መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
መንፈሳዊ፡ህይወት፡ማለት

መንፈሳዊ መሆን ማለት የራሰን ፊቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል
ራሱ ግን በማንም አይመረመርም፡፡ (1ኛ ቆሮ2÷15) ሥርዓተ ሃይማኖትን ትውፊተ አበውን ገንዘብ አድርጎ መኖር መንፈሳዊነት ነው፡፡

አንድን ሰው መንፊሳዊ ነው ለማለት ሊፈጽማቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡እነርሱም፡
1.ተዓምኖ፤(መታመን) ፤እምነትን በተግባራዊ መልስ ማሳየት ማለት ነው፡፡ስለንስሓ የሚሰብከ ንስሓ የገባ መሆን አለበት፡፡ካልሆነ ችግር ነው፡፡ጣዕሙን አያውቀውም፡፡የዘመናችን ሰባክያነ ወንጌል መሠረታዊ ችግር ይህ ነው፡፡የሚጮህ አልጠፋም በተግባር የሚሰብከ
ግን ማግኘት ከባድ እየሆነ ነው፡፡
አንድ አባት አንዱን ሰባኪ ወንጌል ሰው ዕኮ ቤተ ክርስቲያንን አይደለም የጠላው አሉት ! ታዳያ ማንን ነው ሲላቸው ሰባኪው እናንተን ነው የጠላው ያላችሁትን ስለማታደርጉ አሉት ፡፡
አንድ ፓስተርም ጸልዩ አልቅሱ እያለ እሱ ግን አይጸልይም
አያለቅስም ይባስ ብሎ ስልክ ያወራል፡፡ፓሰተር ለምን አንተ አታለቅሰም ? ሲሉት አይ ጌታዬ የእኔ ሥራ ማስለቀስ ነው አለ፡፡

2.ምግባራተ ሠናያት አንድ ሰው እምነትን ተስፋን ገንዘብ ካደረገ በኋላ የሚቀረው ምግባረ ሠናይ ነው፡፡
መንፈሳዊ ሕይወት በማኀበራዊ ሕይወት ከተዋጠ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የነበረው አንድነትይላላል፡፡ሰዎችም ሐሳባቸው ሁሉ ምድራዊ ( ሥጋዊ) ወደ
መሆን ያዘነብላል፡፡ የበዓል ቀናትን ወደ ዕድር ዕቁብ ስብሰባ ይሆንና የመንፈሳዊ ሕይወት መስመር መላቅጡ ይጠፋል፡፡ መንፈሳዊነት በማኀበራዊነት ሲዋጥ በግለሰቡም በማኀበረሰቡም የሚታዩ ምልከቶች አሉ፡፡

1.ምክንያተኝነት፤ሰው ከመንፈሳዊ ሕይወት እየራቀ በሄደ ቁጥር አውቆም ሳያውቀውም ለፈጻማቸው ስሕተቶች ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ ምክንያትን በመደርደር መታለፍን ይፈልጋል፡፡ በአዳምና በሔዋን የታየው የመንፈስ መራቆት የተገለጠው በምክንያተኝነት ነው፡”ወይቤ አዳም
ብእሲትየ እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላዕኩ ”(ዘፍ3÷12)
መ. ምሳ18÷1” ምክንያተ የኀሥሥ በእሲ ዘይፈቅድ
ይትፈለጥ እም አዕርክቲሁ፤ከባልጀሮቹ ይለይ ዘንድ የሚፈልግ ሰው ምክንያት ይፈልጋል፡፡እንደ ሁለቱ አኀው በአንድ ቦታ የሚኖሩ ናቸው፡፡አንዱ የተማረ የበቃ ነው፡፡

አንዱ ያልተማረ ያልበቃ ነው፡፡ያልተማረው ያልበቃው መለየት ፍቃዱ ነውና ጓደኛውን ፀሐይ በየት ትወጣለች ብሎ ጠየቀው በምሥራቅ ብሎ ቢመልስለት ከዚህ ደንቆሮ
ጋር አልኖርም ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡መከራም አገኘው፡፡( ማር ይስሐቅ) ዛሬም አሉ የማይጠቅም ምክንያት በመደርደር ከአገልግሎት የሚርቁ ፡፡

