+ ለንስሓ የሚቀሰቅስ ዶሮ +
🐓🐓🐓🐓🐓
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"ሕማማት" ከተሰኘው መጽሐፍ 2ኛ ምዕራፍ የተወሰደ

+ ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +
ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::
ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::
የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::
ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::
ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::
ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)
ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::
በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
#ሼር

ኦ ፍጡነ ረድኤት
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኦ_ፍጡነ_ረድኤት
ኦ ፍጡነ ረድኤት ፍጡነ ረድኤት
የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሰማዕት
ሰላም ለአንተ ይሁን - - - ፍጡነ ረድኤት
የልዳው ፀሐይ - - - ፍጡነ ረድኤት
በጨካኝ ንጉሥ ፊት ቆምክ አደባባይ
ታማኝ አገልጋይ ነህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ስቃይ ያልበገረህ - - - ፍጡነ ረድኤት
አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሠህ
#አዝ
የፈጣሪውን ስም - - - ፍጡነ ረድኤት
ስለመሰከረ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ
የስቃይ መሣሪያ - - - ፍጡነ ረድኤት
ያላዘናጋህ - - - ፍጡነ ረድኤት
መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ
#አዝ
ለጌታ ተጋዳይ - - - ፍጡነ ረድኤት
ታማኝ ወታደር - - - ፍጡነ ረድኤት
ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር
ስቃይ ቢያደርሱብህ - - - ፍጡነ ረድኤት
በመታገስህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ
#አዝ
ለሰማው ይደንቃል - - - ፍጡነ ረድኤት
የአንተ ሰማዕትነት - - - ፍጡነ ረድኤት
ምሳሌ ይሆናል ለሁሉ ፍጥረት
ገድልህ ይናገራል - - - ፍጡነ ረድኤት
ክብር እንደተሰጠህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዜ የማይሽረው ምግባር ሃይማኖት ነው
ኦ ፍጡነ ረድኤት ፍጡነ ረድኤት
የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሰማዕት
ሰላም ለአንተ ይሁን - - - ፍጡነ ረድኤት
የልዳው ፀሐይ - - - ፍጡነ ረድኤት
በጨካኝ ንጉሥ ፊት ቆምክ አደባባይ
ታማኝ አገልጋይ ነህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ስቃይ ያልበገረህ - - - ፍጡነ ረድኤት
አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሠህ
#አዝ
የፈጣሪውን ስም - - - ፍጡነ ረድኤት
ስለመሰከረ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ
የስቃይ መሣሪያ - - - ፍጡነ ረድኤት
ያላዘናጋህ - - - ፍጡነ ረድኤት
መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ
#አዝ
ለጌታ ተጋዳይ - - - ፍጡነ ረድኤት
ታማኝ ወታደር - - - ፍጡነ ረድኤት
ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር
ስቃይ ቢያደርሱብህ - - - ፍጡነ ረድኤት
በመታገስህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ
#አዝ
ለሰማው ይደንቃል - - - ፍጡነ ረድኤት
የአንተ ሰማዕትነት - - - ፍጡነ ረድኤት
ምሳሌ ይሆናል ለሁሉ ፍጥረት
ገድልህ ይናገራል - - - ፍጡነ ረድኤት
ክብር እንደተሰጠህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዜ የማይሽረው ምግባር ሃይማኖት ነው
“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"
#ቅዱስ_ኤፍሬም
@linkortodoxe21
#ቅዱስ_ኤፍሬም
@linkortodoxe21
እየሱስ ልበል
Audio Extractor
🌿🌿🌱🌱☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘❤️❤️❤️ኢየሱስ ልበል ኢየሱስ እርሱ ነው ህይወቴ የምኖርበት ተስፋ እርሱ ነው እረፍቴ ያለጌታ ብኖርማ እንዴት እሆናለሁ ስለ ስሙ ብነቀፍም ነፍሴን እሰጣለሁ ❤❤❤🌱🌱🌱🌿🌿🌿🌿☘☘☘🍀🍀☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ድንቅ ዘማሪ ገ/ዬሀንስ ገ/ጻድቅ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ድንቅ ዘማሪ ገ/ዬሀንስ ገ/ጻድቅ
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ማ ር ያ ም አባቶች ለድንግል ማርያም ካላቸው ፍቅር የተነሳ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም የስሟ አራት ፊደላትን እንደሚከተለው በምስጢር ይተረጉማሉ።
ይህም አባቶች ለእመቤታችን ላላቸው ፍቅር ሲገልጡ ነው።
ማ= ማህደረ መለኮት የመለኮት ማደሪያ መሆኗን ያጠይቃል። መዝ 45:4 ልዑል ማደሪያውን
ቀደሰ። መዝ 131:13 አለሙ ሁሉ መጻፍ ያዘዘውን በዚህ አለ በዚያ የለም የማይባለውን
የማይችለው የሌለውን ረቂቁን ባህርየ መለኮት በማህፀኗ የተሸከመች ስለሆነች የመለኮት
ማደሪያ ትባላለች።
ር= ርግብዬ ይቤላ ንጉሥ ሰሎሞን ርግብየ ይላታል መደምደምያም አንዲት ናት ለወላጆቿ
የተመረጠች ናት። ልጆች ባዩአት ጊዜም አመሰገኑአት ነገሥታትና አባቶቿም ምስጋና ሰጡአት
ይህች ማን ናት እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይ የጠራች?
መኀ 6:9 ብሏታል እመቤታችን ርግብ ስለ ሰው ወደ እግዚአብሔር በአማላጅነት የምትላክ
የሰላም መልዕክተኛ የምስራች ነጋሪ ናትና ርግብ እንላት አለን የጥፋት የምስራቹን ለኖህ
ያበሰረችው ርግብ ናት። ዘፍ 8:8-12 በአዳምና በልጆቹ ላይ ታዞ የነበረው ጥፋትና የሲኦል
መከራ ማክተም የሆነች ድንግል ማርያም ናት ርግብ የየዋህነት ምሳሌ ናት። ማቴ 10:16
ምክንያቱም ጌታ ከእሷ ጋር ነውና። ሉቃ 1:28
ያ= ያንቀዐዱ ሃቤኪ ኩሉ ፍጥረት ፍጥረት ሁሉ ለምኝልን እያሉ ወደ አንቺ ያንጋጥጣሉ ማለት
ነው። ሰውን ከእግዚአብሔር የምታስታርቅ በሰውና በፈጣሪ መካከል የምትገኝ የፍጥረት ሁሉ
አማላጅ በመሆኗ ፍጥረት ሁሉ አማላጂን እያሉ ያንጋጥጣሉ ከፈጣሪ ምህረትና ይቅርታን
የምታስገኝ ናትና ስለዚህ ሰው ከወደ በላዩ ማንጋጠጥ የተለመደ ነው ድንግል ማርያም ከሁሉ
በላይ ናትና ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን። ሐ.ሥራ 3:3-10
ም= ማለት ምስአል ወምስጋድ ወምሥትስራየ ሀጢአት መስገጃ መለመኛ የሀጢአት
ማስተሰርያ ማለት ነው። የሚሰገደው የሚለመነው በተቀደሰ ሥፍራ እግዚአብሔር ፀጋውንና
ክብሩን ባሳደረበት ቦታ ነው። ይህን የመሰለው ስግደትና ልመና ጸሎት ሀጢአትን
ያስተሰርያል። 2 ዜና 7:11-17 በዚህ አይነት እግዚአብሔር ያደረባት በቅዱስ መንፈሱ
የጎበኛት በምንለምንበት ቅዱስ ሥፍራ ሁሉ የምትመስል ቅድስት ድንግል ማርያም መስገጃ
መለመኛና የሀጢአት ማስተስርያ ትባላለች።
በአማላጅነቷ ሐጢአታችንን እንድስታሰረይልን ቅድስት ሆይ ለምኝልን እንላታለን
በአጠቃላይ ማርያም ማለት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል በፍጹም ፍቅሯና የዋህነት
ያለችን እናታችን ናት።

