምለም መስክ ስፈልግ
#ቢገጥመኝ_ባድማ
ፍቅር አንድነት ስሻ
መለያየት ሆኖ
ሰላሜን ብቀማ
ለሌላም አይደለም
#ቅድስት_ተዋህዶ !
ላንቺ ነው ለእማማ
ጴጥሮስ የቁልቁሊት
ለእምነቱ ተሰቅሎ
ደግሞም እስጢፋኖስ
በድንጋይ ተወግሮ
ሳትነዋወጪ እንዳለሽ ጠብቀው
አንቺን ያስረከቡኝ
#እኔስ_አልተውሽም
አደራ አለብኝ 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
#ዐረገች
ከሰማዮች ይልቅ
#ውብ_ሰማይ ነበረች፣
የጨለማውን ሊቅ
#ድቅድቅ_የሰበረች፣
እውነተኛ ፀሐይ #ከርሷ_ቢፈነጥቅ
ብርሃን ያበሰረች ::
እርሷ ያወጣችው
አማናዊ ፀሐይ፣
እንዳገዘፈችው
ኑሮ በምድር ላይ፣
#ሞቶ_ተነሣና
ከፍ ብሎ ቢያርግ
ቢሔድ ወደ ሰማይ፣
#እርሷም_ሞተችና
ፀሐዩአን ልትፈልግ
#ተነሣች_ወደ_ላይ፣
ዐረገች ወደ ላይ
ብርሃን ልጇን ልታይ :: 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
ከሰማዮች ይልቅ
#ውብ_ሰማይ ነበረች፣
የጨለማውን ሊቅ
#ድቅድቅ_የሰበረች፣
እውነተኛ ፀሐይ #ከርሷ_ቢፈነጥቅ
ብርሃን ያበሰረች ::
እርሷ ያወጣችው
አማናዊ ፀሐይ፣
እንዳገዘፈችው
ኑሮ በምድር ላይ፣
#ሞቶ_ተነሣና
ከፍ ብሎ ቢያርግ
ቢሔድ ወደ ሰማይ፣
#እርሷም_ሞተችና
ፀሐዩአን ልትፈልግ
#ተነሣች_ወደ_ላይ፣
ዐረገች ወደ ላይ
ብርሃን ልጇን ልታይ :: 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
#ጠብቂኝ_እመቤቴ
#የምህረት_ቃልኪዳን አምላክ የሰጠሽ
#የአማኑኤል_እናት መጽናኛዬ ነሽ ፤
ምንም ተስፋ የለኝ #ባንቺ_ነው_እምነቴ
አማልጅኝ ከልጅሽ #ክብረት_እመቤቴ ::
ሕይወቴ ጎስቁሎ በነፍሴ ብዝልም ፤
በምልጃሽ ታምኜ በኪዳንሽ ልቁም ::
#ስምሽን_እየጠራሁ እጽናናለሁኝ ፤
#ስሞት_እንዳልጠፋ ድንግል ጠቢቂኝ ::
ደሃ ምስኪን ሆኜ ለሰዎች ብታይም ፤
ሞልቶ የተረፈ ጥሪት ባይኖረኝም ፤
ስምሽን ብጠራ #ምንም_አይጨንቀኝም
አንቺ ካለሽልኝ #ኑሮዬ_ሙሉ_ነው ፤
አፍሮ አያውቅምና #የተማጽነሽ_ሰው ::
እኔን የሚረዳኝ በአገር ስቸገር
#ዘመድ_ጠያቂ_የለኝ_ፍጽም_ካንቺ_በቀር
ከውጭም ስገባ ከቤትም ብወጣ
ነፍሴ እንድትቀደስ ከርኩስነት አምልጣ