2.መጎምጀት፤መንፈሰዊ ሕይወት የማደጉ ምልከት የሚታወቀው እንደ ሰራፕታዋ መበለት ያለውን አካፍሎ በመመገብ ነው፡፡የተገኘውን ለራስ ብቻ አውሎ ያለተገኘውንም በመጎምጀት መኖር ኃጢአት ሥር ይሰዳል፡፡

3.መመኘት፤ምቀኝነት መንፈሳዊ ሕይወት በሌለበት ምድር
የሚበቅል የልቡና አረም ነው፡፡ምቀኝነት በዘመናችን ምቀኝነት ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት ሰፊ የምሪት
ቦታ አለው፡፡ይህንን ሁሉ መከራ የምናስተናግደው ግን
መንፈሳዊ ሕይወት ጠፍቶና ሥጋዊነት ና ማኀበራዊ ሕይወት ብቻ በነገሠበት ምድር ላይ ነው፡፡

4.መተቸት፤መተቸት አብዛኛውን ጊዜ
“ሊቅነት”ከሚሰማቸው ለነገር ግን የፊደላት እጅና እግር
ከማያውቁ ሰዎች አካባቢ አይጠፋም ፡፡አይሠሩም
የሚሰራውን ይተቻሉ፡፡አያስተምሩም የሚያስተምረውን ዕዳ
ፍዳውን ያሳዩታል፡፡ ታዲያ ምን ይደረግ ተብለው ሲጠየቁ መልስ የላቸውም፡፡ ዕውቀታቸው መንፈሳዊነትን የተላበሰ
ሳይሆን መስፈርቱ ዕውቀት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡የዚህ ችገር ምኝጭ ማኀበራዊንቱ ብቻ በሰፈነባት ምድር ላይ በመሆኑ
አያሰደንቅም፡፡

5.የአኗኗር ለውጥ
ማኀበራዊነት ብቻ በዋጣት ምድር የሚኖሩ ሁሉ አንዱ ያደረገውን ሌላው ካላደረገ ራስን እንደኋላ ቀርነት
መቁጠር የተለመደ ነው ፡፡በዘመናችን ራስን ሁኖ ለመኖር የሚያስችል መንፈሳዊነት ተሟጦ ጠፍቷል፡፡የፊልሙ ጋጋታ የዓለም ገጽታ መለዋወጥ መንፈሳዊ ሕይወታችን ን በድርቅ እየመታው ነው፡፡
ገላትያ 5÷25” በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ
እንመላለስ”



@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned « መንፈሳዊ፡ህይወት፡ማለት መንፈሳዊ መሆን ማለት የራሰን ፊቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም፡፡ (1ኛ ቆሮ2÷15) ሥርዓተ ሃይማኖትን ትውፊተ አበውን ገንዘብ አድርጎ መኖር መንፈሳዊነት ነው፡፡ አንድን ሰው መንፊሳዊ ነው ለማለት ሊፈጽማቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡እነርሱም፡ 1.ተዓምኖ፤(መታመን) ፤እምነትን በተግባራዊ መልስ ማሳየት…»
ጠቃሚ ምክር!

በአንድ ጫካ ውስጥ መልካቸው ነጭ፣ ጥቁር እና ግንባሩ ቦቃ የሆኑ ሶስት በሬዎች ይኖሩ ነበር። አንበሳን ጨምሮ የትኛውም አውሬ
ቢመጣ ክብ በመሥራት እየተዋጉ አላስጠጋ አሉ

አንድ ቀን ግን አያ ጅቦ መጣና “ይሔ ነጭ በሬ ያስጨርሳችኋል፤ እሱ ባይኖር በጨለማ አትታዩም” የሚል መጥፎ ሀሳብ በውስጣቸው ለቀቀባቸው። ሁለቱ በሬዎች ተባብረው ነጩን በሬ አባረሩ ጅቡም ብቻውን አግኝቶት ነጩን በሬ በላው

