መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
.:
ኦርቶዶክሳዊው መነኩሴ አባ ሌቭ ጊሌት በመንፈሳዊ ጽሑፎቹ ላይ አንድ ጊዜ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ "አንተም ኃጢአት በምትሠራ ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚወድህ እርግጠኛ መሆን አለብህ፡፡" ዲያብሎስ በተቃራኒው ሊነግርህ ይችላል ፤ እርሱ ግን ሐሰተኛ ነው፡፡

እናም እንደወደቅህ ወዲያውኑ በተወደደው አባትህ ፊት ተንበርክከህ ፦ "አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም" በለው፡፡ ወዲያውኑ አባትህ በደስታ ሲያቅፍህና በፍቅር ሲስምህ ታገኘዋለህ፡፡ ዳግመኛም በቁርጠኝነት ወደ ውጊያው ተመልሰሃል ማለት ነው፡፡ ይህ የጸጸት መጀመሪያ ተግባር ግን ለንስሐ አባትህ የምታደርገውን ኑዛዜ የሚተካ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወደ ንስሐ አባትህ ዘንድ መቅረብና ከሐጢአትህ ፈጽሞ መታጠብ ቀኖናንም መቀበል ቅድስናና ንጽህናህን የማግኛ ፍጻሜ ነው፡፡
🍒
(አቡነ አትናስዮስ እስክንድር)


@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
New_2015_Tewahedo_mezmur_by_Zamari_Gebre_Yohannis_G_Tsadik_-%E1…
<unknown>
የጻድቅ ሰው ፀሎት ሀይልን ያደርጋል በፀሀይን ያቆማል ሙትን ያስነሳል ከጠላት ዲያብሎስ ነፍሳትን ይነጥቃል ባዶውን ማድጋ በዘይት ይሞላል

ዘማሪ ገ/ዬሀንስ ገ/ጻድቅ
በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
Audio Extractor
🌱🌱🌱🌿🌿🌿🍀🍀🍀🌱🌱
በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ይነገራል ዘመን የሚዋጀን አለን ምስጋና መድሀኒአለም ስመ ገናና🍀🍀🍀🌱🌱🌱🌿🌿🌿🍀🍀🌿🌿🌱🌱
ተወልደ ናሆ
የገና መዝሙር
​​✞ ተወልደ ናሆ

ተወልደ ናሆ ድንግል
ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ
አንዱ በእግዚአብሔር አንዱ በመንፈስ
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሐይ እንዲወጣ
የናፈቅነው ንጉስ ስጋ ለብሶ መጣ
ተወልደ ናሆ ድንግል
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈
መንፈሳዊ፡ህይወት፡ማለት

መንፈሳዊ መሆን ማለት የራሰን ፊቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል
ራሱ ግን በማንም አይመረመርም፡፡ (1ኛ ቆሮ2÷15) ሥርዓተ ሃይማኖትን ትውፊተ አበውን ገንዘብ አድርጎ መኖር መንፈሳዊነት ነው፡፡

አንድን ሰው መንፊሳዊ ነው ለማለት ሊፈጽማቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡እነርሱም፡
1.ተዓምኖ፤(መታመን) ፤እምነትን በተግባራዊ መልስ ማሳየት ማለት ነው፡፡ስለንስሓ የሚሰብከ ንስሓ የገባ መሆን አለበት፡፡ካልሆነ ችግር ነው፡፡ጣዕሙን አያውቀውም፡፡የዘመናችን ሰባክያነ ወንጌል መሠረታዊ ችግር ይህ ነው፡፡የሚጮህ አልጠፋም በተግባር የሚሰብከ
ግን ማግኘት ከባድ እየሆነ ነው፡፡
አንድ አባት አንዱን ሰባኪ ወንጌል ሰው ዕኮ ቤተ ክርስቲያንን አይደለም የጠላው አሉት ! ታዳያ ማንን ነው ሲላቸው ሰባኪው እናንተን ነው የጠላው ያላችሁትን ስለማታደርጉ አሉት ፡፡
አንድ ፓስተርም ጸልዩ አልቅሱ እያለ እሱ ግን አይጸልይም
አያለቅስም ይባስ ብሎ ስልክ ያወራል፡፡ፓሰተር ለምን አንተ አታለቅሰም ? ሲሉት አይ ጌታዬ የእኔ ሥራ ማስለቀስ ነው አለ፡፡

