መንፈሳዊ ህይወት
4.03K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
Forwarded from ሰላም ለኪ ማርያም (EMANDA💗💖)
​​በጾም ወራት "ዓሳ" መብላት ይቻላልን???

ክፍል አንድ

ብዙ ጊዜ ይህ ከላይ ያነሳነው ርዕሰ ጉዳይ ሰዎችን ሲያከራክር እንሰማለን በተለይ በዚህ በያዝነው በዐብይ ፆም ደግሞ ሁኔታው ከፍ ብሎ ምዕመኑ ውዥንብር ውስጥ ሲገባ ይሰተዋላል ዓሳ ፆም አለው የለውም በሚል ንትርክም ጊዜውን ያጠፋል።

ዓሳ ፆም የለውም ብለው የሚከራከሩ ሰወች እንደ መነሻ ምክንያት አድርገው የሚያነሷቸውና የሚከራከሩባቸው ከእውቀት ማነስ የመጡ ሁለት ነጥቦች አሉ።
እነሱም ፦
1ኛ፨ በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት ) ስለ ፆምና ሥርዓቱ በሚዘረዝረው አንቀፅ 15 ላይ ያለውን "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ አሳ" የሚለውና
2ኛ፨ በአብይ ፆም ጊዜ ጌታ ለሐዋርያቱ አሳ አበርክቶ መግቧቸዋል የሚለው ናቸው።

እነዚህን ሁለት ነጥቦች በዝርዝር ስንመለከት
1ኛ. በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት )ላይ እውነት ነው " ኢትብልዑ ... ስጋ ዘእንበለ አሳ " የሚል ትዕዛዝ አለ። እዚህ ትዕዛዝ ውስጥ ለክርክሩ መነሻ የሆነው <ዘእንበለ> የሚለው የግእዝ ቃል ነው! ይህ ቃል በግእዙ ሁለት ትርጉም አለው እነሱም፦
ዘእንበለ = በስተቀር
ዘእንበለ = ሳይቀር (ጭምር) የሚል ነው።

በነዚህ ትርጉሞች መሰረት የትዕዛዙ ትክክለኛ የአማርኛ ፍቺ "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ ዓሳ " ለሚለው "ስጋን ሁሉ አትብሉ ዓሳንም ሳይቀር (ዓሳንም ጭምር) ማለት ሆኖ ሳለ አንዳንድ
ሰዎች ይህንኑ ትዕዛዝ "ስጋን አትብሉ ከዓሳ በቀር" ብለው አጣመው በሁለተኛው ፍቺ በመተርጎም ዓሳን በፆም ወቅት ሲበሉና መብላትም እንደሚቻል
ሲናገሩ እንሰማለን።

ይህ ነገር የቤተ ክርስቲያን አስተምሮ እንዳልሆነ ቅዱስ ሲኖዶስም እንደከለከለ ምዕመኑ ተረድቶ ነገርየውን ከመፈፀም መቆጠብ ያልተፃፈውን የሚያነቡትንም ተው ማለት ይገባዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ደግሞ ዓሳ ደም ስለሌለው በፆም መመገብ ይቻላል የሚሉ አሉ። ይህ ከየዋህነት የሚመጣ አስተሳሰብ ነው ምክንያቱም ሲጀመር ዓሳ ደም አለው ሲቀጥል እነ እንቁላል እነ ወተት እነ አይብና ቅቤ ደም ሳይኖራቸው ነው የፍስክ ሆነው በፆም የማይበሉት።

ይህ ነገር የሚደረገው መፆም ማለት ስጋን ጎድቶ ለነፍስ ማስገዛት እስከሆነ ድረስ አበልፃጊ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ስላለብን ነው ዓሳ ደግሞ ከበግና ከበሬ ስጋ የተሻለ ጥቅም
እንዳለው ይታወቃልና ከበግና ከበሬ ተከልክሎ አሳን መብላት እራስን ማታለል ነው የሚሆነው ስለዚህ አንድ ክርስቲያን በጾም ሰአት ዓሳን መብላት አይችልም ማለት ነው።

ሼር
ክፍል 2 ይቀጥላል


@Ortodox_Ringtones
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
መጻጒዕ

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡ ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል፤ እነዚህም፡- ሰውነታቸው የደረቀ፣ የሰለለና ያበጠ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ ‹መጻጒዕ› ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡ መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ ‹መጻጒዕ› ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡ (ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፲፯ ይመልከቱ)፡፡ ዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ፤ ሰውነታቸው የሰለለ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡


#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
ገብር ኄር

ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡ አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ፣ ዐሥር አድርጎ፣ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ›› ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ፣ ወርዶ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው ‹‹አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ ‹‹አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት፤ እነሆ መክሊትህ!›› ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት!›› ብሎ አዘዘ፡፡

በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው (ክርስቲያን) ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም፣ በጎ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ (አገልጋይ) ይባላል፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ፣ መክሊታቸውን (ጸጋቸውን) ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መክሊትን (ጸጋን) መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡


#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
ልጆቼ! የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደሆነ የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም ታስሬ አስፈትታችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ታምሜ አድናችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ተርቤ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መዓድ ሳይሆን አንዲት ዳቦ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መጠጥ ሳይሆን አንዲት ቀዝቃዛ ኩባያ ውኃ አጠጥታችሁኛልና ነው የሚለን፡፡

በጣም የሚያቀለው ደግሞ እነዚህን ቀላል ትእዛዛት በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸው አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በቃሉ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ስለሚለን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን ነው፡፡ እንግዲያውስ ድሀ ስለሆንኩ እነዚህን ማድረግ አልችልም ብለን ራሳችን ሰነፎች የምናደርግ አንሁን፡፡ ሺህ ጊዜ ደሀ ብንሆን ሁለት ሳንቲም ከሰጠችው መበለት በላይ ድሀ ልንሆን አንችልምና፡፡ ስለዚህ ስንፍናን ከእኛ እናርቅ፡፡

ልጆቼ! እነዚህን በእርሱ እርዳታ ስላደርግንስ ምን እንደምንባል ትገነዘባላችሁን? “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን!” ካላደረግንስ? “እናንተ ርጉማን ከእኔ ዘንድ ሂዱ!” እንግዲያውስ ለእኛ ሳይሆን ለሰይጣንና ለመላእክቱ የተዘጋጀውን እሳት ከሚያገኘን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለእኛ የተዘጋጀውን መንግሥት እንወርስ ዘንድ ዛሬ አብዝተን ዘይት የምንገዛ እንሁን፡፡ እንደነዚያ ሰነፍ ደናግላን እዚያ መግዛት በማይቻልበት ቦታ ሄደን ከምንጠይቅ ዛሬ ሳይመሽብን የሚበቃንን ያህል ዘይት እንግዛ፡፡ ዘይቱ የሚገዛውስ የት ነው? የታመሙት ጋር፤ እስረኞች ጋር፤ ቁርና ሀሩር በሚፈራረቅባቸው ወንድሞቻችናነ እኅቶቻችን ጋር፡፡

ልጆቼ! እንደ ነዌ እዚህ ምድር ባለጸጎች ሆነን ያኔ ከምንለምን ዛሬ አልዓዛርን ልናስበው ይገባል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53)
----------
4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

@linkortodoxe21
(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 15)
----------
17፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤

18፤ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤

19፤ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።

20፤ ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

21፤ አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።

22፤ ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።

@linkortodoxe21
እንካን አደረሳችሁ 😍😍😍
@linkortodoxe21
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤አሰሮ ለሰይጣን፤አግዐዞ ለአዳም፤ሠላም እምዕይዜሰ፤ኮነ ፍስሐ ወሠላም።

'ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጽም ሰላምና ደስታ ሆነ'

" እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም"
(የማቴዎስ ወንጌል 28:6)

😊እንካን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ😊
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
"እሳትን በእሳት ማጥፋት ይቻላልን??
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
" ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም። አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ #የመውጊያውን ብረት #ብትቃወም #ለአንተ #ይብስብሃል #አለው።"
(የሐዋርያት ሥራ 9:5)

@Ortodoxe19
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 13)
----------
1፤ አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?

2፤ እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ሁልጊዜ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደዳል?

3፤ አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፤ ጠላቴ። አሸነፍሁት እንዳይል፥

4፤ የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።

5፤ እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል።

6፤ የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።

👉 @linkortodoxe21
Channel name was changed to «መንፈሳዊ ህይወት»
😍እንካን አደረሳችሁ 😍
ግንቦት 21
እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ የታየችበት ቀን በእኛም ህይወት ትታይልን ከክፍ ነገር ሁሉ ትሰውረን

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
⚪️በዓለ ጰራቅሊጦስ⚪️
መንፈስቅዱስ የወረደበት ቀን እንካን አደረሳችሁ /አደረሰን
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@liniortodoxe21
#የቆሎ_ተማሪ_ዘድንግል


በዳዊት በገና በያሬድ ዝማሬ
እኔም ላወድስሽ ቃላትን ደርድሬ
የጌታዬ እናት ስምሽ ይጣፍጣል
ባህዛብ መካከል አፌ አንችን ይጠራል
ማርያም ማርያም ስልሽ ጠላት ይሸበራል
አሁንም ጠራሁሽ አውሬው እርር ይበል
አምላኬ ስጥራሽ ሰምቻለሁ በፍቅር
እናቴ ለክብርሽ አልሻም ምስክር
ምልጃና ፀሎትሽ ምርኩዜ ሆኖኝ
አሰፈሪውን ለሊት ስንቱን አለፈኩኝ
ልቤ አይከፈትም ዝግ ነው ለጠላቴ
ዘውትር አይለየኝም ስእልሽ ከደረቴ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

፤እንቺ የገነት ምንጭ ፥ የሕይውት ውኃ ጉድጓድ ፥ከሊበኖስም
የሚፈስስ ወንዘ ነሽ። መኃልየመኃለይ ዘሰሎሞን4 ፡ 15

ግጥም፦ዘኪ

🔸 @linkortodoxe21
🔸 @linkortodoxe21
🔸 @linkortodoxe21
ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወ ይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

© ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ አምስቱ የንስሓ መንገዶች፥ ገ. 9

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21