ጅቡ ሌላ ጊዜ ተመለሰና ለጥቁሩ በሬ “ግንባረ ቦቃው ካለ አሁንም ለአደጋ የተጋለጥህ ነህ” አለው፡፡ በዚህ የተነሳ ሁለቱ በሬዎች ተለያዩ፡፡ ጅቡም ግንባረ ቦቃውን በላው። በሌላ ቀን ጅቡ ጥቁር በሬው ጋር ሄደ፡፡ በሬውም “ዛሬ ምን ፈልገህ መጣህ? ልትበላኝ ነው?” አለው

ጅቡም “አንተ እኮ የተበላከው መጀመሪያ ጓደኞችህን አሳልፈህ የሰጠህ ጊዜ ነው” ብሎ ጥቁሩን በሬ በላው፡፡ ልብ ብለን ልንረዳው የሚገባው ነገር ሁሌም ልዩነታችን ውበትና ጥንካሬ የሚኖረው በአንድነታችን ውስጥ ነው! አንድ ስንሆን እንቆማለን፤ ስንከፋፈል እንወድቃለን!
@linkortodoxe21
#አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ

✥በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው :- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

✥በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው :-
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

✥ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር:- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

✥ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል::
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

✥"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ"
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
✥የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን✥


@linkortodoxe21
መጋቤ ሀዲስ እሽቱ አለማየሁ

ቁንጅና ለትዳር ዋስትና አይሆንም!
መታመም ማለት ትሞታለህ ማለት አይደለም!
ሃብታም መሆን የጥሩ እድል ትርጉም አይደለም!
ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር የድሎት ምንጭ አይሆንም!
ጥሩ መኪና መንዳት ለምትደርስበት ቦታ ዋስትና
አይሰጥህም !
ለቤተሰብህ ዶክተር ብትቀጥር ቋሚ የጤና ዋስትና አይኖርህም!
ብዙ መማር ጥበበኛ አያደርግህም!
ሃብታም ማግባት ለደስተኛ ለህይወት ማረጋገጫ አይሆንም!
ክርክር ማሸነፍ ትክክል መሆን አይደለም !
***
ገነት የማያሸልም ምንም ነገር ብትሰራ ጊዜያዊ እና
ውሸት ነው ። ያለ አምላክ የሚራመድ ሰው በድን
ነው፣አንተ በራስህ ላይ ስልጣን የለህም
አንተ ሰውነትህን ታያለህ እሱ ደምስርህን ያያል ። ሁሉም
ነገር ለርሱ ይቻላል በሁሉም ነገር ውስጥ አምላክህን ጣልቃ አስገባ።
@linkortodoxe21
ከእለታት በአንድ ቀን ድህነት ያንገላታው አንድ ሰው ሚስቱንና ሁለት ልጆቹን ትቶ ወደ ሩቅ ሀገር ለሥራ ይሄዳል እዛም ለ10 ዓመታት ከሠራ በኋላ 2500ብር ብቻ አግኝቶ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ መንገድ ይጀምራል።

ሲጓዝም አንድ መነኩሴ መንገድ ላይ ያገኙትና " ልጄ የያዝከውን ብር ስጠኝና በህይወትህ እጅግ የሚጠቅሙህን 3 ምክሮች ልስጥህ ይሉታል። ምንም ሳያንገራግር ብሩን ሰጣቸው።

መነኩሴውም:-
፩. አቋራጭ ነው ብለህ በአቋራጭ አትሂድ
፪. በማያገባህ አትግባህ
፫. ለውሳኔ አትቸኩል
ብለው ምክር ለግሰውት ይሰናበቱታል።