#ጠብቂኝ_እመቤቴ ከዘመኑ ቁጣ 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#የምህረት_ቃልኪዳን አምላክ የሰጠሽ
#የአማኑኤል_እናት መጽናኛዬ ነሽ ፤
ምንም ተስፋ የለኝ #ባንቺ_ነው_እምነቴ
አማልጅኝ ከልጅሽ #ክብረት_እመቤቴ ::
ሕይወቴ ጎስቁሎ በነፍሴ ብዝልም ፤
በምልጃሽ ታምኜ በኪዳንሽ ልቁም ::
#ስምሽን_እየጠራሁ እጽናናለሁኝ ፤
#ስሞት_እንዳልጠፋ ድንግል ጠቢቂኝ ::
ደሃ ምስኪን ሆኜ ለሰዎች ብታይም ፤
ሞልቶ የተረፈ ጥሪት ባይኖረኝም ፤
ስምሽን ብጠራ #ምንም_አይጨንቀኝም
አንቺ ካለሽልኝ #ኑሮዬ_ሙሉ_ነው ፤
አፍሮ አያውቅምና #የተማጽነሽ_ሰው ::
እኔን የሚረዳኝ በአገር ስቸገር
#ዘመድ_ጠያቂ_የለኝ_ፍጽም_ካንቺ_በቀር
ከውጭም ስገባ ከቤትም ብወጣ
ነፍሴ እንድትቀደስ ከርኩስነት አምልጣ
#ጠብቂኝ_እመቤቴ ከዘመኑ ቁጣ 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#ጥንቅር_ብለህ_ቅር
ጥንቅር ብለህ ቅር
ድንገት ተቀራርበን ብትገባ ከልቤ
በሄድኩበት ሁሉ አንተን በማሰቤ
እንድትረዳኝ ማፍቀሬን ብነግርህ
ላንተ ያለኝን ፍቅር ገልጬ ባሳይህ
እኔን በማባበል ማፍቀርሽልህን ነግረህ
እንደምታፈቅረኝ በቃላት አስውበህ
ደጋግመህ ደጋግመህ
#ደጋግመህ ብትነግረኝ
የማደርገው ሳጣ ደስታው ሲያናውጠኝ
ትንሽ እንደቆየህ ደስታዬን አይተህ
ካንት ጋር ለመኖር መስፈርቱን አወጣህ
ማህተብ እንድበጥስ ማርያምን እንድክድ
ተዋህዶን እንድተው ጌታዬን እንዳልወድ
ይህን ካላደረኩ አብረን እንደማንኖር
እየነካካህኝ ቃላት በመደርደር
ለምስኪኑ አፍቃሪህ ደፍረህ ተናገረህኝ
መጨነቄን አይተህ ለዘብ አረክህልኝ
አንትም በሀይማኖትህ
#እኔም በሀይማኖቴ
መኖር እንደምንችል ገብተህም ከቤቴ
የሃይማኖቱ ጉዳይ ሁኖ እንዳስብበት
አሳይመንት ሰጠህኝ እኔም አሰብኩበት
እውነቱን ልገርህ
በልቤ ያለውን በአንደበቴ ላውጣው
አንትን በማፍቀሬ እንዲህ ስህተት ሰራሁ
እኔ ላንተ አልሆንም አንተ ደግሞ ለእኔ
አያገናኘንም ተዋህዶ መሆኔ
ግን እንዴት ደፈርከኝ እንዴትስ አሰብክው
በየቱስ አዕምሮ ይህን አብላላሀው
ከአምላኬ በላይ እማፈቅርህ መሰለህ ?