.:
ኦርቶዶክሳዊው መነኩሴ አባ ሌቭ ጊሌት በመንፈሳዊ ጽሑፎቹ ላይ አንድ ጊዜ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ "አንተም ኃጢአት በምትሠራ ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚወድህ እርግጠኛ መሆን አለብህ፡፡" ዲያብሎስ በተቃራኒው ሊነግርህ ይችላል ፤ እርሱ ግን ሐሰተኛ ነው፡፡
እናም እንደወደቅህ ወዲያውኑ በተወደደው አባትህ ፊት ተንበርክከህ ፦ "አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም" በለው፡፡ ወዲያውኑ አባትህ በደስታ ሲያቅፍህና በፍቅር ሲስምህ ታገኘዋለህ፡፡ ዳግመኛም በቁርጠኝነት ወደ ውጊያው ተመልሰሃል ማለት ነው፡፡ ይህ የጸጸት መጀመሪያ ተግባር ግን ለንስሐ አባትህ የምታደርገውን ኑዛዜ የሚተካ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወደ ንስሐ አባትህ ዘንድ መቅረብና ከሐጢአትህ ፈጽሞ መታጠብ ቀኖናንም መቀበል ቅድስናና ንጽህናህን የማግኛ ፍጻሜ ነው፡፡
🍒
(አቡነ አትናስዮስ እስክንድር)

New_2015_Tewahedo_mezmur_by_Zamari_Gebre_Yohannis_G_Tsadik_-%E1…
<unknown>
☘☘☘☘☘☘☘የጻድቅ ሰው ፀሎት ሀይልን ያደርጋል በፀሀይን ያቆማል ሙትን ያስነሳል ከጠላት ዲያብሎስ ነፍሳትን ይነጥቃል ባዶውን ማድጋ በዘይት ይሞላል☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ዘማሪ ገ/ዬሀንስ ገ/ጻድቅ
ዘማሪ ገ/ዬሀንስ ገ/ጻድቅ
በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
Audio Extractor
☘☘☘🌱🌱🌱🌿🌿🌿🍀🍀🍀🌱🌱
በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ይነገራል ዘመን የሚዋጀን አለን ምስጋና መድሀኒአለም ስመ ገናና🍀🍀🍀🌱🌱🌱🌿🌿🌿🍀🍀🌿🌿🌱🌱

ተወልደ ናሆ
የገና መዝሙር
✞ ተወልደ ናሆ ✞
ተወልደ ናሆ ድንግል
ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ
አንዱ በእግዚአብሔር አንዱ በመንፈስ
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሐይ እንዲወጣ
የናፈቅነው ንጉስ ስጋ ለብሶ መጣ
ተወልደ ናሆ ድንግል
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈
ተወልደ ናሆ ድንግል
ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ
አንዱ በእግዚአብሔር አንዱ በመንፈስ
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሐይ እንዲወጣ
የናፈቅነው ንጉስ ስጋ ለብሶ መጣ
ተወልደ ናሆ ድንግል
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈
👉@linkortodoxe21👈