ይህ ሰው ሲጓዝ ቆይቶ መንገድ የሚጓዙ ነጋዴዎችን ይቀላቀላል እነሱም " በዚህ በኩል የሚወስድ አቋራጭ መንገድ አለ" እንሂድ ወደ ከተማው በፍጥነት ያደርሰናል ይሉታል ...እሱም በአቋራጭ አትሂድ የተባለው ትዝ አለውና "የለም እኔ በዚህ በቀጥታው እሄዳለሁ" ብሎ ከነሱ ተለይቶ ሄደ.....ተጉዞ ከተማው ሲደርስ የከተሜው ሰው ሁሉ "ዛሬ ጠዋት በአቋራጭ ሲሄዱ የነበሩ ነጋዴዎች በሽፍቶች ተገድለው ተገኙ" ብለው ሲያወሩ እጆሮው ገባ። በጣም ተገረመ ቀኑም ስለመሸ በቆመበት አካባቢ የሚያልፍ አንድን ሰው ጠጋ ብሎ" እባክህን ወደ ሃገሬ እየሄድኩ ስለመሸብኝ የማድርበትን ቤት ብትጠቁመኝ ብዬ ነው ይለዋል።

ያም መንገደኛ በእጁ ወደ አንድ ቤት እየጠቆመ "እዛ ቤት ሂድና ጠይቃቸው ነገር ግን ከገባህ ተመልሰህ አትወጣም ይለዋል" በንግግሩ ግራ ቢጋባም ውጭ ከማደር ብሎ የተጠቆመውን በር አንኳኳ....እጅግ መልከ መልካም የሆነ ሰው ይከፍትለታል ማደርያም እንደሚፈልግ ይነግረውና ያስገባዋል....መልከ መልካሙም ወጣት ወደ ቤቱ ያስገባውና ሚስቱን ያሳየዋል .....እጅግም መልከ ጥፉ ነበረች ....እንግዳውም" እንዴት ይሄ እንዴት ይሆናል.......ብሎ ሊናገር ያስብና #በማያገባህ #አትግባ የተባለው ትዝ አለውና ዝም አለ.....በነጋታውም ያ መልከ መልካም ወጣት እንግዳውን ወደ ጓሮ ወስዶ ብዙ የራስ ቅሎች ያሳየውና........አየህ ወንድሜ እኝህ ሁሉ ስለሚስቴ መልክ በማያገባቸው ገብተው የገደልኳቸው ናቸው.....አንተ ግን ምንም ስላላልክ የሃብቴን እኩሌታ እሰጥሃለሁ ብሎ ሰጥቶ አመስግኖ ይሸኘዋል።

እንግዳውም የተሰጠውን ስጦታ ይዞ ለቤተሰቦቹ ለመንገር እየተቻኮለ በሩን ከፍቶ ሲገባ ባለቤቱ ከሁለት ጎረምሶች መሃል ተኝታ ያገኛታል።

እጅግም በመናደድ ወደ ጓዳ ገብቶ መጥረቢያ አንስቶ ወደ መንታ ክፍል እየተንደረደረ ሲገባ እኛ መነኩሴ #ለውሳኔ #አትቸኩል ያሉት ትዝ አለው።
ራሱንም አረጋግቶ እስኪነሱ ይጠብቃል..

ባለቤቱም ከእንቅልፏ ስትነቃ የናፈቃት ባሏን ስላየች እጅጉን ደስ እያላት ጥምጥም ብላ አቀፈችው......በል ሁለቱ ልጆችህን እቀፍና ሳማቸው አለችው።

(ለካ ጥሏቸው የሄደው ትናንሽ ልጆቹ አድገው ነው)

የአባቶች ምክር ነፍስን ያለመልማል
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ታስበላብሃለች

አንድ እምነት የነበረው እረኛ ነበረ ይባላል፡፡ ምሳ ለመብላት ሲፈልግ ያሰማራቸውን በጎች ለቅዱሳን፣ ለመላእክት አደራ ሰጥቶ ይሔዳል፡፡

"ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! እነዚህን በጎቼ ከተኩላ ጠብቅልኝ" ብሎት ይሔዳል፡፡ እንደ እምነቱም በጎቹ ተጠብቀዉለት ያገኛቸዋል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ "ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! አንተ ጠብቅልኝ" ይሏል፡፡ እንዲህ በቅዱሳን እያስጠበቀ ምሳውን በልቶ ይመጣል፡፡