ከእናቴ ከማርያምስ በምን ላስበልጥህ
ወይስ ከማህተቤ እንዴት ላወዳድርህ
አትሳሳት ወንድሜ ፍፁም አልሰማህም
የምትለኝ ሀሳብ ለኔ አይስማማኝም
አንተም በሀይማኖት እኔም በሀይማኖት
ባለንበት እንኑር ሆነን ወንድምና እህት
ደግሞም ተረዳልኝ
#ይሄን እወቅልኝ
ተዋህዶን አስትተህ እኔን ከምትቀርብ
አትምጣ ይቅርብኝ ጥንቅር ብለህ ቅር
ደግሜ እለዋለው ጥንቅር ብለህ ቅር 🙏
#ማፍቀር_ስትጀምር
#ከእምነትህ_ጀምር
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ጥንቅር ብለህ ቅር
ድንገት ተቀራርበን ብትገባ ከልቤ
በሄድኩበት ሁሉ አንተን በማሰቤ
እንድትረዳኝ ማፍቀሬን ብነግርህ
ላንተ ያለኝን ፍቅር ገልጬ ባሳይህ
እኔን በማባበል ማፍቀርሽልህን ነግረህ
እንደምታፈቅረኝ በቃላት አስውበህ
ደጋግመህ ደጋግመህ
#ደጋግመህ ብትነግረኝ
የማደርገው ሳጣ ደስታው ሲያናውጠኝ
ትንሽ እንደቆየህ ደስታዬን አይተህ
ካንት ጋር ለመኖር መስፈርቱን አወጣህ
ማህተብ እንድበጥስ ማርያምን እንድክድ
ተዋህዶን እንድተው ጌታዬን እንዳልወድ
ይህን ካላደረኩ አብረን እንደማንኖር
እየነካካህኝ ቃላት በመደርደር
ለምስኪኑ አፍቃሪህ ደፍረህ ተናገረህኝ
መጨነቄን አይተህ ለዘብ አረክህልኝ
አንትም በሀይማኖትህ
#እኔም በሀይማኖቴ
መኖር እንደምንችል ገብተህም ከቤቴ
የሃይማኖቱ ጉዳይ ሁኖ እንዳስብበት
አሳይመንት ሰጠህኝ እኔም አሰብኩበት
እውነቱን ልገርህ
በልቤ ያለውን በአንደበቴ ላውጣው
አንትን በማፍቀሬ እንዲህ ስህተት ሰራሁ
እኔ ላንተ አልሆንም አንተ ደግሞ ለእኔ
አያገናኘንም ተዋህዶ መሆኔ
ግን እንዴት ደፈርከኝ እንዴትስ አሰብክው
በየቱስ አዕምሮ ይህን አብላላሀው
ከአምላኬ በላይ እማፈቅርህ መሰለህ ?
ከእናቴ ከማርያምስ በምን ላስበልጥህ
ወይስ ከማህተቤ እንዴት ላወዳድርህ
አትሳሳት ወንድሜ ፍፁም አልሰማህም
የምትለኝ ሀሳብ ለኔ አይስማማኝም
አንተም በሀይማኖት እኔም በሀይማኖት
ባለንበት እንኑር ሆነን ወንድምና እህት
ደግሞም ተረዳልኝ
#ይሄን እወቅልኝ
ተዋህዶን አስትተህ እኔን ከምትቀርብ
አትምጣ ይቅርብኝ ጥንቅር ብለህ ቅር
ደግሜ እለዋለው ጥንቅር ብለህ ቅር 🙏
#ማፍቀር_ስትጀምር
#ከእምነትህ_ጀምር
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ስላሴን አመስግኑ
♻️#ሥላሴን_አመስግኑ♻️
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ስላሴን አመስግኑ /2/
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
🔆አዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይድረሰው ከጠዋት እስከማታ
🔆አ.ዝ
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ ስሉስ ቅዱስ ያሉት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሃለን
🔆አዝ
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ስላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና
ሁሌም ይመሩኛል በህይወት ጎዳና
@dnzema
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ስላሴን አመስግኑ /2/
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
🔆አዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይድረሰው ከጠዋት እስከማታ
🔆አ.ዝ
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ ስሉስ ቅዱስ ያሉት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሃለን
🔆አዝ
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ስላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና
ሁሌም ይመሩኛል በህይወት ጎዳና
@dnzema
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
ይህ ✝የህይወት መንገድ✝ የተሰኘ ቴሌግራም ቻናላችን
👉ምክሮችና የአባቶች ተግሳጾች
👉የተለያዩ የህይወት ትምህርቶች
👉የህይወት ችግሮችና መፍትሄዎች
👉መንፈሳዊ ግጥሞች
👉መንፈሳዊ ታሪኮች
👉የቮይስ ትምህርቶች
👉የቪድዮ ትምህርቶች