2.ምግባራተ ሠናያት አንድ ሰው እምነትን ተስፋን ገንዘብ ካደረገ በኋላ የሚቀረው ምግባረ ሠናይ ነው፡፡
መንፈሳዊ ሕይወት በማኀበራዊ ሕይወት ከተዋጠ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የነበረው አንድነትይላላል፡፡ሰዎችም ሐሳባቸው ሁሉ ምድራዊ ( ሥጋዊ) ወደ
መሆን ያዘነብላል፡፡ የበዓል ቀናትን ወደ ዕድር ዕቁብ ስብሰባ ይሆንና የመንፈሳዊ ሕይወት መስመር መላቅጡ ይጠፋል፡፡ መንፈሳዊነት በማኀበራዊነት ሲዋጥ በግለሰቡም በማኀበረሰቡም የሚታዩ ምልከቶች አሉ፡፡

1.ምክንያተኝነት፤ሰው ከመንፈሳዊ ሕይወት እየራቀ በሄደ ቁጥር አውቆም ሳያውቀውም ለፈጻማቸው ስሕተቶች ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ ምክንያትን በመደርደር መታለፍን ይፈልጋል፡፡ በአዳምና በሔዋን የታየው የመንፈስ መራቆት የተገለጠው በምክንያተኝነት ነው፡”ወይቤ አዳም
ብእሲትየ እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላዕኩ ”(ዘፍ3÷12)
መ. ምሳ18÷1” ምክንያተ የኀሥሥ በእሲ ዘይፈቅድ
ይትፈለጥ እም አዕርክቲሁ፤ከባልጀሮቹ ይለይ ዘንድ የሚፈልግ ሰው ምክንያት ይፈልጋል፡፡እንደ ሁለቱ አኀው በአንድ ቦታ የሚኖሩ ናቸው፡፡አንዱ የተማረ የበቃ ነው፡፡

አንዱ ያልተማረ ያልበቃ ነው፡፡ያልተማረው ያልበቃው መለየት ፍቃዱ ነውና ጓደኛውን ፀሐይ በየት ትወጣለች ብሎ ጠየቀው በምሥራቅ ብሎ ቢመልስለት ከዚህ ደንቆሮ
ጋር አልኖርም ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡መከራም አገኘው፡፡( ማር ይስሐቅ) ዛሬም አሉ የማይጠቅም ምክንያት በመደርደር ከአገልግሎት የሚርቁ ፡፡

2.መጎምጀት፤መንፈሰዊ ሕይወት የማደጉ ምልከት የሚታወቀው እንደ ሰራፕታዋ መበለት ያለውን አካፍሎ በመመገብ ነው፡፡የተገኘውን ለራስ ብቻ አውሎ ያለተገኘውንም በመጎምጀት መኖር ኃጢአት ሥር ይሰዳል፡፡

3.መመኘት፤ምቀኝነት መንፈሳዊ ሕይወት በሌለበት ምድር
የሚበቅል የልቡና አረም ነው፡፡ምቀኝነት በዘመናችን ምቀኝነት ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት ሰፊ የምሪት
ቦታ አለው፡፡ይህንን ሁሉ መከራ የምናስተናግደው ግን
መንፈሳዊ ሕይወት ጠፍቶና ሥጋዊነት ና ማኀበራዊ ሕይወት ብቻ በነገሠበት ምድር ላይ ነው፡፡

4.መተቸት፤መተቸት አብዛኛውን ጊዜ
“ሊቅነት”ከሚሰማቸው ለነገር ግን የፊደላት እጅና እግር
ከማያውቁ ሰዎች አካባቢ አይጠፋም ፡፡አይሠሩም
የሚሰራውን ይተቻሉ፡፡አያስተምሩም የሚያስተምረውን ዕዳ
ፍዳውን ያሳዩታል፡፡ ታዲያ ምን ይደረግ ተብለው ሲጠየቁ መልስ የላቸውም፡፡ ዕውቀታቸው መንፈሳዊነትን የተላበሰ
ሳይሆን መስፈርቱ ዕውቀት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡የዚህ ችገር ምኝጭ ማኀበራዊንቱ ብቻ በሰፈነባት ምድር ላይ በመሆኑ
አያሰደንቅም፡፡