አንድ ቀን፦ "እመበቴ ሆይ! ዛሬ አንቺ ጠብቂልኝ" ብሎ ወደ ቤቱ ይሔዳል፡፡ አባቱ አገኙትና፦ "ዛሬ ለማን አስጠብቀህ መጣህ?" አሉት፡፡ "ለእመቤታችን አስጠብቄ መጣሁ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም፦ "አዬ ልጄ! እርሷ'ማ ታስበላብሃለች" አሉት፡፡ "ለምን? ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ መላእክት የጠበቁትን እርሷ አትጠብቅምን?" ይላቸዋል፡፡ "አይ ልጄ! የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፡ የተራበ አውሬ መጥቶ ቢበላ ትከለክለዋለችን? ታስበላብሃለች" ሲሉት "እውነትም" ብሎ ወደ መንጎቹ ሮጠ ይባላል፡፡

ርህርህተ ሕሊና ሆይ! ዘወትር በምልጃሽ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን፡፡ አሜን!!!

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
አንድ መነኩሴ ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ቀርቦ በምሬት እንዲህ አለ :-

"አባቴ በዚህ ገዳም ምንም ጸጋ ምንም ትሩፋት የሌለኝ መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ:: አባ እገሌን እዩት እንደ እርሱ የዋህ የለም! አባ እገሌን እዩአቸው እንደርሳቸው ታጋሽ ማን አለ? አባ እገሌን እዩአቸው ለሁሉ ፍቅር አላቸው!

እኔ ግን ምንም የለኝም አልረባም አባቴ እባክዎ ይጸልዩልኝ የእኔ ጸጋ የእኔ ፍሬ ምንድር ነው?" አለ እያለቀሰ::
አበምኔቱም አይዞህ ጸልይ ብለው አሰናበቱት::

እሱ ከወጣ በኁዋላ ግን አብረዋቸው ላሉት መነኮሳት እንዲህ አሉ :-
"ይህ መነኩሴ በዚህ ገዳም ካሉ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ ተሠጥቶታል:: የወንድሞቹ ኃጢአት አይታየውም
ጽድቃቸውን ግን በትሕትና ሲቆጥር ይውላል:: ከዚህ በላይ ምን ጸጋ አለ? ዝም ያልኩት ይህንን ብነግረው ክብሩን አሳንስበታለሁ ብዬ ነው" አሉ::

"ነፍሳችሁን ተመልከቱ የወንድማችሁንም ኃጢአት አትመልከቱ እግዚአብሔር ያያል" ቅዳሴ እግዚእ

ከዲያቆን ሄኖክ ኃይለ ትምህርቶች የተውሰደ
@linkortodoxe21👈
@linkortodoxe21👈
@linkortodoxe21👈
Forwarded from LikeBot
በዓታ ለማርያም (ታህሳስ 3)

በዚህች ቀን ቅድስት እናታችን ራሱዋን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ የብሉዩዋ ቤተመቅደስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ልትተካ መቃረቡዋን ለማብሠር ወደ ቤተ መቅደስ ያመራችበት ቀን ነው፡፡ ጌታችንም ከእርሱዋ የነሳውን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ የራሱ ቤተመቅደስ በማድረግና እኛንም በጥምቀት የአካሉ ሕዋሳት እንድንሆን በማብቃት ሥጋችንን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ቤተመቅደስ መግባት ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር ቃል ከእርሱዋ በሥጋ በመወለዱ ያገኘነውን ድኅነትና ብዙ ጸጋዎችን እናስባለን፡፡ አሁን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከእርሱዋ የተወለደውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለብሰነዋል፤ (ገላ.3፥27) ከእርሱዋ በነሣው ተፈጥሮ በኩል ሞትን በመስቀሉ ገድሎ ሲያስወግደው፣ እኛም በጥምቀት ከእርሱ ሞት ጋር በመተባበራችን ሞትን ድል የምንነሣበትን ኃይልን ታጥቀናል፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋ ሠርተንበትና አብዝተነው ብንገኝ ከትንሣኤው ተካፋዮች መሆንን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመልን እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ ምክንያት ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ብሉይን ከአዲስ ያገኛኘች መንፈሳዊት ድልድይ ናት፡፡ በብሉይ ያሉት ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን ካለነው ጋር አንድ ማኅበር የፈጠሩትና ከቅዱሳን መላእክትም ጋር እርቅ የወረደው ከእርሱዋ በነሳው ሰውነት በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም” (ኤፌ.2፥19) ብሎ አስተማረ፡፡ ራሷን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ እኛንም በልጁዋ በኩል የመንፈሱ ቤተ መቅደስ እንድንሆን ምክንያት ሆናልናለችና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት ለእኛ ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም አለው፤ ስለዚህም ይህቺን እለት በታላቅ ድምቀት እናከብራታለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን!