👉እለታዊ የብሩክ ንጋት ብሩህ ቀን መርሃግብሮች 👉መንፈሳዊ መዝሙሮችና የተለያዩ🔵መንፈሳዊ🔵 አገልግሎቶችን ያቀርባል።የአገልግሎቶቻችን ተካፋይ ለመሆን ይህንን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
@yehywetmenged
@yehywetmenged
@yehywetmenged
የዚህ ቻናል #እህት የሆነውን ✝ህይወት ቲዩብ✝የተሰኘውን ብዙ አገልግሎቶችን የምናቀርብበትን ቻናል ይመልከቱ።ከወደዱትም❤️ሰብስክራይብ❤️ በማድረግ ቤተሰባaችን ይሁኑ።
youtube.com/c/hiwottube

... ብቻ አንተ በርታ፣ አይዞህ፣
መሥራት ያለብህን ነገር ሥራ፤
በርትተህ ተጋደል፣
. ለእግዚአብሔር ብለህ ከምታደርጋቸው መልካም ነገሮች አንዳቸውም እንኳን፣ እንዲሁ አይጠፋብህም፥ ያለ ዋጋ አይቀሩብህም።
. እያንዳንዱ ጸሎትኽ፣
የምትዘምረው እያንዳንዱ ዝማሬኽ ይመዘገባል፣
. እያንዳንዱ ምጽዋትኽ፣ እያንዳንዱ ጾምኽ ይመዘገባል፣
. እያንዳንዱ በአግባቡ የተከበረ እና የተጠበቀ ትዳር ይመዘገባል።
. ስለ እግዚአብሔር ተብሎ የተኖረ እና የተጠበቀ ንጽሕና ይመዘገል።
. ኾኖም በመዝገቡ ውስጥ ቀዳሚው(የመጀመሪያው) አክሊል ለድንግልና እና ለንጽሕና ነው፤ እንዲህ የምትኖር ከኾነ እንደ መልአክ ልታበራ ይገባሃል።
. ነገር ግን መልካም የኾነውን ዜና ደስ ብሎኽ እንደሰማኽ፣ ከዚኽ ተቃራኒ የኾነዉንም ነገር ሳትሸማቀቅ እና ሳትደናገጥ ስማ!!
. እንያንዳንዱ የቅንዓት እና የምቀኝነት ሥራኽም ይመዘገባል፣
. እያንዳንዱ የአመንዝራነት ሥራኽም ይመዘገባል፣
. እያንዳንዱ የሐሰት መሐላኽም ይመዘገባል፣
. እያንዳንዱ ነቀፌታ እና ስም ማጥፋት፣ መተት፣ ስርቆት፣ ግድያ፣... ኹሉም ይመዘገባል።
ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም

ወዳጀ ሆይ ራስህን እወቅ
ራስን ማወቅ የዕውቀቶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡
ራስህን እወቅ የሚለው ምርጥ አባባል በርግጥ የፈላስፋው ሶቅራጥስ ዘመን ተሸጋሪ የጥበብ ንግግር ነው፡፡
ራስን ከማወቅ ታላቅ ጥቅምን ታገኛለህ፡፡ አንተ ራስህን አመድና ትቢያ እንደሆንክ ስታውቅ ትሁት ትሆናለህ፡፡
ሀጢያትህን ስታወቅ ተፀፃች እና የንስሀ ሰው ትሆናለህ፡፡
አንተ በውስጥህ ጦርነት ያለብህ ፍጡር እንደሆንክ ስታውቅ ጠላቶችህን ታሸንፋለህ፡፡
ፀጋዎችህን በውል ካወቅህ ፈጣሪህንና በአምሳሉ የተፈጠረውን ማንኛውንም ሰው ለማክበር ፈጥነህ ትጠቀምበታለህ፡፡
እናም ወዳጀ ሆይ ራስህን በማወቅ፣ አዕምሮህ ማንነትህንና አንተነትህን ለማጠናከር በሚረዳህ ፣ስሜቶችህን በአውንታዊ አካሄድ በሚያሳድጉ፣ ዓለማዊነትን በልክ በአግባብና በሀላፊነት እንዲሁም መንፈሳዊነትህን የሚያጎሉ ገንቢ ዕውቀቶችን በመያዝ ክፍ በል፡፡
ከዛም ለምትኖርበት ማህበረሰብ እና ለሰው ወገን ሁሉ በሚጠቅም ነገር ላይ ማንነትህንና አንተነትህን ለማዋል የሚበጅህ ዋናው ጉዳይ ራስን ማወቅ ነውና እንደዛው ለማድረግ ሞክር፡፡

ከፈተና እንዲያድንህ እግዚአብሔርን መጥራት
"ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም፡፡ ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች» (መዝ. ፲፮ ፥፰-፱)
«እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ፡፡ በአንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ፡፡ በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው:: እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው:: ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።" (መዝ.፻፪ ፥፳፫-፳፰)
‹‹እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጕስቍላሉ፡፡›› (ኤር. ፳፥፲፩)
‹‹አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቁጣው? በልቡ፡፡ አይመራመረኝም ይላልና፡፡ አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቊጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት ድሀ ራሱን ለአንተ ይተዋል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ፡፡" (መዝ. ፲፥ ፲፪-፲፬)