5.የአኗኗር ለውጥ
ማኀበራዊነት ብቻ በዋጣት ምድር የሚኖሩ ሁሉ አንዱ ያደረገውን ሌላው ካላደረገ ራስን እንደኋላ ቀርነት
መቁጠር የተለመደ ነው ፡፡በዘመናችን ራስን ሁኖ ለመኖር የሚያስችል መንፈሳዊነት ተሟጦ ጠፍቷል፡፡የፊልሙ ጋጋታ የዓለም ገጽታ መለዋወጥ መንፈሳዊ ሕይወታችን ን በድርቅ እየመታው ነው፡፡
ገላትያ 5÷25” በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ
እንመላለስ”



@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት pinned « መንፈሳዊ፡ህይወት፡ማለት መንፈሳዊ መሆን ማለት የራሰን ፊቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም፡፡ (1ኛ ቆሮ2÷15) ሥርዓተ ሃይማኖትን ትውፊተ አበውን ገንዘብ አድርጎ መኖር መንፈሳዊነት ነው፡፡ አንድን ሰው መንፊሳዊ ነው ለማለት ሊፈጽማቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡እነርሱም፡ 1.ተዓምኖ፤(መታመን) ፤እምነትን በተግባራዊ መልስ ማሳየት…»
ጠቃሚ ምክር!

በአንድ ጫካ ውስጥ መልካቸው ነጭ፣ ጥቁር እና ግንባሩ ቦቃ የሆኑ ሶስት በሬዎች ይኖሩ ነበር። አንበሳን ጨምሮ የትኛውም አውሬ
ቢመጣ ክብ በመሥራት እየተዋጉ አላስጠጋ አሉ

አንድ ቀን ግን አያ ጅቦ መጣና “ይሔ ነጭ በሬ ያስጨርሳችኋል፤ እሱ ባይኖር በጨለማ አትታዩም” የሚል መጥፎ ሀሳብ በውስጣቸው ለቀቀባቸው። ሁለቱ በሬዎች ተባብረው ነጩን በሬ አባረሩ ጅቡም ብቻውን አግኝቶት ነጩን በሬ በላው

ጅቡ ሌላ ጊዜ ተመለሰና ለጥቁሩ በሬ “ግንባረ ቦቃው ካለ አሁንም ለአደጋ የተጋለጥህ ነህ” አለው፡፡ በዚህ የተነሳ ሁለቱ በሬዎች ተለያዩ፡፡ ጅቡም ግንባረ ቦቃውን በላው። በሌላ ቀን ጅቡ ጥቁር በሬው ጋር ሄደ፡፡ በሬውም “ዛሬ ምን ፈልገህ መጣህ? ልትበላኝ ነው?” አለው

ጅቡም “አንተ እኮ የተበላከው መጀመሪያ ጓደኞችህን አሳልፈህ የሰጠህ ጊዜ ነው” ብሎ ጥቁሩን በሬ በላው፡፡ ልብ ብለን ልንረዳው የሚገባው ነገር ሁሌም ልዩነታችን ውበትና ጥንካሬ የሚኖረው በአንድነታችን ውስጥ ነው! አንድ ስንሆን እንቆማለን፤ ስንከፋፈል እንወድቃለን!
@linkortodoxe21
#አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ

✥በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው :- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

✥በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው :-
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

✥ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር:- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

✥ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል::
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

✥"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ"
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
✥የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን✥


@linkortodoxe21
መጋቤ ሀዲስ እሽቱ አለማየሁ

ቁንጅና ለትዳር ዋስትና አይሆንም!
መታመም ማለት ትሞታለህ ማለት አይደለም!
ሃብታም መሆን የጥሩ እድል ትርጉም አይደለም!
ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር የድሎት ምንጭ አይሆንም!
ጥሩ መኪና መንዳት ለምትደርስበት ቦታ ዋስትና
አይሰጥህም !
ለቤተሰብህ ዶክተር ብትቀጥር ቋሚ የጤና ዋስትና አይኖርህም!
ብዙ መማር ጥበበኛ አያደርግህም!
ሃብታም ማግባት ለደስተኛ ለህይወት ማረጋገጫ አይሆንም!
ክርክር ማሸነፍ ትክክል መሆን አይደለም !
***
ገነት የማያሸልም ምንም ነገር ብትሰራ ጊዜያዊ እና
ውሸት ነው ። ያለ አምላክ የሚራመድ ሰው በድን
ነው፣አንተ በራስህ ላይ ስልጣን የለህም
አንተ ሰውነትህን ታያለህ እሱ ደምስርህን ያያል ። ሁሉም
ነገር ለርሱ ይቻላል በሁሉም ነገር ውስጥ አምላክህን ጣልቃ አስገባ።
@linkortodoxe21