Share share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ከራሳቸው ውጪ ደስታን የሚፈልጉ እንደምን ምስኪኖች ናቸው? ደስታን በባእድ ምድር በጉዞ የሚፈልጉ አሉ። በሀብትና በዝና መካከል የሚፈልጉ ወገኖች አሉ፤ በታላቅ ይዞታና በንብረት መካከል የሚፈልጉ አሉ፤ መራራ ፍፃሜ ባላቸው በውበትና በተቃራኒ ፆታ መካከል የሚፈልጉ አሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ ደስታን ከራሳችን ውጪ ለመገንባት መሞከር በተደጋጋሚ በመሬት ርእደት በሚናወጥ ሥፍራ ላይ እንደ መገንባት ነው።

ደስታ የሚገኘው በእኛው ውስጥ እንጂ ከእኛ ውጪ አይደለም። ምስጉን ማለት ይህን ሁኔታ የተገነዘበ ሰው ነው። ደስታ ማለት የልብ ንፅህና ነው፤ እንዲህ አይነቱን ልብ እግዚአብሔር ማደሪያ ያደርገዋልና። ስለዚህ ንፁህ ልብ ያላቸው ወገኖች ክርስቶስ እንዲህ ይላቸዋል፦ በእነሱ እኖራለሁ፣ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸው እሆናለሁ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 2ኛ ቆሮ. 6፥16 እንዲህ አይነት ወገኖች ምን ይጎድልባቸዋል? ምንም። "

(አባ ሳራባሙን - የበረሃ ፈርጦች መጽሐፍ ገጽ 14 በመምህር ምትኩ አበራ)

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ሥዕላትን_ይፈቅዳልን ?
🖋 በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

★ ጽሑፉን ካነበቡ በኋላ #Forward & #Pin በማድረግ ለሌሎችም እናሳውቅ!!!

💠 በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን ፣ የድንግል ማርያም ፣ የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ ፣ መብራት ሲያበሩ ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ደግሞ ‹ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!› ‹‹በላይ በሰማይ ካለው ፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም›› ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ ፳፥ ፬)

💠 በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም ፣ በምድርም ፣ ከምድርም በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን ፣ በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ ለመሳል እንዴት ደፈረች? እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት? የሚለው ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡

💠 በቀጥታ ወደ ምላሹ ከመግባታችን በፊት ከዚያው ከኦሪት ዘጸአት ሳንወጣ ጥቂት ምዕራፎችን እንሻገርና እናንብብ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ … አንደኛውን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ ሥራ … ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘርጉ ፤ የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ ፤ ፊታቸውም እርስ በእርሱ ይተያያል … እኔም በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አነጋግርሃለሁ›› (ዘጸ ፳፭፥ ፲፰-፳፪)

💠 ልብ አድርጉ ፤ ከአምስት ምዕራፎች በፊት ‹ከሰማይ ፣ ከምድርና ከባሕር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› ብሎ ለሙሴ ያዘዘው እግዚአብሔር አሁን ደግሞ በሰማይ ካሉ መላእክት መካከል የሆኑትን የኪሩቤልን ሁለት ምስል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ፣ ክንፎቻቸውን እንዲዘረጉና እንደሚናተፍ ዶሮ እንዲተያዩ አድርጋቸው ፣ እኔም በእነርሱ መካከል አነጋግርሃለሁ አለው፡፡