‹‹ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት። ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቈሉም ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይበሉ፡፡ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች። አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል። አቤቱ፥ እንደ ኣንተ ማን ነው? ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።" (መዝ. ፴፭፥፪-፬ ፣ መዝ. ፴፭ ፱-፲)
"አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ:: አቤቱ፥ ድምፄን ስማ ጆሮህ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን፡፡" (መዝ. ፻፳፱ ፥ ፩-፪) "ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም፡፡ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል፡፡" (መዝ. ፻፳ ፥ ፩-፰)
(ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስና ሥራዎቹ - በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

++ በሰንበት መፍረስ ++
የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡
ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡
ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡
እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!
ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡
✍ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ

ያለነው እንጸናለን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
✞ ያለነው እንጸናለን
ያለነው እንጸናለን /የሔዱት ይመጣሉ/2/2
ከበረቱ ውጪ /ብዙ በጎች አሉ/2/
ቸርነቱን ቀምሰን ምህረቱን አይተናል
ባርነት ሽሮ ልጆቼ ብሎናል
ከዚህ ፍቅር ጌታ ወዴት እንሄዳለን
ግራ ቀኝ አንልም በቤቱ እንፀናለን
አዝ________________
ጠላት እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ቢዘምት
እንሻገራለን ፈተናውን በእምነት
ኃይሉን ያለበሰን ኃይለኛውን አስሮ
ባውሎና በወጀብ ከኛጋር ነው አብሮ
አዝ________________
መንጋውን ሊያበዛ መራራ የጠጣው
ለጠፉት በጎች ነው ኢየሱስ የመጣው
በረቱ እንዲሞላ በፍቅር ይጣራል
ጆሮ ያለው ይሽማ ወዴት ናችሁ ይላል
አዝ________________
ኮብልሎ የሄደው ታናሽህ ሲመለስ
መላእክትን ምሰል ታላቅ ይበልህ ደስ
ይታረድ ፍሪዳው አታጥቁር ፊትህን
ባክኖ እንኮን ቢመጣ ሳመው ወንድምህን
NEW ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ያለነው እንጸናለን /የሔዱት ይመጣሉ/2/2
ከበረቱ ውጪ /ብዙ በጎች አሉ/2/
ቸርነቱን ቀምሰን ምህረቱን አይተናል
ባርነት ሽሮ ልጆቼ ብሎናል
ከዚህ ፍቅር ጌታ ወዴት እንሄዳለን
ግራ ቀኝ አንልም በቤቱ እንፀናለን
አዝ________________
ጠላት እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ቢዘምት
እንሻገራለን ፈተናውን በእምነት
ኃይሉን ያለበሰን ኃይለኛውን አስሮ
ባውሎና በወጀብ ከኛጋር ነው አብሮ
አዝ________________
መንጋውን ሊያበዛ መራራ የጠጣው
ለጠፉት በጎች ነው ኢየሱስ የመጣው
በረቱ እንዲሞላ በፍቅር ይጣራል
ጆሮ ያለው ይሽማ ወዴት ናችሁ ይላል
አዝ________________
ኮብልሎ የሄደው ታናሽህ ሲመለስ
መላእክትን ምሰል ታላቅ ይበልህ ደስ
ይታረድ ፍሪዳው አታጥቁር ፊትህን
ባክኖ እንኮን ቢመጣ ሳመው ወንድምህን
NEW ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21