💠 ከዘጸአት ሳንወጣ እግዚአብሔር አሁንም ለሙሴ እንዲህ አለው፦ ‹‹መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ አድርግ ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ›› በማለት ከወርቅ ከተቀረጹት ሁለት ኪሩቤል በተጨማሪ በመጋረጃ ላይ በጥልፍ መልክ ኪሩቤል እንዲሣሉ አዘዘው፡፡ (ዘጸ ፳፮፥ ፴- ፴፩) እግዚአብሔር በሰማይ ካሉት የማንንም ምሳሌ አታድርግ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ራሱ የሚጥስ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን? ኪሩቤል ‹በሰማይ ካለው ማናቸውም ነገር› ውስጥ አይደሉምን? የተቀጠቀጠ ወርቅስ የተቀረጸ ምስል አይደለምን? ይህን ጥያቄ እንደ ዋዛ መተው እንዴት ይቻላል?

💠 መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘጸአት ብቻ ቢሆን ሁለት ማስረጃ ጠቅሰን እንተወው ነበር፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር ‹‹እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሠጠው›› ተብሎ የተነገረለት ጠቢቡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ሲፈጽም ይህንን አደረገ፦ ‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሌላኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ… ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው›› ይላል፡፡ (፩ኛ ነገ ፮፥ ፳፫- ፳፰)

💠 ጠቢቡ በዚህ አልበቃውም ፤ የቤተ መቅደሱን ግንብ ዙሪያውን ባዶ እንዲሆን አልተወውም ‹‹በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ›› ይላል፡፡ (፩ኛ ነገ ፮፥ ፳፱) በአጭሩ ጠቢቡ ሰሎሞን እንደ ሙሴ በመጠን ያነሡ ሳይሆኑ ዐሥር ክንድ የሚረዝሙ ኪሩቤልን ከወይራ ሠርቶ በወርቅ ሲለብጥ ከምድርም አበባና ዘንባባን በቤተ መቅደሱ ምስል አድርጎ ቀረጸ፡፡

★ ‹የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡ ሕጉ የሚጠናቀቅበት ‹አትስገድላቸው አታምልካቸውም› የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የከለከላቸው የተቀረጹ ምስሎች አምላኬ ነህ ተብለው ለፈጣሪ የሚገባ የአምልኮ ስግደት የሚሰገድላቸው ጣዖታትን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ለማንኛውም በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከሰማይ ከምድር ከባሕር ያሉ ፍጥረታትን በምስል ቀርጾ አምላኬ አንተ ነህ ብሎ እንዳይሰግድ የተከለከለው ክልከላ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላእክት መቅረጽ አይገባም ለማለት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የተሳሳተ መሆኑን ራሱ ባለቤቱ ሕጉን ከሠራ በኋላ በዚያው ዘመን የመላእክቱን ሥዕልና ቅርጽ በማሠራት አሳይቶናል፡፡

💠 እዚህ ላይ አንድ ነገር እናስተውል ፤ ከላይ ባየናቸው የቤተ መቅደሱ ውስጥ ሥዕላት በተደጋጋሚ የተሣሉት መላእክት ብቻ ከመላእክትም ኪሩቤል ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደምናየው ከሙሴ በፊት የነበሩ እንደ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላቸው በቤተ መቅደሱ ለምን አልተሣለም? ምናልባት ለቅዱሳን ሰዎች ሥዕል አይገባ ይሆን? ያሰኛል፡፡

💠 አይደለም፤ እንደሚታወቀው ቤተ መቅደሱ የሰማያት ምሳሌ ሲሆን በሰማያት በልዕልና የሚኖር አምላክ ከሕዝቡ መካከል በረድኤት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ያሉት ነገሮች ሁሉም በሰማያት በእግዚአብሔር መንግሥትና ከእግዚአብሔር ጋር ያሉትን ነገሮች የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ ወደ ሲኦል በወረዱበት በዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእግዚአብሔር ረድኤት ርቀው በሞት ጥላ መካከል ናቸውና የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ በሆነው መቅደስ ውስጥ አልተሣሉም፡፡ በዚያ ቤተ መቅደስ የተሣሉት መላእክት ከመላእክትም ለታቦቱ ዙፋንነት ምሥጢር የሚቀርቡት በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋኑን የሚሸከሙት ኪሩቤል ናቸው፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🕯``ማንኛውም ሰው በዚህ ምድር ሲኖር ከሁለት አንዱን መምረጥ ይኖርበታል ክርስቶስን የሚወድ ወይም ክርስቶስን የሚዋን መሆን ከዚህ ውጪ ምርጫ እድል ፈንታም የለም፡፡"!🕯

💡የነግህ[የጠዋት] ዳቤ💡
           #አደራ_አለብኝ
 

#ብርሃን_ይሆናል ስል
ቢውጠኝ ጨለማ
ለምለም መስክ ስፈልግ
#ቢገጥመኝ_ባድማ
ፍቅር አንድነት ስሻ
መለያየት ሆኖ
ሰላሜን ብቀማ
ለሌላም አይደለም
#ቅድስት_ተዋህዶ !
ላንቺ ነው ለእማማ
ጴጥሮስ የቁልቁሊት
ለእምነቱ ተሰቅሎ
ደግሞም እስጢፋኖስ
በድንጋይ ተወግሮ
ሳትነዋወጪ እንዳለሽ ጠብቀው
አንቺን ያስረከቡኝ
#እኔስ_አልተውሽም
አደራ አለብኝ 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
          #ዐረገች


ከሰማዮች ይልቅ
#ውብ_ሰማይ ነበረች፣
የጨለማውን ሊቅ
#ድቅድቅ_የሰበረች
እውነተኛ ፀሐይ #ከርሷ_ቢፈነጥቅ
ብርሃን ያበሰረች ::
እርሷ ያወጣችው
አማናዊ ፀሐይ፣
እንዳገዘፈችው
ኑሮ በምድር ላይ፣
#ሞቶ_ተነሣና
ከፍ ብሎ ቢያርግ
ቢሔድ ወደ ሰማይ፣
#እርሷም_ሞተችና
ፀሐዩአን ልትፈልግ
#ተነሣች_ወደ_ላይ
ዐረገች ወደ ላይ
ብርሃን ልጇን ልታይ :: 🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@libkortodoxe21
           #ጠብቂኝ_እመቤቴ


#የምህረት_ቃልኪዳን አምላክ የሰጠሽ
#የአማኑኤል_እናት መጽናኛዬ ነሽ ፤
ምንም ተስፋ የለኝ #ባንቺ_ነው_እምነቴ
አማልጅኝ ከልጅሽ #ክብረት_እመቤቴ ::
ሕይወቴ ጎስቁሎ በነፍሴ ብዝልም ፤
በምልጃሽ ታምኜ በኪዳንሽ ልቁም ::
#ስምሽን_እየጠራሁ እጽናናለሁኝ ፤
#ስሞት_እንዳልጠፋ ድንግል ጠቢቂኝ ::
ደሃ ምስኪን ሆኜ ለሰዎች ብታይም ፤
ሞልቶ የተረፈ ጥሪት ባይኖረኝም ፤
ስምሽን ብጠራ #ምንም_አይጨንቀኝም
አንቺ ካለሽልኝ #ኑሮዬ_ሙሉ_ነው
አፍሮ አያውቅምና #የተማጽነሽ_ሰው ::
እኔን የሚረዳኝ በአገር ስቸገር
#ዘመድ_ጠያቂ_የለኝ_ፍጽም_ካንቺ_በቀር
ከውጭም ስገባ ከቤትም ብወጣ
ነፍሴ እንድትቀደስ ከርኩስነት አምልጣ
#ጠብቂኝ_እመቤቴ ከዘመኑ ቁጣ  🙏
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21